Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    10—የመጨረሻዎቹ መቅሰፍቶችና ፍርድ

    በወርሃ መስከረም 1850 ዓ.ም. ላይ በሰቶን ቬርሞንት በወቅታዊው እውነት አማኞች በተደረገ የጀነራል ኮንፈረንስ ጉባዔ የሱስ መቅደሱን ለቅቆ ሲወጣ ሰባቱ የመጨረሻ መቅሰፍቶች እንደሚወርዱ ተመልክቼ ነበር መልአኩ እንዲህ ሲል ተናገረ «ለኃጥአን ጥፋትና ሞት መንስዔ የእግዚአብሔርና የበጉ ቁጣ ነው፡፡ አምላካዊውን ሰንደቅ ያነገበው የእግዚአብሔር ሠራዊት በእግዚአብሔር ድምፅ ብርቱ ቢሆንም ነገር ግን የተጻፈው ፍርድ በዚያን ወቅት ገቢራዊ አይሆንም፡፡ ፍርዱ ገቢራዊ የሚሆነው በአንድ ሺሁ ዓመት መዝጊያ ላይ ነው፡፡» EWAmh 35.1

    ጻድቃን የማይሞተውን ለብሰው ተለውጠውና ከየሱስ ጋር በአንድነት በደመና ከተነጠቁ በኋላ፣ በገናዎቻቸውን፣ መጎናጸፊያቸውንና ዘውዳቸውን ተቀብለው ወደ ከተማዋ ይገባሉ፡፡ የሱስና ጻድቃን ለፍርድ ይቀመጣሉ---የህይወትና የሞት መጽሐፍትም ይከፈታሉ፡፡ የህይወት መጽሐፍ የቅዱሳኑን መልካም ተግባራት የያዘ ሲሆን የሞት መጽሐፍ ደግሞ የኃጥአኑን ክፉ ተግባራት ይዞአል፡፡ እነዚህ መጻሕፍት ከሕግ መጻሕፍት፣ ከመጽሐፍ ቅዱስና ሰዎች ከሚዳኙባቸው መንገዶች ጋር ይስተያያሉ፡፡ ጻድቃን ከየሱስ ጋር በአንድ ድምጽ በሟች ኃጥአን ላይ ፍርዳቸውን ይሰጣሉ፡፡» መልአኩ ልብ ብለሽ ተመልከች በማለት «ከየሱስ ጋር በፍርድ የተቀመጡት ጻድቃን---ኃጥአን በምድራዊ ህይወታቸው በሠሩት መጠን ይፈርዷቸዋል፡፡ ይህ እነርሱ የሚቀበሉት ፍርድ በስሞቻቸው ተርታ ተቀምጦአል፡፡» አለኝ፡፡ የተመለከትኩት ነገር ቅድስቲቱ ከተማ ወደ ምድር ከመውረዷ አስቀድሞ ቅዱሳኑ ለአንድ ሺህ ዓመት ከየሱስ ጋር በሚነግሡበት ወቅት የሚሠሩትን ሥራ ነበር ከዚያም በአንድ ሺሁ ዓመት መዝጊያ ላይ የሱስ ከመላእክቱና ከመላው ጻድቃን ጋር በአንድነት በመሆን ቅድስቲቱን ከተማ ትተው ሲወርዱ---ሞተው የነበሩ ሙታን---በተለይም እርሱን «የወጉት” ሰዎች ይነሳሉ---ከመላእክቱና አብረውት ከነበሩት ቅዱሳን ጋር ሆኖ በሙሉ ግርማው በሩቁ ይመለከቱታል---ከእርሱ የተነሳም ዋይ ዋይ ይላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች የአጆቹንና የእግሮቹን ምስማሮች ጠባሳ እንዲሁም በጦር የወጉትን ጎኑን ይመለከታሉ፡፡ የምስማሮቹና የጦሩ ጠባሳ የርሱ ክብር ይሆናሉ፡፡ የሱስ በደብረዘይት ተራራ ላይ የሚቆመውና ተራራው ተከፍሎ የኃያል መስክ ገጽታን የሚላበሰው በአንድ ሺሁ ዓመት መጨረሻ ላይ ነው፡፡ በወቅቱ ከፊቱ የሚኮበልሉ ከሞት የተነሱ ኃጥአን ናቸው፡፡ ከዚያም ቅድስቲቱ ከተማ ከሰማይ ትወርድና በታላቁ መስክ ላይ ታርፋለች በዚህን ወቅት ሰይጣን በመንፈሱ አማካኝነት ኃጥአንን ያነሳሳል፡፡ በከተማዋ ያለው ሠራዊት አነስተኛ---የእርሱ ሠራዊት ግን ግዙፍና ኃያል እንደሆነ በማውሳት ቅዱሳኑን አሸንፈው ከተማዋን ይነጥቁ ዘንድ ይሸነግላቸዋል፡፡ EWAmh 35.2

    በተመካበት በዚያን ወቅት ቅዱሳኑ የእግዚአብሔርን ገነት ውበትና ክብር እየተመለከቱ በከተማቸው ውስጥ ነበሩ፡፡ የሱስ ከበላያቸው ሆኖ እየመራቸው ነበር፡፡ ለቅጽበት ያህል ጊዜ ያ ተወዳጁ አዳኛችን ከመካከላችን ሄዶ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ወዲያውኑ «ኑ እናንተየአባቴ ብሩካን፤ ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” የሚል ተወዳጅ ድምጹም ስንሰማ በእርሱ ዙሪያ ተሰባሰብን፡፡ ከዚያም እርሱ የከተማዋን በራፎች እንደዘጋቸው እርግማኖቹ በኃጠአኑ ላይ ወረዱ፡፡ ጻድቃን ክንፎቻቸውን ተጠቅመው ወደ ከተማዋ ግንብ ጫፍ ላይ ወጡ፡፡ የሱስም ከእነርሱ ጋር አብሮአቸው የነበረ ሲሆን፤ አናቱ ላይ የደፋው ዘውድ እጅግ ውብና ባለ ግርማ ነበር፡፡ ቁጥሩ ሰባት የሚደርስ---በዘውድ ላይ የተነባበረ ዘውድ ደፍቶ ነበር የጻድቃኑ ዘውዶች በከዋክብት የተንቆጠቆጡ እጅግ ንጹህ ወርቆች ነበሩ፡፡ የእነዚህ የየሱስን ገጽታ የሚያንጸባርቁ ሕዝቦች ፊት በክብር ያበራ ነበር፡፡ በአንድነትም ብድግ ብለው ወደ ከተማዋ ጫፍ ሲተሙ ሳለ በትዕይንቱ አብልጬ ተደነቅኩ፡፡ EWAmh 36.1

    ኃጥአን ያጡትን ነገር ተመለከቱ ከዚያም ከእግዚአብሔር ትንፋሽ የወጣ እሳት በላያቸው ላይ ወርዶ በላቸው፡፡ ይህ የፍርዱ ፍጻሜ ነበር በአንድ ሺሁ ዓመት የፍርድ ምርመራ ጻድቃን ከየሱስ ጋር በአንድ ድምጽ የሰጡትን ፍርድ ኃጥአን ተቀበሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ወጥቶ በኃጥአን ላይ የወረደው ያው እሳት መላውን ምድር አነጻው፡፡ ብጥስጣሽና ያረጁ ተራሮች በኃይለኛው ሙቀት ቀለጡ፤ ይህ እሳት ከባቢውን አየር እንኳ ሳይቀር በላው፡፡ ከዚህ በኋላ እጅግ ግርማ ያለውና ያማረው---የወረስነው ነገር ከፊታችን ተገለጠ--- እነሆ መላዋን አዲሲቱን ምድር ምድር ወረስን፡፡ ሁላችንም ድምጾቻችንን ከፍ አድርገን «ከብር ይሁን---ሐሌሉያ!” በማለት ጮኽን፡፡ EWAmh 36.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents