Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    18—ጸሎትና እምነት

    የጌታ ልጆች መጸለይን ችላ እንዳሉ ያለማቋረጥ ተመልክቼ ነበር---በተለይ የምስጢር ጸሎት፡፡ ብዙውን ጊዜ ስሜታቸውን ብቻ በመከተላቸው ልዩ መበትና ግዴታቸው የሆነው እምነታቸውን የመለማመዱ ተግባር አይታይባቸውም ነበር፡፡ ስሜት እምነት ባለመሆኑ እነዚህ ሁለቱ የተለያዩ ናቸው፡፡ እምነት የምንለማመደው የእኛ የሆነ ነገር ሲሆን በሐሴት የተሞሉ ስሜቶችና በረከቶች ደግሞ ከእግዚአብሔር የሚሰጡ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ ህያው በሆነ የእምነት መስመር ውስጥ አልፎ ወደ ነፍስ የሚደርስ ሲሆን ያንን እምነት የመለማመዱ ኃይል ያለው በእኛው ውስጥ ነው፡፡ EWAmh 52.1

    እውነተኛ እምነት ጥልቅ ግንዛቤ ከማግኘታችንና ስሜቱን ከመጋራታችን አስቀድሞ የተባረከውን ተስፋ የግል ማድረግ ላይ የተመሰረተነው፡፡ ልመናችንን በሁለተኛው መጋረጃ ውስጥ ወዳለው በእምነት በመላክ እምነታችን የተባረከውን ተስፋ እንዲጨብጥ መፍቀድና የግላችን ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህ ሲሆን እምነታችን ደግፎ የያዘውን በረከት መቀበላችንን እንደ ቃሉ ማመን አለብን «ስለዚህ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደ ተቀበላችሁ አድርጋችሁ ብታምኑ ይሆንላችኋል” (ማር. 11:24): እዚህ ላይ ገና በቅጡ ልብ ሳንለው በረከቶቹን እንደተቀበልን አድርገን የምናምንበትን እርቃኑን የቆመ እምነት እናገኛለን፡፡ ቃል የተገባው በረከት በቅጡ ሲስተዋልና በዚያም ሐሴት ማድረግ ሲጀመር እምነት እየተዋጠ ይሄዳል፡፡ ነገር ግን ከፍ ያለውን መጠን መንፈስ ቅዱስ ካልወሰደውና የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ካልተሰማቸው በቀር እምነት ሊኖራቸው እንደማይችል አድርገው ብዙዎች ይገምታሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ አካሄድ እምነት--በእምነት ከሚገኘው በረከት ጋር እንዲምታታ ያደርጋል፡፡ እምነትን የምንለማመድበት በጣም አመቺው ጊዜ በመንፈስ ምስኪን መሆናችን ሲሰማን ነው፡፡ ጥቅጥቅ ያሉና በጽልመት የተዋጡ ደመናዎች በአእምሮአችን ላይ ሲያልፉ ያኔ ህያው እምነት ጨለማውን በስቶ ደመናዎቹን ይበትናቸዋል፡፡ እውነተኛ እምነት በእግዚአብሔር ቃል በተሰጡ ተስፋዎች ላይ ያርፋል፡፡ ይህን አምላካዊ ቃል የሚታዘዙ ብቻ አስደናቂዎቹን ተስፋዎች የራሳቸው ያደርጋሉ «በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተቢኖሩ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ ይሰጣችኋልም” (ዮሒ. 15:7)፡፡ «ትእዛዛቱንም ስለምንጠብቅና በፊቱም ደስ የሚያሰኘውን ስለምናደርግ የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እንቀበላለን” (1ኛ ዮሐ. 3፡፡22)፡፡ EWAmh 52.2

    የምስጢር ጸሎታችንን አብልጠን ማድረግ አለብን፡፡ ክርስቶስ የወይን ግንድ ሲሆን እኛ ደግሞ ቅርንጫፎች ነን፡፡ በመሆኑም ማደግና ማበብ እስካለብን ድረስ ህያው ከሆነው ወይን ያለማቋረጥ መጠጣትና መመገብ አለብን፡፡ ነገር ግን ከወይኑ ከተለየን አንዳችም ብርታት አይኖረንም፡፡ EWAmh 53.1

    በእስራኤል እምነትና ኃይል መኖሩ ያከተመው ለምን እንደሆነ መልአኩን ጠየቅኩት፡፡ እርሱም እንዲህ አለኝ «ከዚህ ስፍራ ስትሄጂ ልመናሽን በጠንካራ እምነት ወደ ዙፋኑ አቅርቢ፡፡ የተሰጡት ተስፋዎች የታመኑ ናቸው፡፡ እመኚ የለመንሻቸውንም ነገሮች ታገኛለሽ፡፡” ከዚያም ወደ ኤልያስ እንድመለከት ሆንኩ፡፡ እርሱ ልክ እንደ እኛ ስሜቱን ተከትሎ መሄድ ይችል የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በጽናት ጸለየ፡፡ እምነቱ ፈተናን እንዲያልፍ አስቻለው፡፡ በጌታ ፊት ሰባት ጊዜ ከጸለየ በኋላ በመጨረሻ ደመናው ታየ እኛ የታመኑትን ተስፋዎች በመጠራጠር በእምነታችን ማነስ አዳኙን እንዳቆሰልነው ተመልክቻለሁ፡፡ ገብርኤል እንዲህ ሲል ተናገረ «የጦር ትጥቅሽን ልበሺ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ የእምነት ጋሻ ውስጂ፡፡ ጋሻው ልብሽንና ህይወትሽን ከክፉ ፍላጻ ይጠብቅልሻል»፡፡ ጠላት ተክዘው የተቀመጡትን ዓይኖች ከየሱስ ላይ በመንቀል በፍቅሩ፣ በከፈለው ዋጋና ታላቅ በሆነው ምህረቱ በመኖር ፋንታ ወደራሳቸው እንዲመለከቱ ማድረግ ከቻለ፤ ለሚያቀርብላቸው ጸንፈኛ ፈተናዎች የተጋለጡ በመሆን የእምነት ጋሻዎቻ ቸውን አስወግዶ ያለመውን ማግኘት ይችላል፡፡ በመሆኑም ደካሞች ወደ የሱስ በመመልከትና በእርሱ በማመን እምነትን ሊለማመዱ ይገባል፡፡ EWAmh 53.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents