Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 12—ታታሪነት (ትጋት)

  [በምዕራፍ 65 ላይ ‹‹ስንፍና›› የሚለውን ክፍል ያንብቡ]

  ጥረት አድርግና ከግብ ድረስ።--ድል የሚገኘው ጠንክሮ በማጥናት፣ ጠንክሮ በመስራት እና በማይደክም ትጋት ነው። ሰዓታትን አታባክን፣ ቅጽበትን አታባክን። ልባዊ የሆነ እና ታማኝነት ያለበት ሥራ ውጤቶች ይታያሉ አድናቆትም ይቸራቸዋል። ጠንካራ የሆኑ አእምሮዎች እንዲኖሩአቸው የሚሹ ሰዎች ሊያገኙ የሚችሉት ተግተው በመሥራት ነው። የአእምሮ ኃይልና ብቃት የሚጨምረው ስንጠቀመው ነው። ጠንካራ የሚሆነው ሳንሰለች ስናሰራው ነው። የአእምሮና የአካል ኃይሎቹን እጅግ በትጋት የሚጠቀም ሰው ከሁሉ የሚበልጡ ውጤቶችን ያገኛል። እያንዳንዱ የአካል ኃይል በሥራ ብርቱ ይሆናል። --RH, Mar 10, 1903. {1MCP 99.1}1MCPAmh 82.1

  ልትደርስበት የምትችለውን ከፍተኛ ችሎታ አግኝ። የትምህርት እውነተኛው ዓላማ በጥንቃቄ መታየት አለበት። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው አድገውና ተሻሽለው መመለስ ያለባቸውን ችሎታዎችና ኃይሎች ሰጥቷል። እርሱ የሰጠን ስጦታዎች በሙሉ የተሰጡት የተቻለውን ያህል ጥቅም ላይ እንዲውሉ ነው። እያንዳንዳችን ለእግዚአብሔር የከበረ ሥራ ለመስራትና ሰብአዊነትን ለመባረክ እንድንችል ኃይሎቻችንን እንድናሳድግና ጠቃሚ ሆነን ለመገኘት ሊገኝ የሚቻለውን ከፍተኛ ችሎታ እንድንናገኝ ይጠይቃል። ያለን እያንዳንዱ መክሊት፣ የአእምሮ ችሎታ ቢሆን ወይም ገንዘብ ወይም ተጽእኖ ከእግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ ከዳዊት ጋር ሆነን ‹‹ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፣ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃል›› ማለት እንችላለን (1ኛ ዜና 29፡ 14)። --RH, Aug 19, 1884. (FE 82.) {1MCP 99.2}1MCPAmh 82.2

  ጥሩ የአእምሮ ችሎታዎች የአጋጣሚ ውጤት አይደሉም።--በማንኛውም የሥራ መስመር እውነተኛ ስኬት በድንገት የሚገኝ ወይም የአጋጣሚ ወይም የአርባ ቀን እድል ውጤት አይደለም። የእግዚአብሔር ፈቃድ ከውስጥ ወደ ውጭ የመሥራት፣ የእምነትና በራስ የመወሰን መብት ሽልማት፣ የምግባረ ጥሩነትና ዓላማን ለማሳካት ተግቶ የመስራት ውጤት ነው። ጥሩ የአእምሮ ችሎታዎችና ከፍ ያለ የግብረገብ ቅኝት የአጋጣሚ ውጤቶች አይደሉም። እግዚአብሔር መልካም እድሎችን ይሰጣል፤ ስኬት የሚደገፈው እነዚህን መልካም ዕድሎች በመጠቀማችን ላይ ነው። --PK 486 (1917). {1MCP 100.1}1MCPAmh 82.3

  የምንፈልገው አእምሮን ማሰልጠን ነው።--አእምሮን ማሰልጠን እንደ ሕዝብ የምንፈልገውና የጊዜውን ጥያቄዎች ለማሟላት ሊኖረን የሚገባ ነገር ነው። ድህነት፣ ዝቅ ያለ መነሻ፣ እና ምቹ ያልሆኑ አከባቢዎች የአእምሮን እድገት መከልከል የለባቸውም። የአእምሮ ክፍሎች በፈቃድ ቁጥጥር ሥር መሆን አለባቸው፤ አእምሮ እንዲባዝንና አንዱንም ነገር ሳይጨርስ በአንድ ጊዜ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች እንዲደናቀፍ መፈቀድ የለበትም። {1MCP 100.2}1MCPAmh 82.4

  በሁሉም ትምህርቶች ችግር ሊያጋጥም ይችላል፣ ነገር ግን ተስፋ በመቁረጥ በፍጹም አታቋርጥ። ፈልግ፣ ተማር፣ ጸልይ፤ እያንዳንዱን ችግር በቆራጥነትና በትጋት ተጋፈጥ፤ እንዲረዱህ የፈቃድን ኃይልና የትዕግስትን ጸጋ በመጋበዝ የእውነት እንቁ ግልጽና ውብ ሆኖ፣ እርሱን በማግኘት ሂደት ካጋጠሙ ችግሮች የተነሣ የበለጠውን ውድ ሆኖ፣ በፊትህ እስኪቀመጥ ድረስ በትጋት ቆፍር። {1MCP 100.3}1MCPAmh 83.1

  ስለዚህ ሁሉንም የአእምሮ ጉልበት በዚህ አንድ ነጥብ ላይ ብቻ በማድረግና ያለማቋረጥ ሌሎች ሰዎች ትኩረት እንዲያደርጉበት በማደፋፈር ሁል ጊዜ በዚህ ነጥብ ላይ አትቆይ፣ ነገር ግን ሌላ የትምህርት ዓይነት ውሰድና በጥንቃቄ መርምር። በዚህ ሁኔታ ምስጢር ምስጢርን እየተከተለ ይገለጥልሃል። በዚህ መንገድ ሁለት ጠቃሚ ድሎች ይገኛሉ። ጠቃሚ የሆነ እውቀት ብቻ የምታገኝ ሳይሆን አእምሮ በሥራ ላይ መሆኑ የአእምሮ ብርታትና ኃይል ይጨምራል። አንድን ምስጢር ለመክፈት የተገኘው ቁልፍ ከዚህ በፊት ያልተገኙ ሌሎች ውድ የእውቀት እንቁዎችን ሊያሳድግ ይችላል። --4T 414 (1880). {1MCP 100.4}1MCPAmh 83.2

  የአእምሮ ሕግ።--አእምሮ በደንብ ከሚተዋወቃቸው ነገሮች አቅጣጫ ሊጠብም ሊሰፋም ይችላል የሚለው የአእምሮ ሕግ ነው። የአእምሮ ኃይሎች በብርታትና ባለማቋረጥ እውነትን የመፈለግ ሥራ ላይ ካልተሰማሩ በስተቀር በእርግጠኝነት ይጠቡና የእግዚአብሔርን ቃል ጥልቅ ትርጉሞች ለመረዳት ችሎታ ያጣሉ። አእምሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ርዕሰ ጉዳዮች ያላቸውን ግንኙነት ለማወቅ ጥቅስን ከጥቅስ ጋር፣ መንፈሳዊ ነገሮችን ከመንፈሳዊ ነገሮች ጋር የማመሳከር ሥራ ላይ ሲሰማራ ይሰፋል። ላይ ላዩን መሄድ ትታችሁ ወደ ውስጥ ጠለቅ ብላችሁ ግቡ፤ ማሰብን የሚፈልጉ ውድና ከፍተኛ የሆኑ ሀብቶች ብልሃተኛና ትጉህ የሆነ ተማሪን በመጠበቅ ላይ ናቸው።--RH, July 17, 1888. (MYP 262.) {1MCP 101.1}1MCPAmh 83.3

  ተደብቀው ያሉ ኃይሎችን ለተግባር አንቀሳቅሷቸው።--በተለመዱ የሕይወት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሥራ ላይ እንዲውሉ ቢቀሰቀሱ ኖሮ ግለሰቡን ከዓለም ታላላቅ መሪዎች ተርታ ሊያስቀምጡ የሚችሉ የተደበቁ ኃይሎች እንዳሉት ሳይገነዘብ ዕለታዊ ሥራውን እያከናወነ በትዕግስት የሚለፋ ግለሰብ አለ። እነዚያን ተደብቀው ያሉ ኃይሎችን ለመቀስቀስና ለማሳድግ ብልሃተኛ የሆነ የእጅ ንካት ያስፈልጋል። ኢየሱስ ከራሱ ጋር ያገናኛቸውና በራሱ እንክብካቤ ሥር አድርጎ የሶስት ዓመት ሥልጠና እንዲያገኙ ዕድል የሰጣቸው እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎችን ነበር። በማንኛውም የታላላቅ መምህራን (ራቢዎች) ትምህርት ቤት ወይም የፍልስፍና አዳራሽ ውስጥ የሚሰጥ የትምህርት ዘርፍ በጠቃሚነቱ ከዚህ ጋር አይስተካከልም ነበር። --CT 511 (1913). {1MCP 101.2}1MCPAmh 83.4

  ብዙዎች በአእምሮአቸው ግዙፋን ሊሆኑ ይችሉ ነበር።--ከሰራተኞቻችን መካከል ብዙዎቹ አነስተኛ ደረጃ በመድረሳቸው ረክተው ከመቀመጥ ይልቅ ቢተጉና ጠለቅ አድርገው ቢያስቡና ቢመራመሩ ኖሮ ዛሬ በአእምሮ ችሎታቸው ግዙፋን መሆን በቻሉ ነበር። ከወጣቶቻችን መካከል ብዙዎቹ ጥልቀት የሌላቸውና በክርስቶስ ኢየሱስ ሙሉ ወንዶችና ሴቶች ወደ መሆን ደረጃ ያለማደግ አደጋ ውስጥ ያሉ ናቸው። ትምህርትን በተመለከተ በቂ እውቀትና መረዳት እንዳላቸው ይሰማቸዋል፣ ከዚህ የተነሣ ማጥናትን ስለማይወዱ ሊያገኙ የሚችሉአቸውን ሀብቶች ሁሉ ለማግኘት አጥልቀው አይቆፍሩም። --Lt 33, 1886. {1MCP 101.3}1MCPAmh 84.1

  ራስን መቆጣጠር (ሥነ ሥርዓት ማስያዝ) አስፈላጊ ነው።--እግዚአብሔር የአእምሮ ክፍሎችን እንድናሰለጥን ይፈልግብናል። የአእምሮ ክፍሎቻችንን ማሳደግ የሚያስፈልግበት ምክንያት፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ ለእግዚአብሔር ክብር እውነትን እጅግ ከፍተኛ በሆኑ ምድራዊ ኃይላት ፊት ማቅረብ እንድንችል ነው። ልብንና ባሕርይን የሚለውጠው የእግዚአብሔር ኃይል ደግሞ በየቀኑ ያስፈልጋል። የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ የሚል እያንዳንዱ ግለሰብ ራሱን መቆጣጠር አለበት፤ አእምሮና ፈቃድ ለእግዚአብሔር ሀሳብና ፈቃድ ተገዥ የሚሆኑት በዚህ መንገድ ነው። በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ቁርጠኝነት ያለበት ራስን መቆጣጠር ከአንደበተ ርቱእነትና እጅግ ብሩህ ከሆኑ ተሰጥኦዎች የበለጠ ነገር ይፈጽማል። ተራ አእምሮ፣ በደንብ ከሰለጠነ፣ ራስን መቆጣጠር ከማይችል እጅግ ከተማረ አእምሮና እጅግ ትልቅ ከሆኑ ተሰጥኦዎች የበለጠና ከፍ ያለ ነገር ይሰራል። --RH, July 28, 1896. {1MCP 101.4}1MCPAmh 84.2

  የሚያገናዝቡ አእምሮዎችን መላእክት ይቆጣጠራሉ።--የሚያገናዝቡ አእምሮዎችን ለመቆጣጠር የሰማይ መላእክት ሥራ ላይ ሲሆኑ የእነርሱ ኃይል ከጨለማ ሰራዊት ኃይል እጅግ የበረታ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር የቀረበ ግንኙነት የሌላቸውና የእግዚአብሔርን መንፈስ ለይተው የማያውቁ ግን ቅዱስ ከሆኑ ነገሮች ጋር የሚሰሩ አእምሮዎች አሉ። የእርሱ ጸጋ ክርስቶስን ወደመምሰል ካልለወጣቸው በስተቀር ውኃ የሚያፈስ ዕቃን ለቆ እንደሚወጣ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ትቶአቸው ይሄዳል። እነዚህ ሰዎች ያላቸው ብቸኛው ተስፋ እግዚአብሔርን በፍጹም አእምሮአቸው፣ ልባቸውና ነፍሳቸው መሻት ነው። ያኔ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለማሸነፍ ጥረት ያደርጋሉ። ሰይጣን ዕድል ከተሰጠው ሀሳብንና ዝንባሌን ይሰርቃል። --MS 11, 1893. {1MCP 102.1}1MCPAmh 84.3

  እጅግ ከፍተኛ የሆነ የተቀደሰ ፍላጎት ይፈለጋል።--‹‹ጸጋዬ ይበቃሃል›› (2ቆሮ. 12፡ 9) የሚለው አረፍተ ነገር ታላቁ መምህር የሰጠው መተማመኛ ነው። በእነዚህ ቃላት ውስጥ ያለውን መገለጥ ያዝና ጥርጣሬንና አለማመንን በፍጹም አታውራ። ታታሪ ሁን። ንጹህ በሆነና ባልተበከለ ኃይማኖት ውስጥ ግማሽ በግማሽ አገልግሎት የለም። ‹‹እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም አእምሮህና በፍጹም ኃይልህ ውደድ›› (ማርቆስ 12፡30)። የእግዚአብሔርን ቃል ከሚያምኑ ሰዎች እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የተቀደሰ ፍላጎት ይፈለግባቸዋል።--SpTEd 30, June 12, 1896. (CT 360.) {1MCP 102.2}1MCPAmh 85.1

  እግዚአብሔር በሰጣችሁ ማንነት ቁሙ።--እግዚአብሔር የማሰብና የመተግበር ችሎታ ስለሰጠን ሸክም መሸከም የምንችለው የምናደርገውን ነገር በጥንቃቄ በማድረግና ከእርሱ ጥበብን በመሻት ነው። እግዚአብሔር በሰጣችሁ ማንነት ቁሙ። የሌላ ሰው ጥላ አትሁኑ። እግዚአብሔር በውስጣችሁ ይሰራል፣ በእናንተ ይሰራል፣ በእናንተ አማካይነትም ይሰራል። --MH 498, 499 (1905). {1MCP 103.1}1MCPAmh 85.2

  ዓለምን እያበላሸ ያለው ሻጋታ (አስቀድሞ መገመትን ይወድ ለነበረ አገልጋይ የተሰጠ ተግሳጽ)።--የእውነት መምህር መሆን የሌለብህ ሰው ነህ። በልምምድህና ስለ እግዚአብሔር ባለህ እውቀት አሁን ካለህበት እጅግ ርቀህ መሄድ ነበረብህ። እግዚአብሔር ከፍተኛ እድገት የሚጠበቅባቸውን የአእምሮ ክፍሎች ስለሰጠህ በማስተዋልህ ሰው መሆን አለብህ። አስቀድሞ ከሚገመት የተፈጥሮ ዝንባሌህ ራስህን ብታፋታና ከዚህ በታቃራኒ አቅጣጫ ሰርተህ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው አገልግሎት መስጠት ትችል ነበር። {1MCP 103.2}1MCPAmh 85.3

  አእምሮህን በትክክል አሳድገህ ቢሆንና ለእግዚአብሔር ክብር ተጠቅመህ ቢሆን ኖሮ የማስጠንቀቂያ መልእክትን ለዓለም ለማድረስ ሙሉ በሙሉ ብቁ ትሆን ነበር። ነገር ግን የዓለም ሻጋታ አእምሮህን እጅግ ከመጉዳቱ የተነሣ አልተቀደሰም። በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ የተዋጣልህ ሰራተኛ እንድትሆን የሚያደርጉህን ክፍሎች እያሳደግካቸው አልነበርክም። አእምሮህን በትክክለኛው መስመር የማስተማር ሥራን ወደ ፊት መቀጠል ትችላለህ። እውነትን በተመለከተ አሁን ብልህ ካልሆንክ ስህተቱ የራስህ ብቻ ይሆናል። --Lt 3, 1878. {1MCP 103.3}1MCPAmh 85.4

  ያለማቋረጥ ወደ ፊት ተንቀሳቀስ።--የእግዚአብሔር መላእክት ብሩህና የሚያበራ ብርሃን አድርገውህ ሳታቋርጥ በጽናት ወደ ፊት እንድትጓዝ ልብህን በቅዱስ ቅንዓት እንዲያነሳሱ ፍላጎትህ የተቀደሰ ፍላጎት እንዲሆን እፈልጋለሁ። መላው አንተነትህ-አካል፣ ነፍስና መንፈስ- የተቀደሰ ሥራን ለመሥረት ቢቀደሱ ኖሮ ነገሮችን የሚገነዘቡ ክፍሎች ኃይልና ጥሩነት ይጨምር ነበር። በክርስቶስ ጸጋ አማካይነት ከፊትህ ወደ ተቀመጠው ከፍተኛ መስፈርት ለመድረስ ጥረት ማድረግ አለብህ። እግዚአብሔር በራሱ የሥራ መስክ ፍጹም እንደሆነ አንተም በራስህ የሥራ መስክ ፍጹም መሆን ትችላለህ። ክርስቶስ ‹‹የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ›› (ማቴ 5፡ 48) ብሎ አልተናገረምን? --Lt 123, 1904. {1MCP 103.4}1MCPAmh 86.1

  እያንዳንዱን ኃይል አሳድግ።--እርሱ (እግዚአብሔር) ያለ ማቋረጥ በቅድስና፣ በደስተኛነትና በጠቃሚነታችን እንድናድግ ይፈልጋል። ሁሉም እንደ ተቀደሱ ስጦታዎች ለመቁጠር፣ እንደ እግዚአብሔር ሥጦታዎች ለማድነቅ እና በትክክል ሥራ ላይ ለማዋል መማር ያለባቸው ችሎታዎች አሉአቸው። ወጣቶች የእነርሱነታቸውን እያንዳንዱን ኃይል እንዲያጎለብቱና እያንዳንዱን የአካል ክፍል በንቃት ሥራ ላይ እንዲያውሉ ይፈልጋል። ሰማያዊውን ሀብት ለወደ ፊት ሕይወት በማስቀመጥ በዚህ ሕይወት ጠቃሚና ክቡር የሆነውን ነገር ሁሉ እንዲደሰቱበት፣ ጥሩ እንዲሆኑና ጥሩ ነገር እንዲሰሩ ይፈልጋል። --MH 398 (1905). {1MCP 104.1}1MCPAmh 86.2

  ሁሉም ሊደርሱባቸው የሚችሉአቸው መልካም ዕድሎች።--የሞራልና መንፈሳዊ ኃይሎችን ለማጠናከር ሁሉም ሊደርሱባቸው የሚችሉአቸው መልካም ዕድሎችና አጋጣሚዎች አሉ። አእምሮ ሊሰፋና ሊከብር የሚችል ሲሆን በሰማያዊ ነገሮች ላይ እንዲያርፍ መደረግ አለበት። ኃይሎቻችን እስከ መጨረሻው ማደግ አለባቸው፣ ይህ ካልሆነ የእግዚአብሔርን መስፈርት ማሟላት ያቅተናል። {1MCP 104.2}1MCPAmh 86.3

  አእምሮ በሰማይ አቅጣጫ ካልፈሰሰ በስተቀር ከእግዚአብሔር ጋር የተለየ ግንኙነት ከሌላቸው ከዓለማዊ ፕሮጀክቶችና የንግድ ድርጅቶች ጋር በመጠመድ በቀላሉ የሰይጣን ሰለባ ይሆናል። ውሥጣዊ ቅንዓትና መሰጠት፣ እንዲሁም እረፍት የለሽ ጉልበትና ትኩስ ፍላጎት በዚህ ሥራ ላይ ሲውልና ሰብአዊ ጥረቶች በፍጹም ማግኘት ለማይችሉት ነገር ተስፋ ሳይቆርጡ ሲታገሉ ሲያይ በቁጥጥሩ ሥር መሆናቸውን ስለሚገነዘብ ሰይጣን በአጠገብ ቆሞ ይስቃል። በተጨማሪም የአእምሮን፣ የአጥንትንና የጡንቻን ብርታት በፍጹም ሊተገበር ለማይችል ነገር ለመስጠት መሰረት በሌለው የማታለያ ፍቅር ተይዘው እንዲቆዩ ማድረግ ከቻለ እግዚአብሔር የእኔ ናቸው የሚላቸውና የእግዚአብሔር የሆኑት የአእምሮ ኃይሎች ከትክክለኛው ዓለማ ወደ ሌላ አቅጣጫ ስለተቀየሩ ይደሰታል። --Lt 17, 1886. {1MCP 104.3}1MCPAmh 86.4

  የየዕለቱን መሻሻል ጠላት መግታት የለበትም።--ከፍ ወዳለና ቅዱስ መስፈርት ለመድረስ ቁርጥ ውሳኔ አድርግ፤ ከፍ አድርገህ አልም፤ ልክ ዳንኤል እንዳደረገው ልባዊ በሆነ ዓላማ ባለማቋረጥና በትዕግስት ሥራ። ይህ ሲሆን ጠላት ሊያደርግ የሚችለው ምንም ነገር ቢሆን የየዕለቱን መሻሻል ሊገተው አይችልም። አለመመቸቶች፣ ለውጦች፣ ግራ መጋባቶች መኖራቸው ባይካድም በአእምሮ ብርታትና በሞራል ኃይል ያለማቋረጥ ወደ ፊት መቀጠል ትችላለህ። {1MCP 104.4}1MCPAmh 87.1

  ምርጫው ካልሆነ በስተቀር ማንም አለአዋቂ መሆን የለበትም። እውቀት የአእምሮ ምግብ ስለሆነ ያለማቋረጥ ማግኘት አለባችሁ። የክርስቶስን መምጫ የምንጠብቅ ሰዎች ይህን ሕይወት ሁል ጊዜ በተሸናፊው ወገን ሆነን ሳይሆን መንፈሳዊ ስኬቶችን በማስተዋል ለመኖር ቁርጠኞች መሆን አለብን። በአሸናፊ ወገን ያላችሁ የእግዚአብሔር ሰዎች ሁኑ። {1MCP 105.1}1MCPAmh 87.2

  እውቀት የሚፈልጉት ሁሉ ሊደርሱበት በሚችሉበት ቦታ ይገኛል። የእግዚአብሔር እቅድ አእምሮ በጥልቀት፣ በሙላትና በግልጽ በማሰብ ጠንካራ እንዲሆን ነው። ሄኖክ እንዳደረገው ከእግዚአብሔር ጋር ተራመድ፤ እግዚአብሔርን አማካሪህ ካደረግክ መሻሸል ታሳያለህ። --Lt 26d, 1887. {1MCP 105.2}1MCPAmh 87.3

  እግዚአብሔርን ያዝና ወደ ፊት ሂድ።--እግዚአብሔር ለሰው አእምሮን ከሰጠው በኋላ መሻሸል ያለባቸውን ችሎታዎች ለገሰው። ስለዚህ ከንቱነትን ፣ ፌሽታን፣ እና እርኩሰትን ሁሉ በማስወገድ እግዚአብሔርን አጥብቆ መያዝ ያስፈልጋል። የባሕርይ ጉድለቶችን ሁሉ አሸንፍ። {1MCP 105.3}1MCPAmh 87.4

  ምንም እንኳን ሰው ቁልቁል የሚወስደውን መንገድ የመፈለግ ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ ቢኖረውም ልባዊ ከሆነ ሰብአዊ ጥረት ጋር ሊቀላቀል የሚችል ኃይል አለ። የእርሱን የፈቃድ ኃይል የመቃረን ዝንባሌ ይኖረዋል። ከዚህ መለኮታዊ እርዳታ ጋር የሚቀላቅል ከሆነ የፈታኙን ድምፅ መቋቋም ይችላል። ነገር ግን የሰይጣን ፈተናዎች ከእርሱ ጉድለት ካለባቸው ኃጢአተኛ ዝንባሌዎች ጋር ስለሚጣጣሙ ኃጢአት እንዲሰራ ይገፋፉታል። ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር ምን ማድረግ እንዳለበት የሚነግረውን መሪውን ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ነው። እግዚአብሔር የዘላለማዊ ክብርን አክሊል በማቅረብ በሰማይ ካለው ዙፋኑ እየጠራህ መልካሙን የእምነት ገድል እንድትጋደልና ሩጫውን በትዕግስት እንድትሮጥ ይጠይቅሃል። በእያንዳንዷ ደቂቃ በእግዚአብሔር ታመን። እርሱ ወደ ፊት ሊመራህ ታማኝ ነው።--Lt 26d, 1887. {1MCP 105.4}1MCPAmh 87.5

  እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው ከፍ ያለ የፍጽምና መስፈርት።--እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው የፍጽምና መስፈርት እጅግ ከፍ ያለው ሰብአዊ አእምሮ መድረስ ከሚችለው በላይ ከፍ ያለ ነው። ራስን ለእግዚአብሔር ቀድሶ መስጠት-እግዚአብሔርን መምሰል-መደረስ ያለበት ግብ ነው። በተማሪው ፊት የማያቋርጥ እድገት ማሳየት የሚጠበቅበት መንገድ ተከፍቷል። እያንዳንዱን መልካም፣ ንጹህና የከበረ ነገር የሚያካትት ማሳካት ያለበት ዓላማ፣ መድረስ ያለበት መስፈርት አለ። በእያንዳንዱ እውነተኛ የእውቀት ዘርፍ በተቻለ ፍጥነትና መሄድ እስከሚችልበት ርቀት ድረስ መቀጠል አለበት። ነገር ግን ጥረቶቹ ሰማይ ከምድር የሚርቀውን ያህል ከራስ ወዳድነትና ከጊዜያዊ ነገሮች መራቅ እስከሚቻልበት ድረስ ከፍ ወዳሉ ነገሮች ይመራሉ። --Ed 18, 19 ( 1903). {1MCP 105.5}1MCPAmh 88.1

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents