Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    70—የምድር ባዶ መሆን

    ትኩረቴ እንደገና ወደ ምድር ሆነ፡፡ ኃጥአን ጠፍተው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሙት አካላቸው በምድር ላይ ተዘርሮ ይታይ ነበር የመጨረሻዎ ቹን መቅሰፍቶች የያዘው የእግዚአብሔር ቁጣ የምድር ነዋሪዎችን በመጎብኘ ቱ ኃጥአን ከህመም የተነሳ ጥርሶቻቸውን እንዲያፋጩና እግዚአብሔርን እንዲራገሙ አድርጎአቸው ነበር ለያህዌ ቁጣ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች የነበሩት ሐሰተኛ እረኞች ዐይኖቻቸው ወደ ውስጥ ሰርጉደውና ምላሳቸው በላንቃቸው ላይ ተጣብቆ ነበር፡፡ ቅዱሳን በእግዚአብሔር ድምፅ ከዳኑ በኋላ ኃጥአን እርስ በርስ በቀላቸውን ይወጡ ጀመር ምድር በደም ጎርፍ የተሞላች መሰለች:: ሙት አካል ከአንደኛው የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው EWAmh 215.1

    የተተወች ምድረበዳ መሰለች፡፡ ከተሞችና መንደሮች በርዕደ መሬት ወደሙ:: ተራሮች ታላላቅ ሸለቆዎችን እየተዉ ከስራቸው እየተነቀሉ ተነሱ፡፡ ትላላቅ ዐለቶች ከባህርም ሆነ ከደረቁ መሬት እየተተፉ በመበተን ስፍራውን ሁሉ ሞሉት፡፡ ግዙፍ ዛፎች ከነሥራቸው በመነቀል በምድሪቱ ላይ ተንጋለሉ፡፡ እንዲህ ያለው የተመሰቃቀለና የወደመ ምድር የሰይጣንና መላእክቱ የሚቀጥሉት አንድ ሺህ ዓመታት መኖሪያ ይሆናል፡፡ ሰይጣን በዚህ መልኩ በግዞት በመኖር በወደመው የምድር ገጽ ላይ ወዲያና ወዲህ እየተቅበዘበዘ በእግዚአብሔር ሕግ ላይ የማመጹን ውጤት ይመለከታል፡፡ ለአንድ ሺህ ዓመት እርሱ መንስዔ የሆነበትን የእርግማን ፍሬ ይቀምሳል፡፡ ሰይጣን ወዳልወደቁት ዓለማት በመሄድ እንዲበጠብጥ ስለማይፈቀድለት በምድር ላይ ብቻውን ይወሰናል፡፡ በእነዚህ ዘመናት ሰይጣን ከመጠን በላይ የሆነ ሥቃይ ይደርስበታል፡፡ እርሱ ውድቀት ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ ክፉ ባህሪውን ያለማቋረጥ ሲለማመድ ቢኖርም ነገር ግን በዚያን ጊዜ ኃይሉ ተነፍጎ ከውድቀቱ አንስቶ ሲሠራ የኖረውን እንዲመለከት ይተዋል፡፡ ሰይጣን ለፈጸመው የክፋት ተግባርና ሌሎች ኃጢአት እንዲሠሩ መንስዔ ለመሆኑ ቅጣቱን የሚቀበልበትን አስፈሪ መጨረሻውን--- ፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ይመለከታል፡፡ EWAmh 215.2

    ከዚህ በኋላ መላእክትም ሆኑ የዳኑት ቅዱሳን በሰይጣን ፈተናም ሆነ ችግር ስለማይደርስባቸው እንዲሁም ያልወደቁት ሌሉች ዓለማት ከአርሱ መገኘትና ፈተና ነጻ በመሆናቸው የተዋጁትና መላእክት እንደ አስር ሺህ የሙዚቃ መሣሪያዎች ያለ የድል ጩኸት ሲያስተጋቡ አደመጥኩ፡፡ EWAmh 215.3

    በመቀጠል የሱስና የዳኑት የተቀመጡባቸውን ዙፋኖች ተመለከትኩ፡፡ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ነገሥታትና ካኅናት ሆነው ነግሠዋል፡፡ ክርስቶስ ከዳኑት ቅዱሳን ጋር በመሆን የሞቱትን ኃጥአን ህይወት በእግዚአብሔር ቃል መሰረት በመጽሐፉ ተጸፎ ከሚገኘው ጋር በመመርመር ሲዳኙ ተመለከትኩ፡፡ ኃጥአን እንደ ሥራቸው ክብደት የሚከፈላቸው ሲሆን ቅጣታቸው ከስማቸው ትይዩ በሞት መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ነበር፡፡ ዕይጣን የሚቀበለው ቅጣት እርሱ ካሳታቸው በእጅጉ የላቀ ነበር በመሆኑም የእርሱ ሥቃይ ከእነርሱ ጋር መወዳደር የሚችል አልነበረም: ደግሞስ እርሱ ያሳታቸው ሁሉ ጠፍተው እርሱ ግን ብቻውን በመኖሩ እየተሰቃየ አይደል? EWAmh 216.1

    የኃጥአን ፍርድ ሥራ ካበቃ በኋላ በአንድ ሺሁ ዓመት መጨረሻ ላይ የሱስ ከተማዋን ትቶ ሲወጣ ቅዱሳንና የመላእክት ሰራዊት ተከትለውት ወጡ፡፡ የሱስ በታላቅ ተራራ ላይ ወረደ፡፡ እግሮቹ ተራራውን ሲነኩ ተራራው ተከፈለና ወደ ግዙፍ መስክነት ተቀየረ፡፡ ከዚያም ቀና ብለን ታላቅና ውብ የሆነችውን ከተማ ተመለከትን፡፡ ከተማዋ አሥራ ሁለት መሰረቶችና በሮች የነበሯት ሲሆን በያንዳንዱ በራፍ ላይ አንዳንድ መላእክት ነበሩ፡፡ እኛ ም «ከተማዋ! ታላቂቱ ከተማ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደች!” ብለን ጮኽን:: ከዚያም በታላቅ ክብር የሱስ ባዘጋጀው ግዙፍ ሜዳ ላይ አረፈች:: EWAmh 216.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents