Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፳፰—የፍርድ ምርመራ - የሕይዎትን መዝገብ መገናኘት

    “ዙፋኖች እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ” ይላል ነብዩ ዳንኤል፣ “በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደበረዶ ነጭ የራሱም ጠጉር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፤ መንኮራኩሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ፣ የእሳት ፈሳሽ ከፊቱ ይፈልቅና ይወጣ ነበር፤ ሺህ ጊዜ ሺህ ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ አዕላፋትም በፊቱ ቆመው ነበር፤ ለፍርድም ተቀመጠ መጻሕፍትም ተገለጡ።” [ዳን 7÷9፣10]።GCAmh 347.1

    የሰዎች ባህርያትና ሕይወት በዓለም ሁሉ ፈራጅ ፊት የሚፈተሽበት፣ ለእያንዳንዱም ሰው “እንደ ሥራው መጠን” የሚከፈልበት የታላቁና አስፈሪው ቀን ራዕይ ለነብዩ የቀረበው በእንዲህ ሁኔታ ነበር። በዘመናት የሸመገለው እግዚአብሔር አባት ነው። መዝሙረኛው እንዲህ ይላል፦ “ተራሮች ሳይወለዱ ምድርም ዓለምም ሳይሰሩ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ” [መዝ 90÷2]። የፍጡር ሁሉ መነሻ፣ የሕግ ሁሉ ምንጭ፣ ፍርድም የሚሰጥ እርሱ ነው። ቁጥራቸው “ሺህ ጊዜ ሺህ፣ እልፍ አዕላፋትም” የሚሆን፣ አገልጋዮችና መስክሮች የሚሆኑ ቅዱሳን መላእክት በዚህ ታላቅ ፍርድ ሸንጎ ይታደማሉ።GCAmh 347.2

    “እነሆም የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማያት ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ ወደፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብርም መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱ የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው” [ዳን 7÷13፣14]። እዚህ ላይ የተገለፀው የክርስቶስ ምፅዓት፣ ወደ ምድር የሚመጣበት ዳግም ምፅዓቱ አይደለም። የመካከለኛነት (የአማላጅነት) ሥራውን በጨረሰ ጊዜ ግዛት፣ ክብርና መንግሥት ይቀበል ዘንድ በሰማይ ወዳለው በዘመናት ወደ ሸመገለው ይመጣል። በ2300 ቀናቱ መጨረሻ፣ በ1844 ዓ.ም እንደሚፈፀም በትንቢት የተነገረው ምፅዓትም ወደ ምድር የሚያደርገው ዳግም ምፅዓት ሳይሆን፣ ይህ [በዘመናት ወደ ሸመገለው፣ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚሄድበት] ምፅዓት ነው። በሰማያዊ መላእክት ታጅቦ ታላቁ ሊቀ ካህናችን ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ይገባል፤ በዚያም ስፍራ በአባቱ መገኘት ስለ ሰው የሚያደርገውን የመጨረሻውን አገልግሎት ይፈጽማል። ይህም አገልግሎት የፍርድ ምርመራን ተግባር በማከናወን ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ለተገባቸው ሁሉ ስርየት ያደርግ ዘንድ ነው።GCAmh 347.3

    በምሳሌና ጥላው ሥርዓት፣ በስርየት ቀን አገልግሎት መሳተፍ የሚችሉት በኑዛዜና በንስሐ ወደ እግዚአብሔር የቀረቡ በኃጢአት መስዋዕቱም ኃጢዓታቸው ወደ መቅደሱ የተላለፈላቸው ብቻ ነበሩ። በመጨረሻው ስርየት ታላቅ ቀንና በፍርድ ምርመራውም የሚታዩት የእግዚአብሔር ታማኝ አገልጋዮች [ነን ባዮች] መዝገቦች ብቻ ናቸው። የኃጥአን ፍርድ ለየቅልና የተነጠለ ሥራ ሲሆን የሚከናወነውም ቆይቶ ነው። “ፍርድ የሚጀምርበት ጊዜ አለና በእግዚአብሔር ቤት። አስቀድሞም በእኛ የሚጀምር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?” [1ኛ ጴጥ 4÷17]።GCAmh 347.4

    የሰዎችን ስምና የሰሯቸውን ሥራዎች የያዙት በሰማይ ያሉት መዛግብት የፍርዱን ውሳኔዎች የሚወስኑ ናቸው። ነብዩ ዳንኤል ሲናገር፦ “ለፍርድም ተቀመጠ መጻሕፍትም ተገለጡ” ይላል። ገላጩ [የሱስ] ይህንኑ ትእይንት ሲገልፀው እንዲህ ይጨምርበታል፦ “ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፣ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።” [ራዕይ 20÷12]።GCAmh 347.5

    የሕይወት መጽሐፍ ወደ እግዚአብሔር አገልግሎት የገቡትን ሁሉ ስም ይዟል። የሱስ ለደቀ መዛሙርቱ “ስማችሁ ግን በሰማያት ስለተፃፈ ደስ ይበላችሁ” [ሉቃ 10÷20] አላቸው። “ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት” [ፊልጵ 4÷3] መካከል እንዲሆኑ ጳውሎስ ስለታማኝ አጋር ሰራተኞቹ ይናገራል። “እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን” አቆልቁሎ በመመልከት ዳንኤል የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንደሚድኑ “በመጽሐፍ ተጽፎ የተገኘው….እያንዳንዱ ይድናል” [ዳን 12÷1] በማለት ይናገራል። ገላጩም [የሱስም] “ወደ እግዚአብሔር ከተማ የሚገቡት ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ የተፃፉት ብቻ ናቸው” ይላል [ራዕይ 21÷27]።GCAmh 348.1

    “እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ” [ሚል 3÷16] መልካም ሥራቸው ይሰፍርበት ዘንድ “የመታሰቢያ መጽሐፍ” በእግዚአብሔር ፊት ይጻፋል። የእምነት ንግግሮቻቸው፣ የፍቅር ድርጊቶቻቸው፣ በሰማይ ይመዘገባል። ይህንን እያስታወሰ ነህምያ ሲናገር፣ “አምላኬ ሆይ ስለዚህ አስበኝ ለአምላኬም ቤት ያደረግሁትን ወረታዬን አታጥፋ” [ነህ 13÷14] ይላል። እያንዳንዱ የጽድቅ ሥራ በእግዚአብሔር የመታሰቢያ መጽሐፍ ውስጥ ፍፁም የማይጠፋ እንዲሆን ይደረጋል። እዚያ፣ መቋቋም የተቻለው እያንዳንዱ ፈተና፣ ማሸነፍ የተቻለው እያንዳንዱ ክፋት፣ የተነገረው እያንዳንዱ የኃዘኔታ ቃል፣ በታማኝነት ይመዘገባል። እያንዳንዱ የመስዋዕትነት ተግባር፣ ስለ ክርስቶስ የታለፈው እያንዳንዱ ስቃይና ሀዘን ይመዘገባል። መዝሙረኛው፣ “ቅብዝበዛዬን [መቅበዝበዜን] ትቆጥራለህ። አንተ እንቤን [እንባዬን] በስልቻህ አስቀምጥ በመጽሐፍህ የተፃፈ አይደለምን?” [መዝ 56÷8] ይላል።GCAmh 348.2

    የሰዎች ኃጢአት የሚመዘገብበት መዝገብም አለ። “እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን ወደ ፍርድ ያመጣዋልና” [መክ 12÷14]። “ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል።” ይላል አዳኙ፣ “ከቃልህም የተነሳ ትፀድቃለህና ከቃልህም የተነሳ ትኮነናለህና” [ማቴ 12÷36፣37]። የተደበቁ ዓላማዎችና ፍላጎቶች ሁሉ በማይሳሳተው መዝገብ ይሰፍራሉ። “በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሐን የሚያወጣ፣ የልብንም ምክር የሚገልጥ እግዚአብሔር ነውና” [1ኛ ቆሮ 4÷5]። “እነሆ በፊቴ ተጽፎአል ኃጢአታችሁና የአባቶቻችሁ ኃጢአት በአንድ ላይ።” [ኢሳ 65÷6፣7]።GCAmh 348.3

    የእያንዳንዱ ሰው ሥራ በእግዚአብሔር ፊት እየተከለሰ (እየታየ) ያልፋል፤ ታማኝ ወይም እምነት አጉዳይ ተብሎም ይመዘገባል። በእያንዳንዱ ስም ትይዩ፣ በሰማይ መጻሕፍት፣ በሚያስገርም ሁኔታ አንዳች ጠብ ሳትል እያንዳንዷ የስህተት ቃል፣ እያንዳንዷ የራስ ወዳድነት ተግባር፣ እያንዳንዷ ያልተፈፀመች ኃላፊነት፣ እያንዳንዷ የምስጢር ኃጢአት ከእያንዳንዷ ጮሌ አስመሳይነት ጋር ትመዘገባለች። ቸል የተባሉ፣ ከሰማይ የተላኩ ማስጠንቀቂያዎች ወይም ተግሳፆች፣ የባከኑ ቅጽበተ-አፍታዎች፣ ያልተሻሻሉ እድሎች፣ ለመልካም ወይም ለክፋት የዋለ ተጽዕኖ ከአድማሰ-ሰፊ ውጤቱ ጋር፣ ሁሉም በሚመዘግበው መልአክ ይፃፋሉ።GCAmh 348.4

    በፍርድ ጊዜ የሰዎች ባህርያትና ሕይወት መለኪያ ሆኖ የሚቀርበው የእግዚአብሔር ሕግ ነው። ጠቢቡ እንዲህ ይላል፦ “የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና እግዚአብሔርን ፍራ ትዕዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ…. ወደ ፍርድ ያመጣዋልና” [መክ 12÷13፣14]። ሐዋርያው ያዕቆብ ወንድሞቹን ሲገስጽ፣ “በነፃነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፤ እንዲህም አድርጉ።” [ያዕ 2÷12] ይላል።GCAmh 349.1

    በፍርድ ጊዜ “ሊያገኙ የሚገባቸው [የተገባቸው ሆነው የተቆጠሩ]” በፃድቃን ትንሳኤ ዕድል ፈንታ ይኖራቸዋል። የሱስ እንዲህ ብሎአል፦ “ያን ዓለምና ከሙታን ትንሣኤ ሊያገኙ የሚገባቸው…. እንደ መላእክት ናቸውና [….ከመላእክት ጋር እኩል ናቸውና/….are equal unto the angels] የትንሳኤ ልጆች ስለሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።” [ሉቃ 20÷35፣36]። እንደገናም፣ “መልካም ያደረጉ ለሕይወት ትንሳኤ ይወጣሉና” [ዮሐ 5÷29] ይላል። “ለሕይወት ትንሳኤ” የተገባቸው እንደሆኑ ሳይፈረድላቸው በፊት፣ የሞቱት ፃድቃን አይነሱም [የሞቱ ጻድቃን ለሕይወት የሚነሱት፣ “ለሕይወት ትንሳኤ” የተገባቸው ናቸው ተብሎ ከተፈረደላቸው በኋላ ነው።] ስለዚህም መዝገባቸው በሚመረመርበት፣ ጉዳያቸው ውሳኔ በሚያገኝበት ጊዜ በችሎት ላይ በአካል አይገኙም ማለት ነው።GCAmh 349.2

    ስለ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት ሊማፀን ጠበቃቸው ሆኖ ክርስቶስ ይቀርባል። “ማንም ኃጢአት ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ፃድቅ የሆነ የሱስ ክርስቶስ ነው” [1ኛ ዮሐ 2÷1]። “ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባምና፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።” “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” [ዕብ 9÷24፤ 7÷25]።GCAmh 349.3

    በፍርድ ጊዜ የመዝገብ መጻሕፍት ሲከፈቱ፣ በየሱስ ያመኑት ሁሉ ሕይወት በእግዚአብሔር ፊት ይዳሰሳል። አስቀድመው በምድር ይኖሩ ከነበሩት ይጀምርና፣ ጠበቃችን፣ የእያንዳንዱን ቀጣይ ትውልድ መዝገብ ያቀርብና በሕይወት ባሉት ይጨርሳል። እያንዳንዱ ስም ይጠቀሳል፤ እያንዳንዱ ጉዳይም ይመረመራል። ስሞች ተቀባይነት ያገኛሉ፣ ስሞች ተቀባይነት ያጣሉ። ያልተናዘዙአቸውና ይቅር ያልተባሉ፣ በመዝገብ መጽሐፍ ውስጥ የቀሩ (ያልተፋቁ) ኃጢአቶች ያሏቸው እነርሱ ስማቸው ከሕይወት መጽሐፍ ይፋቃል። ተጽፎ የነበረው የመልካም ሥራቸው መዝገብም ከእግዚአብሔር የመታሰቢያ መጽሐፍ ይወገዳል። ጌታ ለሙሴ ሲናገር “የበደለኝን እርሱን ከመጽሐፌ እፍቀዋለሁ” [ዘፀ 32÷33] ይላል። ነብዩ ሕዝቅኤል ደግሞ፣ “ፃድቁም ከጽድቁ ቢመለስ፣...ርኩሰትም ቢሰራ፣ የሰራት ጽድቅ ሁሉ አትታሰብለትም” [ሕዝ 18÷24] ይላል።GCAmh 349.4

    ከልባቸው ኃጢአትን የተናዘዙ፣ የክርስቶስም ደም በእምነት እንደሚያስተሰረይ መስዋዕት አድርገው የተቀበሉ ሁሉ፣ በስማቸው ትይዩ፣ በሰማይ መጻሕፍት ምሕረት የተደረገለት ተብሎ ይሰፍራል፤ የክርስቶስ ጽድቅ ተካፋዮች በመሆናቸው፣ ባህርያቸውም ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር የተስማማ ሆኖ በመገኘቱ ኃጢአታቸው ይፋቅላቸዋል፤ እርሳቸውም የዘላለም ሕይወት የተገባቸው ሆነው ይቆጠራሉ። በነብዩ ኢሳያስ አማካኝነት ጌታ ሲናገር፦ “እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ ክፋትህን የምደመስስ ስለ እኔ [ስለ እራሴ ስል]፤ ኃጢአትህንም አላስባትም” [ኢሳ 43÷25]። የሱስ አለ፦ “ድል የነሳ ይህ ነጭ ልብስ ይለብሳል። ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አላጠፋውም፤ ስሙንም አምንበታለሁ [እመሰክርለታለሁ]፣ በአባቴ ፊት በመልአክቱም።” “ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።” [ራዕይ 3÷5፤ ማቴ 10÷32፣33]።GCAmh 349.5

    በምድራዊ ችሎቶች፣ በሰዎች መካከል የሚከናወኑ እጅግ ትኩረትን የሚስቡ ዳኝነቶች፣ በሰማያዊ ፍርድ ቤት ዘንድ በሕይወት መጽሐፍ ስማቸው የተፃፉ እነርሱ በምድር ሁሉ ፈራጅ ፊት ቀርበው ሲመረመሩ ከሚንፀባረቀው ትኩረት ጋር ሲነጻፀሩ ላመል ታህል እንደማለት ናቸው። በሰማይ ያለውን ዳኝነት ለመወከል (ለመመሰል) እጅግ አናሳ ናቸው። በደሙ አምነው ያሸነፉ ሁሉ መተላለፋቸው ይቅር እንዲባልላቸው፣ ወደ ኤደን ቤታቸው እንዲመለሱና ከእርሱ ጋር “የቀደመችው ግዛት” በጋራ ወራሽ ሆነው ይነግሱ ዘንድ [ሚክ 4÷8] መለኮታዊው አማላጅ የክስ መልሱን ያቀርባል። ሰይጣን የእኛን ዘር ለመፈተንና ለማሳሳት ባደረገው ጥረት በሰው ፍጥረት ላይ የነበረውን መለኮታዊ እቅድ ሊያሰናክል አስቦ ነበር፤ አሁን ግን ክርስቶስ ይህ እቅድ ተግባራዊ እንዲሆን፣ ሰውም ፈጽሞ ወድቆ የማያውቅ (ኃጢአት ሰርቶ የማያውቅ) ሆኖ እንዲቆጠር ይጠይቃል። ለሕዝቦቹ የሚጠይቀው ሙሉና ፍፁም የሆነ ምሕረትና ጽድቅ ብቻ ሳይሆን ከእርሱ ክብር እንዲጋሩና በዙፋኑም ላይ መቀመጫ እንዲያገኙ ጭምር ነው።GCAmh 350.1

    በፀጋው ስር ላሉ የሱስ ሲሟገትላቸው ሳለ ሰይጣን ደግሞ ተላላፊዎች እንደሆኑ አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ይከሳቸዋል። ታላቁ አታላይ፣ ወደ ጥርጥር እንዲገቡ፣ በእግዚአብሔር ላይ እምነት እንዲያጡ፣ ከፍቅሩ ራሳቸውን እንዲነጥሉና ሕጉንም እንዲጥሱ ሲጥር ኖሯል። አሁን ወደ ሕይወታቸው መዝገብ፣ ወደ ባህርያቸው ጉድለቶች፣ አዳኛቸውንም ስላዋረደው፣ ክርስቶስን ስለማይመስለው ጠባያቸው፣ ይፈጽሙት ዘንድ ወደገፋፋቸው ወደ ሁሉም ኃጢአታቸው እያመለከተ፣ በዚህም ምክንያት፣ የእርሱ ተገዥዎች መሆናቸውን ያትታል።GCAmh 350.2

    የሱስ ለኃጢአታቸው ማስተባበያ አያቀርብም፤ ነገር ግን ፀፀታቸውንና እምነታቸውን ያሳያል፤ ይቅርታ ሲጠይቅላቸው ሳለም የቆሰሉ እጆቹን በአባቱና በመላእክት ፊት አንስቶ፣ “በስማቸው አውቃቸዋለሁ፤ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጫቸዋለሁ” በማለት ያውጃል። “የእግዚአብሔር መስዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤ አቤቱ ሆይ የተሰበረውንና የተደቆሰውን ልብ አትንቅም” [መዝ 51÷17]። የሕዝቦቹም ከሳሽ ለሆነው እንዲህ ይናገራል፦ “ሰይጣን ሆይ እግዚአብሔር ይገስጽህ፤ የሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገስጽህ፤ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን?” [ዘካ 3÷2]። “እንዲህ ዓይነት ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን” [ኤፌ 5÷27] አድርጎ ለአባቱ ያቀርባቸው ዘንድ ለእርሱ የታመኑትን በራሱ የጽድቅ ልብስ ያለብሳቸዋል። ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ እንደሰፈሩ ይቀራሉ፤ እነርሱንም በተመለከተ ተጽፎአል፦ “የተገባቸው ስለሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።” [ራዕይ 3÷4]።GCAmh 350.3

    የአዲሱ ቃል ኪዳን ተስፋ ሙሉ በሙሉ በመፈፀም በእንዲህ ሁኔታ ተግባራዊ ይሆናል። “ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ ደግሞም በደላቸውን አላስብም።” “በዚያች ወራት በዚያም ዘመን ይላል እግዚአብሔር የእሥራኤል በደል ይፈለጋል እርሱም የለም፤ የይሁዳም ኃጢአት አይገኝም” [ኤር 31÷34፤ 50÷20]። “በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቁጥቋጥ (branch) ለጌጥና ለክብር ይሆናል፤ ከእሥራኤልም ወገን ላመለጡ ሰዎች የምድሪቱ ፍሬ ለትምክህትና ለውበት ይሆናል። በጽዮንም የቀረ ሁሉ በየሩሳሌምም የተረፈ ቅዱስ ይባላል በየሩሳሌምም ለሕይወት የተፃፈ ሁሉ።” [ኢሳ 4÷2፣3]።GCAmh 351.1

    የፍርዱ ምርመራና የኃጢአት መፋቅ ሥራ ከጌታ ዳግም ምፅዓት በፊት የሚከናወን ሥራ ነው። ሙታን የሚዳኙት በመጽሐፉ እንደተፃፈው በመሆኑ ጉዳያቸው ተመርምሮ ውሳኔ ከተሰጣቸው በኋላ ካልሆነ በስተቀር የሰዎች ኃጢአት ሊፋቅ አይችልም። ሐዋርያው ጴጥሮስ ግልጽ አድርጎ እንደተናገረው የአማኞች ኃጢአት የሚፋቀው “የእረፍት [የመታደስ] ዘመን ትመጣላችሁ ዘንድ ከእግዚአብሔር ፊት። የሱስ ክርስቶስንም ይሰድላችሁ ዘንድ” [የሐዋ ሥራ 3÷19፣20] የሚለው ቃል በሚፈፀምበት ዘመን ነው። የፍርድ ምርመራው ሲጠናቀቅ፣ ክርስቶስ ይመጣል፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ይከፍል ዘንድ ዋጋው ከእርሱ ጋር ይሆናል።GCAmh 351.2

    በምሳሌያዊው አገልግሎት፣ ሊቀ ካህኑ፣ ለእሥራኤል ስርየት ካደረገ በኋላ ወደ ውጪ መጥቶ ጉባኤውን ይባርክ ነበር። ክርስቶስም እንደ መካከለኛ ሥራውን ሲፈጽም “ያድናቸው ዘንድ…ያለ ኃጢአት” [ዕብ 9÷28] የሚጠባበቁ ሕዝቦቹን በዘላለም ሕይወት ይባርክ ዘንድ ይገለጣል። ካህኑ ኃጢአት ከመቅደሱ ሲያስወግድ በሚለቀቀው ፍየል ራስ ላይ እንደሚናዘዝ ሁሉ ክርስቶስም ኃጢአትን ሁሉ በኃጢአት ምንጭ/መነሻና አነሳሽ በሆነው በሰይጣን ላይ ያኖረዋል። ፍየሉ የእሥራኤልን ኃጢአት ተሸክሞ “ወደ በረሃ [a land not inhabited]” ይለቀቅ ነበር [ዘሌዋ 16÷22]፤ ሰይጣንም የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንዲፈጽሙት ያደረጋቸውን የኃጢአት ኩነኔ ተሸክሞ ምድረ በዳ በሆነች፣ ምንም በማይኖርባት ምድር ላይ ተገድቦ ለአንድ ሺህ አመት ይቆያል። በመጨረሻም ሁሉንም ኃጢአት በሚያጠፋው እሳት፣ ሙሉውን የኃጢአት መቀጮ ያገኛል። እንዲህም በኃጢአት መወገድ የታላቁ የማዳን እቅድ ወደ ፍፃሜ ይደርሳል፤ ክፋትን ለመተው የፈቀዱ ሁሉ መቤዠታቸው እንዲህ ይከናወናል።GCAmh 351.3

    ለፍርድ በተመደበው ሰዓት — 2300 ቀናት ባበቁበት በ1844 ዓ.ም — የምርመራውና ኃጢአትን የመፋቁ ሥራ ተጀምሯል። የክርስቶስን ስም በራሳቸው ላይ አድርገው (ተሸክመው) የሚያውቁ ሁሉ በጥንቃቄ የሚካሄደውን ምርመራ ማለፍ አለባቸው። “ሕያዋንም ሆኑ ሙታን፣ ሁለቱም በመጽሐፍ ተጽፎ እንደነበረ እንደሥራቸው መጠን ፍርድ ይቀበላሉ።” [ራዕይ 20÷12]።GCAmh 351.4

    ኑዛዜ ያልተደረገባቸውና ያልተተው ኃጢአቶች ይቅርታ አያገኙም፤ ከመዝገብ መጻሕፍትም አይፋቁም፤ በኃጢአተኛው ላይ በእግዚአብሔር ቀን ይመሰክሩበት ዘንድ ይቀራሉ እንጂ። የክፋት ሥራውን የፈፀመው በጠራራ ፀሐይ ወይም በውድቅት ጨለማ ይሆናል፤ መልስ መስጠት በሚገባን በእርሱ ፊት ግን ክፍትና ግልጽ ነበሩ። የእግዚአብሔር መላእክት እያንዳንዱ ኃጢአት ሲፈፀም አይተዋል፤ በማይሳሳተው መዝገባቸውም መዝግበውታል። ኃጢአት ከአባት፣ ከእናት፣ ከሚስት፣ ከልጆችና ከባልደረቦች ሊደበቅ፣ ሊካድ ወይም ሊሸፈን ይችላል። ኩነኔውን ከፈፀመው በስተቀር ስለ ስህተቱ የሚጠረጥር ማንም ላይኖር ይችላል፤ በሰማይ ሊቆች ፊት ግን እርቃኑን የቀረ ነው። እጅግ ጥቅጥቅ ያለው የሌሊት ጨለማ፣ የማታለያ ጥበቦች ሁሉ ረቂቅነት፣ አንዲት ቅንጣት ሃሳብን እንኳ ከዘላለማዊው ከእግዚአብሔር እውቀት ለመጋረድ ብቁ አይደሉም። የእያንዳንዱ የክፋት ሥራና የእያንዳንዱ ሚዛናዊ ያልሆነ ተግባር ሁሉ እቅጩን የሆነ መዝገብ እግዚአብሔር አለው። ቅዱስ ለመምሰል በሚደረግ ታይታ እርሱ አይታለልም፤ ባህርይን ሲመዝን ስህተት አይሰራም። በልባቸው ብልሹ በሆኑ፣ በእነርሱ፣ ሰዎች ሊታለሉ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን ሁሉን መሸፈኛ በስቶ ይገባል፤ የውስጠኛውን ሕይወትም ያነባል።GCAmh 351.5

    እንዴት ያለ ከባድ ሐሳብ ነው! ቀን አልፎ ቀን ሲተካ፣ እያንዳንዱ ቀን ወደ ዘላለም እያሳለፈ፣ የመዝገቡን ጭነት ለሰማያዊ መዛግብት ያሸክማል። አንዴ የተነገሩ ቃላት፣ አንዴ የተፈፀሙ ድርጊቶች ፈጽሞ መመለስ (አለመሆን፣ መቀልበስ) አይችሉም፤ መልካሙንም ክፉውንም መላእክት መዝግበዋቸዋል። በዓለም ላይ ያለ እጅግ ወደር የሌለው ድል አድራጊ ጦረኛ፣ የአንዲት ቀንዋን መዝገብ እንኳ ማስቀረት አይችልም። ድርጊቶቻችን፣ ቃላቶቻችን፣ እጅግ ድብቅ የሆኑት ፍላጎቶቻችን እንኳ ደስታ ወይም ዋይታ በሚሆነው የመዳረሻችን ሚዛን ላይ ክብደት ይጨምራሉ፤ በእኛ ዘንድ የተረሱ ቢሆኑም ለማጽደቅ ወይም ለመኮነን ግን ምስክርነታቸውን ያሰፍራሉ።GCAmh 352.1

    የፊት ገጽታዎች በሰዓሊው ገበታ ላይ ዝንፍ ሳይሉ፣ በትክክል ተመስለው እንደሚሳሉ ሁሉ ባህርይም እንዲሁ በታማኝነት በሰማይ መጻሕፍት ይሰፍራል። ለዚህ፣ የሰማይ ፍጡራን ፊት ለፊት ለሚመለከቱት መዝገብ፣ የሚሰጠው ትኩረት ግን እንዴት አናሳ ነው! የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም የሸፈነው መጋረጃ ቢገለጥና፣ በፍርድ ቀን እንደገና የሚገናኙትን፣ እያንዳንዱን ቃልና ተግባር መልአኩ ሲመዘግብ የሰው ልጆች ቢመለከቱ፣ በየቀኑ የሚነገሩ ስንት ቃላት ከአፍ ሳይወጡ ይቀሩ ነበር፤ ስንት የተሰሩ ሥራዎች ከመሰራት ይተዉ ነበር።GCAmh 352.2

    በፍርድ ጊዜ፣ ጥቅም ላይ የዋለው እያንዳንዱ ክህሎት፣ በጥብቅ ይመረመራል። ሰማይ ያበደረንን መክሊት እንዴት ነው ጥቅም ላይ ያዋልነው? ጌታ በምፅዓቱ ጊዜ የራሱን ከነወለዱ ይቀበል ይሆን? በእጅ፣ በልብ፣ በአዕምሮ፣ በአደራ የተሰጡንን ክህሎቶች አሻሽለናቸዋል? ለእግዚአብሔር ክብር ለዓለምስ በረከት አውለናቸዋል? ጊዜያችን፣ ብዕራችን፣ ድምጻችን፣ ገንዘባችን ወይስ ተጽዕኖአችን እንዴት ነው የምንጠቀምበት? በምስኪኑ፣ በተጎሳቆለው፣ በወላጅ አልባው ወይም በመበለቷ አካል አምሳል ለምናየው ክርስቶስ ምን አድርገንለታል? እግዚአብሔር የቅዱስ ቃሉ ግምጃ ቤት አድርጎናል፤ ሰዎች የመዳን ጥበብ ይኖራቸው ዘንድ በተሰጠን ብርሐንና እውነት ምን አድርገንበታል? እንዲሁ በቃል ብቻ የክርስቶስ እምነት አለኝ ለሚል አባባል የወጣ ዋጋ የለም፤ እውነተኛ ሆኖ የሚቆጠር ፍቅር በሥራ የተገለፀው ብቻ ነው። በሰማይ እይታ ማንኛውንም ተግባር ዋጋ ያለው የሚያደርገው ፍቅር ብቻ ነው። ከፍቅር የተደረገ ማንኛውም ነገር፣ በፍጡራን ግምት ምኑንም ያህል አናሳ ዋጋ ያለው ቢመስል፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትና ሽልማት አለው።GCAmh 352.3

    የተደበቀው የሰዎች ራስ ወዳድነት በሰማይ መጻሕፍት የተገለጠ ነው። ለባልንጀሮቻቸው ማከናወን የነበረባቸው ኃላፊነቶች፣ የአዳኙንም መጠይቆች የረሱበት መዝገብ አለ። የክርስቶስ ንብረት የሆነው ጊዜ፣ ሃሳብና ጉልበት ምን ያህል፣ በተደጋጋሚ ለሰይጣን እንደተሰጠ እዚያ ያያሉ። መላእክት ወደ ሰማይ የሚወስዱት መዝገብ አሳዛኝ መዝገብ ነው። በሳል አእምሮ ያላቸው ፍጡራን፣ የክርስቶስ ታማኝ ተከታዮች [ነን ባዮች] የዓለማዊ ንብረቶችን በመሰብሰብ ወይም ምድራዊ መቦረቂያዎችን በማጣጣም ተመስጠዋል። ገንዘብ፣ ጊዜና ጉልበት ለታይታና ራስን ለማርካት መስዋዕት ይሆናሉ። ለፀሎት፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለመመርመር፣ ነፍስን ዝቅ ለማድረግና ኃጢአትን ለመናዘዝ የሚጠፋው ጊዜ ግን እጅግ አናሳ ነው [የለም ማለት ይቀላል]።GCAmh 353.1

    ጥንቅቅ አድርገን በምናውቀው ሥራ ላይ ትኩረት አድርጎ እንዳይኖር አእምሮአችንን የሚይዙ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዘዴዎች ሰይጣን ይፈጥርልናል። ስርየት የሚያስገኘውን መስዋዕትና እጅግ ኃያል የሆነውን አስታራቂ ወደ እይታ እንዲያመጡ የሚያደርጉትን ታላላቅ እውነቶች የአታላዮች ቁንጮ ይጠላቸዋል። ሁሉም ነገር የሚወሰነው አዕምሮን (ሰዎችን) ከየሱስና ከእርሱ እውነት ገለል አድርጎ በሌላ መንገድ ሊመራቸው በመቻሉ ላይ እንደሆነ ያውቃል።GCAmh 353.2

    የአዳኙን የመካከለኛነት (የአማላጅነት) ጥቅም የሚጋሩ ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ፍርሃት ውስጥ፣ ፍፁም ለሆነ ቅድስና ካለባቸው ኃላፊነት ጋር ጣልቃ የሚገባ ምንም ነገር መፍቀድ የለባቸውም። ውድ ዋጋ ያላቸው ሰዓታት ለፈንጠዝያ፣ ለታይታ ወይም ትርፍ ለማግኘት ከመዋል ይልቅ ልባዊ በሆነና በፀሎት ለታጀበ የእውነት ቃል ጥናት መዋል ይገባቸዋል። የቤተ መቅደሱና የፍርድ ምርመራ ርዕሶች በእግዚአብሔር ሕዝቦች ዘንድ በደንብ መስተዋል አለባቸው። እያንዳንዳቸው ስለ ታላቁ ካህናቸው ደረጃና ሥራ በግላቸው እውቀት ሊኖራቸው ይገባቸዋል። ያለበለዚያ በዚህ ጊዜ አስፈላጊ የሆነውን እምነት ሥራ ላይ ማዋል ወይም እግዚአብሔር ያቀደላቸውን ደረጃ መያዝ የማይቻላቸው ይሆናሉ። እያንዳንዱ ግለሰብ የሚያድነው ወይም የሚያጠፋው ነፍስ አለው። እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር ፍርድ ቤት ያልተቋጨ ጉዳይ አለው። እያንዳንዱ ሰው ታላቁን ፈራጅ ፊት ለፊት መገናኘት ይኖርበታል። ታዲያ ችሎት ሲሰየም፣ መጻሕፍትም ሲከፈቱ፣ በመጨረሻው ቀን ከዳንኤል ጋር ሁሉም በዕጣ ክፍሉ ሲቆም ያለውን ትዕይንት፣ እያንዳንዱ አዕምሮ ያሰላስል ዘንድ እንዴት አስፈላጊ ነው!GCAmh 353.3

    በእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ብርሐን የተቀበሉ ሁሉ፣ እግዚአብሔር አደራ የሰጣቸውን እነዚህን ታላላቅ እውነቶች ይመሰክሩ ዘንድ ይገባቸዋል። በሰማይ ያለው ቤተ-መቅደስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሲል የሚያከናውነው ሥራ ማዕከል ነው። በምድር ላይ የሚኖርን እያንዳንዱን ነፍስ ይመለከታል። ወደ ዘመን ማብቂያ ያመጣንና በጽድቅና በኃጢአት መካከል ባለው ግብግብ ድል የሚደረግበትን ጉዳይ በመግለጥ የመዳንን እቅድ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። እነዚህን ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉም በጥሞና ይመረምሩዋቸው ዘንድ፣ በርዕሶቹም ውስጥ ስላለው ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቃቸው፣ ለእያንዳንዱ ግለሰብ መልስ መስጠት ይችሉ ዘንድ እጅግ አስፈላጊ ነው።GCAmh 353.4

    ክርስቶስ ለሰዎች ሲል በሰማይ መቅደስ የሚያከናውነው የማማለድ ሥራ ልክ በመስቀል ላይ የመሞቱን ያህል ለመዳን እቅድ አስፈላጊ ነው። በሞቱ ያንን ሥራ ጀመረ፤ በሰማይ ይፈጽመው ዘንድም ከሞት ከተነሳ በኋላ አረገ። “ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ” [ዕብ 6÷20] ወደገባበት መጋረጃው በእምነት መግባት አለብን። እዚያ የቀራንዮ መስቀል ብርሐን ያንፀባርቃል። በዚያ ስፍራ የመዳንን ምስጢራት በተመለከተ የተሻለ መረዳት እናገኛለን። የሰው ልጅ መዳን የተከናወነው ሊተመን የማይችል ዋጋ ሰማይን አስከፍሎ ነው፤ የተሰዋው መስዋዕት፣ የተጣሰው የእግዚአብሔር ሕግ ሊጠይቀው ከሚችለው ሰፊ መጠይቅ ጋር እኩል ነው [መስዋዕቱ = የሕጉ መጠይቅ]። ወደ አባት ዙፋን የሚወስደውን መንገድ ክርስቶስ ከፍቶታል፤ በመካከለኛነቱ (በአስታራቂነቱ) አማካኝነትም ወደ እርሱ በእምነት የሚመጡ እውነተኛ መሻታቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ይቀርባል።GCAmh 354.1

    “ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረት ያገኛል” [ምሳ 28÷13]። ጥፋታቸውን የሚደብቁና የሚያስተባብሉ እነርሱ ሰይጣን እንዴት እንደሚፍነከነክባቸው፣ በያዙት አቅጣጫ ምክንያት ሰይጣን ክርስቶስንና ቅዱሳን መላእክትን እንዴት በንቀት እንደሚዘልፋቸው [እንደሚገዳደራቸው] ቢመለከቱ ኖሮ ተጣድፈው ኃጢአቶቻቸውን በተናዘዙ፣ ባራቋቸውም ነበር። በባህርይ ግድፈት አማካኝነት ሰይጣን አዕምሮን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ይችል ዘንድ ይሰራል፤ እነዚህ ጉድለቶች ከተበረታቱ እንደሚያሸንፍ ያውቃል። ስለዚህ እጅግ አገደኛ (ገዳይ) በሆነ ማደናገሪያው ሊያታልላቸው፣ ያሸንፏቸውም ዘንድ የማይቻላቸው ይሆኑባቸው ዘንድ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ነው። ነገር ግን የሱስ በቆሰሉት እጆቹ፣ በበለዘው አካሉ አማካኝነት ስለ እነርሱ ይማፀናል፤ ይከተሉት ዘንድ ለሚሹ ሁሉ “ፀጋዬ ይበቃሃል[ችኋል]” ይላቸዋል [2ኛ ቆሮ 12÷9]። “ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ። እኔ የዋህ ነኝና ልቤም ትሁት ነውና ዕረፍት ለነፍሳችሁ ታገኛላችሁ። ቀንበሬ መልካም ነውና ሸክሜም ቀሊል ነውና” [ማቴ 11÷29፣30] ይላቸዋል። ስለዚህም ማንም ግድፈቶቹ የማይሽሩ እንደሆኑ አያስብ፤ [ጉድለቶቹን] ማሸነፍ ይቻለው ዘንድ እግዚአብሔር እምነትና ፀጋ ይሰጣል።GCAmh 354.2

    አሁን እየኖርን ያለነው በታላቁ የስርየት ቀን ነው። በምሳሌና ጥላው (በብሉይ ኪዳን) አገልግሎት ሊቀ ካህኑ ለእሥራኤል ስርየት እያካሄደ በሚሆንበት ጊዜ ከሕዝቡ መካከል እንዳይቀሰፉ፣ ሁሉም፣ ኃጢአታቸውን በመናዘዝና በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን በማዋረድ ነፍሳቸውን ያሰቃዩ ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ ስሞቻቸው ከሕይወት መጽሐፍ [ሳይፋቁ] እንዲቀሩላቸው የሚፈልጉ ሁሉ፣ አሁን በቀሩት ጥቂት የምሕረት ቀናቶቻቸው ስለ ኃጢአት በማዘንና በእውነተኛ ፀፀት በእግዚአብሔር ፊት ነፍሳቸውን ቢያሰቃዩ ይበጃቸዋል። ጥልቅ የሆነ፣ ታማኝ የልብ ምርመራ መካሄድ አለበት። ብዙ ታማኝ ክርስቲያኖች በቀላል፣ ብዙም እርባና በሌለው መንፈስ የመርካታቸው አባዜ ሊወገድ ይገባዋል። የበላይነቱን ለመቆናጠጥ የሚጥሩትን የክፉ ዝንባሌዎች ሊያሸንፉ በሚፈልጉ ሁሉ ፊት ከባድ ውጊያ ተደቅኖአል። የመዘጋጀት ሥራ ግላዊ ሥራ ነው። የምንድነው በቡድን አይደለም፤ የአንዱ ንጽህናና መሰጠት፣ እነዚህ ባህርያት የሚጎለውን የሌላውን አያካክስም። ሁሉም ሕዝቦች በእግዚአብሔር ፊት ለፍርድ ማለፍ የሚገባቸው ቢሆንም ቅሉ፣ በምድር ላይ ሌላ ፍጡር እንደሌለ ያህል አድርጎ የእያንዳንዱን ግለሰብ መዝገብ እጅግ ተጠንቅቆ በነቂስ ይመረምራል። እያንዳንዱ ተመርምሮ፣ እድፍ፣ ነቁጥ ወይም አንዳች ነገር የሌለው ሆኖ መገኘት አለበት።GCAmh 354.3

    ከስርየቱ የማጠቃለያ ሥራ ጋር የተገናኙት ትዕይንቶች አጅግ የከበዱ፣ የከበሩም ናቸው። በዚያ ውስጥ የተካተቱት ነገሮች [ለወደፊት] እጅግ አስፈላጊ ናቸው። አሁን ፍርዱ በላይኛው ቤተ መቅደስ እየተላለፈ ነው። ይህ ሥራ ለበርካታ አመታት ሲካሄድ ቆይቷል [ከ1844 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን]። በቅርብ - ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ ማንም ባያውቅም - ፍርዱ ወደ ሕያዋን መዝገብ ይደርሳል። በሚያስፈራው በእግዚአብሔር መገኘት ፊት ሕይወታችን ይፈተሻል። ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ “ጊዜው መቼ እንደሆነ አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፣ ፀልዩም” [ማር 13÷33] የሚለውን የአዳኙን ማስጠንቀቂያ እያንዳንዱ ነፍስ ያዳምጥ ዘንድ አስፈላጊ ነው። “ባትተጋም እኔ እመጣብሃለሁ እንደ ሌባ። የምመጣብህንም ሰዓት አታውቅም።” [ራዕይ 3÷3]።GCAmh 355.1

    የፍርድ ምርመራው ሥራ በሚጠናቀቅበት ጊዜ የሁሉም ሰው መዳረሻ ለሞት ይሆን ለሕይወት የሚወሰን ይሆናል። በሰማይ ደመና ጌታ ከመገለጡ ከጥቂት ጊዜ በፊት የምሕረት ጊዜ ያበቃል። በራዕይ፣ ክርስቶስ ወደዚያ ጊዜ እየተመለከተ ሲናገር፦ “አመፀኛው ወደፊት ያምጽ፣ እርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ፣ ፃድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፣ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ አለ። እነሆ እመጣለሁ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።” [ራዕይ 22÷11፣12] ይላል።GCAmh 355.2

    ሰዎች፣ እያተከሉ፣ እያነፁ፣ እየበሉና እየጠጡ፣ የመጨረሻው፣ የማይቀለበሰው ውሳኔ በላይ በመቅደሱ እንደታወጀ ሳያስተውሉ፣ ፃድቃንም ኃጢአተኞችም በሟች ሁኔታቸው ሆነው በዚያን ጊዜም በምድር ላይ ይኖራሉ። ከጥፋት ውኃ በፊት፣ ኖህ ወደ መርከቡ ከገባ በኋላ እግዚአብሔር በውስጥ ዘጋበት፤ ከሃዲዎችም በውጪ ቀሩ፤ ሆኖም ጥፋታቸው እንደተወሰነባቸው ሳያውቁ፣ ልቅ፣ የደስታ- ፍቅር ያለበትን ሕይወታቸውን ለሰባት ቀናት ቀጠሉበት፤ ሊመጣ ያለውን የፍርድ ማስጠንቀቂያ ተሳለቁበት። አዳኙ ሲናገር፣ “የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል” አለ [ማቴ 24÷39]። ኮሽ ሳያደርግ፣ እንደ ውድቅት ሌባ ሳይስተዋል፣ የእያንዳንዱ ሰው መዳረሻ እንደተወሰነ ለኃጢአተኞችም የተዘረጋው ምሕረት እንደተወሰደ የሚያመለክተው ወሳኝ ሰዓት ይመጣል።GCAmh 355.3

    “….ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ” [ማር 13÷ 35፣36]። መጠበቃቸው አዝሏቸው ወደ ዓለም መስዕቦች የሚዞሩ ሰዎች ሁኔታ እጅግ አደገኛ ነው። ነጋዴው ትርፍ ለማግኘት ተወስውሶ ሳለ፣ ደስታ (ፈንጠዝያ) አፍቃሪው እርካታ ሲያሳድድ ሳለ፣ የፋሽን ሴት ልጅ መሽቀርቀሪያዋን እያበጃጀች ሳለች — የምድር ሁሉ ፈራጅ “በሚዛን ተመዘንህ ቀልለህም ተገኘህ” ብሎ የሚያውጀው በዚያች ሰዓት ሊሆን ይችላል [ዳን 5÷27]።GCAmh 355.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents