Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፴፩—የርኩሳን መናፍስት ውክልናዎች

    የሚታየው ዓለም ከማይታየው ዓለም ጋር ያለው ግንኙነት፣ የእግዚአብሔር መላእክት አገልግሎትና የርኩሳን መናፍስት ውክልናዎች፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ የተቀመጡ ከመሆናቸውም በላይ ከሰው ልጆች ታሪክ ጋር በማይነጣጠል መልኩ የተገመዱ ናቸው። “መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉ” [ዕብ 1÷14] ቅዱሳን መላዕክት በብዙዎች ዘንድ እንደ ሙት መናፍስት የሚቆጠሩ ሆነው ሳለ የርኩሳን መናፍስትን መኖርን አስመልክቶ ደግሞ እያደገ የመጣ የመጠራጠር አዝማሚያ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ግን ክፉና መልካም መላእክት ስለመኖራቸው ብቻ ሳይሆን እነዚህ ከሙታን በድን የወጡ አካል የሌላቸው የሙት መናፍስት ላለመሆናቸው የማያጠራጥር ማስረጃ ያቀርባል።GCAmh 370.1

    ከሰው ፍጥረት በፊት መላእክት ሕያው ነበሩ፤ ምክንያቱም የምድር መሰረት በተጣለ ጊዜ፣ “የማለዳ አጥቢያ ኮከቦች አንድ ሆነው ባመሰገኑ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ልጆችም ደስ ባላቸው ጊዜ” ነበር [እዮብ 38÷7]። ከሰው ውድቀት በኋላ መላእክት የሕይወትን ዛፍ ይጠብቁ ዘንድ ተልከው ነበር፤ ይህም የሆነው አንድም ሰብአዊ ፍጡር ከመሞቱ በፊት ነበር። መላእክት በተፈጥሮ ከሰው የሚበልጡ ናቸው፤ ዘማሪው ዳዊት “የሰው ልጅን ከመላእክት በጥቂት አሳነስከው” ይላልና [መዝ 8÷5]።GCAmh 370.2

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ሰማያዊ ፍጡራን፣ ስለ ቁጥራቸው ብዛት፣ ስለ ኃይላቸውና ክብራቸው እንዲሁም ከእግዚአብሔር መንግሥት ጋር ስላላቸው ዝምድና፣ ከመዋጀት ሥራ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ጭምር መረጃ ተሰጠቶናል። “እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቷል መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።” ነብዩም፣ “በዙፋኑም ዙሪያ… የብዙ መላእክት ድምጽ ሰማሁ” ይላል ። “ፈቃዱን” የሚያደርጉ “አገልጋዮቹ” የቃሉንም ድምጽ የሚሰሙ “ብርቱና ኃያላን….መላእክቱ” የነገሥታት ንጉሥ ባለበት አዳራሽ ውስጥ በተጠንቀቅ ይጠብቃሉ። [መዝ 103÷19-21፤ ራዕይ 5÷11]። በነብዩ ዳንኤል የታዩ የሰማይ መልክተኞች ሺህ ጊዜ ሺህ፣ እልፍ አእላፋት ነበሩ። ሐዋርያው ጳውሎስ ደግሞ “ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት [ወደማይቆጠሩ/innumerable] መላእክት” ብሎ ይገልጻቸዋል። [ዳን 7÷10፤ ዕብ 12÷22]። የእግዚአብሔር መልእክተኞች እንደመሆናቸውም በሚያስደንቅ ክብር፤ “እንደ መብረቅ ምስያ” [ሕዝ 1÷14] በሆነ ፍጥነት ወደፊት ይገሰግሳሉ። በአዳኛችን አጠገብ የታየው መልአክ “መልኩ እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር”፤ ጠባቂዎቹን በፍርሃት አርበደበዳቸው፤”እንደ ሞቱም ሆኑ” [ማቴ 28÷3-4]። ትምክህተኛው አሦራዊው ሰናክሬም እግዚአብሔርን በዘለፈና ባንቋሸሸ ጊዜ፣ እሥራኤልንም ለማጥፋት በዛተ ጊዜ፣ “በዚያች ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ከአሦራዊያን ጭፍራ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰው ገደለ።” ከሰናክሬምም “ሠራዊት ተዋጊዎች መሪዎችና አለቆች ሞቱ።” “ስለዚህ ንጉሡ በውርደት ወደ ገዛ አገሩ ተመለሰ።” [2ኛ ነገሥት 19÷35፤ 2ኛ ዜና 32÷21]።GCAmh 370.3

    መላእክት፣ የምሕረትን ተልእኮዎች ይዘው ወደ እግዚአብሔር ልጆች ይላካሉ። የበረከትን የተስፋ ቃል ይዘው ወደ አብርሐም፤ ጻድቁን ሎጥን ከእሳት ጥፋት ለማትረፍ ወደ ሰዶም፤ በረሃብና በድካም በምድረ በዳ ሊሞት በተቃረበ ጊዜ ወደ ኤልያስ፤ በጠላቶች ተከቦ በነበረበት ጊዜ በእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ትንሽዋን ከተማ ለመክበብ ወደ ኤልሳዕ፤ እግዚአብሔርን በማያውቅ ንጉሥ ቤት ሆኖ መለኮታዊ ጥበብን በሚሻበት ጊዜ፣ እንዲሁም የአንበሳ እራት ይሆን ዘንድ በተተወ ጊዜ ወደ ዳንኤል፤ በሄሮድስ የምድር እስር ቤት ውስጥ እንዲሞት በተፈረደበት ጊዜ ወደ ጴጥሮስ፤ በፊልጵስዩስ ወደነበሩ እስረኞች፤ የባህር ማዕበል በተነሳባቸው ምሽት ወደ ጳውሎስና ጓደኞቹ፤ ወንጌልን ይቀበል ዘንድ የቆርኔሊዎስን አእምሮ ብሩህ ለማድረግ፤ ጴጥሮስ የመዳንን መልእክት ይዞ ወደ አሕዛብ እንዲሄድ ለመላክ፤ በእንዲህ ሁኔታ ቅዱሳን መላእክት በዘመናት ሁሉ የእግዚአብሔርን ወገኖች ሲያገለግሉ ኖረዋል።GCAmh 370.4

    ለእያንዳንዱ የክርስቶስ ተከታይ ጠባቂ መልአክ ተሹሞለታል። እነዚህ ሰማያዊ ጠባቂዎች ከሰይጣን ኃይል የሚመክቱላቸው የጻድቃን ቅጥሮች ናቸው። ሰይጣንም “በውኑ እዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራው በከንቱ ነውን? እርሱን ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን?” በማለት ለዚህ እውቅና ሰጥቷል [እዮብ 1÷9-10]። እግዚአብሔር ሕዝቡን ይጠብቅ ዘንድ ስለሚጠቀመው ልዑክ በመዝሙረኛው ዳዊት አነጋገር እንዲህ ተብሎ ተቀምጦአል፣ “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” [መዝ 34÷7]። በእርሱ ስለሚምኑት መድሃኒታችን ሲናገር እንዲህ አለ፣ “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ።”[ማቴ 18÷10]። የእግዚአብሔርን ልጆች ለማገልገል የተሾሙት መላእክት በማንኛውም ጊዜ ወደ እርሱ ፊት መቅረብ ይችላሉ።GCAmh 371.1

    ስለዚህ ለአታላዩ ኃይልና ለማያንቀላፋው ለጨለማው ልዑል ክፋት የተጋለጡ፣ ከክፉ ኃይላት ሁሉ ጋር ለሚታገሉት የእግዚአብሔር ወገኖች የማያቋርጥ የሰማይ መላእክቶች ጥበቃ እንዳለላቸው ተረጋግጦላቸዋል። ይህ የጥበቃ ዋስትና ሳያስፈልግ የተሰጠ አይደለም። እግዚአብሔር ለልጆቹ የፀጋና የጥበቃ የተስፋ ቃል የሚሰጥበት ምክንያት፤ ቁጥራቸው የበዛ፣ ለክፋት ቆርጠው የተነሱ፣ የማይታክቱ፤ ከክፋታቸውና ከኃይላቸው የተነሳ ቸልተኛና የማይሰማ የሆነ ማንም ሰው ደህና ሊሆን የማይችልበት፣ መመከት ያለባቸው የክፋት ሰራዊቶች ስላሉ ነው።GCAmh 371.2

    ርኩሳን መናፍስት መጀመሪያ ሲፈጠሩ ኃጢአት አልባ የሆኑ፤ በተፈጥሮ፣ በኃይልና በክብር አሁን የእግዚአብሔር መልእክተኞች ከሆኑት ቅዱሳን ፍጡራን ጋር እኩል የነበሩ ናቸው። ነገር ግን በኃጢአት በመውደቃቸው ለእግዚአብሔር መዋረድና ለሰዎች ጥፋት በአንድነት አብረዋል። በሰይጣን አመጽ በመተባበራቸው ከእርሱ ጋርም ከሰማይ በመጣላቸው በቀጣዮቹ ዘመናት ሁሉ ከመለኮታዊ ስልጣን ጋር በሚያደርገው ጦርነት ተባብረዋል። ስለ ህብረታቸውና መንግሥታቸው፣ ስለ ተለያዩ ማዕረጎቻቸው፣ ስለእውቀታቸውና ስለጮሌነታቸው እንዲሁም በሰው ልጆች ሰላምና ደስታ ላይ ስለሚቀይሱት የተንኮል ንድፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ተነግሮናል።GCAmh 371.3

    የብሉይ ኪዳን ታሪክ ስለ ርኩሳን መናፍስት መኖርና ስለውክልናቸው አልፎ አልፎ ይጠቅሳል። ነገር ግን ርኩሳን መናፍስት ኃይላቸውን እጅግ ጉልህ በሆነ ሁኔታ የገለጹት ክርስቶስ በዚህ ምድር በነበረበት ጊዜ ነበር። ክርስቶስ ለሰው ልጅ መዋጀት የተዘጋጀውን እቅድ ለመፈጸም የመጣ ሲሆን ሰይጣን ደግሞ ዓለምን የመግዛት ባለመብትነቱን ለማረጋገጥ የቆረጠበት ጊዜ ነበር። ከፍልስጤም ምድር በቀር በሌሎች የዓለም ክፍሎች የጣዖት አምልኮን መመስረት ችሎ ነበር። ለሰይጣን አገዛዝ እጅዋን ሙሉ በሙሉ ወዳልሰጠች ብቸኛ አገር የሰማይን ብርሐን በሕዝቡ ላይ ያበራ ዘንድ ክርስቶስ መጣ። በዚህ ቦታ ሁለት ተቀናቃኝ ሃይሎች የበላይነት ይገባኛል አሉ። የሱስ እርሱን የሚሹትን፣ ከእርሱ ዘንድ ሰላምንና ይቅርታን ማግኘት ይችሉ ዘንድ የፍቅር እጆቹን ዘርግቶ ይጠራቸው ነበር። የጨለማ ሰራዊቶች ቁጥጥራቸው ገደብ የለሽ እንዳልሆነ (ውስን እንደሆኑ) በመገንዘብ የክርስቶስ ተልእኮ ከተሳካ ግዛታቸው በቅርብ እንደሚያበቃ አስተዋሉ። ሰይጣን በሰንሰለት እንደታሰረ አንበሳ ተቆጥቶ፣ በእምቢተኝነት በሰዎች አካልም ሆነ በነፍሳቸው ላይ ኃይሉን ገለጸ።GCAmh 371.4

    ሰዎች በርኩሳን መናፍስት የመያዛቸው ሃቅ በአዲስ ኪዳን በግልጽ ተጠቅሷል። እንዲህ ሲሰቃዩ የነበሩት ሰዎች እንዲሁ በተፈጥሮ በሚመጣ ህመም ብቻ አልነበረም። ክርስቶስ ከምን ጋር እየታገለ እንደነበር ፍጹም የሆነ ግንዛቤ ነበረው። የርኩሳን መናፍስትን በአካል መኖርና ሥራቸውን አውቆታል።GCAmh 372.1

    ስለ ቁጥራቸው ብዛት፣ ስለ ኃይላቸውና ስለ ተንኮላቸው እንዲሁም ስለክርስቶስ ኃይልና ምሕረት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጌርጌሴኖን በመናፍስት የተያዙ ሰዎች የተፈወሱበት ቀልብን የሚስብ አስደናቂ ምሳሌ ተቀምጧል። እነዚህ በሰይጣን የተያዙ ምስኪን እብዶች የሚገድባቸውን ሁሉ አሻፈረኝ በማለት እየተቅበዘበዙ፣ አረፋን እየደፈቁ፣ በቁጣ እየገነፈሉ አየሩን በጩኸት ይሞሉት ነበር። የራሳቸውን አካል እየጎዱ፣ ወደ እነርሱ ሊቀርብ የሞከረውን ሁሉ ለአደጋ ያጋልጡ ነበሩ። የሚደማውና መልኩን ያጣው ሰውነታቸው እንዲሁም የተቃወሰው አእምሮአቸው ለጨለማው ልዑል አስደሳች ትዕይንት ነበር። በዚህ አኳኋን የሚሰቃዩትን ከተቆጣጠራቸው አንዱ ርኩስ መንፈስ “ስሜ ሌጊዎን ነው ብዙ ነንና” ሲል ተናግሯል [ማር 5÷9]። በሮም የጦር ሰራዊት ውስጥ አንድ ሌጊዎን ከሶስት እስከ አምስት ሺህ ወታደሮችን ይይዛል። የሰይጣን ሰራዊቶችም በክፍለ ጦር የተደራጁ ሲሆን እነዚህ ርኩሳን መናፍስት የተመደቡበት የጦር ክፍልም ከሌጊዎን ያነሰ አልነበረም።GCAmh 372.2

    በእርጋታ ራሳቸውን ያስገዙ ብልህና ገራገር የሆኑ ሰዎችን በአዳኙ ፊት ትተው፣ በየሱስ ትዕዛዝ፣ ርኩሳን መናፍስቱ ተጠቂዎቻቸውን ለቀው ሄዱ። አጋንንቱ ግን የአሳማ መንጋን ይዘው ወደ ባህር እንዲገቡ ተፈቀደላቸው። ለጌርጌሰኖን ነዋሪዎች ግን የአሳማዎቻቸው ኪሳራ ክርስቶስ ከሰጣቸው በረከቶች በለጠባቸውና መለኮታዊ ፈዋሹን ከዚያ ለቆ እንሄድ ተማፀኑት። ይህም ውጤት ሰይጣን አስቀድሞ ያሳካው ዘንድ የቀየሰው ነበር። ስለ ኪሳራቸው ወቀሳን በየሱስ ላይ እንዲጥሉ በሕዝቡ ዘንድ ከራስ ወዳድነታቸው የመነጨ ፍርሃት በመቀስቀስ የእርሱን ቃል እንዳይሰሙ አገዳቸው። ነቀፋውን፣ ሊሆን ወደሚገባው ወደ ራሱና ወደ ወኪሎቹ በማድረግ ፈንታ፣ ሰይጣን ክርስቲያኖች የእጦት፣ የእድለ ቢስነትና የስቃይ መንስኤዎች እንደሆኑ አድርጎ ዘወትር ይወነጅላቸዋል።GCAmh 372.3

    የክርስቶስ ዓላማዎች ግን አልተሰናከሉም። እርሱ ርኩሳን መናፍስቱ አሳማዎቹን እንዲያጠፉ የፈቀደላቸው ለትርፍ ሲሉ እነዚያን ርኩስ እንስሶች የሚያረቡትን አይሁዳውያን ለመገሠፅ ነበር። ክርስቶስ አጋንቶቹን ባይከለክል ኖሮ አሳማዎቹን ብቻ ሳይሆን እረኞቹንም፣ ባለቤቶቹንም ወደ ባሕር ውስጥ ያሰጥሟቸው ነበር። የጠባቂዎቹና የባለቤቶቹ መትረፍ፣ ለመቤዤታቸው በምህረቱ የተደረገ በእሱ ኃይል ብቻ የተከናወነ ነበር። በተጨማሪም ይህ ክስተት የተፈቀደው ሰይጣን በሰውም ሆነ በእንስሳ ላይ የሚያሳየውን የጭካኔ ኃይል ደቀ መዛሙርቱ አይተው ይመሰክሩ ዘንድ ነው። ተከታዮቹ፣ ሊገጥሙት ያላቸው ጠላታቸው እውቀት እንዲኖራቸው ብሎም እንዳይታለሉና እንዳይሸነፉ ክርስቶስ ፈለገ። የአካባቢው ሰዎች እርሱ የሰይጣንን እሥራት ለመስበርና ምርኮኞቹን ለማስለቀቅ ኃይል ያለው መሆኑን ያዩ ዘንድ ፈቃዱ ነበር። የሱስ ከሥፍራው ለቆ የሄደ ቢሆንም በእርሱ ድንቅ ሥራ ነፃ የወጡት ሰዎች ግን የረድኤታቸውን ምሕረት ይመሰክሩ ዘንድ ቀርተዋል።GCAmh 372.4

    ሌሎች ተመሳሳይ ባህርይ ያላቸው ክስተቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበዋል። ሰይጣን ክፉኛ ሲያሰቃያት ለነበረው ለሲሮፊኒቃዊትዋ ሴት ልጅ የሱስ በቃሉ ጋኔኑን አስወጥቶላታል [ማር 7÷26-30]። “ጋኔን ያደረበት እውር ዲዳም” [ማቴ 12÷22]፣ ወጣት፣ ዲዳ መንፈስ የነበረበት ብዙ ጊዜም “ሊያጠፋው ወደ እሳትም ወደ ውሃም [የ]ጣለው” [ማር 9÷17-27]፤ “በርኩስ ጋኔን መንፈስ” [ሉቃ 4÷33-36] ሲሰቃይ የነበረውና በቅፍርናሆም የነበረውን ምኩራብ የሰንበት ፀጥታ ያወከው፣ እነዚህ ሁሉ በሩኅሩኁ አዳኝ ተፈውሰዋል። በእያንዳንዱ ገጠመኞቹ ማለት ይቻላል፣ ክርስቶስ ጋኔንን እንደ አስተዋይ ፍጡር እየጠራው፣ ተጠቂዎቹን ለቆ እንዲወጣና ከዚያም ወዲያ እንዳያሰቃያቸው ያዘው ነበር። በቅፍርናሆም የሚያመልኩም ታላቁን ኃይሉን በማየት “ሁሉም መደነቅ ያዛቸው እርስ በርሳቸውም ይህ ቃል ምንድር ነው? በስልጣንና በኃይል ርኩሳን መናፍስትን ያዝዛልና፣ ይወጡማል ብለው ተነጋገሩ።” [ሉቃ 4÷33-36]።GCAmh 373.1

    በአጋንንት የተያዙ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በታላቅ ስቃይ ውስጥ እንዳሉ ተደርጐ ይቀርባል፤ ሆኖም በተለየ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የማይጠቃለሉ ነበሩ። ከሰው አቅም በላይ የሆነን ኃይል ለማግኘት ሲሉ ሰይጣናዊ ተጽእኖን በአዎንታ የሚቀበሉ ነበሩ፤ በእርግጥም እነዚህ ከአጋንንት ጋር ፀብ አልነበራቸውም። ከዚህም መደብ መካከል የመተንበይ መንፈስ የያዙ እንደ ሲሞን ማጐስ፣ እንደ ዓስማተኛው ኤሊሞስ እንዲሁም ጳውሎስንና ሲላስን በፊልጵሲዩስ ስትከተል የነበረችው ልጅ ይጠቀሳሉ።GCAmh 373.2

    ቀጥተኛ የሆነውና በገፍ የቀረበው የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት ቢኖርም የዲያብሎስንና የርኩስ መላእክቱን መኖርና ተግባር እንደሚክዱ፣ እንደእነርሱ፣ ከርኩስ መናፍስት ተጽኖዎች፣ የበለጠ አደጋ የሚጋረጥባቸው የሉም። የክፋት ሥራቸው እውቀት እስከሌለን ድረስ፣ ግምት ውስጥ ሊገባ የማይችል ሰፊ ዕድል አላቸው፤ የራሳቸውን ጥበብ ምሪት እየተከተልን ነው ብለው ሲያስቡ ሳለ፣ ብዙዎች፣ [መናፍስት] ለሚሰነዝሩት ሃሳብ ጆሮ ይሰጣሉ። ለዚህም ነው ወደ ዘመን ማብቂያ በተቃረብን ጊዜ፣ ለማታለልና ለማጥፋት ሰይጣን ከምን ጊዜውም በበለጠ ኃይል በሚሰራበት ጊዜ፣ እርሱ በህይዎት እንደሌለ ያለውን እምነት በሁሉም ስፍራ የሚነዛው። ራሱንና የአሰራሩን ዘዴ መደበቅ የርሱ መርሀ-ግብር ነው።GCAmh 373.3

    እኛ ከእርሱ መሳሪያዎች ጋር እንደመተዋወቃችን ያለ ታላቁን አታላይ የሚያስፈራው ነገር የለም። የራሱን እውነተኛ ባሕሪና ዓላማ ይበልጥ በሰወረ ቁጥር፣ ከፌዝና ከንቀት ያለፈ የጠነከረ ስሜት እንዳይቀሰቀስበት አድርጐ ራሱን ይወክላል። አስቂኝ ወይም አፀያፊ ምስል ያለው፣ ቅርፁ የተዛባ፣ ግማሽ እንስሳ ግማሽ ሰው አስመስለው ሲስሉት ደስ ይለዋል። ራሳቸውን እንደ አስተዋይና አዋቂ አድርገው በሚያስቡት ሰዎች ዘንድ በጭዋታና በፌዝ ስሙ ሲነሳ መስማት ያስደስተዋል።GCAmh 373.4

    ሰይጣን በፍፁም ጥበብ ራሱን ከመደበቁ የተነሳ “በእርግጥ እንደዚህ አይነት ፍጡር ይኖር ይሆን?” የሚለው ጥያቄ በስፋት እንዲጠየቅ ምክንያት ሆኖአል። በግልፅ ከተቀመጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት ይልቅ የሚነዛው የሐሰት ንድፈ ሐሳብ በመላው ኃይማኖታዊ ዓለም ተቀባይነት ማግኘቱ የሰይጣንን ስኬት የሚያስረዳ ነው። የእግዚአብሔር ቃል፣ እጅግ ክፉ ስለሆነው ተግባሩ በርካታ ምሳሌዎችን የሚሰጠን፣ ምስጢራዊ ኃይላቱን የሚገልጥልን፣ ብሎም ከጥቃቱ እንጠበቅ ዘንድ በተጠንቀቅ እድንሆን የሚያደርገን፣ ሰይጣን፣ ተፅእኖውን ልብ የማይሉትን ሰዎች አእምሮ በቀላሉ ለመቆጣጠር ስለሚችል ነው።GCAmh 374.1

    በኃይል ከሚበልጠው ከመድኃኒታችን መጠለያና መድንን ማግኘት የማንችል ቢሆን ኑሮ፣ የሰይጣን ኃይልና ተንኮል ቢያሸብረን የተገባው ነበር። ንብረታችንንና ሕይወታችንን ከክፉ ሰዎች እንጠብቅ ዘንድ ቤታችንን በመቀርቀርያና በቁልፍ ዘግተን በጥንቃቄ እንጠብቃለን። ነገር ግን ወደ እኛ ለመድረስ ሳያቋርጡ መግቢያ የሚሹትን፣ ጥቃታቸውንም ለመከላከል በራሳችን ምንም አቅም የሌለንን፣ ክፉ መላእክትን እምብዛም አናስባቸውም። ቢፈቀድላቸውስ አእምሮአችንን ማምታታት፣ አካላችንን ማዛባትና ማሰቃየት፣ ጥሪታችንንና ሕይወታችንን ማጥፋት ይችላሉ። ብቸኛ የደስታ ምንጫቸው መከራና ውድመት ነው። ርኩሳን መናፍስት ይቆጣጠሯቸው ዘንድ እግዚአብሔር እስኪተዋቸው ድረስ የመለኮትን መጠይቅ እምቢ በማለት ለሰይጣን ፈተናዎች እጅ የሚሰጡ የእነርሱ ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነው። ክርስቶስን የሚከተሉ ግን በእርሱ ጥበቃና ጥንቃቄ ስር ስለሆኑ ሁሌም ለአደጋ ያልተጋለጡ ናቸው። በጥንካሬያቸው የሚያይሉ መላእክት እንዲጠብቋቸው ከሰማይ ይላካሉ። ክፉው፣እግዚአብሔር በሕዝቦቹ ዙርያ ያቆመውን ጥበቃ ጥሶ ማለፍ አይቻለውም።GCAmh 374.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents