Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፳፬—በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ

    የቤተ መቅደሱ ጉዳይ የ1844ቱን ቅሬታ ምስጢር የከፈተ ቁልፍ ነበር። ፍፁም ሙሉ የሆነ፣ በስምምነት የተቆራኘ የእውነት መዋቅር እንዳለ፣ የእግዚአብሔር እጅ ታላቁን የአድቬንት እንቅስቃሴ እንደመራው፣ የሕዝቦቹን ደረጃና ተግባር ሲያሳውቅም ወቅታዊ ኃላፊነታቸው ምን እንደሆነ የገለጠበት፣ ይህንን ሁሉ ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነበር። የየሱስ ደቀ መዛሙርት ከአሰቃቂው ስቅይትና የሃዘን ሌሊት በኋላ “ጌታን ባዩ ጊዜ” ደስ እንዳላቸው ለዳግም ምፅዓቱ በእምነት ሲመለከቱ የነበሩትም እንዲሁ አሁን ሃሴት አደረጉ። ለአገልጋዮቹ ሽልማት ይሰጥ ዘንድ በክብር ይገለጥ ዘንድ ሲጠባበቁት ነበር፤ ተስፋቸው ሲሟሽሽ የሱስን ማየት ተሳናቸው። በመቃብሩ ደጃፍ ከነበረችው ማሪያም ጋር፦ “ጌታዬን [ጌታችንን] ወስደውታል፤ ወዴት እንዳኖሩት አላውቅም [አናውቅም]” [ዮሐ 20÷13] ብለው ጮኸዋል። አሁን እንደገና ንጉሳቸውና ተቤዣቸው ሆኖ በቅርብ ሊገለጥ፣ ሩኅሩኁን፣ ታላቁን ካህናቸውን በቅድስተ ቅዱሳኑ ተመለከቱት። ከቤተ መቅደሱ የሚወጣው ብርሐን ያለፈውን፣ የወቅቱንና የወደፊቱን ቦግ አደረገው። በማይሳሳተው አቅርቦቱ እግዚአብሔር እንደመራቸው አወቁ። እንደመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ሁሉ እነርሱም ራሳቸው የተሸከሙትን መልእክት ማስተዋል ያልቻሉ ቢሆንም አካሄዳቸው ግን በእያንዳንዱ አቅጣጫ ትክክል ነበር። አዋጁን በማወጃቸው የእግዚአብሔርን አላማ አከናውነዋል፤ በጌታ በኩልም ልፋታቸው ከንቱ ሆኖ አልቀረባቸውም። “ለሕያው ተስፋ….ሁለተኛ” [1ኛ ጴጥ 1÷4] ተወልደው “በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሴት”[1ኛ ጴጥ 1÷9] ደስ ተሰኙ።GCAmh 307.1

    የዳንኤል ምዕራፍ 8÷14 ትንቢት “እስከ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ማታና ጠዋት ድረስ ነው ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነፃል” እና የመጀመሪያው መልአክ መልዕት “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት” የሚሉት ሁለቱም የሚያለክቱት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የክርስቶስን አገልግሎት፣ የፍርድ ምርመራውን እንጂ ሕዝቦቹን ለመቤዤትና ኃጥአንን ለማጥፋት የክርስቶስን መምጣት አልነበረም። ስህተቱ የነበረው የትንቢት ዘመናቱን በማስላት ላይ ሳይሆን በ2300 ቀናቱ መጨረሻ ስለሚከናወነው ክስተት ነበር። በዚህ ስህተት ምክንያት አማኞቹ ቅር በመሰኘት ተሰቃይተዋል፤ ሆኖም በትንቢት የተነገረውና ይጠብቁት ዘንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ የነበረው ነገር ሁሉ ተከናውኖአል። የተስፋቸውን መጨለም እያንጎራጎሩ በነበረበት በዚያ ጊዜ፣ በመልእክቱ አስቀድሞ የተነገረው፣ ለባሪያዎቹ ዋጋቸውን ለመስጠት ጌታ ከመገለጡ በፊት ሊከናወን የሚገባው ክስተት ተፈጽሞ ነበር።GCAmh 307.2

    ክርስቶስ የመጣው ግን እንደጠበቁት ወደ ምድር ሳይሆን፣ አስቀድሞ በምሳሌ እንደተገለጠው፣ በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር መቅደስ፣ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ነበር። በዚህ ጊዜ በዘመናት ወደ ሸመገለው እንደሚመጣ በነብዩ ዳንኤል ተመልክቷል። “በሌሊት ራዕይ አየሁ፣ እነሆም የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማያት ደመና ጋር መጣ” ወደ ምድር ሳይሆን “በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ ወደፊቱም አቀረቡት።” [ዳን 7÷13]።GCAmh 307.3

    ይህ መምጣት በነብዩ ሚልክያስም አስቀድሞ ተነግሮ ነበር። “እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ እነሆ ይመጣል ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር” [ሚል 3÷1]። የጌታ ወደ መቅደሱ መምጣት ለሕዝቦቹ ያልተጠበቀ፣ ድንገተኛ ነበር፤ እየፈለጉት የነበሩት እዚያ ስፍራ አልነበረም። የጠበቁት፣ “እግዚአብሔርን የማያውቁትን ለጌታችንም ለየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን በእሳት ነበልባል” ይበቀል ዘንድ ወደ ምድር እንዲመጣ ነበር። [2ኛ ተሰ 1÷8]።GCAmh 308.1

    ሕዝቡ ግን አምላካቸውን ለመገናኘት ገና ዝግጁ አልነበሩም። ገና ሊከናወንላቸው የሚገባ የመዘጋጀት ሥራ አለ። አዕምሯቸውን በሰማይ ወዳለው የእግዚአብሔር መቅደስ የሚመራ ብርሐን ሊሰጣቸው ነበረው፤ በዚያም ስፍራ ታላቁ ሊቀ ካህናቸው ሲያገለግል በእምነት ሲከተሉት አዲስ ሃላፊነቶች ይገለጣሉ። ሌላ የማስጠንቀቂያና የመመሪያ መልእክት ለቤተ ክርስቲያን ይሰጣት ዘንድ ነበረው።GCAmh 308.2

    ነቢዩ እንዲህ ይላል፦ “ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገስ የሚችል ማነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማነው? እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፤ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፤ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቁርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ” [ሚል 3÷2፣3]። በቤተ መቅደሱ ውስጥ የክርስቶስ የማማለድ ሥራ በሚጠናቀቅበት ጊዜ በዚህ ምድር ላይ በሕይወት የሚኖሩ እነርሱ በቅዱስ እግዚአብሔር እይታ ያለ አማላጅ ይቆማሉ። ልብሳቸው ያለምንም ነቁጥ መሆን አለበት፤ ባህርያቸው በደም መረጨት፣ ከኃጢአት መንፃት አለበት። በእግዚአብሔር ፀጋና በራሳቸው ያላሰለሰ ጥረት ከክፋት ጋር በሚደረገው ጦርነት አሸናፊዎች መሆን አለባቸው። የፍርድ ምርመራው በሰማይ እየቀጠለ ባለበት ወቅት፣ ንስሐ የገቡ ኃጢአት ከመቅደሱ እየተወገደ ባለበት ሰዓት፣ የተለየ የመንፃት ሥራ፣ ኃጢአትን የማስወገድ ሥራ በምድር በሚኖሩ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ዘንድ መተግበር አለበት። ይህ ሥራ በራዕይ 14 ላይ በተቀመጡት መልእክቶች የበለጠ ግልጽ ሆኖ ተብራርቷል።GCAmh 308.3

    ይህ ሥራ በሚከናወንበት ጊዜ የክርስቶስ ተከታዮች ለእርሱ መገለጥ የተዘጋጁ ይሆናሉ። “እግዚአብሔርም እንደ ድሮው ዘመንና እንደ ቀደሙት ዓመታት በይሁዳና በየሩሳሌም ቁርባን ደስ ይለዋል” [ሚል 3÷4]። ጌታችን በሚመጣበት ጊዜ ወደራሱ የሚቀበላት ቤተ ክርስቲያን “እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር” የሌለባት ትሆናለች [ኤፌ 5÷27]። ከዚያም “እንደ ማለዳ ብርሐን የምትጎበኝ፣ እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች አላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሰራዊት የምታስፈራ” [መሃልዪ 6÷10] ሆና ትወጣለች።GCAmh 308.4

    ክርስቶስ ወደ መቅደሱ ከመምጣቱ በተጨማሪ፣ ስለ ዳግም ምፅዓቱ፣ ፍርድ ለመፈፀም ስለ መምጣቱ በእነዚህ ቃላት ሚልክያስም እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ በመተተኞችና በአመንዝሮች በሐሰትም በሚምሉ፣ የምንደኛውን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቲቱንና ድሃ አደጉን በሚያስጨንቁ፣ የመፃተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፣ እኔን በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር” [ሚል 3÷5]። ይሁዳ ደግሞ ስለ ተመሳሳዩ ትዕይንት ሲያመለክት እንዲህ ይላል፦ “እነሆ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአት ሥራቸው ኃጢአተኞችን እንዲወቅስ ከአዕላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል” [ይሁዳ 14፣15]። ይህ አመጣጥ እና የጌታ ወደ መቅደሱ መምጣት ልዩነት ያላቸውና የተነጣጠሉ ክስተቶች ናቸው።GCAmh 308.5

    እንደ ሊቀ ካህናችን ሆኖ መቅደሱን ያነፃ ዘንድ የክርስቶስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መምጣት በዳንኤል 8÷14 እንዲስተዋል የተደረገው፤ በዘመናት ወደ ሸመገለው የሚመጣው የሰው ልጅ በዳንኤል 7÷13 የተነገረው፤ እንዲሁም የክርስቶስ ወደ መቅደሱ መምጣት በሚልክያስ የተነገረው፣ እነዚህ የሚገልፁት ስለ ተመሳሳዩ (አንድ) ክስተት ነው። ሙሽራው ወደ ሠርጉ የሚመጣበት፣ በአሥርቱ ደናግልት ምሳሌ በክርስቶስ የተብራራው በማቴዎስ 25 የሚገኘውም ይህንን ክስተት የሚወክል ነው።GCAmh 309.1

    በ1844 ዓ.ም በበጋ እና በመኸር ወራት “እነሆ ሙሽራው ደረሰ” የሚለው አዋጅ ተሰጠ። በልባሞቹና በሰነፎቹ ደናግልት የተወከሉት ሁለቱ ጎራዎች ተፈጠሩ፤ አንደኛው ቡድን የጌታን መገለጥ በደስታ የሚጠባበቅ፣ ይገናኝ ዘንድም በትጋት ይዘጋጅ የነበረ ሲሆን ሌላኛው ጎራ ደግሞ በፍርሃት ተጽዕኖ፣ በስሜት በመነሳሳት በእውነት ንድፈ ሃሳብ ብቻ ረክቶ በእግዚአብሔር ፀጋ ግን የተራቆተ ነበር። በምሳሌው ሙሽራው በመጣ ጊዜ “ተዘጋጅተው የነበሩት ከእርሱ ጋር ወደ ሠርጉ ገቡ” [ማቴ 25÷10]። እዚህ ላይ ግልጽ እንደተደረገው የሙሽራው መምጣት ተግባራዊ የሚሆነው ከሠርጉ ቀደም ብሎ ነው። ሠርጉ የሚወክለው ክርስቶስ ለመንግሥቱ የሚያደረገውን አቀባበል ነው። የመንግሥቱ ወኪልና መዲና የሆነችው ቅድስት ከተማ፣ አዲሲቷ የሩሳሌም “ሙሽራይቱ የበጉ ሚስት” ተብላ የምትጠራዋ ናት። መልአኩ ለዮሐንስ እንዲህ አለው፣ “ወደዚህ ና የበጉንም ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ።” “በመንፈስም ወሰደኝ” ይላል ነብዩ “ቅድስቲቱን ከተማ የሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ” [ራዕይ 21÷9፣10]። እናም ሙሽራይቱ ቅድስት ከተማይቱን ስትወክል ሙሽራውን ሊገናኙ የወጡት ደናግልት ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምሳሌዎች እንደሆኑ ግልጽ ነው። በራዕዩ መሰረት በሠርጉ እራት ላይ እንግዶች የሆኑት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ናቸው። [ራዕይ 19÷9]። ስለዚህ እንግዶች ከሆኑ ሙሽራይቱን ሊወከሉ አይችሉም ማለት ነው። በነብዩ ዳንኤል እንደተነገረው በዘመናት ከሸመገለው በሰማይ “ግዛትና ክብር መንግሥትም” ይቀበላል፤ የመንግሥቱን መዲና አዲሲቱን የሩሳሌምን “ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ” ይቀበላታል [ዳን 7÷14፤ ራእይ 21÷2]። መንግሥቱን ከተቀበለ በኋላ በበጉ የሠርግ እራት ግብዣ ላይ ይሳተፉ ዘንድ “ከአብርሃም፣ ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር” [ማቴ 8÷11፤ ሉቃ 22÷30] በመንግሥቱ ገበታ ላይ እንዲቀመጡ ሕዝቦቹን ለመቤዤት የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶች ጌታ ሆኖ በክብሩ ይመጣል።GCAmh 309.2

