Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፪—የመጀመሪያዎቹ ምዕተ ዓመታት ስደት

    የሱስ ስለ የሩሳሌም ዕጣ ፈንታ እንዲሁም ስለ ዳግም ምፅዓቱ ሁኔታ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገልጽላቸው ሳለ ከእነርሱ ከሚወሰድበት ሰዓት ጀምሮ ነጻ ሊያወጣቸው በኃይልና በክብር እስከሚመጣበት ጊዜ ያለውን የሕዝቦቹን ገጠመኝም እንዲሁ ተናግሮ ነበር። በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ አዳኙ በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚወድቀውን አውሎ ነፋስ አየ። ወደፊት ስላለው ክስተትም ጠልቆ በመግባት በሚመጡት የጽልመትና የስደት ዘመናት ሕዝቦቹን በኃይል የሚመታውን፣ ፍርሥራሽም ትቶ የሚያልፈውን ከባድ ተግብ(ውሽንፍር) አይኖቹ ተመለከቱ። በጥቂቱ ሆኖም እጅግ አስፈላጊ በሆኑ ቃላት የዚህ ዓለም መሪዎች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን የሚሰፍሩትን የቅጣት ቁና ተናገረ [ማቴ 24÷9፣21፣22]። የክርስቶስ ተከታዮች እርሱ የተራመደበትን የውርደት፣ የነቀፋና የስቃይ ዱካ መከተል ይኖርባቸዋል። በመድኃኔዓለም ላይ የተንጸባረቀው ጥላቻ በስሙ በሚያምኑ ሁሉ ላይ የሚደገም ይሆናል።GCAmh 32.1

    አዳኙ የተናገራቸው ቃላት የሚፈጸሙ ለመሆናቸው የጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መስክሮአል። የምድርና የሲኦል ኃይላት በአንድ ላይ ተሰድረው የክርስቶስ ተቃዋሚነታቸውን በተከታዮቹ ላይ ገለጹ። ወንጌሉ ስኬት ካገኘ ቤተ መቅደስዋና የመሰውያ ስፍራዋ እንደሚጠፉ የጣዖት አምላኪዋ ቤተ ክርስቲያን ተገነዘበች፤ በመሆኑም ሃይሏን አሰባስባ ክርስትናን ለማጥፋት ቆርጣ ተነሳች። የስደት እሳት ተቀጣጠለ። ክርስቲያኖች የነበራቸውን ሁሉ ተነጥቀው ከቤታቸው ተባረሩ፤ “መከራ በሆነበት በትልቅ ተጋድሎ” አለፉ [ዕብ 10÷32]። “መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእሥራትና በወህኒ ተፈተኑ” [ዕብ 11÷36፣37፣38]፤ አያሌ ሰዎች ምስክርነታቸውን በደማቸው አተሙ። ባርያና ጨዋ፣ ሃብታምና ድሀ፣ የተማሩትና ያልተማሩት፣ ሁሉ ያለ ርኅራኄ ታረዱ።GCAmh 32.2

    በኔሮ የግዛት ዘመን ጳውሎስ በተሰዋበት ጊዜ ገደማ የጀመሩት እነዚህ ስደቶች ግለታቸው አንዳንዴ ከፍ አንዳንዴ ደግሞ ዝቅ እያለ ለብዙ መቶ ዓመታት ቀጠለ። ክርስቲያኖች እጅግ ዘግናኝ የሚባሉትን ወንጀሎች እንደፈጸሙ ተደርገው ከመከሰሳቸውም በላይ የከባድ መቅሰፍቶች ማለትም የረሃብ፣ የቸነፈርና የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት እነርሱ እንደሆኑ ይቆጠር ነበር። የሕዝባዊ ጥላቻና ጥርጥር ኢላማ ከመሆናቸው የተነሳ ወሬ አቀባዮች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ በደል የሌለባቸውን ለመጠቆም በተጠንቀቅ ይቆሙ ነበር። በመንግሥት ላይ እንዳመጹ ተቃዋሚዎች፣ የኃይማኖት ጠላቶችና የሕብረተሰብ ተባይ ተደርገው ይፈረድባቸው ነበር። አያሌ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በትያትር ማሳያ ቤቶች ለዱር አራዊት ተወርውረዋል፤ አልያም በቁማቸው በእሳት ተቃጥለዋል። አንዳንዶቹ ተሰቀሉ፤ ሌሎች ደግሞ የዱር እንሰሳትን ቆዳ እንዲለብሱ ተደርገው በውሾች ተቦጫጭቀው እንዲበሉ ወደ ሕዝብ መሰብሰቢያዎች (ስታዲየሞች) ተገፍትረዋል። አብዛኛውን ጊዜ በክብረ በዓላት ወቅት የእነዚህ ክርስቲያኖች ቅጣት የሕዝብ ዋና መዝናኛ ይደረግ ነበር። በትዕይንቱ ለመቦረቅ ብዙ ሕዝብ ይሰበሰብ ነበር፤ ያልታደሉትን ጣዕረ-ሞትም በሳቅና የድጋፍ ጩኸት ያጅቡት ነበር። መጠለያ በፈለጉበት ስፍራ ሁሉ የክርስቶስ ተከታዮች እንደ ዱር አውሬ ይታደኑ ነበር። በምድረበዳ፣ በተራቆቱና ገለልተኛ ስፍራዎች መደበቂያ ይሹ ዘንድ ተገደዱ። “ሁሉም እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ” [ዕብ 11÷36፣37፣38]። የመቃብር ዋሻዎች ለሺዎች መሸሸጊያ ሆኑ። ከሮም ከተማ ወጣ ብለው ባሉ ኮረብታዎች ስር፣ በመሬትና በቋጥኝ ሥር የተቆፈሩ ረጃጅም መተላለፊያ መንገዶች ነበሩ። ጨለማና ውስብስብ የሆነው የመሬት ውስጥ መተላለፊያ ከከተማዋ ቅጥር አልፎ ብዙ ምእራፎች የሚሄድ ነበር። በእነዚህ የምድር ውስጥ ስፍራዎች የክርስቶስ ተከታዮች ሬሳቸውን ይቀብሩ ነበር። በሚጠረጠሩበትና በሚወገዙበት (የሕግ ከለላቸው በሚነሳበት) ጊዜም እነዚህ ቦታዎች መጠለያዎቻቸው ነበሩ። ሕይወት ሰጪው ጌታ፣ መልካሙን ተጋድሎ የተጋደሉትን ሁሉ በሚቀሰቅስበት ጊዜ፣ ስለ ክርስቶስ ሰማዕት የሆኑ ብዙዎች ከነዚያ ደብዛዛ ዋሻዎች ይወጣሉ።GCAmh 32.3

    እጅግ በከበደው ስደት እንኳ እነዚህ የየሱስ ምስክሮች እምነታቸውን ሳያጎድፉ ጠብቀዋል። ከማናቸውም ዓይነት ምቾት ቢገለሉም፣ የፀሐይ ብርሐን ተነፍገው ቤታቸውን በጨለማ ሆኖም በሰላማዊው የመሬት ጉያ ቢያደርጉም፣ የምሬት ቃል ግን ፈጽሞ ከአፋቸው አልወጣም። ድህነትና ጭንቀትን ይቋቋሙ ዘንድ በእምነት፣ በትዕግስትና በተስፋ ቃላት እርስ በእርስ ይበረታቱ ነበር። የምድርን በረከት ሁሉ አጥተው መራቆታቸው በክርስቶስ ያላቸውን እምነት ይክዱ ዘንድ ሊያስገድዳቸው አልቻለም። [ለእነርሱ] ፈተናና ስደት ወደ እረፍታቸውና ወደ ሽልማታቸው የሚያቀርቧቸው እርምጃዎች እንጂ ሌላ አልነበሩም።GCAmh 33.1

    እንደ ቀደሙት የእግዚአብሔር ባርያዎች ሁሉ “ተሰቃዩ፣ መዳንም አልወደዱም፣ የሚበልጥ ትንሳኤ ይቀበሉ ዘንድ።” [ዕብ 11÷35]። ነብያትም እንዲሁ ከእነርሱ በፊት ተሳደዋልና፣ ስለ ክርስቶስ ሲሉ መከራን በሚቀበሉበት ጊዜ፣ ሽልማታቸው በሰማይ ታላቅ ነውና እጅግ ደስ ሊሰኙ እንደሚገባቸው የተነገራቸውን የጌታቸውን ቃላት አስታወሱ። ለእውነት ይሰቃዩ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ተቆጥረዋልና ሀሴት ያደርጉ ነበር፤ የድል መዝሙርም ከሚንጣጣው ነበልባል መካከል ወደ ላይ ይወጣ ነበር። በእምነት ወደ ሰማይ አንጋጠው ሲመለከቱ ክርስቶስና መላእክቱ ከሰማይ ጣራ በጥልቅ ፍላጎት አተኩረው ወደ እነርሱ ሲመለከቱ፣ ለአይበገሬነታቸውም አዎንታ ሲለግሱ ያዩ ነበር። ቃል ከእግዚአብሔር ዙፋን ወደ እነርሱ መጣ፣ “እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።” [ራዕ 2÷10]።GCAmh 33.2

    የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ያጠፋ ዘንድ በኃይል የተሞከሩት የሰይጣን ጥረቶች ከንቱ ሆኑ። የየሱስ ደቀ መዛሙርት ሕይወታቸውን የሰዉለት ታላቁ ተጋድሎ፣ እነዚህ ታማኝ፣ ደረጃቸውን ያስጠበቁ አማኞች በተሰለፉበት ሲወድቁ አላበቃም፤ በመሸነፍ ድል ነሱ። የእግዚአብሔር ሰራተኞች ተሰዉ፣ ሥራው ግን በቀጣይነት ወደፊት ተራመደ። ወንጌሉ መስፋፋቱን ቀጠለ፣ የሚደግፉትም ቁጥር ይጨምር ጀመር። የሮም ንስሮች እንኳ ወደማይደፍሯቸው ሥፍራዎች ጭምር ሰርስሮ ገባ። ማሳደዱ እንዲቀጥል ሲጎሰጉሱ የነበሩትን የአህዛብ መሪዎች በምክንያት ሲገዳደር አንድ ክርስቲያን እንዲህ አለ፦ “ልታሰቃዩን፣ ልትጎዱንና ልታስጨንቁን ትችላላችሁ፣ እርጉምነታችሁ ድካማችንን ቢፈትነውም ጭካኔያችሁ ግን ምንም አይፈይድም። ሌሎች ይቀላቀሉን ዘንድ ለማሳመን ጠንካራ ግብዣ ከመሆን አልዘለለም። መታጨዳችን ሲጨምር፣ ማቆጥቆጣችን የበለጠ ይበዛል፤ የክርስቲያኖች ደም ዘር ነው።”- Tertullian, Apology, paragraph 50.GCAmh 33.3

    በሺዎች የሚቆጠሩ ታስረው ተገደሉ፤ ነገር ግን ቦታቸውን የሚሞሉ ሌሎች ተነሱ። ለእምነታቸው የተሰውት እነርሱ የክርስቶስነታቸው ተረጋገጠ፤ በእርሱም ዘንድ አሸናፊዎች ተብለውም ተቆጠሩ። መልካሙን ገድል ተጋድለዋል፣ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ የክብር ዘውዳቸውን ይቀበላሉ። በጽናት ያለፉት ሰቆቃ፣ ክርስቲያኖች እንዲቀራረቡ ወደ አዳኛቸውም እንዲጠጉ አደረጋቸው፤ የሕይወታቸው ምሳሌነትና የሞታቸው ዋቢነት የእውነት ቋሚ ምስክር ነበር። እንዲህ ይሆናል ተብሎ በማይጠበቅበት ሥፍራ የሰይጣን ተገዥዎች ለእርሱ የሚሰጡትን አገልግሎት እየተዉ በክርስቶስ ሰንደቅ አላማ ስር መመዝገብ ጀመሩ።GCAmh 34.1

    ስለዚህም ሰይጣን የእግዚአብሔርን መንግሥት በተሻለ ስኬት መዋጋት ይቻለው ዘንድ በክርስቲያኖች ቤተ-መቅደስ ውስጥ ባንዲራውን የመትከል እቅዱን ነደፈ። የክርስቶስ ተከታዮች መታለል ከቻሉና እግዚአብሔርን ካሳዘኑ፣ ኃይላቸው፣ ቅጥራቸውና ጽናታቸው ስለማይቀጥል በቀላሉ መታደን የሚችሉ ይሆናሉ።GCAmh 34.2

    ታላቁ ተቃዋሚ በኃይል ማሳካት ያልቻለውን፣ አሁን በብልጠት የማታለያ ስልቱ ለማስፈጸም ይጥር ጀመር። ስደት ቆመ፣ ቦታውም አደገኛ ማባበያ በሆኑት የጊዜያዊ ብልጽግናና የምድራዊ ክብር ተተካ። ሌሎች በጣም አስፈላጊ እውነቶችን ወደ ጎን ትተው ሳለ፣ ጣዖት አምላኪዎች የክርስትናን እምነት በከፊል እንዲቀበሉ ተመሩ። የሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እንደሚቀበሉ፣ በሞቱና በትንሳኤውም እንደሚያምኑ መሰከሩ። የኃጢአተኝነት ወቀሳ ግን አልተሰማቸውም፣ ንስሐ መግባትና የልብ መለወጥ አስፈላጊ ሆኖ አልታያቸውም። ክርስቶስን በማመን መሠረት ላይ ሁሉም በአንድነት ይቆሙ ዘንድ፣ እነርሱ የድርሻቸውን ጥቂት ነገሮች እንደተው ሁሉ፣ ክርስቲያኖችም በበኩላቸው መተው የሚገባቸውን የተወሰኑ ነገሮቻቸውን [እውነቶቻቸውን] እንዲተዉ ጣዖት አምላኪዎቹ ሃሳብ አቀረቡ።GCAmh 34.3

    አሁን ቤተ ክርስቲያን በአስፈሪና እውን አደጋ ስር ወደቀች። እስር፣ ግርፋት፣ እሳትና ሰይፍ ከዚህ ጋር ሲወዳደሩ እንደ በረከት ነበሩ። የተወሰኑ ክርስቲያኖች አስታራቂ ሃሳቡን ለመቀበል እንደማይቻላቸው በመናገር ፀንተው ቆሙ። ሌሎቹ ደግሞ የእምነታቸው የተወሰኑ ባህርያት(መለዮዎች) እንዲቀሩ፣ ወይም ማሻሻያ እንዲደረግባቸውና ክርስትናን በከፊል ከተቀበሉት ጋር አንድ እንዲሆኑ በመስማማት፣ ህብረት መፍጠራቸው እውነቱን በከፊል የተቀበሉት ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስትና ለመለወጣቸው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተናገሩ። ለታማኝ የክርስቶስ ተከታዮች ያ ጊዜ የጥልቅ ሃዘን ሰዓት ነበር። እምነታቸውን ያበላሽ ዘንድ፣ ብሎም አእምሮአቸውን ከእውነት ቃል ያርቅ ዘንድ አስመሳይ የክርስትና ካባ ተከናንቦ ሰይጣን እጁን ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገባ።GCAmh 34.4

    በመጨረሻም አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ደረጃቸውን ዝቅ ለማድረግ ተስማምተው የክርስትናና የጣዖት አምላኪዎች ህብረት ተመሠረተ። ጣዖት አምላኪዎች እንደተለወጡ፣ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያበሩ አንደሆኑ ቢናገሩም የማምለኪያ ቁሶቻቸውን ብቻ ወደ ክርስቶስ፣ ወደ ማርያምና ወደ ቅዱሳት ምስሎች ጭምር በመለወጥ በዚያው በጣዖት አምላኪነታቸው ቀጠሉ። በዚህ ሁናቴ ወደ ቤተ ክርስቲያን የመጣው የጣዖት አምልኮ የብክለት እርሾ ክፉ ሥራውን ቀጠለ። እውነት ያልሆኑ አስተምህሮዎች፣ ከንቱና አጓጉል የአምልኮ ስነ ሥርዓቶች፣ የጣዖት አምልኮ በአል አከባበሮች ከቤተ ክርስቲያንዋ እምነትና አምልኮ ጋር ተዋሃዱ። የክርስቶስ ተከታዮች ከጣዖት አምላኪዎች ጋር ህብረት ሲፈጥሩ የክርስትና ኃይማኖት ተበላሸ፤ ቤተ ክርስቲያንም ንጽህናዋንና ሃይሏን አጣች። ሆኖም በእነዚህ ማታለያዎች ያልተወሰዱ ጥቂቶች ነበሩ። ለእውነት ጸሐፊ (ምንጭ) ታማኝ ሆነው ቀጠሉ፤ እግዚአብሔርንም ብቻ አመለኩ።GCAmh 34.5

    የክርስቶስ ተከታዮች ነን በሚሉ መካከል ምንጊዜም ያሉት ሁለት ጎራዎች ናቸው። አንደኛው ወገን የአዳኙን ሕይወት በማጥናት ጎዶሎአቸው ተስተካክሎ ከምሳሌአቸው ከየሱስ ጋር እንዲስማማ ከልባቸው ሲጥሩ፣ ሌላኛው ወገን ስህተቶቻቸውን እርቃን የሚያስቀሯቸውን ግልጽና ተግባራዊ እውነቶች ይሸሻሉ። ፈጽማ ጥሩ ደረጃ ላይ ናት በተባለላት ሁኔታዋ እንኳ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእውነተኛው፣ በንጹሁና በሃቀኛው ብቻ የተዋቀረች አልነበረችም። በፈቃደኝነት ለኃጢአት የሚገዙ እነርሱ በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኙ አዳኛችን አስተምሯል፤ ሆኖም ስህተታቸውን አስተውለው የማረም ዕድል ያገኙ ዘንድ የባህርይ ግድፈት ካለባቸው ጋር ራሱን አገናኝቶ የትምህርቶቹን የምሳሌነቱን ጥቅሞች ለገሳቸው። ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል አንደኛው ከዳተኛ(ባንዳ) ነበር። ይሁዳ ተቀባይነትን ያገኘው የባህርይ ግድፈቱን እንደያዘ ቢሆንም የባህርይው ጉድለቶች ግን ለተቀባይነቱ[ደቀ መዝሙር ሆኖ እንዲመረጥ] ምክንያት አልነበሩም። ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ያቆራኘው በየሱስ ትምህርትና አርአያነት የክርስቲያን ባህርይ የሚያጠቃልለው ምን እንደሆነ እንዲማር፣ ከዚያም ስህተቱን እንዲያስተውል ተመርቶ ንስሐ እንዲገባ፣ በመለኮታዊ ፀጋ እርዳታም “እውነትን በመታዘዝ” ነፍሱን እንዲያነጻ ነበር። በደግነት በተሰጠው ብርሐን ግን ይሁዳ አልተመላለሰበትም። ለኃጢአት በመገዛት የሰይጣንን ፈተናዎች ወደ ራሱ ጋበዘ። የክፋት አሻራ ያላቸው ባህርያቱ የበላይነት ስፍራን ያዙ። የጨለማ ኃይላት አእምሮውን ይቆጣጠሩት ዘንድ ፈቀደ፤ ጥፋቶቹ ሲነቀፉ ተቆጣ፤ በመሆኑም ጌታውን የካደበትን አስፈሪ ወንጀል እንዲፈጽም ተመራ። እግዚአብሔርን በመምሰል ሽፋን ኃጢአትን የሚወዱ(የሚያበረታቱ) ሁሉ፣ የሚሄዱበትን የኃጢአት መንገድ በማውገዝ ሰላማቸውን የሚያውኩትን በተመሳሳይ ሁኔታ ይጠሏቸዋል። ልክ ይሁዳ እንዳደረገው፣ ለራሳቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ የሚገስጿቸውን፣ ምቹ አጋጣሚ ሲያገኙ ይከዷቸዋል።GCAmh 35.1

    በስውር ኃጢአት የሚሰሩ፣ ሆኖም ስለ እግዚአብሔር መሰልነታቸው የሚያወሩ ሰዎች ሐዋርያትንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገጥመዋቸው ነበር። ለእግዚአብሔር ሁሉን የሰጡ አስመስለው ከፊሉን በስስት ለራሳቸው ያስቀሩት አናንያና ሰጲራ የአታላዮችን ድርሻ ተወኑ። የእውነት መንፈስ የእነዚህን የአስመሳዮች ትክክለኛ ባህርይ ለሐዋርያት ገለጸላቸው፤ በቤተ ክርስቲያን ንጽህና ላይ የመጣውን መጥፎ ጥፋት የእግዚአብሔር ፍርድ አስወገደው። ይህም የሚሳየው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚደረገውን የክርስቶስ መንፈስ እንደሚያውቅ መረጋገጡ ለግብዞችና ለክፉ አድራጊዎች ታላቅ ድንጋጤ እንደነበረ ነው። በልምድና በባህርይ የክርስቶስ ቋሚ ተወካዮች ከሆኑት ጋር ተቆራኝተው ለረጅም ጊዜ መቀጠል አልቻሉም። ፈተናና ስደት በተከታዮቹ ላይ ሲመጣ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ለመሆን የመረጡት ለእውነት ሲሉ ሁሉንም ነገራቸውን ለመተው ፈቃደኛ የሆኑት ብቻ ነበሩ። ስለሆነም በአንጻራዊነት፣ ስደት እስከቀጠለ ድረስ ቤተ ክርስቲያን በተሻለ ንጽህና ነበረች። [ስደቱ] ሲያቆም፣ ታማኝነትና ሃቀኝነት የጎድላቸው አዳዲስ አባላት ተጨመሩ፣ ሰይጣንም ለእግሩ መቆናጠጫ ያገኝ ዘንድ መንገድ ተከፈተለት።GCAmh 35.2

    ነገር ግን በብርሐን ልዑልና በጽልመት ልዑል መካከል አንድነት የለም፤ በተከታዮቻቸው መካከልም ሕብረት ሊኖር አይችልም። ክርስቲያኖች ከጣዖት አምልኮ በከፊል ከተለወጡ ጋር አንድ ለመሆን ሲስማሙ፣ ከእውነት እያራቀ፣ እያራቀ በሚወስዳቸው መንገድ ላይ መራመድ ጀመሩ። አያሌ ቁጥር ያላቸውን የክርስቶስን ተከታዮች በማታለል ስለተሳካለት ሰይጣን በደስታ ተፍነከነከ። ሃይሉንም በበለጠ አጠናክሮ በእነዚህ ሰዎች ላይ በማውረድ፣ ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነው የቆሙትን ያሳድዱ ዘንድ አነሳሳቸው። በአንድ ወቅት ለእውነት ቆመው ከነበሩት [አሁን በተቃራኒው ጎራ ከተሰለፉት] ሰዎች በተሻለ ትክክለኛውን የክርስትና እምነት እንዴት መቃወም እንዳለበት የሚያውቅ ሰው አልነበረም። እነዚህ ከሃዲ ክርስቲያኖች ከፊል ጣዖት አምላኪ አጋሮቻቸው ጋር በመተባበር በጣም ወሳኝ በሆኑት የክርስቶስ አስተምህሮ መለያ ባህርያት ላይ በማነጣጠር ጦርነት አወጁ።GCAmh 36.1

    በቀሳውስት (በቅድስና) አልባሳት ውስጥ ተደብቀው ወደ ቤተ ክርስቲያን የገቡትን ማታለያዎችና ርኩሰቶች ተቋቁመው ጸንተው ለመቆም የመረጡ እነርሱ በሙሉ ኃይላቸው እልህ አስጨራሽ ትግል ማድረግ ነበረባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የእምነት መለኪያ መሆኑ ቀረ። የኃይማኖት ነጻነት አስተምህሮ እንደ ኑፋቄ ተቆጠረ፤ የሚደግፉትም ሁሉ ተጠሉ፤ በህገ-ወጥነትም ተፈረጁ።GCAmh 36.2

    ከረጅምና ኃይለኛ ብጥብጥ በኋላ አሁንም ከጣዖት አምልኮና ከስህተት ትምህርት ራስዋን ነጻ ለማድረግ የማትስማማ ከሆነ፣ የቀሩት ጥቂት እውነተኛ ክርስቲያኖች ከከሃዲዋ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያላቸውን ሁሉንም ግንኙነቶች ለማቋረጥ ወሰኑ። የእግዚአብሔርን ቃል መታዘዝ ካለባቸው መለያየት አማራጭ የሌለው እርምጃ እንደሆነ ተረዱ። የራሳቸውም ነፍስ ለሞት የሚያበቃ ስህተት ይታገሱ ዘንድ፣ የልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውንም እምነት አደጋ ላይ የሚጥል ተምሳሌት ይተው ዘንድ አልተቻላቸውም። ለእግዚአብሔር ታማኝ ከመሆን ጋር የሚስማማ እስከሆነ ድረስ ለሰላምና ለአንድነት ማንኛውንም ነገር ለመተው ዝግጁ ነበሩ። ሆኖም መርህን ሰውተው ይገዙት ዘንድ ሰላም ያን ያህል ዋጋ ያለው ሆኖ አልተሰማቸውም። አንድነት የሚገኘው በእውነትና በጽድቅ ላይ በመደራደር ብቻ ከሆነ፣ መለያየት፣ ይባስ ብሎም ጦርነት ይኑር።GCAmh 36.3

    እነዚያን ቆራጥ ነፍሳት ያቆሟቸው መርሆች በእግዚአብሔር ሕዝቦች ልብ እንደገና ቢታደሱ(ቢነቃቁ) ለቤተ ክርስቲያንና ለዓለም መልካም ይሆንላታል። ለክርስትና እምነት ምሰሶ የሆኑትን አስተምህሮዎች በተመለከተ የሚያሳስብ ቸልተኝነት አለ። እነዚህ ጉዳዮች ያን ያክል አስፈላጊ አይደሉም የሚለው አስተሳሰብ ስር እየሰደደ ነው። ለመቃወምና ለማጋለጥ ሲሉ ከዘመናት በፊት የነበሩት የእምነት ሰዎች ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የጣሉባቸው የሐሰት ጽንሰ ሃሳቦችና አደገኛ ማሳሳቻዎች፣ ዛሬ የክርስቶስ ተከታዮች ነን በሚሉ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ አዎንታዊ ድጋፍ ያገኙ ዘንድ ይህ መቆርቆዝ የሰይጣንን ወኪሎች እጅ እያጠናከረ ይገኛል።GCAmh 36.4

    የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በርግጥም የተለዩ ሕዝቦች ነበሩ። ነቀፋ የሌለው ባህርያቸውና የማይዋዥቀው እምነታቸው የኃጢአተኛውን ሰላም የሚረብሽ ቀጣይ ተግሳጽ ነበር። በቁጥር ጥቂት ቢሆኑም፣ ድሃዎች፣ ደረጃ-የለሽና የክብር ማዕረግ የሌላቸው የነበሩ ቢሆኑም ባህርያቸውና አስተምህሮዎቻቸው በታወቀበት ሥፍራ ሁሉ ለክፉ አድራጊዎች ድንጋጤ ነበሩ። ስለዚህ አቤል የእግዚአብሔር መሰልነት በሌለው ቃየን ይጠላ እንደነበር እነርሱም በኃጢአተኞች ተጠሉ። ቃየን አቤልን ለገደለበት ተመሳሳይ ምክንያት፣ የመንፈስ ቅዱስን ገደብ አሽቀንጥረው መጣል የሚፈልጉ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ገደሉ። የዚህ ባህርይ ንጽህናና ቅድስና ለራስ ወዳድነታቸውና ለብልሹነታቸው የማያቋርጥ ነቀፋ ስለሆነባቸው፣ አይሁዳውያን የሱስን ያልተቀበሉትና የሰቀሉት በዚሁ ተመሳሳይ ምክንያት ነበር። ከክርስቶስ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፣ ታማኝ ደቀ መዛሙርቱ የኃጢአትን መንገድ የሚወዱትንና የሚከተሉትን ጥላቻና ተቃውሞ ቀስቅሰዋል።GCAmh 36.5

    ታዲያ እንደዚህ ከሆነ እንዴት ነው ወንጌሉ የሰላም መልእክት ተብሎ የሚጠራው? ኢሳያስ ስለሚወለደው መሲህ አስቀድሞ ሲናገር፦ “የሰላም ልዑል” የሚል ማዕረግ ሰጥቶት ነበር። ክርስቶስ መወለዱን መላዕክት ለእረኞች ሲያበስሩ፣ በቤተልሔም ሜዳዎች፣ “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ” ብለው ዘምረው ነበር [ሉቃ 2÷14]። በእነዚህ ትንቢታዊ አዋጆችና “ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም” [ማቴ 10÷34] በሚሉት የክርስቶስ ቃላት መካከል ተቃርኖ ያለ ይመስላል። በትክክል ከተስተዋሉ ግን ሁለቱ ፍጹም ስምምነት ያላቸው ናቸው። ወንጌሉ የሰላም መልእክት ነው። ክርስትና ለሚቀበሉትና ለሚታዘዙት ሰላምን፣ መስማማትንና ደስታን በዓለም ዳርቻ ሁሉ የሚያሰራጭ መዋቅር ነው። የክርስቶስ ኃይማኖት፣ ትምህርቶቹን የሚቀበሉትን ሁሉ በጠበቀ ወንድማማችነት አቀራርቦ አንድ ያደርጋቸዋል። ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ብሎም እርስ በርሱ ማስታረቅ የየሱስ ተልዕኮ ነበር። አብዛኛው ዓለም ግን የክርስቶስ ቀንደኛ ጠበኛ በሆነው በሰይጣን ቁጥጥር ሥር ነው። ወንጌሉ የሚያቀርባቸው የሕይወት መርሆዎች ከእነርሱ ልማድና ፍላጎት ጋር ሙሉ በሙሉ የሚቃረኑ በመሆናቸው በአመጽ ይነሱበታል። ኃጢአታቸውን የሚገልጠውንና የሚያወግዘውን ንጽህና ይጠሉታል፤ ትክክለኛውንና ቅዱሱን መጠይቁን ይፈጽሙ ዘንድ የሚገፋፏቸውንም ያሳድዳሉ፣ ይደመስሳሉ። የሚያቀርባቸው የከበሩ እውነቶች ጸብንና ጥላቻን ስለሚቀሰቅሱ፣ ከዚህ አንጻር ነው ወንጌሉ ሰይፍ ተብሎ የሚጠራው።GCAmh 37.1

    ጻድቃን በኃጢአተኞች እጅ ስደት ይደርስባቸው ዘንድ የሚፈቅደው ሚስጥራዊው አቅርቦት በእምነት ደካማ ለሆኑ ለብዙዎች ታላቅ ግራ መጋባት ምክንያት ሆኖ ቆይቷል። በመልካምነታቸውና በንጽህናቸው ተወዳዳሪ የሌላቸው እነርሱ በጨካኝ ጉልበታቸው ሲጎሳቆሉ ሳለ፣ እጅግ ወራዳ ተግባር የሚፈጽሙትን በማበልጸጉ ምክንያት፣ አንዳንዶች በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን አመኔታ እስከመተው ድረስ የተዘጋጁ ሆነዋል። እውነተኛ ፈራጅና ሩኅሩኅ አምላክ፣ በሃይሉም መጠን-የለሽ የሆነው ጌታ፣ እንዲህ ዓይነት የፍርድ መጓደልንና ጭቆናን እንዴት ይታገሳል? የሚል ጥያቄ ይነሳል። ይህ እኛን የሚመለከት ጥያቄ አይደለም። እግዚአብሔር ስለ ፍቅሩ አጥጋቢ ማስረጃ ሰጥቶናል፣ በመሆኑም የፈቃዱን አሰራር ስለማንረዳው ብቻ መልካምነቱን ልንጠራጠር አይገባንም። በጽልመትና በፈተና ጊዜ ነፍሳቸውን የሚያስጨንቀውን ጥርጥር ወደፊት ተመልክቶ መሲሁ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ “ባርያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን ቃል አስቡ። እኔን አሳደውኝ እንደሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዷችኋል።” [ዮሐ 15÷20]። በእርጉም ሰዎች ጭካኔ ተከታዮቹ ሊደርስባቸው ከሚችለው ማናቸውም አይነት ግፍ በላይ የሱስ ስለእኛ ተሰቃይቷል። በግርፋትና በሰማዕትነት ፀንተው ያልፉ ዘንድ የተጠሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ውድ ልጅ ያለፈበትን ዱካ የሚከተሉ ናቸው።GCAmh 37.2

    “ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም” [2ኛ ጴጥ 3÷9]፤ ልጆቹን አይረሳም፤ ቸልም አይልም። ሆኖም ማንም ፈቃዱን ያደርግ ዘንድ የሚወድ ሁሉ በበደለኞች እንዳይታለል፣ እውነተኛ ባህርያቸውን ይገልጹ ዘንድ ለኃጥአን ይፈቅድላቸዋል። በተጨማሪም፤ ምሳሌአቸው ስለ እምነትና ስለ እግዚአብሔርን መምሰል እውንነት (ተግባራዊነት) ሌሎችን ያሳምን ዘንድ፣ የማይናወጠው አቋማቸውም ከሃዲዎችንና እምነት የለሾችን ያወግዝ ዘንድ፣ ጻድቃን ራሳቸው የበለጠ ይነጥሩ ዘንድ፣ በስቃይ እቶን እሳት ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋሉ።GCAmh 38.1

    የአመጻቸውን ጽዋ ሲሞሉ፣ በፍጹም ውድመታቸው የእርሱን ፍትሃዊነትና ምሕረት ሁሉም ያዩ ዘንድ፣ ለእርሱ ያላቸው ጥላቻ ገሃድ እንዲወጣ፣ እንዲበለጽጉም እግዚአብሔር ለኃጢአተኞች ይፈቅድላቸዋል። ሕጉን የተላለፉና ሕዝቦቹን የጨቆኑ ሁሉ ለሥራቸው የሚገባቸውን አቻ ፍርድ የሚያገኙበት፣ በእግዚአብሔር አማኞች ላይ የተፈጸመ እያንዳንዱ ጭካኔ ወይም የፍርድ መዛባት ልክ በክርስቶስ በራሱ ላይ እንደተፈጸመ ተቆጥሮ የሚቀጣበት፣ ያ የበቀል ቀኑ በፍጥነት ይደርሳል።GCAmh 38.2

    የዛሬዎቹን አብያተ ክርስቲያናት ቀልብ መሳብ የሚገባው ሌላ በጣም አስፈላጊ ጥያቄ አለ። ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር፣ “በእውነትም በክርስቶስ የሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።” [2ኛ ጢሞ 3÷12] ይላል። ታዲያ ለምንድነው በአብዛኛው ስደት የቀዘቀዘ የሚመስለው? ብቸኛው ምክንያት ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ከዓለም ደረጃ (መስፈርት) ጋር ራስዋን ስላስማማች ተቃውሞን ስለማትቀሰቅስ ነው። በዚህ በእኛ ዘመን ያለው ኃይማኖት፣ በክርስቶስና በሐዋርያት ዘመን የነበረው የክርስትና እምነት ንጹህና ቅዱስ ባህርይ አሻራ ያለው አይደለም። ክርስትና በዓለም እጅግ ተወዳጅ ኃይማኖት ሆነበት ምክንያት ከኃጢአት ጋር ለመደራደር ካለው ፍላጎት የተነሳ፣ የእግዚአብሔር ቃል ታላላቅ እውነቶች በቸልተኝነት በመታየታቸውና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሕያው የሆነ እግዚአብሔርን መሰልነት በመመናመኑ ነው ። እስኪ የቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ኃይል ይታደስ፣ የስደት መንፈስ እንደገና ያንሰራራል፣ የስደት እሳትም እንደገና ይቀጣጠላል።GCAmh 38.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents