Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  (ለ) በሥራ ግንኙነቶች በሌሎች ላይ መደገፍና አለመደገፍ (ጥገኝነትና ጥገኛ አለመሆን)

  የአንድ ሰው አእምሮ።--ለክርስቶስ የሚሰሩ ሰዎች አስቀድሞ ሀላፊነት ባላቸው በአንዳንድ ሰዎች ፊት ከቀረበው ነገር በቀር ምንም ሌላ እርምጃ መሄድ እንደሌለባቸው እንዲያምኑ ማድረግ ስህተት ነው። ሰዎች ሰዎችን እንደ እግዚአብሔር እንዲመለከቱ መማር የለባቸውም። በሰራተኞች መካከል አብሮ መምከርና የተግባር አንድነት አስፈላጊ ሆኖ ሳለ የአንድ ሰው አእምሮና የአንድ ሰው ውሳኔ የሚቆጣጠር ኃይል መሆን የለበትም። --RH, Aug 7, 1894. {1MCP 263.1}1MCPAmh 215.2

  በብቃት ለማደግ።--እግዚአብሔር የሕዝቡ ገዥ ስለሆነ አእምሮዎቻቸውን ለእርሱ የሚሰጡትን ያን አእምሮ እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ያስተምራቸዋል። ውሳኔ ሰጭ ችሎታቸውን ሥራ ላይ ሲያውሉ በብቃት ያድጋሉ። የእግዚአብሔር ቅርስ ከትላልቅና ከትናንሽ ዕቃዎች የተሰራ ቢሆንም እያንዳንዱ የየራሱ ሥራ አለው። የአንድ ሰው አእምሮ፣ ወይም የሁለት ወይም የሶስት ሰው አእምሮዎች፣ በእርግጠኝነት ሁሉም ሊከተሉት እስከሚችሉ ድረስ ችግር እንደሌለባቸው ተደርገው እምነት ሊጣልባቸው አይገባም። ሁሉም ወደ እግዚአብሔር ይመልከቱ፣ በእርሱ ይታመኑ፣ በእርሱ ኃይል ሙሉ በሙሉ እምነት ይኑራቸው። ሰዎች ከመውደቅ ሊጠብቁአችሁ ኃይል ስለሌላቸው ከሰው ጋር ሳይሆን ከክርስቶስ ጋር ይጠመዱ። --Lt 88, 1896. {1MCP 263.2}1MCPAmh 215.3

  ውሳኔ ሰጭ ለሆነ ሰው የተሰጠ ምክር።--በእግዚአብሔር ተደገፍ። ሌሎች ሰዎች አእምሮዎቻቸውን በአንተ አእምሮ ውስጥ እንዲያራግፉ አትፍቀድ። በማሳመን ችሎታቸው በውሸት መንገዶች እንዲመሩህ መፍቀድ የለብህም። ‹‹አልተውህም፣ አልጥልህምም›› (ዕብ. 13፡ 5) ባለው ላይ ሙሉ በሙሉ ታመን።--Lt 92, 1903. {1MCP 263.3}1MCPAmh 216.1

  በእግዚአብሔር መደገፍ መተማመንን ይገነባል።--ሰዎች በሰዎች ላይ መደገፍን ሲያቆሙ፣ እግዚአብሔርን ብቃታቸው ሲያደርጉ፣ አንዱ በሌላ ላይ የበለጠ መተማመንን ያሳያሉ። በእግዚአብሔር ላይ ያለን መታመን እጅግ ደካማ ከመሆኑ የተነሣ በእርስ በርሳችን ላይ ያለን መተማመንም እግጅ አነስተኛ ነው።--SpT Series A, No. 3, p 48, 1895. (TM 214.) {1MCP 263.4}1MCPAmh 216.2

  በራስ መተማመን ወደ ፈተና ይመራል።--ሰለሞን የዓለምን አድናቆትና አግራሞት የቀሰቀሰ ጥበብ ማግኘት የቻለው ልባዊ በሆነ ጸሎትና በእግዚአብሔር በመደገፍ ነበር። ነገር ግን ከብርታቱ ምንጭ ተለይቶ በራሱ በመተማመን ወደ ፊት በተንቀሳቀሰ ጊዜ የፈተና ሲሳይ ሆነ። ከዚያ በኋላ ለዚህ እጅግ ጠቢብ ለነበረው ንጉሥ የተሰጡት አስደናቂ ኃይሎች የነፍሳት ጠላት እጅግ ውጤታማ ወኪል እንዲሆን ብቻ አደረገው። --GC 509 (1911). {1MCP 264.1}1MCPAmh 216.3

  በሌሎች መደገፍ ማለት አለመብሰል ማለት ነው።--በትክክል ዋልታን እንደሚያመለክት እንደ አቅጣጫ ጠቋሚ (ኮምፓስ) መርፌ በእያንዳንዱ አስቸኳይ ሁኔታ ውስጥ እውነተኛ መሆን ያለባቸው ሰዎች ራሳቸውን ከጥላቻ ለመከለል በሚያደርጓቸው ጥረቶችና አይሳካልኝም በሚል ፍርሃት ኃላፊነቶችን በመሸሽ ብቃት የጎደላቸው ሆነዋል። ትልቅ የአእምሮ ችሎታ ያላቸው ሰዎች መሸከም ያለባቸውን ሸክሞች ለመቀበልና ለመሸከም ፈሪዎች ስለሆኑ ሥነ-ሥርዓትን በተመለከተ ሕጻናት ናቸው። ብቁ መሆንን ችላ እያሉ ናቸው። የእግዚአብሔር ሥራ በሚፈልገው ሁኔታ ራሳቸው ማድረግ ሲችሉ ሌላ ሰው እንዲያቅድላቸውና እንዲያስብላቸው በአንድ ሰው ላይ እጅግ ረዥም ለሆነ ጊዜ ተማምነውበታል። በእያንዳንዱ ነጥብ ላይ የአእምሮ ጉድለቶች ያጋጥሙናል። {1MCP 264.2}1MCPAmh 216.4

  ሌሎች እንዲያቅዱላቸውና እንዲያስቡላቸው ረክተው የሚቀመጡ ሰዎች ሙሉ እድገት የላቸውም። ለራሳቸው እንዲያቅዱ ቢተዉ ኖሮ የሚያመዛዝኑና በደንብ አስልተው የሚሰሩ ሰዎች መሆን ይችሉ ነበር። ነገር ግን ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው ሲደረጉ ሙሉ በሙሉ የተለየ ነገር ይሆንባቸዋል፤ ይህን ችሎታ ሙሉ በሙሉ ያጡታል። የማቀዱንና የማሰቡን ጉዳይ ሌሎች ሊያደርጉላቸው የሚገባ ይመስል ብቃትና ችሎታ የሌላቸው ሆነው በመቅረታቸው የረኩ ናቸው። አንዳንድ ሰዎች ለራሳቸው መንገድ ለመጥረግ ፍጹም የማይችሉ ይመስላሉ። የማቀዱንና የመማሩን ሥራ እንዲሰሩላቸው፣ አእምሮና ውሳኔ ሰጭ እንዲሆኑላቸው ሁል ጊዜ በሌሎች ላይ መደገፍ አለባቸውን? እንደ እነዚህ ባሉ ወታደሮች እግዚአብሔር ያፍርባቸዋል። ተራ ማሽኖች ሆነው ሳሉ በሥራው ውስጥ በሚኖራቸው በማንኛውም ድርሻ ቢሆን እርሱ አይከበርም።--3T 495, 496 (1875). {1MCP 264.3}1MCPAmh 217.1

  ጥገኛ ያልሆኑ ሰዎች ይፈለጋሉ።--እንደ መስተዋት ማጣበቂያ (እንደ አሜሪካ ጭቃ) ቅርጽ የሚሰራባቸው ሳይሆን ልባዊ ጥረት የሚያደርጉ ጥገኛ ያልሆኑ ሰዎች ይፈለጋሉ። ሥራው ተዘጋጅቶላቸው እንዲቀርብ የሚፈልጉ ሰዎችን፣ የተወሰነ ሥራ ሰርተው የተወሰነ ደሞዝ የሚፈልጉ ሰዎችን፣ ከሁኔታዎች ጋር የመለማመድ ወይም የመሰልጠን ችግር ሳይገጥማቸው ገጣሚ ሆነው ለመገኘት የሚሹ ሰዎችን እግዚአብሔር በሥራው ውስጥ እንዲሰሩ አይጠራቸውም። ሁኔታዎች አስገዳጅ ሲሆኑ ችሎታዎቹን ከማንኛውም የሥራ ኃላፊነት ጋር የማያለማምድ ሰው ለዚህ ጊዜ የሚሆን ሰው አይደለም። {1MCP 265.1}1MCPAmh 217.2

  እግዚአብሔር ከሥራው ጋር የሚያገናኛቸው ሰዎች ጡንቻ የሌላቸው ወይም የባሕርይ ግብረገባዊ ኃይል የሌላቸው አንካሶች ወይም ጅማት የለሾች አይደሉም። ሰዎች በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ድርሻቸውን ለመወጣት ሥነ-ሥርዓት መማር የሚችሉት በማያቋርጥና ትዕግስት ባለበት ሥራ ብቻ ነው። እነዚህ ሰዎች ሁኔታዎችና አከባቢያቸው እጅግ የማይመቹ ቢሆኑም ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም። ለእግዚአብሔር ክብርና ለነፍሳት ጥቅም ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር ይህን ያህል የጎላ እንዳልሆነ ያለ ጥርጥር እርግጠኞች እስኪሆኑ ድረስ ሙሉ በሙሉ እንዳልተሳካላቸው አድርገው ዓላማቸውን መተው ይለባቸውም።-- 3T 496 (1875). {1MCP 265.2}1MCPAmh 217.3

  ያልተቀደሰ ከጥገኝነት ነጻ መሆን የሚመነጨው ከራስ ወዳድነት ነው።--ጠቃሚነታችንን የሚያበላሽና ካላሸነፍን በስተቀር መጥፋታችንን እርግጠኛ እንዲሆን የሚያደርጉ በራስ ብቃት ወይም ችሎታ የመተማመንና ያልተቀደሰ ከጥገኝነት ነጻ የመሆን ክፋቶች የሚመነጩት ከራስ ወዳድነት ነው። የእግዚአብሔር መልአክ ደግሞ ደጋግሞ የነገረኝ መልእክት ‹‹አብራችሁ ምከሩ›› የሚል ነው። ሰይጣን በአንድ ሰው ፍርድ አሰጣጥ ላይ ተጽእኖ በመፍጠር ለእርሱ እንዲመቹ አድርጎ ነገሮችን ለመቆጣጠር ጥረት ሊያደርግ ይችላል። የሁለት ሰዎችን አእምሮዎች ወደ ስህተት በመምራት ሊሳካለት ይችላል፤ ነገር ግን ብዙዎች አብረው ሲመክሩ የበለጠ ደህንነት አለ። እያንዳንዱ እቅድ በቅርበት ይተቻል፤ እያንዳንዱ ወደ ፊት የሚደረግ እንቅስቃሴ የበለጠውን በጥንቃቄ ይጠናል። ከዚህ የተነሣ ውዝግብን፣ ግራ መጋባትንና ሽንፈትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ያለ ጥንቃቄ የተሰሩና ክፉ ምክርን የተከተሉ እንቅስቃሴዎች የመኖራቸውን አደጋ ይቀንሳል። በመከፋፈል ውስጥ ድክመትና ሽንፈት አለ።--5T 29, 30 (1882). {1MCP 265.3}1MCPAmh 218.1

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents