Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    45—የሳውል መለወጥ

    ሳውል የጌታን መንገድ የሚከተሉትን ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን አስሮ ወደ የሩሳሌም ለመውሰድ የሚያስችለውን ደብዳቤ ይዞ ጉዞውን ወደ ደማውቆ ባቀናበት ወቅት የክፉው መላእክት ዙሪያውን ከበውና ከፍ ከፍ ብለው ይታዩ ነበር ነገር ግን ብርሃን ከሰማይ ድንገት ዙሪያውን ሲያንጸባርቅበት የክፉ መላእክት ከስፍራው ሲበሩ በምድር ላይ ወደቀ፡፡ «በዚያን ጊዜም ሳውል፤ ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ? የሚል ድምጽ ሰማ፡፡ ሳውልም ጌታ ሆይ ንተማን ነህ?’ በማለት ጠየቀ: አኔማ አንተ የምታሳድደኝ የሱስ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተይብስብሃል’ አለው፡፡ ጳውሎስ እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ “ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? አለው:፡፡ አሁንም ተነስተህ ወደ ከተማይቱ ግባ ማድረግ የሚገባህም ይነገርሃል’ አለው፡፡” ከሳውል ጋር ይጓዙ የነበሩትም ሰዎች ድምጹን እየሰሙ ማንም ባላዩ ጊዜ አፋቸውን ይዘው ቆሙ፡፡ የሰማያዊው ብርሃን ክብር ዐይኖቹን በማሳወሩ አንጸባራቂው ብርሃን ካለፈ በኋላ ሳውል ከወደቀበት ተነስቶ ዐይኑን ሲገልጥ ፈጽሞ ማየት አልቻለም ነበር ስለዚህ ስዎቹ እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አስገቡት፡፡ ሳውል ለሦስት ቀናት እንደታወረ ቆየ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ እህል ውሃ አልቀመሰም ነበር፡፡ ከዚያም ሳውል ወደ ወህኒ ሊወስዳቸው ካሰባቸው ሰዎች ወደ አንዱ ጌታ መልአኩን ልኮ አንዲህ አለው «ቀጥተኛ ጎዳና በተባለው መንገድ ይሁዳ ወደ ተባለ ሰው ቤት ሂድ እዚያም ሳውል የሚባል አንድ የጠርሴስ ሰው እየጸለየ ነውና ፈልገው ምክንያቱም ሐናንያ የሚባል ሰው እርሱ ወዳለበት መጥቶ እጁን እንደሚጭንበትና ዐይኑ እንደሚበራለት በራእይ አይቶአል” EWAmh 141.2

    ሐንንያ በዚህ ጉዳይ ስህተት ሊኖር እንደሚችል ፍርሃት ስለገባው ስለ ሳውል ሰምቶት የነበረውን ለጌታ መንገር ጀመረ:: ነገር ግን ጌታ ሐናንያን እንዲህ አለው «ሂድ፤ ይህ ሰው በአሕዛብና በነገሥታት ፊት እንዲሁም በእስራኤል ሐዝብ ፊት ስሜን እንዲሸከም የተመረጠ ዕቃዬ ነው፧ እኔም ስለ ስሜ ምን ያህል መከራ መቀበል እንዳለበት አሳየዋለሁ፡፡» ሐናንያ ጌታ የነገ ረውን በመታዘዝ ወደ ተባለው ቤት ገብቶ እጁን ጫነበትና «ወንድሜ ሳውል ሆይ፤ ወደዚህ ስትመጣ የተገለጠልህ ጌታ የሱስ ዐይንህ እንዲበራና በመንፈስ ቅዱስም እንድትሞላ እኔን ልኮኛል» አለው፡፡EWAmh 142.1

    ሳውል ወዲያውኑ የዐይኑን ብርሃን በመቀበል ተነስቶ ተጠመቀ፡፡ ሳውል የሱስ በእርግጥም የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን በምኩራባቸው ገብቶ አስተማረ: የሰሙት ሁሉ በመገረም «ይህ ሰው በየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሲያጠፋ የነበረ አይደለምን? ደግሞም ወደዚሀ የመጣው እነርሱን አስሮ ወደ ካኅናት አለቆች ሊወስዳቸው አልነበረምን?» አሉ፡፡ ሳውል ግን እየበረታ ሄደ በደማስቆ ለሚኖሩትም አይሁድ የሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ማስረጃ እያቀረበ አፋቸውን ያስይዛቸው ነበር፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎች ሳውልን የሚያውቁት በየሱስ ስም የሚያምኑትን በቅንአት ሲያሳድድና እየያዘ እንዲገደሉ ሲሰጥ ቢሆንም ነገር ግን አሁን ከአንደበቱ ሲወጡ የሚሰሟቸው ተአምራዊ ንግግሮች በእርገጥም የሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንዲያምኑ አደረጋቸው፡፡ ጳውሎስ ተሞክሮውን ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ጋር ያቆራኘዋል፡፡ ጳውሎስ የጌታን መንገድ የሚከተሉትን ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን እስከ ሞት እያሳደደና እየያዘ ወህኒ ይከታቸው የነበ ረ ቢሆንም ነገር ግን ለተመሳሳይ ተልዕኮ ወደ ደማስቆ ባደረገው ጉዞ በድንገት ዙሪያው በብርሃን ተሞላ፤ የሱስ እራሱን ገለጸለት፣ የእግዚብሔር ልጅ መሆኑንም አስተማረው፡፡ EWAmh 142.2

    ሳል የሱስን በድፍረት በመስበኩ በብዙዎች ላይ ግዙፍ ተጽእኖ ማሳደር ቻለ፡፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀት የነበረው ጳውሎስ ጌታን አግኝቶ ከተለወጠ በኋላ በየሱስ ማንነት ዙሪያ በሚናገሩት ትንቢቶች ላይ መለኮታዊ ብርሃን ስለበራለት እውነትን በግልጽ እንዲናገርና ማንኛውንም ቃሉን የመጠምዘዝ አካሄድ እንዲያርም አስቻለው፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በማረፉ ግልጽና ብርቱ በሆነ አቀራረብ አድማጮቹን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት ወደነበሩት ጊዜያት በመውሰድ ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ እርሱ ሥቃይ፣ ሞትና ትንሳኤ የተናገሩት ፍጻሜ ማግኘቱን አሳያቸው፡፡ EWAmh 143.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents