Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 38—በትምህርት ሚዛንን መጠበቅ

  ትምህርት ዘላለማዊ እንደምታ አለው። ትምህርት መጨረሻ በሌለው ዘላለም ውጤቱ የሚታይ ሥራ ነው። --6T 154 (1900). {1MCP 359.1}1MCPAmh 294.1

  በአካል ውስጥ መጣጣምን መመለስ።--የትምህርት እውነተኛው ዓላማ በነፍስ ውስጥ የእግዚአብሔርን ምስል መመለስ ነው። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰውን በአምሳሉ ፈጠረ። የከበሩ ችሎታዎችን ሰጠው። አእምሮው ሚዛናዊ የሆነ እና የአካል ክፍሎቹም የተጣጣሙ ነበሩ። ነገር ግን ውድቀትና ውጤቶቹ እነዚህን ስጦታዎች አዛብተዋል። ኃጢአት በሰው ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ምስል አበላሽቶአል፣ ደምስሶታልም። የድነት እቅድ የተዘጋጀውና ለሰው የአመክሮ ሕይወት የተሰጠው ይህን ለመመለስ ነበር። መጀመሪያ ወደ ተፈጠረበት ፍጽምና መመለስ የሕይወት ትልቁ ዓላማ--ሌላውን ዓላማ ሁሉ የሚያካትት ዓላማ ነው። ወጣቶችን በማስተማር ሂደት ከመለኮታዊ ዓላማ ጋር መተባበር የወላጆችና የመምህራን ዓላማ መሆን አለበት፤ ይህን ሲያደርጉ ‹‹ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሰራተኞች›› ይሆናሉ። --PP 595 (1890). {1MCP 359.2}1MCPAmh 294.2

  ሁሉም ችሎታዎች መጎልበት አለባቸው።--ሰዎች ያሉአቸው የተለያዩ ዓይነት ችሎታዎች ሁሉ--የአእምሮ፣ የነፍስና የአካል---በእግዚአብሔር የተሰጡት ሊደረስ የሚቻለውን ከፍተኛ የልቀት ደረጃ ለመድረስ ሥራ ላይ እንዲውሉ ነው። ነገር ግን ወደ እርሱ ምስል መለወጥ ያለብን የእግዚአብሔር ባህርይ ልግስናና ፍቅር ስለሆነ ነው፤ ይህ ራስ ወዳድና የግል የሆነ ባህል ሊሆን አይችልም። ፈጣሪ የሰጠን እያንዳንዱ የአካል ክፍል፣ እያንዳንዱ ባሕርይ ለእርሱ ክብርና ባልንጀሮቻችንን ከፍ ለማድረግ ሥራ ላይ መዋል አለበት። በዚህ ሥራ ውስጥ እጅግ ንጹህ፣ ክቡርና ደስታ ያለበት እንቅስቃሴ ይገኛል። -- PP 595 (1890). {1MCP 359.3}1MCPAmh 294.3

  እውነተኛ ትምህርት ሰፊ ነው።--እውነተኛ ትምህርት ማለት አንድን የትምህርት ዘርፍ ከመማር የበለጠ ነው። ሰፊም ነው፤ የሁሉንም የአካል ኃይሎችና የአእምሮ ችሎታዎች የተጣጣመ እድገት ያካትታል፡ እግዚአብሔርን መውደድንና ፈሪሀ-እግዚአብሔርን ስለሚያስተምር የህይወትን ሀላፊነቶች በታማኝነት ለመወጣት መዘጋጀት ነው።--CT 64 (1913). {1MCP 360.1}1MCPAmh 294.4

  ለእያንዳንዱ ተግባር ለመዘጋጀት ሁሉን ያካተተ እድገት።--ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሰራተኞች የሚሆኑ ለእያንዳንዱ የአካል ክፍል ፍጹም እንዲሆንና ለአእምሮ ብቃት መጣር አለባቸው። እውነተኛ ትምህርት ማለት እያንዳንዱን ተግባር ለማከናወን የአካል፣ የአእምሮና የግብረገብ ኃይሎችን ማዘጋጀት ነው። ይህ ለዘላለም ሕይወት ጸንቶ የሚኖር ትምህርት ነው። --COL 330 (1900). {1MCP 360.2}1MCPAmh 294.5

  ሁሉም ኃይሎች ማደግ እስከሚችሉበት ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርሱ።--በባትል ክሪክ ያለው ኮሌጅ በአገራችን ካለው ከማንኛውም መሰል ተቋም ይልቅ በእውቀትና በግብረገብ እድገት ከፍ ካለ መስፈርት ላይ እንዲደርስ የእግዚአብሔር እቅድ ነው። ወጣቶች በሳይንስ ከፍተኛ ስኬትን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር እውቀት እርሱን የማስከበር እውቀት እንዲኖራቸው፤ የተስተካከለ ባሕርይ በማጎልበት በዚህ ዓለም ጠቃሚዎች ለመሆን ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋጁና ለዘላለማዊው ሕይወት የግብረገብ ገጣሚነትን እንዲያገኙ የአካል፣ የአእምሮና የግብረገብ ኃይሎችን የማሳደግን አስፈላጊነት መማር አለባቸው።--4T 425 (1880). {1MCP 360.3}1MCPAmh 295.1

  የሁሉም ዓይነት ሳይንሶች እውቀት ኃይል ነው።--በመካከላችን የተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች አስፈላጊ የሆኑ ፍላጎቶችን የሚያካትቱ ስለሆኑ ከፍተኛ ሀላፊነት ያላቸው ናቸው። በተለየ ሁኔታ ትምህርት ቤቶቻችን ለመላእክትና ለሰዎች የሚታዩ አስደናቂ ትዕይንቶች ናቸው። የሁሉም ዓይነት ሳይንሶች እውቀት ኃይል ስለሆነ የምድር ታሪክን የመዝጊያ ትዕይንት ለሚቀድመው ሥራ ለመዘጋጀት በትምህርት ቤቶቻችን ከፍተኛ ሳይንስ እንዲሰጥ የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው። ለሥራው በሰለጠኑ ወኪሎች አማካይነት እውነት ወደ ምድር እጅግ ሩቅ ቦታዎች መሄድ አለበት። ነገር ግን የሳይንስ እውቀት ኃይል ሆኖ ሳለ ኢየሱስ ለዓለም ለመስጠት በአካል የመጣበት እውቀት የወንጌል እውቀት ነበር። የእውነት ብርሃን ብሩህ ጮራዎቹን እስከ ምድር ዳር ድረስ ሊያበራ ስለነበር የእግዚአብሔርን መልእክት መቀበል ወይም አለመቀበል የነፍሳትን ዘላለማዊ መዳረሻ አካትቶ ነበር።--RH, Dec 1, 1891. (FE 186.) {1MCP 360.4}1MCPAmh 295.2

  ወጣቶች አሳቢዎች እንዲሆኑ።--በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው እያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር ከፈጣሪ ኃይል ጋር ተመሳሳይ የሆነ ኃይል--ግለሰባዊነት፣ የማሰብና የማድረግ ኃይል ተሰጥቶታል። ይህን ኃይል ያጎለበቱ ሰዎች ኃላፊነትን የሚሸከሙ፣ በድርጅት ውስጥ መሪዎች የሚሆኑ እና በባሕርይ ላይ ተጽእኖ የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው። ይህን ኃይል ማሳደግ፣ ወጣቶች ዝም ብለው የሌሎች ሰዎችን ሀሳብ የሚያንጸባርቁ ሳይሆኑ አሳቢዎች እንዲሆኑ ማድረግ የእውነተኛ ትምህርት ሥራ ነው። {1MCP 361.1}1MCPAmh 295.3

  ጥናታቸውን ሰዎች ባሉት ወይም በጻፉት ላይ ከመወሰን ይልቅ ተማሪዎች ወደ እውነት ምንጮች፣ በተፈጥሮና በመገለጥ ውስጥ ወዳሉት ሰፊ የምርምር መስኮች ይመሩ። የተግባርና የመዳረሻ ታላላቅ እውነቶች ላይ ካሰላሰሉ አእምሮ ይሰፋል፣ ይበረታልም። የትምህርት ተቋማት የተማሩ ልፍስፍስ ሰዎችን ከማምረት ይልቅ ለማሰብና ለማድረግ ብርቱ የሆኑ፣ የሁኔታዎች ባሪያዎች ሳይሆን ጌታ የሆኑ፣ የአእምሮ ስፋት፣ የጠራ አስተሳሰብ እና ላመኑበት ነገር ድፍረት ያላቸውን ሰዎች ያመርታሉ። --Ed 17, 18 (1903). {1MCP 361.2}1MCPAmh 295.4

  እውነተኛ ትምህርት ባህርይን ያጎለብታል።--ወጣቶችን ማስተማርና ማሰልጠን አስፈላጊና የከበረ ሥራ ነው። የዚህ ትምህርትና ስልጠና ትልቁ ዓላማ መሆን ያለበት ግለሰቡ የአሁኑን ሕይወት ተግባራት በትክክል ለማከናወንና በመጨረሻ ወደ ፊት ሊመጣ ወዳለው ዘላለማዊ ሕይወት ለመግባት ገጣሚ እንዲሆን ተገቢ የሆነ የባህርይ ግንባታ ማግኘት ነው። ሥራው የተሰራበትን ሁኔታ ዘላለም ይገልጠዋል። አገልጋዮችና መምህራን ስለ ኃላፊነታቸው ሙሉ መረዳት ቢኖራቸው ኖሮ ዛሬ በዓለም ላይ ነገሮችን በተለየ ሁኔታ ማየት እንችል ነበር። ነገር ግን በአመለካከቶቻቸውና በተግባሮቻቸው እጅግ ጠባብ ናቸው። የሥራቸውን አስፈላጊነትና የሥራቸውን ውጤት ጥቅም አይገነዘቡም። --4T 418 (1880). {1MCP 361.3}1MCPAmh 296.1

  ትልቁ ዋጋ ባህርይን ለመገንባት ነው።-- ተማሪዎች [በአቮንዳል ትምህርት ቤት ያሉ] በትጋትና በታማኝነት ይሰራሉ። የነርቭ ብርታትን፣ የጡንቻ ጥንካሬንና እንቅስቃሴን እያገኙ ነው። ይህ ትምህርት ከትምህርት ቤቶቻችን ብርቱና ብቃት ያላቸውን ወጣቶች፣ ወደ አንድ አቅጣጫ ያጋደለ ትምህርት የሌላቸውን፣ ነገር ግን ሁሉን ያካተተ የአካል፣ የአእምሮና የግብረገብ ስልጠና ያላቸውን የሚያመርት ተገቢ የሆነ ትምህርት ነው። {1MCP 362.1}1MCPAmh 296.2

  ባህርይን የሚገነቡ ሰዎች ትምህርት ትልቅ ዋጋ እንዲኖረው የሚያደርገውን መሰረት መጣልን መርሳት የለባቸውም። ይህ ራስን መስዋዕት ማድረግን ይጠይቃል፣ ነገር ግን መደረግ አለበት። አካላዊው ስልጠና በተገቢ ሁኔታ ከተሰጠ ለአእምሮ ሥራ ያዘጋጃል። ነገር ግን አንዱ ብቻውን ከሆነ ምን ጊዜም ቢሆን ጉድለት ያለበትን ሰው ይፈጥራል። {1MCP 362.2}1MCPAmh 296.3

  አካላዊ ሥራ ከአእምሮ ጥረት ጋር ተደባልቆ አእምሮንና ሞራሎችን ጤናማ በሆነ ሁኔታ ስለሚጠብቅ እጅግ የተሻለ ሥራ ይሰራል። ከዚህ ስልጠና የተነሣ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቶቻችን ለተግባራዊ ሕይወት እውቀት ያላቸው፣ የአእምሮ ችሎታዎቻቸውን ለተሻለ ነገር መጠቀም የሚችሉ ሆነው ይወጣሉ። ለተማሪዎቻችን ፍትሃዊ መሆን ከፈለግን የአካልና የአእምሮ እንቅስቃሴዎች መዋሃድ አለባቸው። በዚህ ዕቅድ ተማሪዎች በሚሰሩበት ጊዜ የሚያጋጥም አለመመቸት ቢኖርም እዚህ [አውስትራሊያ] ሙሉ እርካታ በሚሰጥ ሁኔታ ስንሰራ ቆይተናል። --SpT Series A, No. 4, p 16, Aug 27, 1895. (TM 241.) {1MCP 362.3}1MCPAmh 296.4

  ብዙዎች እውነተኛ መርሆዎችን መረዳት ያቅታቸዋል።--ብዙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመጨረስ እጅግ ስለሚጣደፉ በሚያደርጉት በማንኛውም ነገር የተሟሉ አይደሉም። መርህን ተከትለው ለመስራት በቂ ድፍረትና ራስን የመቆጣጠር አቅም ያላቸው ጥቂቶች ናቸው። አብዛኞቹ ተማሪዎች የእውነተኛ ትምህርትን ዓላማ መረዳት ስለማይችሉ ይህን ዓላማ ወደማሳካት በሚመራው መንገድ መሄድ ያቅታቸዋል። ለሕይወት ደስታና ስኬት እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ትምህርት ችላ ይሉና በሂሳብ ወይም በቋንቋዎች ጥናት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። ከከርሰ ምድር ተመራማሪ ጋር የመሬትን ጥልቅ ቦታዎች ማሰስ የሚችሉ ወይም ከህዋ ተመራማሪ ጋር ሰማይን ማካለል የሚችሉ ብዙዎች ስለ ራሳቸው አካል አስደናቂ አሰራር ለማወቅ ትንሽ ፍላጎት እንኳን የላቸውም። ሌሎቹ ደግሞ በሰው አካል ውስጥ ስንት አጥንቶች እንዳሉ መንገርና እያንዳንዱን የአካል ክፍል በትክክል መግለጽ ይችላሉ፣ ነገር ግን ሕይወት እርግጠኛና በማይለያዩ ሕጎች ቁጥጥር ሥር ከመሆን ይልቅ በጭፍን ዕድል የሚመራ ይመስል ስለ ጤና ሕጎችና ስለ በሽታ ፈውሶች እውቀት የሌላቸው ናቸው። --ST, June 29, 1892. (FE 71, 72.) {1MCP 362.4}1MCPAmh 297.1

  ትምህርት የጭንቅላት ብቻ አይደለም።--ስለ ተግባራዊ ሥራ እውቀት ሳያገኙ የመጽሐፍት እውቀትን ብቻ የሚያካብቱ ተማሪዎች ሚዛናዊ ትምህርት እንዳገኙ መናገር አይችሉም። በተለያየ መስመር ባሉ ሥራዎች ላይ ሊውል የሚችለው ጉልበት ችላ ተብሏል። ትምህርት አእምሮን መጠቀምን ብቻ አያካትትም። አካላዊ ሥራ ለእያንዳንዱ ወጣት አስፈላጊ የሆነ የሥልጠና አካል ነው። ተማሪ እንዴት ጠቃሚ በሆነ ሥራ ላይ እንደሚሰማራ ካልተማረ የትምህርት አስፈላጊ የሆነ ክፍል ይጎድላል ማለት ነው።--CT 307, 308 (1913). {1MCP 363.1}1MCPAmh 297.2

  አካልና አእምሮ በእኩል መስራት አለባቸው።--አእምሮን እጅግ ከፍ ላለ አገልግሎት የማሰልጠንን አስፈላጊነት በተመለከተ ብዙ ተብሏል። አእምሮ እጅግ ከፍተኛ የሆኑ ኃይሎቹን ሥራ ላይ እንዲያውል ከሰለጠነ አንዳንድ ጊዜ ለተሟላ የሰው እድገት የአካልና የግብረገብ ተፈጥሮን ያበረታል ወደሚል አመለካከት መርቶአል። ይህ ውሸት መሆኑን ጊዜና ልምድ አረጋግጠዋል። እግዚአብሔር የሰጣቸውን አስደናቂ አካላቸውን በተገቢ ሁኔታ ለመጠቀም በምንም መንገድ ብቁ ያልሆኑ ወንዶችና ሴቶች ከኮሌጅ ተመርቀው ሲወጡ ተመልክተናል። መላው አካል የተዘጋጀው ለተግባር እንጂ ተግባር ለመፍታት አይደለም። {1MCP 363.2}1MCPAmh 297.3

  የአካል ኃይሎች ከአእምሮ ኃይሎች ጋር እኩል በሥራ ካልተጠመዱ በአእምሮ ላይ ከመጠን ያለፈ ጫና ይመጣበታል። እያንዳንዱ የሰብአዊ አካል ማሽን የተመደበለትን ሥራ ካልሰራ በቀር የአእምሮ ኃይሎች ለምንም ያህል ጊዜ ቢሆን ችሎታቸው እስከሚፈቅደው ከፍተኛ ደረጃ ድረስ ጥቅም ላይ ሊውሉ አይችሉም። ተፈጥሮአዊ ኃይሎች በተፈጥሮ ሕጎች መገዛት አለባቸው፣ የአካል ክፍሎችም በተጣጣመ መልኩና እነዚህ ሕጎች በሚፈቅዱት መሰረት ለመስራት መሰልጠን አለባቸው። በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ያሉ መምህራን ይህን ኃላፊነት ገለል ሳያደርጉ ከእነዚህ ዝርዝሮች አንዱንም ቢሆን ችላ ማለት አይችሉም። ተማሪዎች ደማቅ ታይታ እንዲፈጽሙ የአእምሮ እውቀት በማግኘት ረገድ ከፍ ያለ ዓለማዊ መስፈርትን እንዲሹ ኩራት ሊመራቸው ይችላል፤ ነገር ግን ወንዶችንና ሴቶችን በተግባራዊ ሕይወት ውስጥ ለእያንዳንዱ አንገብጋቢ ነገር ገጣሚ ለማድረግ አስፈላጊ ወደሆኑ ጠንካራ ነገሮች ሲመጣ የዚህ ዓይነቶቹ ተማሪዎች ለሕይወት ስኬት በከፊል ብቻ የተዘጋጁ ናቸው። በማንኛውም የሥራ ዘርፍ ቢሰማሩ ብዙ ጊዜ ጉድለት ያለበት ትምህርታቸው ወደ ውድቀት ይመራቸዋል።--5T 522 (1889). {1MCP 364.1}1MCPAmh 298.1

  የሕይወት ሸክምን ለማምለጥ አይደለም።--ትምህርት የሕይወትን የማይመቹ ተግባሮችንና ከባድ ሸክሞችን እንዴት ማምለጥ እንደሚችሉ ለማስተማር እንዳልሆነ በሚገልጽ ሀሳብ ወጣቶች ይገረሙ፤ ዓላማው የተሻሉ ዘዴዎችንና ከፍ ያሉ ዓላማዎችን በማስተማር ሥራውን ለማቅለል ነው። የሕይወት እውነተኛው ዓላማ ለራሳቸው ማግኘት የሚችሉትን ከፍተኛ የሆነ ጥቅም ለራሳቸው ማግኘት ሳይሆን በዓለም ውስጥ ባለው ሥራ ላይ ድርሻቸውን በመወጣትና ደካማ ወይም መሃይም ለሆኑት የእርዳታ እጃቸውን በመዘርጋት አዳኛቸውን ማክበር እንደሆነ አስተምሩአቸው።--Ed 221, 222 (1903). {1MCP 364.2}1MCPAmh 298.2

  የተጣጣመ እድገት ይፈለጋል።--ራስን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ልንማረው የምንችለው እጅግ ጠቃሚ ትምህርት ነው። የአእምሮ ሥራ ሰርተን ወይም የአካል እንቅስቃሴ አድርገን እዚያው መቆም የለብንም፤ ሰብአዊ ፋብሪካን (ማሽንን) የሚሰሩ የተለያዩ ክፍሎችን--አእምሮን፣ አጥንትን፣ ጡንቻን፣ ራስንና ልብን-- በደንብ መጠቀም አለብን። --YI, Apr 7, 1898. (SD 171). {1MCP 364.3}1MCPAmh 298.3

  አለማወቅ መንፈሳዊነትን አይጨምርም።--ወጣቶች ለሌሎች ለማስረዳት ስለሚሞክሩአቸው ጠቃሚ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች እውቀት ሳይኖራቸው መጽሐፍ ቅዱስን የማብራራትና በትንቢቶች ላይ ገለጻ የመስጠት ሥራ ውስጥ መግባት የለባቸውም። በጥሩ ትምህርት ቤት የመማር እድል አግኝተው ቢሆን እንኳን በተለመዱ የትምህርት ዘርፎች ላይ ጉድለት ሊኖራቸው ስለሚችል ሊያደርጉ የሚችሉትን መልካም ነገር ማድረግ ሊያቅታቸው ይችላል። አለማወቅ የማንኛውንም የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ባይ ትህትና ወይም መንፈሳዊነት አይጨምርም። የትምህርት እውቀት ባለው ክርስቲያን የመለኮታዊ ቃል እውነቶች በደንብ ሊደነቁ ይችላሉ። ክርስቶስ ምሁራዊ በሆነ ሁኔታ በሚያገለግሉት ሊከበር ይችላል። የትምህርት ትልቁ ዓላማ እግዚአብሔር የሰጠንን ኃይሎች የመጽሐፍ ቅዱስን ኃይማኖት በደንብ በሚወክሉበትና የእግዚአብሔርን ክብር በሚያስተዋውቁበት ሁኔታ እንድንጠቀም ማስቻል ነው። --3T 160 (1872). {1MCP 364.4}1MCPAmh 298.4

  ትምህርት ብርቱ ጥረቶችን ይጠይቃል።--ተማሪዎች እንዲያስቡና እውነቶችን ለራሳቸው እንዲረዱ መምህራን ሊመሩአቸው ይገባል። የመምህር ማብራራት ወይም የተማሪዎች ማመን በቂ አይደለም፤ ጥያቄ መቀስቀስ አለበት፣ ተማሪውም የእውነትን ጉልበት እያየ ለመሆኑ ማረጋገጫ በመስጠትና በሥራ ላይ በማዋል እውነትን በራሱ ቋንቋ ወደ መግለጽ መሳብ አለበት። በብርቱ ጥረት ወሳኝ የሆኑ እውነቶች በአእምሮ ውስጥ መቀረጽ አለባቸው። ይህ አዝጋሚ ሂደት ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን አስፈላጊ በሆኑ ርዕሶች ላይ ተገቢ የሆነ ትኩረት ሳይሰጡ በችኮላ ከመግባት ይልቅ የበለጠ ዋጋ አለው። የእግዚአብሔር ተቋማት የእርሱ ተወካዮች ስለሆኑ ከዓለም ተቋማት ልቀው እንዲገኙ ይጠብቅባቸዋል። ከእግዚአብሔር ጋር በትክክል የተገናኙ ሰዎች በመርከቡ መሪ ላይ ከሰብአዊ ወኪል የሚበልጥ ቆሞ እንዳለ ለዓለም ያሳያሉ።--6T 154 (1900). {1MCP 365.1}1MCPAmh 299.1

  በደንብ የሚታወቁ ምልክቶችን ማቆም።--ወጣቶች በአስቸኳይ ጊዜያቶች ሊመሩባቸው የሚችሉባቸውን በደንብ የሚታወቁ ምልክቶች ያቁሙ። የሚሰሩና በደንብ የጎለበቱ የአካል ኃይሎችንና የጠራ፣ ጠንካራና የሚሰራ ተግባራዊ አእምሮ የሚሻ ችግር ሲመጣ፣ እያንዳንዱ የእጅ ንካት ማሳየት ያለበት ከባድ ሥራ ሊሰራ ባለበትና ግራ መጋባቶችን ከእግዚአብሔር ጥበብ በመሻት ብቻ መጋፈጥ በሚቻልበት ጊዜ፣ ችግሮችን ተግቶ በመስራት ማሸነፍን የተማሩ ወጣቶች ለሰራተኞች ለሚቀርበው ጥሪ ‹‹እነሆኝ፣ እኔን ላክ›› በማለት ምላሽ ይሰጣሉ። የወንድና ሴት ወጣቶች ልብ እንደ መስታወት የጠራ ይሁን። አስተሳሰቦቻቸው ከንቱ አይሁኑ፣ ነገር ግን በመልካም ተግባርና በቅድስና ይቀደስ። ከዚህ ሌላ መሆን አይጠበቅባቸውም። ከአስተሳሰብ ንጽህና ጋር በመንፈስ ቅድስና ሕይወታቸው ሊሞረድ፣ ከፍ ሊልና ሊከብር ይችላል። --SpT Series B, No. 1, pp 31, 32, July, 1900. {1MCP 365.2}1MCPAmh 299.2

  ትክክለኛ የሆኑ ልማዶችን መመስረት አስፈላጊ ነው።--ለሕይወት ሥራ በሚያቅዳቸው ዕቅዶቹ ሁሉ ከፍ አድርጎ ማለም የእያንዳንዱ ወጣት የማይናወጥ ዓላማ መሆን አለበት። ሁሉንም ነገሮች ስታስተዳድር የእግዚአብሔር ቃል የሚሰጥህን መስፈርት እንዳለ ተጠቀም። ይህ የክርስቲያን አዎንታዊ ተግባር ስለሆነ አዎንታዊ ደስታውም መሆን አለበት። ክርስቶስ የገዛህ ንብረት ስለሆንክ ለራስህ አክብሮትን አሳድግ። {1MCP 366.1}1MCPAmh 300.1

  ትክክለኛ የሆኑ ልማዶችን በመመስረት ሂደት የሚገኝ ስኬት፣ በከበረውና ጽድቅ በሆነው ነገር እድገት ማሳየት፣ ሁሉም ዋጋ የሚሰጡት ተጽእኖ እንዲኖርህ ያደርጋል። ከራስህ ሌላ ለሆነ ነገር ኑር። {1MCP 366.2}1MCPAmh 300.2

  አንድን ነገር እንድታደርግ የሚያነሳሱህ ምክንያቶች ንጹህና ከራስ ወዳድነት የጸዱ ከሆኑ፣ ሁል ጊዜ የሆነ ሰው ማድረግ ያለበትን ሥራ እየፈለግክ ከሆነ፣ በትህትና ለማዳመጥና የገርነት ሥራዎችን ለመስራት ሁል ጊዜ ንቁ ከሆንክ፣ ሳታስበው የራስህን ሀውልት እየገነባህ ነው። ሁሉም ልጆችና ወጣቶች እንዲሰሩት እግዚአብሔር እየጠራ ያለው ሥራ ይህ ነው። --SpT Series B, No. 1, p 32, July, 1900. {1MCP 366.3}1MCPAmh 300.3

  ራስን መቻል የትምህርት አስፈላጊው ክፍል።--ብዙ ተማሪዎች በመማር ራሳቸውን ለመቻል እጅግ አስፈላጊ የሆነ ስልጠናን ያገኛሉ። ወጣት ወንዶችና ሴቶች ዕዳ ውስጥ ከመግባት ወይም በወላጆቻቸው ራስን መካድ ላይ ከመደገፍ ይልቅ በራሳቸው ይደገፉ። በዚህ ሁኔታ የገንዘብን፣ የጊዜንና የመልካም አጋጣሚዎችን ዋጋ ስለሚማሩ የስራ ፈትነትንና የአባካኝነትን ልማዶች እንዲፈጽሙ ለሚመጣው ፈተና ተጋላጭነታቸው እጅግ አነስተኛ ይሆናል። ቁጠባ፣ ተግቶ መስራት፣ ራስን መካድ፣ ተግባራዊ የሆነ የንግድ አያያዝ፣ እና የዓላማ ጽናት በደንብ ሥራ ላይ ከዋሉ ለሕይወት ጦርነት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መሳሪያዎች አካል ይሆናሉ። ተማሪዎች የተማሩት ራስን የመርዳት ትምህርት ብዙ ትምህርት ቤቶች ከተቸገሩበትና ጠቃሚነታቸውን ሽባ ለማድረግ ብዙ አስተዋጽኦ ካደረገው የዕዳ ሸክም የትምህርት ተቋሞችን ወደ ማዳን ይመራል። --Ed 221 (1903). {1MCP 366.4}1MCPAmh 300.4

  ትምህርት ማህበራዊ አቋምን ይቀርጻል።--በመላው ዓለም ሕብረተሰብ በትርምስምስ ውስጥ ስለሆነ መሰረታዊ የሆነ ለውጥ አስፈላጊ ነው። ለወጣቶች የሚሰጥ ትምህርት መላውን ማህበራዊ አቋም መቅረጽ አለበት።--MH 406 (1905). {1MCP 367.1}1MCPAmh 300.5

  ግብርናን የሚያስተምር ትምህርት ቤት አስፈላጊነት።--ተቀጥሮ የማይሰራውን ሰፊ ሕዝብ በማሰማራት ትምህርት ቤቶቻችን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ሊረዱ ይችላሉ። በሺሆች የሚቆጠሩ ረዳት የለሽና እየተራቡ ያሉ ፍጡራን፣ በየቀኑ የወንጀለኞች ቁጥር እየጨመረ እንዲሄድ እያደረጉ ያሉ፣ መሬትን በማረስ ሥራ ጥበብና ትጋት ያለበትን ሥራ እንዲሰሩ ቢመሩ ኖሮ ደስተኛ በሆነ፣ ጤናማና ከጥገኝነት ነጻ በሆነ ሕይወት ራሳቸውን መርዳት ይችሉ ነበር። --Ed 220 (1903). {1MCP 367.2}1MCPAmh 300.6

  ትምህርት በሕይወት ዘመን ሁሉ ይቀጥላል።--በክርስቶስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በፍጹም ተመርቀው አያውቁም። በተማሪዎቹ መካከል ሽማግሌዎችና ወጣቶች አሉ። የመለኮታዊ መምህርን መመሪያዎች የሚያዳምጡ ሰዎች በጥበብ፣ በጸባይ መታረምና በነፍስ ክቡርነት ሁል ጊዜ እየጨመሩ በመሄድ ለዘላለም መሻሻል ወደሚቀጥልበት ከፍተኛ ትምህርት ቤት ለመግባት ዝግጁ ይሆናሉ።--CT 51 (1913). {1MCP 367.3}1MCPAmh 301.1

  እውነተኛ ምኞት።--ውድ ወጣቶች ሆይ፣ የሕይወታችሁ እቅድና ዓላማ ምንድን ነው? ምኞታችሁ በዓለም ላይ ዝናና ስልጣን የምታገኙበትን ትምህርት ለማግኘት ነውን? አንድ ቀን በእውቀት ታላቅነት ቁንጮ ላይ ለመቆም፣ በመማክርትና በሕግ አውጪ ጉባኤዎች በመቀመጥ ለአገር ሕጎችን ለማውጣት የምታስባቸው ለመግለጽ የማትደፍራቸው ሀሳቦች አሉን? በእነዚህ ምኞቶች ውስጥ ምንም ስህተት የለም። እያንዳንዳችሁ መድረስ የምትፈልጉበትን ማለም ትችላላችሁ። ዝቅተኛ በሆነ ስኬት መርካት የለባችሁም። ዓላማችሁ ከፍ ያለ ይሁንና ወደ መስፈርቱ ለመድረስ ማድረግ የሚገባችሁን ሁሉ አድርጉ።-- RH, Aug 19, 1884. (FE 82.) {1MCP 367.4}1MCPAmh 301.2

  እጅግ አስፈላጊ የሆነ እውቀት።--ወጣቶች እውቀትን ለማግኘት መሄድ በሚችሉት ፍጥነትና መጓዝ እስከሚችሉት ርቀት ድረስ ወደ ፊት መቀጠል አለባቸው…። ሲማሩ እውቀታቸውን ያጋሩ። አእምሮአቸው ሥነ-ሥርዓትንና ኃይልን ማግኘት የሚችለው እንዲህ ሲሆን ነው። የትምህርታቸውን ዋጋ የሚወስነው እውቀታቸውን የሚጠቀሙበት ሁኔታ ነው። የተገኘውን እውቀት ለሌሎች ለማጋራት ጥረት ሳይደረግ በትምህርት ላይ ረዥም ጊዜ ማጥፋት ብዙ ጊዜ ትክክለኛ የሆነ እድገት ከማምጣት ይልቅ ማነቆ ይሆናል። በቤት ውስጥም ሆነ በትምህርት ቤት የተማሪው ጥረት መሆን ያለበት እንዴት እንደሚያጠና እና ያገኘውን እውቀት እንዴት ለሌሎች እንደሚያካፍል ለመማር መሆን አለበት። የተጠራበት ጥሪ ምንም ቢሆን፣ የተጠራው በሕይወት እስካለ ድረስ ተማሪና መምህር ለመሆን ነው። -- MH 402 (1905). {1MCP 368.1}1MCPAmh 301.3

  ዛሬ ወጣቶቻችን ማግኘት ያለባቸው እጅግ አስፈላጊ ትምህርት፣ በላይ ባለው ትምህርት ቤት ላሉ ከፍተኛ ክፍሎች ገጣሚ የሚያደርጋቸውና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለዓለም እንዴት እንደሚገልጡ የሚያስተምራቸው ትምህርት ነው። --RH, Oct 24, 1907. (FE 512.) {1MCP 368.2}1MCPAmh 301.4

  አስፈላጊ የሆነው ትምህርት እግዚአብሔርንና እርሱ የላከውን ማወቅ ነው። {1MCP 368.3}1MCPAmh 302.1

  እያንዳንዱ ልጅና እያንዳንዱ ወጣት ስለ ራሱ እውቀት ሊኖረው ይገባል። እግዚአብሔር የሰጠውን አካላዊ መኖሪያና ይህን አካላዊ መኖሪያ በጤንነት ሊያቆዩት የሚችሉትን ሕጎች መረዳት አለበት። ሁሉም በተለመዱ የትምህርት ዘርፎች ሙሉ በሙሉ መመስረት አለባቸው። ለእያንዳንዱ ቀን የሕይወት ተግባሮች ገጣሚ የሆኑ፣ በተግባር የሚገለጥ ችሎታ ያላቸው ወንዶችና ሴቶች የሚያደርጋቸው የኢንዱስትሪ ስልጠና ሊኖራቸው ይገባል። በዚህ ላይ በሚስዮናዊነት የተለያዩ መስመሮች ስልጠናና ተግባራዊ ልምምድ መጨመር አለበት። --MH 402 (1905). {1MCP 368.4}1MCPAmh 302.2

  የትኛው ‘የዩኒቨርሲቲ ትምህርት’ ከዚህ ጋር ሊስተካከል ይችላል?”--“ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው።…” ስለዚህ ዓለም ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው ይገባል።……ለዚህ ሥራ በሺሆች የሚቆጠሩ ወጣቶች ራሳቸውን መስጠት አለባቸው።…እያንዳንዱ ክርስቲያን መምህር…በሥሩ ያሉ ወጣቶች በዚህ ሥራ እንዲሳተፉ ለማዘጋጀት ያደፋፍራቸው፣ ይርዳቸውም። {1MCP 368.5}1MCPAmh 302.3

  ወጣቶች በጣም ትልቅ ጥቅም ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርግ የሥራ መስመር የለም።…ከመላእክት ጋር አብራው ሰራተኞች ናቸው፤ መላእክት ተልዕኮአቸውን የሚፈጽሙባቸው ሰብአዊ ወኪሎች ናቸው። መላእክት በድምፆቻቸው እየተናገሩ በእጆቻቸው ይሰራሉ። ሰብአዊ ሰራተኞች ከሰማያዊ ወኪሎች ጋር ሲተባበሩ ትምህርታቸውና ልምዳቸው ጥቅም አለው። እንደ መማሪያ መንገድ ከዚህ ጋር የሚስተካከል ምን ‹‹የዩኒቨርሲቲ ኮርስ›› ነው? --Ed 270, 271 (1903). {1MCP 369.1}1MCPAmh 302.4

  እውቀትን ማጋራት አስፈላጊ ነው። ትምህርታቸው የተሟላ እንዲሆን ተማሪዎች ሚስዮናዊ ሥራ ለመስራት፣ በዙሪያቸው ባለው ማህበረሰብ ውስጥ ካሉ ቤተሰቦች መንፈሳዊ ፍላጎቶች ጋር ለመተዋወቅ ጊዜ መስጠት አለባቸው። ያገኙትን እውቀት ለመጠቀም ጊዜ በማያገኙላቸው ትምህርቶች መጫን የለባቸውም። በስህተት ውስጥ ካሉት ጋር በመተዋወቅና እነርሱን ወደ እውነት በመውሰድ ልባዊ የሆነ ሚስዮናዊ ጥረት እንዲያደርጉ መደፋፈር አለባቸው። ራስን ዝቅ በማድረግ፣ ከክርስቶስ ጥበብን በመሻት፣ በመጸለይና ለጸሎት በመንቃት፣ ሕይወታቸውን ያበለጸገውን እውቀት ለሌሎች መስጠት ይችላሉ። --CT 545, 546 (1913). {1MCP 369.2}1MCPAmh 302.5

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents