Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፲፫—በኔዘርላንድና በስካንዲናቪያ

    አምባገነኑ የጳጳሳዊ ሥርዓት በኔዘርላንድ ገና ቀደም ብሎ ቆራጥ ተቃውሞን ቀስቅሶ ነበር። ከሉተር ዘመን ሰባት መቶ ዓመት ቀደም ብሎ በአምባሳደርነት ወደ ሮም በተላኩና የ”ቅዱስ ስልጣን መቀመጫውን” እውነተኛ ባህርይ በተረዱ ሁለት ጳጳሳት የሮማው ሊቀ-ጳጳስ ያለፍርሃት ተወንጅሎ ነበር፦ “እግዚአብሔር ልዕልቱና ባለቤቱ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ለቤተሰብዋ የተከበረች ዘላለማዊ አቅርቦት ትሆን ዘንድ መሰረታት፤ የማይደበዝዝና የማይበላሽ እጅ መንሻ፣ ዘላለማዊ ዘውድና ንጉሣዊ በትርም ለግሶአታል። ይህ ሁሉ ግን እንደ ተቀባይ ሌባ የሆንከው አንተን የሚጠቅም ነው፤ በቤተ-መቅደስ ውስጥ እራስህን እግዚአብሔር አድርገህ መስርተሃል፤ መልካም እረኛ በመሆን ፈንታ በበጎች መካከል ያለ ተኩላ ሆነሃል። ጠቅላይ ጳጳስ መሆንህን እንድንቀበል ታደርጋለህ፤ አንተ ግን ፈላጭ ቆራጭ ነህ…. ነኝ ብለህ ራስህን እንደምትጠራው የአገልጋዮች አገልጋይ መሆን ሲገባህ፣ የጌቶች ጌታ ለመሆን ታሴራለህ…. የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለንቀትህ ትዳርጋቸዋለህ…. በምድር ዳርቻዎች የሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት ሁሉ መሥራች (አናፂ) መንፈስ ቅዱስ ነው። እኛ ዜጎች የሆንባት የአምላካችን ከተማ ሰማያትን ሁሉ ትደርሳለች፤ መለኮታዊ እንደሆነች ከምታስመስለውና ከሰማይ ጋር እኩል ነኝ ከምትለው፤ ማስተዋሌ ዘላለማዊ ነው ብላ በኩራት ከምትናገረው፤ እንዲያውም ምክንያት ማቅረብ ቢሳናትም ፈጽማ ጥፋት አጥፍታ እንደማታውቅ፣ ጥፋት መሥራትም ፈጽማ እንደማትችል ከምትናገረው፣ በቅዱስ ነብያት ባቢሎን ተብላ ከምትጠራው ከተማ ትበልጣለች።”-Gerard Brandt, History of the Reformation in and About the Low Countries, b. 1, ገጽ 6።GCAmh 175.1

    ይህንን ተቃውሞ በማስተጋባት ሌሎችም ከዘመን ዘመን ተነስተዋል። እነዚህን የተለያዩ ስፍራዎችን የሚያዳርሱ፣ በተለያየ ስም የሚታወቁ ቀደምት መምህራን የቫውዶይስ ሚስዮናዊያንን ባህርይ ተላብሰው የወንጌሉን እውቀት በሁሉም ስፍራ በማሰራጨት፣ ወደ ኔዘርላንድም ሰርገው ገቡ። አስተምህሮዎቻቸው በፍጥነት ተስፋፋ። የዋልደንሳዊያንን መጽሐፍ ቅዱስ አንድ በአንድ ወደ ደች ቋንቋ ተረጎሙት። “ከፍተኛ ጥቅም በውስጡ አለ” አሉ፣ “ቀልድ የለበትም፤ ተረት (አፈ-ታሪክ) የለበትም፤ ተራና የማይረባ ነገር የለበትም፤ ማታለያ በዚያ የለም፣ ከእውነት ቃላት በቀር በዚያ ሌላ ምንም ነገር የለም። በእርግጥ እዚህም እዛም ጠንካራ ቅርፊት አለው፤ ሆኖም በዚህ ውስጥ እንኳ መልካምና ቅዱስ የሆነው መቅኔና ጣፋጭነት በቀላሉ መገኘት የሚችል ነው። የጥንትዋ እምነት ወዳጆች በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንዲህ ብለው ፃፉ።GCAmh 175.2

    አሁን የሮማዊ ስደት ተጀመረ። ሆኖም በእስር፣ በግርፋት መሀል፣ ኃይማኖትን በተመለከተ የማይሳሳተው ስልጣን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እንደሆነ፣ “በስብከት ሊማረክ ይገባዋል እንጂ ማንም ሰው እንዲያምን ሊገደድ እንደማይገባው” በቆራጥነት በማወጅ የአማኞች ቁጥር መበራከቱን ቀጠለ።GCAmh 175.3

    የሉተር አስተምህሮዎች በኔዘርላንድ ለም አፈር አገኙ፤ እውነተኛና ታማኝ አገልጋዮች ወንጌልን ለመስበክ ተነሱ። ሜኖ ሳይመንስ ከሆላንድ ክፍለ ሃገራት በአንዱ የተገኘ ነበር። የተማረ የሮማዊ ካቶሊክ፣ በቅስና የተቀባው ይህ ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ፈጽሞ አልነበረውም፤ ወደ ኑፋቄ ተታልዬ እገባለሁ በሚል ፍራቻ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ፈቃደኛ አልነበረም። በቅዱስ ቁርባን ጊዜ የሚወስደው ዳቦና ወይን ሲባረክ፣ ወደ የክርስቶስ ደምና ስጋ ይለወጣል የሚለው አስተምህሮ ጥርጣሬ ሲያስጨንቀው፣ ከሰይጣን የመጣ ፈተና እንደሆነ በማመን በፀሎትና በፀፀት ራሱን ነፃ ለማድረግ ሞከረ፤ ሆኖም አልተሳካለትም። ወደ ብክነትና የተዋረደ ኑሮ ራሱን በመዝፈቅ የህሊናን ወቃሽ ድምጽ ፀጥ ለማሰኘት ቢሞክርም አልሆነለትም።ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አዲስ ኪዳንን እንዲያጠና ተመራ፤ ይህም ከሉተር ጽሁፎች ጋር ተዳምሮ የተሐድሶውን እምነት እንዲቀበል ረዳው። ብዙም ሳይቆይ በአንድ አቅራቢያ ሰፈር ውስጥ እንደገና በመጠመቁ ምክንያት ሞት የተፈረደበት ሰው አንገቱን ሲቀላ ተመለከተ። ይህም ስለ ህፃናት ጥምቀት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እንዲያጠና ገፋፋው። ለዚህ የህፃናት ጥምቀት ምንም መረጃ ከመፅሐፍ ቅዱስ ማግኘት አልቻለም፤ ንስሐ መግባትና እምነት ለመጠመቅ ቅድመ ሁኔታዎች እንደሆኑ ግን በበርካታ ቦታዎች እንደተጠቀሱ ተገነዘበ።GCAmh 175.4

    ሜኖ ከሮም ቤተ ክርስቲያን ለቀቀ፤ የተቀበለውን እውነት ለማስተማር ሕይወቱን ሰጠ። በጀርመንና በኔዘርላንድ፣ ትርጉም አልባ፣ የማይመስልና ሕዝብን ለአመጽ የሚያነሳሳ አስተምህሮ በአንድ የአክራሪ መደብ ይራገብ ነበር፤ ይህ አስተምህሮ ስነ-ሥርዓትን፣ መልካም ስነ-ምግባርን በመጣስ ወደ ብጥብጥና ሁከት አመራ። እነዚህ እንቅስቃሴዎች በመጨረሻ ወደ አሰቃቂ ውጤት እንደሚመሩ በመረዳት የነዚህን አክራሪዎች ጋጠ-ወጥ እቅድና የስህተት ትምህርቶች ሜኖ በሀይል ተቃወመ። ነገር ግን በእነዚህ አክራሪዎች ተታለው የነበሩ፣ ሆኖም አጥፊ የሆነ አስተምህሮዎቻቸውን የተው፣ ብዙ ሰዎች ነበሩ። የዋልደንሳዊያን ትምህርት ፍሬዎች የነበሩ ከጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ሲወርድ ሲዋረድ የመጡ አሁንም ብዙ ሰዎች ነበሩ። በእነዚህ የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል በመሆን ሜኖ በታላቅ ትጋትና ስኬት ለፋ።GCAmh 176.1

    ከባባድ መከራዎችን፣ ድህነትን እያስተናገደ፣ በተደጋጋሚም ለሕይወቱ አደገኛ የሆኑ ሁኔታዎችን እየተጋፈጠ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋራ ለሃያ አምስት ዓመታት ወደ ተለያዩ ስፍራዎች ይጓዝ ነበር። በዋነኛነት በኑሮ ደረጃ ዝቅ ያሉትን ኢላማው በማድረግ በኔዘርላንድና በሰሜናዊ ጀርመን ቦታዎች ተመላለሰ፣ ተፅዕኖው ግን ወሰኑን በማስፋት ተሰራጨ። የተማረው ትምህርት ውስን ቢሆንም፣ በተፈጥሮ አንደበተ ርቱዕ የነበረው ሜኖ፣ የማይነቃነቅ አቋም (ማንነት)፣ ትሁት መንፈስና መልካም ፀባይ፣ እውነተኛና ልባዊ ቅድስና የነበረው፣ የሚያስተምረውን መርህ በሕይወቱ የተገበረ፣ ሕዝቡም እምነት እንዲጥሉበት ያደረገ ሰው ነበረ። ተከታዮቹ ተበትነውና ተጨቁነው ነበር። በስህተት እንደ አክራሪዎቹ ሙንስተራዊያን(Munsterites) እየተቆጠሩ ለከባድ መከራ ተዳረጉ። ያም ሆኖ በጥረቱ አያሌ ሰዎች ተለወጡ።GCAmh 176.2

    የተሐድሶ አስተምህሮዎቹ በኔዘርላንድ ያገኙትን ተቀባይነት ያህል በሌላ በየትኛውም ስፍራ አላገኙም ነበር። አስተምህሮዎቹን የተቀበሉ፣ ከዚህ የባሰ አስከፊ ስደት የገጠማቸው ተከታዮች በጥቂት ሃገራት ቢኖሩ ነው። በጀርመን አገር ቻርለስ 5ኛ ተሐድሶውን ከልክሎ ነበር፤ ደጋፊዎቹን በሙሉ ወደ ማቃጠያ ስፍራው ቢያመጣቸው ደስታው ነበር፤ ነገር ግን ልዑላኑ አምባገነናዊ ስርዓቱን ተቃውመው ተነሱ። በኔዘርላንድ ስልጣኑ ከፍተኛ ነበርና የስደት አዋጆች በተከታታይ በፍጥነት ይታወጁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ፣ መስማት ወይም መስበክ፣ ከዚያም አልፎ ስለ እርሱ ወሬ ማውራት ጭምር በቃጠሎ ሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነበር። በምስጢር ወደ እግዚአብሔር መፀለይ፣ ለምስል አልሰግድም ማለት፣ ወይም መዝሙር መዘመርም በሞት የሚያስቀጣ ነበር። ጥፋተኛ እንደሆኑና እንደሚመለሱ በግልጽ የተናገሩ እንኳ የሚፈረድባቸው የነበረ ሲሆን ወንዶች ከሆኑ በሰይፍ ይገደሉ ነበር፣ ሴቶች ከሆኑ ደግሞ ከነነፍሳቸው ይቀበሩ ነበር። ፀንተው የቆሙትም አንዳንድ ጊዜ ይህ [አይነቱ] ቅጣት ይፈፀምባቸው ነበር። በቻርለስና በፊሊፕ 2ኛ የግዛት ዘመን በሺዎች የሚቆጠሩ እረገፉ።GCAmh 176.3

    በአንድ ወቅት ከካቶሊክ አምልኮአዊ ሥርዓት ቀርታችኋል፣ በቤትም አምልኮ ታካሂዳላችሁ ተብለው አንድ ሙሉ የቤተሰብ አባላት በመርማሪዎች ፊት ቀረቡ። በድብቅ ስለሚያከናውኑት ተግባር የመጨረሻው ልጃቸው ሲመልስ “እግዚአብሔር እውቀት እንዲጨምርልን፣ ኃጢአታችንንም ይቅር እንዲለን ተንበርክከን እንፀልያለን። የግዛት ዘመኑ የተትረፈረፈ፣ ሕይወቱ የደስታ እንዲሆን ስለንጉሣችን እንፀልያለን። እግዚአብሔር ይጠብቃቸው ዘንድ ለዳኞቻችንም እንፀልያለን።” በማለት መለሰ። የተወሰኑት ፈራጆች ውስጣቸው ቢላወስም አባቱና አንድ ወንድሙ እንዲቃጠሉ ተደረገ።GCAmh 177.1

    የአሳዳጆቹ የሚነድ ቁጣ በሰማዕታት እምነት በእኩል ኃይል ይመከት ነበር። ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሴቶችና ገና ያላገቡ ኮረዳዎች ሁሉ ፍንክች የማይል ጀግንነት አሳዩ። “ባላቸው ሲቃጠል ሚስቶች ከጎኑ በመቆም የሚያጽናና ቃል በጆሮው ያንሾካሹኩለት፣ ወይም ፈገግ ይል ዘንድ መዝሙር ይዘምሩለት ነበር።” “ወደ ሌሊት የመኝታ ክፍላቸው እንደሚገቡ ሆነው ወጣት ሴቶች ከነነፍሳቸው ወደሚቀበሩበት መቃብር ወረዱ፣ ወይም ወደ ሰርጋቸው እንደሚሄዱ ሁሉ እጅግ የሚያምረውን ልብሳቸውን ለብሰው ወደ መታረጃውና ወደ እሳቱ አመሩ።”GCAmh 177.2

    የጣዖት አምልኮ ወንጌሉን ሊያጠፋ እንደለፋበት ዘመናት ሁሉ፣ “የክርስቲያኖች ደም ዘር ነበር።” ስደት ያደረገው ነገር ቢኖር የእውነትን ምስክሮች ማብዛት ነበር። በየዓመቱ ሊያሸንፈው ባልቻለው ንቅንቅ በማይለው በሰዎች አቋም እንደ እብድ ያደረገው ንጉሠ ነገሥት፣ የጭካኔ ተግባሩን ፈፀመ፣ ልፋቱ ግን ከንቱ ሆነ። በኦሬንጁ በክቡር ዊሊያም አብዮት በመጨረሻ እግዚአብሔርን በነፃነት የማምለክ መብትን ወደ ሆላንድ አመጣ።GCAmh 177.3

    በፒየድሞንት ተራራዎች፣ በፈረንሳይ መስኮችና በሆላንድ የባህር ዳርቻዎች ወንጌሉ የተስፋፋው በደቀ መዛሙርቱ ደም እየተቀባ ነበር። ወደ ሰሜናዊ አገራት ግን በሰላም ገባ። በዊተንበርግ የነበሩ ተማሪዎች ወደ አገራቸው ሲመለሱ የተሐድሶውን እምነት ተሸክመው ወደ ስካንዲናቪያ ሄዱ። የሉተር ጽሁፎች መታተምም ብርሃኑን አስፋፋው። ቀለል ያሉት፣ በችግር የማይፈቱት ሰሜናዊ ሕዝቦች ከሮማ የአጉል አምልኮ፣ እብሪትና ብልሽት ተመልሰው ንፁህና ውስብስብ ወዳልሆኑት፣ ሕይወት ወደሚሰጡት የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ፊታቸውን አቀኑ።GCAmh 177.4

    ታውሰን፣ “የዴንማርክ ተሐድሶ አራማጅ” የጭሰኛ ልጅ ነበር። ልጁ ገና በልጅነቱ ሰፊ ማስተዋል የነበረው እንደነበር ምልክቶች ነበሩ፤ ትምህርት የመማር ጥማት የነበረው ቢሆንም የወላጆቹ ሁኔታ ይህንን የሚፈቅድ አልነበረምና ወደ ገዳም ገባ። በዚህ ስፍራ የሕይወቱ ንጽህና ከትጋቱና ከታማኝነቱ ጋር ተዳምሮ የአለቃውን ሞገስ አተረፈለት። ጥናቱ ያረጋገጠው ለቤተ ክርስቲያን ጥሩ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ተሰጥኦ ያለው፣ የወደፊት ተስፋ የሚጣልበት ወጣት እንደነበረ ነው። በመሆኑም በጀርመን ወይም በኔዘርላንድ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች በአንዱ ገብቶ እንዲማር ተወሰነለት። ወደ ዊተንበርግ እንዳይሄድ ከመከልከሉ በቀር ወጣቱ ተማሪ የፈለገውን ዩኒቨርሲቲ እንዲመርጥ ተፈቀደለት። የቤተ-ክህነት ምሁር የኑፋቄ መርዝ አደጋ እንዲጋረጥበት አያስፈልግም፤ መነኩሴዎቹ ነበሩ እንዲህ የተናገሩት።GCAmh 177.5

    ታውሰን፣ እንደ አሁኑ ድሮም የሮማዊነት ጠንካራ ምሽግ ወደ ነበረው ወደ ኮሎኝ ተላከ። ብዙም ሳይቆይ አምላክን ለመገናኘት በማለት ምሁራኑ በፀሎትና በመመሰጥ የሚፈጽሙት ድርጊት አፀየፈው። በተመሳሳይ ጊዜ ገደማ የሉተርን ጽሑፎች አገኘ። በግርምትና በፍንደቃ አነበባቸው፤ የተሐድሶ አድራጊውን ግላዊ መመሪያዎችም ለማጣጣም ጥልቅ ፍላጎት አደረበት። ይህን ማድረግ ማለት ግን ገዳሙንና አለቃውን ማስቆጣትና ድጋፉንም ማጣት ማለት ነበር። ብዙም ሳይቆይ ውሳኔውን ወስኖ፣ በዊተንበርግ በተማሪነት ተመዘገበ።GCAmh 178.1

    ወደ ዴንማርክ ሲመለስ ወደነበረበት ገዳም ገባ። በሉተራዊነት ገና ማንም አልጠረጠረውም ነበር። ምስጢሩን ይፋ ሳያደርግ፣ የግብረ አበሮቹን ጥላቻ ሳይቀሰቅስ ወደ ንጹህ እምነትና የተሻለ የቅድስና ሕይወት ይመራቸው ዘንድ ይጥር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስን ከፍቶ እውነተኛ ትርጉሙን አብራራላቸው፤ በመጨረሻም የኃጥአን ጽድቅ ክርስቶስ እንደሆነና የመዳን ብቸኛ ተስፋም እርሱ እንደሆነ ሰበከላቸው። ሮምን በጀግንነት ይደግፋል ብሎ ከፍተኛ ተስፋ የነበረው ኃይማኖታዊ መሪ ቁጣ እጅግ ነደደ። ወዲያውኑ ከነበረበት ገዳም ወደ ሌላ ተዛውሮ በራሱ ክፍል ብቻ እንዲሆን ተገድቦ በጥብቅ ክትትል ስር ሆነ።GCAmh 178.2

    ብዙም ሳይቆይ ለአዲሶቹ ሞግዚቶቹ ታላቅ ሽብር በለቀቀ ሁኔታ በርካታ መነኩሴዎች ወደ ፕሮቴስታንትነት እንደተለወጡ አወጁ። በታሰረበት ክፍል ቋሚ ዘንጎች መሃል ታውሰን ለወዳጆቹ የእውነትን እውቀት አካፈለ። የዴንማርክ አባቶች ቤተ ክርስቲያንዋ ኑፋቄን ለማጥፋት የዘረጋችውን እቅድ በብልሃት ቢተገብሩት ኖሮ፤ የታውሰን ድምጽ እንደገና ባልተሰማ ነበር። ነገር ግን በአንድ የምድር ውስጥ ወህኒ ቤት በመቅበር ፈንታ ከገዳሙ አባረሩት። አሁን አቅመ-ቢስ ሆኑ። በዚህ ጊዜ የወጣ ንጉሣዊ አዋጅ ለአዲሱ እምነት አስተማሪዎች ጥበቃ ቸረ። ታውሰን መስበክ ጀመረ። አብያተ ክርስቲያናቱ ክፍት ሆኑለት፣ ሕዝቡም ለማዳመጥ በዙሪያው ይሰበሰብ ጀመር። ሌሎችም የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰብኩ ነበሩ። አዲስ ኪዳን ወደ ዴንማርክኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በስፋት ተሰራጨ። ይህንን ሥራ ለመደምሰስ ጳጳሳውያኑ ያደረጉት ጥረት እንዲያውም እድሜ ጨመረለት፤ ዴንማርክ ብዙም ሳትቆይ የተሐድሶውን እምነት እንደተቀበለች በይፋ አወጀች።GCAmh 178.3

    በስዊድንም ከዊተንበርግ ምንጭ የጠጡ ወጣቶች የሕይወትን ውሃ ለትውልድ አገራቸው ሰዎች ይዘው ሄዱ። በስዊድኑ ተሐድሶ መሪዎች ከነበሩት ውስጥ ሁለቱ፤ በኦሬብሮ ቀጥቃጭ የነበረው ሰው ልጆች፣ ኦላፍ እና ላውረንሽየስ ፔትሪ በሉተርና በሜላንክተን ስር የተማሩ ሲሆን፣ የቀሰሙትን እውነት ለማስተማር የሚተጉ ነበሩ። ልክ እንደ ታላቁ ተሐድሶ አራማጅ የኦላፍ ጥልቅ ቀናኢነትና አንደበተ ርዕቱነት ሕዝቡን አነሳሳ፣ ላውረንሽየስ ደግሞ እንደ ሜላንክተን የተማረ፣ በጥልቀት አሳቢና የተረጋጋ ነበረ። ሁለቱም ለእምነታቸው የተሰጡ፣ በስነ መለኮት ጥናት ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ፣ እውነትንም በማስፋፋት ፍንክች የማይል ድፍረት የነበራቸው ነበሩ። የጳጳሳዊ ተቃውሞ እጦት አልነበረም። የካቶሊክ ቀሳውስት ያልተማረውንና በአጉል አምልኮ የተጠመደውን ሕዝብ አነሳሱት። ኦላፍ ፔትሪ በተደጋጋሚ ለአመጽ በተነሳሳው ሕዝብ ጥቃት ይደርስበት ነበር፤ በብዙ አጋጣሚዎችም ከሞት አፋፍ ደርሶ አምልጧል። እነዚህ ተሐድሶ አራማጆች ግን በንጉሡ የተወደዱና ጥበቃም ይደረግላቸው የነበሩ ናቸው። በሮማዊ ቤተ ክርስቲያን አገዛዝ ስር፣ ሕዝቦች በድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቀው በጭቆናም ጎብጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስን ተነፍገው ታይታና ሥነ-ሥርዓት ብቻ በሚያንፀባርቅ የይስሙላ ኃይማኖት ተይዘው፣ የጥንቶቹ እምነት የለሽ አያቶቻቸው ሲከተሉት ወደነበረው የአጉል እምነትና የጣዖት አምልኮ እየተመለሱ ነበር። አገሪቱ በሚቀናቀኑ ጎራዎች ተከፋፍላ ቀጣይነት ያለው ባላንጋራነታቸው የሁሉንም ሕዝብ ስቃይ ያበዛ ነበር። በመንግሥትና በቤተ ክርስቲያን ላይ ተሐድሶ ለማምጣት ቆርጦ የተነሳው ንጉሥ ሮምን በመቃወም ረገድ አቅም ያላቸውን እነዚህን ተሐድሶ አራማጆች በደስታ ተቀበላቸው።GCAmh 178.4

    ንጉሠ ነገሥቱና የስዊድን ቀንደኛ ሰዎች በተገኙበት የሮማን ደጋፊዎች በመቃወም ኦላፍ ፔትሪ በከፍተኛ ክህሎት የተሐድሶ እምነቱን አስተምህሮዎች ደግፎ ተከራከረ። የእምነቱ መሰረታዊ አስተምህሮዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግልጽና ቀላል ሆነው ሁሉም ሰው እንዲረዳቸው ሆነው የቀረቡ በመሆናቸው የአባቶች ትምህርት ተቀባይነት ማግኘት ያለበት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምሩ ከሆነ ብቻ መሆን እንዳለበት አወጀ። ክርስቶስ፦ “ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ሌላ አይደለም” [ዮሐ 7÷16] አለ። ጳውሎስም ሲሰብክ ከተቀበለው ወንጌል የተለየ ሌላ የሚሰብክ ቢኖር የተረገመ ይሆናል ብሎአል [ገላ 1÷8]። “ታዲያ እንዴት ነው” አለ የተሐድሶ አራማጁ “ሌሎች እንደፈለጉ ቀኖናዎችን በማወጅ ለድነት እንደሚያስፈልጉ አድርገው በሰዎች ላይ መጫን እንደሚችሉ የሚያስቡት?” የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በማሳየት፣ “መጽሐፍ ቅዱስ እና መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ” የሚለው የፕሮቴስታንቶች መመሪያ የእምነትና የተግባር ደንብ እንደሆነ አስረግጦ ተናገረ።GCAmh 179.1

    ይህ ፉክክር በአንፃራዊነቱ ብዙም ይፋ ያልሆነ ቢሆንም “የተሐድሶ አድራጊዎች ሰራዊት መዝገብና ተዋረድ ምን አይነት ሰዎችን ያቀፈ እንደነበር ያሳየናል። ትኩረታችን ግሩም ወደሆኑት ማዕከሎች፣ ወደ ዊተንበርግና ወደ ዙሪክ ስናጠበው፣ እንደ ሉተር፣ ሜላክቶን፣ ዝዊንግልና አይኮላፓዲየስ አይነቶቹ ዝነኛ ስሞች ላይ ስናተኩር፣ እነዚህ ዝነኞች ናቸው የተሐድሶ መሪ የነበሩት ተብሎ ቢነገረን ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ከእነርሱ በታች የነበሩት እነርሱን የሚመስሉ አልነበሩም። ወደ ስዊድን፣ ብዙም ገናና ወዳልነበረው ትርኢት ስንዞር፣ ትሁቶቹ ኦላፍ ፔትሪና ላውረንሽየስ ፔትሪ…. ከመሪዎቹ እስከ ደቀ መዛሙርቱ ድረስ….ስንመለከት ምን እናገኛለን? ድንቁርና ያልያዛቸው፣ ጎሰኛ ያልሆኑ፣ አወዛጋቢ ምላሳሞች ያልነበሩ፣ ከዚያ እጅግ የተለዩ ነበሩ። የጦር መሳሪያው ግምጃ ቤት የለገሳቸውን መሳሪያ በአግባቡ መጠቀም የቻሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ያጠኑ፤ የትምህርት ቤቶችን ማደናገሪያና የሮም ሹሞችን በቀላሉ ድል መንሳት የቻሉ ምሁራንንና የኃይማኖት ትምህርት ሊቆችን እንመለከታለን።”-Ibid., b. 10, ch. 4።GCAmh 179.2

    ከዚህ ክርክር የተነሳ የስዊድኑ ንጉሥ የፕሮቴስታንት እምነትን ተቀበለ። ከዚያም ብዙም ሳይቆይ ብሔራዊ መማክርቱ ይህንን ደግፎ ውሳኔ አሳለፈ። አዲስ ኪዳን በኦላፍ ፔትሪ አማካኝነት ወደ ስዊድንኛ ቋንቋ ተተርጉሞ የነበረ ሲሆን፣ በንጉሡ ፍላጎት ሁለቱ ወንድሞች አጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲተረጉሙ ሃላፊነት ተሰጣቸው። እናም ለመጀመሪያ ጊዜ የስዊድን ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ቃል በራሳቸው ቋንቋ መማር ጀመሩ። በግዛቱ ሁሉ አገልጋዮች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያብራሩ በትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎችም መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እንዲማሩ ብሔራዊ ጉባኤው ትዕዛዝ አስተላለፈ።GCAmh 179.3

    በቀጣይነትና በእርግጠኝነት የድንቁርናና የአጉል አምልኮ ጽልመት በተባረከው የወንጌል ብርሐን እየተገለጠ ሄደ። ከሮማዊ ጭቆና ስትላቀቅ አገሪቱ ገናናነትንና ታላቅነትን ተጎናጽፋ፣ ከአሁን ቀደም ደርሳበት የማታውቀው ደረጃ ላይ ደረሰች። ስዊድን ፕሮቴስታንታዊነትን ደግፈው ከሚቆሙ መካከል አንድዋ ሆነች። እስከ አሁን ድረስ ደካማ የነበረችው ትንሽ አገር በአውሮፓ ውስጥ ካሉ አገራት የእርዳታ እጅዋን የዘረጋች ብቸኛ አገርና ከአንድ መቶ ዓመት በኋላም ከባድ ጥፋት ባንዣበበ ጊዜ በሰላሳ ዓመቱ አሰቃቂ ጦርነት ጀርመንን ለማትረፍ የተነሳች አገር ለመሆን በቃች። ሁሉም ሰሜናዊ አውሮፓ በሮም አምባገነናዊ ግዛት እንደገና ለመውደቅ የተቃረበ መሰለ። በዚህ ጊዜ የስዊድን ሰራዊት በመንቀሳቀስ በጀርመን ድል እየተቀዳጀ የነበረውን ጳጳሳዊ እንቅስቃሴ ወደ ሽንፈት በመለወጥ ለካልቪኒስቶችና ለሉተራዊያን ፕሮቴስታንቶች መቻቻልን፣ ተሐድሶውን ለተቀበሉ ሌሎች አገራት ደግሞ የህሊና ነጻነት ድልን ማስገኘት ቻለ።GCAmh 180.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents