Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፴፪—የሰይጣን ወጥመዶች

    ከስድስት ሺህ ዓመታት በላይ ለሆነ ዘመን ሲካሄድ የቆየው፣ በክርስቶስና በሰይጣን መካከል የሚደረገው ታላቁ ተጋድሎ በቅርቡ ያበቃል። ክፉውም ጠላት፣ ክርስቶስ ለሰው ልጆች የሚያከናውነውን ተግባር ለማደናቀፍና ነፍሳትን በወጥመዱ ጠፍሮ ለመያዝ ጥረቱን እጥፍ ያደርጋል። ይከናወንለት ዘንድ የሚሻው ዓላማው፣ አዳኙ የሱስ የማማለድ ሥራውን እስኪደመድምና ለኃጢአት የሚደረግ መሥዋዕት እስኪያበቃ ድረስ ሰዎች በበደላቸው ሳይፀፀቱ በጨለማ ውስጥ ይዞ ማቆየት ነው።GCAmh 375.1

    ኃይሉን ለመቋቋም የሚደረግ የተለየ ጥረት ሲጠፋ፤ በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በዓለም ግዴለሽነት ሲያይል፣ እንዳሻው የሚመራቸውን ምርኮኞቹን የማጣት አደጋ የለበትምና ሰይጣን ስጋት አይገባውም። ነገር ግን ነፍሳት ዘላለማዊ ወደ ሆኑ ነገሮች ትኩረታቸውን ሲያዞሩና “እድን ዘንድ ምን ላድርግ?” [የሐዋ ሥራ 16÷30] በማለት መጠየቅ ሲጀምሩ የክርስቶስን ኃይል መሳ ለመሳ ለመግጠምና የመንፈስ ቅዱስን ተጽዕኖ ለመቀልበስ በመሻት ሥራ ላይ ይሰማራል።GCAmh 375.2

    መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው በአንድ ወቅት የእግዚአብሔር መላእክት በጌታ ፊት ለመቆም በመጡ ጊዜ ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ። [እዮብ 1÷6]። አመጣጡ ለዘመናት ንጉሥ ለመስገድ ሳይሆን በጻድቃን ላይ የራሱን የክፋት ዓላማ ለማሳካት ነበር። ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት ዛሬም ሰዎች እግዚአብሔርን ለማምለክ በሚሰበሰቡበት ስፍራ እርሱም ይገኛል። ምንም እንኳ ከእይታ ቢሰወር በአምልኮ ላይ የሚገኙትን ሰዎች አእምሮ ለመቆጣጠር በትጋት እየሰራ ነው። ልክ እንደ አንድ ብልሃተኛ የጦር መሪ እቅዶቹን በቅድሚያ ይነድፋል። የእግዚአብሔር አገልጋይ ቃሉን ሲመረምር ሲመለከት፣ ለሕዝቡ ሊቀርብ ያለውን መልእክት መዝግቦ ይይዛል። ከዚያም የማሳሳት ብልጠቱንና ብልሃቱን ሁሉ ተጠቅሞ ሁኔታዎችን በመቆጣጠር በዚያው ነጥብ ላይ [ሊሰበክ በሚዘጋጀው ሃሳብ ላይ]፣ እያሳሳታቸው ያሉት ሰዎች መልእክቱ እንዳይደርሳቸው ያደርጋል። ይህ የማስጠንቀቂያ መልእክት በይበልጥ የሚያስፈልገው ግለሰብ የእርሱ መገኘት ግድ ወደሆነበት የሥራ ጉዳይ እንዲሄድ ይገፋፋዋል፤ ወይም ደግሞ በሆነ ሌላ ምክንያት፣ ለህይዎት፣ የህይዎት ሽታ ይሆኑለት የነበሩትን ቃላት እንዳይሰማ ይከለከላል።GCAmh 375.3

    በተጨማሪም ሰይጣን የጌታ አገልጋዮች ሕዝቡን ስለከበበው መንፈሳዊ ጨለማ ሲጨነቁ ይመለከታል። በእግዚአብሔር መለኮታዊ ፀጋና ኃይል የግዴለሽነት፣ የደንታቢስነትና የስንፍና መተት እንዲሰበር ከልባቸው የሚያደርሱትንም ጸሎት ያደምጣል። ከዚያም በኋላ በታደሰ ቅንአት የጥበብ ሥራውን በትጋት ያቀላጥፋል። ሰዎችን ሆዳቸው አምላካቸው እንዲሆን፣ ወይም በሌላ ራሳቸውን በሚያረኩበት ነገር እንዲጠመዱ በመፈተን ስሜቶቻቸው እንዲደነዝዙ በማድረግ ይማሩዋቸው ዘንድ እጅግ የሚያስፈልጓቸውን እነዚያን ነጥቦች ሳይሰሙ እንዲቀሩ ያደርጋቸዋል።GCAmh 375.4

    ጸሎትንና ቃሉን መመርመርን ቸል ይሉ ዘንድ መምራት የሚችላቸው እነርሱ በጥቃቶቹ እንደሚሸነፉ ሰይጣን ጠንቅቆ ያውቃል። እናም አእምሮን [በብቸኝነት] ለመያዝ የሚቻለውን ሁሉ ዘዴ ይፈጥራል።GCAmh 375.5

    እውነትን ለማወቅ ከመጣር ይልቅ ከሚቃረኑአቸው ከእነርሱ የባህርይ እንከንን ወይም የእምነት ስህተትን መፈለግ ኃይማኖታቸው (ሞያቸው) ያደረጉ እግዚአብሔር-መሰል ነን ባይ መደብ ሁልጊዜም አሉ። እንደነዚህ ያሉቱ የሰይጣን ቀኝ እጅ ረዳቶች ናቸው። የወንድሞች ከሳሾች ጥቂቶች አይደሉም፤ እግዚአብሔር በሚሰራበትና አገልጋዮቹም እውነተኛ ስግደት ለእርሱ በሚያቀርቡበት ሰዓት፣ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ንቁ ይሆናሉ። እውነትን በሚወዱና በሚታዘዙ ቃላትና ተግባራት ላይ የሐሰት ቀለም ይቀባሉ። ልባዊ፣ ቀናኢና ራሳቸውን የካዱ የክርስቶስን አገልጋዮች፣ የተታለሉ ወይም አታላይ እንደሆኑ አድርገው ያቀርቧቸዋል። ልምድ በሌላቸው አእምሮዎች ዘንድ ያልተጨበጠ ወሬ በማናፈስ ጥርጥርን ለማነሳሳት የእያንዳንዱዋን እውነተኛና ክቡር ሥራ ምክንያት ማጣመም ተግባራቸው ነው። ንፁህና ጽድቅ የሆነው ነገር ርኩስና አሳሳች መስሎ እንዲታይ ለማድረግ ሊታሰብ በሚችል መንገድ ሁሉ ይጥራሉ።GCAmh 375.6

    ነገር ግን የእነርሱን ማንነት በተመለከተ ማንም ሊታለል አይገባውም። የማን ልጆች እንደሆኑ፣ የማንን ፈለግ እንደሚከተሉና የማንን ተግባር እንደሚፈፅሙ በቀላሉ መለየት ይቻላል። “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።” [ማቴ 7÷16]። መንገዳቸው፣ መርዘኛ፣ ስም አጥፊና “የወንድሞቻችን ከሳሽ” [ራእይ 12÷10] ከሆነው ከሰይጣን መንገድ ጋር ይመሳሰላል።GCAmh 376.1

    እርሱ ሊያጠፋ ካሰባቸው ሰዎች የተለያየ ምርጫና ችሎታ ጋር ገጣሚ እንዲሆኑ ተደርገው የተዘጋጁ ኑፋቄዎችን በማደል፣ ታላቁ አታላይ የተገኘውን ማንኛውንም አይነት የስህተት ትምህርት በማቅረብ ነፍሳትን ለማጥመድ ዝግጁ የሆኑ አያሌ ወኪሎች አሉት። ቅንነት የጎደላቸው፣ ያልተለወጡ፣ ጥርጥርንና አለማመንን የሚያደፋፍሩ፣ የእግዚአብሔር ሥራ ወደፊት እንዲገፋና እነርሱም አብረው እንዲገሰግሱ የሚሹትን ሁሉ የሚያሰናክሉ አባላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ማምጣት እቅዱ ነው። ብዙዎች በእግዚአብሔርም ሆነ በቃሉ ላይ እውነተኛ (ተጨባጭ) እምነት ሳይኖራቸው ከተወሰኑ የእውነት መርሆች ጋር ይስማሙና ክርስቲያን ተብለው ይደበለቃሉ፤ በእንዲህም ሁኔታ የስህተት ትምህርቶቻቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዎች እንደሆኑ አድርገው ማስተዋወቅ እንዲችሉ ይደረጋሉ።GCAmh 376.2

    ሰዎች ምንም ነገር ቢያምኑ ውጤቱ ለውጥ የለውም የሚለው አቋም እጅግ ውጤታማ ከሆኑት የሰይጣን ማታለያ ዘዴዎች አንዱ ነው። እውነት፣ በፍቅር የሚወስዳትን፣ የተቀባዩን ነፍስ እንደምትቀድስ ሰይጣን ያውቃል። ስለዚህም የሀሰት ፅንሰ ሀሳቦችንና ተረታ ተረቶችን ሌላ ወንጌል አድርጎ ለመተካት ሳያሰልስ እየሰራ ነው። ከመጀመሪያው ጀምሮ የእግዚአብሔር ባሪያዎች የሀሰት አስተማሪዎችን ሲታገሉአቸው የኖሩት ጨካኝ ስለነበሩ ብቻ ሳይሆን ለነፍስ አደገኛ የሆኑ ስህተቶችን ያስተምሩም ስለነበር ጭምር ነው። ኤልያስ፣ ኤርምያስና ጳውሎስ፣ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ቃል የሚያርቁትን ያለ ፍርሃት በጥብቅ ተቃውመዋቸዋል። ትክክለኛውን ኃይማኖት መያዝ አላስፈላጊ እንደሆነ አድርጎ የሚያይ ልል አስተሳሰብ በእነዚያ ቅዱሳን የእውነት ጠባቂዎች አእምሮ ስፍራ አላገኘም።GCAmh 376.3

    በክርስትናው ዓለም የሚታዩት ግልጽ ያልሆኑና ምናባዊ (ተጨባጭነት የሌላቸው) የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጓሜዎች እንዲሁም እምነትን በተመለከተ በክርስቲያኑ ዓለም የሚገኙ፣ እርስ በራሳቸው የሚጣረሱ አያሌ ፅንሰ ሀሳቦች ሰዎችን በማደናገር እውነትን እንዳያስተውሉ ለመከልከል የተዘጋጁ የታላቁ ባላጋራችን ሥራዎች ናቸው። በክርስትናው ዓለም ባሉ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ላለው አለመጣጣምና ክፍፍል ዋነኛው መንስኤ ባብዛኛው፣ ተወዳጅ ፅንሰ ሀሳብን ይደግፍ ዘንድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ግብ ግብ የመግጠም የተንሰራፋ ልማድ ስላለ ነው። የፈቃዱን እውቀት ያገኙ ዘንድ በተዋረደ ልብ የእግዚአብሔርን ቃል በጥንቃቄ በማጥናት ፈንታ፣ ብዙዎች፣ ወጣ ያለ ወይም አዲስ ነገር ለማግኘት ብቻ ይጥራሉ።GCAmh 376.4

    የስህተት አስተምህሮዎችን ወይም ኢ-ክርስቲያናዊ ምግባሮችን ለመደገፍ ሲሉ፣ አንዳንዶች፣ የተወሰነውን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ከዐውደ ምንባቡ [ከምዕራፉ አጠቃላይ ትርጉም የተለየ ይዘት] ነጥለው፣ የቀረው ንባብ ክፍል ፈጽሞ የተለየ ትርጉም ያለው ሆኖ ሳለ፣ ምናልባትም የአንዲት ጥቅስን ክፋይ ብቻ ወስደው የእነርሱን ሃሳብ እንደምትደግፍ አድርገው ያቀርባሉ። በእባቡ (በዲያብሎስ) ብልሃት ለሥጋ ምኞታቸው እንዲስማማ ታስቦ በተቀናጀ የንግግር ቁርጥራጭ ጀርባ ራሳቸውን ይመሽጋሉ። በእንዲህ አይነት ሁኔታ ብዙዎች ሆን ብለው የእግዚአብሔርን ቃል ያጣምማሉ። ጥልቅ የማለም ችሎታ (active imagination) ያላቸው ሌሎች ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ምስሎችና ተምሳሌቶች ወስደው፣ የእግዚአብሔር ቃል ራሱን በራሱ የሚፈታ መሆኑ ሳይገዳቸው፣ የራሳቸውን ቅዠት (ምናባዊ ምኞት) እንዲስማሙ አድርገው ይተረጉሙና እንግዳ አመለካከቶቻቸውን እንደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች አድርገው ያስተምራሉ።GCAmh 377.1

    የቃሉ ጥናት ያለ ፀሎት፣ ያለ ትህትና እንዲሁም ለመማር ፈቃደኛ ባልሆነ መንፈስ በሚከናዎንበት ጊዜ፣ ፈጽሞ ቀላልና ግልጽ የሆኑትም ሆነ እጅግ ውስብስብ የሆኑት ምንባቦች ከእውነተኛ ትርጉማቸው ይጣመማሉ። መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት የተቀደሱ እውነቶቹንም ለራሳቸው የመረዳት ዕድልን ነፍገዋቸው ሳለ፣ ጳጳሳዊ መሪዎች እንደነዚህ ያሉትን፣ አላማቸውን በደንብ የሚያሳኩትን ምንባቦች መርጠው፣ ለራሳቸው እንደሚስማማቸው ተርጉመው፣ ለሕዝቡ ያቀርቧቸዋል። ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ራሱ እንደሚነበበው፣ ለሰዎች ሊሰጥ ይገባል። ሰዎች መጠነ ሰፊ መዛባት የተካሄደበት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከሚኖራቸው፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት ከናካቴው ባያገኙ ይሻላቸዋል።GCAmh 377.2

    ከፈጣሪያቸው ፈቃድ ጋር ለመተዋወቅ ለሚሹ ሁሉ መመሪያ ይሆን ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስ ተነደፈ። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የትንቢትን እርግጠኛ ቃል ሰጠ፤ መላእክት፣ ራሱ ክርስቶስ ጭምር በቅርቡ ሊሆኑ ያላቸውን ነገሮች ይገልጡ ዘንድ ወደ ዳንኤልና ወደ ዮሐንስ መጡ። እነዚያ ድነታችንን የሚመለከቱ አስፈላጊ ጉዳዮች ምስጢር ሆነው ይቀሩ ዘንድ አልተተውም። በቅንነት እውነትን ለማወቅ የሚሻውን ለማደናገርና ለማሳሳት እንዲችሉ ሆነው አልተገለጹም። በነቢዩ በዕንባቆም አማካኝነት ጌታ እንዲህ ብሏል፣ “አንባቢው ይፈጥን ዘንድ….ራዕዩን ጻፍ፣ በጽላት ላይ ግለጠው [Write the vision and make it plain….]” [ዕንባ 2÷2]። በፀሎት ልብ ውስጥ ሆነው ለሚያጠኑት ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል ግልጽ ነው። እያንዳንዱዋ እውነተኛ ታማኝ ነፍስ ወደ እውነት ብርሐን ትመጣለች። “ብርሐን ለጻድቃን ወጣ” [መዝ 97÷11]። እናም፣ አባላቶችዋ፣ እንደተሰወረ መዝገብ እውነትን ከልብ የሚፈልጉ ካልሆኑ በስተቀር የትኛዋም ቤተ ክርስቲያን በቅድስና ወደፊት አትራመድም።GCAmh 377.3

    እርሱ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ያለፋታ ዘወትር በመሥራት ላይ ያለ ቢሆንም፣ ነፃ አስተሳሰብ በሚለው ጨኸት ምክንያት ሰዎች ለባለጋራቸው መሳሪያዎች የታወሩ ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስን በፍጡር ግምቶች መተካት ሲሳካለት፣ የእግዚአብሔር ሕግ ወደ ጎን ይገፈተራል፣ ነፃ ነን ሲሉ ሳለ አብያተ ክርስቲያናት በኃጢአት ባርነት ውስጥ ይሆናሉ።GCAmh 377.4

    ለብዙዎች ሳይንሳዊ ምርምር ርግማን ሆኖአል። ለሳይንስና ለስነ-ጥበብ አዳዲስ ግኝቶች፣ በዓለም ላይ የብርሐን ጅረት እንዲፈስ እግዚአብሔር ፈቅዷል፤ ሆኖም የእውቀት ቁንጮዎች እንኳ በምርምራቸው በእግዚአብሔር ቃል ካልተመሩ የሳይንስንና የመገለጥን [የመጽሐፍ ቅዱስን] ዝምድና ለመመርመር በሚያደርጓቸው ሙከራዎች ግራ ይጋባሉ።GCAmh 378.1

    ስለቁሳዊና ስለመንፈሳዊ፣ ስለሁለቱም፣ ያለው የሰብአዊ ፍጡር እውቀት ከፊልና ፍጹም ያልሆነ ነው። ስለሆነም ብዙዎች የሳይንስ አመለካከታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ገለጻዎች ጋር ማጣጣም ይሳናቸዋል። ብዙዎች ተራ ፅንሰ ሀሳቦችንና መላምቶችን እንደ ሳይንሳዊ እውነቶች አድርገው ይቀበሉና “በውሸት ሳይንስ ተብለው በሚጠሩ” ትምህርቶች አማካኝነት የእግዚአብሔር ቃል መፈተን እንዳለበት ያስባሉ። ፈጣሪና ሥራዎቹ ከእነርሱ መረዳት በላይ ናቸው፤ እነዚህንም በተፈጥሮ ሕግጋት አማካኝነት ማብራራት ባለመቻላቸው ምክንያት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እምነት የማይጣልበት ተደርጎ ይታያል። የብሉና የሐዲስ ኪዳናትን መዛግብት አስተማማኝነት የሚጠራጠሩ እነርሱ እንዲያውም ባብዛኛው አንድ እርምጃ ጨምረው የእግዚአብሔርን መኖር ይጠራጠራሉ፤ ዘላለማዊ ኃይልም ተፈጥሮአዊ ክስተት እንደሆነ አድርገው ይቆጥራሉ። መልህቃቸውን ከለቀቁ በኋላም በከሃዲነት ቋጥኝ ላይ በፍለጋ እንዲቅበዘበዙ ይተዋሉ።GCAmh 378.2

    እንዲህም ብዙዎች ከእምነት ይስታሉ፤ በዲያብሎስም ይታለላሉ። የሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው በላይ ጠቢባን ይሆኑ ዘንድ ጥረዋል፤ ሰብዓዊ ፍልስፍናም በለዘላለማዊ ዘመናት [እንኳ] ፈጽሞ የማይገለጹትን ምስጢራት ለማግኘትና ለማብራራት ሲሞክር ኖሯል። ሰዎች፣ ስለ ራሱና ስለ አላማዎቹ እግዚአብሔር የገለጠውን ቢመረምሩና ቢያስተውሉ፣ የያህዌን ክብር፣ ግርማና ኃይል የሚያዩበት ሁኔታ፣ የራሳቸውን መናኛነት ተገንዝበው ለራሳቸውና ለልጆቻቸው በተገለጠው ረክተው እንዲቀመጡ ያደርጋቸው ነበር።GCAmh 378.3

    እግዚአብሔር ስላልገለጠውና እንድናስተውለውም ስለማይሻው ነገር በማሰስና በመገመት የሰውን አእምሮ መያዝ ከሰይጣን ማታለያዎች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ነው። ሉሲፈር በሰማይ የነበረውን ስፍራ ያጣው በእንዲህ ሁኔታ ነበር። የእግዚአብሔር ምክሮች(የአላማው ሚስጥራት) በሙሉ ስላልተገለጹለት እርካታ-ቢስ ሆነ፤ በተሰጠው፣ ምጡቅ በሆነው ደረጃው፣ የራሱን ሥራ በተመለከተ የተገለጠውን ነገር ሙሉ ለሙሉ ትኩረት ነፈገው። ተመሳሳዩን እርካታ ማጣት በስሩ ባሉት መላእክት ላይ በማነሳሳት፣ ውድቀታቸውን እውን አደረገው። አሁን በዚያው ተመሳሳይ መንፈስ የሰዎችን አእምሮ መሙላት ይፈልጋል፤ የእግዚአብሔርን ቀጥተኛ ትእዛዛትም እንዲንቁ ሊመራቸው ይጥራል።GCAmh 378.4

    ግልጽ የሆኑትንና የሰሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ለመቀበል ፈቃደኞች ያልሆኑ እነርሱ ንቃተ ህሊናን ጸጥ የሚያሰኙ አስደሳች ተረቶችን ያለማቋረጥ ይፈልጋሉ። የሚቀርቡት አስተምህሮዎች መንፈሳዊነታቸው፣ ራስን መካዳቸውና ራስን ማዋረዳቸው አናሳ በሚሆንበት መጠን ቅቡልነታቸውም በዛው ልክ ይጨምራል። እነዚህ ሰዎች ሥጋዊ ፍላጎቶቻቸውን ያረኩ ዘንድ የአእምሮ ኃይላትን ያቆረቁዛሉ፣ በንስሐ ውስጥ በሆነች ነፍስ፣ ለመለኮት ምሪትም ከልብ በሚደረግ ጸሎት መጽሐፍ ቅዱስን እንዳይመረምሩ በራሳቸው ጥበብ በኩራት ተወጥረው ከአጉል እምነት መከለያ የላቸውም። የልብን ምኞት ለማቅረብ ሰይጣን ዝግጁ ነው፤ በእውነት ምትክም ማጭበርበሪያዎቹን ያሳልፋቸዋል። የጳጳሳዊው ኃይል በሰዎች አእምሮ ላይ ጉልበት ያገኘው በእንዲህ ሁኔታ ነበር፤ መስቀል ያለው በመሆኑ ምክንያት እውነቱን ባለመቀበል፣ ፕሮቴስታንቶችም ተመሳሳዩን መንገድ እየተከተሉ ነው። ከዓለም ጋር ልዩነት እንዳይኖራቸው በማሰብ ምቾትንና መርሐ-ግብርን ያጠኑ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል ቸል የሚሉ እነርሱ በኃይማኖታዊ እውነት ፈንታ ውጉዝ ኑፋቄ እንዲቀበሉ ይተዋሉ። እያንዳንዱ ሊታሰብ የሚችል የስህተት አይነት ሁሉ፣ እውነትን በፈቃዳቸው እምቢ ባሉት ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። አንዱ ማታለያ በሰቆቃ የሚመለከት እርሱ ሌላ ለመቀበል ዝግጁ ይሆናል። “ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ” ስለሚላቸው መደቦች ጳውሎስ ሲናገር “በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል” [2ኛ ተሰሎ 2÷10-12] ይላል። እንደዚህ አይነት ማስጠንቀቂያ በፊታችን ሆኖ እያለ ስለምንቀበላቸው አስተምህሮዎች ጥንቁቅ እንሆን ዘንድ ያስፈልገናል።GCAmh 378.5

    እጅግ ውጤታማ ከሆኑት የታላቁ አታላይ መሳሪያዎች መካከል የመናፍስታዊነት አታላይ ትምህርቶችና ሐሰተኛ ተዓምራቶች ይገኙበታል። እንደ የብርሐን መልአክ ሆኖ ባልተጠረጠረበት ስፍራ መረቦቹን ይዘረጋል። መረዳት ይቻላቸው ዘንድ ሰዎች የእግዚአብሔርን መጽሐፍ ከልባዊ ፀሎት ጋር ቢያጠኑ፣ ሐሰተኛ አስተምህሮዎች ይቀበሉ ዘንድ በጨለማ አይተውም። ነገር ግን እውነትን አንቀበልም ሲሉ ግን የመታለያ ታዳኝ ይሆናሉ።GCAmh 379.1

    ሌላኛው አደገኛ ስህተት ክርስቶስ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት ሕያው እንዳልነበረ በመናገር መለኮትነቱን የሚክደው አስተምህሮ ነው። ይህ ጽንሰ ኃሳብ መጽሐፍ ቅዱስን እናምናለን በሚል ሰፊ መደብ በአዎንታ ተቀባይነት አግኝቷል፤ ነገር ግን ይህ፣ አዳኛችን ከአባቱ ጋር ስላለው ግንኙነት፣ ስለእርሱ መለኮታዊ ባህርይና ስለ ቀደምት-ሕያውነቱ በተመለከተ የተናገራቸውን፣ ፍንትው ያሉትን ንግግሮቹን በቀጥታ የሚቃረን ነው። እጅግ ምክንያት አልባ በሆነ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስን በማጣመም ካልሆነ መስተቀር ይህ ጉዳይ ሊሰላሰል አይችልም። ሰው ስለድነት ሥራ ያለውን መረዳት ዝቅ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር እንደተሰጠ መገለጥ አድርጎ መጽሐፍ ቅዱን እንዳይቀበለው እምነትን ያኮስሳል። ይህ የበለጠ አደገኛ ሲያደርገው፣ ለመጋፈጥም ደግሞ አስቸጋሪ ያደርገዋል። መለኮታዊው መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስን መለኮትነት አስመልክቶ የሚሰጠውን ምስክርነት ሰዎች አንቀበልም ካሉ፣ ጉዳዩን አንስቶ ከእነርሱ ጋር መከራከር ከንቱ ነው፤ ምክያቱም፣ መከራከሪያው ምኑንም ያህል አሳማኝ ቢሆን እነርሱን አያሳምናቸውም። “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።” [1ኛ ቆሮ 2÷14]። ይህንን ስህተት የተቀበለ ማንም ሰው የክርስቶስ ባህርይ ወይም ተልዕኮ፣ ወይም እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ስላለው ታላቅ የማዳን እቅድ ትክክለኛ መረዳት ሊኖረው አይችልም።GCAmh 379.2

    ሌላኛው ረቂቅና ተንኮለኛ ስህተት ደግሞ፣ ሰይጣን ግላዊ ማንነት (አካላዊ ሕያውነት) ያለው ፍጡር አይደልም፣በመጽሐፍ ቅዱስም ስሙ የተጠቀሰው የሰዎችን ክፉ ሐሳብና ምኞት እንዲሁ ለመወከል ነው የሚለው፣ በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣው እምነት ነው።GCAmh 379.3

    ከተወዳጅ መድረኮች በስፋት የሚያስተጋባው፣ የክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ማለት እያንዳንዱ ሰው በሚሞትበት ጊዜ ጌታ ወደሟቹ የሚመጣበት ነው የሚለው አስተምህሮ፣ በሰማይ ደመና የሚከናወነውን አካላዊ መገለጡን ከሰዎች አዕምሮ የማግለያ መሳሪያ ነው። ለዓመታት ሰይጣን እንዲህ ሲል ቆይቶአል፣ “እነሆ በእልፍኝ ነው [በተሰወረ ክፍል ውስጥ ነው/He is in the secret chambers]” [ማቴ 24÷23-26]፤ ይህንን ማታለያ በመቀበልም ብዙ ነፍሳት ጠፍተዋል።GCAmh 380.1

    እንደገናም፣ ዓለማዊ ጥበብ፣ ፀሎት አስፈላጊ እንዳልሆነ ያስተምራል። የሳይንስ ሰዎች፣ ለፀሎት እውን መልስ ሊኖር አይችልም፣ ይህ ሕግን የሚጥስ ተዓምር ይሆናል፣ ተዓምራት የሚባሉ ነገሮች ደግሞ የሉም ይላሉ። ዓለማት ቋሚ በሆኑ ሕጎች እንደሚተዳደር፣ እግዚአብሔርም እነዚህን ሕጎች የሚፃረር አንዳች ነገር እንደማያደርግ ይናገራሉ። የመለኮታዊ ሕጎች አሰራር መለኮታዊ ነጻነትን እንደሚነፍግ አድርገው በእንዲህ ሁኔታ እግዚአብሔር በራሱ ሕጎች የተጠፈረ እንደሆነ አድርገው ያቀርቡታል። እንደዚህ አይነቱ ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት ጋር የሚቃረን ነው። በክርስቶስና በሐዋርያቱ ተዓምራት አልተከናወኑም? ያው ሩኅሩኅ አዳኝ፣ ሕያው ነው፣ በሰዎች መካከል እየታየ ሲመላለስ እንደነበረበት ጊዜ ሁሉ ዛሬም በእምነት የሚደረግን ፀሎት ለመስማት ዝግጁ ነው። ተፈጥሮአዊው (the natural) ከተፈጥሮ በላይ ከሆነው (the supernatural) ጋር ይተባበራል። ባንጠይቀው ኖሮ የማይሰጠንን፣ በእምነት ለተደረገ ፀሎት መልስ አድርጎ መስጠት የእግዚአብሔር እቅድ አካል ነው።GCAmh 380.2

    በክርስቲያኑ ዓለም አብያተ ክርስቲናት ዘንድ እየተስፋፉ ያሉ የስህተት አስተምህሮዎችና ምናባዊ ሐሳቦች ቁጥር ስፍር የላቸውም። በእግዚአብሔር ቃል ከተተከሉት የወሰን ምልክቶች መካከል አንዱን ማስወገድ የሚያመጣውን የክፋት ውጤት መገመት አይቻልም። ይህንን ለማድረግ የሚደፍሩ እነርሱ አንድ እውነት ብቻ አንቀበልም ብለው የመቅረታቸው ዕድል በጣም የጠበበ ነው [በአንድ ብቻ አይቆሙም፤ በርካታ እውነቶችን ወደመካድ ይመራሉ]። የለየላቸው ከኃድያን እስኪሆኑ ድረስ አብዛኛዎቹ የእውነትን መርህ፣ አንዱን በሌላው እያስከተሉ፣ ወደ ጎን የመገፍተሩን ተግባር ይቀጥሉበታል።GCAmh 380.3

    በብዛት ተቀባይነት ያላቸው የስነ መለኮት ትምህርት ስህተቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች ይሆኑ የነበሩትን ብዙ ነፍሳት ወደ ጥርጥር ነድተዋቸዋል። አንድ ሰው ስለ ፍትህ፣ ስለ ምሕረትና ስለ ቸርነት ካለው ማስተዋል ጋር አብረው የማይሄዱትን (ስሜቱን የሚጎዱትን) አስተምህሮዎች መቀበል የማይቻለው ነው፤ እነዚህ [ስህተት ያለባቸው አስተምህሮዎች] ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች እንደሆኑ ተደርገው ስለሚቀርቡለት፣ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብሎ መቀበል እምቢ ይላል።GCAmh 380.4

    ይህም ሰይጣን ማሳካት የሚፈልገው አላማው ነው። በእግዚአብሔርና በቃሉ ላይ ያለውን መተማመን እንደማውደም የሚመኘው ሌላ ነገር የለም። የተጠራጣሪዎች ታላቅ የጦር ሰራዊት መሪ ሆኖ ይቆማል፣ ነፍሳትንም አደናግሮ ወደ እርሱ ጎራ ለማሰለፍ ኃይሉን ሁሉ ይጠቀማል። መጠራጠር እንደ ፋሽን እየተቆጠረ መጥቷል። ፀሐፊውን (ጌታን) በተጠራጠረበት በዚያው ምክንያት፣ የእግዚአብሔርን ቃልም በጥርጥር የሚመለከት ሰፊ መደብ አለ - ምክንያቱም ኃጢአትን ይገስጻል፣ ያወግዛልምና። መጠይቆቹን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ያልሆኑ እነርሱ ስልጣኑን ለመገልበጥ ይጥራሉ። ከቃሉ ወይም ከስብከቱ ስህተት ለማግኘት ብቻ በማሰብ መጽሐፍ ቅዱስን ያጠናሉ፣ ወይም ከተቀደሰው መድረክ ትምህርቱን ይሰማሉ። ሃላፊነታቸውን ቸል ለማለታቸው ሰበብ ለማግኘት ወይም ትክክለኛ እንደሆኑ አድርገው ራሳቸውን ለማሳመን ሲሉ ከኃድያን የሚሆኑ ጥቂት አይደሉም። ሌሎች ደግሞ ከኩራትና ከስንፍና የተነሳ የጥርጥር መርሆዎችን ይተገብራሉ። ቀለል ያለ ነገርን አፍቃሪዎች (ጭንቅ የማይፈልጉ) ስለሆኑ፣ ጥረትና ራስን መካድን የሚጠይቀውን፣ ክብር ያለውን ምንም ነገር በማሳካት ራሳቸውን ለማስጠራት ስለማይችሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በመኮነን የላቀ ጥበብ ባለቤትነትን ዝና ለማትረፍ ያልማሉ። በመለኮታዊ ጥበብ መገለጥ ያልታወደው ውስን አእምሮ ለማስተዋል አቅመ-ቢስ የሆነበት ብዙ ነገር አለ፤ በመሆኑም ለማውገዝ አጋጣሚ ያገኛሉ። ባለማመን፣ በመጠራጠርና በእምነት አጉዳይነት ጎራ መቆም መልካም (የላቀ የግብረ ገብነት ደረጃ) እንደሆነ የሚሰማቸው የሚመስሉ ብዙዎች አሉ። በሃቀኝነት በሚመስል ታይታ ስር ግን እንደዚህ አይነት ሰዎች በራስ መተማመንና በኩራት እንደሚገፉ የሚገለጥ ይሆናል። ሌሎችን የሚያደናግር አንዳች ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማግኘታቸው ሐሴት የሚያደርጉ ብዙዎች አሉ። አንዳንዶች ክርክር ከማፍቀራቸው የተነሳ ብቻ መጀመሪያ በስህተት ጎን ሆነው ይኮንናሉ፣ ምክንያትም ያቀርባሉ። እንዲህ በማድረጋቸው በወፍ አጥማጁ ወጥመድ ውስጥ ራሳቸውን እየተበተቡ እንደሆነ አያስተውሉም። ነገር ግን እምነተ-ቢስነትን በአደባባይ ከመሰከሩ በኋላ፣ ያንኑ አቋም ይዘው መጽናት እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። በዚህም ሁኔታ እግዚአብሔርን ከማይመስሉ ጋር ያብራሉ፣ የገነትን በርም በራሳቸው ላይ ይዘጋሉ።GCAmh 380.5

    [ቃሉ] መለኮታዊ ባህርይ ያለው ለመሆኑ እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ በቂ ማስረጃ ሰጥቷል። ድነታችን የሚመለከቱት ታላላቅ እውነቶች በግልጽ ቀርበዋል። በእውነት ለሚፈልጉት ሁሉ እንደሚሰጥ ቃል በተገባው በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ እያንዳንዱ ሰው እነዚህን እውነቶች ለራሱ መረዳት ይችላል። እምነታቸውን ያሳርፉበት ዘንድ ጠንካራ መሰረት እግዚአብሔር ለሰዎች ተጥቷል።GCAmh 381.1

    ሆኖም የዘላለማዊውን አምላክ እቅዶችና ዓላማዎች ሙሉ ለሙሉ ይረዳ ዘንድ ውስኑ የሰዎች አእምሮ ብቁ አይደለም። በመመርመር እግዚአብሔርን ፈጽሞ ልናውቀው አይቻለንም። ግርማዊነቱን የጋረደበትን መጋረጃ ድንበሩን በገፋ እጅ (በድፍረት) ልንገልጠው መሞከር የለብንም። ሐዋርያው እንዲህ ይናገራል፣ “ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም” [ሮሜ 11÷33]። መጠን የለሽ ፍቅርና ምሕረት ውስን ካልሆነ ኃይል ጋር እንደተጣመረ እናውቅ ዘንድ ከእኛ ጋር ያለውን አሰራሩን፣ ድርጊቱንም የሚመራው፣ ሀሳቡ ምን እንደሆነ ያህል ብቻ እንገነዘባለን። በሰማይ ያለው አባታችን ሁሉንም ነገር በጥበብና በጽድቅ ያስተዳድራል፤ በክቡር መገዛት ልንሰግድለት ይገባል እንጂ እርካታ-ቢሶችና ተጠራጣሪዎች መሆን የለብንም። ማወቃችን ለመልካም የሚሆንልንን ያህል እርሱ አላማዎቹን ይገልጽልናል፤ ከዚያ በተረፈ ሁሉን ቻይ የሆነውን እጅ፣ በፍቅር የተሞላውን ልብ መታመን ግድ ይለናል።GCAmh 381.2

    እግዚአብሔር ለእምነት በቂ ማስረጃ የሰጠ ቢሆንም ላለማመን ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን በሙሉ ግን ፈጽሞ አያስወግድም። ጥርጥሮቻቸውን ለመስቀል ማንጠልጠያዎች የሚፈልጉ ሁሉ ያገኟቸዋል። እያንዳንዱዋ ተቃውሞ እስክትወገድ፣ ለመጠራጠርም ምንም ዕድል እንዳይኖር እስኪሆን ድረስ የእግዚአብሔርን ቃል ለመቀበልና ለመታዘዝ እምቢ የሚሉ እነርሱ ፈጽመው ወደ ብርሐኑ አይመጡም።GCAmh 381.3

    እግዚአብሔርን አለማመን፣ ከእርሱ ጋር በጠላትነት ላይ ያለው ያልተለወጠው ልብ ተፈጥሮአዊ ውጤት ነው። ሆኖም እምነት በመንፈስ ቅዱስ ይበረታታና በሚኮተኮተው መጠን ብቻ ይፋፋል። ያለ ቆራጥ ጥረት ማንም ሰው በእምነት ጠንካራ መሆን አይችልም። አለማመን ሲበረታታ እየጠነከረ ይሄዳል፤ ሰዎችም እምነታቸውን አጽንቶ ለማቆም እግዚአብሔር በሰጣቸው ማስረጃዎች ተደግፈው በመኖር ፈንታ ለመጠየቅና ለማማረር ለራሳቸው ፈቀድ ከሰጡ ጥርጥሮቻቸው በቀጣይነት የበለጠ እየተረጋገጡላቸው ይሄዳሉ።GCAmh 382.1

    የእግዚአብሔርን ተስፋዎች የሚጠራጠሩ፣ በፀጋውም ማረጋገጫዎች ላይ እምነት የሌላቸው እነርሱ ጌታን እያዋረዱ ናቸው። ተጽዕኖአቸውም ሌሎችን ወደ ክርስቶስ በመሳብ ፈንታ፣ ከእርሱ እንዲርቁ ያደርጋቸዋል። ጽልመት የተላበሰ ረጅምና ሰፋፊ ቅርንጫፎቻቸውን አንሰራፍተው በመዘርጋት ወደ ሌሎች እጽዋት የፀሐይ ብርሐን እንዳይደርስ በመከለል በሚቀዘቅዘው ጥላ ሥር ተልፈስፍሰው እንዲጎብጡና እንዲሞቱ የሚያደርጉ ምርት-አልባ ዛፎች ናቸው። የእነዚህ ሰዎች የእድሜ ልክ ሥራ የራሳቸው የማያባራ የተቃውሞ ምስክር ሆኖ ይገለጥባቸዋል። የተትረፈረፈ ምርት ከመስጠት የማይዘል የጥርጥር ዘር እየዘሩ ናቸው።GCAmh 382.2

    ከጥርጥር ነፃ ለመውጣት ከልባቸው ለሚሹ ያለው አንድ መንገድ ብቻ ነው። ስለማያስተውሉት ነገር ከመጠየቅና በመናኛ ነገሮች ከመነታረክ ይልቅ በላያቸው ላይ እያንጸባረቀ ላለው ብርሐን ትኩረት ይስጡ፤ የበለጠ ብርሐን ይቀበላሉ። ይረዱት ዘንድ ግልጽ የተደረገላቸውን እያንዳንዱን ኃላፊነት ይወጡ፣ ከዚያም አሁን የሚጠራጠሩአቸውን ማስተዋልና መተግበር እንዲችሉ ይደረጋሉ።GCAmh 382.3

    እውነት የሚጠይቀውን ራስን መካድንና መስዋእትነትን መሸሽ የሚፈልጉትን፣ ለመታለል ፈቃደኛ የሆኑትንም የሚያታልል፣ ከእውነትም ጋር እጅግ የሚመሳሰል ውሸት ሰይጣን ማቅረብ ይችላል፤ ነገር ግን የትኛውንም ዋጋ ከፍላ እውነቱን ለማወቅ ከልብ የምትሻን አንዲትም ነፍስ በኃይሉ ቁጥጥር ሥር ያደርግ ዘንድ አይችልም። ክርስቶስ እውነት ነው፤ “ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሐን” ነው [ዮሐንስ 1÷9]። ሰዎችን ወደ ሁሉም እውነት ይመራ ዘንድ የእውነት መንፈስ ተልኳል። በእግዚአብሔር ልጅ ስልጣንም እንዲህ ታውጆአል፣ “ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ” “አንድም ፈቃዱን ያደርግ ዘንድ የሚወድ ቢኖር እርሱ ትምህርቱን ያውቃል” [ማቴዎስ 7÷7፤ ዮሐንስ 7÷17]።GCAmh 382.4

    ሰይጣንና ሰራዊቱ እያቀናበሩዋቸው ስላሉት ደባዎች የክርስቶስ ተከታዮች አያውቁም ማለት ይቻላል (የሚያውቁት እጅግ አናሳ ነው)። ጥልቅ ለሆኑት እቅዶቹ መሳካት ሲል ግን መቀመጫውን በሰማያት ያደረገ እርሱ እነዚህን መሳሪያዎች ያከሽፋቸዋል። እግዚአብሔር፣ ሕዝቦቹ በፈተና ቋያ ልምምድ ውስጥ እንዲያልፉ የሚፈቅደው፣ ይህ ሂደት ለመጨረሻው ድላቸው አስፈላጊ ስለሆነ እንጂ በችግራቸውና በጭንቀታቸው ደስ ስለሚሰኝ አይደለም። የፈተናው ዋና አላማ የክፋትን ማታለያዎች ሁሉ እንዲቋቋሙ ማዘጋጀት ነውና በራሱ ክብር ሁልጊዜ ከፈተና ይሸፍናቸው ዘንድ አልተቻለውም።GCAmh 382.5

    በንስሐና በተደቆሰ ልብ ሆነው ኃጢአታቸውን ቢናዘዙና ቢተዉ፣ በእምነትም ተስፋዎቹን ቢጨብጡ፣ ኃጥዕ ሰዎችም ሆኑ አጋንንት የእግዚአብሔርን ሥራ ሊያስተጓጉሉ፣ የእርሱንም መገኘት ከሕዝቦቹ ይከለክሉ ዘንድ አይችሉም። እያንዳንዱ ፈተና፣ እያንዳንዱ ተቃራኒ ተፅእኖ፣ ግልጽም ቢሆን ድብቅ፣ በውጤታማነት መቋቋም የሚቻለው “በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።” [ዘካሪያስ 4÷6]።GCAmh 382.6

    “የእግዚአብሔር ዓይኖች በጻድቃን ላይ ናቸው፣ ጆሮቹዎም ልመናቸውን ይሰማሉ….ማነው የሚጎዳችሁ የመልካም ተከታዮች ብትሆኑ” [1ኛ ጴጥ 3÷12፣13]። በለዓም፣ በሽልማት በረከት ተወስውሶ በእሥራኤል ላይ መድገም ሲጀምር፣ ለጌታም በመሰዋት በሕዝቦቹ ላይ መርገም ለማውረድ ሲጥር፣ ሊያውጅ የፈለገውን ክፋት የእግዚአብሔር መንፈስ ከለከለው፤ በለዓምም፣ “እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? እግዚአብሔር ያልተጣላውን እንዴት እጣላለሁ?”፤ “የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን” ይል ዘንድ ተገደደ። መስዋዕትም እንደገና ሲቀርብ እግዚአብሔርን መሰልነት ያልነበረው ነብይ እንዲህ አለ፣ “እነሆ፥ ለመባረክ ትዕዛዝን ተቀብያለሁ እርሱ ባርኮአል፥ እመልሰውም ዘንድ አልችልም። በያዕቆብ ላይ ክፋትን አልተመለከተም፣ በእሥራኤልም ጠማማነትን አላየም፣ አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነው፣ የንጉሥም እልልታ በመካከላቸው አለ።” “በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥ በእሥራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እሥራኤል፦ እግዚአብሔር ምን አደረገ! ይባላል።”[ዘኁል 23÷8፣10፣20፣21፣23]። ሆኖም ሦስተኛ መሰውያ ተሰርቶ በለዓም እርግማ ማግኘት ይችል ዘንድ ሞከረ፤ ነገር ግን ፈቃደኛ ካልነበሩት የነብዩ ከንፈሮች የእግዚአብሔር መንፈስ የምርጦቹን ብልፅግና በማወጅ የጠላቶቻቸውን ሞኝነትና ክፋት ገሰፀ፣ “የሚመርቅህ ሁሉ የተመረቀ ይሁን፥ የሚረግምህም ሁሉ የተረገመ ይሁን።” [ዘኁል 24÷9]።GCAmh 383.1

    በዚህ ወቅት የእሥራኤል ሕዝቦች ለእግዚአብሔር ታማኞች ነበሩ፤ ለህጎቹ ታዛዥነታቸውን እስከቀጠሉ ድረስም በምድርም ሆነ በሲኦል ያለ ምንም ኃይል ሊያሸንፋቸው አይችልም። ነገር ግን በለዓም በእግዚአብሔር ሕዝቦች ላይ ያውጀው ዘንድ ያልተፈቀደለት እርግማን፣ በስተመጨረሻ ኃጢአት እንዲሰሩ በመገፋፋት ይደርስባቸው ዘንድ ተሳካለት። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በተላለፉ ጊዜ፣ ከእርሱ ራሳቸውን ነጠሉ፣ የአጥፊው ኃይልም ይደርስባቸው ዘንድ ተተው።GCAmh 383.2

    በክርስቶስ ውስጥ የምትኖር፣ ከሁሉም የደከመችው ነፍስ ለጽልመት ሰራዊት ከአቅሙ በላይ እንደምትሆን፣ ራሱንም በገሃድ ቢገልጽ እንደሚገጠምና እንደሚገታ ሰይጣን ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህም ከጦሩ ጋር ሸምቆ አደጋ ሊጥል፣ ወደ እርሱ ግዛትም እግራቸውን ለመስደድ የደፈሩትን ሁሉ ሊያጠፋ ተዘጋጅቶ ሳለ፣ የመስቀሉን ወታደሮች ከጠንካራው ምሽጋቸው ሊያርቃቸው ይጥራል። ከአደጋ ልንጠበቅ የምንችለው በየዋኅት መደገፍ በእግዚአብሔር ስንደገፍና ለሁሉም ህጎቹ ተገዥዎች ስንሆን ብቻ ነው። ለአንድ ቀንም ሆነ ለአንድ ሰዓት ያለ ጸሎት ደህንነት ያለው ማንም የለም። ቃሉን እናስተውል ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብ እንዲሰጠን በተለየ ሁኔታ መማፀን አለብን። የፈታኙ ማታለያ ብልሃቶች፣ እርሱንም በስኬታማነት ለመቋቋም የሚያስችሉ መንገዶች እዚህ ተገልጸዋል። ሰይጣን፣ በክፍለ ምንባቦቹ ላይ የራሱን ትርጉም በመጫን ሊያወላድፈን ተስፋ የሚያደርግ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በመጥቀስ የተዋጣለት ሊቅ ነው። በእግዚአብሔር መደገፋችን ከእይታችን ሳይጠፋ በተዋረደ ልብ ሆነን መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ይገባናል። የሰይጣንን መሳሪያዎች በቋሚነት እየተከላከልን ሳለ፣ ሳናሰልስ፣ “ወደ ፈተና አታግባን” እያልን መፀለይ አለብን።GCAmh 383.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents