Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ታላቁ ተጋድሎ

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፵፩—የምድር ባዶ መሆን

    “ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና እግዚአብሔርም አመፃዋን አሰበ።” “እርስዋ እንደሰጠችው መጠን ብድራት መልሱላት፤ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ስቃይና ኃዘን ስጡአት። በልብዋ፦ ንግስት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ባልቴትም [ባል የሌላት] አልሆንም፣ ኃዘንም ከቶ አላይም ስላለች። ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ኃዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፣ በእሳትም (ፈጽማ) ትቃጠላለች፣ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና። ከእርስዋ ጋር የሴሰኙና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት ስለ እርስዋ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ…. ታላቂቱ ከተማ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን ወዮልሽ፣ በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና።” [ራዕይ 18÷5-10]።GCAmh 470.1

    “ከቅምጥልናዋ የተነሳ ባለጠጋዎች የሆኑ” “የምድር ነጋዴዎች” “ስቃይዋን ከመፍራት የተነሳ ከሩቅ ቆመው፦ በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊ ልብስ ለተጎናፀፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፣ ወዮላት ይህን የሚያህል ባለጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና” [ራዕይ 18÷5-10፣ 3፣ 15-17] ይላሉ።GCAmh 470.2

    የእግዚአብሔር ቁጣ በሚጎበኝበት ጊዜ በባቢሎን ላይ የሚወርዱት ፍርዶች እንዲህ ያሉ ናቸው። የአመጽዋን ጽዋ ሞላች፤ ሰዓትዋም ደርሶአል፣ ለጥፋት ጎምርታለች።GCAmh 470.3

    የእግዚአብሔር ድምጽ የሕዝቦቹን ባርነት በሚለውጥበት ጊዜ፣ በታላቁ የሕይወት ትንቅንቅ፣ ሁሉንም ነገራቸውን ያጡት የእነርሱ መንቃት አስደንጋጭ ይሆናል። የምሕረት ጊዜ በቀጠለበት ዘመን በሰይጣን ማታለያዎች ታውረው የኃጢአት መንገዳቸውን ትክክል አድርገው ቆጥረውት ነበር። እንደ እነርሱ ካልታደሉት መብለጣቸውን በማሳየት ኃብታሞች በኩራት ይምቦጠረሩ ነበር፤ ሆኖም ብልጽግናቸውን ያገኙት የእግዚአብሔርን ሕግ በመጣስ ነበር። የተራበውን ለማብላት፣ የታረዘውን ለማልበስ፣ ፍትህን ለማድረግ፣ ምሕረትንም ለመውደድ ቸል አሉ። ራሳቸውን ከፍ ከፍ ለማድረግ የፍጡር ባልንጀሮቻቸውን ሞገስ ለማግኘት ፈለጉ። አሁን፣ ታላቅ ያደረጋቸውን ሁሉ ተነጠቁ፤ መናጢ ድሆች ሆኑ፤ ያለ ምሽግም ቀሩ። ከፈጣሪያቸው ይልቅ በመረጧቸው ጣኦቶቻቸው ውድመት እጅግ ደነገጡ። ነፍሳቸውን ለምድራዊ ኃብትና ተድላ ሸጡ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለፀጋ ይሆኑ ዘንድ አልወደዱም። ውጤቱም፦ ሕይወታቸው ስኬት-አልባ ሆነ። ደስታዎቻቸው ወደ ብስጭት ተቀየሩ፤ ኃብታቸው ወደ ብልሽት የተለወጠ ሆነ። የእድሜ ልክ ጥሪት በአፍታ ተጠራርጎ ተወሰደ። ታላላቅ፣ ግርማ ሞገስ ያላቸው ቤቶቻቸው ሲፈራርሱ፣ ወርቅ ብሮቻቸው ሲበተኑ ባለፀጎች እርር ኩምትር አሉ። የሰቆቃ እንጉርጉሮአቸው ግን እነርሱም ከጣኦቶቻቸው ጋራ ሊጠፉ በመሆናቸው ፍርሃት ፀጥ ተደረገ።GCAmh 470.4

    ኃጥአን፣ እግዚአብሔርን ወይም ባልንጀሮቻቸውን ቸል በማለታቸው ሳይሆን እግዚአብሔር ስላሸነፈ በፀፀት ተሞሉ። ውጤቱ አሁን የሚታየው ስለሆነ ሙሾ አወረዱ፤ ከኃጢአታቸው ግን ንስሐ አልገቡም። ቢቻላቸውስ ድል ለመንሳት የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም።GCAmh 470.5

    ያላገጡባቸውንና የተሳለቁባቸውን፣ ፈጽመው ያጠፏቸውም ዘንድ የፈለጓቸውን እነዚያውን መደቦች በቸነፈር፣ በማዕበልና በመሬት መናወጥ ውስጥ ምንም ሳይሆኑ ሲያልፉ ዓለም አየ። ለሕጉ ተላላፊዎች እንደሚፋጅ እሳት የሆነው እርሱ ለሕዝቦቹ ከአደጋ መጠለያ እልፍኝ ነው።GCAmh 471.1

    የሰዎችን ሞገስ ለማግኘት እውነትን የሰዋ አገልጋይ የትምህርቶቹ ባህርይና ተጽዕኖ ምን እንደነበር አሁን ተረዳ። ከጠረጴዛው ፊት ሲቆም፣ በጎዳናዎች ሲራመድ፣ በተለያዩ የሕይወት ገጽታዎች ከሰዎች ጋር ሲወያይ ሁሉን የሚያይ አይን ይከተለው እንደነበር ገሃድ ሆነ። እያንዳንዷ የነፍስ ስሜት፣ እያንዳንዷ የተፃፈች መስመር፣ የተነገረችው እያንዳንዷ ቃል፣ በሐሰት ምሽግ ያርፉ ዘንድ ሰዎችን የመራች እያንዳንዷ ተግባር የተበተነች ዘር ነበረች፤ አሁን በዙሪያው ባሉ፣ በተጎሳቆሉና በጠፉ ነፍሳት ዘንድ ምርቱን ተመለከተ።GCAmh 471.2

    እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የሕዝቤን ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን ሰላም ሰላም ይላሉ። እኔም ያላሳዘንሁትን የፃድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፣ በሕይወትም ትኖራለህ ብላችሁ ከክፉ መንገድ እንዳይመለስ የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና።” [ኤር 8÷11፤ ሕዝ 13÷22]።GCAmh 471.3

    “የማሰማሪያየን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው እነሆ የሥራችሁን ክፋት እጎበኝባችኋለሁ።” “ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና….እናንተ እረኞች አልቅሱ ጩኹም፤ እናንተ የመንጋ አውራዎች በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ። ሽሽትም ከእረኞች ማምለጥም ከመንጋ አውራዎች ይጠፋል። (the shepherds shall have no way to flee, nor the principal of the flock to escape.)” [ኤር 23÷1፣2፤ 25÷34፣35]።GCAmh 471.4

    ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ትክክለኛ ግንኙነት ጠብቀው እንዳልቆዩ አገልጋዮችና ሕዝቡ አስተዋሉ። ልክና ፃድቅ የሆነው ሕግ አመንጪ በሆነው ላይ እንዳመፁ ተመለከቱ። መሬት አንድ ሰፊ የጥል ሜዳ፣ አንድ የሙስና ማቋቻ እስክትሆን ድረስ፣ መለኮታዊ መመሪያዎችን ወደ ጎን መገፍተር በሺዎች የሚቆጠሩ የክፋት፣ የፀብ፣ የጥላቻና የኃጢአት ምንጮችን ከፈተ። እውነትን አሻፈረኝ ብለው፣ ስህተትን ሲኮተኩቱ ለነበሩ ለእነርሱ አሁን የሚታያቸው እይታ ይህ ነው። አልታዘዝ ባዮችና እምነት አጉዳዮች ፈጽመው ላያገኙት ያጡትን - የዘላለማዊ ሕይወትን - የማግኘት ጥማታቸውን ምንም ቋንቋ ይገልፀው ዘንድ አይችልም። ለችሎታቸውና ለአንደበተ ርቱዕነታቸው ዓለም ሲያመልካቸው የነበሩ ሰዎች አሁን እነዚህን ነገሮች በትክክለኛ መልካቸው አዩአቸው። በመተላለፍ ያጡት ምን እንደሆነ ገባቸው። ታማኝነታቸውን ሲጠየፉና ሲያፌዙባቸው በነበሩት እግር ላይ ወድቀው፣ እግዚአብሔር እንደሚወዳቸው መሰከሩ።GCAmh 471.5

    ሕዝቡ ሲታለሉ እንደነበረ አስተዋሉ። ወደ ጥፋት የመራኸኝ አንተ ነህ፣ አንቺ ነሽ እየተባባሉ ተወነጃጀሉ፤ ነገር ግን እጅግ መራር ውግዘታቸውን በአገልጋዮች ላይ ለመቆለል ተተባበሩ። እምነት የጎደላቸው እረኞች ስለ መልካም ነገሮች ተንብየዋል። ሰሚዎቻቸው የእግዚአብሔርን ሕግ ዋጋ ቢስ አድርገው፣ በቅድስናው የሚጠብቁትን ደግሞ እንዲያሳድዱ መርተዋል። አሁን በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነው እነዚህ አስተማሪዎች የማታለል ሥራቸውን በዓለም ፊት ተናዘዙ። እልፍ አዕላፋት በቁጣ በገኑ። “ጠፍተናል!” “የውድመታችን ምክንያት ደግሞ እናንተ ናችሁ” አሉ። ከዚያም በሐሰተኛ እረኞች ላይ ተነሱ። በአንድ ወቅት እጅግ አድናቂዎቻቸው የነበሩ እነርሱ ራሳቸው እጅግ አሰቃቂ የሚባለውን እርግማን አዥጎደጉዱባቸው። የክብር ዘውድ ሲደፉላቸው የነበሩት እነዚያው እጆች ሊያጠፏቸው ተዘረጉ። የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ሊያርዱ የነበሩ ሰይፎች አሁን ጠላቶቻቸውን ለማጥፋት ጥቅም ላይ ዋሉ። በሁሉም ስፍራ ጥልና ደም መፋሰስ ሆነ።GCAmh 471.6

    “እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ድምጽ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከስጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፣ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል” [ኤር 25÷31]። ለስድስት ሺህ ዓመታት ታላቁ ተጋድሎ (ተቃርኖ) ሲካሄድ ኖሮአል። የሰውን ልጆች ያስጠነቅቁ፣ እውቀት እንዲኖራቸውና እንዲድኑ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅና ሰማያዊ መልዕክተኞች ከክፉው ኃይል ጋር ሲፋለሙ ቆይተዋል። አሁን ሁሉም ውሳኔአቸውን አድርገዋል፤ ከእግዚአብሔር ጋር ከሚያደርገው ጦርነት ኃጥአን ሙሉ ለሙሉ ከሰይጣን ጋር አብረዋል። የተረገጠው ሕጉ ስልጣን ትክክል እንደሆነ እግዚአብሔር የሚያሳይበት ሰዓት መጥቶአል። አሁን ተቃርኖው ከሰይጣን ጋር ብቻ አይደለም፤… ከሰዎችም ጋር እንጂ። “እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና”፤ “ኃጥአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል።” [ኤርም 25÷31]GCAmh 472.1

    “ስለተሰራው ርኩሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግንባር ላይ” የመዳን ምልክት ተጽፎአል [ሕዝ 9÷4]። አሁን በሕዝቅኤል ራዕይ፣ የሚያጠፉ መሳሪያዎች በያዙ ሰዎች የተወከለው፣ እንዲህ ተብሎም ትዕዛዝ የተሰጠው የሞት መልአክ ይመጣል፦ “ሽማግሌውን፣ ጎበዙን፣ ቆንጆይቱንም፣ ህፃናቶቹንም፣ ሴቶችን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ።” ነብዩ እንዲህ ይላል፦ “በቤቱም አንፃር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።” “They began at the ancient men which were before the house.” [ሕዝ 9÷1-6]። የውድመት ሥራ፣ የሕዝቡ መንፈሳዊ ጠባቆች እንደሆኑ በመሰከሩት መካከል ተጀመረ፤ ሐሰተኛ ዘቦች መጀመሪያ ወዳቂዎች ሆኑ። ሊታዘንላቸው ወይም ሊተርፉ የሚችሉ አንዳች የሉም። ወንዶች፣ ሴቶች፣ ልጃገረዶችና ትናንሽ ልጆች አንድ ላይ ጠፉ።GCAmh 472.2

    “በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቁጣውን ያመጣባቸው ዘንድ እነሆ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ አትከድንም” [ኢሳ 26÷21]። “እግዚአብሔርም ከየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀጽፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው እንደቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዓይኖቻቸውም በአይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፤ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። በዚያም ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ሽብር በእነርሱ ላይ ይሆናል፤ እያንዳንዱም የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ እጁም በባልንጀራው ላይ ይነሳል” [ዘካ 14÷12፣13]። በራሳቸው በሚነደው ፍላጎቶቻቸው የእብደት ጥል ውስጥ ሆነው፣ በኃይል በሚወርደው ባልተቀላቀለው በእግዚአብሔር ቁጣ፣ የምድር ነዋሪዎች ኃጥአን ወደቁ — ካህናት፣ ገዥዎችና ሕዝቡ፣ ባለጠጋና ድኃ፣ የከበረና የተዋረደ “በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይከማቹም፣ አይቀበሩምም።” [ኤር 25÷33]።GCAmh 472.3

    ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ፣ ኃጥአን ከምድረ ገጽ ይጠፋሉ፦ ከአፉ በሚወጣው መንፈስ ይበላሉ፤ በክብሩም ነፀብራቅ ይጠፋሉ። ክርስቶስ ሕዝቦቹን ወደ እግዚአብሔር ከተማ ይወስዳቸዋል፤ ምድርም ነዋሪ-አልባ ትደረጋለች። “እነሆ እግዚአብሔር ምድርን ባዶ ያደርጋታል፤ ባድማም ያደርጋታል፤ ይገለብጣትማል፤ በእርስዋም የተቀመጡትን ይበትናል።” “ምድር መፈታትን ትፈታለች፤ ፈጽማም ትበላሻለች፤ እግዚአብሔር ይህንን ቃል ተናግሯልና።” “ሕጉን ተላልፈዋልና ስርዓቱንም ለውጠዋልና የዘላለሙን ቃል ኪዳንም አፍርሰዋልና። ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች፤ በእርስዋም የተቀመጡ ይቀጣሉ፤ ስለዚህ የምድር ሰዎች ይቃጠላሉ፣ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።” [ኢሳ 24÷1፣3፣5፣6]።GCAmh 472.4

    መላዋ ምድር ምንም የሌለባት ምድረ በዳ መሰለች። በመሬት መንቀጥቀጥ የወደሙት ከተሞችና መንደሮች፣ የተፈነገሉት ዛፎች፣ በባህር የተወረወሩት ወይም በምድር በራስዋ የተተፉት የተሰነጣጠቁ ቋጥኞች፣ በምድር ላይ ተበትነዋል፤ ከምድር በታች ያሉ ዋሻዎችም ከመሰረታቸው የተቀደዱት ተራሮች የት እንደነበሩ ምልክት ሆኑ።GCAmh 473.1

    አሁን በስርየት ቀን በሚደረገው የመጨረሻው ክቡር አገልግሎት የተመሰለው ክስተት ይከናወናል። በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የሚከናወነው አገልግሎት፣ በኃጢአትም መስዋዕት ደም አማካኝነት የእሥራኤል ኃጢአት በተወገደ ጊዜ፣ የሚለቀቀው ሕያው ፍየል በእግዚአብሔር ፊት ይቀርብ ነበር፤ የሊቀ ካህኑም ጉባኤ ባለበት በእርሱ ላይ “የእሥራኤልን ልጆች በደል ሁሉ መተላለፋቸውንም ሁሉ ኃጢአታቸውንም ይናዘዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመው” [ዘሌዋ 16÷21] ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ የስርየት ሥራ በሰማያዊው መቅደስ በተፈፀመ ጊዜ፣ በእግዚአብሔርና በሰማያዊ መላእክት ፊት፣ በተዋጁትም ሰራዊት ፊት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ኃጢአት በሰይጣን ላይ ይደርጋል፤ እንዲፈጽሙት ላደረጋቸው ክፋት ሁሉ ጥፋተኛ መሆኑ ይታወጃል። የሚለቀቀው ፍየል ሰው ወደማይኖርበት ምድረበዳ ይሰደድ እንደነበረ፣ እንዲሁ ሰይጣን ባዶ ወደ ሆነችው፣ ማንም ወደማይኖርባት፣ ቀፋፊ ምድረ በዳ ወደሆነችው ምድር ይለቀቃል።GCAmh 473.2

    ስለ ሰይጣን መወገድ፣ ምድርም ወደምትገባበት የምስቅልቅልና የውድመት ሁኔታ ገላጩ [የሱስ] አስቀድሞ ይናገራል። ይህ ሁኔታም ለአንድ ሺህ አመት እንደሚቆይ ይናገራል። የጌታን ዳግም ምፅዓት ትዕይንቶችና የኃጥአንን ጥፋት ከገለፀ በኋላ ትንቢቱ ይቀጥላል፦ “የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። የቀደመውንም እባብ ዘንዶውንም እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፣ ሺህ ዓመትም አሰረው፣ ወደ ጥልቅም ጣለው አሕዛብንም ወደፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈፀም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማህተም አደረገበት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ ይገባዋል።” [ራዕይ 20÷1-3]።GCAmh 473.3

    “ጥልቁ [ዲካ የሌለው ጉድጓድ/bottomless pit]” የሚለው አገላለጽ በምስቅልቅልና በጽልመት ውስጥ የምትሆነውን ምድር እንደሚወክል በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችም ማስረጃ አለ። “በመጀመሪያ” ስለነበረው የምድር ሁኔታ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገብ “ምድርም ባዶ ነበረች፤ አንዳችም አልነበረባትም (without form & void)፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ” ይላል [ዘፍጥረት 1÷2]። [እዚህ ላይ “በጥልቁ፣ deep” ተብሎ የተተረጎመው ቃል በራዕይ 20÷1-3 “ጥልቁ፣ bottomless” ተብሎ ከተተረጎመው ጋር ተመሳሳይ ነው]። ቢያንስ በከፊል ምድር ወደዚህ ሁኔታ እንደምትመለስ ትንቢት ያስተምራል። ወደ ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን እየተመለከተ ነብዩ ኤርምያስ እንዲህ ይላል፦ “ምድሪቱንም አየሁ፤ እነሆም ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም [was without form & void]፤ ሰማያትንም አየሁ፣ ብርሐንም አልነበረባቸውም። ተራሮችን አየሁ እነሆም ተንቀጠቀጡ፣ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ። አየሁ እነሆም ሰው አልነበረም፣ የሰማይም ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር። አየሁ እነሆም ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፤ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቁጣው የተነሳ ፈርሰው ነበር” [ኤር 4÷23-27]።GCAmh 473.4

    የሰይጣንና የክፉ መላእክት የአንድ ሺህ ዓመት መኖሪያ የሚሆነው እዚህ ነው። ያልወደቁትን ይፈትንና ይረብሽ ዘንድ ወደሌሎች ዓለማት መግባት አይፈቀድለትም፤ በምድር የተወሰነ ይሆናል። ታሰረ የሚባለው ከዚህ አንፃር ነው፤ ኃይሉን የሚጠቀምባቸው የሚቀሩ አንዳች ነገሮች የሉም። ለብዙ ምዕተ ዓመታት ብቸኛ ደስታው ከነበረው የማታለልና የማጥፋት ሥራው ሙሉ ለሙሉ ይለያያል።GCAmh 474.1

    ነብዩ ኢሳይያስ ስለ ሰይጣን ከስልጣን መውረድ ሲመለከት እንዲህ ይላል፦ “አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቆረጥህ!” “አንተ በልብህ ወደ ሰማይ አርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ።” “በልዑልም እመሰላለሁ (I will be like the Most High) አልህ። ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓድም ጥልቅ ትወርዳለህ። የሚያዩህ ይመለከቱሃልና፦ በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ መንግሥታትንም ያናወጠ፣ ዓለሙንም ሁሉ ባድማ ያደረገ፣ ከተሞችንም ያፈረሰ ምርኮኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን ብለው ያስተውሉሃል።” [ኢሳ 14÷12-17]።GCAmh 474.2

    ለስድስት ሺህ አመት የቀጠለው የሰይጣን የአመጽ ሥራ “ምድርን ያንቀጠቀጠ” ነበር። “ዓለሙን ሁሉ ባድማ አደረገ፤ ከተሞችንም አፈረሰ”፤ “ምርኮኞችንም ወደ ቤታቸው አልሰደደም።” ለስድስት ሺህ አመት እስር ቤቱ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ተቀብሎአል፤ ለዘላለምም እስረኛ አድርጎ ይይዛቸው ነበር። ሆኖም ግን ክርስቶስ እሥራቱን ፈትቶ እስረኞችን ነፃ አድርጓል።GCAmh 474.3

    አሁን ኃጥአን እንኳ ከሰይጣን ኃይል ውጭ ሆነዋል። ኃጢአት ያመጣውን የእርግማን ውጤት እንዲያስተውል ከክፉ መልአክቱ ጋር ብቻውን ቀርቷል። “የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ በቤታቸው በመቃብር በክብር አንቀላፍተዋል። አንተ ግን እንደተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል (ወጥተሃል)….ምድርህን አጥፍተሃልና ሕዝብህንም ገድለሃልና ከእነርሱ ጋር በመቃብር በአንድነት አትሆንም።” [ኢሳ 14÷18-20]።GCAmh 474.4

    የእግዚአብሔርን ሕግ በመቃወም ማመጽ የሚያመጣውን ውጤት ያይ ዘንድ በምድረበዳዋ ምድር ለአንድ ሺህ ዓመታት ወዲያ ወዲህ ይንከራተትባታል። በዚህ ጊዜ ስቃዩ እጅግ ከባድ ነው። ከወደቀ ጀምሮ የማያቋርጥ የሥራ ሕይወቱ የጥሞና ማሰላሰሉን አጥፍቶበታል (በጥንቃቄ የማሰብ ችሎታው/ትውስታው ጠፍቶአል)፤ አሁን ግን ኃይሉን አጥቶ፣ በሰማይ መንግሥት ላይ ካመጸ ከመጀመሪያ ጊዜ አንስቶ ስለተጫወተው ሚና እንዲያሰላስል፣ ስለሰራው ክፋት ሁሉ፣ ስለሚሰቃይበት የወደፊት አስፈሪ ክስተት፣ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዲጠብቅ፣ እንዲሰሩ ምክንያት ስለሆነባቸው ኃጢአቶችም እንዲቀጣ ተትቶአል።GCAmh 474.5

    የሰይጣን መታሰር ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ደስታንና ሐሴትን ያመጣል። ነብዩ እንዲህ ይላል፦ “በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከኃዘንህና ከመከራህ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል፤ ይህንንም ምሳሌ በባቢሎን ንጉሥ [እዚህ ላይ ሰይጣንን የሚወክል ነው] ላይ ታነሳለህ። እንዲህም ትላለህ፦ አስጨናቂ እንዴት አረፈ [ተወ]! አስገባሪም እንዴት ፀጥ አለ! እግዚአብሔር የዝንጉዎችን በትር ሰበረ፤ የሰለጠኑትንም ሽመላ። አሕዛብን በቁጣው የመታ፣ በማያቋርጥ መምታት። በመዓቱም አሕዛብን በታቹ ያደረገ፣ አሳዳጃቸው የሚከለክለው ሳይኖር።” [ኢሳ 14÷3-6]።GCAmh 474.6

    በሺህ አመት ጊዜ፣ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ትንሳኤ መካከል፣ የኃጥአን ፍርድ ይከናወናል። ሐዋርያው ጳውሎስ ስለዚህ ፍርድ ሲያመለክት ዳግም ምፅዓቱን ተከትሎ የሚመጣ ክስተት እንደሆነ ይጠቁማል። “ስለዚህ በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሐን የሚያመጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ” [1ኛ ቆሮ 4÷5]። ዳንኤልም ሲናገር በዘመናት የሸመገለው በመጣ ጊዜ “ፍርድ ለልዑል ቅዱሳን ተሰጣቸው” [ዳንኤል 7÷22]። በዚህ ጊዜ ፃድቃን ለእግዚአብሔር እንደ ነገሥታትና ካህናት ሆነው ይነግሳሉ (ይገዛሉ)። ዮሐንስ በራዕይ እንዲህ ይላል፦ “ዙፋኖችንም አየሁ፣ በርሳቸውም ተቀመጡባቸው፣ ፍርድም ተሰጣቸው።” “የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ሺህ ዓመት ይነግሳሉ” [ራዕይ 20÷4፣6፤ 1ኛ ቆሮ 6÷2፣3]። በጳውሎስ አስቀድሞ እንደተነገረው “ፃድቃን በዓለም ላይ የሚፈርዱት” በዚህ ጊዜ ነው [ራዕይ 20÷4፣6፤ 1ኛ ቆሮ 6÷2፣3]። ሥራቸውን ከሕጉ መጽሐፍ (ከመጽሐፍ ቅዱስ) ጋር እያወዳደሩ በአካል ላይ እንደተሰራው መጠን እያንዳንዱን ጉዳይ እየወሰኑ፣ ከክርስቶስ ጋር በአንድነት በኃጥአን ላይ ይፈርዳሉ። ከዚያም ኃጥአን ሊገጥማቸው ያለው የስቃይ ፈተና እንደሥራቸው ተለክቶ ይቀመጣል። በየስማቸውም አንጻር በሞት መጽሐፍ ይሰፍራል።GCAmh 475.1

    ሰይጣንና ርኩስ መላእክቱም በክርስቶስና በሕዝቦቹ ይዳኛሉ። ጳውሎስ ይላል፦ “በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን?” [ራዕይ 20÷4፣6፤ 1ኛ ቆሮ 6÷2፣3]። ይሁዳም ሲናገር፣ “መኖሪያቸውን የተውትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እሥራት ከጨለማ በታች እስከታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቋቸዋል።” [ይሁዳ 6]። በሺው አመት መጨረሻ ሁለተኛው ትንሣኤ ይሆናል። “የተጻፈው ፍርድ” ይተገበር ዘንድ በእግዚአብሔርም ፊት ይቀርቡ ዘንድ ኃጥአን ከሞት ይነሳሉ። እዚያም ገላጩ[የሱስ] የጻድቃንን ትንሣኤ ካብራራ በኋላ እንዲህ ይላል፣ “የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ አመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አይኖሩም” [ራዕይ 20÷5]። ኢሳይያስም ኃጥአንን በተመለከተ ሲናገር፣ “ግዞተኞች በጉድጓድ እንደሚከማቹ በአንድነት ይከማቻሉ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፣ ከብዙ ቀንም በኋላ ይጎበኛሉ።” [ኢሳ 24÷22]።GCAmh 475.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents