Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    44—የእስጢፋኖስ ሞት

    በየሩሳሌም ደቀ መዛሙርቱ በከፍተኛ ፍጥነት እየበዙ ይሄዱ ነበር አብዛኞቹ ቀሳውስትም ለእምነቱ ታዛዥ ነበሩ፡፡ በእምነት የተሞላው እስጢፋኖስ በሕዝቡ መሃል ታላላቅ ድንቅ ነገሮችንና ታምራዊ ምልክቶችን ያደርግ ነበር፡፡ ቀሳውስቱ ከወግና ልማድ እንዲሁም ከመስዋዕት ስጦታዎች ፊታቸውን በማዞር የሱስን እንደ ታላቅ መስዋዕት አድርገው መቀበላቸውን የአይሁድ የኃይማኖት መሪዎች በመመልከታቸው በቁጣ ገነፈሉ፡፡ እስጢፋኖስ የማያምኑ ቀሳውስቶችንና ሽማግሌዎችን በመውቀስ ከላይ በተሰጠው ኃይል የሱስን በፊታቸው ከፍ ከፍ በማድረግ ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም ነበር፡፡ ስለዚህ እስጢፋኖስ በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲሰነዝር ሰምተናል የሚሉ ሰዎችን በስውር አዘጋጁ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሕዝቡን፣ የአገር ሽማግሌዎቹንና የሕግ መምህራኑን በማነሳሳት እሰጢፋኖስን አስይዘው በአይሁድ ሸንጎ ፊት አቀረቡት፡፡ ከዚያም የናዝሬቱ የሱስ ይህን ስፍራ እንደሚያጠፋውና ከሙሴ የተቀበልነውን ወግ እንደሚለውጥ ሲናገር ሰምተናል በማለት መሰከሩበት፡፡ EWAmh 139.2

    እስጢፋኖስ በዳኞቹ ፊት በተቀመጠ ጊዜ የእግዚአብሔር ክብር ብርሃን በገጽታው ላይ አርፎ ነበር፡፡ «በሸንጎው ተቀምጠው የነበሩትም ሁሉ እስጢፋኖስን ትኩር ብለው ሲመለከቱት ፊቱ የመልአክ ፊት መስሎ ታያቸው:፡፡” እስጢፋኖስ በተመሰረተበት ክስ ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጥ በተጠየቀ ጊዜ ከሙሴና ከነቢያት ጀምሮ የእስራኤላውያንን ልጀች ታሪክ በመዳሰስ እግዚአብሔር እንዴት እንደተገናኛቸውና ስለ ክርስቶስ እንዴት በትንቢት እንደተነገረ አሳያቸው፡፡ የቤተመቅደሱን ታሪክ በመጥቀስ እግዚአብሔር በእጅ በተሠራ መቅደስ ውስጥ እንደማይኖር ይፋ አደረገላቸው:: አይሁዳውያኑ ያንን ቤተመቅደስ ከማምለካቸው የተነሳ ማንም በቤተመቅደሱ ላይ ከሚናገር ይልቅ በእግዚአብሔር ላይ ቢናገር ይመርጡ ስለ ነበር በሽንጎው ስብሰባ ላይ የነበሩ ሁሉ እጅግ ተቆጡ፡፡ እስጢፋኖስ ስለ ክርስቶስ ሲናገር በሚናገር ጊዜ ቤተመቅደሱን በመጥቀሱ ስዉ ንግግሩን እንደተቃወመ ቢመለከትም እርሱ ግን «እናንት ልባችሁና ጆሮአችሁ ያልተገረዘ አንገተ ደንዳኖች! ልክ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ሁል ጊዜ ትቃወማላችሁ” በማለት ያለ ፍርሃት ገሰጻቸው፡፡ ሕዝቡ የሚመለከተው የኃይማኖታቸውን ውጪኛውን አምልኮ ብቻ በመሆኑ ልባቸው ሻግቶና በሚገድል ክፋት ተሞልቶ ነበር፡፡ እስጢፋኖስ አባቶቻቸው ነቢያትን በማሳደድ የሠሩትን ጭካኔ የተሞላውን ተግባር በመንገር እነዚህ እርሱ የጠቀሳቸው ክርስቶስን በመቃወምና በመስቀል ታላቅ ኃጢአት መሥራታቸውን ይፋ አደረገላቸው «ከነቢያት መሃል አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን አለ? የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን እንኳ ገድለዋልî እናንተም አሁን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ገደላችሁትም::” EWAmh 140.1

    እነዚህ ግልጽና ስለት ያላቸው እውነቶች በተነገሩ ጊዜ ቀሳውስቱና ገዢዎቹ በእጅጉ ተቆጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት ‹‹እስጢፋኖስ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኩር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር፧እንዲሁም የሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፤ እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጀም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አð ሰዉ ግን አሰማውም ነበር ብታላቅ ድምጽ እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፍነው እርሱ ወዳለበት በአንድነት እሮጡ፤ ይዘውም ከከተማው ወጪ ጣሉት፤ በድንጋይም ይወግሩት ጀመር: እስጢፋኖስ እየተወገረ እያለ ተንበርኮ በታላቅ ድምጽ ታ ሆይ! ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው› በማለት ጮኸ:: EWAmh 140.2

    እስጢፋኖስ በቤተክርስቲያን የነበረን አስፈላጊ ክፍት ቦታ እንዲሽፍን በተለይ የተነሳ ኃያል የእግዚአብሔር ሰው መሆኑን ተመልክቻለሁ፡፡ የእስጢፋኖስ ሞት በደቀ መዛሙርቱ መሃል ታላቅ እጦት መሆኑን ለተረዳው ሰይጣን ይህ ክስተት ድል ነበር ሆኖም ሰይጣን ያገኘው ድል ጊዜያዊ ነበር: ምክንያቱም እስጢፋኖስ ሲወገር ምስክር ከሆኑት ለአንዱ የሱስ እራሱን የሚገልጥለት ሰው በዚያ ነበር ምንም አንኳ ሳውል በእስጢፋኖስ ላይ ድንጋይ የመወርወር ድርሻ ባይኖረውም ነገር ግን እንዲገደል ፈቃደኛ ነበር ሳውል የየሱስን ተከታዮች በማደንና በየቤታቸው እየተዘዋወረ ይዞ ለገዳዮቻቸው በመስጠት ለእግዚአብሔር በቅንአት እየሠራ እንደሆነ ያምን ነበር፡፡ ሳውል የተማረና ችሎታ የነበረው ሰው ስለነበር ቅንአቱና ዕውቀቱ በአይሁድ ዘንድ ከፍተኛ ክብር እንዲቸረው አድርጎ ነበር ሆኖም ሳውል በብዙ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ዘንድ የሚፈራ ሰው ነበር፡፡ ሰይጣን በእግዚአብሔር ልጅና በተከታዮቹ ላይ የአመጻ ሥራ ለመሥራት ሳውል የነበረውን ችሎታ በሚገባ ተጠቅሞበት ነበር፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር የዚህን ታላቅ ጠላት ኃይል በመሰባበር በግዞቱ ስር የነበሩትን ነጻ ማውጣት ይችላል፡፡ ሳውል የየሱስን ስም እንዲሰብክ፣ ደቀ መዛርትን በሥራቸው እንዲያበረታና በተለይ ደግሞ የአስጢፋኖስን ቦታ እንዲሸፍን በክርስቶስ «የተመረጠ ዕቃ» ነበር፡፡EWAmh 141.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents