Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    (ሠ) የአእምሮ ከጥገኝነት ነጻ መሆን

    እውነተኛ የሆነ ከጥገኝነት ነጻ መሆን ትዕቢተኝነት አይደለም።--እውነተኛ የሆነ የአእምሮ ከጥገኝነት ነጻ መሆን ትዕቢተኝነት አይደለም። ወጣቶች ሌሎች በሚሉት ወይም በሚያደርጉት ነገር ተጽእኖ ሥር ሳይወድቁ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የራሳቸውን አመለካከት እንዲመሰርቱ ይመራቸዋል። ከማያምኑ፣ ከከሃዲዎች ወይም ከአረመኔዎች ጋር አብረው ሲሆኑ እግዚአብሔርን የማያምኑ ጓደኞቻቸውን ምሬቶችና ቀልዶች በመቃወም በቅዱስ እውነቶች ላይ ያላቸውን እምነት ወደ መመስከርና ከጥቃት ወደ መከላከል ይመራቸዋል። የክርስቲያን ነን ባዮችን ስህተቶች ለሕዝብ ማሳየት መልካም ምግባር እንደሆነ ከሚያስቡት እና በኃይማኖት፣ በሀቀኝነትና በመልካም ምግባር ላይ ከሚያሾፉት ጋር አብረው ቢሆኑ ኖሮ ትክክለኛ የሆነ የአእምሮ ነጻነት፣ ማሾፍ ትክክለኛ ለሆነ ክርክር የማይረባ ምትክ መሆኑን በገርነት ግን በድፍረት እንዲያሳዩ ይመራቸዋል። ምንም ሳይሆን ከሚያማርረው ባሻገር በእርሱ ላይ ተጽእኖ ወደሚፈጥርበት፣ የእግዚአብሔርና የሰው ጠላት ወደሆነው፣ እንዲመለከትና ወኪሉ በሆነው ሰው ውስጥ የሚሰራውን እንዲቃወም ያስችለዋል።--RH, Aug 26, 1884. (FE 88, 89.) {1MCP 268.4}1MCPAmh 220.5

    ግላዊ ከጥገኝነት ነጻ መሆን ያስፈልጋል።--እግዚአብሔር ባስቀመጣቸው ቦታ በመስራት ያሉአቸውን የአካል ክፍሎች ሳይጠቀሙ የተለየ አጋጣሚ ቢያገኙ ኖሮ ትልቅና ጥሩ ነገር እንደሚሰሩ በመናገር ራሳቸውን የሚያታልሉ ሰዎች አሉ። ሰው ሁኔታዎችን መፍጠር ይችላል፣ ነገር ግን ሁኔታዎች በፍጹም ሰውን መፍጠር የለባቸውም። ሰው ሁኔታዎችን እንደሚሰራባቸው መሳሪያዎች አድርጎ መያዝ አለበት። ሁኔታዎችን መቆጣጠር አለበት፣ ነገር ግን ሁኔታዎች እንዲቆጣጠሩት በፍጹም መፍቀድ የለበትም። የግለሰብ ከጥገኝነት ነጻ መሆንና የግለሰብ ኃይል አሁን የሚፈለጉ ችሎታዎች ናቸው። የግለሰብን ባህርይ መስዋዕት ማድረግ አያስፈልግም፣ ነገር ግን መስተካከል፣ መታረም፣ ከፍ ማለት አለበት።--3T 496, 497 (1875). {1MCP 269.1}1MCPAmh 221.1

    ከጥገኝነት ነጻ በመሆን ምን ያህል ርቆ መሄድ እንደሚቻል።--እግዚአብሔር ከሕዝቦቹ የሚጠብቀው ዓይን ለዓይን እንዲተያዩና ተመሳሳይ አእምሮና ተመሳሳይ ውሳኔ አሰጣጥ እንዲኖራቸው ሥነ-ሥርዓት እንዲማሩና የተግባር ቅንጅት እንዲኖራቸው ነው። የዚህ ዓይነት ነገሮችን ለማምጣት ብዙ መደረግ ያለበት ነገር አለ…። እግዚአብሔር ግለሰብነታችንን እንድንተው አይፈልግብንም። ነገር ግን ይህ የግለሰብ ከጥገኝነት ነጻ የመሆን ጉዳይ እስከ ምን ድረስ እንደሆነ በትክክል የሚፈርድ ሰው ማን ነው? . . . {1MCP 269.2}1MCPAmh 221.2

    ጴጥሮስ ወንድሞቹን እንዲህ በማለት አጥብቆ ይመክራል፣ ‹‹እንዲሁም ጎበዞች ሆይ፣ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትህትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና ለትሁታን ግን ፀጋን ይሰጣል።››ሐዋርያው ጳውሎስም በፊልጵስዩስ ያሉ ወንድሞችን አንድ እንዲሆኑና ራሳቸውን ዝቅ እንዲያደርጉ አጥብቆ ይመክራቸዋል፡- ‹‹በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፣ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፣ የመንፈስ ሕብረት ቢሆን፣ ምህረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፣ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ አሳብ ተስማሙ፣ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳን አታድርጉ፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር።›› --3T 360 (1875). {1MCP 269.3}1MCPAmh 221.3

    የእግዚአብሔር ኃይል መደገፊያችን (መተማመኛችን)።--ወንድሞች ሆይ፣ ዓይናችሁን በእግዚአብሔር ክብር ላይ በማተኮር እንድትንቀሳቀሱ እማጸናችኋለሁ። ኃይሉ መታመኛችሁ፣ ጸጋው ብርታታችሁ ይሁን። ቅዱሳት መጻሕፍትን በማጥናትና ልባዊ በሆነ ጸሎት ስለ ተግባራችሁ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ እንድታገኙና በታማኝነት ልትፈጽሙት እሹ። በትናንሽ ነገሮች ታማኝነትን ማሳደግ አስፈላጊ ነው፣ ይህን ስታደርግ በታላላቅ ኃላፊነቶች ላይ ታማኝ የመሆን ልማዶችን ታገኛለህ። በሕይወታችን በየዕለቱ የሚናያቸው ትናንሽ ክስተቶች ብዙ ጊዜ ልብ ሳንላቸው ያልፋሉ፣ ነገር ግን ባሕርይን የሚቀርጹት እነዚህ ነገሮች ናቸው። እያንዳንዱ የሕይወት ክስተት ለመልካም ወይም ለክፉ ትልቅ ነው። አእምሮ በማንኛውም ከባድ ቦታ ለመቆም የሚያስችለውን ኃይል ለማግኘት በዕለታዊ ፈተናዎች አማካይነት መሰልጠን ያስፈልገዋል። በፈተናና በችግር ቀናት ከእያንዳንዱ ከሚቃወም ተጽእኖ ነጻ ሆነህ ለእውነት ጸንተህ መቆም እንድትችል ዙሪያህ በግንብ መታጠር አለበት።--4T 561 (1881). {1MCP 270.1}1MCPAmh 222.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents