Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፳፭—መለወጥ የማይችለው የእግዚአብሔር ሕግ

    “በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ውስጥ ታየ” [ራእይ 11÷19]። የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት፣ በመቅደሱ በሁለተኛው ክፍል፣ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ነው። ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ በነበረው በምድራዊው ድንኳን ይህ ክፍል ይከፈት የነበረው በታላቁ የስርየት ቀን፣ ለመቅደሱ መንፃት ነበር። ስለዚህ በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ እንደተከፈተና የኪዳኑም ታቦት እንደታየ የሚናገረው አዋጅ የሚያመለክተው በ1844 ዓ.ም ክርስቶስ የስርየትን የመጨረሻ ሥራ ለማከናወን ሲገባ፣ በሰማይ ያለው ቤተ መቅደስ፣ ቅድስተ ቅዱሳን መከፈቱን ነው። በቅድስተ ቅዱሳን ያለውን አገልግሎት ለመጀመር ወደዚያ ሲገባ በእምነት ታላቁ ሊቀ ካህናቸውን የተከተሉ እነርሱ የኪዳኑን ታቦት ተመልከተዋል። የቤተ መቅደሱን ጉዳይ እያጠኑ በነበሩበት ጊዜ፣ የአዳኙን የአገልግሎት ለውጥ አስተውለዋል፤ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ሆኖ ሲያገለግል፣ ስለ ኃጢአተኞች በደሙ ሲማልድ ተመልክተዋል።GCAmh 314.1

    በምድር ላይ የነበረው ድንኳን የእግዚአብሔር ሕግ መርሆዎች የተቀረፁባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች የያዘ ነበር። የታቦቱ ጥቅም የሕጉን ጽላቶች መያዙ ብቻ ነበር፤ ዋናው ቅድስና የሰጠው መለኮታዊ መመሪያዎች በውስጡ መኖራቸው ነበር። በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ሲከፈት የኪዳኑ ታቦት ታየ። በሲና ነጎድጓድ መካከል በእግዚአብሔር በራሱ የተነገረው፣ በጽላቶቹ ላይም በራሱ ጣት የተፃፈው ሕግ፣ በሰማይ ባለው መቅደስ ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳኑ መለኮታዊው ሕግ በቅድስና ተቀርጾ ተቀምጧል።GCAmh 314.2

    መመሪያዎቹ በጽላቶቹ ላይ የተፃፉት፣ ሙሴም በኦሪት በጽሁፍ ያሰፈረው፣ በሰማያዊው ቤተ መቅደስ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ሕግ፣ ዋናው ቅጂ ነው (The great Original ነው)። ወደዚህ አስፈላጊ የሆነ ነጥብ መረዳት የደረሱ እነርሱ የተቀደሰና ባህርይው የማይለወጥ የሆነውን መለኮታዊ ሕግ እንዲያዩ ተመሩ፤ ከምንጊዜውም የበለጠ የአዳኙን ቃላት ኃይል ተገነዘቡ፣ “ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም” [ማቴ 5÷18]። የፈቃዱ መገለጥ፣ የባህርይውም ማህደር፣ “ምስክርነቱ በሰማይ የታመነ” [መዝ 89÷37] ሆኖ ለዘላለም ይፀና ዘንድ ይገባዋል። አንድም ትዕዛዝ አልተሰረዘም፣ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አልተቀየረችም። መዝሙረኛው እንዲህ ይላል፦ “አቤቱ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ይኖራል”፤ “ትዕዛዛቱም ሁሉ የታመነ ነው ለዘላለምም የፀና ነው።” [መዝ 119÷89፤ 111÷7፣8]።GCAmh 314.3

    “የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፤ ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህን ሁሉ አድርግ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ ወንድ ልጅህም፣ ሴት ልጅህም፣ ሎሌህም ገረድህም ከብትህም በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትስሩ፤ እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፣ ባህርንም ያለባቸውን ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን አርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም” [ዘጸ 20÷ 8-11] ተብሎ መጀመሪያ እንደታወጀው፣ በአሥርቱ ትዕዛዛት ጉያ ውስጥ ያለው አራተኛው ትዕዛዝ ነው።GCAmh 314.4

    የቃሉ ተማሪዎች የሆኑትን ልቦች የእግዚአብሔር መንፈስ ነካ። የፈጣሪን የእረፍት ቀን ቸል በማለት መመሪያውን በጭፍንነት እንደተላለፉ በመረዳት ጥፋተኛነት ተሰማቸው። እግዚአብሔር በቀደሰው ፈንታ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ለምን እንደሚከበር ምክንያቱን መመርመር ጀመሩ። አራተኛው ትዕዛዝ እንደቀረ ወይም ሰንበት እንደተቀየረ የሚያረጋግጥ አንድም ማስረጃ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማግኘት አልቻሉም፤በመጀመሪያ ሰባተኛውን ቀን የቀደሰው ባርኮት ፈጽሞ አልተወሰደም። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅና ለማድረግ በቅንነት ሲመኙ ቆይተዋል፤ እናም አሁን ራሳቸው የእግዚአብሔርን ሕግ ተላላፊዎች እንደሆኑ ሲገባቸው ሃዘን ልባቸውን ሞላው፤ ሰንበትንም በቅድስና በመጠበቅ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት አሳዩ።GCAmh 315.1

    እምነታቸውን ለመገልበጥ የተደረጉት ጥረቶች ጠንካራና በርካታም ነበሩ። ምድራዊው መቅደስ የሰማያዊው ምሳሌ ወይም አምሳያ ከሆነ በምድር በነበረው ታቦት ውስጥ የተቀመጠው ሕግ በሰማይ ባለው ታቦት ውስጥ ያለው ሕግ ግልባጭ እንደሆነ፣ ሰማያዊውን መቅደስ የተመለከተን እውነታ መቀበል ለእግዚአብሔር ሕግ መጠይቅ እውቅና መስጠት፣ አራተኛውን ትዕዛዝ ሰንበትን ማክበር እንደሆነ ማንም ሊስተው አልቻለም። የክርስቶስን፣ በሰማያዊ መቅደስ ያለበትን አገልግሎት የሚገልፁትን፣ ስምሙ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎች መሪርና ቆራጥ ተቃውሞ የገጠማቸው ምክንያት ምስጢር እዚህ ላይ ነበር። እግዚአብሔር የከፈተውን በር ሰዎች ሊዘጉ፣ የዘጋውን በር ደግሞ ሊከፍቱ ፈለጉ። ነገር ግን “የሚከፍት የሚዘጋም የሌለ፣ የሚዘጋ የሚከፍትም የሌለ” እርሱ አውጆአል። “እነሆ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼሃለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም” [ራእይ 3÷7፣8]። ክርስቶስ የቅድስተ ቅዱሳኑን በር ወይም አገልግሎት ከፈተ፤ ከተከፈተው የሰማያዊው መቅደስ በር የሚያንፀባርቅ ብርሐን ይወጣ ነበር፤ በተቀረፀው ሕግ ውስጥም አራተኛው ትዕዛዝ እንደተካተተ ታየ፤ እግዚአብሔር የመሰረተውን ማንም ሰው ሊሽረው አይችልም።GCAmh 315.2

    የክርስቶስን አማላጅነት፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ዘላለማዊነት በተመለከተ የተሰጠውን ብርሐን የተቀበሉ፣ በራእይ 14 የቀረቡት እውነቶች እነዚያው ራሳቸው እንደሆኑ ደረሱበት። የዚህ ምዕራፍ መልእክቶች በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ለጌታ ዳግም ምፅዓት የሚያዘጋጅ ሶስት እጥፍ ማስጠንቀቂያ የያዙ ናቸው። [በመግለጫ ስር ማስታወሻ 8ን ይመልከቱ]። “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና” የሚለው አዋጅ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ክርስቶስ ወደሚያከናውነው የማጠቃለያ ሥራ የሚጠቁም ነው። የአዳኙ የማማለድ ሥራ እስኪያልቅ፣ ወደ ምድር ተመልሶም ሕዝቦቹን ወደራሱ እስኪወስድ ድረስ መታወጅ ያለበትን እውነት የሚያውጅ ነው። በ1844 ዓ.ም የጀመረው የፍርድ ሥራ በሕይወት ያሉም ሆነ የሞቱ ሁሉ ጉዳያቸው ውሳኔ እስኪያገኝ መቀጠል አለበት፤ ስለሆነም የሰብዓዊ ዘር የምሕረት ደጅ እስኪዘጋበት ድረስ የሚቀጥል ይሆናል። ሰዎች ዝግጁ ሆነው ለፍርዱ መቆም ይችሉ ዘንድ “እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባህርንም የውሃንም ምንጮች ለሰራው ስገዱለት” በማለት መልእክቱ ያዛቸዋል። እነዚህን መልእክቶች የመቀበል ውጤቱ በእነዚህ ቃላት ተገልጧል። “የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁ የሱስንም በማመን የሚፀኑ እነዚህ ናቸው።” [ራእይ 14÷12]። ለፍርዱ መዘጋጀት ይችሉ ዘንድ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ያስፈልጋቸዋል። ያ ሕግ በፍርድ ጊዜ የባህርይ ደረጃ መመዘኛ ይሆናል። ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር “ሕግም ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ በሕግ ይፈረድባቸዋል….ይህም እግዚአብሔር በየሱስ ክርስቶስ….በሰው ዘንድ የተሰወረውን በሚፈርድበት ቀን ይሆናል” ይላል፤ በተጨማሪም “ሕግን የሚያደርጉ ይፀድቃሉ” [ሮሜ 2÷12-16]። የእግዚአብሔርን ሕግ ለመጠበቅ እምነት አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም “ያለ እምነት እርሱን ደስ ማሰኘት አይቻልም።” “በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው።” [ዕብ 11÷6፤ ሮሜ 14÷23]።GCAmh 315.3

    በመጀመሪያው መልአክ፣ ሰዎች “እግዚአብሔርን እንዲፈሩ ክብርንም እንዲሰጡት”፣ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ እንደሆነም አድርገው እንዲያመልኩት ተጠርተዋል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ሕጉን መታዘዝ አለባቸው። ጠቢቡ ሰው እንዲህ ይላል፣ “እግዚአብሔርን ፍራ ትዕዛዙንም ጠብቅ፣ ይህ የሰው ሁለንተና ነውና” [መክ 12÷13]። ትዕዛዛቱን የማያደርግ ማንኛውም አምልኮ ደስ ሊያሰኘው አይችልም። “ትዕዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና” “ሕግን ከመስማት ጆሮውን የሚመልስ ፀሎቱ አፀያፊ ናት።” [1ኛ ዮሐ 5÷3፤ ምሳሌ 28÷9]።GCAmh 316.1

    እግዚአብሔርን የማምለክ ኃላፊነት፣ እርሱ ፈጣሪ በመሆኑ፣ የሌሎቹ የሁሉም ሕያውነት ምክንያት እርሱ በመሆኑ ጭብጥ ላይ የተመሠረተ ነው። ከአሕዛብ አማልክት በላይ ሊከበርና ሊመለክ እንደሚገባው በገለፀበት በየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፣ በዚያ ስፍራ የመፍጠር ኃይሉ ማስረጃ ተጠቅሷል። “የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት [Idols] ናቸውና፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሰራ” [መዝ 96÷5]። “እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ ዓይናችሁን ወደ ላይ አንስታችሁ ተመልከቱ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው?” “ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር እርሱም ምድርን የሰራ ያደረገ….እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም” [ኢሳ 40÷25፣26፤ 45÷18]። ባለመዝሙሩ እንዲህ ይላል፣ “እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደሆነ እወቁ እርሱ ሰራን እኛም ራሳችን አይደለንም፤ ኑ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንበርከክ” [መዝ 100÷3፤ 95÷6]። በሰማይ ያሉ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ቅዱስ ፍጡራን አክብሮታቸው ለእግዚአብሔር ለምን እንደሆነ ምክንያት ሲሰጡ፣ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል።” [ራዕይ 4÷11] ይላሉ።GCAmh 316.2

    በራእይ 14 ሰዎች ፈጣሪን እንዲያመልኩ ተጠርተዋል፤ በሶስት እጥፍ መልእክት አማካኝነትም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እየጠበቁ ያሉ ሰዎች እንዳሉ ትንቢቱ ወደ እይታ ያመጣዋል። ከእነዚህ ትዕዛዛት ውስጥ አንዱ እግዚአብሔር ፈጣሪ እንደሆነ በቀጥታ ወደ እርሱ የሚጠቁም ነው። አራተኛው መመሪያ “ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው…. እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን ባህርንም ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን አርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም” [ዘፀ 20÷10፣11] ይላል። ሰንበትን በተመለከተ እግዚአብሔር በተጨማሪ ሲናገር፣ “እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቁ ዘንድ … ምልክት ነው” አለ [ሕዝ 20÷20]። የተሰጠው ምክንያትም፣ “እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ፣ በሰባተኛውም ቀን ከሰራው ስላረፈና ስለተነፈሰ ነው።” [ዘፀ 31÷17]።GCAmh 316.3

    “የሰንበት እንደ የፍጥረት መታሰቢያነት አስፈላጊ የሆነው፣ አምልኮ የሚገባው እግዚአብሔር እንደሆነ እውነተኛውን ምክንያት ሁልጊዜ አዲስ ስለሚያደርገው ነው”፤ ምክንያቱም እርሱ ፈጣሪ እኛ ደግሞ የእርሱ ፍጡራን ነንና። “ስለዚህም ሰንበት በመለኮታዊ አምልኮ መሰረት ላይ ያለች ናት፤ ምክያቱም ይህንን ታላቅ እውነት ተወዳዳሪ በሌለው ግሩም አኳኋን ታስተምራለች፤ ሌላ ማንኛውም ተቋም እንደዚህ አያደርግም። እውነተኛው የመለኮታዊ አምልኮ መሰረት፣ በሰባተኛው ቀን የሚደረገው አምልኮ ብቻ ሳይሆን የሁሉም አምልኮዎች መሰረት፣ የሚገኘው በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ባለው ልዩነት ውስጥ ነው። ይህ ታላቅ ጭብጥ ሊያረጅ የሚችል አይደለም፤ ፈጽሞ ሊረሳም አይገባውም።”-J.N. Andrews, History of the Sabbath, Chapter 27’ ይህንን እውነት በሰዎች አዕምሮ ምንጊዜም ለማስቀመጥ ነበር እግዚአብሔር ሰንበትን በኤደን ገነት ያስቀመጠው፤ እርሱን ልናመልከው የሚገባን ምክንያቱ ፈጣሪያችን ስለሆነ የመሆኑ እውነታ እስካላቋረጠ ድረስ፣ ሰንበት የዚህ እውነት ምልክትና መታሰቢያ ሆና ትቀጥላለች። ሰንበት በአለማቀፋዊነት ሁሉ ተጠብቃ ቢሆን ኖሮ አምልኮና ክብር የሚገባው ፈጣሪ መሆኑን ያስተውል ዘንድ የሰው ሃሳብና ፍላጎት ወደ እርሱ ይመራ ነበር፤ ጣዖት አምላኪ፣ እምነት የሌለው ወይም ከኃዲም በፍፁም አይኖርም ነበር። ሰንበትን መጠበቅ “ሰማይንና ምድርን ባህርንም የውኃንም ምንጮች ለሰራው” ለእውነተኛው እግዚአብሔር ታማኝ የመሆን ምልክት ነው። ከዚህም በመነሳት እግዚአብሔርን እንዲያመልኩና ትዕዛዛቱንም እንዲጠብቁ የሚያዘው መልእክት፣ አራተኛውን ትዕዛዝ በተለየ ሁኔታ እንዲጠብቁት ይጠራቸዋል።GCAmh 317.1

    የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ከሚጠብቁና የየሱስ እምነት ካላቸው በተቃራኒ፣ ሶስተኛው መልአክ የሚጠቁምባቸው “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ደግሞ ከእግዚአብሔር ቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል” ተብሎ በጥፋቶቻቸው ላይ ከባድና አስፈሪ ማስጠንቀቂያ የተቀሰረባቸው፣ ሌላ መደብ (የሕብረተሰብ ክፍሎች) አሉ [ራእይ 14÷9፣10]። ይህንን መልእክት ለመረዳት ጥቅም ላይ የዋሉትን ተምሳሌቶች በትክክል መተርጎም አስፈላጊ ነው። በአውሬው፣ በምስሉ፣ በምልክቱ፣ የተወከለው ምንድን ነው?GCAmh 317.2

    እነዚህ ተምሳሌቶች የሚገኙበት የትንቢት አረፍተ ነገር የሚጀምረው፣ በራእይ 12 ክርስቶስ ሲወለድ ለመግደል በሚጥረው አውሬ ነው። ዘንዶው ሰይጣን እንደሆነ ተነግሯል።[ ራእይ 12÷9]። አዳኙን ለመግደል በሄሮድስ ላይ የተንቀሳቀሰው እርሱ ነበር። ነገር ግን የሰይጣን ዋና ወኪል የነበረው በመጀመሪያዎቹ የክርስቲያን ምዕተ ዓመታት በክርስቶስና በሕዝቦቹ ላይ ጦርነት ሲያደርግ የነበረው፣ ቀዳሚ ሐይማኖቱ (በስፋት ተንሰራፍቶበት የነበረው ኃይማኖት) ጣዖት አምልኮ የነበረው፣ የሮማ መንግሥት ነበር። ስለሆነም ዘንዶው በዋነኛነት የሚወክለው ሰይጣንን ሆኖ ሳለ በሁለተኛ ደረጃ የጣዖት አምላኪዋ ሮምም ተምሳሌት ነው።GCAmh 317.3

    በምዕራፍ 13 [ከቁጥር 1-10] ሌላ አውሬ ተጠቅሷል። “ነብር ይመስል ነበር።” ዘንዶውም “ሃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ስልጣን” የሰጠው ነው። ይህ ተምሳሌት አብዛኛዎቹ ፕሮቴስታንቶች እንደሚያምኑት በጥንታዊው የሮም ግዛት ተይዞ የነበረውን ኃይል ዙፋንና ስልጣን የተካውን የጳጳሳዊውን ሥርዓት የሚወክል ነው። ነብር ስለሚመስለው አውሬ እንዲህ ተብሏል፣ “ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው…. እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውን በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ። ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው። በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ስልጣን ተሰጠው።” ይህ በዳንኤል 7 ላይ ከተጠቀሰው ትንሽ ቀንድ መግለጫ ጋር ሙሉ ለሙሉ አንድ አይነት ሊሆን ምንም የማይቀረው ትንቢት ያለምንም ጥርጥር የሚጠቁመው ወደ ጳጳሳዊው ሥርዓት ነው።GCAmh 317.4

    “አርባ ሁለት ወርም እንዲሰራ ስልጣን ተሰጠው።” ነቢዩ ሲናገር፣ “ከራሶቹም ለሞት እንደታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ” [I saw one of his heads as it was wounded to death) [ራእይ 13÷3]። እንደገናም “ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገደል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል።” አርባ ሁለቱ ወራት በዳንኤል 7 ላይ ካሉት ሶስት ዓመት ተኩል ወይም 1260 ቀናት “እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኩሌታ ዘመንም” ከተባሉት ጋራ እኩል ናቸው። ይህም ጊዜ የጳጳሳዊው ስልጣን የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚጨቁንበት ዘመን ነበር። ይህ ጊዜ በቀደሙት ምዕራፎች እንደተገለጸው፣ ጳጳሳዊው ሥርዓት በ538 ዓ.ም ሲቋቋም የጀመረ ሲሆን በ1798 ዓ.ም አብቅቷል። በዚያን ጊዜ ጳጳሳዊው ስርዓቱ ተገርስሶ ሊቀ ጳጳሱም በፈረንሳይ ጦር እስረኛ ሲሆን ጳጳሳዊው ኃይል የሞቱ ቁስል ደረሰበት፤ እናም ሊማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል የሚለው ትንቢት ተፈፀመበት።GCAmh 318.1

    በዚህ ጊዜ ሌላ ተምሳሌት ይተዋወቃል። ነብዩ እንዲህ ይላል፣ “ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ የበግ ቀንዶችም የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት።” [ራዕይ 13÷11]። የዚህ አውሬ መልክና የተነሳበት አኳኋን የሚወክለው ሕዝብ (መንግሥት) ባለፉት ተምሳሌቶች ከተወከሉት የተለየ እንደሆነ ያመለክታል። ዓለምን የሚገዙት ታላላቅ መንግሥታት “አራቱ የሰማይ ነፋሳት በታላቁ ባህር ላይ” [ዳን 7÷2] የሚነሱ፣ አደን የሚያድኑ አራዊት ሆነው ለነብዩ ዳንኤል ታይተዋል። በራዕይ 17፣ ውኃዎች “ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም” [ራዕይ 17÷15] እንደሚወክሉ መልአኩ አብራርቷል። ነፋሳት ደግሞ የጥል ተምሳሌቶች ናቸው። በታላቁ ባህር ላይ የሚጋጩት አራቱ የሰማይ ነፋሳት፣ መንግሥታት ወደ ኃይልና ስልጣን ሲመጡ የሚያደርጉትን የወረራና የአብዮት አሰቃቂ ትዕይንት የሚወክል ነው።GCAmh 318.2

    የበግ የሚመስሉ ቀንዶች የነበሩት አውሬ ግን የታየው “ከምድር ሲወጣ” ነበር። ራሱን ያቋቁም ዘንድ ሌሎች ኃይላትን ገልብጦ በመውጣት ፈንታ በዚህ የተወከለው መንግሥት፣ በፊት ተይዞ ባልነበረ ምድር መነሳት ያለበት ሲሆን፣ ቀስ በቀስ በሰላማዊ መንገድ የሚያድግ ይሆናል። “ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም” ያሉበት፣ በሚናወጥ ባህር፣ ከተጨናነቀውና ከሚታገለው የአሮጌው ዓለም ሕዝብ መካከል የሚነሳ አይሆንም ማለት ነው። በምዕራባዊው አሕጉር መታሰስ አለበት።GCAmh 318.3

    በ1798 ዓ.ም እያደገ የነበረ ኃይል፣ የጥንካሬና የታላቅነት ተስፋ ሰንቆ የዓለምን ትኩረት እየሳበ የነበረ የአዲሱ ዓለም መንግሥት ማን ነበር? የተምሳሌቱ ፍቺ ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም። የዚህን ትንቢት ዝርዝር የሚያሟላ አገር አንድና አንድ ብቻ ነው። ያለምንም ጥርጥር የሚያመለክተው ወደ ተባበሩት አሜሪካ (United States of America) ነው። ከቅዱሱ ፀሐፊ ቃላት ጋር ሙሉ ለሙሉ አንድ ሊሆኑ ምንም ባልቀራቸው የሚደጋገሙ ሐሳቦች፣ ስለዚህች አገር መነሳትና ማደግ፣ ተናጋሪውና የታሪክ አዋቂው በውል ሳያስተውል በተመሳሳይ ቋንቋ ገልጾታል። አውሬው የታየው “ከምድር ሲወጣ” ነበር፤ እንደ ተርጓሚዎች ከሆነ እዚህ ላይ የተጠቀመው “ሲወጣ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው “ሲያድግ ወይም እንደ ቡቃያ ሲያቆጠቁጥ” ማለት ነው። እንደተመለከትነውም ይህች አገር ቀደም ብሎ ባልተያዘ ምድር መነሳት አለባት። አንድ የታወቀ ፀሃፊ የአሜሪካን መነሳት ሲገልጽ፤ “ ከባዶ ስፍራ የመውጣትዋ ምስጢር”ን ሲገልጽ “ ድምጽ ሳያሰማ እንደሚያድግ ዘር ወደ ታላቅ መንግሥት አደግን” ይላል [G. A. Townsend, in The new World compared with the Old ገጽ 462]። በ1850 ዓ.ም አንድ የአውሮፓ መጽሄት ስለ አሜሪካ ግሩም ግዛትነት ሲናገር፣ “ብቅ እያለ ያለ፣” ዝም ባለው ምድር መካከል ኃይልና ክብር በየቀኑ እየጨመረ ያለ” በማለት ገልፆታል [The Dublin Nation]። ኤድዋርድ ኢቨሬት ይህችን አገር ስለገነቡ የሐይማኖት ስደተኞች ሲናገር፦ “ገላጣ ካለመሆኑ የተነሳ ደስ የማይል ነገር የሌለው፣ ገለል ያለ፣ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ ፈላጭ ቆራጮች የማያዘወትሩት፣ ከአደጋ ነፃ የሆነ ስፍራ፣ ትንሽዋ የለይዳን ቤተ ክርስቲያን የህሊና ነፃነት የምታገኝበት ስፍራ ፈልገው ነበርን? እነሆ በሰላም የተያዙት ታላላቅ ክፍለ ሀገራት…. እነርሱ የመስቀሉን መፈክሮች ተሸክመዋል።”-Speech Delivered at Plymouth, Massachusetts, Dece. 22, 1824, ገጽ 11’GCAmh 318.4

    “የበግ ቀንዶች የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት።” የበግ ቀንድ የሚመስሉት ቀንዶች ወጣትነትን፣ የዋህነትንና ገርነትን የሚያመለክቱ ሲሆን፣ ለነብዩ “ሲወጣ” ተብሎ የተነገረውን በ1798 ዓ.ም የአሜሪካ የነበራትን ባህርይ በትክክል የሚገልጽ ነው። መጀመሪያ ወደ አሜሪካ ኮብልለው የሄዱት ክርስቲያኖች ከንጉሣዊ ጭቆናና ከኃይማኖት መሪዎች ተቀባይነት ማጣት ለመራቅ ፍላጎታቸው ነበረ። በግለሰባዊና በሐይማኖታዊ ነፃነት ሰፊ መሰረት ላይ የቆመ መንግሥት ለማቋቋም ቁርጥ ሃሳብ ነበራቸው። የነፃነት አዋጁ፣ “ሰዎች ሁሉ የተፈጠሩት እኩል ነው” የሚለውን ታላቅ እውነት የያዘ “ለሕይወት፣ ለነፃነትና ለደስታ መሻት” ያለውን ሊጣስ የማይችል መብት የተጎናፀፉ ናቸው ሲል ያስቀምጠዋል። በሕዝቡ የተመረጡ ወኪሎች ሕግ እንዲያወጡና ያንን ሕግም እንዲያስተዳድሩ የሚያደርግ፣ ህገ መንግሥቱ ለሕዝቡ በራሳቸው የመተዳደርን መብት የሚያረጋግጥ ነው። እያንዳንዱ ሰው ህሊናው በመራው መንገድ እግዚአብሔርን ማምለክ ይችል ዘንድ የኃይማኖት ነፃነትም ተሰጥቶ ነበር። ሪፐብሊካዊነትና ፕሮቴስታንታዊነት የሃገሪቱ አብይ መርሆዎች ሆኑ። የኃይልዋና የብልጽግናዋ ምስጢራት እነዚህ መርሆዎች ናቸው። በክርስቲያኑ ዓለም ሁሉ የተጨቆኑና የተረገጡ በፍላጎትና በተስፋ ወደዚህች አገር ፊታቸውን አዙረዋል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ እርስዋ መግባት ይሻሉ፤ በምድር ካሉ ኃያላን መንግሥታት አንዷ የመሆንን ስፍራ በመያዝ አሜሪካ ተመንድጋለች።GCAmh 319.1

    ነገር ግን የበግ የሚመስሉ ቀንዶች የነበሩት “እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር በፊተኛውም አውሬ ስልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቁስል ለተፈወሰለት ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል…. የሰይፍም ቁስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬውም ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።” [ራዕይ 13÷11-14]።GCAmh 319.2

    ተምሳሌቱ የበግ የሚመስሉ ቀንዶችና የዘንዶ ድምጽ፣ በተወከለችዋ አገር ንግግርና ድርጊት መካከል ያለውን አስደናቂ መጣረስ የሚጠቁም ነው። “ይናገራል” የሚለው የሃገሪቱ የሕግ አውጪና ተርጓሚ ባለስልጣናትን ድርጊት የሚያሳይ ነው።ይህን በመተግበርም የመርሀ-ግብሩ መሰረት እንደሆኑ አድርጎ ላስቀመጣቸው ለነዚያ ነፃ አስተሳሰብ እና ሰላማዊ መርሆዎች የማስመሰል መልክ ይሰጣቸዋል። “እንደ ዘንዶ” ይናገራል “በፊተኛውም አውሬ ስልጣን ሁሉን ያደርጋል” የሚለው ትንቢት በግልጽ የሚተነብየው በዘንዶውና በነብር መሰል አውሬ የተወከሉት መንግሥታት ሲያንፀባርቁት የነበረውን ያለመቻቻልና፣ የማሳደድ መንፈስ እንደሚያጎለብት ነው። ሁለት ቀንዶች ያሉት አውሬ “ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል” ሲል የሚያመለክተው ለጳጳሳዊ ስርዓቱ ክብር ሲባል መጠበቅ ያለባቸው የተወሰኑ ትዕዛዞች የዚህችን አገር ስልጣን በመጠቀም ተግባራዊ ይሆኑ ዘንድ ይሰራል ማለት ነው።GCAmh 320.1

    እንደዚህ ዓይነቱ ድርጊት፣ ለዚህ መንግሥት መርሆዎች፣ ጠንካራ ተጽዕኖ ማሳረፍ ለሚችሉት ነፃ ተቋሞችዋ፣ ለነፃነት አዋጁ ቀጥተኛና ክቡር መኃላዎች እንዲሁም ለህገ መንግሥቱ በቀጥታ ተፃራሪ ይሆናል። መንግሥታዊ ኃይል በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቅም ላይ እንዳይውል የማይቀረውም ያለመቻቻልና የስደት ውጤቱ እንዳይከሰት የሃገሪቱ መሥራቾች በጥንቃቄ እንዲጠበቅ ለማድረግ ጥረዋል። ህገ መንግሥቱ፣ “የተወካዮች ምክር ቤቱ የአንድ ኃይማኖታዊ ተቋምን በተመለከተ እንዲከበር የማድረግ ወይም [ያንን ኃይማኖት] በነፃነት የመከተል መብትን የሚከለክል ሕግ ማውጣት አይችልም።” በተጨማሪም “በአሜሪካ ውስጥ እንደ የሙያ መመዘኛ ሆኖ የሚቀርብ፣ መንግሥታዊ የሥራ ክፍልን ለመያዝ (ሥራ ለመቀጠር) የሚረዳ፣ ኃይማኖታዊ ፈተና፣ መስፈርት ሆኖ መቅረብ ፈጽሞ አይችልም” ይላል። አንድ ኃይማኖት እንዲመለክ የሚያደርግ መንግሥታዊ ትዕዛዝ ሊወጣ የሚችለው የአገሪቱን ነፃነት ለመጠበቅ የተቀመጡትን እነዚህን ቅጥሮች በአይነ-ደረቅነት ከጣሰ ብቻ ነው። የዚህ ድርጊት ተለዋዋጭነት (ወጥ አለመሆን) ግን በተምሳሌቱ ከተወከለው ባህርይ የሚበልጥ አይደለም። በሙያው ንፁህ፣ ገር፣ ጉዳት የማያደርሰው - እንደ በግ ያሉ ቀንዶች የነበሩት - አውሬ እንደ ዘንዶ ይናገራል።GCAmh 320.2

    “ለአውሬውም ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።” እዚህ ላይ በግልጽ የሚናገረው ሕግ የማውጣት ስልጣን በሕዝቡ እጅ የሆነበት የመንግሥት መዋቅር እንዳለ ነው፤ ይህም በትንቢቱ የተጠቀሰችው አገር አሜሪካ እንደሆነች ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ማስረጃ ነው።GCAmh 320.3

    ነገር ግን የ “አውሬውም ምስል” ምንድን ነው፣ እንዴትስ ነው የሚቀረጸው? ምስሉ የሚሰራው ሁለት ቀንድ ባለው አውሬ ሲሆን ለመጀመሪያው አውሬ የሚሰራ ምስል ነው። የአውሬው ምስል በመባልም ይታወቃል። ምስሉ ምን እንደሚመስልና እንዴትስ እንደሚቀረጽ (እንደሚሰራ) ለመረዳት፣ የራሱን የአውሬውን - የጳጳሳዊ ስርዓቱን - ባህርያት ማጥናት ያስፈልገናል። ቀላልና ቀና ከሆነው ወንጌል በመራቅና፣ የአሕዛብን የአምልኮ ሥርዓትና ባህል በመያዝ የቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን ራስዋን ስታበላሽ፣ የእግዚርአብሔርን መንፈስና ኃይል አጣች። የሰዎችን አዕምሮ (ህሊና) ልትቆጣጠር ስትፈልግም የመንግሥትን ኃይል ድጋፍ ፈለገች። በውጤቱም የመንግሥትን ኃይል የተቆጣጠረች፣ የራስዋን ፍላጎት ለማጎልበት፣ በተለይም “ኑፋቄን” ለመቅጣት የመንግሥትን ኃይል የተጠቀመች ቤተ ክርስቲያን ተፈጠረች፤ ያም ጳጳሳዊው ሥርዓት ነበር። የአሜሪካ የአውሬውን ምስል ለመቅረጽ ይቻላት ዘንድ፣ የሐይማኖታዊው ኃይል ሕዝባዊ መንግሥቱን ተቆጣጥሮ፣ ቤተ ክርስቲያን የመንግሥትን ስልጣን ተጠቅማ የራስዋን አላማ ማሳካት መቻል አለባት።GCAmh 320.4

    ቤተ ክርስቲያን የመንግሥትን ኃይል ባገኘችበት ጊዜ ሁሉ አስተምህሮዎቿን የሚቃወሙትን ለመቅጣት ስትጠቀምበት ኖራለች። የሮምን ፈለግ በመከተል ከዓለም ስልጣናት ጋር ህብረት የፈጠሩ የፕሮቴስታንትን አብያተ ክርስቲያናት የህሊናን ነፃነት የመገደብ ተመሳሳይ ዝንባሌ እንዳላቸው አሳይተዋል። የዚህም ምሳሌ የሚሆን የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ተቃዋሚዎችዋን ለረጅም ዘመን ስታሳድድ የኖረች መሆንዋ ነው። በአሥራ ስድስተኛውና በአሥራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመናት፣ ከርስዋ ጋር ያልተስማሙ በሺዎች የሚቆጠሩ አገልጋዮች አብያተ ክርስቲያናቸውን እንዲለቁ ሲገደዱ፣ ፓስተሮችንና ምዕመናንን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ለቅጣት፣ ለእስር፣ ለግርፋትና ለሰማዕትነት ተዳርገዋል።GCAmh 321.1

    የቀደመችው ቤተ ክርስቲያን የመንግሥትን እርዳታ እንድትሻ የመራት ክህደት ነበር። ይህም ጳጳሳዊው ሥርዓት - አውሬው - እንዲመሰረት መንገድ አመቻቼ። ጳውሎስ “ክህደቱ አስቀድሞ….የኃጢአት ሰው” እንደሚገለጥ ያወሳል [There come a falling away first/መጀመሪያ ክህደቱ ይከናወናል፣ and that man of sin ከዚያም የኃጢአት ሰው ይገለጣል] [2ኛ ተሰሎ 2÷3]። ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው ክህደት ለአውሬው ምስል መንገድ ያዘጋጃል። ጌታ ከመገለጡ በፊት፣ በመጀመሪያዎቹ ምዕተ ዓመታት የነበረው አይነት ኃይማኖታዊ ማሽቆልቆል እንደሚከሰት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። “ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንደሚመጣ ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና ገንዘብን የሚወዱ ትምክህተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ እርቅን የማይሰሙ፣ ኃሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ከዳተኞች፣ ችኩሎች፣ በትዕቢት የተነፉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፣ የአምልኮ መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል።” [2ኛ ጢሞ 3÷1-5]። “መንፈስ ግን በግልጥ፣ በኋለኛው ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ ሐይማኖትን ይክዳሉ ይላል”[1ኛ ጢሞ 4÷1]። ሰይጣን “በተዓምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኛ ድንቆችም በዓመጽም መታለል ሁሉ” ይሰራል “ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር” ያልተቀበሉ ሁሉ “ሐሰትን ያምኑ ዘንድ… የስህተትን አሰራር”ም እንዲቀበሉ ይተዋሉ’ [2ኛ ተሰሎ 2÷9-11]። ከዚህ ዓይነቱ ቅድስና-አልባነት ደረጃ ላይ ሲደረስ፣ በመጀመሪያዎቹ ምዕተ ዓመታት የታዩት እነዚያው ውጤቶች ይከተላሉ።GCAmh 321.2

    በፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያለው መጠነ-ሰፊ የአይነት ብዛት (diversity)፣ በግድ አንድ አይነት ለማድረግ መቼም ቢሆን ጥረት ሊደረግ እንደማይችል የማያወላውል ማረጋገጫ እንደሆነ በብዙዎች ይታመናል። ሆኖም በፕሮቴስታንት እምነት ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ጠንካራና እያደገ ያለ ተመሳሳይ የአስተምህሮ ነጥቦችን መሰረት በማድረግ ወደ አንድነት የመምጣት ጽኑ ፍላጎት ለዓመታት ሲታይ ቆይቷል። እንደዚህ አይነቱን ህብረት እውን ለማድረግ፣ ለውይይት በቀረቡ ርዕሶች ላይ በሁሉም መስማማት ባይቻልም፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንፃር [ልዩነቶቹ] መሰረታዊ ቢሆኑም፣ መተዋቸው ግን የግድ አስፈላጊ ይሆናል።GCAmh 321.3

    ቻርለስ ቢቸር በ1846 ዓ.ም ላይ በሰበከው ስብከት ሲናገር፣ “የኢቫንጀሊካል ፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት” የወንጌል አገልግሎት “ከላይ እስከ ታች መጠነ ሰፊ በሆነ የፍጡር ፍርሃት ግፊት እንዲሁ የተመሠረተ ብቻ ሳይሆን የሚኖሩት፣ የሚንቀሳቀሱትና የሚተነፍሱትም ፍፁም ብልሹ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ነው። በየሰዓቱ ለእያንዳንዱ ለተዋረደው ማንነታቸው (ተፈጥሮአቸው) በማጎንበስ እውነትን ጭጭ ለማሰኘት የሚሹ፣ ለክህደትም ጉልበታቸውን የሚያንበረክኩ ናቸው። በሮም ጊዜስ ነገሮች ሲካሄዱ የነበሩት እንዲህ አልነበረምን? ሕይወትዋን (ሮምን) እየኖርነው አይደለም? ከዚህ ቀጥሎስ በቅርቡ የምናየው ምንድን ነው? ሌላ ጠቅላይ ጉባኤ! ዓለም አቀፍ ስብሰባ! የወንጌል (ኢቫንጀሊካል) ህብረት! አለማቀፋዊ እምነት!”- Surmon on “The Bible a Sufficient Creed” Delivered at Fort Wayne, Indiana, Feb. 22, 1846’ ይህንን ማከናወን በተቻለ ጊዜ፣ ፍፁም አንድ አይነትነትን ለማረጋገጥ፣ ኃይልም ለመጠቀም፣ አንድ እርምጃ ብቻ የሚበቃ ይሆናል።GCAmh 322.1

    የአሜሪካ አበይት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉም በሚቀበሏቸው የጋራ አስተምህሮዎቻቸው ነጥቦች ላይ አንድነትን ፈጥረው አዋጆቻቸውን ተግባራዊ እንዲያደርግና ተቋሞቻቸውን ደግፎ እንዲያቆም በመንግሥት ላይ ተጽዕኖ ማድረግ ሲችሉ፣ ያን ጊዜ የሮም መዋቅር/የጳጳሳዊ ሥርዓት ምስል በፕሮቴስታንት አሜሪካ ይቀረፃል ማለት ነው፤ ይህንን በማይቀበሉ ላይ ቅጣት መበየኑ የማይቀረው ውጤት ይሆናል።GCAmh 322.2

    ሁለት ቀንዶች ያሉት አውሬ “ታናናሾችና ታላላቆችም ባለጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፣ የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቁጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል [ያዛል]” [ራዕይ 13÷16፣17]። የሶስተኛው መልአክ ማስጠንቀቂያ “ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ በግንባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ደግሞ… ከእግዚአብሔር ቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል” ይላል። በዚህ መልእክት የተጠቀሰው፣ ይመለክም ዘንድ ሁለት ቀንዶች ባሉት አውሬ ተፈፃሚ የሚደረግለት፣ “አውሬው” የተባለው የመጀመሪያው፣ በራዕይ 13 ነብር መሰል አውሬ የተባለው፣ እርሱም ጳጳሳዊው ሥርዓት ነው። “ለአውሬውም ምስል” ደግሞ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት፣ ህገ-ሐይማኖታቸው በኃይል ተፈፃሚ እንዲሆኑ የመንግሥትን ኃይል ድጋፍ በሚሹበት ጊዜ የሚገነባውን የከሃዲ ፕሮቴስታንታዊነትን ምስል የሚወክል ነው። “የአውሬው ምልክት” ገና ማብራሪያ ይሰጠዋል።GCAmh 322.3

    ስለ አውሬውና ምስሉ አምልኮ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ ትንቢቱ ሲቀጥል፣ “የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁ የሱስንም በማመን የሚፀኑት ቅዱሳን” እነዚህ ናቸው ይላል። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁ አውሬውንና ምስሉን ከሚያመልኩ ምልክቱንም ከሚቀበሉት በተቃራኒ ጎራ በመሰለፋቸው ምክንያት፣ በአንድ በኩል የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጠበቅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ መጣስ፣ በእግዚአብሔር አምላኪዎችና በአውሬው አምላኪዎች መካከል መለያ ይሆናል ማለት ነው።GCAmh 322.4

    የአውሬው የተለየ ባህርይ፣ ብሎም የምስሉም ጠባይ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጣስ ነው። ስለ ትንሹ ቀንድ፣ ጳጳሳዊው ሥርዓት፣ ዳንኤል ሲናገር “ዘመናትና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል” ይላል [ዳን 7÷25]። ይህንን ራሱን ከእግዚአብሔር በላይ ከፍ ከፍ የሚያደርገውን ኃይል ጳውሎስ ሲገልፀው፣ “የኃጢአት ሰው” ይለዋል። አንዱ ትንቢት የሌላኛው ትንቢት መሙያ (ማጠናከሪያ) ነው። የጳጳሳዊው ሥርዓት ራሱን ከእግዚአብሔር በላይ ከፍ ከፍ የሚያደርግበት ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በመለወጥ ነው፤ በዚህ ሁኔታ፣ የተለወጠውን ሕግ፣ እያወቀ፣ የሚያከብር እርሱ ሕጉን ለቀየረው አካል ሉዓላዊ ክብር ይሰጣል ማለት ነው። እንዲህ ዓይነቱ ለጳጳሳዊ ሥርዓት የሚደረገው ታዛዥነት፣ በእግዚአብሔር ፈንታ ለሊቀ ጳጳሱ የታማኝነት ምልክት ይሆናል።GCAmh 323.1

    ጳጳሳዊ ሥርዓት የእግዚአብሔርን ሕግ ለመለወጥ ሞክሯል። ምስልን ማምለክ የሚከለክለው ሁለተኛው ትዕዛዝ፣ ከአሥርቱ ትዕዛዛት እንዲወጣ ተደርጓል፤ አራተኛውም ትዕዛዝ፣ ሰባተኛውን ቀን ሳይሆን የመጀመሪያውን ቀን እንደ ሰንበት ማክበር እንዲቻል ተደርጎ ተለውጧል። ጳጳሳዊያኑ ግን ሁለተኛውን ትዕዛዝ ስለመተዋቸው ምክንያት ሲያቀርቡ በመጀመሪያው ትዕዛዝ ውስጥ ስለተጠቃለለ አላስፈላጊ ነው ይላሉ፤ ሕጉ ይስተዋል ዘንድ እግዚአብሔር እንዳቀደው፣ እንደዛው አድርገው እንዳቀረቡት ይናገራሉ። ይህ በነብዩ የተተነበየው ለውጥ ሊሆን አይችልም። ሆን ተብሎ ታስቦበት የተደረገ ለውጥ ይስተዋላል። “ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል።” በአራተኛው ትዕዛዝ ላይ የሚደረገው ለውጥ ትንቢቱን በትክክል ይፈጽመዋል። ለዚህ ድርጊት ጥቅም ላይ እንደዋለ የተጠቀሰው ብቸኛ ስልጣን የቤተ ክርስቲያን ነው። እዚህ ላይ ጳጳሳዊው ስልጣን በገሃድ ራሱን ከእግዚአብሔር በላይ ያስቀምጣል።GCAmh 323.2

    የመፍጠር ኃይሉ ምልክት በመሆኑ፣ እንዲሁም ፍጡር ሊያከብረውና ሊያመልከው የሚገባ ስለመሆኑ ምስክር ስለሆነ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ለአራተኛው ትዕዛዝ በሚሰጡት ትኩረት በተለየ ሁኔታ የሚለዩ ሆነው ሳለ፣ የአውሬው አምላኪዎች ደግሞ የእግዚአብሔርን መታሰቢያ ቦጫጭቀው በመጣል የሮምን ተቋም ከፍ ከፍ ለማድረግ በሚወስዱት ጥረት ተለይተው ይታወቃሉ። ጳጳሳዊ ስርዓቱ የእብሪት መጠየቁን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰነዘረው እሁድን በሚመለከት ነበር [በመግለጫ ስር ማስታወሻ 9ን ይመልከቱ]። የመንግሥትን ስልጣን የተጠቀመበት የመጀመሪያ ተግባሩ እሁድ እንደ “የጌታ ቀን” እንዲከበር በማስገደድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሳየው የጌታ ቀን ሰባተኛው ቀን እንደሆነ እንጂ የመጀመሪያው ቀን እንደሆነ አይደለም። ክርስቶስ ሲናገር “የሰው ልጅ የሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው አላቸው።” አራተኛው ትዕዛዝ የሚያውጀው “ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው” በማለት ነው። በነብዩ ኢሳይያስ በኩልም ጌታ “የተቀደሰው ቀኔ” በማለት ይሰይመዋል። [ማር 2÷28፤ ኢሳ 58÷13]።GCAmh 323.3

    ክርስቶስ ሰንበትን እንደቀየረ ተደርጎ በተደጋጋሚ የሚነሳው ክርክር በራሱ ቃላት ፉርሽ የተደረገ ነው። በተራራው ስብከቱ ላይ እንዲህ አለ፦ “እኔ ሕግንና ነብያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም ሁሉ እስኪፈፀም ድረስ። እንግዲህ ከእነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትዕዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል። የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥት ሰማያት ታላቅ ይባላል።” [ማቴ 5÷17-19]።GCAmh 323.4

    መጽሐፍ ቅዱስ ለሰንበት መለወጥ ስልጣን እንዳልሰጠ በፕሮቴስታንቱ ዓለም የማይካድ ሐቅ ነው። ይህ እውነት የአሜሪካ በራሪ ጽሑፎች ማህበር (American Tract Society) እና የአሜሪካ እሁድ ሰንበት ትምህርት ህብረት (American Sunday-School Union) በሚያወጧቸው ህትመቶች ውስጥ በግልጽ ተቀምጦአል። ከእነዚህ ሥራዎች መካከል አንዱ “ሰንበትን [እሁድን፣ የሳምንቱን የመጀመሪያ ቀን] በተመለከተ የተሰጠ ትዕዛዝ ወይም ስለ አከባበሩ የተሰጡ ግልጽ መመሪያዎችን በተመለከተ አዲስ ኪዳን ምንም የሚናገረው ነገር እንደሌለ” ይመሰክራል። [George Elliott, “The Abiding Sabbath”, ገጽ 184, a $ 500 prize essay]።GCAmh 324.1

    ሌላኛው ደግሞ “ክርስቶስ እስከሞተበት ቀን ድረስ በቀኑ ላይ የተደረገ ለውጥ አልነበረም” እናም “መዝገቡ እንደሚያመለክተው እነርሱ [ሐዋርያቱ] ሰባተኛው ቀን ሰንበትን ስለመተውና መከበሩም ወደ ሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን እንዲለወጥ ስለማዘዛቸው የሚያሳይ ግልጽ ትዕዛዝ የለም።” [A. E. Waffle, “The Lord’s Day”, pp 185,186 a $1000 prize essay]።GCAmh 324.2

    የሰንበት መቀየር የተፈፀመው በቤተ ክርስቲያናቸው አማካኝነት እንደሆነ ካቶሊኮች ያረጋግጣሉ፤ ፕሮቴስታንቶችም እሁድን በማክበራቸው ለሮም ቤተ ክርስቲያን ስልጣን እውቅና እየሰጡ እንደሆነ ይናገራሉ። “በክርስትና ሐይማኖት የካቶሊክ ማስተማሪያ መጽሐፍ/Catholic Cathechism of Christian Religion” ውስጥ አራተኛውን ትዕዛዝ ለመታዘዝ፣ መጠበቅ ስላለበት ቀን ለቀረበ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ የሚከተለው አረፍተ ነገር ይነበባል፦ “በአሮጌው ሕግ የተቀደሰው ቀን ቅዳሜ ነበር፤ ሆኖም ግን ቤተ ክርስቲያንዋ በክርስቶስ ታዛ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርታ፣ ቅዳሜን በእሁድ ተክታለች፤ ስለዚህ አሁን የምንቀድሰው ሰባተኛውን ቀን ሳይሆን የመጀመሪያውን ቀን ነው። እሁድ ማለት፣ ልክ አሁን እንደተደረገው፣ የጌታ ቀን ነው።”GCAmh 324.3

    የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስልጣን ምልክት እንደሆነ አድርገው ጳጳሳዊ ፀሃፊዎች ሲጠቅሱ “ሰንበትን ወደ እሁድ የመለወጡ ያው ድርጊት፣ ፕሮቴስታንቶችም ፈቃድ የሰጡበት ድርጊት ነው…. ምክንያቱም እሁድን ውልፍት ሳይሉ በማክበራቸው ቤተ ክርስቲያን በዓላትን የማቋቋምና የማጽደቅ እንዲሁም አለማክበር ኃጢአት እንደሆነ ትዕዛዝ የማስተላለፍ ስልጣን እንዳላት እውቅና ይሰጣሉ።” [“Abridgment of Christian Doctrine”]። ታዲያ የሰንበት መለወጥ የሮማ ቤተ ክርስቲያን ስልጣን ምስል ወይም ምልክት፣ “የአውሬው ምልክት” ከመሆን ውጪ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?GCAmh 324.4

    የሮም ቤተ ክርስቲያን የበላይ ነኝ የሚል መጠይቅዋን አሁንም አልተወችም፤ ዓለምና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት እርስዋ የፈጠረችውን ሰንበት ተቀብለው፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ሰንበት ሲቃወሙ ይህንን [የበላይነትዋን] ሃሳብ ተቀብለዋል ማለት ነው። ለለውጡ የአባቶችንና የባህልን ስልጣን እንደምክንያት ቢጠቅሱም ይህንን በማድረጋቸው ግን እነርሱን ከሮም የሚለያቸውን፣ “የፕሮቴስታንት ኃይማኖት መጽሐፍ ቅዱስና መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው” የሚለውን ያንኑ መርህ ቸል ይላሉ። ለጉዳዩ እውነቶች አይኖቻቸውን በፈቃዳቸው ጨፍነው ራሳቸውን እያታለሉ እንደሆነ ጳጳሳዊው ማየት ይችላል። የእሁድ መከበር አስገዳጅ እንዲሆን የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተቀባይነት እያገኘ ሲሄድ ሁሉንም የፕሮቴስታንት ዓለም በሮም ሰንደቅ ዓላማ ስር እንደሚያሰልፍ እርግጠኛነቱ ሲሰማው ሐሴት ያደርጋል።GCAmh 324.5

    ሮማዊያኑ ሲናገሩ፣ “ፕሮቴስታንቶች እሁድን ማክበራቸው፣ ከእራሳቸው ይልቅ፣ ለ[ካቶሊክ] ቤተ ክርስቲያን ስልጣን የሚሰጡት የተለየ ክብር ነው።” [Mgr. Sḗgur, Plain talk about Protestantism of Today, page ገጽ 213]። በፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት በኩል እሁድ እንዲከበር የሚደረገው ማስገደጃ፣ የጳጳሳዊ ስርዓቱ - የአውሬው አምልኮ - ማስገደጃ ነው። አራተኛው ትዕዛዝ የሚፈልገው ምን እንደሆነ እያስተዋሉ በእውነተኛው ሰንበት ፈንታ ሐሰተኛውን ለመጠበቅ የሚመርጡ እነርሱ ይህ እንዲሆን በብቸኝነት ላዘዘው ኃይል የተለየ አክብሮት [አምልኮ] እየሰጡ ናቸው። ነገር ግን ኃይማኖታዊ ኃላፊነትን በግድ ለማስተግበር ሲሉ የመንግሥታዊ ኃይልን በመጠቀም በሚሰሩት በዚያው ድርጊት አብያተ ክርስቲያናቱ ራሳቸው ለአውሬው ምስል ይቀርጻሉ። ስለዚህም እሁድ እንዲከበር በአሜሪካ የሚወጣው አስገዳጅ ትዕዛዝ አውሬውና ምስሉ እንዲመለኩ ለማስገደድ የሚወጣ ትዕዛዝ ነው።GCAmh 325.1

    ነገር ግን እንዲህ በማድረጋቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ሰንበት እየጠበቁ እንደሆኑ ያምኑ የነበሩ ባለፈው ትውልድ የነበሩ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ በዚህ ዘመንም እሁድ የመለኮት ተቋም እንደሆነ ከልባቸው የሚያምኑ በሮማ አብያተ ክርስቲናት ውስጥ ጭምር ያሉ እውነተኛ ክርስቲያኖች አሉ። የአላማቸውን ታማኝነትና ቀናኢነታቸውን እግዚአብሔር ይቀበለዋል። የእሁድ መከበር ግን በሕግ አስገዳጅ በሚሆንበት ጊዜ፣ መላው ዓለም ለእውነተኛው ሰንበት ያለበትን ኃላፊነት በሚረዳበት ጊዜ፣ ሮም ካላት ስልጣን የበለጠ ስልጣን የሌለውን መመሪያ በመታዘዝ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጥስ ማንኛውም ሰው፣ ጳጳሳዊ ሥርዓትን ከእግዚአብሔር በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል። ለሮም የተለየ አክብሮት ይሰጣል፤ በሮም የተቀደሰውን ተቋም ተግባራዊነት አስገዳጅ ለሚያደርገው ኃይልም ክብር ይሰጣል። አውሬውንና ምስሉን ያመልካል። የስልጣኑ ምልክት አድርጎ እግዚአብሔር ያቋቋመውን ተቋም ሰዎች አንቀበልም ሲሉ፣ የበላይነትዋ ምልክት አድርጋ የመረጠችውን በመተካት ሲያከብሩ፣ ያን ጊዜ ለሮም የታማኝነት መግለጫ የሆነውን ምልክት —“የአውሬውን ምልክት” ይቀበላሉ። ጉዳዩ በግልጽ ለሰዎች ቀርቦ፣ በእግዚአብሔር ትዕዛዛትና በሰዎች ትዕዛዛት መካከል እንዲመርጡ ተደርገው፣ በምርጫቸው ሕግን መጣስ እስኪቀጥሉ ድረስ፣ [ይህን ከማድረጋቸው በፊት] “የአውሬውን ምልክት” አይቀበሉም።GCAmh 325.2

    ለፍጡር ከተሰጡ እጅግ አስፈሪ ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ የሚበልጠው በሶስተኛው መልአክ መልክት የተካተተው ነው። ከምሕረት ጋር ያልተቀላቀለውን የእግዚአብሔር ቁጣ የሚያወርድ እጅግ አሰቃቂ ኃጢአት መሆን አለበት። ይህንን አስፈላጊ ጉዳይ በተመለከተ ሰዎች በጨለማ የሚተው አይሆኑም፤ ሊቀጡ ያላቸው ለምን እንደሆነ ሁሉም ያውቁ ዘንድ፣ ያመልጧቸውም ዘንድ ዕድል እንዲያገኙ የእግዚአብሔር ፍርድ ከመውረዱ በፊት ይህንን ኃጢአት የሚያወግዘው ማስጠንቀቂያው የሚሰጥ ይሆናል። የመጀመሪያው መልአክ አዋጁን “ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም” እንደሚናገር ትንቢቱ ያውጃል። የተመሳሳዩ ሶስት እጥፍ መልእክት አካል የሆነው የሶስተኛው መልአክ ማስጠንቀቂያም ያነሰ ስርጭት አይኖረውም [እንደ መጀመሪያዎቹ መልእክቶች ለሁሉም የሚደርስ ይሆናል]። በትንቢት የተገለጸው በታላቅ ድምጽ በሚናገር በሰማይ መካከል በሚበር መልአክ እንደታወጀ ነው፤ የዓለምንም ትኩረት ያገኛል።GCAmh 325.3

    በጠቡ (በፉክክሩ) ጉዳይ የክርስትናው ዓለም በሞላ በሁለት ታላላቅ ጎራዎች ይከፈላል - የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ የየሱስም እምነት ያላቸው [በአንድ በኩል]፣ አውሬውንና ምስሉን የሚያመልኩ ምልክቱንም የሚቀበሉ [በሌላ በኩል]። ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት “ታናናሾች እና ታላላቆችም ባለጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባርያዎችም ሁሉ” የ“አውሬውን ምልክት” [ራእይ 13÷16] ይቀበሉ ዘንድ ለማስገደድ ኃይላቸውን ቢያስተባብሩም የእግዚአብሔር ሕዝቦች ግን አይቀበሉትም። የሙሴንና የበጉን መዝሙር እየዘመሩ፣ “በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቁጥር ላይ ድል ነስተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ” የፍጥሞው ነብይ ያያል [ራእይ 15÷2፣3]።GCAmh 326.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents