Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 19—የወላጅነት ተጽእኖዎች

  በመለኮታዊ መርሆዎች ቁጥጥር ሥር መሆን።--ወላጆች ልጆቻቸውን በእግዚአብሔር ፍርሃትና ፍቅር የማሳደግ እጅግ የከበረ ግዴታ አለባቸው። በቤት ውስጥ እጅግ ንጹህ የሆነ ግብረገብ መጠበቅ አለበት። ለመጽሐፍ ቅዱስ መስፈርቶች በጥብቅ መታዘዝ እንዳለባቸው መማር አለባቸው። የቤት ሕይወት የእግዚአብሔርን ኃይልና ጸጋ ማሳየት እንዲችል የእግዚአብሔር ቃል አስተምህሮዎች አእምሮንና ልብን መቆጣጠር አለባቸው። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በመለኮታዊ መርሆዎችና ጥቅሶች ‹‹እንደ ቤተ መንግሥት ያማረና ያጌጠ›› መሆን አለበት (መዝ. 144፡ 12)። --RH, Nov 10, 1904. {1MCP 163.1}1MCPAmh 134.1

  ወላጆች ልጆችን ማስተዋል ያስፈልጋል።-- ወላጆች የራሳቸውን የልጅነት ጊዜ፣ ለርኅራኄና ለፍቅር ምን ያህል ይጓጉ እንደነበር እና ሲነቀፉና በማያስደስት ሁኔታ ሲገሰጹ እንዴት ያሳዝናቸው እንደነበር መርሳት የለባቸውም። በስሜቶቻቸው እንደገና ልጅ በመሆን የልጆቻቸውን ፍላጎቶች ለመረዳት አእምሮአቸውን ወደ ታች ማውረድ አለባቸው። ነገር ግን ከፍቅር ጋር በተቀላቀለ የአቋም ጽናት ልጆቻቸው እንዲታዘዙአቸው ማድረግ አለባቸው። የወላጆችን ቃል ሳያንገራግሩ መታዘዝ አለባቸው። --1T 388 (1863). 164 {1MCP 163.2}1MCPAmh 134.2

  እግዚአብሔር መንገድ አዘጋጅቷል።-- ልጆች ምን ዓይነት ባሕርይ እያጎለበቱ እንዳሉ ለማየት የእግዚአብሔር መላእክት እጅግ ጥልቅ በሆነ ስሜት ነቅተው እየጠበቁ ናቸው። እኛ ብዙ ጊዜ በእርስ በርሳችን እና በልጆቻችን ላይ እንደምናደርገው እግዚአብሔር በእኛ ላይ ቢያደርግ ኖሮ ፍጹም ተስፋ በመቁረጥ ተደናቅፈን እንወድቅ ነበር። ኢየሱስ ድክመቶቻችንን እንደሚያውቅና ከኃጢአት በቀር ልምምዳችንን ሁሉ እርሱ እንደተካፈለ አውቃለሁ፤ ስለዚህ ለእኛ ብርታትና አቅም ምቹ የሆነ መንገድ አዘጋጅቶልን፣ ልክ እንደ ያዕቆብ፣ አብሮን በመሆኑ ሊያጽናናን እና የማይለየን መሪ ሊሆነን፣ ልጆች በሚችሉት መጠን በእርጋታና በቀስታ አብሮ ወደ ፊት ተጉዞአል። ልጆችን አይንቅም፣ ችላም አይልም፣ ወይም ከመንጋው ኋላ አይተዋቸውም። እነርሱን ከኋላ ትተን ወደ ፊት እንድንጓዝ አላዘዘንም። ከልጆቻችን ጋር ወደ ኋለ ሊተወን በጥድፊያ አልተራመደም። በፍጹም እንደዚህ አላደረገም፤ ነገር ግን ለልጆች እንኳን ሳይቀር የሕይወትን መንገድ አስተካከለው (ምቹ አደረገው)። ወላጆች በጠባቡ መንገድ እንዲመሩአቸው በእርሱ ስም ተጠይቀዋል። እግዚአብሔር ከልጆች ብርታትና ችሎታ ጋር ተስማሚ የሆነ መንገድ ላይ እንድንመራቸው ሀላፊነት ሰጥቶናል። --1T 388, 389 (1863). {1MCP 164.1}1MCPAmh 134.3

  ደስተኛ አለመሆን መታመቅ አለበት።--ወላጆች ሆይ፣ የደስታ ስሜት በማይሰማችሁ ጊዜ መላውን ቤተሰብ በዚህ አደገኛ በሆነ የቁጣ/የብስጭት ስሜት የመመረዝን ትልቅ ኃጢአት መፈጸም የለባችሁም። በእንደዚህ ዓይነት ጊዜያቶች በራሳችሁ ላይ እጥፍ ጥበቃ አድርጉና በከንፈራችሁ ሌሎችን እንዳታስከፉ፣ መልካምና አስደሳች ቃላት ብቻ ለመናገር በልባችሁ ወስኑ። ለራሳችሁ እንዲህ በሉ፡- ‹‹በማያስደስት ቃል የልጆቼን ደስታ አላበላሽም።›› ራሳችሁን በመቆጣጠር እየጠነከራችሁ ትሄዳላችሁ። የነርቭ ሥርዓታችሁ በቀላሉ የሚሰማው አይሆንም። ትክክል በሆኑ መርሆዎች ብርታት ታገኛላችሁ። ተግባራችሁን በታማኝነት እየፈጸማችሁ መሆናችሁን ማወቃችሁ ብርታት ይሰጣችኋል። የእግዚአብሔር መላእክት በጥረቶቻችሁ በመደሰት ይረዱአችኋል። {1MCP 164.2}1MCPAmh 135.1

  ትዕግስት ስታጡ፣ ብዙ ጊዜ ችግሩ ከልጆቻችሁ እንደሆነ በማሰብ፣ ያለ ጥፋታቸው ጥፋተኞች ታደርጉአቸዋላችሁ። በሌላ ጊዜ እነዚያኑ ነገሮች ሊያደርጉ ስለሚችሉ ሁሉም ነገር ተቀባይነት ያለውና ትክክል ሊሆን ይችላል።1MCPAmh 135.2

  ልጆች እነዚህ ወጣገብነቶች መኖራቸውንና ሁል ጊዜ ተመሳሳይ እንዳልሆኑ ያውቃሉ፣ ምልክት አድርገው ይይዛሉ፣ ይሰማቸዋልም። አንዳንድ ጊዜ የሚለዋወጡ ስሜቶችን ለመጋፈጥ ይዘጋጃሉ፣ በሌላ ጊዜያቶች ደግሞ ቁጡና ደስታ የራቃቸው ይሆኑና ተግሳጽን መቀበል ያቅታቸዋል።... {1MCP 164.3}1MCPAmh 135.3

  አንዳንድ ወላጆች ቁጡ ባሕርይ ስላላቸው ሲደክማቸው ወይም ጭንቀት ሲይዛቸው አእምሮአቸውን አያረጋጉም፣ ነገር ግን በምድር ላይ ለእነርሱ እጅግ ክቡር መሆን ለሚገባቸው ሰዎች እግዚአብሔርን የሚያሳዝንና በቤተሰብ ውስጥ ደመናን የሚያመጣ ደስታ ቢስነትንና ትዕግስት የለሽነትን ያሳያሉ። ልጆችን፣ በችግር ውስጥ ሲሆኑ፣ ገርነት ባለበት ርኅራኄ ሊያጽናኑአቸው ይገባል። የጋራ ደግነትና ትዕግስት ቤትን ገነት በማድረግ ቅዱሳን መላእክትን ወደ ቤተሰብ ክበብ ይስባል። --1T 386, 387 (1863). {1MCP 165.1}1MCPAmh 135.4

  ሽባ የሆኑ የወላጆች አእምሮዎች።--ስለ ሰይጣን አሰራርና እንዴት በሥራው እንደሚሳካለት ጥቂት እውቀት አለን። እንዳይ ከተደረግኩት ነገር እንደተረዳሁት የወላጆችን አእምሮዎች ሽባ አድርጎአቸዋል። የራሳቸው ልጆች ሊሳሳቱና ኃጢአተኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለመጠራጠር ዳተኛ ናቸው። ከእነዚህ ልጆች መካካል አንዳንዶቹ ክርስቲያን ነን ስለሚሉ የልጆቻቸው አእምሮዎችና አካሎች እየተበላሹ ሳለ ወላጆች ምንም አደጋ ሳይፈሩ ይተኛሉ። {1MCP 165.2}1MCPAmh 135.5

  አንዳንድ ወላጆች በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ልጆቻቸውን ከራሳቸው ጋር ለማድረግ እንኳን ግድ የላቸውም። ወጣት ልጃገረዶች ስብሰባዎችን ሲሳተፉ ከወላጆቻቸው ጋር ሊቀመጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ከጉባኤው ወደ ኋላ ባሉ መቀመጫዎች ይቀመጣሉ። ቤቱን ለመልቀቅ ሰበብ የመስጠት ልምድ አላቸው። ወንድ ልጆች ይህን ስለሚረዱ ሴቶቹ ከመውጣታቸው በፊት ወይም በኋላ ተከትለው ይወጡና ስብሰባው ሲያበቃ እስከ ቤታቸው ይሸኙአቸዋል። ስለዚህ ነገር ወላጆች ጠቢባን አይደሉም። በድጋሚ እግር ለማፍታታት ሰበብ ይፈጠርና ወንዶችና ሴቶች ልጆች ደስ በሚል ቦታ ወይም በሌላ ቀጠሮ በተያዘበት ቦታ ሊያስጠነቅቅ የሚችል ልምድ ያለው ዓይን በማያይበት ለብቻቸው ይሰበሰቡና ይጫወታሉ፣ በመደበኛነት አብረው በመደሰትም ጊዜ ያሳልፋሉ። --2T 481, 482 (1870). {1MCP 165.3}1MCPAmh 135.6

  አመጋገብና የወላጅነት ተጽእኖዎች።--ወላጆች ቀለል ባለ አመጋገብ ረክተው ጤናማ አኗኗር ቢኖሩ ኖሮ ከብዙ ወጪ መዳን ይቻል ነበር። አባት የቤተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ሲል ከአቅሙ በላይ ለመሥራት አይገደድም ነበር። ቀላልና ለጤና ተስማሚ የሆነ አመጋገብ መከፋትንና ብስጭትን የሚያስከትለውን ከልክ በላይ የነርቭ ሥርዓትንና የእንስሳ ስሜትን የመቀስቀስ ተጽእኖ አይኖረውም ነበር። ተራ የሆነ ምግብ ብቻ ቢመገብ ኖሮ አእምሮው ጥርት ያለ፣ ነርቮቹ ያለማቋረጥ ሥራቸውን የሚሰሩ፣ ጨጓራውም ጤናማ ይሆንና ንጹህ የሆነ የአካል ሥርዓት ስለሚኖረው የምግብ ፍላጎት ማጣት ስለማይኖር የአሁኑ ትውልድ አሁን ካለበት ሁኔታ እጅግ በተሻለ ሁኔታ ላይ በተገኘ ነበር። {1MCP 165.4}1MCPAmh 136.1

  ነገር ግን አሁን በዚህ የመጨረሻ ወቅት እንኳን ሁኔታችንን ለማሻሸል የሆነ ነገር ማድረግ ይቻላል። በሁሉም ነገር መሻትን መግዛት አስፈላጊ ነው። መሻቱን የሚገዛ አባት በጠረጴዛው ላይ ብዙ የተለያዩ ዓይነት ምግቦች ባይኖሩ አያጉረመርምም። ጤናማ የሆነ የአኗኗር ሁኔታ በሁሉም መልኩ የቤተሰብን ሁኔታ ስለሚያሻሽል ሚስትና እናት ለልጆቿ ጊዜ እንድትሰጥ ይፈቅድላታል። {1MCP 166.1}1MCPAmh 136.2

  የወላጆች ትልቁ ጥናት ልጆቻቸውን በዚህ ዓለም ላይ ጠቃሚ ዜጋዎች እንዲሆኑና ከዚህ በኋላ ለሚመጣው ሰማይ ለማዘጋጀት በምን ሁኔታ በደንብ ማሰልጠን እንደሚችሉ ይሆናል። ልጆቻቸው ጌጣጌጥና የጥልፍ ሥራ የሌለባቸውን ንጹህና ተራ፣ ግን ምቹ የሆኑ ልብሶችን ለብሰው በማየት ይረካሉ። ልጆቻቸው በእግዚአብሔር ዕይታ ትልቅ ዋጋ ያለውን የውስጥ ውበት፣ የዋህና ጸጥ ያለ መንፈስ ጌጥ ያላቸው እንዲሆኑ ተግተው ይሰራሉ። --HL (Part 2) 45, 1865. (2SM 437, 438.) {1MCP 166.2}1MCPAmh 136.3

  አባት፣ የቤሰቡ አገናኝ ገመድ ነው።--ክርስቲያን አባት ቤተሰቡን ከእግዚአብሔር ዙፋን ጋር በቅርበት የሚያስተሳስር የቤተሰቡ አገኛኝ ገመድ ነው። በልጆቹ ላይ ያለው ትኩረት በፍጹም መቀነስ የለበትም። ወንድ ልጆች ያሉበት ቤተሰብ አባት እነዚህን እረፍት የለሽ ልጆች እንክብካቤ ሙሉ በሙሉ ለእናት መተው የለበትም። ይህ ለእርሷ እጅግ በጣም ከባድ ሸክም ነው። ራሱን የእነርሱ ወዳጅና ጓደኛ ማድረግ አለበት። ከክፉ ግንኙነት ለመጠበቅ ራሱ ጣልቃ መግባት አለበት። እናት ራሷን መቆጣጠር ሊከብዳት ይችላል። ባል የሚስቱ ድክመት የልጆቹን ደህንነት አደጋ ላይ እየጣለ መሆኑን ካየ እነዚህን ልጆች ወደ እግዚአብሔር ለመምራት ማድረግ የሚችለውን ሁሉ በማድረግ አብዛኛውን ሸክም ራሱ መውሰድ አለበት።--RH, July 8, 1902. {1MCP 166.3}1MCPAmh 136.4

  እናቶች ማነሳሻ (መቀስቀሻ) መፈለግ የለባቸውም። የሚሰለጥኑ የወጣትነት አእምሮዎችና ባሕርያቸው መቀረጽ ያለባቸው ልጆች ያሉአቸው እናቶች ደስተኛና ፍልቅልቅ ለመሆን የዓለምን መቀስቀሻ መፈልግ የለባቸውም። ጠቃሚ የሆነ የሕይወት ሥራ ስላላቸው እነርሱም ሆነ የእነርሱ የሆኑት ጊዜያቸውን ትርፋማ ባልሆነ ሁኔታ ማጥፋት የለባቸውም። ጊዜ እግዚአብሔር ከሰጠን ጠቃሚ መክሊቶች አንዱ ሲሆን ስለ ጊዜ አጠቃቀማችንም ተጠያቂ ያደርገናል። ጊዜን ማጥፋት የአእምሮ ችሎታን ማጥፋት ነው። የአእምሮ ኃይሎች ከፍተኛ የሆነ እድገት የሚያስፈልጋቸው ናቸው። እናቶች አእምሮአቸውን የማሳደግና ልባቸውን ንጹህ አድርገው የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው። የልጆቻቸውን አእምሮዎች ማሻሸል እንዲችሉ ለራሳቸው የእውቀትና የግብረገብ መሻሻል ሊያስገኝላቸው የሚችለውን እያንዳንዱን ነገር ማሻሸል አለባቸው። {1MCP 167.1}1MCPAmh 137.1

  ከሌሎች ጋር የመሆን ተፈጥሮአዊ ዝንባሌያቸውን ያለ ልክ የሚፈጽሙ ሰዎች እንግዶችን ካልጎበኙ ወይም ካላስተናገዱ በቀር ወዲያውኑ የመቁነጥነጥ (የእረፍት የለሽነት) ስሜት ይሰማቸዋል። አስፈላጊና ቅዱስ የሆኑ የቤት ውስጥ ተግባራት ተራና የማያስደስቱ ይሆኑባቸዋል። ራሳቸውን የመመርመርም ሆነ ሥርዓት የማስያዝ ፍቅር የላቸውም። አእምሮ ተለዋዋጭ ለሆኑ ስሜትን ለሚቀሰቅሱ ዓለማዊ ሕይወት ትዕይንቶች ይራባል፤ ዝንባሌን ከመጠን በላይ ለመከተል ልጆች ችላ ተብለዋል፤ መዝጋቢው መልአክ ‹‹የማይጠቅም ባሪያ›› ብሎ ይጽፋል። የእግዚአብሔር ዕቅድ አእምሮዎቻችን ዓላማ ቢስ እንዲሆኑ ሳይሆን በዚህ ሕይወት መልካም የሆነውን እንዲፈጽሙ ነው። --3T 146, 147 (1872). {1MCP 167.2}1MCPAmh 137.2

  ጡት የሚያጠቡ እናቶች ደስተኛ መሆን አለባቸው።--ልጅ ከእናቱ የሚቀበለው የምግብ ጠባይ ይብዛም ይነስም በባሕርዩ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል። እንዲህ ከሆነ እናት ልጇን ስታጠባ መንፈሷን ፍጹም በመቆጣጠር ደስተኛ የሆነ የአእምሮ ሁኔታ መጠበቅ ምንኛ ጠቃሚ ነው። ይህ ከተደረገ የልጁ ምግብ ጉዳት አይደርስበትም፣ እናት በልጇ አያያዝ ላይ የምትከተለው የተረጋጋ፣ ራስን የመቆጣጠር መንገድ የህጻኑን አእምሮ በመቅረጽ ሂደት የሚጫወተው ሚና ብዙ ነው። ሕጻኑ ተናዳጅና በቀላሉ የሚረበሽ ከሆነ የእናት በጥንቃቄ የተሞላ፣ ችኮላ የሌለበት ባሕርይ የማረጋጋትና የማስተካከል ተጽእኖ ይኖረውና የሕጻኑ ጤና እጅግ ይሻሻላል። --RH, July 25, 1899. (CH 80.) {1MCP 167.3}1MCPAmh 137.3

  እናት ራሷን ለመግዛት ጥረት ማድረግ አለባት።--የልጅ ሕይወት ጸጥታ ያለበትና ቀላል በሆነ ልክ ለአካልና ለአእምሮ እድገቱ የበለጠ ምቹ ይሆናል። እናት ሁል ጊዜ ጸጥ ያለች፣ የተረጋጋች፣ ራሷን የገዛች ለመሆን ጥረት ማድረግ አለባት። ብዙ ሕጻናት ለነርቭ መረበሽ ተጋላጭ ስለሆኑ ጨዋና ችኮላ የሌለበት የእናት ባሕርይ ሊነገር ከሚቻለው በላይ ጠቃሚ የሆነ የማረጋጋት ተጽእኖ ይኖረዋል። --MH 381 (1905). {1MCP 168.1}1MCPAmh 138.1

  በቀላሉ የመረበሽ ባሕርይ ያለው ሕጻን በግድ የለሽነት መቁሰል የለበትም።--ትንንሽ ልጆች ሰው አብሮአቸው ሲሆን ይወዳሉ። በአጠቃላይ ሲታይ፣ ልጆች ብቻቸውን በመሆን ስለማይደሰቱ እናት በቤት ውስጥ በምትሆንበት ጊዜ ልጆቿ መሆን ያለባቸው እሷ ባለችበት ክፍል ውስጥ እንደሆነ ሊሰማት ይገባል። እንደዚህ ሲሆን በልጆቿ ላይ አጠቃላይ እይታ ይኖራታል፤ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡላት ትንንሽ ልዩነቶችን ለማስተካከል ዝግጁ ትሆናለች፤ የተሳሳቱ ልምዶችን ወይም የራስ ወዳድነት ወይም የኃይለኛ ስሜት መገለጫዎችን ታስተካክላለች፤ አእምሮአቸውን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ትመልሳለች። ልጆች እነርሱን የሚያስደስታቸው ነገር እናታቸውንም የሚያስደስት ስለሚመስላቸው አወዛጋቢ የሚሆኑባቸውን ትናንሽ ነገሮች እናታቸውን ማማከራቸው ፍጹም ተፈጥሮአዊ ነው። {1MCP 168.2}1MCPAmh 138.2

  እናት ጉዳዩን ቸል በማለት ወይም እንደዚህ ባሉ ጥቃቅን ጉዳዮች መረበሽን እምቢ በማለት በቀላሉ የሚሰማውን የልጇን ልብ ማቁሰል የለባትም። ለእናት ትንሽ የሆነው ነገር ለእነርሱ ትልቅ ነው። በትክክለኛ ሰዓት የሚመጣ አቅጣጫ የሚያሳይ ወይም የማስጠንቀቂያ ቃል ብዙ ጊዜ ትልቅ ዋጋ አለው። ሀሳባቸውን መቀበልን የሚያረጋግጥ ዕይታ፣ ከእናት የሚመጣ የማበረታቻና የሙገሳ ቃል፣ በልጅ ልባቸው ላይ ቀኑን በሙሉ የፀሐይ ጮራ እንዲፈነጥቅ ያደርጋል። --HL (Part 2) 46, 47, 1865. (2SM 438, 439.) 169 {1MCP 168.3}1MCPAmh 138.3

  ከትንንሽ ልጆች ጋር ስትሰሩ በእርጋታ ያዙአቸው።--እናቶች ሆይ፣ ትንንሽ ልጆቻችሁን በእርጋታ ያዙአቸው። ስለ እርሱ (ስለ እግዚአብሔር) ብላችሁ ልጆችን አክብሩአቸው። ያለ አግባብ እንድትይዙአቸው፣ እንደ ሳሎን ጌጥ እንስሳት እንድትመለከቱአቸው ወይም ጠዖታችሁ እንድታደርጉአቸው ሳይሆን ንጹህና የከበረ ሕይወት እንዲኖሩ እንድታስተምሩአቸው ቅዱስ ኃላፊነት እንደተሰጣችሁ አድርጋችሁ ተመልከቱአቸው። እነርሱ የእግዚአብሔር ንብረት ናቸው፤ እርሱ ስለሚወዳቸው ፍጹም የሆነ ባሕርይን እንዲመሰርቱ በመርዳት ረገድ ከእርሱ ጋር እንድትተባበሩ ጥሪ ያቀርብላችኋል። --ST, Aug. 23, 1899. (AH 280.) {1MCP 169.1}1MCPAmh 138.4

  ልጃችሁ የእግዚአብሔር ንብረት ነው።--እህቴ ሆይ፣ ሴት ልጅሽ በእናቷ ቃላት ላይ እምነት እንደሌላት በማወቅሽ ትገረሚያለሽን? ውሸታም እንድትሆን አስተምረሻታል፤ ጌታ ከታናናሾቹ አንዷ በእናቷ ወደ ስህተት መንገድ በመመራቷ አዝኖአል። ልጅሽ የአንቺ አይደለችም፤ እሷ የእግዚአብሔር ንብረት ስለሆነች እንደፈለግሽ ልታደርጊያት አትችዪም። እርሷን ከጥፋት ሊያድን የሚችል ቀጣይነት ያለው ቁጥጥር አድርጊ፤ የእግዚአብሔር እንደሆነች አስተምሪያት። በእንደዚህ ዓይነት ስልጠና በዙሪያዋ ላሉት በረከት ለመሆን ታድጋለች። ሁለታችሁንም ለመግዛት ፣ የራሷን ፈቃድና መንገድ ለመከተል፣ እና ደስ ያሰኛትን ለማድረግ ያላትን ዝንባሌ ማፈን እንድትችዪ ነገሮችን በደንብ ጥርት አድርጎ መለየት ያስፈልጋል። --Lt 69, 1896. {1MCP 169.2}1MCPAmh 139.1

  ብሩህ ዝንባሌዎችና ጣፋጭ የአእምሮ ሁኔታዎች።--ልጆቻችሁን ከሕጻንነት አልጋቸው ጀምራችሁ ራስን መካድንና ራስን መቆጣጠርን አስተምሩአቸው። በተፈጥሮ ውበቶች እንዲደሰቱባቸውና ጠቃሚ በሆነ ሥራ ላይ መላውን የአካልና የአእምሮ ኃይሎችን እንዲያውሉ አስተምሩአቸው። ጤናማ የሰውነት አቋምና ጥሩ ግብረገብ፣ ብሩህ ዝንባሌዎችና ጣፋጭ የአእምሮ ሁኔታዎች እንዲኖራቸው አድርጋችሁ አሳድጉ። ለፈተና መሸነፍ ደካማነትና ክፋት እንደሆነ አስተምሩአቸው፤ ፈተናን መቋቋም ደግሞ የከበረ ነገርና ጀግንነት እንደሆነ አስተምሩአቸው። --CT 127 (1913). {1MCP 169.3}1MCPAmh 139.2

  እናቶች ምሳሌ ናቸው።--እናቶች ሴት ልጆቻቸው ጤናማ አካልና ጥሩ ባሕርይ ይዘው ወደ ሴትነት ደረጃ እንዲደርሱ ከፈለጉ እነርሱ ራሳቸው በዚህ ዘመን ጤንነትን ከሚጎዳ ፋሽን ራሳቸውን በመጠበቅ የሕይወት ምሳሌነትን ማሳየት አለባቸው። በክርስቲያን እናቶች ላይ እነርሱ ከሚገነዘቡት የበለጠ ኃላፊነት አርፎባቸዋል። በዚህ በተበላሸ ዘመን ልጆቻቸው ጠንካራ መርህና የግብረገብ ጤንነት እንዲኖራቸው አድርገው ማሰልጠን አለባቸው።--MS 76, 1900. {1MCP 169.4}1MCPAmh 139.3

  የልጅ ምኞት ሕግ ሲሆን።--በአንዳንድ ቤተሰቦች ውስጥ የልጅ ምኞት ሕግ ነው። የሚመኘው ነገር ሁሉ ይሰጠዋል። የሚጠላውን ነገር ሁሉ እንዲጠላ ይበረታታል። የፈለገውን ነገር ማድረግ ልጅን ደስተኛ ያደርገዋል ተብሎ ይገመታል፣ ነገር ግን እረፍትና እርካታ የለሽ ብቻ ያደርገዋል። የፈለገውን የመመገብ ልምድ ለተለመደውና ለጤና ተስማሚ ለሆነ ምግብ ያለውን ፍላጎትና ጊዜውን በአግባቡ ለመጠቀም ያለውን ፍላጎት አበላሽቶአል፤ የራስን ፍላጎት ማሟላት ባሕርዩን ለአሁንና ለዘላለም የመረበሽ ሥራ ሰርቷል።--RH, May 10, 1898. {1MCP 170.1}1MCPAmh 139.4

  ሰይጣን የልጆችን አእምሮ ለመቆጣጠር ይሻል።--ወላጆች ሆይ፣ ሰይጣን ልጆቻችሁን ወደ ሞኝነት ለመምራት የሚሞክርባቸውን አንዳንድ ማታለያዎች ታውቃላችሁ። ወደ ስህተት መንገድ ሊመራቸው ባለው ኃይል ሁሉ እየሰራ ነው። ብዙዎች አልመውት በማያውቁት ቆራጥነት አእምሮአቸውን ለመቆጣጠርና የእግዚአብሔር ትዕዛዛት በእነርሱ ላይ ምንም ዓይነት ተጽእኖ እንዳይኖራቸው ለማድረግ እየፈለገ ነው። --MS 93, 1909. {1MCP 170.2}1MCPAmh 140.1

  ወላጆች ልጆቻቸውን ከልቦቻቸው ጋር ማስተሳሰር አለባቸው።--ልጆቻችሁ ፊታችሁ ደመና ለብሶ እንዲያዩ አታድርጉ። በፈተና ቢወድቁና ኋላ ከስህተታቸው ተናዘው ብታዩ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ይቅር እንዲላችሁ ተስፋ በምታደርጉበት ሁኔታ በነጻ ይቅር በሉአቸው። በትህትና እያስተማራችሁ ከልባችሁ ጋር አቆራኙአቸው። ይህ ለልጆች ወሳኝ ጊዜ ነው። ከእናንተ ለመለየት ተጽእኖዎች በዙሪያቸው ይዘረጋሉ፤ እነዚህን ተጽእኖዎች መቃወም አለባችሁ። እናንተን ምስጢረኞቻቸው እንዲያደርጉአችሁ አስተምሩአቸው። ፈተናዎቻቸውንና ደስታዎቻቸውን በጆሮአችሁ ሹክ እንዲሉ ፍቀዱላቸው። ይህን ስታበረታቱ ልምድ ለሌላቸው እግሮቻቸው ሰይጣን ካዘጋጃቸው ብዙ ወጥመዶች ትታደጉአቸዋላችሁ። {1MCP 170.3}1MCPAmh 140.2

  የራሳችሁን የልጅነት ጊዜ በመርሳትና እነርሱም ልጆች መሆናቸውን በመርሳት በልጆቻችሁ ላይ ያለ መጠን ጥብቅ አትሁኑባቸው። ፍጹም እንዲሆኑ ወይም በድርጊታቸው በአንድ ጊዜ አዋቂ ወንዶችና ሴቶች እንዲሆኑ አትጠብቁ። ይህንን ካደረጋችሁ እነርሱን መድረስ የምትችሉበትን በር በመዝጋት፣ ሊደርስባቸው ስላለው አደጋ እናንተ ከመንቃታችሁ በፊት ሌሎች ለጋ አእምሮአቸውን እንዲመርዙ፣ ጎጂ ለሆኑ ተጽእኖዎች በር ትከፍታላችሁ። --IT 387 (1863). {1MCP 170.4}1MCPAmh 140.3

  ጠንካራ፣ የተመጣጠነ እርምት።--የእያንዳንዱ ልጅ ደስታ ሊገኝ የሚችለው ጠንካራና ተመጣጣኝ በሆነ እርምት ነው። የልጅ እውነተኛ ጸጋዎች የትዕዛዝን ቃላት የሚሰሙ አድማጭ ጆሮዎች፣ በተግባር መንገድ ለመጓዝና ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ እግሮች ያሉበትን ጨዋነትንና መታዘዝን ያካትታል። የልጅ እውነተኛ መልካምነት በዚህ ሕይወት እንኳን የራሱ ሽልማት አለው። {1MCP 171.1}1MCPAmh 140.4

  የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ልጅ እጅግ አገልጋይ እንዲሆንና በዚህ ሕይወት ጸጋንና እውነትን የተሞላ እንዲሆን ብቻ ሳይሆን እውነተኛና ታማኝ ለሆኑት ሁሉ በላይኛው ቤት የተዘጋጀውን ቦታ ለማግኘትም ስልጠና የሚካሄድባቸው ጊዜያቶች ናቸው። የራሳችንን ልጆችና የሌሎች ሰዎችን ልጆች ስናሰለጥን ያረጋገጥነው ነገር ቢኖር ክፉ እንዳያደርጉ ለሚከለክሉአቸው ወላጆችና አሳዳጊዎች ያላቸው ፍቅር በፍጹም ለሌሎች ካላቸው ፍቅር ያነሰ እንዳይደለ ነው።--RH, May 10, 1898. {1MCP 171.2}1MCPAmh 141.1

  ኢየሱስ ልዩ የሆነ ተወዳጅ ፍቅርን አሳይቶአል።--ኢየሱስ ልጅ በነበረ ጊዜ ልዩ የሆነ ተወዳጅ ባሕርይ ነበረው። ፈቃደኛ የነበሩ እጆቹ ሌሎችን ለማገልገል ሁል ጊዜ ዝግጁ ነበሩ። ምንም ነገር ሊረብሸው የማይችለውን ትዕግስት እና በፍጹም ታማኝነትን መስዋዕት የማያደርገውን እውነተኛነት አሳየ። በመርህ እንደ ዓለት ጽኑ ስለነበር ሕይወቱ ራስ ወዳድነት የሌለበትን ገርነት አሳየ። {1MCP 171.3}1MCPAmh 141.2

  የኢየሱስ እናት ጥልቅ በሆነ ትኩረት ኃይሎቹ ሲገለጡና በባሕርዩ ላይ የነበረውን የፍጽምና አሻራ ተመለከተች። ደስ እያላት ያንን ብሩህና ለመቀበል የተዘጋጀ አእምሮ ለማደፋፈር ፈለገች። አባቱ እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ በተናገረው በዚህ ልጅ ዕድገት ውስጥ ከሰማያዊ ኃይሎች ጋር ለመተባበር በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ጥበብን ተቀበለች። --DA 68, 69 (1898). {1MCP 171.4}1MCPAmh 141.3

  የአእምሮ አስቀድሞ መያዝ ዝቅ ያሉ ሀሳቦችን ይገታል።--የተወደዱ ልጆቻችሁን የአካልና የአእምሮ ኃይሎችንና ፍላጎታቸውን አሰልጥኑ፤ ዝቅ ላሉና ለሚያዋርዱ ሀሳቦች ወይም ፍላጎታቸውን ለማሟላት ቦታ እንዳይሰጡ አስቀድማችሁ አእምሮአቸውን ለማስያዝ እሹ። ለክፋት ብቸኛው ማርከሻ ወይም መከላከያ የክርስቶስ ጸጋ ነው። ከፈለጋችሁ የልጆቻችሁ አእምሮዎች ንጹህና ባልተበላሹ ሀሳቦች እንዲያዙ ወይም በየቦታው ባሉ ክፋቶች--ኩራትና አዳኛቸውን መርሳት--እንዲያዙ ለማድረግ መምረጥ ትችላላችሁ። --Lt 27, 1890. (CG 188.) {1MCP 172.1}1MCPAmh 141.4

  በቀላሉ በማይፈርስ አጥር መታጠር።--የእያንዳንዱ ክርስቲያን ቤት ደንቦች ሊኖሩት ይገባል፤ ወላጆች በቃላቶቻቸውና ለእርስ በርስ ከሚያሳዩት ባሕርይ ልጆች እንዲሆኑ ለሚፈልጉት ነገር የከበረ ሕያው ምሳሌ መስጠት አለባቸው። የንግግር ንጽህና እና እውነተኛ የክርስቲያን ገርነት ያለማቋረጥ መተግበር አለባቸው። ኃጢአትን ማበረታታት፣ መረጃ የሌላው ክፉ ግምት ወይም ክፉ መናገር መኖር የለበትም። {1MCP 172.2}1MCPAmh 141.5

  ልጆችና ወጣቶች ራሳቸውን እንዲያከብሩ፣ ለእግዚአብሔር እውነተኛ እንዲሆኑ፣ ለመርህ እውነተኛ እንዲሆኑ አስተምሩአቸው፤ የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲያከብሩና እንዲታዘዙ አስተምሩአቸው። ያኔ እነዚህ መርሆዎች ሕይወታቸውን ይቆጣጠራሉ፣ ከሌሎች ጋር በሚኖራቸው ግንኙነትም ተፈጻሚ ይሆናሉ። ጎረቤታቸውን እንደ ራሳቸው ይወዳሉ። ደካማ ነፍሳትን ወደ ቅድስናና ወደ ሰማይ በሚመራ መንገድ የሚያደፋፍር ተጽእኖ ያለው ንጹህ ከባቢ አየር ይፈጥራሉ። እያንዳንዱ ትምህርት ከፍ የሚያደርግ፣ የከበረ ባሕርይን የሚፈጥር ከሆነ በሰማይ መጻሕፍት ውስጥ የተመዘገበው ነገር በፍርድ ቀን ለመጋፈጥ የማታፍሩበት ይሆናል። {1MCP 172.3}1MCPAmh 142.1

  የዚህን ዓይነት ትምህርት የሚያገኙ ልጆች በተቋሞቻችን ውስጥ (የትምህርት፣ የጤና፣ የህትመት፣ ወዘተ… ተቋመት) ሸክም፣ የስጋት ምክንያት አይሆኑም፤ ነገር ግን ኃላፊነትን ለሚሸከሙ ሰዎች ብርታትና ድጋፍ ይሆናሉ። ኃላፊነትን የሚጠይቁ ቦታዎችን ለመሙላት ስለሚዘጋጁ በቃልና በምሳሌነት ያለማቋረጥ ሌሎች ትክክል የሆነውን እንዲያደርጉ ይረዳሉ። የሞራል ስሜቶቻቸው ያልደነዙ ሰዎች ትክክለኛ መርሆዎችን ያደንቃሉ ይለማመዱአቸውማል። ስለ ተሰጥኦዎቻቸው ትክክለኛ ግምት ስለሚኖራቸው የአካላቸውን፣ የአእምሮአቸውንና የግብረገብ ኃይሎቻቸውን በደንብ ይጠቀማሉ። {1MCP 172.4}1MCPAmh 142.2

  እንደ እነዚህ ያሉ ነፍሳት ፈተና እንዳያገኛቸው ያለማቋረጥ ዙሪያቸው ተመሽጎአል፤ በቀላሉ ሊፈርስ በማይችል ግንብ ዙሪያቸው ታጥሮአል። እንደ እነዚህ ያሉ ገጸ ባሕርያት፣ በእግዚአብሔር በረከት፣ ብርሃን ተሸካሚዎች ናቸው፤ የእነርሱ ተጽእኖ ሌሎችን ወደ ተግባራዊ የክርስቲያን ሕይወት ከፍ ወደማድረግ ያዘነብላል። መለኮታዊ ሀሳቦችና ግምቶች እንደ እስትንፋስ ተፈጥሮአዊ እስኪሆኑ ድረስ አእምሮ ከፍ ይላል።--Lt 74, 1896. {1MCP 173.1}1MCPAmh 142.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents