Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First

  ምዕራፍ 29—መደገፍና አለመደገፍ (ጥገኝነትና ጥገኛ አለመሆን)

  (ሀ) በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር መደገፍ/መተማመን

  በእግዚአብሔር መደገፍ ፍጹም ነው።--እግዚአብሔር እያንዳንዱ ክርስቶስ የሞተለት ነፍስ ከወይን ግንዱ ጋር በመገናኘት ከግንዱ ምግብ ማግኘት እንዲችል የወይን ተክሉ አካል እንዲሆን ይፈልጋል። በእግዚአብሔር ላይ ያለን መደገፍ ፍጹም ስለሆነ ትሁት ሊያደርገን ይገባል፤ ይህ የሚሆነው በእርሱ መደገፋችን፣ እርሱን ማወቃችን በከፍተኛ ደረጃ ስለሚጨምር ነው። እግዚአብሔር እያንዳንዱን የራስ ወዳድነት ዝርያ አስወግደን፣ የራሳችን ባለቤት ሆነን ሳይሆን ጌታ እንደገዛን ንብረት ሆነን ወደ እርሱ እንድንመጣ ይፈልጋል።--SpT Series A, No. 8, pp 8, 9, 1897. (TM 324, 325.) {1MCP 261.1}1MCPAmh 214.1

  በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር ተደገፉ።--ሰዎች ከእርሱ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት እንዲኖራቸው እግዚአብሔር ይፈልጋል። ከሰብአዊ ፍጡራን ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ የግለሰብ ሀላፊነትን መርህ ይገነዘባል። በግል የመደገፍን ስሜት ለማደፋፈርና በግል ምሪት የማግኘት አስፈላጊነትን በአእምሮ ውስጥ ለማስረጽ ይሻል። ሰዎች እግዚአብሔርን ወደ መምሰል እንዲለወጡ ሰብአዊው ከመለኮታዊው ጋር ህብረት እንዲፈጥር ይመኛል። ሰይጣን ይህን ዓላማ ለማሰናከል ይሰራል። በሰዎች ላይ መደገፍን ለማበረታታት ይሻል። አእምሮዎች ከእግዚአብሔር ወደ ሌላ አቅጣጫ ሲመለሱ ፈታኙ በእርሱ ግዛት ሥር ያደርጋቸዋል። ሰብአዊነትን መቆጣጠር ይችላል።--MH 242, 243 (1905). {1MCP 261.2}1MCPAmh 214.2

  እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ መደገፊያህ አድርግ።--ከዚህ የተለየ ነገር እያደረግህ ከሆነ ቆም ብለህ ለማሰብ ጊዜው አሁን ነው። ባለህበት ቁምና የነገሮችን ቅደም ተከተል ለውጥ…። ከልብህ በመሆን፣ ነፍስህን በማስራብ ወደ እግዚአብሔር ጩህ። ድል እስኪታገኝ ድረስ ከሰማያዊ ወኪሎች ጋር ታገል። መላ አንተነትህን--ነፍስን፣ አካልንና መንፈስን-- በእግዚአብሔር እጆች አስቀምጥና በእርሱ ፈቃድ የተነሳሳህ፣ በእርሱ አእምሮ ቁጥጥር ሥር ያለህ፣ በእርሱ መንፈስ ተሞልተህ እርሱን የምትወድ፣ የተቀደስህ ወኪል ለመሆን ወስን፤ ያኔ ሰማያዊ ነገሮችን በግልጽ ታያለህ።--MS 24, 1891. (SD 105.) {1MCP 262.1}1MCPAmh 214.3

  እግዚአብሔርን አማካሪህ አድርግ።--ግራ የሚያጋቡህን ነገሮች ለወንድም ወይም ለአገልጋይ ከመንገር ይልቅ በጸሎት ወደ ጌታ ውሰዳቸው። አገልጋይን በእግዚአብሔር ቦታ አታስቀምጥ፣ ነገር ግን ጸልይለት። በዚህ ነጥብ ላይ ሁላችንም ተሳስተናል። የክርስቶስ አገልጋይ ከሌሎች ሰዎች የተለየ አይደለም። በእርግጥ ተራ ከሆነ የንግድ ሰው ይልቅ ብልጫ ያላቸው ቅዱስ ኃላፊነቶችን ይሸከማል፣ ነገር ግን የማይሳሳት( ፍጹም) አይደለም። እርሱም በድካም የተከበበ ስለሆነ ጸጋና መለኮታዊ ማብራሪያ ያስፈልገዋል። ለአገልግሎቱ ሙሉ ማረጋገጫ በመስጠት ሥራውን በትክክልና በስኬት መሥራት እንዲችል ሰማያዊ ቅባት ያስፈልገዋል። ስለ ሕይወት መንገድና ስለ ድነት እውቀት የሌላቸው ሰዎች እግዚአብሔርን የሚያከብርን አገልጋይ ሲመለከቱ ለመዳን ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የሚያስተምራቸው ሰው ሆኖ ያገኙታል። {1MCP 262.2}1MCPAmh 214.4

  እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው፣ የክርስቶስ ወንጌል ግብዣዎች ምን እንደሆኑ እና የእርሱ ተስፋዎች የማይለወጡ መሆናቸውን የሚያውቁ ሰዎች ሸክማቸውን ውስን በሆኑ ሰዎች ላይ በሚያስቀምጡበት ጊዜ እግዚአብሔርን ያዋርዳሉ። ሁል ጊዜ አብሮ መምከር ትክክል ነው። አብሮ መወያየትም ትክክል ነው። በማንኛውም ሥራ ውስጥ የሚያጋጥሙአችሁን ችግሮች ለወንድሞቻችሁና ለአገልጋያችሁ ማሳወቅ ትክክል ነው። ነገር ግን ጥበብን ለማግኘት በሰዎች ላይ በመደገፍ እግዚአብሔርን አታዋርዱ። ከላይ የሚመጣውን ጥበብ እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት። አብረዋችሁ የሚሰሩ ሰዎች አብረዋችሁ እንዲጸልዩ ጠይቁአቸው፣ ጌታም ‹‹ሁለት ወይም ሶስት ሆነው በስሜ በተሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እገኛለሁ›› (ማቴ. 18፡ 28) ብሎ የተናገረውን ቃሉን ይፈጽማል። --MS 23, 1899. {1MCP 262.3}1MCPAmh 215.1