Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    51—ተሐድሶ

    ሁሉም ዓይነት ስደቶች በቅዱሳን ላይ ይደርሱ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ለእግዚአብሔር እውነት ሕያው ምስክር የሆኑ ጎልተው ይታዩ ነበር የጌታ መላእክት በታማኝነታቸው እንዲጸኑ የሚያደርጓቸውን ሥራዎች ይሠሩ ነበር: መላእክቱ በጨለማ ውስጥ ሆኖው ነገር ግን ታማኝ ልብ የነበሯቸውን ሰዎች ይፈልጉ ነበር፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ ሰዎች በስህተት ውስጥ ቢቀበሩም ነገር ግን ለእግዚአብሔር የተመረጡ ዕቃዎቹ በመሆን አምላካዊውን እውነት ተሸክመው ድምጾቻቸውን ከፍ አድርገው የሕዝቡን ኃጢአት ይናገሩ ዘንድ ልክ እንደ ሳውል ጠራቸው፡፡ የእግዚአብሔር መላእክት ማርቲን ሉተርን፣ ሜላንክቶንንና ሌሎችንም በተለያዩ ስፍራዎች የነበሩ ልቦችን በመንካት ህያው ለሆነው አምላካዊ ቃል ምስክርነታቸውን ለመስጠት እንዲጠሙ አደረገ፡፡ ጠላት እንደ ጎርፍ በመምጣቱ አምላካዊው ቃል ከእርሱ በተጻራሪ ሊቆም የግድ ነበር፡፡ ሉተር ማዕበሉን ተጋፍጦ ወደፊት በመገስገስ በወደቀችው ቤተክርስቲያን ቁጣ ፊት በመቆም ጥቂቶች ለተቀደሰው አገልግሎታቸው ታማኝ ይሆኑ ዘንድ እንዲያበረታታቸው የተመ ረጠ ሰው ነበር፡፡ ሉተር እግዚአብሔርን እንዳያሳዝን ዘወትር ይፈራ ነበር፡፡ እርሱ በሥራው ጽድቅ ለማግኘት ቢሞክርም ነገር ግን ሰማያዊ ጨረር በአእምሮው የነበረውን ጽልመት አስወግዶ ደኅንነት የሚገኘው በሥራ ሳይሆን ነገር ግን በከበረው የክርስቶስ ደም መሆኑን እንዲያምን እስከሆነበት ጊዜ ድረስ እርካታ አላገኘም ነበር፡፡ ይህ ሲሆን በግሉ ወደ እግዚአብሔር የሚመጣው በጳጳሳቱ ወይም በንስሐ አባቱ አማካኝነት ሳይሆን ነገር ግን በየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ EWAmh 159.2

    በጨለማ ተውጦ በነበረ ማስተዋሉ ላይ የንጋት ብርሃን በመፈንጠቅ አጉል የነበረውን እምነት ያስወገደለት ይህ አዲስና አስደናቂ ብርሃን ለሉተር ምን ያህል የከበረ ነበር! ሉተር ያገኘውን ብርሃን ከማንኛውም ምድራዊ ሐብት የላቀ ዋጋ ሰጠው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል አዲስ ነበር ሁሉም ነገር ተለውጦ ነበር በውስጡ የነበረውን ውበት መመልከት ባለመቻሉ ሲፈራው የነበረው መጽሐፍ አሁን ግን ህይወት---ዘላለማዊ ህይወት ሆነው፡፡ መጽሐፉ ደስታው፣ አጽናኙና የተባረከ መምህሩ ሆነ፡፡ ከዚህ በኋላ መጽሐፉን ከማጥናት እንዲታቀብ ሊከለክለው የሚችል አንዳች ነገር አይኖርም:፡፡ ሉተር ሞትን ይፈራ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን አምላካዊውን ቃል ሲያነብ የነበረው ፍርሃት ሁሉ ተወገደ:፡፡ በዚህም የእግዚአብሔርን ባህሪ በማድነቅ ወደደው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ለራሱ በመመርመር አምላካዊው ቃል ይዞት ባገኘው የከበረ ሐብት ለግሉ ሐሴት ካደረገ በኋላ በመቀጠል ይህ እውነት ለቤተክርስቲያን ባለው አንደምታ ዙሪያ ጥልቅ ምልከታ አደረገ፡፡ ለደኅንነት ተማምኖባቸው በነበሩ ስዎች አጸያፊ ኃጢአት ተስፋ ቆርጦ የነበ ረው ሉተር በእርሱ ላይ አጥልቶ የነበረው ተመሳሳይ ጽልመት አያሌ ዎችንም ሸፍኖ ሲመለከት የዓለምን ኃጢአት በብቸኝነት ማስወገድ ወደሚችለው የእግዚአብሔር በግ እነዚህን ሰዎች ለማመላከት የሚያገኝበትን ዕድል አጥብቆ ተመኘ፡፡ EWAmh 160.1

    ሉተር በጳጳሳዊው ቤተክርስቲያንስህተትና ኃጢአት ላይ ድምጹን ከፍ አድርጎ በመጮኽ ደኅንነት በሥራ እንደሚገኝ አድርጎ በሺህዎች የሚቆጠሩን ጠፍንጎ የነበረውን የጨለማውን ስንሰለት ለመበጣጠት ያላሰለሰ ጥረት ኦደ ረገ፡፡ ሉተር በየሱስ ክርስቶስ የተገኘውን አስገራሚ ደኅንነትና እውነተኛውን ጥልቅ አምላካዊ ጸጋ ሕዝቡ አእምሮውን ከፍቶ ይመለከት ዘንድ ናፈቀ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመርቶ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ኃጢአት በይፋ በመናገሩ ከቀሳውስቱ ዘንድ የተቃውሞ ማዕበል ቢደርስበትም ነገር ግ ተስፋው የለመለመ ነበር፡፡ ምክንያቱም ሉተር በጠንካራው ክንድ ላይ በጽናት በመደፉ ድል ይቀዳጅ ዘንድ በእርሱ ላይ ተማምኖ ነበር ውጊያውን እያፋፋመ በሄደ ቁጥር ተሐድሶ ለማድረግ ምኞታቸው ያልነበ ረው ቀሳውስት ቁጣና ንዴት በእርሱ ላይ እየበረታ መሄድ ጀመረ፡፡ እነዚህ መሪዎች ቤተክርስቲያን በጨለማ እንደተዋጠች እንድትቀር በመመኘት ተልካሻ ደስታቸውንና የነበሩበትን የክፋት ጎዳና እንደያዙ መቅረት መርጠው ነበር፡፡ EWAmh 160.2

    ሉተር ኃጢአትን በመገሰጽና ለእውነት ጠበቃ በመሆን ጽኑ አቋም ያለው፣ ፍርሐት የማያውቀውና ደፋር ሰው እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ አብሮት ያለው ከሁሉ ኃያልና ገናና መሆኑን በመገንዘቡ ለክፉ ሰዎች ወይም ለዲያብሎስ አይጨነቅም ነበር: እውትን የመግለጽ የጋለ ምኞት፣ ብርታትና ደፋርነት ባለጸጋ የነበረው ሉተር በጸንፈኛ አክራሪዎች አደጋ ላይ ሊወድቅ የሚችልበት ሁናቴ ውስጥ ይገኝ ነበር፡፡: ሆኖም ከቀሳውስቱ አመለካከት በተቃራኒ የተሐድሶውን እንቅስቃሴ አንግቦ ወደፊት በመጓዝ ሉተርን የሚ ረዳውን ሜላንክቶንን እግዚአብሔር አስነሳ EWAmh 161.1

    ሜላንክቶን ፈሪና ድንጉጥ፣ ጠንቃቃ እንዲሁም ከፍ ያለ ትዕግሥት የነበ ረው ሰው ነበር፡፡ ሜላንክቶን በእግዚአብሔር ዘንድ በእጅጉ የተወደደ ሰው ነበር፡፡ እርሱ ያካበተው የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት፣ የሚሰጠው ፍርድና የነበረው ጥበብ አስደናቂ ነበር በመሆኑም ለአምላካዊው መርኅ የነበረው ቅንአት ከሉተር ጋር የሚስተካከል ነበር፡፡ ጌታ የእነዚህን ሰዎች ልብ በአንድ በማስተሳሰሩ የማይለያዩ ባልንጀራዎች ነበሩ ሜላንክቶን ፍርሃት አድሮበትና ዝግ ብሎ በነበረበት ሰዓት ሉተር ታላቅ ረዳት ሆኖት ነበር፡፡ በተመሳሳይ ሉተር ከመጠን በላይ በፍጥነት የመገስገስ አደጋ ላይ በነበረ ጊዜ ሜላንክቶን በተራው ረዳት ሆኖታል፡፡ ሜላንክቶን ይከተል የነበረው የሰከነና ጥንቃቄ የተሞላው አካሄድ ነገሮች ሊያስከትሉ የሚችሉትን ውጤት አስቀድሞ እንዲመለከት አስችሎት ነበር በመሆኑም ሥራው ለሉተር ብቻ ባለመተዉ የቆሙለት መርኅ ሊደርስበት ይችል የነበረውን አደጋ ለማስወገድ አስችሎአቸው ነበር፡፡ እንዲሁም ሥራው ለሜላንክቶን ብቻ ቢተው ኖሮ ወደፊት መገስገስ ባልቻለ ነበር እነዚህ ሁለት ሰዎች የተሐድሶውን ሥራ ወደፊት እንዲያራምዱ የተመረጡበትን አምላካዊ ጥበብ ተመልክቼ ነበር፡፡ EWAmh 161.2

    በመቀጠል ቀደም ወዳለው የሐዋርያቱ ዘመን ተሰድጄ እግዚአብሔር ለሥራው ባልንጀራሞች አድርጎ የመረጣቸውን ጴጥሮስንና ዮሐንስን ተመለከትኩ፡፡ ጴጥሮስ ጽኑና የጋለ ምኞት የነበረው ሰው ሲሆን ዮሐንስ ደግሞ የተረጋጋና ትዕግሥተኛ ነበር አንዳንድ ጊዜ ጴጥሮስ ግብታዊነት ይስተዋልበታል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሁናቴ ሲከሰት ተወዳጁ ደቀ መዝሙር በእርጋታና በሰከነ መንፈስ ይከታተለው ነበር፡፡ ሆኖም ይህ አካሄድ በጴጥሮስ ላይ ተሐድሶ አላመጣም፡፡ ነገር ግን እርሱ ጌታውን ከካደ፣ ንስሐ ከገባና ከተለወጠ በኋላ ግብታዊነቱን ከተረጋጋው የዮሐንስ ባህሪ ጋር በአንክሮ ማየት ነበረበት፡፡ ሥራው ለዮሐንስ ብቻ ቢተው ኖሮ የክርስቶስ መርኅዎች ተደጋጋሚ ችግር በገጠማቸው ነበር፡፡ በመሆኑም የጴጥሮስ የጋለ ፍላጎት አስፈልጎ ነበር የእርሱ ደፋርነትና ብርቱ ኃይል የጠላቶቻቸውን አፍ በማዘጋት ብዙውን ጊዜ ይገጥሟቸው ከነበሩ አስቸጋሪ ሁናቴዎች እንዲወጡ አስችሏቸዋል፡፡ ዮሐንስ አሸናፊ እየሆነ ነበር፡፡ እርሱ የነበረው ትዕግሥት፣ ጽናትና ታማኝነት ለክርስቶስ መርኅ መጠነ ሰፊ ድል አቀዳጅቶአል፡፡ EWAmh 161.3

    ከጳጳሳዊው ሥርዓት ኃጢአት በተቃራኒ ተሐድሶ በማድረግ ወደፊት የሚራመዱ ሰዎችን እግዚአብሔር hስነሳ፡፡ ምንም እንኳ ሰይጣን እነዚህን ሕያው ምስክሮች ለማጥፋት ተመኝቶ የነበረ ቢሆንም ጌታ ግን ከለላ ሆናቸው፡፡ አንዳንዶች ለስሙ ክብር ሲባል ምስክርነታቸውን በደማቸው እንዲያትሙ ቢፈቀድም ነገር ግን እንደነ ሉተርና ሜላንኮን ያሉት ብርቱ ሰዎች በህይወት ኖረው የቀሳውስቱን® የጳጳሳቱንና የነገሥታቱን ኃጢአት በማጋለጥ የበለጠውን ክብር ለእግዚአብሔር ማምጣት ነበረባቸው:: ቀሳውስቱ፣ ጳጳሳቱና ነገሥታቱ የሉተርንና አጋሮቹን ድምጽ ሲሰሙ ይሽበሩ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በእነዚህ የተመረጡ ሰዎች አማካኝነት በፈነጠቀው የብርሃን ጨረር ጨለማውን መበተን በመጀመሩ ብዙዎች ይህን ብርሃን በደስታ ተቀብለው ተመላለሱበት፡፡ አንድ ምስክር መስዋዕት ሲሆን በእርሱ እግር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ መርኍን አንግበው ይነሱ ነበር:: EWAmh 162.1

    ነገር ግን በሰማዕታቱ አካል ላይ ብቻ ሥልጣን የነበረው ሰይጣን የአማኞችን እምነትና ተስፋ ማስቀረት ባለመቻሉ ሁናቴው አላረካውም ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በሞታቸው እንኳ በጻድቃን ትንሳኤ የብሩህ ህያውነት ተስፋ ባለ ድል ነበሩ፡፡ እነርሱ ሟች ከሆነው ፍጡር የላቀ ብርቱነት ነበራቸው፡፡ የገጠማቸው ባላንጣ በቀላሉ በመንፈሳዊ ጠላትነት ብቻ የሚታይ ሳይሆን ነገር ግን ከዚያ በላቀ---እምነታችሁን ከመካድና ከመሞት አንዱን ምረጡ እያለ በሰዎች ውስጥ ሆኖ ያለማቋረጥ ከሚደነፋው ሰይጣን ጋር በነበራቸው ግብ ግብ የክርስቲያንን የጦር ዕቃ ለብሰው እራሳቸውን ከማዘጋጀት ውጪ ለአፍታ እንኳ አላንቀላፉም ነበር፡፡ የክርስቶስን ስም ይዘናል ከሚለው ነገር ግን ለእርሱ መርኅ ወኔ ቢስ hሆነው የዓለም አጋማሽ ሕዝብ ይልቅ እነዚህ ጥቂት ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር ላይ ጠንካራ እምነት ነበራቸው ï በፊቱም ይበልጥ የከበሩ ሆነው ይታዩ ነበር፡፡ ቤተክርስቲያን ስደት በደረሰባት ጊዜ አባላቶቿ ኅብረት ነበራቸው፣ ተወዳጆችም ነበሩ፡፡ በእ7ዚአብሔር ላይ የነበራቸውም እምነት ብርቱ ነበር፡፡ ኃጢአተኞች ቤተክርስቲያንን ይቀላቀሉ ዘንድ አልተፈቀደላቸውም ነበር፡፡ ነገር ግን ሁሉንም ነገር ለክርስቶስ ለማስገዛት ፈቃደኞች የሆኑ ሁሉ የእርሱ ደቀ መዛመ ርት መሆን ይችሉ ነበር፡፡ እነዚህ ወገኖቸ ምስኪን፣ ትሁትና ክርስቶስን ለመምሰል የመረጡ ነበሩ:: EWAmh 162.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents