Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፴፮—በቅርቡ ሊሆን ያለው ግጭት - መንስኤዎቹ

    በሰማይ ከነበረው ከመጀመሪያው ታላቁ ተቃርኖ (ተጋድሎ) ጀምሮ የእግዚአብሔርን ሕግ በኃይል መገልበጥ የሰይጣን አላማ ነው። ፈጣሪንም በመቃወም ወደ አመጽ የገባው ይህንን ለማሳካት ነበር፤ ከሰማይ ቢጣልም ተመሳሳዩን ጦርነት በምድር ላይ ቀጥሎበታል። ሽንጡን ገትሮ የሚያሳድደው አላማው ሰዎችን አታሎ የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲጥሱ መምራት ነው። ይህም የሚከናወነው ሕጉን ሙሉ ለሙሉ ወደ ጎን በማድረግ ወይም ከመመሪያዎቹ አንዷን ባለመቀበል ሲሆን በመጨረሻ ውጤቱ ያው ነው። “በአንድ ነጥብ” ላይ የሚሰናከል እርሱ ለሙሉው ሕግ ንቀትን ያንፀባርቃል። ተጽዕኖውና ምሳሌነቱ በመተላለፍ ጎራ ናቸው፤ “በሁሉም በደለኛ” ይሆናል [ያዕቆብ 2÷10]።GCAmh 421.1

    በመለኮታዊ ሕገ-ደንቦች ላይ ንቀት ለማሳረፍ ሲጥር ሰይጣን የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምህሮዎች ስላጣመማቸው መጽሐፍ ቅዱስን እንደሚያምኑ በሚናገሩ በሺህ በሚቆጠሩ ሰዎች እምነት ውስጥ ስህተቶች እንዲቀላቀሉ ተደርገዋል። በእውነትና በስህተት መካከል የሚደረገው የመጨረሻው የከረረ ጥል የእግዚአብሔርን ሕግ በተመለከተ ለረጅም ጊዜ ሲደረግ የነበረው ተጋድሎ ትግል መደምደሚያ እንጂ ሌላ አይደለም። አሁን እየገባንበት ያለው ውጊያ በሰዎች ሕግጋትና በያህዌ መመሪያዎች መካከል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ኃይማኖትና በተረት፣ በወግና ባህል ኃይማኖት መካከል የሚደረግ ውጊያ ነው።GCAmh 421.2

    በዚህ ትግል ውስጥ እውነትንና ጽድቅን ተቃውመው የሚተባበሩት እንደራሴዎች አሁን በትጋት፣ ሥራ ላይ ናቸው። በታላቅ ሰቆቃና ደም ዋጋ ተከፍሎበት ወደ እኛ የወረደው የእግዚአብሔር ቃል ዋጋ-ቢስ ተደርጓል። መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም ሊደርሱበት በሚችሉበት ስፍራ ነው፤ የሕይወታቸው መሪ አድርገው የሚቀበሉት ግን ከቁጥር የሚገቡ አይደሉም። ከሃዲነት በሚያስደነግጥ መጠን፣ በዓለም ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ተንሰራፍቷል። የክርስትና እምነት ምሰሶ የሆኑትን እነዚያኑ አስተምህሮዎች ብዙዎች ክደዋል። በመንፈስ በተመሩ ፀሐፊያን የቀረቡት የፍጥረት ታላላቅ እውነቶች - የሰው ልጅ ውድቀት፣ ስርየትና የእግዚአብሔር ሕግ ዘላለማዊነት - በሙሉም ሆነ በከፊል አማኝ እንደሆነ በሚናገረው፣ ሰፊ ድርሻ ባለው በክርስትናው ዓለም በተግባር ተቀባይነት አጥተዋል። በጥበባቸውና በራስ-መርነታቸው የሚኮሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የማያወላውል እምነትን እንደ ደካማነት ይቆጥሩታል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አላስፈላጊ የሆነ ምሬት መሰንዘር፣ መንፈሳዊነትን በማላበስና (የመንፈሳዊነት ደረጃቸውን ከፍ በማድረግና) በማስተባበል እጅግ አስፈላጊ የሆኑ እውነቶቻቸውን ዋጋ መቀነስ (ማስወገድ) የላቀ ችሎታና የምሁርነት ማስረጃ ነው ብለው ያስባሉ። የእግዚአብሔር ሕግ እንደተለወጠ ወይም እንደተሻረ አድርገው ብዙ አገልጋዮች ሕዝቦቻቸውን፣ ብዙ ፕሮፌሰሮችና አስተማሪዎች ደግሞ ተማሪዎቻቸውን እያስተማሩ ነው፤ የሕጉ መጠይቆች አሁንም ድረስ ገቢራዊነትን የሚጠይቁ እንደሆኑ፣ ቃል በቃል መከበር እንዳለባቸው የሚቀበሉ እነርሱ ከፌዝና ከንቀት በቀር ሌላ እንደማይገባቸው ይታሰባል።GCAmh 421.3

    እውነቱን አንቀበልም በማለታቸው ሰዎች የእውነቱን ደራሲ አሻፈረን ይላሉ። በእግዚአብሔር ሕግ ላይ በመረማመዳቸው የሕግ ሰጪውን ስልጣን ይክዳሉ። የሐሰት አስተምህሮዎችና ጽንሰ-ሐሳቦች ጣዖት መሥራት፣ ከእንጨት ወይም ከድንጋይ ጣዖት የመቅረጽ ያህል ቀላል ነው። ሰይጣን የእግዚአብሔርን [መለያ] ባህርያት ሌላ መልክ አስይዞ በማቅረብ ሰዎች የጌታን ጠባይ እውነተኛ ባልሆነ መልኩ እንዲረዱት ይመራቸዋል። በቃሉ፣ በክርስቶስ እንዲሁም በፍጥረት ሥራዎች የተገለጠው እግዚአብሔር በጣም በጥቂት ሰዎች ሲመለክ ሳለ በብዙዎች ዘንድ በእግዚአብሔር ፈንታ የፍልስፍና ጣዖት ነግሶአል። የተፈጥሮን አምላክ እየካዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈጥሮን ያመልካሉ። የተለየ ቅርጽ የያዘ ቢሆንም፣ በጥንት እሥራኤላዊያን፣ በኤልያስ ዘመን የነበረው ጣዖት አምላኪነት አሁንም በክርስቲያኑ ዓለም አለ። ጥበበኞች መሆናቸው የተመሰከረላቸው በርካታ ሰዎች፣ የፈላስፋዎች፣ የገጣሚዎች፣ የጋዜጠኞች — በነጠሩና ስልጡን በሆኑ ክበባት ውስጥ ያሉ፣ የብዙ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች ይባስ ብሎም የአንዳንድ ስነ-መለኮታዊ ተቋማት አምላክ፣ ከፍንቄ የፀሐይ አምላክ፣ ከበኣል የተሻለ አይደለም።GCAmh 422.1

    የእግዚአብሔር ሕግ ከእንግዲህ በሰዎች ላይ ስልጣን የለውም [እንዲከበር የሚያስገድድ መጠይቅ የለውም] ከሚለው፣ እጅግ በፍጥነት እየተስፋፋ ካለው ዘመናዊ አስተምህሮ የበለጠ፣ በክርስቲያኑ ዓለም ተቀባይነት አግኝቶ የሰማይን ስልጣን በድፍረት የሚገዳደር፣ አመክንዮ የሚያስቀምጠውን የህሊና ትዕዛዝ በቀጥታ የሚቃወም፣ በውጤቱም እጅግ ጎጂ የሆነ ነገር (አስተምህሮ) የለም። እያንዳንዱ ሀገር አክብሮትንና መታዘዝን የሚጠይቅ የራሱ ሕግጋት አሉት፤ ማንኛውም መንግሥት ያለ እነዚህ ሕግጋት መኖር አይቻለውም፤ ታዲያ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ የፈጠራቸውን ፍጡራን የሚያስተዳድርበት ሕግ አይኑረው ማለት መታሰብ የሚችል ነውን? የታወቁ አገልጋዮች፣ አገራቸውን የሚያስተዳድሩትን፣ የዜጎቻቸውንም መብት የሚያስከብሩትን ሕግጋት፣ በአደባባይ የሕዝቡን መብቶች የሚገድቡ በመሆናቸው ሊከበሩ አይገባም ብለው አስተማሩ ብለን ብናስብ፣ እነዚህ ሰዎች ለምን ያህል ጊዜ ነው መድረክ ላይ በትዕግስት በዝምታ የሚታለፉት? ነገር ግን የአገራትንና የመንግሥታትን ሕጎች ቸል ማለት፣ የመንግሥታት ሁሉ መሰረት በሆኑት በነዚያ መለኮታዊ መመሪያዎች ላይ ከመረማመድ የባሰ ከባድ ጥፋት ነውን?GCAmh 422.2

    የዓለማት ገዢ ሕጉን አምክኖ፣ ጥፋተኛውን የሚኮንንበትን፣ ታዛዡንም የሚያፀድቅበትን ደረጃ (መከሊያ) ሽሮ፣ ዓለምን ከሚተው ይልቅ መንግሥታት ሕግጋቶቻቸውን ሽረው ሰዎች እንደፈለጉ እንዲያደርጉ ቢለቋቸው የተሻለ አግባብነት ያለው፣ ተቃርኖ የማይፈጥር ይሆናል። የእግዚአብሔርን ሕግ ማፍረስ (ዋጋ ቢስ ማድረግ) ውጤቱ ምን እንደሆነ እናውቃለን? ይህ በተግባር ተሞክሯል። በፈረንሳይ፣ እምነት የለሽነት ተቆጣጣሪ ኃይል ሲሆን፣ የነበረው ትዕይነት አሰቃቂ ነበር። እግዚአብሔር ያስቀመጣቸውን ገደቦች አሽቀንጥሮ መጣል፣ ከአምባገነኖች ሁሉ ጨካኝ የሆነውን [መሪ] ሕግ መቀበል እንደሆነ ለዓለም በተግባር ተገልፆአል። የጽድቅ ደረጃ ወደ ጎን በሚገፈትርበት ጊዜ የክፋት ልዑል በምድር ኃይሉን ይመሰርት ዘንድ መንገድ ይከፈትለታል።GCAmh 422.3

    የመለኮታዊ መመሪያዎች ተቀባይነት ባጡበት በየትኛውም ሥፍራ ሁሉ ኃጢአት፣ ኃጢአት መምሰሉን፣ ጽድቅ መልካምነቱን ያጣል። ለእግዚአብሔር አስተዳደር አንገዛም የሚሉ እነርሱ፣ ራሳቸውን ማስተዳደር ፈጽሞ የማይችሉ ናቸው። ከፍተኛ ጉዳት በሚያስከትሉት ትምህርቶቻቸው ምክንያት፣ በተፈጥሯቸው ለቁጥጥር ትዕግስት የለሽ በሆኑት ልጆችና ወጣቶች ልብ ውስጥ ያለመታዘዝ መንፈስ ይተከላል፤ እናም ሕግ-አልባና የጋጄ ማህበረሰብ ይፈጠራል። የእግዚአብሔርን መስፈርቶች የሚታዘዙትን በቀላሉ የሚያምኑ ናቸው ብለው ሲያፌዙባቸው ሳለ፣ እልፍ አዕላፋት የሰይጣንን ማታለያዎች ሰፍ ብለው ይቀበላሉ። ለአይበገሬ ፍላጎቶቻቸው መሪ ልጓሙን ይሰጣሉ፣ በአሕዛብ ላይ ፍርድ እንዲመጣ ያደረጉትን ኃጢአቶችም ያደርጋሉ።GCAmh 422.4

    የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንዲያቀሉ የሚያስተምሩ እነርሱ፣ አመጽን ለመሰብሰብ አመጽን ይዘራሉ። በመለኮታዊው ሕግ የተቀመጡት መገደቢያዎች ሙሉ ለሙሉ ይነሱ፣ ብዙም ሳይቆይ የሰብአዊ ፍጡር ሕግጋት ቸል ይባላሉ። እምነት የጎደላቸውን ተግባራት፣ ምኞትን፣ በሐሰት መናገርን፣ በማጭበርበር ገንዘብን ማግኘትን፣ እግዚአብሔር ስለሚከለክል፣ ለዓለማዊ ብልጽግናቸው እንቅፋት እንደሆኑ አድርገው ሰዎች በሕግጋቱ ላይ ለመረማመድ የተዘጋጁ ናቸው። እነዚህን መመሪያዎች የማስወገዱ ውጤት ግን ሰዎች ያልገመቱት ይሆናል። ሕግጋቱ መከበር ያለባቸው ባይሆኑ ኖሮ ማንም ለመተላለፍ ለምን ይፈራል? ንብረት ያለ አደጋ መሆኑ ይቀራል። ሰዎች የጎረቤቶቻቸውን ጥሪት በጉልበት ይወስዱ ነበር፤ ከሁሉ ይልቅ ጉልበተኛ የሆነው ከሁሉም በላይ ኃብታም ይሆናል። ሕይወት ራሱ አይከበርም። የጋብቻ መኃላ ቤተሰቡን የሚከልል የተቀደሰ ቅጥር ሆኖ መቆሙ ይቀራል። ጉልበት ያለው እርሱ፣ ከፈለገ የጎረቤቱን ሚስት በኃይል ይወስዳል። አምስተኛው ትዕዛዝ ከአራተኛው ጋር ወደ ጎን ይገፋ ነበር። እንደዛ በማድረጋቸው የተበላሸውን የልባቸውን መሻት የሚያገኙ ከሆነ ልጆች የወላጆቻቸውን ሕይወት ለመቅጠፍ ወደኃላ አይሉም ነበር። የሰለጠነው ዓለም የዘራፊዎችና የገዳዮች መንጋ ሆኖ፣ ሰላም እረፍትና ደስታ ከምድር ይጠፋ ነበር።GCAmh 423.1

    ለእግዚአብሔር መጠይቆች ከመታዘዝ ሰዎች ተፈትተዋል (ነፃ ሆነዋል) የሚለው አስተምህሮ ከወዲሁ የሞራል አስገዳጅነትን ኃይል በማኮሰስ በዓለም ላይ የኃጢአትን ማዕበል ደጃፍ ከፍቶአል። ሕግ-አልባነት፣ ብኩንነትንና ምግባረ ብልሹነት ልንቋቋመው በሚያቃቅት ማዕበል እየጠረጉን ነው። በቤተሰብ ውስጥም፣ ዲያቢሎስ ሥራውን እየሰራ ነው። በተመሰከረላቸው የክርስቲያን ቤቶች እንኳ ሳይቀር ባንዲራው እየተውለበለበ ነው። ቅናት፣ ክፉ አሉባልታ፣ ግብዝነት፣ መቃቃር፣ በልጦ ለመገኘት መልፋት፣ ጥል፣ የተቀደሱ መታመኖችን መክዳት፣ ምኞትን ማርካት አለ። የማህበራዊ ሕይወትን መሰረትና ቅርጽ ማበጀት የነበረባቸው የኃይማኖታዊ መርሆዎችና አስተምህሮዎች አጠቃላይ መዋቅር ለመውደቅ የተዘጋጀ፣ ወለል ወለል የሚል [ቅርጽ-አልባ] ቁልል ይመስላል። እጅግ ከባድ ጥፋት የሰሩ ወንጀለኞች፣ ለሰሩት ሥራ ወደ ወህኒ ሲገቡ፣ ሰው የሚመኘው አይነት ማዕረግ ያገኙ ይመስል ብዙ ጊዜ የስጦታና የትኩረት ተጠቃሚዎች ይደረጋሉ። ስለ ባህርያቸውና ስለ ወንጀሎቻቸው ከፍተኛ ሽፋን ይሰጣል። የህትመት መገናኛ ብዙሃኑ የርኩሰትን ዘግናኝ ዝርዝር ያትማል፤ በዚህም ሌሎች፣ ማጭበርበር፣ ዘረፋና ግድያ እንዲፈጽሙ ያነሳሳል፤ በሲኦላዊ ሴራው ስኬት ሰይጣን ይፈነጥዛል። በክፋት ፍቅር መናወዝ፣ ሳይተናኮሱ ሕይወትን ማጥፋት፣ በሁሉም ደረጃና መጠን እጅግ እየጨመረ የመጣው ገደብ የለሽነትና ኃጢአት፣ የጥፋትን ማዕበል ተቋቁሞ መቆም ይቻል ዘንድ ምን መደረግ እንዳለበት ይጠይቁ ዘንድ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሁሉ ሊያነቃ ይገባዋል።GCAmh 423.2

    የፍርድ ሸንጎዎች ሙሰኞች ሆነዋል። መሪዎች የሚንቀሳቀሱት በትርፍ መሻትና በስሜታዊ እርካታ ፍቅር እየተዘወሩ ነው። መሻትን አለመግዛት የብዙዎችን አዕምሯዊና አካላዊ ኃይላት ስላጨለመው ሰይጣን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮአቸዋል ማለት ይቻላል። ሕግ አዋቂዎች ተጣመዋል፤ ጉቦ ተቀባይ ሆነዋል፤ ተሞኝተዋል። ስካርና ፈንጠዝያ፣ አነሁላይ ፍላጎት፣ ቅንዓትና የሁሉም ነገር እምነት የለሽነት ሕግን በሚቆጣጠሩ መካከል አሉ። “ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፣ ቅንነትም ሊገባ አልቻለምና።” [ኢሳ 59÷14]።GCAmh 424.1

    በሮም የበላይነት ስር ተንሰራፍተው የነበሩት ኃጢአትና መንፈሳዊ ጽልመት፣ መጽሐፍ ቅዱስን የመጨቆንዋ አይቀሬ ውጤቶች ነበሩ፤ ነገር ግን በኃይማኖት ነፃነት ዘመን፣ በሙላት በሚንቀለቀለው የወንጌል ብርሐን ስር ላለው የተንሰራፋ ክህደት፣ ለእግዚአብሔር ሕግ ተቀባይነት ማጣትና ተከትሎም ለመጣው ብልሹነት መንስኤው የሚገኘው የት ነው? ከአሁን ወዲያ መጽሐፍ ቅዱስን በመከልከል ሰይጣን ዓለምን በቁጥጥሩ ስር ማድረግ የማይችል ስለሆነ፣ ያንኑ አላማውን ለማሳካት ወደሌሎች ዘዴዎች ይዞራል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እምነት እንዳይኖር ቢያደርግ፣ አላማውን ለማሳካትም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ራሱን ለማጥፋት ይጠቅመዋል። የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ የግድ እንደማያስፈልግ የሚናገረውን እምነት በማስተዋወቅ፣ መመሪያዎቹን ሁሉ ምንም እንደማያውቋቸው አድርገው እንዲተላለፉ ሰዎችን በብቃት ይመራቸዋል። አሁንም፣ እንደ ቀድሞ ዘመናት ሁሉ ንድፉን ያስፋፋ ዘንድ በቤተ ክርስቲያን በኩል ይሰራል። የዛሬዎቹ የኃይማኖት ተቋማት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፍንትው ብለው የሚታዩትን፣ ሆኖም በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸውን እውነቶች ለመስማት እምቢ ብለዋል፤ [እነዚህን እውነቶች] ለመዋጋት በሚያደርጉት ሙከራም፣ የሚሰጧቸው ማብራሪያዎችና የሚወስዷቸው አቋሞች የመጠራጠርን ዘር የሚያሰራጩ ሆነዋል። በተፈጥሯዊ አለመሞት (immortality) እና ሰው ከሞተ በኋላ ህሊናው ንቁ ይሆናል የሚለውን ጳጳሳዊ ስህተት የሙጥኝ በማለታቸው፣ የመናፍስታዊነት ማታለያዎች ብቸኛ ቅጥር የሆነውን አሻፈረኝ ብለዋል። የዘላለማዊ ስቃይ አስተምህሮ መጽሐፍ ቅዱስን እንዳያምኑ ብዙዎችን መርቷቸዋል። የአራተኛውን ትዕዛዝ መጠይቆች ያከብሩ ዘንድ ሰዎች አጥብቀው ሲገነዘቡ፣ ሰባተኛውን ቀን ሰንበት ማክበር የሚጠይቅ እንደሆነ ይገለጣል፤ ያከናውኑት ዘንድ ከማይፈልጉት ኃላፊነት ራሳቸውን ነፃ ለማድረግም ሕዝባዊ ተቀባይነት ያላቸው የታወቁ መምህራን የእግዚአብሔርን ሕግ መታዘዝ አስፈላጊ መሆኑ እንደቀረ ይናገራሉ። እንዲህ በማድረጋቸውም ሕጉንና ሰንበትን አንድ ላይ አሽቀንጥረው ይጥላሉ። የሰንበት ተሐድሶ ሥራ እየቀጠለ ሲሄድ፣ የአራተኛውን ትዕዛዝ መጠይቆች ለማስወገድ ሲባል የመለኮታዊው ሕግ ተቀባይነት ማጣት ዓለም አቀፋዊ ለመሆን ምንም አይቀረውም። የኃይማኖታዊ መሪዎች የሚያስተምሩት ትምህርቶች ለቃል ኪዳን አፍራሽነት፣ ለመናፍስታዊነት፣ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕግ ንቀት በር ከፍተዋል፤ በክርስቲያኑ ዓለም ላለው ኃጢአትም በእነዚህ መሪዎች ላይ አስፈሪ ኃላፊነት አርፎአል።GCAmh 424.2

    ሆኖም ይህ መደብ ራሱ፣ በፍጥነት እየተስፋፋ ላለው ብልሹነት ምክንያቱ በአብዛኛው “የክርስቲያን ሰንበት” ተብሎ የሚጠራው በመርከሱ እንደሆነ፣ የእሁድን መጠበቅ አስገዳጅ ማድረግ የሕብረተሰብን ግብረ ገብነት በእጅጉ እንደሚያሻሽለው ይናገራል። ይህ መጠይቅ ደግሞ በተለይ የሚበረታታው፣ የእውነተኛው ሰንበት አስተምህሮ በብዛት በተሰበከበት፣ በአሜሪካ ነው። ይህ እጅግ ታዋቂና አስፈላጊ ከሆኑት የግብረ ገብነት ተሐድሶዎች መካከል የሆነው ራስን የመግዛት ሥራ፣ በአብዛኛው ከእሁድ ንቅናቄ ጋር እየተሰባጠረ የእሁድ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች የሕብረተሰብን ዋና ፍላጎት ለማዳበር እንደሚለፉ አድርገው ራሳቸውን ያቀርባሉ። የማይቀበሏቸውም ሁሉ መሻትን የመግዛትና የተሐድሶ ጠላቶች ተደርገው ይወገዛሉ። የስህተትን መሰረት ለመጣል ሲባል የተጀመረ እንቅስቃሴ፣ በራሱ መልካም ከሆነ ሥራ ጋር መቆራኘቱ፣ ስህተትን በመደገፍ የሚቀርብ መከራከሪያ አይደለም። ከጤናማ ምግብ ጋር አቀላቅለን መርዝን ልንደብቅ እንችል ይሆናል፤ ባህርይውን ግን አንቀይረውም። በተቃራኒው ግን፣ ሳይታወቅ የመበላቱ ዕድል ከፍተኛ ስለሚሆን፣ የበለጠ አደገኛ እንደሆነ ይታመናል። የሚታመን ያስመስለው ዘንድ ሐሰትን ልክ በቂ ከሆነ (ከተመጠነ) እውነት ጋር ማቀላቀል ከሰይጣን መሳሪያዎች አንዱ ነው። የእሁድ እንቅስቃሴ መሪዎች ሕዝቡ የሚፈልጋቸውን ተሐድሶዎችን፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚስማሙ መርሆዎችን ያበረታቱ ይሆናል። ሆኖም ከእነዚህ ጋር የሚመጣ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚፃረር መጠይቅ ስላለ፣ የጌታ አገልጋዮች ሊተባበሯቸው አይችሉም። የሰውን መመሪያ ለመቀበል ሲሉ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ወደ ጎን ማድረጋቸው በምንም ሁኔታ ከበደል ነፃ ሊያደርጋቸው አይችልም።GCAmh 424.3

    በሁለቱ ታላላቅ ስህተቶች ማለትም ነፍስ አትሞትም በሚለውና በእሁድ ቅዱስነት አማካኝነት፣ ሰይጣን ሰዎችን በማታለያዎቹ ሥር ያስገባቸዋል። የፊተኛው፣ ነፍስ አትሞትም የሚለው፣ የመናፍስታዊነትን መሰረት ሲጥል፣ የኋለኛው የእሁድ ቅድስና ደግሞ ከሮም ጋር የጠበቀ ቁርኝትን ይፈጥራል። የአሜሪካ ፕሮቴስታንቶች የመናፍስታዊነትን እጅ ለመጨበጥ፣ ባህረ-ሰላጤውን አቋርጠው እጃቸውን የሚዘረጉ የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ። ከሮማዊነት ኃይል ጋር ይጨባበጡ ዘንድ ገደሉን አልፈው እጃቸውን ይዘረጋሉ፤ በዚህ ሶስት እጥፍ ተጽዕኖ ጥምረት ሥርም ይህቺ አገር፣ የህሊናን መብቶች በመርገጥ የሮምን ዱካ ትከተላለች።GCAmh 425.1

    መናፍስታዊነት፣ የዘመኑን የይስሙላ ክርስትና የበለጠ እየመሰለ ሲሄድ፣ ለማታለልና ለማጥመድ የበለጠ ኃይል ይኖረዋል። እንደ ዘመናዊ የነገሮች አደረጃጀት (አቀራረብ) ሰይጣን ራሱ ይለወጣል። የብርሐንን መልአክ ባህርይ ይዞ ይገለጣል። በመናፍስታዊነት እንደራሴነትም ተዓምራት ይደረጋሉ፣ ህሙማን ይፈወሳሉ፣ ብዙ ሊካዱ የማይችሉ አስደናቂ ተዓምራቶች ይፈፀማሉ። መናፍስቱም በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያምኑ ስለሚናገሩና ለቤተ ክርስቲያን ተቋማትም ያላቸውን አክብሮት ስለሚያንፀባርቁ፣ ሥራቸው የመለኮታዊ ኃይል መገለጥ ተደርጎ ተቀባይነት ያገኛል።GCAmh 425.2

    በታማኝ ክርስቲያኖችና እግዚአብሔርን በማይመስሉ መካከል ያለው መለያ መስመር አሁን ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኖአል። የቤተ ክርስቲያን ምእመናን፣ ዓለም የሚያፈቅረውን ያፈቅራሉ፤ ከእነርሱም [ከዓለማዊያን] ጋር ለመተባበር የተዘጋጁ ናቸው፤ ሰይጣን ደግሞ ወደ አንድ አካልነት ሊያዋህዳቸው ቁርጥ ውሳኔ ያደርጋል፤ በዚህም ሁሉን ወደ መናፍስታዊነት ሰልፍ በመጥረግ ጉዳዩን ያጠነክራል። የእውነተኛ ቤተ ክርስቲያን ማረጋገጫ ምልክት ተዓምራት እንደሆነ የሚኩራሩት ጳጳሳዊያኑ በዚህ አስገራሚ ድርጊት ፈፃሚ ኃይል በቀላሉ ይታለላሉ፤ የእውነትን ጋሻ አሽቀንጥረው የጣሉት ፕሮቴስታንቶችም ይሞኛሉ። ጳጳሳዊያኑ፣ ፕሮቴስታንቶችና ዓለማዊያን ኃይል አልባውን የአምልኮ መልክ ይቀበላል፤ ለዓለም መለወጥ የሚሆን ታላቅ እንቅስቃሴ፣ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን የሺህ አመት መጀመሪያ በዚህ ህብረት ያያሉ።GCAmh 425.3

    የሕዝቡን በሽታዎች በመፈወስ፣ አዲስና የተሻለ ኃይማኖታዊ መዋቅር እንደሚያቀርብ በመናገር፣ ሰይጣን፣ በመናፍስታዊነት አማካኝነት ለሰው ዘር ጠቃሚ እንደሆነ ያስመስላል። በዚያው ተመሳሳይ ሰዓት ግን እንደ አጥፊ ሆኖ ይሰራል። ፈተናዎቹ እልፍ አዕላፋትን ወደ ውድመት እየመሩ ነው። መሻትን አለመግዛት፣ የማመዛዘን ችሎታን ከዙፋኑ ያወርደዋል፤ የስሜት እርካታ፣ ጥልና ደም ማፍሰስ ይከተላሉ። የነፍስን እጅግ መጥፎ ፍላጎቶች ስለሚቀሰቅስ፣ ከዚያም በብልሹነትና በደም አጨማልቆ ተጠቂዎቹን ለዘላለም ስለሚጠርጋቸው ሰይጣን በጦርነት ሐሴት ያደርጋል። እንዲህ ካደረገ በእግዚአብሔር ቀን ይቆሙ ዘንድ ከመዘጋጀት ሥራ የሰዎችን አዕምሮ አቅጣጫ ማሳት ይቻለዋልና መንግሥታት እርስ በርሳቸው ጦርነት እንዲያነሱ ማነሳሳት የእርሱ አላማ ነው።GCAmh 426.1

    ያልተዘጋጁ ነፍሳትን መከር ይሰበስብ ዘንድ ሰይጣን በአየር ንብረት [ማለትም አውሎ ነፋስ፣ ከባድ ዝናብ በመሳሰሉት] አማካኝነትም ይሰራል። የተፈጥሮን የቤተ ሙከራ ምስጢራት አጥንቷል፤ እግዚአብሔር እስከፈቀደበት ጥግ ድረስም ኃይሉን ሁሉ ተጠቅሞ የአየር ንብረትን ይቆጣጠራል። እዮብን እንዲያሰቃይ በተፈቀደለት ጊዜ [የፍየል/የበግ] መንጋዎቹን፣ ከብቶቹን፣ አገልጋዮቹን፣ ቤቶቹን፣ እንዲሁም ልጆቹን፣ እንዴት ባለ ፍጥነት፣ አንዱ ችግር ሌላውን እየተከተለ እየተጠራረጉ ጠፉ። ፍጥረታቱን የሚጠብቃቸው፣ ከአጥፊውም ኃይል የሚከልላቸው እግዚአብሔር ነው። ነገር ግን የክርስቲያኑ ዓለም ለያህዌ ሕግ ንቀትን አሳይቷል፤ እግዚአብሔርም አደርጋለሁ ብሎ የተናገረውን ያንኑ ያደርጋል፤ በረከቶቹን ከምድር ይወስዳል፣ በሕጉም ላይ ከሚያምፁ፣ እንደ እነርሱ እንዲያደርጉ ሌሎችን ከሚያስተምሩና ከሚያስገድዱ የጥበቃ እንክብካቤውን ያነሳል። እግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ በማይጠብቃቸው ሁሉ ላይ ሰይጣን ቁጥጥር አለው። የራሱን እቅድ ለማሳካት ለአንዳንዶቹ ያደላል፣ ያበለፅጋቸዋልም፤ በሌሎቹ ላይ ደግሞ መከራ በማምጣት፣ እንዲህ የሚያሰቃያቸው እግዚአብሔር እንደሆነ ያምኑ ዘንድ ሰዎችን ይመራቸዋል።GCAmh 426.2

    [ሰይጣን] በሽታዎቻቸውን ሁሉ መፈወስ የሚችል ታላቅ ሐኪም እንደሆነ አድርጎ ለሰው ልጆች ቢታይም ብዙ ሕዝብ የሚኖርባቸው ከተሞች እስኪወድሙና ምድረበዳ እስኪሆኑ ድረስ በሽታንና ጥፋትን ያመጣል። አሁን እንኳ፣ በዚህች ሰዓት በሥራ ላይ ነው። በየብስና በባህር አደጋዎችና ጥፋቶች፣ በታላላቅ አውዳሚ እሳቶች፣ በኃይለኛ ነፋስ (tornedo)ና በረዶ፣ በውሽንፍር፣ በጎርፎች፣ በአውሎ ነፋሳት፣ በውኃ ማዕበል፣ በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በእያንዳንዱ ሥፍራ በሺህ አይነት መንገድ ሰይጣን ኃይሉን እየተጠቀመ ነው። እየጎመራ ያለውን አዝመራ ጠራርጎ ይወስደውና ረሃብና ጭንቀት ይከተላል። ለአየሩ ገዳይ ብክለት ይሰጥና በሺዎች የሚቆጠሩ በወረርሽኙ ይረግፋሉ። እነዚህ ጥፋቶች የበለጠ ተደጋጋሚና አስከፊ እየሆኑ የሚሄዱ ናቸው። ውድመት በሰውና በእንስሳ ላይ ይሆናል። “ምድርም አለቀሰች ረገፈችም። ታላላቆች ደከሙ። ምድርም ከሚቀመጡባት በታች ረክሳለች፤ ሕጉን ተላልፈዋልና፣ ስርዓቱንም ለውጠዋልና፣ የዘላለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና” [ኢሳ 24÷4፣5]።GCAmh 426.3

    ከዚያም ለእነዚህ ክፋቶች ሁሉ መንስኤ የሆኑት እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ሰዎች ናቸው በማለት ታላቁ አታላይ ሕዝቡን ያሳምናል። የሰማይን ቁጣ የቀሰቀሰው መደብ፣ ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት መገዛታቸው ለሕጉ ተላላፊዎች የማያባራ ነቀፋ እንዲሆንባቸው ባደረጉት ላይ በመቀሰር፣ የችግሮቻቸው ሁሉ መንስኤ እንደሆኑ አድርገው ይከሷቸዋል። የእሁድ ሰንበትን በመጣስ ሰዎች እግዚአብሔርን እያስቆጡት እንደሆነ፣ ይህም ኃጢአት ከፍተኛ ጥፋት እንዳመጣና የእሁድ መከበር በጥብቅ አስገዳጅ እስኪሆን ድረስ ክፋቱ እንደማያቆም፣ አራተኛው ትዕዛዝ መከበር አለበት የሚሉ እነርሱ፣ ለእሁድ ያለውን አክብሮት የሚያጠፉ፣ (ሕዝቡ) መለኮታዊ ተቀባይነት እንዳያገኝና ወደ ዓለማዊው ብልጽግና እንዳይመለስ የሚያግዱ፣ የሕዝቡ ችግር ፈጣሪዎች እንደሆኑ ይታወጃል። በእንደዚህም ሁኔታ በእግዚአብሔር አገልጋይ ላይ በጥንት ጊዜ የተነሳው ክስ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ በጥሩ መሰረት ላይ ተገንብቶ እንደገና ይደገማል። “አሐብም ኤልያስን ባየው ጊዜ፦ እሥራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን? አለው። ኤልያስም፦ እሥራኤልን የምትገለባብጡ፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ትታችሁ በኣሊምን የተከተላችሁ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔ አይደለሁም አለው” [1ኛ ነገ 18÷17፣18]። የሕዝቡ ቁጣ በሐሰተኛ ክሶች ስለሚነሳሳ፣ ከሃዲዋ እሥራኤል በኤልያስ ላይ የተከተለችውን ተመሳሳይ መንገድ በእግዚአብሔር አምባሳደሮች ላይም ይከተላሉ።GCAmh 427.1

    በመናፍስታዊነት አማካኝነት የተገለጠው፣ ተዓምር አድራጊው ኃይል፣ ከሰው ይልቅ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ በሚመርጡት ላይ የተቃውሞ ተጽዕኖውን ያሳርፋል። ከመናፍስቱ የሚመጡ መልእክቶች፣ የምድሪቱ ሕግ እንደ እግዚአብሔር ሕግ ሆኖ እንዲከበር አዎንታዊ ማረጋገጫ በመስጠት፣ እሁድን የማይቀበሉት ከስህተታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እግዚአብሔር እንደላካቸው ይናገራሉ። በዓለም ላይ ስላለው ታላቅ ብልሹነት (ርኩሰት) በማዘን፣ የግብረገብነት ደረጃው ማሽቆልቆል ምክንያት የእሁድ መርከስ እንደሆነ አድርገው የኃይማኖታዊ መምህራንን ምስክርነት ይደግማሉ። ምስክርነታቸውን አንቀበልም በሚሉ ሁሉ ላይ የሚነሳሳው ቁጣ ታላቅ ይሆናል።GCAmh 427.2

    ሰይጣን በዚህ ከእግዚአብሔር ሕዝቦች ጋር በሚደረግ የመጨረሻው ጦርነት ላይ የሚተገብረው መርሃ ግብር በሰማይ በነበረው ታላቅ ተጋድሎ (ተቃርኖ) መክፈቻ የተጠቀመበት ነው። መገልበጡን እውን ለማድረግ በምስጢር እያንዳንዱን ጥረት እያዋለ ሳለ፣ የመለኮታዊውን አስተዳደር መጽናት ለማጎልበት እንደሚሻ ይናገር ነበር። ያሳካው ዘንድ እየለፋበት የነበረውን ያንኑ ሥራ፣ ቅዱሳን መላዕክት እንዳደረጉት አድርጎ ከሰሳቸው። የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይህንን ተመሳሳይ የማታለል መርሀ ግብር ያሳያል። ራስዋን ከእግዚአብሔር በላይ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ የእርሱን ሕግም ለመለወጥ እየጣረች ሳለ፣ የሰማይ ወኪል እንደሆነች ትናገራለች። በሮም አስተዳደር ስር፣ ለወንጌሉ ታማኝ በመሆናቸው የተገደሉ እነርሱ ክፉ አድራጊዎች ተብለው ተወገዙ፤ ከሰይጣን ጋር አንድ ማህበር ውስጥ እንደሆኑ ታወጀባቸው፤ በወቀሳ እንዲሸፈኑ፣ በሕዝቡም አይን፣ ለራሳቸውም እንኳ ሳይቀር እጅግ አሰቃቂ ወንጀለኞች ሆነው እንዲታዩ መገኘት የተቻለው ዘዴ ሁሉ ተግባር ላይ ውሏል። አሁንም እንደዚሁ ይሆናል። ሰይጣን የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያከብሩትን ለማጥፋት እየጣረ ሳለ፣ ሕግ ተላላፊዎች ተብለው እንዲከሰሱ፣ እግዚአብሔርን የሚያዋርዱ፣ በዓለም ላይም ቅጣት የሚያወርዱ ሰዎች ሆነው እንዲወነጀሉ ያደርጋቸዋል።GCAmh 427.3

    እግዚአብሔር ፈቃድንም ሆነ ህሊናን ፈጽሞ አያስገድድም። ሰይጣን ግን በቋሚነት የሚያዘወትረው መንገድ -ማታለል ያልቻላቸውን ሰዎች በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ - በጭካኔ ማስገደድ ነው። በፍርሃትም ይሁን በኃይል፣ ህሊናን ለመግዛትና ለራሱ ክብር ለማትረፍ ይጥራል። ይህንንም ለማሳካት በኃይማኖታዊና በመንግሥታዊ ባለስልጣናት በኩል በመሥራት፣ የእግዚአብሔርን ሕግ በመገዳደር የሰብአዊ ፍጡርን ሕግጋት አስገዳጅ እንዲያደርጉ ያንቀሳቅሳቸዋል።GCAmh 428.1

    የመጽሐፍ ቅዱስን ሰንበት የሚያከብሩ እነርሱ፣ የሕግና የሥርዓት ጠላቶች፣ የሕብረተሰብን ግብረገብነት ገደቦች በመሰባበር ሥርዓት አልበኝነትንና ብልሹነትን በማስከተል የእግዚአብሔርን ፍርድ በምድር ላይ የሚያስመጡ ተብለው ይወገዛሉ። ትክክለኛውን ድርጊት ልቅም አድርጎ ለመፈፀም የሚያደርጉት ጥንቃቄ፣ መንቻካነት፣ ግትርነትና የስልጣን ንቀት ይባላል። በመንግሥት ላይ ቅር የተሰኙ ተደርገው ይከሰሳሉ። የመለኮታዊውን ሕግ መጠይቆች (ግዴታዎች) የሚክዱ አገልጋዮች፣ በእግዚአብሔር እንደተቀቡ አድርገው ለመንግሥት ባለስልጣናት ስለመታዘዝ ያለውን ኃላፊነት ከመድረክ ያትታሉ። በሕግ አውጪ አዳራሾችና በፍርድ ቤቶች፣ ትዕዛዛት አክባሪዎች፣ ያልሆኑትን መልክ ተሰጥቶአቸው ይፈረድባቸዋል። የሚናገሩት ቃል የውሸት ቀለም ይቀባል፤ በኃሳቦቻቸው ላይ መጥፎ ቅንብር ይከናወንባቸዋል [ለማለት/ለማደረግ የፈለጉት ተጣሞ በመጥፎ ይተረጎምባቸዋል]።GCAmh 428.2

    የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት፣ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚደግፉትን ግልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መከራከሪያዎች አንቀበልም ሲሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቅመው እምነታቸውን መገልበጥ የማይቻላቸውን ሰዎች፣ ፀጥ ለማሰኘት ይሻሉ። ለእውነቱ ዓይናቸውን ቢያውሩም፣ አሁን እየያዙት ያለው መንገድ ግን የተቀረው የክርስቲያኑ ዓለም የሚሰራውን የማይሰሩትን፣ ለጳጳሳዊ ሰንበት መጠይቆችም እውቅና ባለመስጠት ሳያወላውሉ የሚቃወሙትን እነርሱን ወደ ማሳደድ የሚመራ አቅጣጫን ነው።GCAmh 428.3

    ሁሉም መደቦች እሁድን እንዲያከብሩ ለማድረግ ይቻላቸው ዘንድ ጉቦ ለመስጠት፣ ለማግባባት ወይም ለማስገደድ የቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ሹማምንት ህብረት ይፈጥራሉ። የመለኮታዊ ስልጣን እጦት በጨቋኝ አዋጆች ይደጎማል። ፖለቲካዊ ብልሹነት የፍትህን ፍቅርና ለእውነት ያለውን ክብር እያጠፋው ነው፤ በነፃዋ አሜሪካ ሳይቀር አስተዳዳሪዎችና ሕግ አውጪዎች፣ የሕዝብን ድጋፍ ለማትረፍ ሲሉ፣ እሁድ እንዲከበር የሚያስገድድ ሕግ እንዲወጣ ለሚነሳው ሕዝባዊ ጥያቄ እጅ ይሰጣሉ። እጅግ ከፍተኛ መስዋዕትነት ያስከፈለው የህሊና ነፃነት፣ ከዚያ ወዲያ አይከበርም። በቅርቡ በሚመጣው ቅራኔ ለነብዩ ቃላት ጥሩ ምሳሌ የምናይ ይሆናል፦ “ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁትን የየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ።” [ራዕይ 12÷17]።GCAmh 428.4