    “እነሆ ሙሽራው ደረሰ” የሚለው አዋጅ በ1844 ዓ.ም የበጋ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የጌታን ወዲያውኑ መምጣት እንዲጠብቁ አድርጎ ነበር። በተወሰነው ጊዜ ሙሽራው መጥቷል፣ የመጣው ግን ሕዝብ እንደጠበቀው ወደ ምድር ሳይሆን መንግሥቱን የመቀበል ሥነ-ሥርዓት ወደሚደረግበት ወደ ሠርጉ፣ በሰማይ ወደ አለው በዘመናት ወደ ሸመገለው ነበር። “ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሠርጉ ገቡ ደጁም ተዘጋ።” ሥነ ሥርዓቱ የሚፈፀመው በሰማይ ነውና የተዘጋጁት ደግሞ ምድር ላይ ስለሆኑ በሠርጉ ላይ በአካል መገኘት የሚችሉ አይደሉም። የክርስቶስ ተከታዮች “ጌታቸው ከሠርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ” [ሉቃ 12÷36] ሰዎች መሆን ይኖርባቸዋል። ነገር ግን የሚያከናውነውን ሥራ መረዳት፣ ወደ እግዚአብሔርም ፊት ሲቀርብ በእምነት ሊከተሉት ይጠበቅባቸዋል። ወደ ሠርጉ ይሄዳሉ የተባለውም በዚህ መረዳት ነው ።GCAmh 309.3

    በምሳሌው፣ ወደ ሠርጉ የገቡት በማሰሮዎቻቸው ዘይት የያዘውን መብራታቸውን የያዙት ነበሩ። ከመጽሐፍ ቅዱሳት ካገኙት የእውነት እውቀት፣ የእግዚአብሔር መንፈስና ፀጋ የነበራቸው፣ በመራሩ የፈተና ሌሊት የበለጠ ግልጽ ለሆነ ብርሐን መጽሐፍ ቅዱስን እየመረመሩ በትዕግስት የጠበቁት፣ እነዚህ በሰማይ ስላለው መቅደስ ያለውን እውነትና የአዳኙን የአገልግሎት ለውጥ የተመለከቱ፣ በላይ ባለው መቅደስም ሥራውን በእምነት የተከተሉ ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት አማካኝነት ተመሳሳዩን እውነት የሚቀበሉ፣ የመጨረሻውን የማማለድ ሥራ ያከናውን ዘንድ ወደ አባቱ ፊት ሲገባ ክርስቶስን በእምነት የሚከተሉ፣ ሥራው አብቅቶ መንግሥቱን እስኪቀበል የሚከተሉት፣ እነዚህ ሁሉ ወደ ሠርጉ በገቡት የተወከሉ ናቸው።GCAmh 310.1

    በማቴዎስ ወንጌል 22 ባለው ምሳሌ ተመሳሳዩ የጋብቻ ተምሳሌት ይተዋወቃል፤ የፍርድ ምርመራውም ከሠርጉ በፊት እንደሚከናወን በግልጽ ተቀምጧል። ከሠርጉ በፊት ንጉሡ እንግዶችን ለማየት ይመጣል [ማቴ 22÷11]፤ ነቁጥ የሌለበትን፣ በበጉ ደም ታጥቦ ነጭ የሆነውን የባህርይ ልብስ፣ ለሠርግ የተገባውን ልብስ መልበሳቸውን ሊያረጋግጥ ይገባል [ራዕይ 7÷14]። ጎዶሎ የተገኘበት እርሱ ወደ ውጪ ይጣላል፤ በምርመራው ጊዜ የሠርጉን ልብስ ለብሰው የሚገኙ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኛሉ፤ በመንግሥቱ ክፍል፣ በዙፋኑም ላይ መቀመጫ ይኖራቸው ዘንድ የተገባቸው ሆነው ይቆጠራሉ። ይህ የባህርይ ምርመራ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት የተዘጋጀው ማን እንደሆነ የሚወሰንበት ምርመራ፣ በላይ ባለው መቅደስ የሚከናወነው የማጠቃለያ ሥራ፣ የፍርድ ምርመራ፣ ነው።GCAmh 310.2

    የምርመራው ሥራ ሲያልቅ በዘመናት ሁሉ የክርስቶስ ተከታዮች እንደሆኑ የመሰከሩት ሁሉ ጉዳያቸው ተመርምሮ ውሳኔ ሲያገኝ፣ ከዚያ ጊዜ በፊት ሳይሆን፣ ያ ጊዜ ሲደርስ፣ የምሕረት (የአመክሮ) ጊዜ ያበቃል፤ የምሕረት ደጅም ይዘጋል። እናም “ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሠርግ ገቡ ደጁም ተዘጋ” በሚለው በአንድ አጭር አረፍተ ነገር ውስጥ፣ በአዳኙ የመጨረሻ አገልግሎት አማካኝነት፣ ለሰው ልጅ መዳን የተሰራው ታላቅ ሥራ ወደሚጠናቀቅበት ወደዚያ ጊዜ እንወሰዳለን።GCAmh 310.3

    እስካሁን እንዳየነው፣ በሰማይ የሚደረገው አገልግሎት ምሳሌ በነበረው የምድራዊው ቤተ መቅደስ፣ በስርየት ቀን ሊቀ ካህኑ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ በሚገባበት ጊዜ፣ በመጀመሪያው ክፍል (በቅዱስ ስፍራው) የሚከናወነው አገልግሎት ይቆማል። እግዚአብሔርም አዘዘ፣ “እርሱም….አስተሰርዮ እስኪወጣ ድረስ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ማንም አይኖርም” [ዘሌዋ 16÷17]። ስለዚህ የስርየቱን የማጠቃለያ ሥራ ይሰራ ዘንድ ክርስቶስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በገባበት ጊዜ፣ በመጀመሪያው ክፍል የነበረውን አገልግሎቱን አቁሟል። ሆኖም፣ በመጀሪያው ክፍል የነበረው አገልግሎት ሲያበቃ፣ በሁለተኛው ክፍል ያለው አገልግሎት ጀመረ። በተምሳሌታዊው አገልግሎት፣ በስርየት ቀን፣ ሊቀ ካህኑ ቅዱሱን ስፍራ በሚለቅበት ጊዜ፣ ኃጢአታቸውን በእውነት የተናዘዙትን እሥራኤላዊያን በሙሉ ወክሎ፣ የኃጢአት መስዋዕቱን ደም ይዞ ወደ እግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ይገባል። ስለዚህ ወደ ሌላኛው የሥራ ክፍል ለመግባት፣ ክርስቶስ አማላጃችን ሆኖ የሚሰራውን አንዱን የሥራ ክፍል ብቻ አጠናቋል ማለት ነው፤ ስለ ኃጢአተኞች ሲል በደሙ በአብ ፊት አሁንም ገና ይማልዳል።GCAmh 310.4

    በ1844 ዓ.ም ይህ ነጥብ (ትምህርት) በአድቬንቲስቶች ዘንድ አልተስተዋለም ነበር። አዳኙ ይመጣል ተብሎ የተጠበቀበት ጊዜ ካለፈም በኋላ፣ የሚመጣበት ጊዜ ቅርብ እንደሆነ አሁንም ያምኑ ነበር። አስፈላጊው የችግር ጊዜ ላይ እንደደረሱና ክርስቶስ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ስለ ሰው የሚማልድበት ሥራ እንዳበቃ ያምኑ ነበር። የሰው የምሕረት ጊዜ፣ ክርስቶስ በአካል በሰማይ ደመና ከመምጣቱ በፊት፣ ትንሽ ቀደም ብሎ እንደሚያበቃ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምር መሰላቸው። ሰዎች የምሕረትን በር ሲሹ፣ ሲያንኳኩና ሲያለቅሱ በሩ እንደማይከፈትላቸው የሚጠቅሱ ጥቅሶች ይህንን የሚያረጋግጡ መሰሉ። ስለዚህም ክርስቶስ ይገለጥበታል ብለው የጠበቁበት ጊዜ ልክ ከመምጣቱ በፊት ያለውን የዚህን (የምሕረት ማብቂያ) ጊዜ የሚያመላክት መሆን አለመሆኑ ጥያቄ ሆኖባቸው ነበር። በደጅ ስላለው ፍርድ ማስጠንቀቂያ ከሰጡ በኋላ፣ ለዓለም ያላቸው ሥራ እንደተፈፀመ ተሰማቸው፤ እናም ለኃጥአን መዳን የነበራቸው የነፍሳት ሸክም ተወገደ፤ በሌላ በኩል እግዚአብሔርን የማይመስሉትን ደፋርና በስድብ የተሞላ መሳለቅ ሲያዩ፣ ምህረቱን አሻፈረኝ ካሉ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ የተወሰደ ለመሆኑ ሌላ ማስረጃ እንደሆነ አድርገው ቆጠሩት። ይህ ሁሉ ያረጋገጠላቸው የምሕረት(የአመክሮ) ጊዜ እንዳበቃ፤ ወይም እነርሱ ያን ጊዜ እንደገለፁት “የምሕረት ደጃፍ እንደ ተዘጋ” ነበር። [በመግለጫ ስር ማስታወሻ 7ን ይመልከቱ]።GCAmh 311.1

    የቤተ መቅደሱ ጥያቄ ሲመረመር ግን የበለጠ ግልጽ ብርሐን ይዞ መጣ። የ2300 ቀናቱ ማብቂያ፣ በ1844 ዓ.ም ልብ ሊባል የሚገባ አስጊ ክስተትን እንደሚጠቁም ማመናቸው ትክክል እንደነበር አስተዋሉ። ለአንድ ሺህ ስምንት መቶ ዓመታት የሰው ልጆች እግዚአብሔርን ለማግኘት (ወደ እርሱ መድረስ) የቻሉበት የተስፋና የምሕረት በር የተዘጋ መሆኑ እውነት ቢሆንም፣ ሌላ በር ግን ተከፍቷል፣ ክርስቶስ በቅድስተ ቅዱሳን በሚያደረገው ምልጃ በኩል ለሰዎች የኃጢአት ይቅርታ ተሰጠ። አንደኛው አገልግሎት የተዘጋው ሌላኛው እንዲቀጥል ነበር። ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኛው እያገለገለ በነበረበት በሰማያዊው መቅደስ አሁንም “የተከፈተ በር” ነበር።GCAmh 311.2

    ክርስቶስ በራዕይ ለቤተ ክርስቲያን በዚህ ጊዜ የሰጠው ቃል ተግባራዊነት አሁን ታዬ፤ “የዳዊት መክፈቻ ያለው የሚከፍት የሚዘጋም የሌለ፣ የሚዘጋ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነ እርሱ እንዲህ ይላል። ሥራህን አውቃለሁ እነሆ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼሃለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም።” [ራዕይ 3÷7፣8]።GCAmh 311.3

    ስለ እነርሱ የሚያደርገው ምልጃ ጥቅሞች ተቀባይ የሚሆኑት በስርየት ታላቅ ሥራ የሱስን በእምነት የሚከተሉት ናቸው፤ የዚህን አገልግሎት ወደ ማስተዋል የሚያመጣውን ብርሐን አሻፈረኝ የሚሉ፣ ከእርሱ ምንም ጥቅም አያገኙበትም። በክርስቶስ የመጀመሪያ ምፅዓት የተሰጠውን ብርሐን ያልተቀበሉት አይሁዳዊያን፣ የዓለም አዳኝ እንደሆነም ያምኑ ዘንድ እምቢ ያሉት በእርሱ በኩል የመጣውን ይቅርታ ይቀበሉ ዘንድ አልቻሉም። የሱስ ሲያርግ በራሱ ደም አማካኝነት ወደ ሰማያዊው ቤተ መቅደስ በመግባት የማማለዱን በረከቶች በደቀ መዛሙርቱ ላይ ሲያፈስ ሳለ፣ አይሁዳዊያን ጥቅመ-ቢስ መስዋዕታቸውንና ስጦታቸውን መፈፀም ይቀጥሉ ዘንድ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ተተዉ። የምሳሌዎችና የጥላዎች አገልግሎት አብቅቶ ነበር። ሰዎች በቀድሞ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይገቡበት የነበረው በር ከእንግዲህ ክፍት አልነበረም። መገኘት በሚችልበት በብቸኛው መንገድ፣ በሰማያዊው ቤተ መቅደስ አገልግሎት፣ ይፈልጉት ዘንድ አይሁዳዊያን እምቢ አሉ። በመሆኑም ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትን አላገኙም። ለእነርሱ በሩ ተዘግቷል። ክርስቶስ እውነተኛው መስዋዕት እንደሆነ፣ በእግዚአብሔር ፊት ያለው ብቸኛው አማካይ (አማላጅ) እንደሆነ አያውቁም ነበር። በመሆኑም የማዕከለኛነቱን ጥቅሞች መቀበል አልቻሉም።GCAmh 311.4

    እምነት ያልነበራቸው አይሁዳዊያን ሁኔታ፣ የመሃሪው ሊቀ ካህናችንን ሥራ በፈቃዳቸው አላዋቂ ለመሆን የመረጡትን፣ ግድ የለሽና እምነት የሌላቸውን አማኝ ነን ባይ ክርስቲያኖች ሁኔታ የሚገልጽ ነው። በተምሳሌታዊው ሥርዓት ጊዜ ሊቀ ካህኑ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ሲገባ ሳለ፣ የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኙ ዘንድ ከማህበሩም ከመቆረጥ ይተርፉ ዘንድ፣ ሁሉም እሥራኤላዊያን በመቅደሱ ዙሪያ ተሰብስበው ወደር በሌለው አክብሮት ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት እንዲያዋርዱ ይጠበቅባቸው ነበር። በዚህ በእውነተኛው የስርየት ቀን፣ የታላቁ ሊቀ ካህናችን ሥራ እናስተውል ዘንድ፣ ከእኛ የሚጠበቁት ኃላፊነቶችም ምን እንደሆኑ እናውቅ ዘንድ ከቀድሞው የበለጠ ምን ያህል አስፈላጊ ነው።GCAmh 312.1

    እግዚአብሔር በምህረቱ የሚልክላቸውን ማስጠንቀቂያ አሻፈረኝ ብለው ሰዎች ከቅጣት ነፃ መሆን አይቻላቸውም። በኖህ ዘመን ለዓለም የሚሆን መልእክት ከሰማይ ተልኮ ነበር፤ ያንን መልእክት በሚያደርጉት አድራጎት (በአቀባበላቸው) መዳናቸው ተደግፎ ነበር። ማስጠንቀቂያውን እምቢ በማለታቸው የእግዚአብሔር መንፈስ ከኃጢአተኛው ዘር ተነሳ፤ በጎርፍ ውኃም ጠፉ። በአብርሃም ዘመን፣ ለኃጢአተኞቹ የሰዶም ነዋሪዎች ምሕረት መማፀንዋን አቆመች፤ ከሎጥ፣ ከሚስቱና ከሁለት ሴት ልጆቹ በቀር ከሰማይ በተላከው እሳት ሁሉም አለቁ። በክርስቶስ ዘመንም የሆነው እንዲሁ ነው። እምነት ላልነበራቸው ለዚያ ትውልድ አይሁዳዊያን የእግዚአብሔር ልጅ “እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል”[ማቴ 23÷38] አላቸው። ወደ መጨረሻው ዘመን አቆልቁሎ ሲያይ፣ ያው ዘላለማዊው ኃይል “ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ” ሲናገር “በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመጽ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስህተትን አሰራር ይልክባቸዋል” [2ኛ ተሰሎ 2÷10-12] ይላል። የቃሉን ትምህርቶች አንቀበልም ሲሉ እግዚአብሔር መንፈሱን ከእነርሱ ያነሳና ለሚወዷቸው ማታለያዎች ይተዋቸዋል።GCAmh 312.2

    ነገር ግን ክርስቶስ አሁንም ስለ ሰው ይማልዳል፣ ብርሐን ለሚፈልጉ ለእነርሱ ይሰጣቸዋል። ይህ መጀመሪያ በአድቬንቲስቶች የተስተዋለ ባይሆንም በኋላ ግን ትክክለኛውን አቋማቸውን የሚወስኑት መጻሕፍት(ጥቅሶች) በፊታቸው ሲከፈቱ ግልጽ እየሆነላቸው መጣ።GCAmh 312.3

    የ1844 ዓ.ም ማለፍ የአድቬንቲስትን እምነት አሁንም ይዘው ለነበሩ ታላቅ የፈተና ጊዜ ይዞ መጣ። ትክክለኛ አቋማቸውን በማረጋገጥ ረገድ ብቸኛ እፎይታ የሰጣቸው አዕምሯቸውን ወደ ሰማያዊው ቤተ መቅደስ ያመለከተው ብርሐን ነበር። አንዳንዶች የትንቢት ዘመናትን ያሰሉበት የቀደመው አካሄድ ትክክልGCAmh 312.4

    እንዳልሆነ ካዱ፤ ከአድቬንት ንቅናቄው ጋር የነበረውን የመንፈስ ቅዱስ ኃያል ተጽዕኖ ከፍጡር ወይም ከሰይጣናዊ ወኪሎች እንደመጣ ቆጠሩት። ሌላው ቡድን ደግሞ ባለፈው ልምምዳቸው እግዚአብሔር ሲመራቸው እንደነበረ በማመን ጠንካራ አቋም ያዙ፤ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ያውቁ ዘንድ ሲጠባበቁ፣ ሲተጉና ሲፀልዩ ታላቁ ሊቀ ካህናቸው ወደ ሌላ የአገልግሎት ሥራ እንደገባ አስተዋሉ፤ በእምነት ሲከተሉትም የቤተ ክርስቲያንን የመጨረሻ ሥራ ጭምር እንዲመለከቱ ተመሩ። የመጀመሪያውና የሁለተኛው መልአክ መልእክት የተሻለ ትክክለኛ ግንዛቤ ነበራቸውና የራዕይ 14ን የሶስተኛ መልአክ ክቡር ማስጠንቀቂያ ተቀብለው፣ ለዓለም ይሰጡ ዘንድ የተዘጋጁ ሆኑ።GCAmh 313.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents