Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፴፭—የጳጳሳዊው መዋቅር ባህርይና አላማዎች -የህሊና ነጻነት ለአደጋ ሲጋለጥ

    ከቀድሞዎቹ ዘመናት ይልቅ ሮማዊነት አሁን በፕሮቴስታንቶች ዘንድ በጣም የተሻለ ተቀባይነት አለው። ካቶሊካዊነት ባላደገባቸው፣ ጳጳሳዊያኑም ተጽዕኖ ማድረግን ያተርፉ ዘንድ የማግባባት ስልት እየተጠቀሙ ባሉባቸው ሃገራት፣ የጳጳሳዊውን ተዋረድ ከተሐድሶ አብያተ ክርስቲያናት በሚለዩአቸው አስተምህሮዎች ላይ እየጨመረ የመጣ ግድየለሽነት ይታያል፤ ‘ወሳኝ በሆኑት ነጥቦች ላይ፣ ሲባል የቆየውን ያህል የሰፋ ልዩነት የለንም፤ በእኛ በኩል የምናደርገው ጥቂት የአቋም ለውጥ (ከእኔ ይቅር ስምምነት) ከሮም ጋር የተሻለ መግባባት ላይ ያደርሰናል’ የሚለው አስተሳሰብ ሥር እየሰደደ ነው። እጅግ በውድ ዋጋ ለተገዛው የህሊና ነፃነት ፕሮቴስታንቶች ከፍተኛ ግምት የሚሰጡበት ጊዜ ነበር። ጳጳሳዊይነትን እንዲፀየፉ፣ ከሮም ጋር ለመስማማት መሻትም እግዚአብሔርን መካድ እንደሆነ አድርገው ለልጆቻቸው ያስተምሩ ነበር። አሁን የሚያንፀባርቋቸው አስተሳሰቦች ግን ከዚያ እንዴት የተለዩ ናቸው!GCAmh 407.1

    የጳጳሳዊነት ተሟጋቾች ቤተ ክርስቲያንዋ ያለአግባብ ስትወረፍ እንደቆየች ይናገራሉ። የፕሮቴስታንቱ ዓለምም ይህንን አባባል ወደ መቀበሉ አዘንብሏል። በድንቁርናና በጨለማ ዘመናት የአስተዳደርዋ መገለጫ በነበሩት ርኩሰቶችና ምክንያት-አልባ ድርጊቶች የአሁንዋን ቤተ ክርስቲያን መፈረጅ ልክ እንዳልሆነ ብዙዎች ያግባባሉ። ሰቅጣጭ የነበረው ጭካኔዋ የዘመኑ አረመኔነት ውጤት እንደነበር አድርገው ማስተባበያ በመስጠት፣ የዘመናዊው ስልጣኔ ተጽዕኖ አስተሳሰቦችዋን እንደቀየረው አድርገው አቤቱታ ያቀርባሉ።GCAmh 407.2

    እነዚህ ሰዎች በዚህ ጅንን ኃይል አማካኝነት ለስምንት መቶ ዓመታት ሰፍኖ የነበረውን የኃጢአት አይሰሬነት (ስህተት መሥራት አይቻለኝም ያለበትን) መጠይቅ ረስተውት ነውን? እንዲያውም ከመተው በራቀ ሁኔታ፣ ይህ መጠይቅ በአሥራ ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከበፊቱ በባሰ አዎንታዊ አቋም ተረጋግጧል። ሮም “ስህተት አልፈፀመችም፤ ስህተት መሥራትም ፈጽሞ አይቻላትም“(John L. von Mosheim, Institutes of Ecclesiastical Hystory, book 3, century ,part 2, chapter 2, section 9, note 17) በማለት አስረግጣ እየተናገረች ባለፉት ዘመናት አካሄድዋን ሲመሩት የነበሩትን መመሪያዎቿን እንዴት በይፋ ትተዋለች?GCAmh 407.3

    ጳጳሳዊት ቤተ ክርስቲያን ኃጢአት መሥራት አይቻለኝም የምትልበትን መጠይቅ ፈጽሞ አትተወውም። አስተምህሮዎችዋን አንቀበልም ያሉትን ስታሳድድ የፈፀመችው ሁሉ ትክክል እንደነበረ ታምናለች፤ እድሉ ቢገጥማት ያንኑ ድርጊትዋን እንደገና አትደግመውምን? እስቲ በዓለማዊ መንግሥታት የተቀመጠው ገደብ ይነሳ፣ ወደ ቀድሞው ኃይልዋም እንድትመለስ ትደረግ፣ የፈላጭ ቆራጭነትዋና የማሳደድ ተግባርዋ በፍጥነት ተመልሶ ይቀሰቀሳል።GCAmh 407.4

    በቅርብ የነበረ ፀኃፊ [Josiah Strong, D.D, በ “Our Country” ገጽ 46-48] የህሊና ነፃነትን በተመለከተ የጳጳሳዊው መዋቅር ስላለው አስተሳሰብ እንዲሁም ከመርሀ ግብሮችዋም ውጤታማነት የተነሳ በተለይ በአሜሪካ ላይ ስለተጋረጠው አደጋ ሲናገር፦GCAmh 407.5

    “በአሜሪካ ውስጥ ያለውን ካቶሊካዊነት በተመለከተ የሚንፀባረቀውን ማንኛውንም ፍራቻ ከጥላቻ ወይም ከቂልነት ጋር ሊያያይዙ የሚሞክሩ ብዙ ሰዎች አሉ። እንደነዚህ ያሉቱ ለነፃ ተቋማቶቻችን ተዋቃሚ የሆነ ወይም በእድገቱ ላይ አስፈሪ የሆነ፣ በሮማዊነት ባህርይም ሆነ አስተሳሰብ ውስጥ ምንም ነገር አያዩም። እስኪ መጀመሪያ ጥቂት የመንግሥታችንን መሰረታዊ መመሪያዎችን ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መመሪያዎች ጋር እናነፃጽር፦GCAmh 408.1

    “የአሜሪካ ህገ-መንግሥት ለህሊና ነፃነት ዋስትና ይሰጣል። ከዚህ የበለጠ ውድ የሆነ ወይም መሰረታዊ ነገር የለም። በኦገስት (ነሐሴ) 15፣1854 ዓ.ም በስፋት በሚሰራጨው ጥብቅ ደብዳቤ ሊቀ ጳጳስ ፒየስ 9ኛ እንዲህ አለ፦ ̔የህሊና ነፃነትን ደግፈው የሚነሱ ትርጉም አልባና ስህተት የሆኑ አስተምህሮዎች ወይም የእብደት ንግግሮች ማለት — ከሁሉም የባሱ ተባዮች፣ በአንድ መንግሥትም ሊፈሩ የሚገባቸው ተወዳዳሪ የሌላቸው የስህተት ወረርሽኞች ናቸ̕ው። ያው ራሱ ሊቀ ጳጳስ ታህሳስ 8፣ 1864 በፃፈው ደብዳቤ፦ የህሊና ነፃነትንና የኃይማኖት አምልኮ ነፃነትን የሚያረጋግጡትንና ̍ቤተ ክርስቲያንዋ ኃይል መጠቀም የለባትም ብለው አቋም የያዙትን ሁሉ̍ ገዘታቸው።”GCAmh 408.2

    “በአሜሪካ ሮም የምታሰማው የሰላም ቃና የልብ መለወጥን አያመለክትም። የመቻቻል መንፈስ የምታሳየው አቅም በምታጣበት ስፍራ ነው። ጳጳስ ኦ‘ኮነር ሲናገሩ፦ “የኃይማኖት ነፃነት ፀንቶ የሚዘልቀው ለካቶሊኩ ዓለም አደጋ ሳያስከትል ተቃራኒው ጎራ መካሄድ እስካቻለበት ድረስ ብቻ ነው” ብለዋል። የቅዱስ ሊውስ መሪ (ሊቀ) ጳጳስ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ኑፋቄና አለማመን ወንጀሎች ናቸው፤ የክርስቲያን አገራት በሆኑት ለምሳሌ በጣሊያንና በስፔን፣ ሁሉም ሕዝቦች ካቶሊክ በሆኑባቸውና የካቶሊክ እምነትም የምድሪቱ ሕግ አስፈላጊ አካል በሆነበት ሥፍራ፣ እንደሌላ ወንጀል ተደርገው ይቀጣሉ።”GCAmh 408.3

    “እያንዳንዱ ከሊቀ ጳጳሱ ቀጥሎ ያለ ቄስ(ካርዲናል)፣ መሪ ጳጳስ(አርክቢሾፕ) እና ጳጳስ(ቢሾፕ) የሚከተሉት ቃላት የተካተቱበት የታማኝነት መኃላን ለሊቀ ጳጳሱ ይፈጽማል፦ ̍ለጌታችን ለሊቀ ጳጳሡ ወይም ለተጠቀሱት ተተኪዎቹ አማፂ የሆኑ፣ መናፍቃንን፣ ከፋፋዮችን፣ አማጽያንን በተቻለኝ አቅም ሁሉ አሳድዳቸዋለሁ፣ እቃወማቸዋለሁ፡፡̍”-Josiah Strong, Our Country, ch. 5, pars. 2-4GCAmh 408.4

    በሮም ካቶሊክ ማሕበረ ኃይማኖት ውስጥ እውነተኛ ክርስቲያኖች መኖራቸው እርግጥ ነው። ማግኘት እንደቻሉት ብርሐን መጠን እግዚአብሔርን እያገለገሉ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዚያች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሉ። ወደ ቃሉ ይደርሱ ዘንድ አይፈቀድላቸውም፤ በመሆኑም እውነቱን አያውቁም። በሕያው ልባዊ አገልግሎትና በሚደጋገሙ የይስሙላ ታይታዎችና ስነስርዓቶች መካከል ያለውን ልዩነት ፈጽመው አይተው አያውቁም። በአሳሳችና በማያረካ እምነት ውስጥ የተማሩትን እነዚህን ሰዎች እግዚአብሔር በቸርነትና በለዘብታ ይመለከታቸዋል። በዙሪያቸው የተጠመጠመውን ጥቅጥቅ ጨለማ ደርምሶ የሚገባ የብርሐን ጮራ ይልክላቸዋል። በክርስቶስ ያለውን እውነት ይገልጥላቸዋል፤ ብዙዎችም ከሕዝቦቹ ጋር አብረው ይቆማሉ።GCAmh 408.5

    ነገር ግን የሮም ካቶሊክነት እንደ መዋቅር በቀድሞ ታሪክዋ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ አሁን ከክርስቶስ ወንጌል ጋር የተስማማ አይደለም። የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት በታላቅ ጽልመት ውስጥ ናቸው፤ ባይሆንማ ኖሮ የዘመኑን ምልክቶች ባስተዋሉ ነበር። በእቅድዋና በአሰራር ዘዴዎችዋ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ወሰን እጅግ ሰፊ ነው። ዓለምን እንደገና ለመቆጣጠር፣ ስደትን እንደገና ለማስጀመር እንዲሁም ፕሮቴስታንታዊይነት ያደረገውን ሁሉ ለመቀልበስ ለምታደርገው ኃይለኛና ቆራጥ ዝግጅት ተጽኖዋን ማስፋት፣ ጉልበትዋን ማሳደግ ትችል ዘንድ እያንዳንዱን መሳሪያ ጥቅም ላይ በማዋል ላይ ነች። ካቶሊካዊነት በሁሉም አቅጣጫ ሥር እየሰደደ ነው። [በመግለጫ ስር ማስታወሻ 10ን ተመልከቱ]። ፕሮቴስታንት በሆኑ አገራት አብያተ ክርስቲያኖቶችዋ እና መቅደሶችዋ እንዴት እየጨመሩ እንደሆነ እዩ። በፕሮቴስታንቶች በስፋት የሚዘወተሩትን በአሜሪካ እጅግ ተወዳጅ የሆኑትን ኮሌጆችዋንና የኃይማኖት ማሰልጠኞችዋን ተመልከቱ። የመንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ክንውኖች በእንግሊዝ ያለውን እድገትና ወደ ካቶሊክ ለመቀላቀል የሚደረጉ ተደጋጋሚ ክህደቶችን ተመልከቱ። ይህ ክስተት ለንፁሁ የወንጌል መመሪያዎች ዋጋ የሚሰጡትን ሁሉ ድንጋጤ ሊቀሰቅስ ይገባል።GCAmh 408.6

    ፕሮቴስታንቶች ጳጳሳዊነትን ይጎነትላሉ (ይነካካሉ)፣ ድጋፍም ያደርጋሉ፤ ጳጳሳዊያኑ የተገረሙባቸውና፣ ለማመን ያልቻሉዋቸውን የአቋም ማፈግፈጎችና አስታራቂ ሃሳቦች አቅራቢ ሆነዋል። ለትክክለኛው የሮማዊነት ባህርይና በስልጣን የበላይነትዋም ምክንያት ሊመጣ ለሚችለው፣ መስተዋል ላለበት አደጋ ሰዎች ዓይናቸውን እየከደኑ ናቸው። ሰብዓዊና ኃይማኖታዊ ነፃነት እጅግ አደገኛ የሆነውን ጠላት ግስጋሴ መግታት ይቻል ዘንድ ሰዎች መጎስጎስ አለባቸው።GCAmh 409.1

    የካቶሊክ ኃይማኖት የማይስብ፣ አምልኮውም የደነዘ፣ ትርጉመ ቢስ የሥርዓት ድግግሞሽ እንደሆነ አድርገው ብዙ ፕሮቴስታንቶች ያስባሉ። እዚህ ላይ ስህተት ይሰራሉ። ሮማዊነት በአታላይነት ላይ የተመሠረተ ቢሆንም ጥሬነትና ልፍስፍስ አስመሳይነት ግን አይደለም። የሮማ ቤተ ክርስቲያን ኃይማኖታዊ አገልግሎቱ ተወዳዳሪ የሌለው አስደናቂ ሥነ-ሥርዓት ነው። እጅግ የተዋበው ትዕይንትና የከበረ ስርዓቱ የሰዎችን ህዋሳት ያቅበጠብጣል፤ የምክንያትንና የንቃተ ህሊናን ድምፆች ፀጥ ያሰኛል። አይን ይማርካል፣ እፁብ ድንቅ አብያተ ክርስቲያናት፣ ማራኪና መስመሩን የጠበቀ አጀብ፣ የወርቅ መሰዊያዎች፣ በከበሩ ድንጋዮች የተጌጡ ቅዱስ ስፍራዎች፣ ምርጥ ስዕሎች እንዲሁም የሚያማምሩ ቅርፃ-ቅርፆች የውበትን ፍቅር ይኮረኩራሉ። ጆሮም እንዲሁ ይሳባል። መዚቃው ተወዳዳሪ አይገኝለትም። የጥልቅ ኖታ ባለቤት የሆነው መረዋ ኦርጋን ከብዙ ድምፆች ጋር ተዋህዶ በምጡቅ ሉሎችና ምሰሶ በቆመባቸው መስመር በሰሩ ግዙፍ ቤተ መቅደሶች ውስጥ ሲያስገመግም በግርምትና በታላቅ አክብሮት አዕምሮ ላይ አሻራ ሳያሳርፍ አይቀርም።GCAmh 409.2

    ይህ በኃጢአት ህመምተኛ ለሆነው ነፍስ መሻቶች ፌዝ እንጂ ሌላ የማይሆነው ውጫዊ ሽብርቅርቅ፣ ኩፈሳና ሥነ ሥርዓት፣ የውስጣዊ መቆሸሽ ማስረጃ ነው። አዎንታዊ ምስክርነት ለማግኘት የክርስቶስ ኃይማኖት እንደዚህ አይነቶቹ መስህቦች አያስፈልጉትም። ከመስቀሉ በሚያንፀባርቀው ብርሐን፣ ሌላ ማንኛውም ውጫዊ ማስጌጫ እውነተኛ ዋጋውን ሊያጎላው በማይችል አኳኋን፣ እውነተኛ ክርስትና እጅግ ንፁህና ውብ ሆኖ ይታያል። በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ያለው የዋህና ዝግተኛ መንፈስ፣ የቅድስና ውበት ነው [1ኛ ጴጥ 3÷4]።GCAmh 409.3

    የአቀራረብ ልቀት በእርግጥ የጠራና የምጡቅ አስተሳሰብ መግለጫ ነው ማለት አይደለም። የኪነ ጥበብ ከፍታ ያላቸው ንድፎች፣ ጥንቁቅ የምርጫ ንጥረት፣ ሁልጊዜ የሚኖሩት ዓለማዊና ፍትወታዊ በሆኑ አዕምሮዎች ውስጥ ነው። እነዚህ፣ ለነፍስ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች እንዲረሱ፣ ስለወደፊቱ ዘላለማዊው ሕይወት ያለው እይታ እንዲጠፋ፣ ኃይሉ ገደብ ከሌለው ረዳታቸው ገለል እንዲሉና ለዚህ ዓለም ብቻ እንዲኖሩ ሰዎችን ለመምራት ሁልጊዜ በሰይጣን የሚተገበሩ ናቸው።GCAmh 410.1

    የውጫዊ ኃይማኖት ያልተለወጠውን ልብ ይማርካል። የካቶሊክ አምልኮ ታይታና ስነ-ሥርዓት ብዙዎች የሚታለሉበት፣ አሳሳች፣ አስማታዊ ኃይል ያለው ነው። የሮማ ቤተ ክርስቲያን ልክ የሰማይ ደጃፍ እንደሆነች አድርገው ወደ መመልከት ይለወጣሉ። ከእርስዋ ተጽዕኖ በእርግጥ የሚተርፉት በእውነት መሰረት ላይ አጠንክረው እግራቸውን የተከሉ፣ ልባቸውም በእግዚአብሔር መንፈስ የተለወጠ ብቻ ናቸው። በተግባር በመለማመድ የሚመጣ የክርስቶስ እውቀት የሌላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ እነርሱ የአምልኮ መልክ ያለውን ሆኖም ኃይል-አልባ የሆነውን የቅድስና ቁመና እንዲቀበሉ ይመራሉ። እልፍ አዕላፋት የሚመኙት እንዲህ አይነቱን ኃይማኖት ነው።GCAmh 410.2

    ቤተ ክርስቲያንዋ አለኝ የምትለው ኃጢአትን የማስተሰርየት መብት ሮማዊው ኃጢአት ይሰራ ዘንድ ነጻነት እንዲሰማው ያደርጋል። ያለ እርስዋ ክንውን የኃጢአት ይቅርታ የማይሰጥበት የንስሐ ሥርዓትዋም ለክፋት ፈቃድ የሚሰጥ ነው። በወደቀው ሰው ፊት ተንበርክኮ የልቡን ምስጢራዊ ሃሳቦችና ምናቦች በንስሐ የሚያቀርብ እርሱ ሰብአዊ ማንነቱን እያዋረደ፣ እያንዳንዷን የከበረች የነፍስ እሳቤውን እያቆረቆዘ ነው። ስህተት ለሚፈጽም፣ ኃጢአተኛና ሟች ለሆነ፣ አብዛኛውን ጊዜም በወይንና በዝሙት ለተበላሸ ካህን(ቄስ) በሕይወቱ የፈፀማቸውን ኃጢአቶች ዘክዝኮ በማቅረቡ፣ የባህርይ ደረጃው ዝቅ ይላል፤ በመዘዙም ይበከላል። ለእግዚአብሔር ያለው አስተሳሰብ በወደቀው የሰው ዘር አምሳያ ልክ ያሽቆለቁላል፤ ምክንያቱም ቄሱ የክርስቶስ እንደራሴ ሆኖ ቆሟልና! ይህ አዋራጅ የሰው ለሰው የኃጢአት ኑዛዜ ዓለምን እያበላሸ ያለው፣ ለመጨረሻው ውድመትም ገጣሚ እንዲሆን እያዘጋጀ ያለው አብዛኛው ክፋት የሚፈልቅበት የተደበቀው ምንጭ ነው። ሆኖም ምኞቱን ማርካት ለሚያስደስተው ለእርሱ ግን ነፍሱን ለእግዚአብሔር ከሚገልጥ ይልቅ የንስሐ ቅጣት (ሰዎች ከተናዘዙ በኋላ ይቅር እንዲባሉ መፈፀም ያለባቸው ተግባር) ማከናወን ለሰው ተፈጥሮ የበለጠ የሚጥም ነው። ስጋዊ ፍላጎቶችን ከመስቀል ይልቅ በማቅ፣ በሳማና በሚፈትግ ሰንሰለት አካልን ማዋረድ ይቀላል። ስጋዊ ልብ፣ ለክርስቶስ ቀንበር ከማጎንበስ ይልቅ ሌላ ከባድ ቀንበር ለመሸም ፈቃደኛ ነው።GCAmh 410.3

    በክርስቶስ የመጀመሪያ ምፅዓት ጊዜ በነበረችው የአይሁድ ቤተ ክርስቲያንና በሮም ቤተ ክርስቲያን አስደናቂ ተመሳሳይነት አለ። አይሁዳዊያን በድብቅ በእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ሕግ መርህ ላይ እየተረማመዱበት ሳለ መታዘዝን የሚያሳምምና አስቸጋሪ ያደረገውን ወግ ልማድና የማያፈናፍን ግዴታን ጭነው ውጫዊ መመሪያዎቹን ውልፍት ሳይሉ ይጠብቁ ነበር። አይሁዳዊያን ሕጉን እንደሚያከብሩ ይናገሩ እንደነበረ ሁሉ ሮማዊያንም መስቀሉን እንደሚያከብሩ ይናገራሉ። የክርስቶስ መሰቃየት ምልክት የሆኑትን ያከብራሉ፤ እነዚህ ተምሳሌቶች የሚወክሉትን ጌታን ግን በሕይወታቸው ይክዱታል።GCAmh 410.4

    ጳጳሳዊያኑ በአብያተ ክርስቲያናቶቻቸው፣ በመሰዊያዎቻቸውና በአልባሳቶቻቸው ላይ መስቀሎችን ያደርጋሉ። የመስቀሉ መለያ የትም ቦታ ይታያል። በሁሉም ስፍራ ውጫዊ የሆነ ክብርና ከፍ ከፍ መደረግ ይከናወንለታል። የክርስቶስ ትምህርቶች ግን ስሜት በማይሰጥ ወግ ልማድ፣ የሐሰት ትርጓሜዎችና ፍትልክ በማያስብሉ ግዴታዎች ቁልል ስር ተቀብረዋል። አክራሪ አይሁዳዊያንን በተመለከተ አዳኙ የተናገራቸው ቃላት በሮማዊያን መሪዎች ላይ በበለጠ ጥንካሬ ተግባራዊ የሚሆኑ ናቸው፦ “ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትክሻ ይጭናሉ፤ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም” [ማቴ 23÷4]። የቤተ ክርስቲያንዋ ሹማምንት በቅንጦትና በስሜት እርካታ እየኖሩ ሳለ ጥንቁቅ ነፍሳት ግን የተበሳጨን አምላክ ቁጣ በመፍራት በማያባራ ሽብር ውስጥ እንዲኖሩ ይደረጋሉ።GCAmh 411.1

    የስዕሎችና (የምስሎችና) የጥንታዊ ቁሶች አምልኮ፣ ቅዱሳንን መለመን እንዲሁም የሊቀ ጳጳሱ ከፍ ከፍ መደረግ የሰዎችን አዕምሮ ከእግዚአብሔርና ከልጁ ነጥሎ ለመሳብ የተዘጋጁ የሰይጣን መሳሪያዎች ናቸው። ውድመታቸውን እውን ለማድረግም ድነት ከሚያገኙበት ከብቸኛው አምላክ ትኩረታቸውን እንዲያነሱ ይጥራል። “እላንት ደካሞች ሸክናችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ” [ማቴ 11÷28] የሚለውን እርሱን ወደሚተካ ማንኛውም ነገር ይመራቸዋል።GCAmh 411.2

    የእግዚአብሔርን ባህርይ በሐሰት አጣሞ ማቅረብ፣ የኃጢአትን ምንነት ማሳሳት፣ እንዲሁም በታላቁ ተቃርኖ ውስጥ አደጋ የተጋረጠባቸውን አንኳር ጉዳዮች መልክ መቀየር የሰይጣን ያላሰለሰ ጥረት ነው። አደናጋሪ እውነት መሳይ ማታለያው ለመለኮታዊ ሕግ ያለውን ግዴታ በመቀነስ ሰዎች ኃጢአት እንዲሰሩ ፈቃድ ይሰጣቸዋል። በተመሳሳይ ጊዜም፣ በፍቅር ፈንታ በፍርሃትና በጥላቻ ይመለከቱት ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ያላቸውን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያጎለብቱ ያደርጋቸዋል። በራሱ ውስጥ ያለው አረመኔአዊ ባህርይው የፈጣሪ እንደሆነ ተደርጎ ይቀርባል። የኃይማኖት መዋቅሮች አካል ይደረግና በአምልኮ ዘይቤዎች ይተነተናል። በዚህም ሁኔታ የሰዎች አዕምሮ ይታወራል፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ጦርነት ይገጥሙ ዘንድ ሰይጣን በወኪልነት ይቀጥራቸዋል። የመለኮታዊ ባህርያትን አጣሞ ከመረዳት የተነሳ፣ አሕዛብ፣ የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ሰውን መስዋዕት ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ እንዲያምኑ ተደርገው ነበር፤ በጣዖት አምላኪነት የተለያዩ ገጽታዎች ስር አሰቃቂ ጭካኔዎች እንዲፈፀሙ ሆነዋል። ሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የጣዖት አምልኮንና የክርስትናን ገጽታዎች በማጣመር፣ ጣዖት አምላኪነት እንደሚያደርገው ሁሉ የእግዚአብሔርን ባህርይ አጣሞ በማቅረብ፣ በጭካኔያቸውና በዘግናኝነታቸው ያልተናነሱ ድርጊቶችን ወደመፈፀም ዞራለች። ሮም ልዕለ ኃያል በነበረችበት ዘመናት፣ ለአስተምህሮዎችዋ ተቀባይነትን ለማስግኘት የምታስገድድበት የማሰቃያ መሳሪያዎች ነበሯት። ለመጠይቅዋ እጅ ለማይሰጡት ደግሞ የማቃጠያ እንጨት ተተክሎ ነበር። በፍርድ ቀን ሲገለጥ ከሚታወቀው በቀር ፈጽሞ ሊገመቱ የማይችሉ ፍጅቶች ተፈጽመዋል። ተጠቂው ሕይወቱ እንዳያልፍ ተደርጎ ተመን የሌለው ስቃይ እንዲደርስበት ለማድረግ የቤተ ክርስቲያን ሹማምንት፣ በአለቃቸው በሰይጣን ስር ሆነው፣ የስቃይ ዜዴዎችን በጥናት ይፈጥሩ ነበር። የሰብአዊ ፍጡር የጽናት ዲካ እስኪነካ፣ ተፈጥሮ ትግልዋን እስክታቆም፣ ተሰቃዩ ሞትን እንደጣፋጭ ነፃነት በደስታ እስኪቀበለው ድረስ ይህ ዘግናኝ ሂደት ይደጋገም ነበር።GCAmh 411.3

    የሮም ተቃዋሚዎች ዕጣ ፈንታ ይህን ይመስል ነበር። መዋቅርዋን ለሚደግፉ ስቅይት የሚያስከትሉ፣ ቅጥ ያጣ የረሃብ እንዲሁም ምቾት የሚያሳጣ አካላዊ ጉዳት የሚያደርሱ ስነ ስርዓቶች በእያንዳንዱ፣ መታሰብ በሚችለው መንገድ ሁሉ የተቀረጹ፣ ልብን የሚያሳምሙ የተለያዩ አይነት ስርዓቶች ነበሩአት። የሰማይን ሞገስ ለማትረፍ ሲሉ፣ ንስሐ ገቢዎች የተፈጥሮን ሕግጋት በመጣስ የእግዚአብሔርን ሕግጋት ጥሰዋል። የሰውን ልጅ ምድራዊ ጉዞ ለመባረክና በደስታ ለመሙላት የዘረጋውን ገመድ አንድ በአንድ እንዲበጥሱ ተማሩ። ተፈጥሮአዊ ስሜቶቻቸውን በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ፣ ለእግዚአብሔር አፀያፊ እንደሆኑ በመቁጠር፣ ለመሰሎቻቸው የሚያንፀባርቁትን እያንዳንዱን ሐሳብና የርኅራኄ ስሜት በኃይል ለመጨቆን በከንቱ ድካም ሲጥሩ ሕይወታቸውን የከሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቂዎችን [አስክሬን] የቤተ ክርስቲያንዋ ታዛ ይዟል።GCAmh 412.1

    ስለ እግዚአብሔር ሰምተው በማያውቁት መካከል ሳይሆን፣ በክርስቲያኑ ዓለም እምብርትና ዳርቻ ሁሉ ለብዙ መቶ ዓመታት ሲገለጽ የነበረውን፣ የማያወላውለውን የሰይጣን ጭካኔ ለመገንዘብ የምንሻ ከሆነ፣ የሮማዊነትን ታሪክ መመልከት ብቻ ይበቃናል። በዚህ ግዙፍ የማጭበርበሪያ መዋቅር አማካኝነት፣ የክፋት ልዑል፣ ውርደት ለእግዚአብሔር፣ ጉስቁልና ለሰው ልጅ የማምጣትን አላማውን ያሳካል። በተሳካ ሁኔታ ራሱን እንዴት እንደሚደብቅና በቤተ ክርስቲያን መሪዎች አማካኝነት ሥራውን እንደሚያከናውን ስናይ ለመጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ ጥላቻ ለምን እንዳለው በተሻለ ሁኔታ እንረዳለን። ያ መጽሐፍ ከተነበበ የእግዚአብሔር ምሕረትና ፍቅር ይገለጣል፤ እነዚህን ከባድ ጭነቶች በሰው ላይ እንደማይጭንም ይታያል። እርሱ የሚጠይቀው የተሰበረና የሚፀፀት ልብ፣ ራሱን ዝቅ ያደረገና ታዛዥ መንፈስን ብቻ ነው።GCAmh 412.2

    ወንዶችና ሴቶች ለሰማይ ብቁ ይሆኑ ዘንድ በገዳማት ውስጥ ራሳቸውን ዘግተው ይቀመጡ ዘንድ ክርስቶስ በሕይወቱ ምሳሌ አልሰጠም። ፍቅርና ርኅራኄ መታመቅ እንዳለባቸው ፈጽሞ አላስተማረም። የአዳኙ ልብ በፍቅር ተትረፍርፎ ይፈስ ነበር። ሰው ለግብረ ገብነት ፍጽምና እየቀረበ በሄደ መጠን፣ የስሜት ኃይላቱም የበለጠ እየተሳሉ፣ ለኃጢአት ያለው መረዳት እየበረታ፣ ለተጎዱትም ያለው ርኅራኄ ጥልቅ እየሆነ ይሄዳል። ሊቀ ጳጳሱ የክርስቶስ ወኪል እንደሆነ ይናገራል፤ ባህርይው ከአዳኛችን ጋር ሲነፃፀር ግን እንዴት ነው? የሰማይ ንጉሥ እንደሆነ አድርገው ስላላከበሩት ክርስቶስ ሰዎችን ለእስር በመዳረግ፣ እጃቸውና እግራቸው ተወጥሮ በመታሰር ወደሚሰቃዩበት ሥፍራ በመስደድ የሚታወቅበት አንዳች አጋጣሚ ነበርን? ያልተቀበሉትን ሞት ሲፈርድባቸው ድምፁ ተሰምቷልን? በሳምራዊ መንደር ሰዎች ዘንድ ሲፌዝበት ሐዋርያው ዮሐንስ በቁጣ ተሞልቶ “ጌታ ሆይ ኤልያስ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን?” ብሎ በጠየቀ ጊዜ የሱስ ደቀመዛሙሩን በሀዘኔታ እየተመለከተ “የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም” በማለት ጨካኝ መንፈሱን ገሰፀ [ሉቃስ 9÷54፣56]። በክርስቶስ ዘንድ የተንፀባረቀው መንፈስ፣ ወኪሉ ነኝ ከሚለው ጋር ሲነፃፀር ምን ያህል የተለየ ነው።GCAmh 412.3

    የአሰቃቂ ጭካኔዋን መዝገብ በይቅርታ በመሸፈን ዛሬ የሮም ቤተ ክርስቲያን መልካም ገጽታ ለዓለም አቅርባለች። በክርስቶስ መሰል አልባሳት ራስዋን ጀቡናለች፤ ሆኖም አልተለወጠችም። በቀድሞ ዘመናት የነበረው እያንዳንዱ የጳጳሳዊ ሥርዓት መርህ ዛሬም አለ። እጅግ ጥቅጥቅ ባለው የጨለማ ዘመናት የተቀረፁት አስተምህሮዎች አሁንም ድረስ እንደተያዙ ናቸው። ማናቸውም ራሳቸውን አያታልሉ። አሁን ፕሮቴስታንቶች ከፍ ከፍ ለማድረግ በተጠንቀቅ የተዘጋጁለት ጳጳሳዊ ሥርዓት፣ በተሐድሶ ዘመን ኃጢአትዋን ያጋልጡ ዘንድ የእግዚአብሔር ሰዎች ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ይቆሙበት በነበረው ጊዜ ዓለምን ስትገዛ የነበረችው ናት። በነገሥታትና በልዑላን ላይ ጌታ ያደረጋትን የኩራትና የትዕቢት አስተሳሰብ አሁንም እንደያዘች ናት፤ ለእግዚአብሔር ብቻ የተገባውንም የእኔ ያለች ናት። አሁን ያላት የጭካኔና የማንአለብኝ ባይነት መንፈስ፣ የፍጡራንን ነፃነት ስትፈጭና የኃያሉን አምላክ ቅዱሳን ስታርድ ከነበረችበት ጊዜ ያነሰ አይደለም።GCAmh 412.4

    ጳጳሳዊ ሥርዓት፣ ምን እንደምትሆን ትንቢት ያወጀው፣ የኋለኛው ዘመን ክህደት ነው [2ኛ ተሰሎ 2÷3፣4]። አላማዋን በተሻለ መንገድ የሚያሳካላትን ባህርይ መላበስ የመርሃ ግብርዋ አካል ነው፤ በሚለዋወጠው የእስስት ገጽታ ስር ግን የማይለወጠውን የእባቡን መርዝ ደብቃለች። “እምነትንና ቃልኪዳንን ለመናፍቃን የመጠበቅ ግዴታ የለብንም” በማለት ታውጃለች። የሺህ አመት መዝገቡ በቅዱሳን ደም የተፃፈው ይህ ኃይል የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አካል ተደርጎ አሁን እውቅና ይሰጠው?GCAmh 413.1

    ከቀድሞው ዘመን ይልቅ ካቶሊካዊነት ከፕሮቴስታንትነት ጋር ያለው ልዩነት አሁን እንደጠበበ ተደርጎ በፕሮቴስታንት አገራት የሚቀርበው አቤቱታ ያለ ምክንያት አይደለም። ለውጥ አለ፤ ለውጡ ግን በጳጳሳዊ ሥርዓት ውስጥ አይደለም። ካቶሊካዊነት በእርግጥ አሁን ያለውን አብዛኛውን ፕሮቴስታንትነት ይመስለዋል። ምክንያቱም ከተሐድሶ መሪዎች ዘመናት አንስቶ እስካሁን ድረስ ፕሮቴስታንትነት እጅግ በስፋት እያሽቆለቆለ ስለሆነ ነው።GCAmh 413.2

    የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት የዓለምን ሞገስ ለማትረፍ ሲጥሩ ሀሰተኛ ፍቅር ዓይናቸውን አውሮታል። ስለ ሁሉም ክፋት መልካም ማሰብ ጥሩ ነው ብሎ ማመን ትክክል እንደሆነ አድርጎ ከመቀበል በቀር ሌላ አያዩም፤ አይቀሬ ውጤቱም፣ በስተመጨረሻ፣ መልካም ነገር ሁሉ ክፋት እንደሆነ ያምናሉ። አንድ ጊዜ ለቅዱሳን የተሰጠውን እምነት ለመጠበቅ በመቆም ፈንታ፣ በፊት እንደነበረው ሁሉ፣ አሁንም በሮም ላይ ስላላቸው የተሳሳተ ፍረጃቸው ይቅርታ እየጠየቁ፣ ሲያሳዩት ለነበረው ጥላቻቸው ይቅርታዋን እየለመኑዋት ናቸው።GCAmh 413.3

    ብዛት ያላቸው መደቦች፣ ሮማዊነትን በአዎንታ የማይመለከቱ ጭምር፣ ከኃይልዋና ከተጽዕኖዋ የሚያስተውሉት አደጋ እጅግ አናሳ ነው። በመካከለኛው ዘመን ተንሰራፍቶ የነበረው የእውቀትና የግብረ-ገብነት ጽልመት፣ አስተምህሮዎችዋ፣ አጉል እምነቶችዋና ጭቆናዎችዋ እንዲስፋፉ የረዳት እንደነበረ ብዙዎች በመናገር፣ የስልጡን ዘመናት የተሻለ የማሰብ ችሎታ፣ ከሞላ ጎደል ያለው የእውቀት መስፋፋት፣ እየጨመረ የሄደው ኃይማኖታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው የነፃ አስተሳሰብ ዝንባሌዎች፣ የአለመቻቻልንና የፈላጭ ቆራጭነትን እንደገና የማንሰራራት አደጋ ይከለክላሉ ብለው ያምናሉ። እንደዚህ አይነቶቹ ሁኔታዎች፣ በዚህ ማስተዋል በተንሰራፋበት ዘመን ይኖራል ብሎ ማሰብ በራሱ መሳለቂያ ሆኖአል። አዕምሯዊ፣ ግብረ-ገባዊና ኃይማኖታዊ ታላቅ ብርሐን በዚህ ትውልድ ላይ እያንፀባረቀ እንዳለ እሙን ነው። መታወስ ያለበት ነገር ግን የሚሰጠው ብርሐን በጨመረ ቁጥር፣ በሚያጣምሙት ወይም በማይቀበሉት ዘንድ ያለው ጽልመትም በዚያው ልክ እንደሚጨምር ነው።GCAmh 413.4

    በፀሎት የተደገፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለፕሮቴስታንቶቹ ትክክለኛውን የጳጳሳዊውን ሥርዓት ባህርይ በመግለጥ እንዲፀየፉትና እንዲተውት ያደርጋቸው ነበር፤ ነገር ግን ብዙዎች በራሳቸው ጥበብ ተመክተው፣ ወደ እውነት ይመሩ ዘንድ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው እግዚአብሔርን የመፈለግ አስፈላጊነቱ አይታያቸውም። በመንፈሳዊው እውቀት የበለፀግን ነን ብለው ቢኮሩም የመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ የእግዚአብሔር ኃይል እውቀት ገልቱ ናቸው። ንቃተ ህሊናቸውን ዝም የሚያስብሉበት አንዳች ነገርማ ይኖራቸዋል፤ በመንፈሳዊነት ፈጽሞ አናሳ የሆነውንና የተዋረደውን ይሻሉ። የሚመኙት ነገር፣ እርሱን የማስታወሻ ዘዴ እንደሆነ ተደርጎ የሚያልፍ፣ ሆኖም እግዚአብሔርን እንዲረሱ የሚያደርጋቸውን ዘዴ ነው። ጳጳሳዊው ሥርዓት እነዚህን ፍላጎቶች ሁሉ ለማሟላት በደንብ የተዘጋጀ ነው። ዓለምን በሙሉ ሊጠቀልልም ምንም ባልቀረው ሁኔታ ለሰው ዘር ሁለት መደቦች ዝግጁ ሆኖአል — በራሳቸው መልካም ሥራ ለሚድኑትና በኃጢአት ውስጥ እያሉ ለሚድኑ። የኃይሉ ምስጢር ይህ ነው።GCAmh 414.1

    ታላቅ የሆነ የአዕምሮአዊ ጽልመት ጊዜ ለጳጳሳዊው ሥርዓት ስኬት ተስማሚ መሆኑ ታይቷል። ታላቅ የእውቀት ብርሐን ዘመንም በእኩል ለጳጳሳዊው ሥርዓት ውጤታማነት ተስማሚ መሆኑ በተግባር የሚታይ ይሆናል። ባለፉት ዘመናት ሰዎች ያለ እግዚአብሔር ቃልና ያለ እውነት እውቀት በነበሩበት ጊዜ አይኖቻቸው ተሸፍነውባቸው ነበር፤ ለእግሮቻቸው የተዘረጉትን መረቦች ባለማየታቸውም በሺ የሚቆጠሩ በወጥመድ ውስጥ ወድቀዋል። በዚህ ትውልድ ደግሞ “በስህተት ሳይንስ ተብሎ በሚጠራው” የሰው ልጅ ግምታዊ መላምት ነፀብራቅ ምክንያት ዓይናቸው የሚታወር ብዙዎች አሉ፤ ልክ ዓይናቸው በጥምጣም እንደታሰረ ሁሉ መረቡን ሳያስተውሉ ሰተት ብለው ይገባሉ። እግዚአብሔር ያቀደው የሰው ልጅ የአስተሳሰብ የእውቀት ኃይላት ከፈጣሪው የተሰጠው ስጦታ ተደርገው እንዲታዩ፣ ለእውነትና ለጽድቅም አገልግሎት እንዲውሉ ነበር፤ ነገር ግን ኩራትና ጠንካራ መሻት ሲበረታቱ፣ ሰዎች የራሳቸውን ጽንሰ ሐሳቦች ከእግዚአብሔር ቃል በላይ ሲያደርጉ፣ እውቀት ከድንቁርና የባሰ ጉዳት ያመጣል። ስለዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን እምነት የሚያጣጥለው የአሥራ ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሐሰት ሳይንስ፣ ከሚያስደስቱ ቁመናዎቹ ጋር፣ እውቀትን በመደበቅ በጨለማው ዘመን ለግዙፍነቱ በር እንደከፈተ ሁሉ፣ ወደፊትም ጳጳሳዊው ሥርዓት ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ መንገድ ለመጥረግ ውጤታማ መሆኑ ይረጋገጣል።GCAmh 414.2

    አሁን በአሜሪካ እየተካሄደ ያለው ለቤተ ክርስቲያን ተቋማትና ለአገልግሎቶችዋ የመንግሥትን ድጋፍ ለማግኘት በሚደረገው እንቅስቃሴ፣ ፕሮቴስታንቶች የጳጳሳዊውን ዱካ እየተከተሉ ናቸው [በመግለጫ ስር ማስታወሻ 11ን ይመልከቱ]። አይደለም፣ የበለጠ እንጂ፣ በፕሮቴስታንት አሜሪካ ውስጥ፣ በጥንታዊው ዓለም አጥታ የነበረውን የበላይነት እንደገና ለመጨበጥ እንድትችል ለጳጳሳዊው ሥርዓት በር እየከፈቱ ነው። ይህንን እንቅስቃሴ በተለየ ሁኔታ አስፈላጊ የሚያደርገው ደግሞ እየተንሸራሸረ ያለው አብይ አላማ ከሮም ከራስዋ የመነጨው ባህል፣ የስልጣንዋ ምልክት እንደሆነ የምትናገርለት — የእሁድን መከበር ግዴታ ማድረግ መሆኑ ነው። በፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት እየሰረገ ያለው፣ ጳጳሳዊ ሥርዓት ከእነርሱ በፊት ሲያደርገው የነበረውን፣ እሁድን ከፍ ከፍ የማድረግ ተመሳሳይ ተግባር እንዲያከናውኑ የሚመራቸው፣ ከዓለማዊ ወግና ልማድ ጋር የሚስማማው፣ የፍጡራንን ባህል ከእግዚአብሔር ትእዛዛት በላይ የሚያከብረው፣ የጳጳሳዊው ሥርዓት መንፈስ ነው።GCAmh 414.3

    በቅርብ የሚመጣውን ፉክክር ለማሳካት የሚቀጠሩትን ልዑካን አንባቢው ለመረዳት ከፈለገ፣ ሮም ተመሳሳይ አላማዋን ለማሳካት ባለፉት ዘመናት ሥራ ላይ ያዋለቻቸውን ዘዴዎች መዝገብ ብቻ ማገላበጥ ይበቃዋል። ጳጳሳዊያኑና ፕሮቴስታንቶች ተባብረው አስተምህሮዎቻቸውን የሚቃወሙትን ምን ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ ማወቅ ከፈለገ፣ ሮም በሰንበትና በቆሙለት ሰዎች ላይ ያንፀባረቀችውን መንፈስ ይመልከት።GCAmh 415.1

    በመንግሥት ኃይል በተደገፉ፣ በንጉሣዊ ይፋዊ አዋጆች፣ በጠቅላይ ጉባኤዎችና በቤተ ክርስቲያን ሕግጋት አማካኝነት ነበር የጣዖት አምልኮ ክብረ በዓላት በክርስቲያኑ ዓለም የክብር ደረጃ ሊቆናጠጡ የቻሉት። የእሁድን አክብሮት ግዴታ ያደረገው የመጀመሪያው ሕዝባዊ አካሄድ በቆስጠንጢኖስ የወጣው ሕግ ነበር [ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ321 ዓ.ም]። ይህ አዋጅ የከተማ ነዋሪዎች “በክቡሩ የፀሐይ ቀን” እንዲያርፉ ያደረገ ሲሆን በገጠር የሚኖሩ ግን የእርሻ ሥራቸውን ማከናወናቸውን እንዲቀጥሉ የሚፈቅድ ነበር። ይህ የአሕዛብ ተቋም ቢሆንም፣ ክርስትናን ለይስሙላ ከተቀበለ በኋላ በንጉሠ ነገሥታቱ አስገዳጅነት ተግባራዊ የተደረገ ነበር።GCAmh 415.2

    ንጉሣዊው ትዕዛዝ የመለኮታዊውን ስልጣን ለመተካት በቂ አለመሆኑ ሲታይ፣ የልዑላንን ይሁንታ ለማግኘት ሲጥር የነበረው፣ የቆስጠንጢኖስ ልዩ ወዳጅና አወዳሽ የነበረው ጳጳስ ኢውሰቢየስ፣ ክርስቶስ ሰንበትን ከቅዳሜ ወደ እሁድ አሸጋግሮታል የሚለውን ሀሳብ አቀጣጠለው። አዲሱን አስተምህሮ የሚደግፍ አንድ ስንኳ ማረጋገጫ ከመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት ማቅረብ አልተቻለም። ኢውሰቢየስ ሳያስበው ሐሰት ለመሆኑ እውቅና በመስጠት ወደ ትክክለኞቹ የለውጡ ደራሲያን ይጠቁማል። “ሁሉም ነገሮች” አለ፣ “በሰንበት መከናወን ያለባቸውን ማናቸውንም ነገሮች ወደ ጌታ ቀን አዛውረናቸዋል።”- Robert Cox, Sabbath Laws and Sabbath Duties, page 538። ነገር ግን የእሁድ ክርክር፣ መሠረት ያልነበረው ቢሆንም፣ በእግዚአብሔር ሰንበት ላይ ይረማመዱ ዘንድ ለሰዎች የልብ ልብ በመስጠት አገልግሎአል። በዓለም ይከበሩ ዘንድ መሻት የነበራቸው ሁሉ ዝነኛውን በዓል ተቀበሉት።GCAmh 415.3

    ጳጳሳዊ ሥርዓት መሠረቱ እየተጠናከረ ሲሄድ እሁድን ከፍ ከፍ የማድረጉ ሥራ ቀጠለ። ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን በማይሄዱበት ጊዜ የእርሻ ሥራ ያካናውኑ ስለነበረ፣ አሁንም ሰባተኛው ቀን ሰንበት እንደሆነ ይታመን ነበር፤ ለውጡ ግን በቀጣይነት ተግባራዊ ተደረገ። በኃይማኖታዊ ኃላፊነት ያሉ እነርሱ በእሁድ ቀን በማንኛውም ሕዝባዊ/መንግሥታዊ አለመግባባት ፍርድ እንዳይሰጡ ተከለከሉ። ከትንሽ ጊዜ በኋላ በየትኛውም ደረጃ የነበሩ ሰዎች ከተለመደው ሥራቸው እንዲታቀቡ ታዘዙ፤ በነፃ ሰዎች ላይ ቅጣት በመጣል፣ በባርያዎች ላይ ደግሞ ግርፋት በማስተላለፍ የእሁድን መከበር ተግባራዊ አደረጉት። በኋላም ኃብታም ሰዎች የኃብታቸውን ግማሽ በመቀማት እንዲቀጡ፣ ይህም ሆኖ አሁንም ባርያዎች እንዲደረጉ ታወጀ። ዝቅተኛ መደቦች ደግሞ በዘላለም መገለል ይቀጡ ነበር።GCAmh 415.4

    ተዓምራትም እንዲፈጸሙ መጠይቅ ይቀርብ ነበር። ከአስገራሚ ክስተቶች መካከል፣ አንድ በእሁድ ቀን ማሳውን ሲያርስ የነበረ ገበሬ ማረሻውን በብረት እያፀዳ እያለ፣ ብረቱ ከእጁ ጋር በኃይል ተጣብቆበት፣ “ለከፍተኛ ስቃይና ኃፍረት ዳርጎት”-Francis West, Historical and Practical Discourse on the Lords’s Day, page 174። ለሁለት አመት በሄደበት ሁሉ ተሸክሞት ይዞር ነበር የሚለው ይገኝበታል።GCAmh 415.5

    በኋላም የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ቄሱ እሁድን የማያከብሩትን እንዲገስጽ፣ በራሳቸውና በጎረቤቶቻቸውም ላይ እልቂት እንዳይመጣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሂደው ፀሎት እንዲያደርጉ እንዲመክራቸው የሚያደርግ ትዕዛዝ ሊቀ ጳጳሱ ሰጠ። በፕሮቴስታንቶች ጭምር፣ በስፋት ጥቅም ላይ ከመዋሉ የተነሳ፣ በእሁድ ቀን ሰዎች፣ ሥራ ላይ እያሉ በመብረቅ የሚመቱበት ምክንያት [እሁድ] ሰንበት ቢሆን ነው የሚል መከራከሪያ በቤተ ክርስቲያን መማክርት በኩል ቀረበ። “ይህንን ቀን ችላ በማለታቸው የእግዚአብሔር አለመደሰት እንዴት ታላቅ እንደሆነ ግልጽ ነው” አሉ ሹማምንቱ። ከዚያም ቀሳውስት፣ አገልጋዮች፣ ነገሥታት፣ ልዑላንና ሁሉም ታማኝ ሕዝቦች “ቀኑ ወደነበረበት ክብሩ እንዲመለስ ጥንቃቄና ጥረት እንዲያደርጉ ለክርስትና ጥቅም ሲባልም በሚመጣው ዘመን ሁሉ በመሰጠት እንዲከበር ተማጽዕኖ ቀረበ።”-Thomas Morer, Discourse in Six Dialogues on the Name, Notion, and Observation of the Lord’s Day, page 271።GCAmh 416.1

    የመማክርት (የጉባያት) አዋጆች በቂ አለመሆናቸው ሲታይ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ በሕዝቡ ልብ ላይ ፍርሃት በመልቀቅ በእሁድ ከመሥራት እንዲያቆሙ የሚያስገድዳቸውን ይፋዊ አዋጆች እንዲያወጡ ተጠየቁ። በሮም በተካሄደ የጳጳሳት ሸንጎ ከአሁን በፊት የተላለፉት ውሳኔዎች በበለጠ ኃይልና ክብደት እንደገና ተረጋገጡ። ከኃይማኖታዊ ሕጉ ጋርም ተዋህደው በሁሉም የክርስቲያኑ ዓለም በሚባል ደረጃ በመንግሥታዊ ባለስልጣናት አማካኝነት ተግባራዊ ተደረጉ። (Heylyn, History of the Sabbath, pt. 2, ch. 5, sec. 7ን ይመልከቱ)።GCAmh 416.2

    ይህም ሁሉ ተደርጎ ግን የእሁድ መከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስልጣን የሌለው መሆኑ ቀላል የሚባል ኃፍረት አላከናነባቸውም። “ሰባተኛው ቀን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው” የሚለውን የያህዌን ግልጽ አዋጅ ወደ ጎን ለማድረግ፣ የፀሐይ ቀንንም ለማክበር፣ መምህሮቻቸው ስላላቸው መብት ሕዝቡ ይጠይቁ ነበር። የታጣውን የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ለመተካት ሌሎች ማሳኪያ ዘዴዎችን መፈለግ አስፈላጊ ሆነ። በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማጠናቀቂያ ገደማ በእንግሊዝ የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናት ለመጎብኘት የሄደ የእሁድ አጨብጫቢ የእውነት ታማኝ ምስክሮች በሆኑ ሰዎች ተቃውሞ ይገጥመዋል፤ ከዚያም ጥረቶቹ ፍሬ-አልባ ሲሆኑበት ለሩብ አመት ያህል ከአገሩ ይሰወርና አስተምህሮዎቹን የሚያስገድድበት ዘዴ ሲያስስ ይከርማል። ሲመለስም ያጣውን ዘዴ አገኘ፤ ከዚያ በኋላ በነበረው ጥረቱም የተሻለ ስኬት አስመዘገበ። ሲመለስ፣ አልታዘዝ ባዩን የሚያስበረግግ አስከፊ ዛቻዎችን ጨምሮ የተፈለገውን የእሁድ ትዕዛዝ የያዘ ከእግዚአብሔር ከራሱ የተላከ ነው የተባለ ጥቅል ይዞ መጣ። ይህ የከበረ መዝገብ - ልክ እንደሚደግፈው ተቋም በሃሰት ምትክ (መሰረት) የሆነው ሰነድ - ከሰማይ ወርዶ በጎልጎታ በሚገኘው የቅዱስ ሲሞን መሰዊያ ላይ በየሩሳሌም እንደተገኘ ተነገረለት። ሆኖም የዚህ ሰነድ መገኛ ምንጭ በሮም የሚገኘው የጳጳሳዊ ቤተመንግሥት ነበር። የቤተ ክርስቲያንዋን ስልጣንና ብልጽግና ለማፈርጠም ማጭበርበሮችና መስለው የተሰሩ የሐሰት ቅጅዎች በሁሉም ዘመናት በጳጳሳዊ ተዋረዱ ህጋዊ ተደርገው ከፍተኛ ቦታ ሲሰጣቸው ኖረዋል።GCAmh 416.3

    ከቅዳሜ ዘጠነኛው ሰዓት (3pm)፣ ከሰዓት በኋላ፣ ጀምሮ ሰኞ ጠዋት ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ሥራ እንዳይሰራ ጥቅሉ ይከለክላል፤ ትዕዛዝ የማስተላለፍ ስልጣኑም በተለያዩ ተዓምራት ተረጋግጦ ነበር። ከተወሰነው ሰዓት በኋላ የሰሩ ሰዎች በሽባነት እንደተመቱ ተዘገበ። በቆሎውን ለመፍጨት የሞከረ ባለወፍጮ፣ ዱቄት ሲወጣ በማየት ፈንታ የደም ጎርፍ ሲወርድ አየ፤ የውኃው ግፊት ጠንካራ ቢሆንም የወፍጮው ሽክርክሪት ሳይነቃነቅ ቀጥ እንዳለ ቀረ። ምድጃ ውስጥ ሊጥ ያስገባች ሴት፣ ምድጃው በጣም ግሎ የነበረ ቢሆንም ሊጡ ሳይበስል ቡሆ እንደሆነ አገኘችው። በዘጠነኛው ሰዓት (ቅዳሜ) ለመጋገር ሊጥ ያዘጋጀች ሌላኛዋ፣ እስከሰኞ ድረስ ላለመጋገር ወስና ተወችው፣ በሚቀጥለው ቀን ዳቦ ሆኖ፣ በመለኮት ኃይል ተጋግሮ አገኘችው። ቅዳሜ ከዘጠነኛው ሰዓት በኋላ ዳቦ የጋገረ አንድ ሰው በሚቀጥለው ጠዋት ሲቆርሰው ደም ማፍሰስ ጀመረ። እነዚህን የመሳሰሉ የዘበትና የመላምት ፈጠራዎችን በመተረክ የእሁድ ደጋፊዎች ቅዱስነቱን ለማስረጽ ታተሩ። (Roger de Hoveden, Annals, vol. 2, page 526-530ን ይመልከቱ)።GCAmh 417.1

    በእንግሊዝ እንደተደረገው በእስኮትላንድም፣ ከጥንቱ ሰንበት ትንሽ ቆርሰው ከአሁኑ ጋር በመቀላቀል በእሁድ ያለው አክብሮት ከፍተኛ እንዲሆን ማረጋገጥ ተቻለ። ቅዱስ ሆኖ መጠበቅ የነበረበት ሰዓት ግን የተለያየ ነበር። በስኮትላንድ ንጉሥ የወጣው አዋጅ ቅዳሜ እኩለ ቀን (12pm) ጀምሮ ያለው ሰዓት ቅዱስ ሆኖ እንዲቆጠር ከዚያ ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰኞ ጠዋት ማንም ሰው ዓለማዊ ሥራ እንዳይሰራ ይከለክላል።-Morer, page 290, 291።GCAmh 417.2

    ነገር ግን የእሁድን ቅዱስነት መሰረት ለመጣል የተደረጉ ጥረቶች ሁሉ ቢኖሩም ጳጳሳዊያኑ ራሳቸው የሰንበትን (የቅዳሜን) መለኮታዊ ስልጣን በአደባባይ መስክረዋል፤ እንዲተካው የተደረገው ተቋምም ምንጩ ሰው እንደሆነ ተናግረዋል። በአሥራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንድ የጳጳሳዊ ጉባኤ እንዲህ ሲል በግልጽ አውጆአል፦ “ሰባተኛው ቀን በእግዚአብሔር የተቀደሰ እንደነበረ፣ ተቀባይነት አግኝቶ የሚከበረውም በአይሁዳዊያን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩ በሚያስመስሉ ሁሉ እንደሆነ ሁሉም ክርስቲያኖች ሊያስተውሉት ይገባል፤ እኛ ክርስቲያኖች ግን የእነርሱን ሰንበት ወደ ጌታ ቀን ቀይረነዋል።”-Ibid., page 281, 282። ወደ መለኮታዊው ሕግ እጃቸውን የሚሰዱ እነርሱ የሥራቸው ባህርይ ምን እንደነበረ የማያውቁ አልነበሩም። ሆን ብለው አቅደው ራሳቸውን ከእግዚአብሔር በላይ እያደረጉ ነበር።GCAmh 417.3

    ከእርስዋ ጋር በማይስማሙት ላይ ሮም የምትከተለውን ፖሊሲ ምንነት ቁልጭ አድርጎ በተግባር የሚያሳየው ድርጊት ከመካከላቸው የተወሰኑቱ የሰንበት አክባሪዎች በነበሩት ወልንደሶች ላይ የፈፀመችው ረጅምና ደም አፍሳሽ ስደት ነው። ለአራተኛው ትዕዛዝ ታማኝ በመሆናቸው ሌሎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰቃይተዋል። የኢትዮጵያና የአቢሲንያ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ በተለይ በጣም አስፈላጊ (አብይ ተጠቃሽ) ነው። በጨለማው ዘመን ድንግዝግዝታ ውስጥ የመካከለኛው አፍሪካ ክርስቲያኖች ከእይታ ርቀው በዓለም ተረስተው ነበር። ለብዙ መቶ ዓመታትም እምነታቸውን በመከተል ነፃነታቸውን አጣጥመዋል። በመጨረሻ ግን ሮም መኖራቸውን አወቀች፤ ከዚያም ሊቀ ጳጳሱ የክርስቶስ ወኪል እንደሆነ አድርጎ እውቅና እንዲሰጥ ብዙም ሳይቆይ የአቢሲንያ ንጉሠ ነገሥት ተታለለ። ሌሎችንም ጉዳዮች የመቀበሉ ሂደት ቀጠለ። ተወዳዳሪ የሌለው እጅግ ከባድ ቅጣት የያዘ የሰንበትን መከበር የሚከለክል አዋጅ ወጣ። (Michael Geddes, Church Hystory of Ethiopia, page 311, 312ን ይመልከቱ)። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ጳጳሳዊ ፈላጭ ቆራጭነት የሚያበሳጭ ቀንበር የሆነባቸው አቢሲንያውያን ከአንገታቸው ቆርጠው ለመጣል ወሰኑ። ከከባድ ትንቅንቅ በኋላ ሮማዊያኑ ከተቆጣጠሯቸው ስፍራዎች ተወገዱ፤ የጥንታዊ እምነትም ታደሰ። አብያተ ክርስቲያናቱ በነፃነታቸው ሐሴት አደረጉ፤ ማታለሉን፣ አክራሪነቱን እንዲሁም የማያፈናፍነውን የሮም ስልጣን በተመለከተ የተማሩትን ትምህርት ፈጽሞ አልረሱም። በሌላው የክርስቲያን ዓለም ሳይታወቁ በብቸኛ (በዘዋራ) ግዛታቸው ለመቀጠል ደስተኞች ነበሩ።GCAmh 417.4

    ሙሉ ለሙሉ ከመካድዋ በፊት ጳጳሳዊ ቤተ ክርስቲያን ታደርገው እንደነበረው የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበትን [ቅዳሜን] ጠበቁ። በእግዚአብሔር ትዕዛዝ መሰረት ሰባተኛውን ቀን ሲጠብቁ ሳለ፣ ከቤተ ክርስቲያን ባህል ጋር ለመስማማት በእሁድ ቀን ሥራ አይሰሩም ነበር። የጠቅላይ ስልጣን ከተቆናጠጠች በኋላ የራስዋን ከፍ ከፍ ለማድረግ ሮም በእግዚአብሔር ሰንበት ላይ ትረማመድ ነበረች፤ ለአንድ ሺህ ዓመታት ለሚቃረብ ዘመን ተሰውረው የቆዩት የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት በዚህ ክህደት አልተሳተፉም። በሮም ተጽዕኖ ስር በሚሆኑበት ጊዜ፣ እውነተኛውን ትተው ሐሰተኛውን ሰንበት ለማክበር ይገደዱ ነበር። ነፃነታቸውን በተቀዳጁበት ቅጽበት ግን አራተኛውን ትዕዛዝ ወደ ማክበር ተመለሱ [በመግለጫ ስር ማስታወሻ 12ን ይመልከቱ]።GCAmh 418.1

    ሮም ለእውነተኛው ሰንበትና ለደጋፊዎቹ ያላትን ጠላትነት፣ የራስዋ ፈጠራ የሆነውን ተቋምም ለማክበር የምትጠቀምባቸውን ዘዴዎች እነዚህ የቀድሞ መዛግብት በግልጽ ያመለክታሉ። እሁድን ከፍ ከፍ ያደርጉ ዘንድ ጳጳሳዊያኑና ፕሮቴስታንቶች በአንድነት ሲሰለፉ እነዚህ ክስተቶች እንደሚደገሙ የእግዚአብሔር ቃል ያስተምራል።GCAmh 418.2

    የበግ የሚመስሉ ቀንዶች ባለው አውሬ የተወከለው ኃይል “ምድርና በእርሱ የሚኖሩት”ን፣ “ነብር በሚመስል” አውሬ የተመሰለውን ጳጳሱን [ጳጳሳዊ ስርዓቱን] እንዲያመልኩ እንደሚያደርግ የራዕይ 13 ትንቢት ይናገራል። ይህ ሁለት ቀንዶች ያሉት አውሬ “ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል”፤ በተጨማሪም “ታናናሾችና ታላላቆችም ባለጠጋዎችና ድሆችም፣ ጌታዎችና ባርያዎችም ሁሉ የአውሬውን ምልክት” እንዲቀበሉ ያዝዝ ዘንድ አለው [ራዕይ 13÷11-16]። የበግ የሚመስሉ ቀንዶች ባሉት አውሬ የተወከለችው አሜሪካ እንደሆነች ተመልክቷል፤ ይህም ትንቢት የሚፈፀመው ሮም ለበላይነት ስልጣንዋ (ለልዕልናዋ መገለጫ) ልዩ የእውቅና ማረጋገጫ እንደሆነ አድርጋ የምትናገርለትን የእሁድን መከበር አሜሪካ ደግፋ አስገዳጅ በምታደርግበት ጊዜ ነው። ለዚህ ጳጳሳዊ ሥርዓት በሚሰጠው ክብር ግን አሜሪካ ብቸኛ አትሆንም። ሮም በአንድ ወቅት ለስልጣንዋ አውቅና ይሰጡ በነበሩ አገራት ዘንድ የነበራት ተጽዕኖ፣ አሁንም ፈጽሞ አልጠፋም። ወደፊትም ኃይልዋ እንደሚታደስ ትንቢት ይናገራል። “ከራሶቹም ለሞት እንደታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፤ ለሞቱ የሆነውም ቁስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ አደነቀ” [ራእይ 13÷]። የደረሰበት ለሞቱ የሆነው ቁስል በ1798 ዓ.ም የጳጳሳዊ ሥርዓት የተገረሰሰበትን ያመለክታል። ከዚህ በኋላ፣ ነብዩ ሲናገር፦ “ለሞቱ የሆነውም ቁስል ተፈወሰ፤ ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ አደነቀ።” የኃጢአቱ ሰው እስከ ዳግም ምፅዓት ድረስ እንደሚቀጥል ጳውሎስ በግልጽ ይናገራል [2ኛ ተሰሎ 2÷8]። እስከ ፍፃሜው ቀን ድረስ የማታለል ሥራውን ይቀጥልበታል። ባለ ራዕዩ ስለ ጳጳሳዊው ሥርዓት ጭምሮ ሲናገር፦ “በሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተፃፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል” ይላል [ራዕይ 13÷8]። በአሮጌው እና በአዲሱ ዓለም፣ በሮም ቤተ ክርስቲያን ስልጣን አማካኝነት ብቻ ለተቋቋመው የእሁድ ተቋም የሚሰጠው ክብር ለጳጳሳዊው ሥርዓት የሚሰጥ የክብር እውቅና ይሆናል።GCAmh 418.3

    ከአሥራ ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሸ ጀምሮ በአሜሪካ ያሉ የትንቢት ተማሪዎች ይህን ምስክርነት ለዓለም አቅርበዋል። አሁን እየተከናወኑ ባሉት ክስተቶች የሚታየው ወደ ትንቢቱ (prediction) መፈፀም በፍጥነት እየተገሰገሰ መሆኑን ነው። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለመተካት ሲሉ ተዓምራት እንደፈጠሩት ጳጳሳዊ መሪዎች ሁሉ፣ በፕሮቴስታንት ምሁራን ዘንድም ለእሁድ መከበር መለኮታዊ ስልጣን እንዳለ ተደርጎ ይነገራል። በተመሳሳይ መልኩ ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ የላቸውም። የእሁድን ሰንበት በሚጥሱ ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እንደሚጎበኝ በአጽንኦት ሲነገር የነበረው ክስተት እንደገና ይደገማል፤ ከወዲሁ መራገብ ጀምሯል። የእሁድን አክብሮት አስገዳጅ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴም ተቀባይነቱ በፍጥነት እየጨመረ ነው።GCAmh 419.1

    የሮም [ካቶሊካዊት] ቤተ ክርስቲያን ብልጣብልጥነትና ተንኮል እፁብ ድንቅ ሊባል የሚበቃ ነው። ሊሆን ያለውን ቀድማ ማንበብ ትችላለች። ሐሰተኛውን ሰንበት በመቀበላቸው የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ክብር እየሰጧት እንደሆነና፣ ባለፉት ዘመናት ራስዋ ተግባራዊ አድርጋቸው የነበረችውን እነዚያኑ ዘዴዎች ተጠቅመው አስገዳጅ ሊያደርጉት እየተዘጋጁ መሆኑን በማየት፣ ጊዜዋን ትጠብቃለች። የእውነትን ብርሐን አንቀበልም ያሉ እነርሱ፣ እርሷ ያመነጨችውን ተቋም ከፍ ከፍ ለማድረግ ራሱን ስህተት መሥራት የማይቻለው ብሎ የሚጠራውን ኃይል እርዳታ አሁንም ይፈልጋሉ። በዚህ ሥራ ረገድ ፕሮቴስታንቶችን ለመርዳት እንዴት በፍጥነት እንደምትደርስ መገመት አያዳግትም። ለቤተ ክርስቲያን የማይታዘዙት እንዴት መስተናገድ እንዳለባቸው ከጳጳሳዊያን መሪዎች የተሻለ መረዳት ያለው ማን ነው?GCAmh 419.2

    የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን፣ በዓለም ሁሉ ያሉትን ቅርንጫፍ መዋቅሮችዋን ጨምሮ አንድ ግዙፍ ድርጅት ሲሆን በጳጳሳዊው ዙፋን(አሥተዳደር) ቁጥጥር ስር ያለና ፍላጎቱንም እንዲያስፈጽም የተቀረፀ ነው። በምድር ላይ ባሉት እያንዳንዱ አገራት ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን ለሊቀ ጳጳሱ ባላቸው የታማኝነት መኃላ ስር ራሳቸውን ገድበው እንዲኖሩ ይታዘዛሉ። ዜግነታቸውም ሆነ መንግሥታቸው የትኛውም ቢሆን የቤተ ክርስቲያን ስልጣን ከሁሉም በላይ እንደሆነ መቀበል ይጠበቅባቸዋል። ዜጋ ለሆኑበት ሀገር ታማኝ ለመሆን መኃላ የፈፀሙ ቢሆንም ከዚህ በስተጀርባ ግን፣ የእርሷን ፍላጎት የሚፃረር ከሆነ ለመንግሥት የገቡትን እያንዳንዱን ቃል ኪዳን ቢያፈርሱ ከበደል ነፃ እንዲሆኑ የምታደርግበት ለሮም ታዛዥ ለመሆን የሚገባ ቃለ መኃላ አለ።GCAmh 419.3

    እሁድን ከፍ ከፍ በማድረጉ ሥራ የሮምን እርዳታ ለመቀበል ሀሳብ ሲያቀርቡ ፕሮቴስታንቶች የሚያደርጉትን አያውቁም። እነርሱ አላማቸውን ለማሳካት ቆርጠው ሳለ፣ ሮም ደግሞ ያጣችውን የበላይነት እንደገና ለማግኘት፣ ኃይልዋን እንደገና ለመገንባት ታልማለች። በአገራት ጉዳዮች ውስጥ እጅዋን ለማስገባት የምታደርጋቸውን ጮሌና የማያባራ ጥረቶችዋን ታሪክ ይመስክር፤ አንድ ጊዜ እግርዋን ካስገባች በኋላም በልዑላንና በሕዝቡ ውድመት እንኳ ቢሆን የራስዋን ግብ ዳር ለማድረስ ምን እንደምታደርግ ታሪክ ይናገር። ሊቀ ጳጳሱ የአገራትን መብት፣ የእግዚአብሔርንና የሰውን ሕግ የሚፃረሩ ቅጣቶችንና ፍርዶችን ማወጅ እንደሚችል ሮማዊነት በአደባባይ ይናገራል [“The Decretalia”]። [በ1204 ዓ.ም. ሊቀ ጳጳስ IIIኛ፣ የአራጎንን ንጉሥ ፒተር IIኛን፣ የሚከተለውን አስገራሚ መሃላ አስገብቷል፡-“እኔ፣ ፒተር፣ የአራጎንያዊያን ንጉሥ፣ መንግስቴን በታማኝነት በእርሱ እዝ ሥር አድርጌ፣ የካቶሊክን እምነት ከጥቃት እየተከላከልኩ፣ የመናፍቅነት መጣመምን እያሳደድኩ፣ ለጌታዬ ለሊቀ ጳጳስ ኢኖሰንት፣ ከእርሱ በኋላ በእርሱ ቦታ ለሚሆኑ ካቶሊኮችና ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜም ታማኝና ታዛዥ እንደምሆን እመሰክራለሁ፣ ቃልም እገባለሁ።”-John Dowling, The Hysstory of Romanism, b. 5, ch. 6, sec. 55። ይህ፣ “ንጉሥ ነገሥታትን መሻር ለእርሱ ሕጋዊ መሆኑ” እንዲሁም “ተገዥዎች፣ ጻድቅ ላልሆኑ መሪዎቻቸው ከገቡት የታማኝነት መኃላ እርሱ ነፃ ማውጣት ይችላል” መባሉ፣ ከሮማው ሊቀ ጳጳስ የስልጣን ይገባኛል መጠይቅ ጋር የሚስማማ ነው። -Mosheim, b. 3, cent. 11, pt. 2, ch. 2, sec. 9, note 17።(ከGreat Controversy, 1911 edition የተወሰደ)]GCAmh 419.4

    ፈጽሞ የማትለወጥ የመሆንዋን ነገር ሮም የምትኩራራበት ጉዳይ መሆኑ ይታወስ። የግሪጎሪ 7ኛ እና የኢኖሰንት 3ኛ መርሆዎች አሁንም የሮም ቤተ ክርስቲያን መርሆዎች ናቸው። ኃይሉ (ስልጣኑ) የላትም እንጂ ቢኖራት ኖሮ እንዳለፉት ምዕተ ዓመታት ሁሉ አሁንም በታላቅ ብርታት ተግባራዊ ታደርጋቸው ነበር። እስኪ የመንግሥታትን ኃይል መጠቀም ወይም መቆጣጠር ትችል ዘንድ መርሁ በአሜሪካ ይመስረት፣ ኃይማኖታዊ ተግባራትም በመንግሥት ሕግ አስገዳጅ ይሁኑ፣ ባጭሩ የቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ስልጣን ህሊናን ይቆጣጠርና፣ የሮም ድል አድራጊነት በዚህች አገር ላይ ይረጋገጣል።GCAmh 420.1

    በቅርቡ ሊከሰት ስላለው አደጋ የእግዚአብሔር ቃል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፤ እስኪ ይህ ማስጠንቀቂያ ሳይሰማ ይቅርና፣ ወጥመዱን ለማምለጥ ጊዜው ካለፈ በኋላ የሮም አላማዎች በእርግጥ ምን እንደሆኑ የፕሮቴስታንቱ ዓለም የሚረዳ ይሆናል። ሮም በዝምታ ወደ ኃያልነት እያደገች ነው። አስተምህሮዎችዋ፣ በሕግ አውጪ አዳራሾች፣ በአብያተ ክርስቲያናትና በሰው ልቦች ውስጥ ተጽዕኖአቸውን እያሳረፉ ነው። በምስጢራዊ ጓዳዎችዋ ውስጥ የቀድሞ የማሳደድ ሥራዋን የምትደግምበትን የመጠቁና ግዙፍ መዋቅራዊ ወጋግራዎች እየተከለች ነው። የራስዋን አላማ ወደፊት ማስኬድ ትችል ዘንድ ጊዜው በደረሰ ጊዜ ለመናደፍ በስውርና በማይጠረጠርበት ሁኔታ ኃይሎችዋን እያጠናከረች ነው። የምትሻው ነገር ቢኖር ከላይ ሆና ሁሉንም የምትቃኝበት ስፍራ (ፍላጎትዋን ማስጠበቅ የምትችልበት ደረጃ) ማግኘት ነው፤ ይህም ከወዲሁ እየተሰጣት ነው። የሮማዊው አካል አላማ ምን እንደሆነ በቅርቡ እናያለን፣ ዳሰሳውም ይሰማናል። የእግዚአብሔርን ቃል የሚያምንና የሚታዘዝ ማንም ቢኖር ነቀፋንና ስደትን የሚያተርፍ ይሆናል።GCAmh 420.2