Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 23—ፍቅር-መለኮታዊ፣ ዘላለማዊ መርህ

    ፍቅር፣ የተግባር መርህ።--የዘላለማዊ ፍቅር ሰማያዊ መርህ ልብን ሲሞላ፣ ወደ ሌሎች ይፈሳል፣…ይህ የሚሆነው ፍቅር የተግባር መርህ ስለሆነ እና ባህርይን ስለሚያሻሽል፣ ፍላጎትን ስለሚገዛ፣ ኃይለኛ ስሜቶችን ስለሚቆጣጠር፣ ጠላትነትን ስለሚያሸንፍና የፍቅር ስሜቶችን ከፍ ያሉና የከበሩ እንዲሆኑ ስለሚያደርግ ነው። --4T 223 (1876). {1MCP 205.1}1MCPAmh 167.1

    ከማንኛውም ሌላ መርህ የተለየ።--ንጹህ ፍቅር አሰራሮቹ ቀላልና ከማንኛውም ሌላ የተግባር መርህ የተለየ ነው። --2T 136 (1868). {1MCP 205.2}1MCPAmh 167.2

    ኩትኳቶና እንክብካቤ የሚያስፈልገው ጮርቃ ተክል።--ፍቅር ጮርቃ ተክል ስለሆነ መኮትኮትና እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል፤ ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን እንድንወድና ባልንጀራችንን እንደ ራሳችን እንድንወድ፣ ፍቅር የሚዘዋወርበትን ቦታ አግኝቶ ሁሉንም የአእምሮ ኃይሎች፣ ልብን በሙሉ በተጽእኖው ሥር እንዲያደርግ፣ ከዙሪያው የመራርነት ሥሮች በሙሉ መነቀል አለባቸው። --MS 50, 1894. (HC 173.) {1MCP 205.3}1MCPAmh 167.3

    የሰይጣን ምትክ--በፍቅር ቦታ ራስ ወዳድነት።--ካለመታዘዝ የተነሣ የሰው ኃይሎች ስለተዛቡ ራስ ወዳድነት የፍቅርን ቦታ ወሰደ። የሰው ተፈጥሮ እጅግ ከመድከሙ የተነሣ የክፉን ኃይል መቋቋም አልተቻለውም ነበር፤ ፈታኙ እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር የነበረውን ዓላማ ለማሰናከልና ምድርን በመከራና በባዶነት ለመሙላት ዓላማው ሲፈጸም ተመለከተ። --CT 33 (1913). {1MCP 205.4}1MCPAmh 167.4

    ራስ ሲሰጥም ፍቅር ሳይታሰብ በድንገት ይበቅላል።--ራስ በክርስቶስ ውስጥ ሲሰጥም፣ እውነተኛ ፍቅር በድንገት ይበቅላል። ፍቅር ስሜት ወይም ጽኑ ፍላጎት ሳይሆን የተቀደሰ የፈቃድ ውሳኔ ነው። ስሜትን ሳይሆን ለራስ ሞቶ ለእግዚአብሔር ህያው የሆነውን ልብን፣ ነፍስንና ባሕርይን በሙሉ መለወጥን ያካትታል። ጌታችንና አዳኛችን ራሳችንን ለእርሱ እንድንሰጥ ይጠይቀናል። እርሱ የሚፈልገው ራስን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠትን፣ እርሱ ገጣሚ ነው ብሎ እንደሚመለከተው እንዲጠቀምብን ራሳችንን ለእርሱ መስጠትን ነው። ወደዚህ ራስን አሳልፎ የመስጠት ነጥብ እስክንመጣ ድረስ በየትኛውም ቦታ ቢሆን በደስታ፣ ልንጠቅም በምንችልበት ሁኔታ፣ ወይም በተሳካ ሁኔታ መስራት አንችልም። --Lt 97, 1898. (6BC 1100, 1101.) {1MCP 206.1}1MCPAmh 167.5

    ፍቅር ስሜት ሳይሆን መለኮታዊ መርህ ነው።--ከሁሉም በላይ ፍቅር ለእግዚአብሔር እና ለእርስ በርስ ራስ ወዳድነት የሌለበት ፍቅር--ይህ ሰማያዊ አባታችን ሊሰጠን የሚችል ከሁሉ የተሻለ ሥጦታ ነው። ይህ ፍቅር ስሜት ሳይሆን መለኮታዊ መርህ፣ ቋሚ የሆነ ኃይል ነው። ያልተቀደሰ ልብ የዚህ ፍቅር መነሻ ሊሆን ወይም ሊያስገኝ አይችልም። ይህ ሊገኝ የሚችለው ኢየሱስ በነገሰበት ልብ ውስጥ ብቻ ነው። ‹‹እርሱ አስቀድሞ ስለወደደን እንወደዋለን›› (ዮሐንስ 4፡ 19)። በመለኮታዊ ጸጋ በታደሰ ልብ ውስጥ ፍቅር የተግባር ገዥ መርህ ነው።--AA 551 (1911). {1MCP 206.2}1MCPAmh 168.1

    ፍቅር--የአእምሮ እውቀትና የሞራል ብርታት።--ፍቅር ኃይል ነው። በዚህ መርህ ውስጥ የእውቀትና የግብረገብ ብርታት ስለተካተተበት ከእርሱ ሊለይ አይችልም። የሀብት ኃይል የማበላሸትና የማጥፋት ዝንባሌ አለው፤ የጉልበት ኃይል ለመጉዳት ጠንካራ ነው፤ ነገር ግን የንጹህ ፍቅር ብቃትና ዋጋ መልካም ለማድረግና ከመልካም በቀር ምንም ነገር ላለማድረግ ብቃት አለው። በንጹህ ፍቅር የተደረገ ምንም ነገር ቢሆን፣ እጅግ ትንሽ ወይም በሰዎች ዘንድ የተናቀም ቢሆን፣ ሙሉ በሙሉ ውጤታማ ነው፤ እግዚአብሔር ቦታ የሚሰጠው ግለሰቡ ለሰራው የሥራ መጠን ሳይሆን ሥራውን ለመስራት ያነሳሳው ፍቅር ምን ያህል ነው ለሚለው ነው። ፍቅር ከእግዚአብሔር ነው። ያልተለወጠ ልብ ይህን ሰማያዊ መነሻ ያለውንና ክርስቶስ በነገሰበት ብቻ የሚኖረውንና የሚያድገውን ይህን ተክል ሊያበቅል ወይም ሊያስገኝ አይችልም። --2T 135 (1868). {1MCP 206.3}1MCPAmh 168.2

    መልካም መዓዛ ያለውን ከባቢ አየር ውደዱ።--እያንዳንዱ ነፍስ በራሱ ከባቢ አየር ተከቦአል--በእምነት በሚገኝ ሕይወት ሰጭ ኃይል፣ ድፍረትና ተስፋ በተሞላ፣ እና በፍቅር መልካም መዓዛ በጣፈጠ ከባቢ አየር ተከቦአል። ወይም ካለመርካትና ከራስ ወዳድነት ጨለማ የተነሣ ከባድና በራድ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ከተንከባከቡት የኃጢአት ገዳይ ብክለት የተነሣ መርዘኛ ሊሆን ይችላል። ከሚከበን ከባቢ አየር የተነሣ ከእኛ ጋር ግንኙነት የሚፈጥር እያንዳንዱ ሰው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ተጽእኖ ይደርስበታል። --COL 339 (1900). {1MCP 207.1}1MCPAmh 168.3

    ራስ ወዳድነትንና ጠብን ይነቅላል።--የፍቅር ወርቃማው ሰንሰለት፣ በጓደኝነት ስሜትና በፍቅር ማሰሪያ የአማኞችን ልቦች በአንድነት በማሰር፣ እና ከክርስቶስና ከአባት ጋር አንድ በመሆን፣ ግንኙነትን ፍጹም ያደርግና መካድ ስለማይቻለው የክርስትና ኃይል ለዓለም ምስክርነትን ያስተላልፋል…። ያኔ ራስ ወዳድነት ይነቀልና ታማኝነትን ማጉደል አይኖርም። ጠብና መከፋፈል አይኖርም። ከክርስቶስ ጋር እስረኛ በሆነ በማንም ቢሆን ትዕቢተኝነት አይኖርም። አንድም ሰው ቢሆን እየመራው የነበረውን እጅ እንደጣለውና ብቻውን ለመደናቀፍና በራሱ መንገድ ላይ ለመሄድ እንደ መረጠው እንደ ኮብላዩ፣ ስሜታዊ ልጅ ትዕቢት ያለበትን ራስን የመቻል ሚና አይጫወትም።--Lt 110, 1893. (HC 173.) {1MCP 207.2}1MCPAmh 168.4

    የንጹህ ፍቅር ፍሬ።--‹‹ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው›› (ማቴዎስ 7፡ 12)። በዚህ ዓይነቱ መንገድ ላይ የተባረኩ ውጤቶች እንደ ፍሬ ይታያሉ። ‹‹በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል›› (ቁጥር 2)። እርስ በርሳችን ግለት ባለው ንጹህ ፍቅር እንድንዋደድ የሚያስገድደን ጠንካራ ምክንያት እዚህ አለ። ክርስቶስ ምሳሌያችን ነው። መልካም እያደረገ ዞረ። ሌሎችን ለመባረክ ኖረ። ፍቅር ተግባሮቹን ሁሉ ያማሩና የከበሩ እንዲሆኑ አደረገ። {1MCP 207.3}1MCPAmh 169.1

    ሌሎች ለእኛ እንዲያደርጉልን የምንፈልገውን ነገር ለራሳችን እንድናደርግ አልታዘዝንም፤ እኛ ባለንበት ሁኔታዎች ውስጥ ሰዎች እንዲያደርጉልን የምንፈልገውን ነገር እኛ ለሌሎች ማድረግ አለብን። ሁል ጊዜ በምንሰፍርበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርብናል።…{1MCP 208.1}1MCPAmh 169.2

    ተጽእኖ የማሳደር ፍቅርና ለሌሎች ከፍተኛ ግምት የመስጠት ፍላጎት ሥርዓት ያለው ህይወት ሊፈጥርና አዘውትሮ ነውር የለሽ ንግግርን ሊያስገኝ ይችላል። ራስን ማክበር የክፉ መከሰትን ወደማስወገድ ሊመራን ይችላል። ራስ ወዳድ የሆነ ልብ በውጫዊ ሁኔታ የልግስና ተግባርን ሊፈጽም፣ የወቅቱን እውነት ሊቀበል፣ እና ራስን ዝቅ ማድረግንና ፍቅርን ሊያሳይ ይችላል፣ ነገር ግን ለድርጊቱ ያነሳሳው ምክንያት አታላይና ንጹህ ያልሆነ ሊሆን ይችላል፤ ከእንደዚህ ዓይነት ልብ የሚፈልቁ ተግባሮች የህይወት ሽታ፣ የእውነተኛ ቅድስና ፍሬና የንጹህ ፍቅር መርሆዎች የሌላቸው ናቸው። --2T 136 (1868). {1MCP 208.2}1MCPAmh 169.3

    ፍቅር ምህረት ያደርጋል።--የክርስቶስ ፍቅር ጥልቅና ቅን፣ ለሚቀበሉት ሁሉ ማገድ የማይቻል የሚፈስ የሕይወት ምንጭ ነው። በእርሱ ፍቅር ራስ ወዳድነት የለም። ይህ ከሰማይ የሆነው ፍቅር በልብ ውስጥ የሚያድር መርህ ከሆነ በተቀደሰ ግንኙነት እጅግ ለምንወዳቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን ግንኙነት ለምንፈጥራቸው ሰዎች ሁሉ ራሱን ያሳውቃል። ትኩረት ለሚፈልጉ ጥቃቅን ተግባራት ትኩረት ወደ መስጠት፣ ምህረት ወደ ማድረግ፣ የደግነት ተግባራትን ወደ መፈጸም፣ ገር፣ እውነተኛና የሚያደፋፍሩ ቃላትን ወደ መናገር ይመራናል። ልባቸው ለርኅራኄ ለሚራቡ ሰዎች ርኅራኄን ወደ ማሳየት ይመራናል። --MS 17, 1899. (5BC 1140.) {1MCP 208.3}1MCPAmh 169.4

    ፍቅር አንድን ነገር ለማድረግ የሚያነሳሱ ምክንያቶችንና ተግባሮችን ይቆጣጠራል።-- ውጫዊ ለሆነ የሕይወት ጨዋነት እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩረት መስጠት ደስተኛ አለመሆንን፣ የጭካኔ ፍርድን፣ ተገቢ ያልሆነ ንግግርን ሁሉ ለማስቀረት በቂ አይደለም።ራስ ከፍተኛ የትኩረት ጉዳይ በሆነበት እውነተኛ የሆነ የባሕርይ መስተካከል በፍጹም ሊታይ አይችልም። ፍቅር በልብ ውስጥ መኖር አለበት። እውነተኛ የሆነ ክርስቲያን ሙሉ ለሚያደርገው ነገር ማነሳሻ የሚያገኘው ለጌታው ካለው ጥልቅ የሆነ ልባዊ ፍቅር ነው። ለክርስቶስ ካለው ፍቅር ሥር ከወንድሞቹ ላይ የራሱን ጥቅም ያለመፈለግ ፍላጎት ወደ ላይ ይበቅላል። ፍቅር ለባለቤቱ የጠባይ ጸጋን፣ ጨዋነትንና ውበትን ይሰጣል። ፊትን ያበራና ድምጽን በቁጥጥር ሥር ያውላል፤ መላውን ፍጡር ያሻሽላል፣ ከፍ ከፍም ያደርጋል። --GW 123 (1915). {1MCP 208.4}1MCPAmh 170.1

    ፍቅር የሌላውን ሰው የድርጊት ማነሳሻዎች በመልካም ይተረጉማል።--ፍቅር ‹‹የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልንም አይቆጥርም›› (1ኛ ቆሮ. 13፡ 5)። ክርስቶስን የሚመስል ፍቅር ሌሎች ሰዎች አንድን ነገር እንዲያደርጉ ስላነሳሳቸው ነገርና ስለ ተግባራቸው ቀና የሆነ ትርጉም ይሰጣል። አስፈላጊ ባልሆነ ሁኔታ ስህተታቸውን አያጋልጥም፤ ተገቢ ያልሆኑ ዘገባዎችን በጉጉት አያዳምጥም፣ ነገር ግን የሌሎችን መልካም ባህርያት ወደ አእምሮ ለማምጣት ይሻል።--AA 319 (1911). {1MCP 209.1}1MCPAmh 170.2

    ፍቅር መላውን ሕይወት ያጣፍጣል።--እግዚአብሔርን የሚወዱ ሰዎች ጥላቻን ወይም ቅናትን አያስተናግዱም። የዘላለም ፍቅር ሰማያዊ መርህ ልብን ሲሞላ ወደ ሌሎች ይፈሳል። . . . {1MCP 209.2}1MCPAmh 170.3

    ይህ ፍቅር ዝም ብሎ ‹‹እኔና የእኔ›› የሚባሉ ነገሮችን ለማካተት የተፈጠረ ሳይሆን እንደ ዓለም ሰፊና እንደ ሰማይ ከፍ ያለ፣ ከመላእክት ሰራተኞች ፍቅር ጋር የተጣጣመ ነው። ይህ በነፍስ ውስጥ ቦታ የተሰጠው ፍቅር መላውን ሕይወት በማጣፈጥ በዙሪያው ሁሉ የሚያስተካክል ተጽእኖ ያሳርፋል። የዚህ ፍቅር ባለቤት ስንሆን ዕድል ብትስቅልንም ብትኮሳተርብንም ደስተኞች እንሆናለን። {1MCP 209.3}1MCPAmh 170.4

    እግዚአብሔርን ከሙሉ ልባችን ከወደድነው ልጆቹንም መውደድ አለብን። ይህ ፍቅር የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ለነፍስ እውነተኛ ታላቅነትና ክብር የሚሰጥና ሕይወታችንን ከጌታ ሕይወት ጋር የሚያዋህድ ነው። ምንም ያህል ጥሩ ችሎታዎች ቢኖሩንም፣ ምንም ያህል ራሳችንን የተከበርንና የተስተካከልን አድርገን ብንገምትም፣ ነፍስ ለእግዚአብሔርና ለእርስ በርስ ባለን ሰማያዊ ጸጋ በሆነው ፍቅር ካልተጠመቀች በቀር እውነተኛ መልካምነት ስለሚጎድለን፣ ሁሉም ነገር ፍቅርና አንድነት ለሆነበት ሰማይ ገጣሚዎች ሳንሆን እንቀራለን። --4T 223, 224 (1876). {1MCP 209.4}1MCPAmh 170.5

    እውነተኛ ፍቅር መንፈሳዊ ነው።--ፍቅር፣ ከኃይለኛ ፍላጎትና ስሜት በመውጣት፣ መንፈሳዊ ይሆንና በቃላትና በተግባር ይገለጣል። ክርስቲያን ትዕግስት ማጣትና ደስተኛ አለመሆን የሌለበት የተቀደሰ ደግነትና ፍቅር ሊኖረው ይገባል፤ ትህትና የሌላቸው፣ አስቀያሚ ባሕርያት በክርስቶስ ጸጋ መለስለስ አለባቸው። --5T 335 (1885). {1MCP 209.5}1MCPAmh 171.1

    ተግባር ፍቅርን ይመግባል።--ፍቅር ያለ ምግባር መኖር ስለማይችል እያንዳንዱ ተግባር ፍቅርን ይጨምራል፣ ያጠነክራል፣ ያሰፋውማል። ክርክርና የበላይነት ኃይል የለሽ በሚሆኑበት ጊዜ ፍቅር ያሸንፋል። ፍቅር ለትርፍ ወይም ሽልማት ለማግኘት አይሰራም፤ ሆኖም እያንዳንዱ የፍቅር ሥራ ትልቅ ትርፍ ያለውን እርግጠኛ ውጤት እንዲያስገኝ እግዚአብሔር አዝዞአል። ፍቅር በተፈጥሮው ወደ ሌሎች የሚሰርጽና በጸጥታ የሚሰራ፣ ግን ትልልቅ ክፋቶችን በማሸነፍ ዓላማው ብርቱና ኃያል ነው። ተጽእኖው የሚያቀልጥና የሚለውጥ ሲሆን እያንዳንዱ ሌላ ዘዴ ሳይሳካ ሲቀር እርሱ የኃጢአተኞችን ሕይወት በመቆጣጠር ልቦቻቸውን ይነካል። {1MCP 210.1}1MCPAmh 171.2

    የአእምሮ ችሎታ፣ ሥልጣን፣ ወይም ኃይል ሥራ ላይ በዋለበት ሁሉ ፍቅር አይገኝም፣ እኛ ልንደርሳቸው የምንፈልጋቸው ሰዎች የፍቅር ስሜታቸውም ሆነ ፈቃዳቸው የእኛን ሀሳብ የመከላከልና ወደ ኋላ የመግፋት አቋም ስለሚይዝ የመቃወም ብርታታቸው ይጨምራል። ኢየሱስ የሰላም መስፍን ነበር። ወደ ዓለም የመጣው ተቃውሞንና ሥልጣንን ለራሱ ለማስገዛት ነበር። ጥበብንና ብርታትን መጠቀም ነበረበት፣ ነገር ግን ክፉን ለማሸነፍ የተጠቀማቸው ነገሮች የፍቅርን ጥበብና ብርታት ነበር። --2T 135, 136 (1868). {1MCP 210.2}1MCPAmh 171.3

    ለአዲስ የሕይወት መርህ ማስረጃ ይሰጣል።--ሰዎች በራስ ፍላጎት ኃይል ሳይሆን በፍቅር አንድ ሲሆኑ ከእያንዳንዱ ሰብአዊ ተጽእኖ በላይ የሆነ ተጽእኖን ሥራ ያሳያሉ። ይህ አንድነት ሲኖር የእግዚአብሔር ምስል በሰዎች ውስጥ እየተመለሰና አዲስ የሕይወት መርህ በውስጥ እየተተከለ ለመሆኑ ማስረጃ ነው። ከተፈጥሮ ውጭ የሆኑ የክፉ ወኪሎችን ለመቋቋምና በተፈጥሮአዊ ልብ ውስጥ በውርስ የተገኘውን ራስ ወዳድነትን የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲያሸንፍ በመለኮታዊው ተፈጥሮ ውስጥ ኃይል መኖሩን ያሳያል። --DA 678 (1898). {1MCP 210.3}1MCPAmh 171.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents