Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    11—የ2300 ቀናት መጨረሻ

    ዙፋን ተመልክቼ የነበረ ሲሆን በላዩም ላይ አብና ወልድ ተቀምጠውበት ነበር፡፡ ወደ የሱስ ገጽታ መልከት አደረኩና ተወዳጅ ማንነቱን አደነቅኩ፡፡ የአብ አካላዊ ማንነት ክብር በተሞላ ስስ ደመና ተሸፍኖ ስለነበር ልመለከተው አልቻልከም: አብ የእርሱ ዓይነት አካላዊ ቅርጽ እንዳለው የሱስን ጠየቅኩት እርሱም እንዳለው ነገረኝና ነገር ግን ልመለከተው እንደማልችል በማውሳት «የእርሱን አካላዊ ማንነት ክብር ለአፍታ እንኳ ብትመለከች መኖር ታቆሚያለሽ» አለኝ፡፡ የአድቬንቲስት እምነት ተከታዮችን፣ ቤተክርስቲያኒቱንና ዓለምን በዙፋኑ ፊት ሆነው አየሁ: በወቅቱ ሁለት ቡድኖችን የተመለከትኩ ሲሆን አንደኛው ከውስጥ በመነጨ ጥልቅ ፍላጎት በዙፋኑ ፊት አጎንብሶ የሚሰግድ--ሌላው ደግሞ ያለ ፍላጎቱ በግዴለሽነት የቆመ ነበር፡፡ በዙፋኑ ፊት አጎንብሰው የነበሩ ጸሎታቸውን ያቀርl ---ወደ የሱስም ይመለከቱ ነበር፡፡ እርሱም ወደ አባቱ መልከት በማድረግ ተማጽኖውን ሲያቀርብ ብርሃን ከአብ ዘንድ ይወጣና በወልድ ላይ ያርፋል፤ ከወልድም ወደ ሚጸልዩት ቡድኖች ይተላለፋል፡፡ ከዚያም እየጨመረ የሚሄድ የሚያንጸባርቅ ብርሃን ከአብ ውስጥ በመውጣት ወደ ልጁ--- ከልጁም በዙፋኑ ፊት ወደ ነበሩት ሐዝቦች እንደ ሞገድ ተላለፈ፡፡: ነገር ግን ይህን ታላቅ ብርሃን ይቀበሉ የነበሩ በጣም ጥቂቶች ነበሩ፡፡ ብዙዎች ከዚህ ስር በመውጣት ወዲያውኑ ላለመቀበል ተቃውሞአቸውን አሰሙ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ግዴለሾችና ለበርሃኑ ተገቢውን ዋጋ ያልሰጡ ስለነበሩ ብርሃኑ ከእነርሱ ላይ ተነስቶ ሄደ፡፡ ነገር ግን ጥቂቶች ተገቢውን ዋጋ በመስጠታቸው አነስተኛ ቁጥር ካላቸው የጸሎት ቡድኖች ጋር ማጎንበሳቸውን ገፉበት፡፡ የዚህ ቡድን አባላት በሙሉ ብርሃኑን በመቀበል ደስ ተሰኝተውበታል---ገጽታቸውም በክብሩ አብርቶአል EWAmh 37.1

    አብ ከዙፋኑ ተነስቶ የእሳት ነበልባል በሆነው ሠረገላ አማካኝነት መጋ ረጃው ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተቅዱሳኑ ገብቶ ሲቀመጥ ተመልክቼ ነበር፡፡ ከዚያም የሱስ ከዙፋኑ ላይ ሲነሳ አጎንብሰው የነበሩት አብዛኞቹ ከእርሱ ጋር ተነሱ፡፡ የሱስ ከተነሳ በኋላ አንዲት ነጠላ ጨረር እንኳ ከየሱስ ወደ ግዴለሾቹ ሐዝቦች ሲያልፍ አልተመለከትኩም ነበር፡፡ እነዚህ ሕዝቦች ፍጹም በሆነ ጽልመት ውስጥ ተትተው ነበር ነገር ግን የሱስ ከዙፋኑ ብድግ ብሎ ወደ ውጪ አነስተኛ ርቀት በመራቸው ጊዜ ዐይኖቻቸው በእርሱ ላይ እንደተተከሉ ነበሩ፡፡ ከዚያም ቀኝ እጁን ከፍ አድርጎ በማንሳት «ወደ አባቴ ገብቼ ግዛቴን እስክቀበል ልብሶቻችሁን ከጉድፍ አንደጠበቃችሁ ቆዩኝ፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ከሠርጉ ተመልሼ ወደ ራሴ እቀበላችኋለሁ» በማለት ሲናገር ተወዳጅ ድምጹን ሰማን፡፡ ከዚያም የሚንበለበል የእሳት መንኩራኩር የሚመስል፣ በመላእክት የተከበበና በደመና የተሸፈነ ሠረገላ የሱስ ወደነበ ረበት ስፍራ መጣ የሱስ ወደ ሠረገላው ውስጥ ገባና አብ ተቀምጦበት ወደ ነበረው ወደ ቅድስተቅዱሳኑ ስፍራ አመራ፡፡ በዚያ ስፍራ ታላቁ ሊቀ ካኅን የሱስ በአብ ፊት ቆሞ ተመለከትኩ፡፡ በመጎናጸፊያው ጥለት ላይ ደወልና የሮማን ፍሬ ነበር ከየሱስ ጋር ብድግ ብለው የተነሱት እምነታቸውን እርሱ ወደ ነበረበት እጅግ ቅዱስ ስፍራ ይልኩ ነበር «አባት ሆይ መንፈስህን ስጠን” በማለትም ይጸልዩ ነበር ከዚያም የሱስ በላያቸው ላይ መንፈስ ቅዱሳን ይተነፍስባቸው ነበር፡፡ በዚያ እስትንፋስ ውስጥ ብርሃን፣ ኃይል፣ ብርቱ ፍቅር፣ ደሰታና ሰላም ነበር EWAmh 37.2

    አሁንም በዙፋኑ ፊት አጎንብሰው ወደ ነበሩት ለመመልከት ዘወር አልኩ፡፡ እነዚህ ሰዎች የሱስ ቅድስተቅዱሳኑን ትቶ መውጣቱን አላወቁም ነበር፡፡ ሰይጣን በዙፋኑ ላይ ሆኖ የእግዚአብሔርን ሥራ የሚሠራ መስሎ ቀረበ፡፡ እነርሱም ቀና ብለው ወደ ዙፋኑ በመመልከት «አባት ሆይ መንፈስህን ስጠን” በማለት ይጸልዩ ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ ሰይጣን ቅዱስ ያልሆነ ተጽእኖ ያሳድርባቸው ዘንድ እፍ አለባቸው፡፡ በትንፋሹ ውስጥ ብርሃንና ከፍ ያለ ኃይል የነበረ ሲሆን ነገር ግን ጣፋጭ ፍቅር፣ ደስታና ሰላም አልነበረም፡፡ የሰይጣን ዓላማ እነርሱን እንደተታለሉ ለማስቀረትና የእግዚአብሔርን ልጆች ወደ ኋላ በመመለስ ለማሳት ነበር፡፡ EWAmh 38.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents