Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የፀሐፊዋ መቅድም

    ኃጢአት ከመግባቱ በፊት አዳም ከፈጣሪው ጋር ያልተገደበ ግንኙነት ነበረው። ነገር ግን በመተላለፍ ሰው ራሱን ከእግዚአብሔር ከነጠለ በኋላ ይህ ግሩም ዕድል ከሰው ዘር ተወስዷል። ሆኖም በድነት እቅድ ምክንያት በምድር የሚኖሩ ከሰማይ ጋር አሁንም ግንኙነታቸው ይቀጥል ዘንድ መንገድ ተከፈተ። በመንፈሱ አማካኝነት እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር ይገናኛል፤ በተመረጡ አገልጋዮቹ በኩል በሚሰጠው መገለጥ አማካኝነትም መለኮታዊ ብርሐን ለዓለም ይደርሳል። “ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፤ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።” [2ኛ ጴጥ 1÷21]።GCAmh .0

    በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በጽሁፍ የሰፈረ መገለጥ አልነበረም። ከእግዚአብሔር የተማሩት እነርሱ እውቀታቸውን ለሌሎች [በቃል] እያካፈሉ ሲወርድ ሲዋረድ ከአባት ወደ ልጅ ሲተላለፍ ኖረ። በጽሁፍ የተገለጠ ቃሉን የማዘጋጀት ሥራ በሙሴ ተጀመረ። የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው መገለጦችም በመለኮታዊ መጽሐፍ ውስጥ ተቀመጡ። ይህም ሥራ የሕግና የፍጥረት ታሪክ ፀሐፊ ከነበረው ሙሴ ጀምሮ፣ ተወዳዳሪ የሌለውን፣ እፁብ ድንቅ የሆነውን የወንጌል እውነት ዘጋቢ እስከነበረው ዮሐንስ ድረስ፣ ለረዥም ዘመናት፣ ማለትም ለአንድ ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት ቀጠለ።GCAmh .0

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ እግዚአብሔር መሆኑን ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቁማል። የተጻፈው ግን በሰዎች ጣት ነበር። የመጻሕፍቱ የተለያየ የአጻጻፍ ዘይቤ የብዙ ፀሐፍያንን ባህርይ ያሳያል። የተገለጹት እውነቶች፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት” ሁሉ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነው [2ኛ ጢሞ 3÷16]። የተገለጹት ግን በሰባዊ ቋንቋ ነው። ዘላለማዊው አምላክ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ወደ አገልጋዮቹ አዕምሮና ልብ ብርሐንን አንጸባረቀ፣ ህልሞችንና ራዕዮችን ተምሳሌቶችንና ምልክቶችን ሰጠ፣ በዚህ ሁኔታ እውነት የተገለጠላቸው ይህንኑ ሃሳብ በሰው ቋንቋ አሰፈሩት።GCAmh .0

    አሥርቱ ትእዛዛት በእግዚአብሔር በራሱ የተነገሩ፣ በራሱም ጣት የተጻፉ ነበሩ። የመለኮት እንጂ የሰው ቅንብር አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ ግን - እግዚአብሔር-ሰጥ የሆኑት እውነቶቹ በሰው ቋንቋ ተገልጸው - የመለኮትንና የሰውን ጥምረት የሚወክል ነው። ይህ ጥምረት የእግዚአብሔር ልጅ እና የሰው ልጅ በሆነው በክርስቶስም ተገልጧል። ስለዚህ በክርስቶስ እንደሆነው ሁሉ በቃሉም እንዲሁ ነው፦ “ቃልም ሥጋ ሆነ… በእኛ አደረ።” [ዮሐ 1÷14]።GCAmh .0

    በደረጃ፣ በሙያ፣ በአዕምሮአዊና በመንፈሳዊ ስጦታዎች በስፋት በተለያዩ ሰዎች፣ በተለያዩ ዘመናት የተፃፉ እንደመሆናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት በገለጽዋቸው ፍሬ ሀሳቦች አይነትና የአፃፃፍ ዘዴ የተለያየ መልክ የያዙ ናቸው። የተለያዩ ጸሐፍያን የተለያዩ አገላለፆችን ተጠቅመዋል። አንድ አይነቱ እውነት (ፍሬ ሀሳብ) ከአንዱ ፀሐፊ ይልቅ በሌላኛው የበለጠ ጎልቶ እንዲታይ ተደርጎ የተገለጸበት ሁኔታ አለ። ብዙ ጸሐፊዎችም አንድን ፍሬ ሃሳብ በተለያዩ ሁኔታዎችና ተዛማጅነት ያላቸው አቀራረቦች ተጠቅመው ስለሚጽፉ፤ ለአስመሳዩ፣ ለግድ-የለሹና በእውቀት ላይ ያልተመሠረተ ሀሳብ ለሚሰነዝረው አንባቢ [መጽሐፍGCAmh .0

    ቅዱሳት] ስምሙ ያልሆኑ፣ እርስ በእርስ የሚቃረኑ ሲመስሉ፤ በጥንቃቄ ለሚመረምራቸው፣ የሚገባቸውን ክብር ሰጥቶ ለሚያስተውላቸው ተማሪ ግን መሰረታዊ ስምምነታቸው ቁልጭ ብሎ ይታየዋል።GCAmh .0

    በተለያዩ ሰዎች የቀረበ በመሆኑ፣ እውነት በተለያዩ ገጽታዎቹ ተገልጦአል፤ አንዱ ጸሐፊ በጽሑፉ የተወሰነ ክፍል ላይ በተለይ ተመስጦ፣ ከራሱ ሕይወት ልምምድ ወይም ከመቀበልና ከመረዳት አቅሙ ጋር የሚመሳሰሉትን ነጥቦች ሲጨብጥ፣ ሌላኛው ደግሞ ሌላ ጎኑን ይረዳል። እናም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሁለቱም በየግል አእምሮአቸውን የበለጠ የመሰጣቸውን ያቀርባሉ። በእነርሱ ውስጥ ያለውን የእውነትን የተለያዩ ገጽታዎች ያሳያሉ። በጥቅሉ ሲታይ ግን ፍጹም መስማማት በሁሉም ዘንድ አለ። በእንዲህ ሁኔታ የተገለጹት እውነቶችም አንድ ላይ ሲሆኑ፣ የሰዎችን አጠቃላይ ሁኔታና የሕይወት ልምምድ በሁሉም አቅጣጫ እንዲዳስስ አስፈላጊው ሁሉ የተካተተበት፣ አንድ ፍጹም ሙሉ የሆነ መጽሐፍ ሆነዋል።GCAmh .0

    ሰዎችን በመጠቀም መልእክቱን ለዓለም ለማስተላለፍ እግዚአብሔር ደስተኛ ነው። እርሱ ራሱ በመንፈስ ቅዱሱ አማካኝነት ሰዎችን መርጦ ይህንን ሥራ እንዲፈጽሙ አስችሏቸዋል። ምን መናገር፣ ምን መጻፍ እንዳለበት ይመርጥ ዘንድ አእምሮን መርቷል። እምቅ ሃብቱ ለምድራዊ ፍጡሮቹ በአደራነት ተሰጥቷል፤ ሆኖም ምንጩ ሰማይ ነው። ምስክሩ የሚተላለፈው የአገላለጽ ፍጹምነት በጎደለው የሰው ቋንቋ ነው፤ ሆኖም የእግዚአብሔር ምስክር ነው። እናም ታዛዡና አማኙ የእግዚአብሔር ልጅ በውስጡ ፀጋና እውነት የሞላበት የመለኮታዊ ኃይል ክብርን ይመለከታል።GCAmh .0

    እግዚአብሔር በቃሉ ለድነት አስፈላጊ የሆነውን እውቀት ለሰዎች ሰጥቷል። መጻሕፍቱ ስልጣን ያላቸው፣ ስህተት ይሆኑ ዘንድ የማይቻላቸው የእርሱ ፈቃድ መገለጫዎች ተደርገው ሊወሰዱ ይገባቸዋል፤ የባህርይ ደረጃ አውጭዎች፣ የአስተምህሮ ገላጮችና የልምድ መፈተኛዎች ናቸው። “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” [2ኛ ጢሞ3÷16-17]።GCAmh .0

    ሆኖም እግዚአብሔር በቃሉ አማካኝነት ፈቃዱን ለሰዎች ማስታወቁ የመንፈስ ቅዱስን በቀጣይነት መገኘትና ምሪቱን አላስፈላጊ አላደረገውም። እንዲያውም በተቃራኒው ቃሉን ለባርያዎቹ ይገልጽ ዘንድ፣ ብርሐን ይፈነጥቅባቸውና ትምህርቶቹንም ገቢራዊ ያደርግ ዘንድ አዳኛችን መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክ ቃል ገብቷል። ለመጽሐፍ ቅዱስ እውን መሆን መሰረቱ የእግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ የመንፈሱ አስተምህሮ ቃሉ ከሚለው ተጻራሪ ይሆን ዘንድ ፈጽሞ የማይቻል ነው።GCAmh .0

    ትምህርቶችና ተሞክሮዎች መለካትና መፈተን የሚችሉበትን ደረጃ የሚያስቀምጠው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን መጻሕፍት በግልጽ የሚናገሩ በመሆናቸው መንፈሱ የተሰጠው መጽሐፍ ቅዱስን እንዲተካ አልነበረም፤ መቸም ቢሆን አይሰጥም። ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ ይላል፣ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነብያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና” [1ኛ ዮሐ 4÷1]። ኢሳያስም እንዲህ ይላል፣ “ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ! እንዲህም ያለውንGCAmh .0

    ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም [እንዲህ አይነቱን ቃል የማይናገሩት ብርሐን በውስጣቸው ስለሌለ ነው/…because there is no light in them]።” [ኢሳ 8÷20]።GCAmh .0

    ብርሐን እንደበራላቸው በሚናገሩ፣ የእግዚአብሔር ቃል ምሪት እንደማያስፈልጋቸው በሚያትቱ፣ በስህተት ውስጥ ባሉ ሰዎች/መደቦች ምክንያት በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ ነቀፋ ሲደርስ ቆይቷል። [እነዚህ ሰዎች] ለነፍሳቸው የተሰጠ የእግዚአብሔር ድምጽ አድርገው በሚቆጥሩት ግምታዊ አስተሳሰባቸው የሚመሩ ናቸው። የተቆጣጠራቸው መንፈስ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ አይደለም። መጻሕፍቱን ቸል በማለት፣ ይህ ግምትን የመከተል ነገር ሊመራ የሚችለው ወደ ድንግርግር፣ ወደ መታለልና ወደ ጥፋት ብቻ ነው። የአጥፊውን እቅድ ወደ ፊት ከማራመድ በቀር ሌላ ፋይዳ የለውም። የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ለክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ የጽንፈኞችንና የአክራሪዎችን ስህተት በመጠቀም በመንፈስ ሥራ ላይ የንቀት ድባብ እንዲጣል በማድረግ ይህንን ጌታ ራሱ የሰጠውን የኃይል ምንጭ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ቸል እንዲሉት ማድረግ ከሰይጣን መሳሪያዎች አንዱ ነው።GCAmh .0

    ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በመስማማት በወንጌሉ ስርጭት ዘመን ሁሉ መንፈሱ ሥራውን መቀጠል ነበረበት። የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በተሰጡበት ዘመናት ሁሉ በተቀደሰው ደንብ የሚካተቱትን ከመግለጹ በተጨማሪ ለግለሰቦች አእምሮ ብርሐን ማካፈሉን አላቆመም ነበር። ከቅዱስ መጻሕፍቱ መሰጠት ጋር ምንም በማይዛመዱ ጉዳዮች ላይ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሰዎች ማስጠንቀቂያ፣ ተግሳጽ፣ ምክርና ትምህርት እንዴት ሲቀበሉ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ያትታል። ከተናገሩት ውስጥ ምንም ተጽፎ የማይገኝ በተለያዩ ዘመናት የነበሩ ነብያቶችም ተጠቅሰው እናገኛለን። በተመሳሳይ ሁኔታም መጻሕፍቱ ተጽፈው ካለቁ በኋላ መንፈስ ለእግዚአብሔር ልጆች ሊገልጥ፣ ሊያስጠነቅቅና ሊያጽናና ሥራውን መቀጠል ነበረበት።GCAmh .0

    የሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ቃል ገብቷል፦ “አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል። እኔም የነገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።” “እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ይመራችኋል…. የሚመጣውን ይነግራችኋል።” [ዮሐ 14÷26፤ 16÷13]። ቃሉ በግልጽ እንደሚያስተምረው እነዚህ ተስፋዎች ለሐዋርያት ዘመን ብቻ የተወሰኑ ሳይሆኑ በዘመናት ሁሉ ለክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የተሰጡ ናቸው። አዳኙም ለተከታዮቹ ያረጋግጥላቸዋል፦ “እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” [ማቴ 28÷20]። ጳውሎስም ሲናገር የመንፈስ መገለጥና ስጦታዎች ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡት “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት ሙሉ ሰውም ወደ መሆን የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ህንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ” ነው ይላል። [ኤፌ 4÷12፣13]።GCAmh .0

    በኤፌሶን ለነበሩ አማኞች ጳውሎስ ሲፀልይ፤ “የክብር አባት የጌታችን የየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ አይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን…. ከሁሉም የሚበልጥ የሃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው።” [ኤፌ 1÷17-19] አለ። ጳውሎስ ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን የተመኘው በመለኮታዊ መንፈስ አገልግሎትGCAmh .0

    ምክንያት የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል ጥልቅ ሃሳቦች ለአእምሮ በመክፈትና መረዳትን በመጨመር የሚገኘውን በረከት ነበር።GCAmh .0

    በጴንጤቆስጤ ቀን ከተከሰተው አስደናቂ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ በኋላ ኃጢአታቸው ይሰረይላቸው ዘንድ በንስሐ እንዲቀርቡና እንዲጠመቁ ጴጥሮስ ሕዝቡን አጥብቆ መከራቸው፤ እንዲህም አለ፦ “የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ። የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።” [የሐዋ ሥራ 2÷38-39]።GCAmh .0

    ከታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ክስተቶች ጋር እጅግ በተዛመደ ሁኔታ፣ በተለየ መልኩ መንፈሱን እንደሚገልጥ በነብዩ በኢዮኤል በኩል ጌታ ተስፋ ሰጥቷል [ኢዮኤ 2÷28]። ይህ ትንቢት በጴንጤቆስጤ ቀን በወረደው መንፈስ ቅዱስ ከፊል ፍጻሜን አግኝቷል። ሙሉ በሙሉ ፍጻሜ የሚያገኘው ለወንጌሉ የማጠናቀቂያ ሥራ በሚላከው የመለኮታዊ ፀጋ መገለጥ ይሆናል።GCAmh .0

    መጨረሻው እየቀረበ ሲሔድ በመልካምና በክፋት መካከል ያለው ተቃርኖ(ተጋድሎ) በእጅጉ እየጨመረ ይሄዳል። የሰይጣን ቁጣ በዘመናት ሁሉ በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሲገለጽ ኖሯል። የክፋትን ኃይል መቋቋም ይችሉ ዘንድ እግዚአብሔር ለሕዝቦቹ ፀጋውንና መንፈሱን ሲለግስ ቆይቷል። የክርቶስ ሐዋርያት ወንጌሉን ተሸክመው ለዓለም ሊያደርሱ፣ ለወደፊት ዘመናትም ሊመዘግቡት በነበረበት ጊዜ፣ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ስጦታ በተለየ ሁኔታ ተበርክቶላቸው ነበር። ቤተ ክርስቲያን ወደ መጨረሻው ነጻ የምትወጣበት ጊዜ ስትቃረብ ግን ሰይጣን በታላቅ ኃይል ሥራውን ይሰራል። “ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ” [ራእይ 12÷12] ይወርዳል። “በተዓምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኛ ድንቆችም።” [2ኛ ተሰሎ 2÷9] ይሰራል። የላቀ አእምሮ ባለቤት የሆነው፣ በአንድ ወቅት የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ የበላይ የነበረው ሰይጣን ለስድስት ሺህ ዓመታት ሙሉ ለማታለልና ለጥፋት ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል። ይህ ለዘመናት በዘለቀው ትንቅንቅ የካበተው ዲያቢሎሳዊ ጥበብና ብልጠት በሙሉ፣ የተሳለው አረመኔያዊነት ሁሉ በመጨረሻው ፍልሚያ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለመውጋት የሚጠቀምበት ይሆናል። በዚህ የጥፋት ጊዜ “ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ” [2ኛ ጴጥ 3÷14] በፊቱ የሚቆም ሕዝብ ይዘጋጅ ዘንድ የእግዚአብሔር ሕዝቦች የጌታን ዳግም ምፅዓት ማስጠንቀቂያ ለዓለም ያውጁ ዘንድ አላቸው። በዚህ ዘመን ያለው የመለኮታዊ ጸጋና ኃይል ለቤተ ክርስቲያን ያለው አስፈላጊነት በሐዋርያት ዘመን ከነበረው ያነሰ አይደለም።GCAmh .0

    በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ (ብርሐን) አማካኝነት ለረጅም ዘመናት የቀጠለው በመልካምና በክፉ መካከል ያለው ፍልሚያ ትእይንት ለዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ ተገልጦላታል። የድነታችን ምንጭ፣ የሕይወት ልዑል በሆነው በክርስቶስና የእግዚአብሔር ቅዱስ ሕግ የመጀመሪያ አፍራሽ፣ የኃጢአት ጀማሪ በሆነው በክፋት ልዑል በሰይጣን መካከል ያለውን ታላቁን ተጋድሎ፣ በተለያዩ ዘመናት የተከናወኑትን ተግባራት አይ ዘንድ ተፈቀደልኝ። በክርስቶስ ላይ ያለው የሰይጣን ጥላቻ በጌታ ተከታዮችም ላይ ሲገለጽ ቆይቷል። የእግዚአብሔር ሕግ መርሆዎች ጥላቻ፣ የማታለል መንገዱ፣ ስህተት እውነት እንዲመስል የሚያደርግበት፣ የሰው ሕጎች የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲተኩ የሚያሳምንበት፣ ብሎም ሰዎች ከፈጣሪ ይልቅ ፍጡርን እንዲያመልኩGCAmh .0

    የሚመራበት ተመሳሳይ አሰራሩ፣ ወደ ኋላ መለስ ተብሎ ታሪክ ቢመረመር ከጥንት ጀምሮ ሲጠቀምበት እንደቆየ ይታያል። የእግዚአብሔርን ባህርይ አጣሞ በማቅረብ ሰዎች ስለፈጣሪ ያላቸውን ግንዛቤ በማዛባት በፍርሃትና በጥላቻ እንዲመለከቱት እንጂ በፍቅር እንዳያዩት ማድረግ፤ መለኮታዊ ሕጉን ወደ ጎን ለመገፍተር ጥረት በማድረግ ሰዎች ከሕጉ መጠይቅም ነጻ እንደሆኑ እንዲሰማቸው መጣሩ፤ የማታለል ተግባሩን የተቃወሙትንም ማሳደዱ፤ በሁሉም ዘመናት በንቃት ሲተገብራቸው የቆዩ ባህርያት ናቸው። በኃይማኖት አባቶች፣ በነብያትና በሐዋርያት እንዲሁም በሰማዕታትና በተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪዎች ታሪክ ውስጥ የእነዚህ እኩይ ተግባራት ዱካዎች ይገኛሉ።GCAmh .0

    ባለፉት ዘመናት እንዳደረገው ሁሉ በታላቁ የመጨረሻ ፍልሚያም ሰይጣን ተመሳሳይ መርሃ-ግብር ይተገብራል፤ ተመሳሳይ መንፈስ ያንጸባርቃል፤ ለተመሳሳይ ግብ ይሰራል። ሲሆን የቆየው ወደፊትም ይሆናል፤ ልዩነቱ የሚመጣው ትንቅንቅ ዓለም ከአሁን በፊት አይቶት በማያውቀው እጅግ አሰቃቂ በሆነ ግለት የሚካሄድ መሆኑ ነው። የሰይጣን ማታለያዎች የባሰ ጮሌነት የተላበሱ፤ ጥቃቱም የበለጠ ቁርጠኛ ይሆናል። የሚቻል ቢሆን የተመረጡትን እንኳ ወደ ስህተት ይመራል። [ማር 13÷22]።GCAmh .0

    የእግዚአብሔር መንፈስ አእምሮዬን ከፍቶ የቃሉን ታላላቅ እውነቶች ሲገልጽልኝ፣ ያለፉትንና የሚመጡትን ክስተቶች ሲያሳየኝ፣ የተገለጠውን ለሌሎች አሳውቅ ዘንድ፤ ባለፉት ዘመናት የነበረውን የተጋድሎውን ታሪክ እንድዳስስ፣ በተለይም ደግሞ በፍጥነት እየቀረበ ባለው የወደፊት ትግል ላይ ብርሐን ማሳረፍ በሚችልበት አኳኋን አቀርበው ዘንድ ታዝዣለሁ። ይህንንም አላማ ለማሳካት በተለያዩ ዘመናት ለዓለም የተሰጡትን፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተከናወኑትን፤ የሰይጣንን ቁጣ የቀሰቀሱትን፤ የዓለም አፍቃሪ ቤተ ክርስቲያንን ጥላቻ ያተረፉትን “ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱትም” [ራዕይ 12÷11] በተባለላቸው ንፁኃን ተጠብቀው የቆዩትን ታላላቅ እውነቶች የሚገልጹትን ክስተቶች ለመምረጥና በየፈርጃቸው ለማስቀመጥ ጥረት አድርጌአለሁ።GCAmh .0

    በእነዚህ መዛግብት ውስጥ በፊታችን ስላለው ጦርነት አመላካች ክስተቶችን እናያለን። በእግዚአብሔር የቃል ብርሐን፣ በመንፈሱም የመገለጽ ነጸብራቅ አማካኝነት፣ በጌታ ምፅዓት ጊዜ “ያለ ነቀፋ” ይገኙ ዘንድ ያላቸው መሸሽ የሚገባቸውን አደጋዎችና የኃጥኡን (የሰይጣንን) መሳሪያዎች ተገልጠው ማየት እንችላለን።GCAmh .0

    የተሐድሶውን የእድገት እንቅስቃሴ ገሃድ ያደረጉት ባለፉት ዘመናት የተከናወኑት ታላላቅ ክስተቶች፣ በፕሮቴስታንቱ ዓለም በውል የታወቁና በዓለም አቀፋዊነትም እውቅና የሰጣቸው ታሪኮች ናቸው። ማንም ሊክዳቸው የማይችላቸው ሃቆች ናቸው። ጥቅም ላይ አዋዋላቸው አግባብነት ያለው መሆኑ ተጠብቆ እውነቶቹ ተጠጋግተው፣ በተቻለ መጠን ብዙ ቦታ ሳይፈጁ፣ እንደ አስፈላጊነቱ ተመጥነው፣ ይህ መጽሐፍ ከሚዳስሳቸው ጉዳዮች ይዘት ጋር ስምሙ እንዲሆኑ አድርጌ ታሪኩን በአጭሩ አቅርቤዋለሁ። በአንዳንድ ስፍራ የታሪክ ፀሐፊው የጉዳዩን ሁለንተናዊ ገጽታ በአጭር ለመግለፅ ክስተቶችን አንድ ላይ ያደረገበት ወይም ዘርዘር ብለው የተገለጹትን በሚመች ሁኔታ ያጠቃለለበት ሁኔታ በሚኖርበት ጊዜ የታሪክ ፀሐፊው ቃላት ራሳቸው ተጠቅሰዋል። ሆኖም ጽሑፎቹ የተጠቀሱት፣ ጉዳዩ ዝግጁ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ እንዲቀርብ ለመርዳት እንጂ ለፀሐፊው ስልጣን እውቅና ለመስጠት ካለመሆኑ የተነሳ ከጥቂቶች በስተቀርGCAmh .0

    የተለየ እውቅና ለማንም አልተሰጠም። አሁን ባለንበት ዘመን ስላሉ፣ የተሐድሶውን ሥራ ወደፊት ስለሚያራምዱ ልምድና አስተያየት በመተረክ ደረጃም ያሳተሟቸው መፃሕፍት በተመሳሳይ ሁኔታ አልፎ አልፎ ጥቅም ላይ ውለዋል።GCAmh .0

    ወደፊት ለሚመጡት ክስተቶች አስፈላጊ የሆኑትን ጭብጦችና መርሆዎች ለማጉላት ካለው አላማ ጋር ሲነጻጸር፣ ባለፉት ዘመናት የተከናወኑትን ትግሎች በተመለከተ አዲስ እውነት ማቅረብ ያን ያህል የዚህ መጽሐፍ ትኩረት አይደለም። ሆኖም በብርሐንና በጨለማ ኃይላት መካከል የሚደረገው ተጋድሎ አካል በመሆናቸው እነዚህ ያለፉ ጊዚያቶች ጽሁፎች አዲስ ጠቀሜታ እንዳላቸው ታይተዋል። በቀድሞ እንደነበሩት የተሐድሶ ታጋዮች ሁሉ በምድራዊ ቁስ ውድመት እንኳ ሳይበገሩ፣ “ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ የሱስ ክርስቶስ ምስክር” [ራዕይ 1÷9] ይመሰክሩ ዘንድ ለሚጠሩ ለእነርሱ፣ መንገዳቸውን ቦግ የሚያደርግ፣ [በጸሐፊዎቹ] አማካኝነት በሚመጣው ዘመን ላይ ብርሐን እንዲያርፍ ተደርጎአል።GCAmh .0

    በስህተትና በእውነት ያለውን ታላቅ የተጋድሎ ትዕይንት መግለጽ፣ የሰይጣንን የማታለል ብልሃት ማጋለጥ፣ በተሳካ ሁኔታ እርሱን ለመቋቋም የሚያስችሉትን መጠቆም፤ እግዚአብሔር ለፍጡራን የሚያሳየው ቅንነትና ትክክለኛ ፍርድ በሙላት ይገለጽ ዘንድ የኃጢአት መነሻም ሆነ መደምደሚያ ባህርይ ላይ ጮራ በመፈንጠቅ ለታላቁ የክፋት ችግር አጥጋቢ መፍትሄ ማግኘት፣ ብሎም ቅዱስና የማይለወጥ ባህርይ ያለውን ሕጉን ማሳየት፣ የዚህ መጽሐፍ አላማ ነው። በዚህ መጽሐፍ ተጽእኖም ምክንያት ነፍሳት ከጽልመት ኃይል ወጥተው “በቅዱሳንም ርስት በብርሐን [ተካፋዮች ይሆኑ ዘንድ]” [ቆለ 1÷12] ለወደደንና ራሱን አሳልፎ ለሰጠን ምስጋና ይሆን ዘንድ የፀሐፊዋ ልባዊ ጸሎት ነው።GCAmh .0

    ኤ. ጂ. ዋይት/Ellen G. White

    ሂልድስበርግ, ካሊፎርኒያ

    ግንቦት 1888 ዓ.ም እ.አ.አ.

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents