Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 2—ክርስቲያንና የሥነ-ልቦና ትምህርት

  የአእምሮ ሕጎች የተሰጡት በእግዚአብሔር ነው።--አእምሮን የፈጠረውና ሕጎቹን የሰጠው እርሱ ከእነርሱ ጋር በመስማማት ለእድገቱ የሚያስፈልገውን ነገር ሰጠ። . [ማስታወሻ፡-በመጽሐፍ ቅዱስና በእውነተኛ ሳይንስ መካከል ፍጹም መጣጣም አለ። የስነ ልቦና ትምህርት የአእምሮና የሰብአዊ ባሕርይ ሳይንስ ጥናት ነው።]—Education, 41 (1903).1MCPAmh 11.1

  በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሥነ-ልቦና ትምህርት እውነተኛ መርሆዎች።--የሥነ-ልቦና ትምህርት እውነተኛ መርሆዎች በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ይገኛሉ። ሰው የራሱን ዋጋ አያውቀውም። የእምነቱ ጀማሪና ፈጻሚ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ ስለማይመለከት የሚያደርገውን ነገር የሚያደርገው ባልተለወጠ በተፈጥሮ ባህርይ ነው። ወደ ኢየሱስ የሚመጣ፣ በእርሱ የሚያምንና እርሱን ምሳሌው የሚያደርግ፣ ‹‹ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣን ሰጣቸው›› የሚሉትን ቃላት ትርጉም ይገነዘባሉ።...በእውነተኛ መለወጥ ልምምድ ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች፣ ብርቱ በሆነ መረዳት፣ መዳናቸውን በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ለመፈጸም ለእግዚአብሔር ያላቸውን ኃላፊነት፣ ከኃጢአት ለምጽ መዳናቸውን ፍጹም ለማድረግ ያላቸውን ኃላፊነት ይገነዘባሉ። እንደዚህ ዓይነት ልምምድ በትህትናና በመታመን በእግዚአብሔር ላይ ወደ መደገፍ ይመራቸዋል።—Manuscript 121, 1902. (My Life Today, 176.)1MCPAmh 11.2

  ለእግዚአብሔር የተሰጠ አእምሮ በተጣጣመ ሁኔታ ያድጋል።--ሰዎች ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ከሰጡ እርሱ እንዳሉ ይቀበላቸውና አስተምሮ ለአገልግሎቱ ያዘጋጃቸዋል። የእግዚአብሔር መንፈስ በነፍስ ውስጥ ተቀባይነት ካገኘ ሁሉንም የነፍስን ኃይሎች ያነቃቃቸዋል። በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ያለ አንዳች ቁጥብነት ለእግዚአብሔር የተሰጠ አእምሮ በተጣጣመ ሁኔታ ስለሚያድግ እግዚአብሔር የሚፈልጋቸውን ነገሮች ለመገንዘብና ለመፈጸም ብርታት ያገኛል። ደካማና የሚዋዥቅ ባህርይ ወደ ብርታትና ወደ ጽናት ይለወጣል። ቀጣይነት ያለው መሰጠት በኢየሱስና በደቀ መዛሙርቱ መካከል የቀረበ ግንኙነት ስለሚፈጥር ክርስቲያን በባህርዩ እንደ ጌታው ይሆናል። ጥርት ያሉና ሰፊ አመለካከቶች ይኖሩታል። ነገሮችን ዘልቆ የሚረዳ፣ ፍርድ አሰጣጡም ሚዛናዊ የሆነ ይሆናል። በጽድቅ ፀሐይ ሕይወት ሰጭ ኃይል ስለተነቃቃ ለእግዚአብሔር ክብር ብዙ ፍሬ ማፍራት ይችላል።—Gospel Workers, 285, 286 (1915).1MCPAmh 11.3

  የንጹህ ክርስቲያን ሕይወት ሳይንስ።--ንጹህ፣ የተሟላ፣ የማይለዋወጥ ክርስቲያናዊ የሕይወት ሳይንስ የሚገኘው የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት ነው። ይህ ማንኛውም ምድራዊ ፍጡር ሊያገኘው የሚችል እጅግ ከፍተኛ ትምህርት ነው። በትምህርት ቤታችን ያሉ ተማሪዎች በእድገት መሰላል ላይ ለመውጣትና ክርስቲያናዊ መልካም ምግባር በመለማመድ ንጹህ ሀሳቦችን፣ የጸዳ አእምሮንና ልብን ይዘው መውጣት እንዲችሉ መማር ያለባቸው ትምህርቶች እነዚህ ናቸው። ትምህርት ቤቶቻችን ከጤና ማሰልጠኛ ተቋሞቻችን ጋርና የጤና ማሰልጠኛ ተቋሞቻችን ከትምህርት ቤቶቻችን ጋር የተገናኙ እንዲሆኑ የምንመኘው ከዚህ የተነሣ ነው። እነዚህ ተቋሞች በአዲስ ኪዳንና በብሉይ ኪዳን ውስጥ በተሰጠው የወንጌል ትህትና መመራት አለባቸው።—Manuscript 86, 1905.1MCPAmh 12.1

  በሰላም ከባቢ አየር መከበብ።--በእግዚአብሔር ሥልጠና ሥር ያሉ ሁሉ ከራሳቸው ልብ ጋር፣ ከተፈጥሮ ጋርና ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት የጸጥታ ሰዓት ያስፈልጋቸዋል...። እርሱ ለልባችን ሲናገር በየግላችን መስማት አለብን። እያንዳንዱ ድምጽ ጸጥ ብሎ፣ በጸጥታ በፊቱ ስንጠብቅ የነፍስ ጸጥታ የእግዚአብሔር ድምጽ የበለጠውን እንዲጎላ ያደርገዋል። ‹‹ጸጥ በሉ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ እወቁ›› በማለት ያዘናል...። በሚጣደፍ ሕዝብና የሕይወት አድካሚ ሥራዎች በሚያስከትሉት ውጥረት መካከል በዚህ መልኩ የታደሰ ሰው በብርሃንና ሰላም ከባቢ አየር ይከበባል። አዲስ የአካልና የአእምሮ ብርታት ስጦታን ይቀበላል።—The Ministry of Healing, 58 (1905).1MCPAmh 12.2

  የክርስቶስ ኃይማኖት ውጤታማ የሆነ ፈውስ።--ሰይጣን የበሽታ ምንጭ ነው፤ ሀኪም ከእርሱ ሥራና ኃይል ጋር ጦርነት እየገጠመ ነው። የአእምሮ ሕመም በሁሉም ቦታ ይታያል...። ከሃዲዎች የአእምሮ መታወክን ለኃይማኖት በመስጠት [የቤት ችግሮች፣ የኃጢአት ጸጸት፣ እና ለዘላለም የሚነደው የገሃነም እሳት ፍርሃት አእምሮን ሚዛናዊ እንዳይሆን ስላደረገ] እነዚህን አሳዛኝ ሁኔታዎች እጅግ ተጠቅመውባቸዋል፤ ነገር ግን ይህ እነርሱ በየጊዜው ሊጋፈጡት የማይፈልጉት ግልጽ የሆነ ስምና ዝናን የማጥፋት ጽሁፍ ነው። የክርስቶስ ኃይማኖት፣ የአእምሮ መታወክ ሕመም መንስኤ ከመሆን እጅግ የራቀ ከመሆኑም በላይ፣ ፍቱን የነርቮች አረጋጊ ስለሆነ ለዚህ ችግር እጅግ ውጤታማ ከሆኑ ፈውሶች መካከል አንዱ ነው።—Testimonies for the Church 5:443, 444 (1885).1MCPAmh 12.3

  ወደ ሰላም ክልል መግባት።--ፈተናዎች ሲገጥሙአችሁ፣ ችግር፣ ግራ መጋባትና ጨለማ ነፍሳችሁን የከበበ ሲመስል፣ ባለፈው ጊዜ ብርሃን ወዳያችሁበት ወደዚያ ተመልከቱ። በክርስቶስ ፍቅርና በእርሱ ጥበቃ ሥር እረፉ...። ከአዳኙ ጋር ግንኙነት ስንፈጥር ወደ ሰላም ክልል እንገባለን።—The Ministry of Healing, 250 (1905).1MCPAmh 12.4

  አላስፈላጊ ስጋቶች ሁሉ ተወገዱ።--ሰዎች ወደ ዕለታዊ ሥራቸው ሲሄዱ፣ በጸሎት ላይ ሲሆኑ፣ ማታ ሲተኙና ጧት ሲነሱ፣ ሀብታም ሰው በቤተ መንግስቱ ሆኖ ዓለሙን ሲቀጭ፣ ወይም ደሃ ሰው የምግብ እጥረት ባለበት ጠረጴዛ ዙሪያ ልጆቹን ሲሰበስብ፣ እያንዳንዳቸው በሰማያዊ አባት በርኅራኄ ይታያሉ። እግዚአብሔር ሳያይ የሚፈስ እንባ የለም። እርሱ የማያየው ፈገግታ የለም። ይህን ሙሉ በሙሉ ብናምን ኖሮ አላስፈላጊ የሆኑ ስጋቶች ሁሉ ይወገዱ ነበር። ሕይወታችን አሁን እንደሆነው በተስፋ መቁረጥ አይሞላም ነበር፤ ሁሉም ነገር፣ ትልቅ ወይም ትንሽ ቢሆን፣ በችግሮቻችን ብዛት ግራ በማይጋባው ወይም ክብደታቸው በማያሸንፈው በእግዚአብሔር እጆች ይተዉ ነበር። ያኔ ለብዙዎች እንግዳ በሆነባቸው የነፍስ እረፍት እንደሰት ነበር።—Steps to Christ, 86 (1892).1MCPAmh 13.1

  ነፍስን ሥነ-ሥርዓትን በማስተማር መግራት።--ክርስቲያኖች ሆይ፣ ክርስቶስ በእኛ ተገልጦአልን? በቀላሉ የማይደክሙ ጤናማ አካሎችና ጠንካራ አእምሮዎች፣ ከራስ ባሻገር ወደ ስራውና ወደ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ውጤት የሚመለከቱ አእምሮዎች እንዲኖሩን መስራት አለብን። ይህ ሲሆን እንደ ጥሩ ወታደሮች ችግርን ለመቋቋም በጥሩ መንገድ ላይ ነን። ችግሮችን ማየት የሚችሉና ከእግዚአብሔር በሚመጣ ጥበብ በችግሩ ውስጥ ማለፍ የሚችሉ፣ ከባድ ከሆኑ ችግሮች ጋር ታግለው ማሸነፍ የሚችሉ፣ አእምሮዎችን እንፈልጋለን። ከችግሮች ሁሉ እጅግ ከባዱ ችግር ራስን መስቀል፣ በመንፈሳዊ ልምምዶቻችን ችግርን መሸከምና ነፍስን ጽኑ በሆነ ሥነ-ሥርዓት ማሰልጠን ነው። ይህ ምናልባት በመጀመሪያ የምንፈልገውን ምርጥ እርካታ ላያመጣ ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን ኋላ የሚመጣው ውጤት ሰላምና ደስታ ይሆናል።—Letter 43, 18991MCPAmh 13.2

  ክርስቶስ ብርታት ለመስጠትና ወደ ቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ ኃይል አለው።--ክርስቶስ ሰማይን ለሰው ሲከፍት ሳለ፣ እርሱ የሚሰጠው ሕይወት የሰውን ልብ ለሰማይ ክፍት ያደርገዋል። ኃጢአት ከእግዚአብሔር የሚለየን ብቻ ሳይሆን በሰብአዊ ነፍስ ውስጥ እርሱን የማወቅን ፍላጎትና ችሎታንም ያጠፋል። የክርስቶስ ተልእኮ ይህን ሁሉ የክፉ ሥራ ማጥፋት ነው። በኃጢአት ምክንያት ሽባ የሆኑ የነፍስ ኃይሎችን፣ የጨለመ አእምሮን፣ የተዛባ ፈቃድን፣ የማነቃቃትና ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ኃይል አለው። የዩኒቨርስን ሀብቶች ይከፍትልንና እነዚህን የተሰጡንን ሀብቶች ለይተን የማወቅና የራሳችን የማድረግ ኃይል ይሰጣል።—Education, 28, 29 (1903).1MCPAmh 13.3

  እግዚአብሔር ወይም ሰይጣን ይቆጣጠራል።--በቁርጠኝነት በእግዚአብሔር መንፈስ ቁጥጥር ሥር ያልሆነን እያንዳንዱን አእምሮ ሰይጣን ይቆጣጠረዋል።—Letter 57, 1895 (Testimonies to Ministers and Gospel Workers, 79).1MCPAmh 13.4

  እያንዳንዱ የምናፈቅረው ኃጢአት ባሕርይን ያዳክማል።--ለጊዜው የተንከባከብናቸው ኃጢአቶች በሂደት በቀላሉ ሊተዉ ይችላሉ በማለት ማንም ራሱን አያታልል። ይህ እንዲህ አይደለም። እያንዳንዱ የተንከባከብነው ኃጢአት ባሕርይን በማድከም ልማድን ያጠናክራል፣ የዚህ ውጤቱ የአካል፣ የአእምሮና የሞራል ዝቅጠት ነው። ለሰራችሁት ስህተት ተናዛችሁ እግራችሁን በትክክለኛው መንገድ ላይ ልታቆሙ ትችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን በአእምሮአችሁ ውስጥ የተቀረጸው ነገርና ከክፉ ጋር ያደረጋችሁት ትውውቅ ትክክል በሆነውና ባልሆነው መካከል መለየትን ከባድ ያደርግባችኋል። በተመሰረቱ የስህተት ልምዶች አማካይነት ሰይጣን በተደጋጋሚ ጥቃት ያደርስባችኋል።—Christ’s Object Lessons, 281 (1900).1MCPAmh 14.1

  የመምህር ሥነ-ልቦናዊ ብቃቶች።--የመምህር ልምዶችና መርሆዎች ከሥነ-ጽሁፍ ብቃቶቹ የበለጠ አስፈላጊ መሆናቸው ከግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት። እውነተኛ ክርስቲያን ከሆነ ተማሪዎቹ የቀለም ትምህርትን እንዲያገኙ ከሚፈልገው ጋር እኩል በሆነ ሁኔታ የአካል፣ የአእምሮ፣ የግብረገብና መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት እንዳለባቸው ይሰማዋል። ትክክለኛ የሆነ ተጽእኖ ማሳደር እንዲችል በራሱ ላይ ፍጹም ቁጥጥር ሊኖረውና ልቡ በእይታው፣ በቃላቶቹና በተግባሮቹ በሚታይ ለልጆቹ ባለው ፍቅር መሞላት አለበት። የባሕርይ ጽናት ሊኖረው ይገባል፣ ይህ ሲሆን የተማሪዎቹን አእምሮዎች ሊቀርጽና በሳይንሶቹ ላይም ትምህርት ሊሰጥ ይችላል። ወጣቶች በልጅነት ዕድሜያቸው የሚያገኙት ትምህርት በአጠቃላይ ባሕርያቸውን ለሕይወት ዘመናቸው ይቀርጻል። ከልጆች ጋር የሚሰሩ ሰዎች የአእምሮ ኃይሎች ለተሻለ ነገር ጥቅም ላይ መዋል እንዲችሉ እንዴት በተሻለ ሁኔታ እንደሚመሩአቸው ለማወቅ የአእምሮ ችሎታዎችን በሥራ ላይ ሲያውሉ በጣም መጠንቀቅ አለባቸው።—Testimonies for the Church 3:135 (1872).1MCPAmh 14.2

  ሰው አዲስ ፍጥረት ለመሆን።--ሰዎች የክርስቶስ መንግስት ተገዦች መሆን አለባቸው። በተቆጠረላቸው በመለኮታዊ ኃይል አማካይነት ለአምላካቸው ታማኝ ወደመሆን ይመለሳሉ። በሕጎችና በአከባቢያችን ባሉ ነገሮች አማካይነት እግዚአብሔር ከሰው መንፈሳዊ ሕይወት ጋር ሰማያዊ ግንኙነት ለማድረግ ስለወሰነ በዚህ ተግባር ውስጥ እንደ ሳይንስና እንደ ንፋስ እንቅስቃሴ ምስጢራዊ የሆነ ነገር አለ (ዮሐንስ 3፡ 7፣ 8)። ክርስቶስ እንዲህ አለ፣ ‹‹መንግስቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም›› (ዮሐንስ 18፡ 36)። በምድራዊ መንግስታት ላይ የተጽእኖ አሻራውን ቢያሳርፍባቸውም መለኮታዊ ምሳሌን ሳያበላሽ ከእነርሱ ትንሽ አሻራ እንኳን መቀበል አይችልም። እግዚአብሔር በሰብአዊ ልብ ውስጥ የሚሰራው ሥራ ባሕርይ ለሚቀበለው ሰው መንፈሳዊ ስለሆነ እግዚአብሔር ለሰው የሰጠውን ማንኛውንም ችሎታ ሳያጠፋ ወይም ሳያዳክም እያንዳንዱን ሰው አዲስ ፍጥረት ያደርጋል። ከመለኮታዊ ተፈጥሮ ጋር ለመገናኘት ገጣሚ የሆነውን እያንዳንዱን ባሕርይ ያነጻል። ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ስለሆነ ሰው ከላይ ሲወለድ ሰማያዊ ሰላም ነፍስን ይሞለዋል።—Manuscript 1, 1897. (Special Testimony to the Battle Creek Church 3:8-9.)1MCPAmh 14.3

  ትክክል የሆነ ነገር ስህተትን ያስወግዳል።--ወላጆች ሆይ፣ የልጆቻችሁ አእምሮዎች ክቡር በሚያደርጉ ሀሳቦች ወይም በተንኮል ስሜት እንዲሞሉ የምትወስኑት እናንተ ናችሁ። ንቁ አእምሮአቸውን ያለ ሥራ ልታቆዩም ሆነ ክፉን በቁጣ ልታርቁት አትችሉም። የስህተት ሀሳቦችን ማስወገድ የሚቻለው ትክክለኛ መርሆዎችን በማሳደግ ብቻ ነው። ወላጆች በልጆቻቸው ልብ ውስጥ የእውነትን ዘሮች ካልዘሩ በስተቀር ጠላት እንክርዳድን ይዘራል። መልካም ጠባይን የሚያበላሹ ክፉ ግንኙነቶችን የሚከላከለው ብቸኛው ነገር ጥሩና ትክክለኛ የሆነ ትምህርት ነው። እውነት ነፍስን ከሚገጥሟት ማብቂያ ከሌላቸው ፈተናዎች ይከላከላል።—Counsels to Parents, Teachers, and Students, 121 (1913).1MCPAmh 15.1

  የእኔ የሆነው አንድ ቀን ብቻ ነው።--በዚህ ሕይወት ጠቃሚዎች እንድንሆን ሁላችንም ከቀን ወደ ቀን መሰልጠን፣ መገራትና መማር አለብን። በአንድ ጊዜ አንድ ቀን ብቻ--ይህን አስብ። አንድ ቀን የእኔ ነው። በዚህ አንድ ቀን ማድረግ የምችለውን አደርጋለሁ። ለሌላ ሰው በረከት፣ ረዳት፣ አጽናኝ፣ አዳኜ የሆነው ጌታ ማረጋገጫ የሚሰጠው ምሳሌ ለመሆን የንግግር መክሊቴን እጠቀማለሁ። ዛሬ በእኔ ውስጥ መልካም ክርስቲያናዊ ባሕርያት እንዲያድጉ በትዕግስት፣ በደግነት፣ ራስን በመተው ራሴን እመራለሁ። በየጧቱ ራስን፣ ነፍስን፣ አካልንና መንፈስን ለእግዚአብሔር ቀድሰህ ስጥ። የመሰጠትንና በአዳኝህ የመታመንን ልምዶች የበለጠ አጠናክር። ጌታ ኢየሱስ እንደሚወድህና በባህርይህ ወደ እርሱ ሙሉ ሰውነት እንድታድግ እንደሚመኝ በሙሉ መታመን ልታምን ትችላለህ። በእርሱ ፍቅር እንድታድግ፣ በመለኮት ፍቅር ሙላት ሁሉ እንድትጨምርና እንድትበረታ ይመኛል። ያኔ ለአሁንና ለዘላለም የሚሆን ከፍተኛ ዋጋ ያለው እውቀት ታገኛለህ።—Letter 36, 1901 (In Heavenly Places, 227.)1MCPAmh 15.2

  በደንብ ሚዛናዊ የሆኑ አእምሮዎች እንዴት እንደሚጎለብቱ።--ሥራ በረከት ነው። ሥራ ሳንሰራ ጤናማ መሆን የማይቻል ነገር ነው። ሁሉም የአካል ክፍሎች በተገቢ ሁኔታ እንዲያድጉና ወንዶችና ሴቶች ሚዛናዊ የሆኑ አእምሮዎች እንዲኖሩአቸው ከተፈለገ እነዚህ የአካል ክፍሎች ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው።—Testimonies for the Church 3:154, 155 (1872).1MCPAmh 15.3

  እውቀትና ሳይንስ በመንፈስ ቅዱስ መጎልበት አለባቸው።-- የአንድ ግለሰብ መክሊቶች የተሟላ ጥቅም መስጠት የሚችሉት በእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ ቁጥጥር ሥር ሲሆኑ ብቻ ነው። የኃይማኖት ትዕዛዛትና መርሆዎች እውቀትን በማግኘት ሂደት የመጀመሪያ እርምጃዎች ሲሆኑ በእውነተኛ ትምህርት መሰረት ላይ የሚገኙ ናቸው። እውቀትና ሳይንስ የከበሩ ተግባራትን ማከናወን እንዲችሉ በእግዚአብሔር መንፈስ መጎልበት አለባቸው። ክርስቲያን ብቻውን እውቀትን በትክክል ሊጠቀምበት ይችላል። ሳይንስ በተሟላ ሁኔታ መደነቅ እንዲችል ከኃይማኖታዊ አቋም አንጻር መታየት አለበት። ይህ ሲሆን ሁሉም ሳይንስን የፈጠረውን አምላክ ያመልካሉ። በእግዚአብሔር ፀጋ የከበረ ልብ የትምህርትን እውነተኛ ዋጋ በደንብ ይገነዘባል። እግዚአብሔር በፈጠራቸው ሥራዎቹ ውስጥ የሚታዩ የእርሱ ባሕርያት ሊደነቁ የሚችሉት የፈጣሪ እውቀት ሲኖረን ብቻ ነው። መምህራን ወጣቶችን ወደ እውነት ምንጭ፣ የዓለምን ኃጢአት ወደሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፣ ለመምራት ከእውነት ጽንሰ-ሀሳብ ጋር ብቻ መተዋወቅ ሳይሆን ስለ ቅድስና መንገድ ተግባራዊ እውቀትም ሊኖራቸው ይገባል። እውቀት ለመልካም ነገር ኃይል መሆን የሚችለው ከእውነተኛ ኃይማኖተኛነት ጋር ሲጣመር ነው። ከራስ ነጻ የሆነ ነፍስ የከበረ ይሆናል። ክርስቶስ በልብ ውስጥ በእምነት ሲኖር በእግዚአብሔር እይታ ጠቢባን ያደርገናል።—Manuscript 44, 1894.1MCPAmh 16.1

  መላው አካል ለሰማይ የፈውስ ወኪሎች ክፍት ነው።--ክርስቶስ የሕይወት ውኃ ምንጭ ነው። ብዙዎች የሚያስፈልጋቸው ስለ እርሱ ጥርት ያለ እውቀት ነው፤ በትዕግስትና በትህትና፣ ግን በትጋት መላው አካል እንዴት ለሰማይ የፈውስ አካሎች ክፍት እንደሚሆን መማር አለባቸው። ከእግዚአብሔር የሚመጣው የፍቅር ፀሐይ ብርሃን የጨለሙትን የነፍስን ክፍሎች ሲያበራ፣ የማያቋርጥ ድካምና አለመርካት ያበቁና እርካታ የሚሰጥ ደስታ ለአእምሮ ብርታትና ለአካል ጉልበትን ይሰጣል።—The Ministry of Healing, 247 (1905).1MCPAmh 16.2

  ጸጋዎች በቅጽበት አያድጉም።--የከበሩ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋዎች በቅጽበት አያድጉም። ድፍረት፣ ፅናት፣ የዋህነት፣ እምነት፣ በሚያድነው የእግዚአብሔር ኃይል የማይናወጥ መታመን፣ ሊገኙ የሚችሉት በዓመታት ልምምድ ነው። ቅዱስ ጥረትና ትክክል ለሆነው ነገር ጽኑ መታዘዝ ባለበት ሕይወት የእግዚአብሔር ልጆች መዳረሻቸውን ማተም አለባቸው።—The Ministry of Healing, 454 (1905).1MCPAmh 16.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents