Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፲፰—አሜሪካዊ ተሐድሶ አራማጅ

    ቅን፣ ታማኝ-ልብ የነበረው ገበሬ፣ የመጽሐፍ ቅዱሳትን መለኮታዊ ስልጣን እንዲጠራጠር የተመራ፣ ሆኖም በታማኝነት እውነትን ለማወቅ ጥልቅ ፍላጎት የነበረው ሰው የክርስቶስን ዳግም ምፅዓት በማወጅ እንዲመራ በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሔር ተመረጠ። እንደ አብዛኛዎቹ የተሐድሶ መሪዎች ዊሊያም ሚለር በህፃንነት ሕይወቱ በድህነት ትግል ያለፈ፣ በመሆኑም የጥንካሬንና ራስን የመካድ ታላላቅ ትምህርቶችን የቀሰመ ነበር። በመካከላቸው ያደገባቸው የቤተሰብ አባላት ደግሞ ከጥገኝነት ነጻ በሆነ፣ ነፃነትን በሚወድ መንፈስ፣ በጽናት፣ በችሎታና በቆራጥ ታጋይነት ባህሪያቸው የሚታወቁ ነበሩ። እነዚህ ባህርያት በእርሱም ባህርይ ውስጥ ገነው የሚታዩ ነበሩ። አባቱ በአብዮቱ ጦር ውስጥ ሻምበል ነበር፤ በዚያ የነውጥ ጊዜ ባሳለፈው ትግልና ስቃይ የከፈለው መስዋዕትነት የሚለርን የህጻንነት ዘመን የድህነት ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረ የሚያሳይ ነው።GCAmh 233.1

    ጥሩ የአካል ብቃት የነበረው ሲሆን፣ በልጅነቱ እንኳ የአዕምሮ ብስለቱ ከተለመደው ላቅ ያለ እንደሆነ የሚያስረዱ ምልክቶች ነበሩ። እያደገ ሲሄድ ይህ ማንነቱ የበለጠ ገሃድ እየወጣ ሄደ። አዕምሮው ንቁና በውል የጎለበተ፣ ለእውቀትም ጥልቅ ጥማት ያለው ነበረ። የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ባይገጥመውም ለማጥናት ያለው ፍቅር ነገሮችን በጥንቃቄ የማጤን ልማዱና ነገሮችን በቅርበት መርምሮ የመተቸት ችሎታው ሚዛናዊ አስተያየት መስጠት የሚችልና ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው ሰው አደረገው። ሊነቀፍ የማይችል ግብረ-ገብ ባህርይና የሚቀናበት ማንነት የተላበሰ፣ በሃቀኝነት፣ በቆጣቢነትና በለጋስነት በአጠቃላይ ስመ-ጥር ነበር። የማጥናት ልማዱ አሁንም እንደተጠበቀ ቢሆንም፣ በኃያል ጉልበቱና ገቢሩ ብቁነትን የተጎናፀፈው ገና አስቀድሞ ነበር። የተለያዩ መንግሥታዊና ወታደራዊ ኃላፊነቶችን በብቃት በመወጣቱ የኃብትና የዝና በሮች ወለል ብለው የተከፈቱለት ይመስል ነበር።GCAmh 233.2

    እናቱ በጣም ግሩም የኃይማኖት ሰው ነበረች፤ በህፃንነቱ በኃይማኖት ተጽእኖ ሥር ሆኖ እንዲያድግ ተደርጓል። ሆኖም የጎልማሳነት ዘመኑ እንደጀመረ የሰው ልጅ በሚያቀርበው ምክንያት ላይ የተመሠረተ እምነት [ለምሳሌ ትንቢትንና ተዓምራትን የማይቀበል እምነት] ካላቸው ጋር አብሮነት መሰረተ፤ ተጽዕኖአቸው የበረታበት ምክንያት በአብዛኛው መልካም ዜጎች፣ ሩህሩህና ትሁት ባህርይ ያላቸው ስለሆኑ ነበር። እነርሱ ይኖሩበት እንደነበረው፣ በክርስቲያን ተቋማት ተከበው መኖራቸው በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ባህርያቸው አካባቢያቸውን መስሎ እንዲቀረፅ አድርጎ ነበር። አክብሮትንና ልበ ሙሉነትን ያጎናፀፋቸው ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ነበር፤ ሆኖም እነዚህ መልካም ስጦታዎች እየተጣመሙ ሄደው የእግዚአብሔርን ቃል እስከመቃወም የሚያደርስ ተጽእኖ ነበራቸው። ከእነዚህ ሰዎች ጋር በመጎዳኘቱ ሚለርም የእነርሱን አስተሳሰብ እንዲቀበል ተገፋፍቶ ነበር። የወቅቱ የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ሊወጣው የማይችል የሚመስሉ ችግሮችን ደቀነበት። ሆኖም አዲስ እምነቱ መጽሐፍ ቅዱስን ያስተወው ቢሆንም በምትኩ ግን የተሻለ ነገር አላገኘበትም፤ በመሆኑም በውስጡ እርካታ አልነበረም። ያም ሆኖ ይህንን እምነቱን ለአሥራ ሁለት ዓመታት ያህል እንደያዘ ቆየ። በሰላሳ አራት አመቱ ግን እንደ ኃጢአተኛ፣ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለ መንፈስ ቅዱስ ለልቡ ተናገረው። በቀድሞው እምነቱ ከመቃብር ባሻገር ደስታን የሚያረጋግጥለት አንዳች ነገር አልነበረውም። የወደፊቱ፣ ጨለማና ተስፋ የሚያስቆርጥ ነበር። ካለፈ በኋላ ስለዚህ ጊዜ ስሜቱ ሲናገር እንዲህ አለ፦GCAmh 233.3

    “ውድመት ቀዝቃዛና የሚያሸማቅቅ ስሜት ነበር፤ ተጠያቂነት ደግሞ በእርግጥ የሁሉም መጥፊያ ነበር። ሰማዩ በራሴ ላይ ያለ ነሐስ፣ ምድር ደግሞ በእግሬ ሥር እንዳለ ብረት ነበሩ። ዘላለም - ምንድን ነበረ? ሞትስ - ለምን ነበር? የበለጠ ምክንያት ስፈልግ (ምክንያታዊነቴ በጨመረ ቁጥር) በተግባር ከመግለጽ እየራቅሁ ሄድኩ። የበለጠ ባሰብኩ ቁጥር መደምደሚያዎቼ የበለጠ እየተበታተኑ ሄዱ። ማሰብ ለማቆም ሞከርኩኝ፤ ሃሳቦቼን መቆጣጠር ግን አልቻልኩም፤ በእውነት ጎስቋላ ነበርኩ፤ መንስኤውን ግን አላውቀውም ነበር። አጉረመርምና እማረር ነበር፤ በማን ላይ እንደማጉረመርም ግን እውቀቱ አልነበረኝም። ስህተት የሚባል ነገር እንደነበር አውቅ ነበር፤ ትክክልን ግን የትና እንዴት እንደማገኛት አላውቅም ነበር። አለቀስኩ ሆኖም ተስፋ አልነበረውም….”GCAmh 234.1

    በዚህ ሁኔታው ውስጥ ሆኖ ለጥቂት ወራት ቆየ። “በድንገት”፣ አለ ሲናገር፣ “የአንድ አዳኝ ባህርይ በእውን በአዕምሮዬ ተቀረፀ። መልካምና ሩህሩህ የሆነ፣ ለሚተላለፉት ስርየት ራሱ የሆነ ብሎም ከስቃይና ከኃጢአት ቅጣት የሚያድነን አንድ አካል ያለ መሰለኝ። ወዲያውኑ እንደዚያ ያለ አካል ምን ያህል አስደሳች ሊሆን እንደሚችል ተሰማኝ፤ ራሴን ወደ እቅፉ ጥዬ ምህረቱን መተማመን አሰብኩ። ሆኖም ግን እንደዚህ አይነት አካል በእርግጥ መኖሩን እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? የሚለው ጥያቄ ተነሳ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ እንደዚህ አይነት አዳኝ ለመኖሩ ቀርቶ ወደፊት ስለሚኖረው ሁኔታ እንኳ መረጃ ማግኘት አልቻልኩም።”GCAmh 234.2

    “መጽሐፍ ቅዱስ እኔ የምፈልገውን አይነት አዳኝ ወደ እይታዬ እንዳመጣ ተረዳሁ። መንፈስ የሌለበት መጽሐፍ ለወደቀው ዓለም የሚያስፈልጉትን፣ ፍጹም ገጣሚ የሆኑ መርሆዎችን እንዴት ሊያጎለብት እንደቻለ ግራ ተጋባሁ። መጽሐፍ ቅዱሳት ከእግዚአብሔር የሆኑ የተገለጡ ምስጢራት መሆናቸውን እንድቀበል ተገደድሁ። የደስታዬ ምንጭ ሆኑ፤ የሱስ ጓደኛዬ ሆነ። አዳኙ ለእኔ ከአሥር ሺህ ሰው መካከል የላቀ ሆነብኝ። ቀድሞ ጨለማና እርስ በርስ የሚጣረሱ የነበሩት መጽሐፍ ቅዱሳት አሁን ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሐን ሆኑ። አዕምሮዬ ሰከነ፣ ረካም። በሕይወት ውቅያኖስ መካከል ጌታ እግዚአብሔር ቋጥኝ ሆኖ አገኘሁት። አሁን መጽሐፍ ቅዱስ አብይ ጥናቴ ሆነ፤ በታላቅ ደስታም መርምሬዋለሁ ማለት በትክክል እችላለሁ። ግማሹ እንኳ እንዳልተነገረኝ አወቅሁ። ውበቱንና ክብሩን ከአሁን በፊት እንዴት ላየው እንዳልቻልኩ ገረመኝ፤ አልቀበለውም ብዬ ትቸው ልቀር እችል እንደነበረም ሳስብ ደነቀኝ። ልቤ የሚያሻውን ለእያንዳንዱ የነፍሴ በሽታ መድሃኒት የሚሆነውን ሁሉንም ነገር ተገልፆ አገኘሁት። ሌላ ነገር የማንበብ አምሮቴ ጠፋ፤ ከእግዚአብሔር ጥበብ አገኝ ዘንድ ልቤን ጠመድኩት።”-S. Bliss, Memoirs of Wm. Miller, ገጽ 65-67።GCAmh 234.3

    [ሚለር] ይጠላው የነበረውን ኃይማኖት አሁን በአደባባይ እንደሚያምን መሰከረ። እምነት አልባ ጓደኞቹ ግን እርሱ ራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ስልጣን ላይ የሚያነሳውን ተቃውሞ በመከራከሪያነት ለማንሳት የዘገዩ አልነበሩም። በዚያን ወቅት ሊመልስላቸው ዝግጁ አልነበረም። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ መገለጥ ከሆነ ከራሱ ጋር የሚጣጣም ይሆናል። የሰውን ልጅ ለማስተማር እስከተሰጠ ድረስ ከእርሱ መረዳት መጠን ጋር የሚስማማ መሆን አለበት ብሎ አሰበ። መጽሐፍ ቅዱስን በራሱ ለማጥናት፣ እየተስተዋለ ያለው መጣረስም ሊስማማ የማይችል እንደሆነ ማረጋገጥ እንዳለበት ወሰነ።GCAmh 234.4

    ቀድሞ ይዟቸው የነበረውን የአስተሳብ አቅጣጫዎች ወደ ጎን ለማድረግ እየጣረና የተፃፉ ማብራሪያዎችን (commentaries) እየተወ፣ በመጽሐፍ ጠርዝ ላይ በተፃፉት ማጣቀሻዎችና የቃላት ዝርዝር አማካኝነት ጥቅስን ከጥቅስ ጋር ማነፃፀሩን ተያያዘው። ዘወትር በስልት ማጥናቱን ቀጠለ። ከዘፍጥረት ጀምሮ ጥቅስ በጥቅስ እያነበበ የብዙ ገጾች ትርጉም ተገልፆለት ከሁሉም መሰናክሎች ነፃ በሚሆንበት ፍጥነት ጥናቱን ቀጠለ። የተሰወረ ነገር በሚያገኝበት ጊዜ ከጉዳዩ ጋር ሊነፃፀር የሚችል ማንኛውንም ጥቅስ የመመርመር ልማድ ነበረው። እያንዳንዱ ቃል በርዕሰ-ጽሁፉ ላይ ያለው ትክክለኛ ትርጉም እንደተጠበቀ ሆኖ የእርሱ እይታም ተያያዥነት ካለው ከእያንዳንዱ ጽሁፍ ጋር ከተስማማ አስቸጋሪነቱ እዛ ላይ ያበቃል። ሊረዳው ያልቻለው የመጽሐፍ ክፍል ካጋጠመው በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማብራሪያ ያገኝ ነበር። በሚያጠናበት ጊዜ ለመለኮታዊ እውቀት ከልቡ ይፀልይ ነበርና በፊት ለመረዳት ያስቸገረው ሃሳብ አሁን ግልጽ ይሆንለት ጀመር። የመዝሙረኛውን ቃላት በተግባር ተለማመደ፦ “የቃልህ ፍቺ ያበራል፣ ህፃናቶችንም አስተዋዮች ያደርጋል” [መዝ 119÷130]።GCAmh 235.1

    ሌሎቹን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በተረጎመበት (በተረዳበት) መንገድ የዳንኤልንና የራእይን መፃሕፍት በጥልቅ ፍላጎት አጠና፤ ትንቢታዊ ምልክቶቹን መረዳት እንደሚቻል ሲያውቅ እጅግ ተደሰተ። ቀደምት የተፈፀሙት ትንቢቶችም ተግባራዊ የተደረጉበት አኳኋን ቃል በቃል እንደተፈፀሙ አስተዋለ፤ የተለያዩ ምስሎች፣ ዘይቤያዊ አነጋገሮች፣ ምሳሌዎች፣ መመሳሰሎችና የመሳሰሉት እዛው ባለው ዝምድናቸው የተብራሩበት ወይም የተገለፁበት ሁኔታ በሌላ ጥቅስ ትርጉም የተሰጣቸው ነበሩ፤ በመሆኑም በዚህ ሁኔታ ሲብራሩ፣ በቀጥታ፣ ቃል በቃል ይስተዋሉ ዘንድ ይገባቸው ነበር። “መጽሐፍ ቅዱስ የተገለፀ ሥርዓተ-እውነት፣ በግልጽና በቀላል ሁኔታ የተሰጠ በመሆኑ [የእግር] መንገደኛው ሰው፣ ሞኝ ቢሆንም እንኳ ሊስት የማይገባው መሆኑን ሳውቅ ረካሁ” ይላል።-Bliss, ገጽ 70። ደረጃ በደረጃ የትንቢትን ታላላቅ ዱካዎች እየተከተለ ሲሄድ የእውነት ሰንሰለት እየተያያዘ፣ እየተያያዘ በመገለጥ ለጥረቱ ዋጋ ከፈለው። የሰማይ መላዕክት አዕምሮውን እየመሩ መጽሐፍ ቅዱስን ይረዳው ዘንድ ግልጽ ያደርጉለት ነበር።GCAmh 235.2

    ትንቢቶች ከአሁን ቀደም የተፈፀሙበትን አኳኋን በመውሰድ ገና ያልተፈፀሙት ተግባራዊ የሚሆኑበትን ሁኔታ ለመገመት የቀድሞውን እንደመመዘኛ (መስፈርት) በመጠቀም ዓለም ወደ ፍፃሜ ከመምጣቱ በፊት ለአንድ ሺህ ዓመት የክርስቶስ መንፈሳዊ ግዛት እንደሚኖር የሚንፀባረቀው በስፋት ተቀባይነት ያለው ሃሳብ የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ እንደሌለው አረጋገጠ። ከክርስቶስ በአካል ዳግም መምጣት በፊት አንድ ሺህ የጽድቅና የሰላም ዓመታት እንዳሉ የሚጠቁመው አስተምህሮ የእግዚአብሔርን ቀን ፍርሃት በእጅጉ ወደ ፊት አሽቀንጥሮ፣ አርቆ የሚገፋ ነው። አስደሳች ሊሆን ቢችል እንኳ መከሩ እስኪደርስ፣ የዓለም መጨረሻ እስኪሆን ድረስ፣ ስንዴውና እንክርዳዱ አንድ ላይ እንደሚያድጉ ክርስቶስና ሐዋርያቱ ካስተማሩት ጋር የሚቃረን ነው። [ማቴ 13÷30፣ 38-41]። “ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች እየሳቱና እያሳቱ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ” [2ኛ ጢሞ 3÷13፣1] “በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህንን እወቅ” [2ኛ ጢሞ 3÷13] እንደሚል፣ የጨለማ መንግሥት ጌታ እስኪመጣ ድረስ እንደሚቀጥልና ከአፉ በሚወጣው መንፈስ እንደሚጠፋ፣ በመገለጡም ብርሐን እንደሚሻር [ክርስቶስና ሐዋርያቱ] አስተምረዋል [2ኛ ተሰሎ 2÷8]። የዓለም መለወጥና የክርስቶስ መንፈሳዊ ግዛት አስተምህሮ በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም። እስከ አሥራ ስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ በአብዛኛው በክርስቲያኖች ተቀባይነት አላገኘም ነበር። እንደሌላው ስህተት ሁሉ የዚህም ውጤት ክፋት ነበር። ሰዎች የጌታን ምፅዓት ወደ ፊት አርቀው እንዲመለከቱ፣ ምፅዓቱ ለመቃረቡም ጠቋሚ ይሆኑ ዘንድ ለተሰጡት ምልክቶች ትኩረት እንዳይሰጡ የሚያስተምር ነበር። ጽኑ መሰረት የሌላቸውን፣ ልበ ሙሉነትና ደህንነት እንዲሰማቸው በማድረግ ጌታቸውን ይገናኙ ዘንድ አስፈላጊ የሆነውን መዘጋጀት ከማድረግ የሚያዘናጋቸው ነው።GCAmh 235.3

    ሚለር የክርስቶስ በአካል መገለጥ ትምህርትን ቃል በቃል፣ በግልጽ ሁኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ አገኘው። ጳውሎስ እንዲህ አለ፦ “ጌታ ራሱ በትዕዛዝ በመላዕክትም አለቃ ድምጽ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና” [1ኛ ተሰሎ 4÷16]። አዳኙ ደግሞ “የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል” “መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና” [ማቴ 24÷30፣27] ብሏል። በሰማይ ሰራዊት ሁሉ ይታጀባል። “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላዕክቱ ሁሉ” መላዕክቱንም “ከታላቅ መለከት ድምጽ ጋር ይልካቸዋል… ለእርሱም የተመረጡትን ይሰበስባሉ’” [ማቴ 25÷31፤ 24÷31]።GCAmh 236.1

    በመምጣቱም የሞቱ ፃድቃን ይነሳሉ፤ በሕይወት ያሉትም ይለወጣሉ፤ “ሁላችንም አናንቀላፋም” ይላል ጳውሎስ “የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችንም በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሳሉ፤ እኛም እንለወጣለን። ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና” [1ኛ ቆሮ 15÷51-53]። በተሰሎንቄ ደብዳቤውም የጌታን ምፅዓት ከገለፀ በኋላ “በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሳሉ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።” ይላል [1ኛ ተሰሎ 4÷16፣17]።GCAmh 236.2

    ከክርስቶስ አካላዊ መገለጥ በፊት ሕዝቦቹ መንግሥቱን አይቀበሉም። አዳኙ እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላዕክቱ ሁሉ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል። በጎቹን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ብሩካን ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” [ማቴ 25÷31-34]። እዚህ ላይ በተሰጡት ጥቅሶች እንደምናስተውለው የሰው ልጅ ሲመጣ የሞቱት የማይሞተውን ለብሰው ይነሳሉ፤ ሕያዋንም ይለወጣሉ። በዚህም ታላቅ ለውጥ መንግሥቱን ለመቀበል ይዘጋጃሉ፤ ጳውሎስ ይላልና፦ “ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም” [1ኛ ቆሮ 15÷50]። ሰው አሁን ባለው ሁኔታው ሟችና በስባሽ ነው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ግን የማትበሰብስና ለዘላለም የምትፀና ናት፤ ስለሆነም የሰው ልጅ አሁን ባለው ይዘቱ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባ ዘንድ አይቻለውም። የሱስ ሲመጣ ግን ዘላለማዊነትን በሕዝቦቹ ላይ ያደርጋል፤ ከዚያም ይጠራቸውና እስካሁን ወራሾች ብቻ ተብለው የተጠሩበትን መንግሥት ያወርሳቸዋል።GCAmh 236.3

    ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት ይፈፀማሉ ተብለው በአጠቃላይ ይታመንባቸው የነበሩ፣ እንደ ዓለም አቀፍ የሰላም መንግሥት፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ላይ እንደ መመስረት ያሉ ክስተቶች ከዳግም ምፅዓት በኋላ የሚመጡ ክንውኖች እንደሆኑ እነዚህና የመሳሰሉት ጥቅሶች ለሚለር አዕምሮ ግልጽ አደረጉለት። በተጨማሪም የዘመኑ ምልክቶችና የዓለም ሁኔታ ሁሉ ከመጨረሻዎቹ ቀናት ትንቢታዊ አገላለጽ ጋር የተስማሙ ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ብቻ ምድር ባለችበት ሁኔታ እንድትቀጥል የተወሰነላት ጊዜ ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ነው ወደሚለው ድምዳሜ እንዲደርስ ተገደደ።GCAmh 237.1

    “ሌላው አዕምሮዬን በጣም የነካኝ ማስረጃ” አለ ሲናገር፣ “የመጽሐፍ ቅዱስ ቅደም ተከተል” ነበር። ተተንብየው ከአሁን በፊት ፍጻሜ ያገኙ ክስተቶች በተወሰኑ ጊዜያት ውስጥ የተከናወኑ እንደሆኑ ማወቅ ቻልሁ። እስከ የጥፋት ውኃ የነበረው መቶ ሃያ አመት፣ [ዘፍ 6÷3]፤ የአርባ ቀኑ የዝናብ ትንበያና ከጥፋት ውሃ በፊት የነበሩት ሰባት ቀናት፣ [ዘፍ 7÷ 4]፤ የአብርሃም ዘር በእንግድነት የሚኖርበት አራት መቶ ዓመታት፣ [ዘፍ 15÷13]፤ የጠጅ አሳላፊውና የእንጀራ አበዛው የሶስት ቀናት ህልሞች፣ [ዘፍ 40÷12-20]፤ የፈርኦን ሰባቱ ዓመታት፣ [ዘፍ 41÷28-54]፣ አርባ አመት በበረሃ፤ [ዘሁል 14÷34]፤ የሶስት ዓመት ተኩል ረሃብ፣ [1ኛ ነገስት 17÷1]፤ [ሉቃስ 4÷25ንም ይመልከቱ]፤ የሰባ አመቱ ምርኮኛነት፣ [ኤር 25÷11]፤ የናቡከደናፆር ሰባቱ ዘመናት፣ [ዳን 4÷13-16]፤ ሰባቱ ሳምንታት፣ ስድሳና ሁለቱ ሳምንታት፣ እንዲሁም አንዱ ሳምንት በአይሁዳዊያን ላይ የተወሰኑት በአጠቃላይ ሰባዎቹ ሳምንታት፣ [ዳን 9÷24-27]፤ በእነዚህ ዘመናት የተወሰኑት ክስተቶች ሁሉ፣ በአንድ ወቅት ትንቢት ብቻ ነበሩ። ከዚያም እንደ ትንቢታቸው ፍፃሜ አገኙ።-Bliss, ገጽ 74, 75።GCAmh 237.2

    ስለዚህ፣ እንደ እርሱ ማስተዋል፣ መጽሐፍን በሚያጠናበት ጊዜ እስከ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ድረስ የሚዘልቁ በቅደም ተከተል የሚፈፀሙ የተለያዩ ዘመናት እንዳሉ ሲገባው እግዚአብሔር ለባሪያዎቹ የገለጠላቸው “የተወሰኑት ዘመኖች” ከመሆናቸው ውጪ ሌላ ትርጉም እንደሌላቸው አድርጎ ተቀበላቸው። “ምስጢሩ”፣ አለ ሙሴ፣ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው” [ዘዳግ 29÷29]። እግዚአብሔር በነብዩ አሞጽ በኩል ሲናገር “ጌታ ምስጢሩን ለባሪያዎቹ ለነብያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም” [አሞፅ 3÷7]። ስለዚህም የእግዚአብሔር ቃል ተማሪዎች፣ በሰው ልጅ ታሪክ ሊፈፀሙ ያላቸውን አስደናቂ ክስተቶች በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በግልጽ ተጠቁመው እንደሚገኙ በልበ ሙሉነት፣ በእርግጠኛነት መጠበቅ ይችላሉ።GCAmh 237.3

    “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ … የሚጠቅም” [2ኛ ጢሞ 3÷16] እንደሆነ “ሙሉ በሙሉ ሳምን” ይላል ሚለር፤ “በማንኛውም ጊዜ በሰው ፈቃድ የመጣ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ በተነሳሱ ቅዱሳን ሰዎች መምጣቱን [2ኛ ጴጥ 1÷21] “መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናትና ተስፋ ይሆንልን ዘንድ ለትምህርታችን” [ሮሜ 15÷4] መፃፉን ስረዳ ክስተቶችን በቅደም ተከተል የሚያስቀምጡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፣ ልክ እንደሌሎቹ የመጽሐፍ ክፍሎች ሁሉ የእኛ ጥልቅ ትኩረት የሚያሻቸው እንደሆኑ ከመቀበል መታቀብ አልቻልኩም። በመሆኑም እግዚአብሔር በምህረቱ ይገልጥልን ዘንድ ተገቢ ሆኖ ያገኘውን ለመረዳት በሚደረገው ጽኑ ትግል የትንቢት ዘመናትን አድበስብሶ የማለፍ መብት እንደሌለኝ ተሰማኝ።”-Bliss, ገጽ 75።GCAmh 237.4

    የዳግም ምፅዓትን ዘመን በበለጠ የገለጸው የመሰለው ትንቢት ዳን 8÷14 ነበር፦ “እስከ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ማታና ጠዋት ድረስ ነው ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነፃል።” መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ ማብራሪያ ሰጭ እንደሆነ ተቀብሎ ያወጣውን ሕግ በመከተል አንድ ቀን በትንቢታዊ አገላለጽ አንድ አመትን እንደሚወክል ተረዳ፤ [ዘሁል 14÷34፤ ሕዝ 4÷6]፤ የ2300 ትንቢታዊ ቀናት ወይም በትርጓሜው መሰረት ዓመታት፣ ከአይሁዳዊያን ተላልፎ ከተሰጠው ዘመን እርቆ የሚያልፍ እንደሆነ በመረዳት ስለዚያ የቤተ መቅደስ ሥርዓት እንደማያወራ ተረዳ። ሚለር በክርስትናው ዓለም በስፋት የሚታመነውን ምድር ቤተ መቅደስ ናት የሚለውን የክርስቲያን እይታ በመቀበል በዳንኤል 8÷14 የተነገረው የቤተ መቅደስ መንፃት የሚወክለው በክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ምድር በእሳት የምትፀዳበትን ክስተት ነው በማለት ተቀበለ። ያ ከሆነ ደግሞ ለ2300 ቀናት ትክክለኛው መጀመሪያ ከተገኘ፣ የዳግም ምፅዓት ዘመን በእርግጠኛነት መታወቅ ይችላል ብሎ ደመደመ። ስለዚህ ያ ታላቁ የፍፃሜ ቀን ዘመን ሊታወቅ ይችላል፤ “የወቅቱ ክስተት ከኩራቱ፣ ከኃይሉ፣ ከልታይ ልታይ ባይነቱና ከከንቱነቱ፣ ከክፋተኛነቱና ከጭቆናው ጋር ወደ ፍፃሜ የሚመጣበት…. እርግማን ከምድር የሚነሳበት፣ ሞት የሚገረሰስበት፣ ለነብያትና ለቅዱሳን እንዲሁም ስሙን ለሚፈሩ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁሉ ሽልማት የሚበረከትበት፣ ምድርን ያጠፏት የሚወድሙበት” ያ ቀን ሊታወቅ ይችላል።-Bliss, ገጽ 76።GCAmh 238.1

    በአዲስና በበለጠ ጥልቅ ፍላጎት፣ አሁን እጅግ አስፈላጊና አሳብን ሁሉ የሚሰርቀውን ጉዳይ ለማጥናት ቀኑንና ሌሊቱን ሁሉ በመጠቀም ሚለር ትንቢታትን መመርመር ተያያዘው። በዳንኤል ስምንተኛው ምዕራፍ ውስጥ የ2300 ቀናት መጀመሪያ መቼ እንደሆነ ፍንጭ ማግኘት አልቻለም፤ መልአኩ ገብርኤል ዳንኤል ህልሙን ያስተውለው ዘንድ እንዲረዳው ቢታዘዝም፣ የሰጠው ግን የከፊል ማብራሪያ ነበር። በቤተ ክርስቲያንዋ ላይ የሚመጣው አሰቃቂ ስደት ለነብዩ በራዕይ ሲገለጽ አካላዊ ጥንካሬው ከዳው። ያንን መሸከም አልተቻለውምና መልአኩ ለተወሰነ ጊዜ ተወው፤ “ተኛሁ አያሌም ቀን ታመምሁ”፤ “ስለ ራዕዩም እደነቅ ነበር”፣ ይላል፣ “የሚያስተውለው ግን አልነበረም።” [ዳን 8÷27]።GCAmh 238.2

    ሆኖም እግዚአብሔር መልዕክተኛውን አዘዘ፣ “ራዕዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው” [ዳን 8÷16]፤ ተልዕኮው መፈፀም አለበት። ትዕዛዙን ተቀብሎ መልአኩ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ዳንኤል ተመልሶ “ጥበብና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ”፤ “አሁንም ነገሩን መርምር፣ ራዕዩንም አስተውል” [ዳን 9÷22-23፣ 25-27]። በምዕራፍ ስምንት ራዕይ ውስጥ ሳይብራራ የቀረ ነጥብ አንድ ብቻ ነበር። እርሱም ጊዜን በተመለከተ ማለትም የ2300 ቀናት ክፍለ-ጊዜ ጉዳይ ነበር፤ ስለዚህም መልአኩ ማብራራቱን በመቀጠል በጊዜ ጉዳይ ብቻ አተኮረ፦GCAmh 238.3

    “በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባኤ ተቆጥሮአል.… ስለዚህ እወቅ አስተውልም የሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትዕዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሲሁ ድረስ ሰባት ሱባኤና ስድሳ ሁለት ሱባኤ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሰራለች። ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሲህ ይገደላል፤ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም… እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባኤ ያፀናል፤ በሱባኤውም እኩሌታ መስዋዕቱንና ቁርባኑን ያስቀራል።” [ዳን 9÷25-27]።GCAmh 239.1

    መልአኩ ወደ ዳንኤል ተልኮ የነበረው በስምንተኛው ምዕራፍ ያየውንና ሊረዳው ያልቻለውን ነጥብ ያስረዳው ዘንድ ግልጽ አላማ ይዞ ነበር፤ እርሱም ዘመንን (ጊዜን) የተመለከተ ነበር— “እስከ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ማታና ጠዋት ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነፃል” [ዳን 8÷14]። “አሁንም ነገሩን መርምር ራዕዩንም አስተውል” [ዳን 9÷23] በማለት ዳንኤልን ከተናገረው በኋላ የመጀመሪያዎቹ የመልአኩ ቃላት “በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባኤ ተቀጥሮአል” የሚሉ ነበሩ። ከዚህ ላይ “ተቀጥሮአል” ተብሎ የተተረጎመው ቃል፣ ቃል በቃል የሚያመላክተው “ይገደላል [ይቆረጣል]” የሚለውን ነው። 490 ዓመታትን የሚወክሉት ሰባዎቹ ሳምንታት በተለይ ከአይሁዳዊያን ጋር በተያያዘ እንደተቆረጡ በመልአኩ ተናግሯል። ሆኖም ከምን ነበር የተቆረጡት? በምዕራፍ ስምንት የተጠቀሰው ብቸኛ የጊዜ ቀመር 2300ዎቹ ቀናት ስለሆነ የሰባ ሳምንታቱ የተቆረጡበት ዘመን መሆን አለበት፤ ስለዚህ ሰባዎቹ ሳምንታት የ2300 ቀናት አካል መሆን አለባቸው፤ በመሆኑም ሁለቱ ዘመናት አንድ ላይ ነው የሚጀምሩት ማለት ነው። ሰባዎቹ ሳምንታት የሚጀምሩት የሩሳሌምን ለመጠገንና ለመሥራት ትዕዛዙ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ እንደሆነ መልአኩ ተናግሯል። ይህ ትዕዛዝ የተላለፈበት ጊዜ መታወቅ ከቻለ ታላቁ የ2300 ቀናት ዘመን መጀመሪያ ቀመር በእርግጠኛነት ይታወቃል ማለት ነው።GCAmh 239.2

    አዋጁ በእዝራ መጽሐፍ ሰባተኛው ምዕራፍ ውስጥ ይገኛል [እዝራ 7÷12-26]። ይህ አዋጅ ምንም ሳይሸራረፍ በሙሉነቱ የወጣው፣ በአርጤክስስ፣ በፋርስ ንጉሥ በ457 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነበር። በእዝራ 6÷14 ግን በየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት “እንደ ፋርስም ነገሥታት እንደ ቂሮስና እንደ ዳርዮስ እንደ አርጤክስስም ትዕዛዝ [አዋጅ]” እንደ ተሰራ ተገልጿል። አዋጁን በማመንጨት እንደገና በማረጋገጥና በመፈፀም እነዚህ ሶስት ነገሥታት 2300ቹ ዓመታት የሚጀምሩበትን ምልክት ትንቢቱ በሚጠቁመው መስፈርት የተሟላ ያደርጉታል። ከክርስቶስ ልደት በፊት 457 ዓመተ ዓለም አዋጁ የተፈፀመበት፣ የትዕዛዙ ዘመን ተደርጎ ሲወሰድ፣ ሰባ ሳምንታቱን በተመለከተ የተነገረው ትንቢት እያንዳንዱ ዝርዝር ፍፃሜ ማግኘቱን ያሳያል።GCAmh 239.3

    “የሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትዕዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሲህ ድረስ ሰባት ሱባኤና ስድሳ ሁለት ሱባኤ ይሆናል።” ማለትም ስድሳ ዘጠኝ ሳምንታት ወይም 483 ዓመታት ነው። የአርጤክስስ አዋጅ ተግባራዊ የሆነው ከክ. ል. በፊት በ457 ዓ.ዓ. የመከር ወቅት ነበር። ከዚህ ቀን በመነሳት 483 ዓመታት ሲጨመሩ ከክርስቶስ ልደት በኋላ እስከ 27 ዓ.ም የመከር ወቅት ይደርሳሉ። [በመግለጫ ስር ማስታወሻ 3ን ይመልከቱ] በዚያን ጊዜ ይህ ትንቢት ተፈፀመ። “መሲህ” የሚለው ቃል የሚወክለው “የተቀባው”ን ነው። በ27 ዓ.ም. መከር ወቅት ክርስቶስ በዮሐንስ ተጠመቀ። የመንፈስን መቀባትም ተቀበለ። ሐዋርያው ጴጥሮስ ሲመሰክር፦ “እግዚአብሔር የናዝሬቱን የሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው” አለ [የሐዋ ሥራ 10÷38]። አዳኙ ራሱ ሲናገር፦ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና” ብሏል [ሉቃ 4÷18]። ከጥምቀቱ በኋላም “የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና፦ ዘመኑ ተፈፀመ” እያለ ወደ ገሊላ መጣ [ማር 1÷14-15]።GCAmh 239.4

    “እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባኤ ያደርጋል” [ዳን 9÷27]። “ሱባኤ” ተብሎ እዚህ የተገለፀው የሰባዎቹ ሳምንታት የመጨረሻው ነው።በተለየ ሁኔታ ለአይሁዳዊያን የተሰጡት የመጨረሻዎቹ ሰባት ዓመታት ናቸው። ከ27 ዓ.ም እስከ 34 ዓ.ም. በሚዘልቀው በዚህ ዘመን መጀመሪያ ክርስቶስ ራሱ በአካል በኋላም በደቀ መዛሙርቱ አማካኝነት የወንጌሉን ጥሪ በተለይ ለአይሁዳዊያን ያቀረበበት ጊዜ ነበር። የመንግሥቱን መልካም የምሥራች ይዘው ደቀ መዛሙርቱ በሚወጡበት ጊዜ፣ የአዳኙ ትዕዛዝ፦ “በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ ወደ ሳምራዊያንም ከተማ አትግቡ። ይልቅስ የእሥራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ” [ማቴ 10÷5፣6] የሚል ነበር።GCAmh 240.1

    “በሱባኤውም እኩሌታ መስዋዕቱንና ቁርባኑን ያስቀራል” [ዳን 9÷27]። በ31 ዓ.ም ማለትም ከተጠመቀ ከሶስት ዓመት ተኩል በኋላ ጌታችን ተሰቀለ። ቀራንዮ ላይ በተፈፀመው በዚህ ታላቅ መስዋዕት ምክንያት ለአለፉት አራት ሺህ ዓመታት ስለ እግዚአብሔር በግ ሲያመለክት የነበረው የመስዋዕት ሥርዓት አበቃ። ተወካይና ወካይ(አካልና ጥላ) ተገኛኙ፤ የስነሥርዓቱ አካል የነበሩት ሁሉም መስዋዕቶችና ቁርባኖች ከዚያ በኋላ መቆም ነበረባቸው። በተለየ ሁኔታ ለአይሁዳዊያን የታደሉት ሰባ ሳምንታት ወይም 490 ዓመታት እንዳየነው በ34 ዓ.ም አብቅተዋል። በአይሁዳዊያን ሸንጎ (the sanhedrin) ተግባር አማካኝነት በእስጢፋኖስ መስዋዕትነትና የክርስቶስን ተከታዮች በማሳደድ፣ እሥራኤል ወንጌሉን አሻፈረኝ ማለትዋን በተግባር አተመች። ከዚያም የድነት መልእክቱ በተመረጡት ሕዝቦች ብቻ ከእንግዲህ ላይወሰን ለዓለም ተሰጠ። በስደት ምክንያት ከየሩሳሌም እንዲወጡ የተገደዱት ደቀ መዛሙርቱ “ቃሉን እየሰበኩ ዞሩ።” “ፊሊጶስም ወደ ሰማርያ ከተማ ወርዶ ክርስቶስን ሰበከላቸው” [የሐዋ ሥራ 8÷4፣5፤ 22÷21]። ጴጥሮስ በመለኮት ምሪት ፈሪሃ-እግዚአብሔር ለነበረው ለቄሳርያው መቶ አለቃ ለቆርኔሊዎስ ወንጌልን ከፈተለት። ወደ ክርስቶስ የተማረከው ጽኑው ጳውሎስ፣ “ወደ አሕዛብ ከዚህ ወደ ሩቅ” [የሐዋ ሥራ 22÷21] ሂዶ የምሥራቹን ይሰብክ ዘንድ ተልዕኮ ተሰጠው።GCAmh 240.2

    እስከዚህ ድረስ እያንዳንዱ ትንቢት በሚያስገርም ሁኔታ ተፈጽሞአል፤ የሰባው ሳምንታት መጀመሪያም ጥያቄ በማያስነሳ ሁኔታ ከክ. ል. በፊት 457 ዓ.ዓ ማብቂያውም በ34 ዓ.ም እንደሆነ ተረጋግጧል። ከዚህ መረጃ በመነሳት 2300 ቀናት የሚያልቁበትን ዘመን ማወቅ ከባድ አይደለም። ሰባ ሳምንታቱ ማለትም 490ዎቹ ቀናት ከ2300 ቀናት ተቀንሰው የሚቀረው 1810 ቀናት ነበሩ። 490 ቀናቱ ካለቁ በኋላ 1810 ቀናቱ ገና ፍፃሜ ማግኘት ያለባቸው ዘመናት ነበሩ። ከ34 ዓ.ም ጀምሮ 1810 ዓመታት ሲጨመሩ ወደ 1844 ዓ.ም ያመጣናል። በመሆኑም የዳንኤል 8÷14ቶቹ 2300 ቀናት በ1844 ያበቃሉ። ከዚህ ታላቅ ትንቢታዊ ዘመን ማለቅ በኋላ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ምስክርነት “መቅደሱ ይነፃል”፤ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ተቀባይነት አግኝቶ የነበረው፣ በዳግም ምፅዓት ጊዜ የሚከናወነው የመቅደሱ መንፃት ዘመን መቼ እንደሆነ ታወቀ።GCAmh 240.3

    በመጀመሪያ ሚለርና ጓዶቹ የ2300 ቀናት መጨረሻ 1844 ፀደይ ወቅት እንደሆነ ቢያምኑም ትንቢት ግን የጠቆመው የዚያ ዓመት መከር እንደሆነ ነበር [በመግለጫ ስር ማስታወሻ 3ን ይመልከቱ]። የዚህ ነጥብ የተሳሳተ መረዳት የፊተኛው ቀን (ፀደዩ) የጌታ መምጫ እንደሆነ አድርገው ለተቀበሉ ግራ መጋባትንና ሀዘንን አምጥቶባቸዋል። ሆኖም ይህ ክስተት የ2300 ቀናት ማብቂያ 1844 ዓ.ም እንደሆነ የሚናገረውን ክርክር ጥንካሬ ቅንጣት ታክል የሚያሰንፈው ባለመሆኑ የመቅደሱ መንጻት ታላቅ ክስተትም እንዲሁ መፈፀም ይኖርበታል።GCAmh 241.1

    ሁሌም እንደሚደረገው ሁሉ ከእግዚአብሔር የመጡ መገለጦች እንደሆኑ ያረጋግጥ ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት የቀጠለው ሚለር ጥናቱን ሲጀምር አሁን ከደረሰበት መደምደሚያ እደርሳለሁ የሚል ቅንጣት ታክል ግምት አልነበረውም። የምርምሩ ውጤት ምን እንደሆነ ለራሱ እንኳ ግምት መስጠት አልቻለም። የመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ግን ወደ ጎን ይገፈትረው ዘንድ የማይቻል ግልጽና አሳማኝ ነበር።GCAmh 241.2

    ሚለር፣ ሁለት ዓመታትን ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዳዋለ፣ በ1818 ዓ.ም፣ ሕዝቦቹን ይቤዥ ዘንድ ከሃያ አምስት ዓመታት ገደማ በኋላ ክርስቶስ ይገለፃል ወደሚለው ጠንካራ እምነት ላይ ደረሰ። “እጅግ በሚያስፈነድቀው ክስተት ልቤን የሞላውን ደስታ፣ በተዋጁት ደስታ ለመሳተፍ ነፍሴ ያላትን ጽኑ ምኞት መናገር አያስፈልገኝም” አለ ሚለር። “አሁን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ለእኔ አዲስ መጽሐፍ ሆነልኝ። በእርገጥም የአመክንዮ ድግስ ሆነልኝ። ጨለማ፣ ረቂቅ ወይም ስውር የሆነብኝ ሁሉ አሁን ከቅዱስ ገፆቹ ከወረደው ግልጽ የብርሐን ወጋገን የተነሳ ጠፋ። እናም እንዴት ግልጽና ውብ በሆነ መልኩ እውነት እንደታየኝ! ቀደም ሲል በቃሉ ውስጥ ያገኘኋቸው መጣረሶችና ወጥነት ማጣት በሙሉ ተወገዱ። ገና ሙሉ በሙሉ መረዳት የለኝም ብዬ የፈረጅኳቸው ብዙ ክፍሎች ቢኖሩም አያሌ ብርሐን ወጥቶ በፊት ጨለማ የሆነውን አእምሮዬን በማብራቱ፤ እንዲህ በማድረጌ ከትምህርቱ የተነሳ ይገኛል ብዬ አስቤው የማላውቀውን ደስታ መጽሐፉን በማጥናቴ አገኘሁ።”-Bliss, ገጽ 76, 77።GCAmh 241.3

    “እነዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ የተተነበዩ እጅግ አስፈላጊ ክስተቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊፈፀሙ እንዳላቸው ከምር በማመኔ የራሴን አዕምሮ እጅግ የነካውን ይህንን መረጃ በተመለከተ ለዓለም ያለብኝ ኃላፊነት በታላቅ ኃይል ወደቀብኝ።”-Ibid., ገጽ 81። የተቀበለውን ብርሐን ለሌሎች የማካፈል ኃላፊነት እንዳለበት የሚሰማውን ስሜት ማስቆም አልቻለም። ከከሃዲዎች ተቃውሞ እንደሚገጥመው ጠብቋል። እንደሚወዱት የሚመሰክሩለትን አዳኝ ለመገናኘት ባለው ተስፋ ግን ክርስቲያኖች እንደሚደሰቱ እርግጠኛ ነበር። ብቸኛው ፍራቻው የነበረው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊፈፀም ያለው ታላቅ የመዳን ክስተት በሚፈጥረው ታላቅ ደስታ ተሸንፈው፣ እውነቱን በተግባር የሚያረጋግጠውን መጽሐፍ ቅዱስ በበቂ ሁኔታ ሳይመረምሩ አስተምህሮውን ይቀበላሉ የሚል ነበር። ስለዚህም ስህተት መሥራትን ፈርቶ ሌሎችንም ወደ ተሳሳተ መንገድ እንዳይመራ ሰግቶ ይህንን እውነት ለመናገር አመነታ። የደረሰበትን መደምደሚያ የሚደግፉለትን ማስረጃዎች እንደገና ለመከለስ ተገፋፋ። ያስቸገረውን እያንዳንዱን ነጥብ በጥንቃቄ ለመመርመር ወሰነ። ጭጋግ በፀሐይ ጨረር ፊት እንደሚጠፋ ተቃውሞዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ብርሐን ፊት እልም እንደሚሉ ተረዳ። እዚህ ለመድረስ ከወሰደበት ከአምስት ዓመት በኋላም በአቋሙ ትክክለኛነት ሙሉ በሙሉ አመነ።-Bliss, ገጽ 92።GCAmh 241.4

    እናም አሁን በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የተሰጠ ትምህርት መሆኑን ያመነውና ለሌሎች የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለበት የገባው እውነት በትኩስ ኃይል ያነሳሳው ጀመር። “ሥራዬን በምሰራበት ጊዜ” ይላል፣ ” ያለማቋረጥ በጆሮዬ ያቃጭል ነበር፣ ለዓለም የተጋረጠበትን አደጋ ሂድ ንገር።” ይህ ጥቅስ ያለማቋረጥ ይመጣብኝ ነበር፦ “ኃጢአተኛውን፦ ኃጢአተኛ ሆይ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፣ ደሙን ግን ከአንተ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ከመንገዱ ይመለስ ዘንድ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ በኃጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል” [ሕዝ 33÷8-9]። ኃጢአተኞች በተሳካ ሁኔታ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸው እልፍ አዕላፋት ንስሐ እንደሚገቡ ይሰማኝ ነበር። ማስጠንቀቂያው ባይደርሳቸው ግን ደማቸው ከእጄ የሚጠየቅ መሰለኝ።”GCAmh 242.1

    አንድ የሆነ አገልጋይ ሰምቶ፣ ኃይላቸውን ተገንዝቦ፣ ያውጃቸው ዘንድ ራሱን አሳልፎ ይሰጣል ብሎ ለገመተው ሁሉ፣ በመፀለይ፣ ዕድል ባገኘ ቁጥር አቋሙን በግል ማቅረብ ጀመረ። ማስጠንቀቂያውን በመናገር ረገድ ግን ራሱ ኃላፊነት እንዳለበት ያመነበትን፣ የሚሰማውን ስሜት ዝም ማስባል አልቻለም። ቃላቱ እየተደጋገሙ ወደ አዕምሮው ይመጡ ነበር፦ “ሂድና ለዓለም ንገር፣ ደማቸውን ከእጅህ እሻለሁ።” ለመጀመሪያ ጊዜ በ1831 ዓ.ም በአደባባይ የእምነቱን ምክንያቶች እስከተናገረበት ጊዜ ድረስ ጭነቱ ነፍሱን እያስጨነቀው ለዘጠኝ ዓመታት ጠበቀ።GCAmh 242.2

    የነብይነትን ሥራ ያከናውን ዘንድ የመለየት በርኖስ ተቀብሎ በሬዎቹን ከመከተል እንደተጠራው እንደ ኤልሳዕ፣ ዊልያም ሚለርም እርሻውን ትቶ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምስጢራት ለሕዝቡ ይገልጥ ዘንድ ተጠራ። በመንቀጥቀጥ ወደሥራው በመግባት ከትንቢት ዘመናት ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ዳግም መገለጥ ድረስ አድማጮቹን ደረጃ በደረጃ መራቸው። በንግግሩ የመጣውን ሰፊ የፍላጎት መነቃቃት በማየት በእያንዳንዱ ጥረቱ ብርታትና ድፍረት እያተረፈ ሄደ።GCAmh 242.3

    ሚለር ሃሳቡን በአደባባይ ለመግለጽ የተስማማው የእግዚአብሔር ጥሪ እንደተደረገለት በነገሩት ወንድሞቹ ልመና ብቻ ነበር። አሁን ሃምሳ አመቱ ነው፤ በሕዝብ ፊት የመናገር ልምድ የለውም፤ በፊቱ ስላለው ሥራ ገጣሚ ያለመሆኑ ስሜት ሸክም ከብዶታል። ሆኖም ከጅምሩ ነፍሳትን የማዳን ጥረቶቹ በአስደናቂ ሁኔታ ተባርከው ነበር። በመጀመሪያ ትምህርቱ የኃይማኖት መነቃቃትን በመፍጠር ሁለት ሰዎች ሲቀሩ በቀር ሰላሳ ቤተሰብ በሞላ ተለወጡ። በሌላ ስፍራዎችም እንዲናገር ወዲያውኑ ተገፋፋ፤ በሄደበት ስፍራ ሁሉ ማለት ይቻላል ጥረቱ የእግዚአብሔር ሥራ መነቃቃትን አመጣ። ኃጢአተኞች ተለወጡ፤ ክርስቲያኖችም ወደ በለጠ ቅድስና አደጉ፤ ደይስቶች (በሰው አመክንዮ የሚምኑ/deists) እና ከሃዲዎች ለመጽሐፍ ቅዱስና ለክርስትና ኃይማኖት እውነት እውቅና እንዲሰጡ ተመሩ። ጥረት ያደርግባቸው ከነበሩት መካከል የተሰጠው ምስክርነት፦ “በሌሎች ሰዎች ተጽዕኖ ክበብ ውስጥ ያልሆኑ መደቦችን መድረስ ይቻላል።” “ትምህርቱ የሕዝቡን አዕምሮ ወደ ኃይማኖት ታላላቅ ጉዳዮች እንዲነሳሳ የሚያስችል ሆኖ የተዘጋጀ፣ እያደገ ያለውን ዓለማዊነትና የዘመኑን ፍትዎታዊነት እንዲያስቆም ሆኖ የታሰበ ነበር።” ይላል።GCAmh 242.4

    በእያንዳንዱ ከተማ ማለት ይቻላል በአስሮች፣ በአንዳንዶቹ ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከትምህርቱ የተነሳ ተለወጡ። በብዙ ቦታዎች ሁሉም የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት (denominations) ማለት በሚባል ደረጃ ክፍት ሆኑለት፤ ያስተምራቸው ዘንድ የሚመጣለት ግብዣም ሁልጊዜ ብዙ የምዕመናንን ጉባኤዎች ከሚመሩ አገልጋዮች ነበር። ባልተጋበዘበት ቦታ ላለመሥራት ያስቀመጠው፣ የራሱ የሆነ የማይቀር ሕግ ነበረው፤ ሆኖም ብዙም ሳይቆይ የሚጎርፈውን የአስተምረን መጠይቅ ግማሹንም ማስተናገድ አልቻለም።GCAmh 243.1

    የዳግም ምፅዓቱን እቅጩን ጊዜ በተመለከተ እርሱ የያዘውን አቋም የማይቀበሉ ሰዎችም እንኳ ስለ ክርስቶስ መምጣት እርግጠኛነትና ጊዜውም ስለመቅረቡ ብሎም መዘጋጀት እንደሚያስፈልጋቸው አምነው ነበር። በተወሰኑት ትላልቅ ከተሞች ሥራው የሚስተዋል ተጽዕኖ ፈጠረ። አልኮል ሻጮች ሥራቸውን አቁመው ሱቆቻቸውን ወደ የስብሰባ ክፍሎች ቀየሯቸው። የቁማር ዋሻዎች ተደረመሱ፤ ከሃዲዎች፣ደይስቶች፣ ዩኒቨርሳሊስቶች (universalists)፣ እጅግ የተናቁ ሴሰኞች — ከመካከላቸው ለብዙ ዓመታት የአምልኮ ቦታ ውስጥ ገብተው የማያውቁ — ሁሉ ተለወጡ። በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የፀሎት ስብሰባዎች ተቋቋሙ፣ በተለያዩ ስፍራዎች በየሰዓቱ ማለት ይቻላል የሆነ ቦታ የፀሎት ጊዜ ነበር፤ የንግድ ሰዎች በእኩለ ቀን ለፀሎትና ለምስጋና ይሰበሰቡ ነበር። ብክነት የሚታይበት መቅበጥበጥ አልነበረም፤ የሰከነ መንፈስ በሰዎች ሁሉ አዕምሮ ይንፀባረቅ ነበር። የእርሱ ሥራ ልክ እንደ ቀድሞዎቹ የተሐድሶ አራማጆች ሁሉ፣ እንዲያው ዝም ብሎ ስሜትን የማነሳሳት ነገር ሳይሆን በሚያሳምን ሁኔታ እንዲረዱት የማድረግና ህሊናቸውን የማነሳሳት ሥራ ያከናውን ነበር።GCAmh 243.2

    በ1833 ዓ.ም ሚለር አባል የነበረበት የባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን የመስበክ ፈቃድ ሰጠው። የቤተ ክርስቲያኒቱ ብዛት ያላቸው አገልጋዮችም ሥራውን አፀደቁለት፤ እናም ሥራው የቀጠለው በእነርሱ ሙሉ እውቅናና ፈቃድ ነበር።GCAmh 243.3

    ጥረቶቹ በዋናነት በኒው ኢንግላንድና በመካከለኛ ግዛቶች የተወሰኑ ቢሆንም ጉዞውንና መስበኩን ያለማቋረጥ ቀጠለ። ለብዙ ዓመታት፣ ወጪውን የሚሸፍነው ሙሉ በሙሉ ከራሱ ኪስ ከሚወጣ ገንዘብ ነበር፤ ከዚያ በኋላም ወደ ተጋበዘባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለመድረስ በቂ የሆነ ገንዘብ ተሰጥቶት አያውቅም ነበር። በመሆኑም ምንም አይነት የገንዘብ ጥቅም የማያገኝባቸው ሕዝባዊ አገልግሎቶች በንብረቱ ላይ ከባድ የወጪ ጫና በመፍጠራቸው በዚህ ምድር ሕይወት የነበረው ጥሪት ቀስ በቀስ እየተመናመነ ሄደ። በርካታ ቁጥር ያለው ቤተሰብ አባት ነበር፤ ሆኖም የቤተሰቡ አባላት በሙሉ ገንዘብ ቆጣቢና ታታሪ ስለነበሩ፣ ከእርሻው የሚገኘው ምርት ለቤተሰቡም ሆነ ለእርሱ የሚበቃ ነበር።GCAmh 243.4

    በ1833 ዓ.ም ማለትም ሚለር የክርስቶስን በቅርብ መምጣት ማስረጃዎች በግልጽ ማቅረብ ከጀመረ ከሁለት ዓመት በኋላ አዳኙ ለዳግም ምፅዓቱ ምልክት እንደሆነ ተስፋ የሰጠው የመጨረሻው ምልክት ተከሰተ። የሱስ ሲናገር “ክዋክብት ከሰማይ ይወድቃሉ” [ማቴ 24÷29] አለ። የእግዚአብሔር ቀን ምልክት የሆኑትን ክስተቶች በራዕይ ሲመለከት፣ ዮሐንስ “በለስም በብርቱ ንፋስ ተናውጣ ቃርያዋን ፍሬ እንደምትጥል የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ወደቁ።” [ራዕይ 6÷13] ይላል። ይህ ትንቢት በታላቁ የሜቴዎር መውረድ በህዳር 13፣ 1833 ዓ.ም አንፀባራቂና አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ፍፃሜ አገኘ። ይህ የከዋክብት መውደቅ ከተመዘገቡ ተመሳሳይ ክስተቶች መካከል በመጠነ ሰፊነቱና በግሩም ትዕይንቱ ተወዳዳሪ የሌለው ነበር። “በአሜሪካ ሰማይ ላይ በሞላ ለሰዓታት የዘለቀ የእሳት ቀውጢ ተፈጠረ። ሰፈራ ከተጀመረ ጀምሮ በአንደኛው ነዋሪ ዘንድ በግርምት የታዬ፣ በሌላው ደግሞ ፍርሃትና ድንጋጤ የፈጠረ እንደዚህ አይነት ሰማያዊ ክስተት በዚህች አገር ሆኖ አያውቅም።” “በአስደናቂነቱና ግሩም ገጽታው አሁንም በብዙ አዕምሮዎች እየተመላለሰ ነው.…ሜቴዎሮቹ ወደ ምድር እንደወረዱበት አይነት ያለ ከባድ ዝናብ ዘንቦ አያውቅም፤ ምሥራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜንና ደቡብ፣ ሁሉም ያው ነበር። በአንድ ቃል ሰማያት ሁሉ በእንቅስቃሴ ላይ ነበሩ.… በፕሮፌሰር ሲሊማን መጽሔት ላይ እንደተገለፀው ትዕይንቱ በሁሉም የአሜሪካ ክፍሎች ታይቷል። ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት እስከ ብርሐን ወገግታ ህዋው ፀጥ ረጭ ያለና ደመና አልባ ነበር። አስደናቂና ግሩም ነፀብራቆች ያለማቋረጥ በሰማያት በሞላ ይታዩ ነበር።”-R. M. Devens, American Progess; or, The Great Events of the Greatest Century, ch. 28, pars. 1-5።GCAmh 243.5

    “ያንን እጅግ የሚያምረውንና የተዋበውን ትዕይንት የሚገልጽ ቋንቋ የለም፤ ማንም ያላየው የግርማውን ትዕይንት በአዕምሮው መሳል የሚችል የለም። ሁሉም ከዋክብት ያለባቸው ሰማያት ወደ አንድ ከፍታ የተሰባሰቡ ይመስሉ ነበር፤ ከዚያም ከፍታ በመብረቅ ፍጥነት፣ በአንድ ላይ ወደ ሁሉም ዳርቻ ወደ ፊት ያስወነጭፉ ነበር፤ ትዕይንቱ የሚያባራ ግን አልነበረም፤ ለእንደዚያ አይነት ትዕይንት እንደተዘጋጁ በሚመስል ሁኔታ ሺዎች በተወነጨፉበት መስመር ሌሎች ሺዎች በፍጥነት ይወነጨፉ ነበር።”-F. Reed, in the Christian Advocate and Journal, Dec. 13, 1833። “የአንድ የበለስ ዛፍ በከባድ አውሎ ነፋስ ሲናወጥና ፍሬው ሲረግፍ ትክክለኛ ትዕይንቱን ማስተዋል የሚቻል አይደለም።”-“The Old Country Man”, in Portland Evening Advertiser; Nov. 26, 1833።GCAmh 244.1

    ይህ ትዕይንት ከተከናወነ ከአንድ ቀን በኋላ ሄንሪ ዳና ዋርድ ስለ አስገራሚው ክስተት ጽፏል፦ “እንደማስበው እንደትናንትና ጥዋቱ አይነት ትዕይንት ማንም ፈላስፋም ሆነ ሊቅ አልተናገረም፤ አልመዘገበምም። የክዋክብት መውደቅ የሚለው ሃሳብ በእርግጥም የሚወድቁ ከዋክብት ማለት መሆኑን መረዳት ከተቸገርን ቃል በቃል እውነት እንደሆነ የሚያስረዳው ብቸኛው መንገድ ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ አመት በፊት[አሁን ከሁለት ሺህ አመት ገደማ በፊት] አንድ ነብይ በትክክል የተነበየው መሆኑ ነው።”GCAmh 244.2

    እናም የሱስ ደቀ መዛሙርቱን “እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደቀረበ እወቁ” [ማቴ 24÷33] በማለት ያስጠነቀቀባቸው የመምጣቱ ምልክቶች ከሆኑት ውስጥ የመጨረሻው በእንደዚህ ሁኔታ ተከሰተ። ከእነዚህ ምልክቶች በኋላ ዮሐንስ ያየው በቀጣይነት የሚሆነው ታላቅ ክስተት ሰማይ እንደመጽሐፍ ተጠቅልሎ ሲያልፍ፣ ምድር ስትናወጥ፣ ተራሮችና ደሴቶች ከስፍራቸው ሲወሰዱ፣ ኃጥአንም በፍርሃት ከሰው ልጅ ፊት ሲሸሹ ነበር።GCAmh 244.3

    የከዋክብትን መውደቅ የተመለከቱ ብዙዎች ክስተቱ “የሚመጣው አሰቃቂ ቀን አምሳያ፣ በትክክልም ሊመጣ ያለውን የቀደመ፣ የዚያ ታላቅና አስፈሪ ቀን የምሕረት ምልክት”፣ ሊመጣ ላለው ፍርድ ማሳያ ጅማሮ እንደሆነ አድርገው ተመለከቱት።-“The Old Counry Man”, in PortlandGCAmh 244.4

    Evening Advertiser; Nov. 26, 1833። በመሆኑም የብዙዎች ትኩረት ወደ ትንቢቱ መፈፀም አዘነበለ፤ ብዙዎችም የዳግም ምፅዓቱን ማስጠንቀቂያ ልብ ይሉ ዘንድ ተመሩ።GCAmh 245.1

    በ1840 ዓ.ም ሌላ አስደናቂ፣ የትንቢት ፍፃሜ ያገኘ ክስተት አያሌ ትኩረት መሳብ ቻለ። ከሁለት ዓመት በፊት ዳግም ምፅዓቱን ከሚሰብኩ ዋነኛ አገልጋዮች መካከል አንዱ የሆነው ዮስያስ ሊች የራዕይ ምዕራፍ 9ን ማብራሪያ አሳትሞ ነበር። በዚህም ትንታኔው የኦቶማን ስርዎ-መንግሥት እንደሚወድቅ በመግለጽ፣ መውደቂያ አመቱን ብቻ ሳይሆን ክስተቱ የሚፈፀምበትን ቀን ጭምር ተናግሮ ነበር። ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ የትንቢት ዘመናት ስሌት የተመሠረተው ይህ ማብራሪያ እንደሚያትተው ከሆነ የቱርክ መንግሥት በነሐሴ 11 ቀን 1840 ዓ.ም ሉአላዊነቱን አሳልፎ ይሰጣል። ይህ ትንበያ ሰፊ ህትመት ሽፋን አግኝቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የድርጊቶችን አቅጣጫ በጉጉት ይጠባበቁ ነበር።-Josiah Litch, in Signs of the Times and Expositor of Prophecy, Aug. 1, 1840።GCAmh 245.2

    በዚያው በተተነበየው ጊዜ በእንደራሴዎችዋ አማካኝነት ቱርክ የተባበሩት አውሮፓ ኃይላትን ጥበቃ ተቀበለች፤ በዚህም ራስዋን በክርስቲያን አገራት ቁጥጥር ስር አደረገች፤ ክስተቱ ትንቢቱ ክንዋኔ እንዲያገኝ አደረገው። የሆነው ሲታወቅም ሚለርና ጓዶቹ ትንቢትን ለመተርጎም የሚጠቀሙበት መርህ ትክክል እንደሆነ አእላፋት አመኑ፤ ለምፅዓት (ለአድቬንት) እንቅስቃሴም ግሩም ማበረታቻ ኃይል ፈጠረ። የተማሩና ስልጣን ያላቸው ሰዎች ከሚለር ጋር በመተባበር ሰሩ፤ ከ1840 እስከ 1844 ዓ.ም ባለው ጊዜም ሥራው በፍጥነት ተስፋፋ።GCAmh 245.3

    ዊሊያም ሚለር በሃሳብና በጥናት የተገራ ጠንካራ የአዕምሮ ጉልበት የያዘ ሰው ነበር፤ ከጥበብ ምንጭ ጋር ራሱን በማቆራኘት ከእነዚህ ክህሎቶቹ ላይ የሰማይን ጥበብ አከለበት። የባህርይ ሀቀኝነትና የግብረ ገብነት ልቀት ቦታ በሚሰጡበት ሥፍራ ሁሉ ክብርና ከፍተኛ ግምት ይሰጠው የነበረ፣ እጅግ በጣም ውድ ዋጋ ያለው ሰው ነበረ። እውነተኛ፣ ከልብ የመነጨ ቸርነትን ከክርስቲያናዊ ትህትናና ራስን ከመግዛት ኃይል ጋር በማዋሃድ ሁሉንም ሰው በጥሞና የሚያዳምጥ፣ ለማናገር ቀላል፣ የሌሎችን አስተያየት ለመቀበል፣ ክርክራቸውንም ለመመዘን ዝግጁ የነበረ ሰው ነበረ። ከስሜታዊነትና ከመፍነክነክ ነፃ ሆኖ ሁሉንም ጽንሰ-ሃሳቦችና አስተምህሮዎች በእግዚአብሔር ቃል ይመዝናቸው ነበር፤ ግሩም የሆነው የማመዛዘን ችሎታው፣ ልቅም ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀቱ ጋር ተደምሮ ስህተቱ ስህተት እንደሆነ ለማረጋገጥ፣ ውሸትንም ለማጋለጥ አስችሎት ነበር።GCAmh 245.4

    እንዲህም ሆኖ ግን ሥራውን ያለ መሪር ተቃውሞ ማካሄድ አልቻለም። ልክ እንዳለፉት የተሐድሶ አራማጆች ሁሉ ያቀረባቸው እውነቶች በታዋቂ ኃይማኖተኛ መምህራን ዘንድ ድጋፍ ሊያገኙ አልቻሉም። እነዚህ ሰዎች አቋማቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ ማስጠበቅ ሲሳናቸው ወደ አባቶች ወግና ልማድ፣ ወደ ሰብአዊ ፍጡራን አባባሎችና አስተምህሮዎች ያዘነብሉ ዘንድ ተገደዱ። በአድቬንት (በዳግም ምፅዓት) እውነት ሰባኪዎች ዘንድ ተቀባይነት የነበረው ብቸኛ ምስክር ግን የእግዚአብሔር ቃል ነበር። “መጽሐፍ ቅዱስ እና መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ” ህገ-ቃላቸው ነበር። በተቃራኒዎቻቸው በኩል መገኘት ያልተቻለው መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገ ክርክር በማጣጣልና በሹፈት የተጀቦነ ነበር። ብቸኛ ጥፋታቸው የጌታቸውን መመለስ በደስታ የሚጠባበቁ፣ የቅድስና ሕይወት ለመኖር የሚጥሩ፣ ለመገለጡም ይዘጋጁ ዘንድ ሌሎችን የሚያሳስቡ መሆናቸው የነበረውን ሰዎች በአደባባይ ለማጥላላት ጊዜ፣ ገንዘብና ክህሎቶች በሥራ ላይ ውለው ነበር።GCAmh 245.5

    የሰዎችን አዕምሮ ከዳግም ምፅዓት ርዕሰ-ጉዳይ ፈቀቅ ለማድረግ ልባዊ የሆነ ጥረት ተደረገ። ከክርስቶስ መምጣትና ከዓለም መጨረሻ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ትንቢቶች ማጥናት ኃጢአት እንደሆነ፣ ሰዎች ሊሸማቀቁበት የሚገባ ድርጊት እንዲመስል ተደረገ። በዚህም የተነሳ ሕዝብ በብዛት የሚከተለው ኃይማኖት በእግዚአብሔር ቃል የነበረውን እምነት ሸረሸረው። አስተምህሮአቸው ሰዎችን ኃይማኖት-የለሽ አደረጋቸው፤ ብዙዎች የራሳቸውን፣ እግዚአብሔርን መሰልነት የሌለበትን ዝሙታዊ መንገድ ለመከተል ፈቃድ የወሰዱበት ሆነ። ከዚያም የክፋት ፀኃፊዎች ሁሉንም ነገር በአድቬንቲስቶች/በምፅዓቱ ተጠባባቂዎች ላይ አላከኩት (የሆነው መጥፎ ነገር ሁሉ ሊከሰት የቻለው በአድቬንቲስቶች ምክንያት ነው አሉ)።GCAmh 246.1

    ቤቶች እስኪጨናነቁ ድረስ የብልሆችንና የጥሞና አድማጮችን ትኩረት በብዛት መሳብ ቢችልም፣ ከፌዝና ከውግዘት ባለፈ የሚለር ስም በኃይማኖት ህትመቶች ዘንድ እምብዛም አይጠቀስም ነበር። በኃይማኖታዊ መምህራን አቋም የልብ ልብ የተሰማቸው ግድ የለሾችና እግዚአብሔርን የማይመስሉ ሰዎች ወደ ባለጌ ቅጽል ስሞች፣ ወደ ተዋረዱ ስድቦችና ቀልዶች ፊታቸውን በማዞር በእርሱና በሥራዎቹ ላይ አጥንት የሚሰብሩ፣ ፀያፍ ስድቦችን ማውረድ ጀመሩ። በቅርብ ሊመጣ ስላለው ፍርድ ለዓለም ኮስተር ያለ ማስጠንቀቂያ ያደርስ ዘንድ፣ ምቾት ያለውን ቤቱን ለቆ በራሱ ወጪ ከከተማ ከተማ፣ ከመንደር መንደር የሚንከራተተው ሽበታሙ ሰው ጽንፈኛ፣ ውሸታም፣ በግምት ላይ የተመሠረተ፣ ወሮ-በላ እንደሆነ ተደርጎ በንቀት ተወገዘ።GCAmh 246.2

    በላዩ ላይ የተቆለለው መሳለቂያ፣ ውሸትና ስድብ፣ ኃይማኖታዊ ካልሆነው ፕረስ (ህትመት) ሳይቀር ቁጣ ያዘለ ምሬትና ተቃውሞ አስከተለ። ይህንን እጅግ [ከአዕምሮ የሚያልፍ] ሞገስና አስፈሪ ውጤት ያለውን ርዕሰ-ጉዳይ እንዲህ አቅልሎ፣ ብልግና በተቀላቀለበት ቀልድ ማቅረብ፣ በዓለማዊያኑ በኩል በደጋፊዎቹ ስሜት መጫወት ብቻ ሳይሆን “በፍርድ ቀን መዘበት፣ እግዚአብሔርን ራሱን መስደብ፣ በአስደንጋጩ ፍርድ-ሸንጎው ላይ ማላገጥ ጭምር ነው።”-Bliss, ገጽ 183።GCAmh 246.3

    የክፋት ሁሉ ቀስቃሽ የአድቬንትን መልእክት ተጽዕኖ መቃወም ብቻ ሳይሆን፣ መልዕክተኛውንም ጭምር ማጥፋት ፈልጓል። ኃጢአታቸውን በመገሰጽ፣ ራሳቸውን ማርካታቸውን በማወክ ሚለር የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በሰሚዎቹ ልብ ውስጥ ተግባራዊ ሥራ እንዲሰራ አደረገ። ግልጽ የሆኑትና የሚቆራርጡት ቃላቱ ጠላትነትን አነሳሱ። በቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የተንፀባረቀው፣ ለመልእክቱ የነበረው ተቃውሞ በምግባራቸው ይበልጥ የረከሱትን መደቦች የልብ ልብ በመስጠት ወደ የባሰ እርቀት ጉዳዩን እንዲገፉበት አበረታታቸው። የስብሰባ ቦታውን ለቆ ሲሄድ ለመግደል ጠላቶቹ አሴሩ። ሆኖም ቅዱሳን መላእክት በተሰበሰቡት ሰዎች መካከል ነበሩ። አንዱም መልአክ ሰው ተመስሎ የእግዚአብሔርን አገልጋይ እጅ ይዞ በመምራት በቁጣ ከሚጠብቁት ሰዎች አስመለጠው። ሥራው ገና አላለቀም፤ አላማቸው አልተሳካላቸውምና ሰይጣንና ቆንስላዎቹ አዘኑ።GCAmh 246.4

    ተቃውሞውን ሁሉ ተቋቁሞ በአድቬንት እንቅስቃሴ ዘንድ ያለው ፍላጎት ማድረጉን ቀጠለ። ከአሥርና ከመቶዎች ተነስቶ ምዕመናኑ በሺዎች ተቆጠሩ። ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ብዙ ተከታዮችን ማግኘት ተቻለ፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን በተለወጡት ሰዎች ላይ ጭምር የተቃውሞ መንፈስ መንፀባረቅ ጀመረ፤ ከዚያም የሚለርን አቋም በደስታ በተቀበሉት ላይ አብያተ ክርስቲያናት እርምጃ መውሰድ ጀመሩ። ይህ ድርጊታቸው የጽሁፍ መልስ እንዲሰጥበት ገፋፍቶት በሁሉም የኃይማኖት አብያተ ክርስቲያናት ላሉ ክርስቲያኖች የእርሱ አስተምህሮዎች ትክክል አይደሉም ከተባሉ ስህተቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲያሳዩት ተገዳደራቸው።GCAmh 247.1

    “እናንተ ራሳችሁ ሕግ ነው ብላችሁ የፈቀዳችሁት፣ የእምነታችንና የተግባራችን ብቸኛ መመሪያ ከሆነው” አለ፣“እንድናምንበት በእግዚአብሔር ቃል ከታዘዝንበት ውጪ ሌላ ያመንነው ነገር አለን? ከመድረክና ከህትመት እንደዚህ አይነት ጥላቻ የተሞላበት ውግዘት እንድትሰነዝሩብን እኛን ከቤተ ክርስቲያናችሁና ከአምልኮአችሁ እንድታገሉን ያደረጋችሁ ምን ሥራ ሰርተን ነው? ጥፋተኞች ከሆንን እባካችሁ ስህተታችን የት ላይ እንደሆነ ጠቁሙን፤ መሳሳታችንን ከእግዚአብሔር ቃል ዘንድ አሳዩን፤ በቂ ልግጫ አስተናግደናል፤ ያ ግን እኛ እንደተሳሳትን በፍፁም ሊያሳምነን አይችልም። አቋማችንን ሊያስለውጠን የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።የመጨረሻ አቋማችን የተገነባው በጥንቃቄና በፀሎት፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ነው።”-Ibid., ገጽ 250, 252።GCAmh 247.2

    ከዘመን ዘመን በባሪያዎቹ አማካኝነት እግዚአብሔር ወደ ዓለም የሚልካቸው ማስጠንቀቂያዎች በተመሳሳይ ጥርጣሬና እምነት-አልባነት የሚታዩ ናቸው። ከጥፋት ውኃ በፊት የነበሩት ኃጢአቶች እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን በዓለም ላይ እንዲያመጣ ሲያደርጉት፤ ከክፋት መንገዳቸው ዘወር ለማለት ዕድል ፈንታ ይኖራቸው ዘንድ መጀመሪያ እቅዱን አሳወቃቸው። የእግዚአብሔር ቁጣ በጥፋታቸው እንዳይገለጽ፣ ንስሐ እንዲገቡ የሚያስጠነቅቀው ደወል ለአንድ መቶ ሃያ ዓመታት አቃጨለ። መልእክቱ ግን የማይረባ፣ ተረት ተረት መሰላቸው፤ አላመኑትምም። በኃጢአታቸው የባሰ ተደፋፍረው የእግዚአብሔርን መልዕክተኛ አላገጡበት፤ ልመናውን አቃለሉት፤ በመላምት ያምናል ብለው ከመወንጀል ደረሱ። አንድ ሰው የዓለምን ኃያል ሰዎች ተገዳድሮ እንዴት ሊቆም ይችላል? የኖህ መልእክት እውነት ከነበረ፣ ለምን መላው ዓለም ሊያየውና ሊያምን አልቻለም? የአንድ ሰው እምነት ቃል ወይስ የሺዎች ጥበብ! ለማስጠንቀቂያው ዋጋ ይሰጡ ዘንድ፣ በመርከቡም ይጠለሉ ዘንድ አልወደዱም።GCAmh 247.3

    ፌዘኞች ወደ ዓለም ክስተት አነጣጠሩ፤ ሳይለዋወጡ ወደሚከታተሉት ወቅቶች፣ ዝናብ ጠብ አድርጎ ወደማያውቀው ሰማያዊ ህዋ፣ በሌሊት በሚገኙ ለስላሳ ጠሎች አማካኝነት ወደሚታደሱት አረንጓዴያማ መስኮች እየተመለከቱ፦ “በምሳሌ አይናገርምን?” በማለት ጮሁ [ሕዝ 20÷49]። በንቀትም፣ ጽድቅ ሰባኪው ወፍ ዘራሽ ሃሳብ ደጋፊ እንደሆነ በመናገር፣ ተድላን በበለጠ በማሳደድ፣ በፊት ከነበረው በላቀ ሁኔታ የጥፋት መንገዳቸውን ገፉበት። አለማመናቸው ግን ሊሆን ያለውን ክስተት አላደናቀፈውም። ከበቂ በላይ የንስሐ ዕድል በመስጠት እግዚአብሔር ለረጅም ጊዜ ታግሷቸዋል።ሆኖም በተወሰነው ጊዜ በምህረቱ አሻፈረኝ ባዮች ላይ ፍርዱ ወረደ።GCAmh 247.4

    ዳግም ምፅዓቱን በተመለከተ ተመሳሳይ የሆነ አለማመን እንደሚኖር ክርስቶስ ይናገራል፦ “የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉን እስኪወስድ ድረስ” በኖህ ዘመን የነበሩ ሰዎች አላወቁም፤ “የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።” [ማቴ 24÷39]። የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝቦች ከዓለም ጋር ተዋህደው፣ እነርሱ እንደሚኖሩት እየኖሩ፣ በተከለከሉ እርካታዎች አብረው ሲካፈሉ፣ የዓለም ድሎት የቤተ ክርስቲያንም ምቾት ሲሆን፣ የጋብቻ ደውሎች ሲሰሙና ሁሉም ወደ ረጅም ዘመን ዓለማዊ ብልጽግና በጉጉት ሲመለከት፣ ያኔ በድንገት መብረቅ ከሰማያት ቦገግ ሲል፣ የብሩህ ራዕያቸውና ከእውነት የራቀው ተስፋቸው መቋጫ ይደርሳል።GCAmh 248.1

    ሊመጣ ስለነበረው የጥፋት ውኃ ዓለምን ያስጠነቅቅ ዘንድ እግዚአብሔር አገልጋዩን እንደላከ ሁሉ፣ የመጨረሻው ፍርድ መቅረቡን ያሳውቁ ዘንድ የተመረጡ መልዕክተኞቹን ላከ። በኖህ ዘመን የነበሩት ዘመናዊያን በጽድቅ ሰባኪው ትንቢቶች የማላገጥ ሳቅ ሲስቁ እንደነበረ ሁሉ፣ በሚለር ዘመንም፣ አያሌ ሰዎች፣ ታማኝ የእግዚአብሔር ተከታዮች ነን የሚሉቱ ጭምር፣ በማስጠንቀቂያ ንግግሮቹ ተሳለቁ።GCAmh 248.2

    የክርስቶስ ዳግም ምፅዓትና አስተምህሮና ስብከት በአብያተ ክርስቲያናት እንዲህ እጅግ የተጠሉት ለምን ይሆን? ለኃጥአን የጌታ ምፅዓት ስቃይና ውድመት ይዞ ሲመጣ፣ ለጻድቁ ደግሞ በደስታና በተስፋ የተሞላ ነው። ይህ ታላቅ እውነት በዘመናት ሁሉ የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝቦች መጽናኛ ሆኖ ኖሮአል። ታዲያ ለምንድን ነው ልክ እንደ ፀኃፊው (እንደ አብ)፣ ታማኝ ነን ለሚሉ ሕዝቦቹ “የእንቅፋት ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት” የሆነው? [1ኛ ጴጥ 2÷7] “ሄጄም ስፍራ ባዘጋጀሁላችሁ.… ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ” [ዮሐ 14÷3] ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ቃል የገባው ጌታችን ራሱ ነው። ወደ ሰማይ እንደወጣ እንዲሁ ተመልሶ በአካል እንደሚመጣ በሚያበስረው ማጽናኛ ያበረታቷቸው ዘንድ መላእክትን ያዘዘው፣ የተከታዮቹ ብቸኝነትና ሃዘን ጥልቅ እንደሚሆን የገባው፣ ሩህሩሁ አዳኛችን ነበር። ይወዱት የነበረውን የእርሱን የመጨረሻ ውልብታ ለማየት ወደ ላይ አንጋጠው ሲያፈጡ ትኩረታቸውን የሳቡ ቃላትን ሰሙ፣ “የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው የሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል” [የሐዋ ሥራ 1÷11]። በመልአክቱ መልእክት ምክንያት ተስፋ እንደገና ታድሶ አቆጠቆጠ። ደቀ መዛሙርቱም “በብዙ ደስታ ወደ የሩሳሌም ተመለሱ፤ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ” [ሉቃ 24÷52፣53]። ደስ እያላቸው የነበሩት ክርስቶስ ስለተለያቸውና ለዓለም እንግልትና ፈተና ስለተተዉ አልነበረም፤ እንደገና እንደሚመጣ መልአኩ በሰጣቸው ማረጋገጫ እንጂ።GCAmh 248.3

    የክርስቶስ መምጣት አዋጅ፣ ያኔ በመላእክት አማካኝነት ለቤተልሄም እረኞች ሲነገር እንደሆነው ሁሉ አሁንም የታላቅ ደስታ የምሥራች ሊሆን ይገባዋል። አዳኙን ከልባቸው የሚወዱት ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ከተመሠረተው አዋጅ የተነሳ ማድረግ የሚችሉት ነገር ቢኖር በደስታ ማመስገን ነው፤ ምክንያቱም የዘላለም ሕይወት ተስፋቸው ማዕከል ያደረጉት እርሱ፣ በመጀመሪያ ምፅዓቱ እንደሆነው ሊሰደብ፣ ሊጠላ፣ ተቀባይነት ሊያጣ ሳይሆን ሕዝቦቹን ለመቤዠት በኃይልና በክብር ስለሚመጣ ነው። ሳይመለስ እንዲቀር የሚፈልጉት አዳኙን የማይወዱት ናቸው። ከሰማይ በተላከው መልእክት ምክንያት ከተቀሰቀሰው ጥላቻና ብስጭት የበለጠ አብያተ ክርስቲያናት ከእግዚአብሔር እንደተለዩ የሚያስረዳ የማያወላውል ማረጋገጫ ሊኖር አይችልም።GCAmh 248.4

    የምፅዓቱን አስተምህሮ የተቀበሉት እነርሱ ንስሐ ለመግባትና ራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት ለማዋረድ ተነቃቅተው ነበር። ብዙዎች በክርስቶስና በዓለም መካከል ሲያነክሱ (ሲያወላውሉ) ቆይተዋል፤ “ቁርጥ አቋም የመውሰድ ጊዜ እንደደረሰ አሁን ተሰማቸው። የዘላለም ነገር ያልጠበቁት እውነታ ደቀነባቸው። ሰማይ ወደ እነርሱ እንዲቀርብ ሆነ፤ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኛነታቸው ተሰማቸው። ክርስቲያኖች አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት ይኖራቸው ዘንድ ተበረታቱ። ጊዜው አጭር እንደሆነ፣ ለባልንጀሮቻቸው ማድረግ ያለባቸው ነገር ሁሉ በፍጥነት መደረግ እንዳለበት እንዲሰማቸው ተደረገ። ምድር ሸሸች፣ ዘላለማዊነት በፊታቸው የሚገለጥ መሰለ፤ ነፍስን የሚገጥማት ዘላለማዊ ደስታ ወይም ስቃይ ማንኛውንም አላፊ ግብ የሚያስንቅ ሆነ።” የእግዚአብሔር መንፈስ አረፈባቸው፤ ለእግዚአብሔር ቀን ይዘጋጁ ዘንድ ለወንድሞቻቸውና ለኃጢአተኞች የሚያቀርቡት ልባዊ ተማፅኖ ጉልበት አገኘ። በዝምታ የሚመሰክረው የዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ውጫዊ ወግና ሥርዓት ለሚከተሉና ላልተቀደሱ የቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የማያባራ ወቀሳ ሆነባቸው። እነዚህ ሰዎች ደስታን የማሳደድ ጥረታቸውን፣ ገንዘብ ለማካበት የነበራቸውን ቁርጠኛነትና ዓለማዊ ክብርን የመሻት ፍላጎታቸውን የሚረብሽ ነገር አልፈለጉም፤ ለዚያም ነው የአድቬንት እምነትንና አስተምህሮውን በሚያውጁት ላይ ጠላትነትና ተቃውሞ የተነሳው።GCAmh 249.1

    የትንቢት ዘመናትን አቆጣጠር ተንተርሰው የተነሱት መከራከሪያዎች አይበገሬ ሲሆኑባቸው፣ ትንቢታቱ የታተሙ (ያልተከፈቱ) እንደሆኑ በማስተማር ተቃዋሚዎች ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ጥናት እንዳይደረግ ለማሳነፍ አጥብቀው ይጥሩ ነበር። እንዲህም ፕሮቴስታንቶቹ የሮማዊነትን ፈለግ ተከተሉ። ጳጳሳዊቷ ቤተ ክርስቲያን ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳያገኝ ስታደርግ፣ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ የቅዱስ ቃሉ አስፈላጊ ክፍል የሆኑት፣ በተለይም በእኛ ዘመን የሚከናወኑ እውነቶችን ወደ እይታ የሚያመጣው ቃል መስተዋል የሚቻል አይደለም በማለት ተከራከሩ።GCAmh 249.2

    አገልጋዮችና ሕዝቡ የዳንኤልና የራእይ የትንቢት መፃሕፍት ለመረዳት የማይቻሉ ምስጢራት እንደሆኑ አወጁ። ሆኖም ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ሲናገር በዘመናቸው ሊፈፀሙ ስላላቸው ክስተቶች የነብዩን የዳንኤልን ቃላት እንዲመለከቱ ሲመራቸው ነበር፤ እንዲህም አለ፦ “አንባቢው ያስተውል” [ማቴ 24÷15]። ራዕይ መጽሐፍ ምስጢር እንደሆነና ለመረዳት የማይቻል ነው ብሎ መፈረጅ ከመጽሐፉ ርዕስ ጋር የሚቃረን ነው [ርዕሱ መገለጥ/Revelation ነው]፤ “የየሱስ ክርስቶስ ራዕይ እግዚአብሔር የሰጠው ፈጥኖ የሚሆነውን ለባርያዎቹ ይገልጥ ዘንድ….ምስጋና ይገባዋል [የተባረከ ነው]፣ ለሚያነብ የዚህንም ትንቢት ነገር [ቃል] ለሚሰሙ በእርሱ የተጻፈውንም ለሚጠብቁ ዘመኑ ቀርቦአልና” [ራዕይ 1÷1-3]።GCAmh 249.3

    ነብዩም አለ፦ “የሚያነበው ብፁዕ ነው።” የማያነቡ አሉ፤ በረከቱ ለእነርሱ አይደለም። ትንቢታትን በተመለከተ ምንም ዓይነት ነገር መስማት የማይፈልጉም አሉ፤ በረከቱ ለዚህ መደብ አይደለም - “የሚሰሙ እነርሱ” ደግሞ- ትንቢታትን በተመለከተ ምንም አይነት ነገር መስማት የማይፈልጉ ጥቂቶች አሉ፤ በረከቱ ለዚህ መደብም አይደልም’ “በውስጡ የተፃፈውን የሚጠብቁ” ብዙዎች በራእይ ውስጥ ለተቀመጡት ማስጠንቀቂያዎችና ትዕዛዛት ትኩረት መስጠት አሻፈረኝ ይላሉ፤ ከእነዚህ ውስጥ ተስፋ የተገባለትን በረከት የመጠየቅ ማናቸውም መብት የላቸውም። በትንቢት ርዕሰ-ጉዳዮች የሚሳለቁ፣ በጽሞና በተሰጡት ተምሳሌቶችም የሚያፌዙ፣ ሕይወታቸውንም አድሰው ለሰው ልጅ መምጣት የማይዘጋጁ ሁሉ፣ እነርሱ አይባረኩም።GCAmh 249.4

    ሰዎች፣ የመንፈስን ምስክርነት እያዩ፣ ራዕይ ምስጢር ነው፤ ከፍጡራንም ማስተዋል በላይ ነው፤ ብለው ለማስተማር እንዴት ደፈሩ? የተገለጠ ምስጢር፣ የተከፈተ መጽሐፍ ነውና። የራዕይ ጥናት የሰዎችን አዕምሮ ወደ ዳንኤል ትንቢቶች የሚያመላክት፣ ሁለቱም በዚህ ዓለም ታሪክ መደምደሚያ ሊከናወኑ ያላቸውን ክስተቶች በተመለከተ ለሰዎች ከእግዚአብሔር የተሰጠውን እጅግ አስፈላጊ ትምህርት የሚገልፁ ናቸው።GCAmh 250.1

    ለዮሐንስ ጥልቅና አጓጊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን ተሞክሮ ትዕይንቶች ተገለጡለት። እርሱ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ደረጃ (አቋም)፣ አደጋዎች፣ ግጭቶችና የመጨረሻውን መዳን አይቷል። ለሰማያዊው ጎተራ ነዶ፣ ወይም ለጥፋት እሳት ገለባ አድርገው የዓለምን መከር የሚያደርሱትን የመደምደሚያ መልእክቶች መዝግቧል። በተለይም ለመጨረሻዋ ቤተ ክርስቲያን ብሎም ከስህተት ወደ እውነት ለሚመለሱ ለእነርሱ በፊታቸው ስላሉት አደጋዎችና ጦርነቶች ያውቁ ዘንድ መጠነ ሰፊ አስፈላጊነት ያላቸው ጉዳዮች ለእርሱ ተገልፀውለታል። በምድር ላይ ሊመጣ ያለውን በተመለከተ ማንም በድንግዝግዝ ውስጥ መሆን አይገባውም።GCAmh 250.2

    ታዲያ በዚህ ቅዱስ ትዕዛዝ አስፈላጊ ክፍል የሆነውን በተመለከተ ለምንድንነው አላዋቂነት የተንሰራፋው? ትምህርቱን ለመመርመር አጠቃላይ ፍላጎት ማጣት ያለው ለምንድን ነው? ማታለያዎቹን የሚያጋልጥበትን ነገር ከሰዎች የመደበቅ የጨለማው ልዑል የተጠና ጥረት ውጤት ነው። ገላጩ ክርስቶስ፣ ራዕይ እንዳይጠና የሚቀሰቀሰውን ጦርነት ወደፊት በመመልከት፣ የትንቢትን ቃል የሚያነቡ፣ የሚሰሙና የሚያደርጉት ሁሉ በረከት እንደሚሆንላቸው የተናገረው በዚህ ምክንያት ነው።GCAmh 250.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents