Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    25—ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት መዘጋጀት

    (የካቲት 17/ 1853 ዓ.ም.)

    የተወደዳችሁ ወንድምና እህቶች ክርስቶስ በቅርቡ ዳግም እንደሚገለጥና አሁን እየሰበክን ያለነው ለኃጢአተኛው ዓለም መሰጠት ያለበትን የመጨረሻውን የምህረት መልእክት መሆኑን በሙሉ ልባችን እናምናለን? ምሳሌ ያችን በእርግጥም---ምሳሌ መሆን ያለበት ነው? ይህን ክፉ አል በመቀየር የእርሱን ባለ ግርማ አካል የሚያለብሰንን ጌታችንና አዳኛችን የሆነውን የሱስ ክርስቶስን እየተጠባበቅን መሆናችንን--በህይወታችንም ሆነ በተቀደሰው አነጋገራችን በዙሪያችን ላሉት ሁሉ እናሳያለን? እነዚህን ነገሮች አምነናቸዋል፧በሚገባ ተገንዝበናቸዋል ብዬ ለመናገር እፈራለሁ፡፡ አሉን የምንላቸውን በእጅጉ አስፈላጊ እውነቶች የተቀበሉ እምነታቸውን ሊያሳዩ ይገባል፡፡ ብዙዎች ለዚህ ዓለም ትኩረት በመስጠት አያሌ መደሰቻ ስፍራ ዎችን አብዝተው ሲፈልጉ ይስተዋላሉ፡፡ አእምሮ ስለአለባበስ ብቻ አብልጦ እንዲያስብ ተትቶአል፤ አንደበታችን ስለ ሙያችን ሐሰት በመናገር ዋጋ ቢስና የማይረባ በሆነ አነስተኛ ነገር ተጠምዶአል፡፡ EWAmh 82.1

    መላእክት ያዩናልï ይጠብቁናል፡፡ ብዙውን ጊዜ ከንቱ በሆነ ቃል! በማሾፍ፣ በማፌዝ እንዲሁም በግዴለሽነት በምናደርጋቸው ድርጊቶች እነዚህን መላእክት አብልጠን እናሳዝናቸዋለን፡፡ ምንም እንኳ ድል ለማግኘት አሁንም ሆነ ወደፊት ጥረት የምናደረግና የምናገኘው ቢሆንም ነገር ግን ያገኘ ነውን ድል ጠብቀን ካልተጓዝን ወደ ተመሳሳይ ግዴለሽነት አዘቅት ውስጥ በመግባት ፈተናን ማለፍና ጠላትን መቋቋም የማንችል እንሆናለን፡፡ ከወርቅ የከበረውን የእምነታችንን መፈተኛ ወቅት ማለፍ አንችልም፣ ስለ ክርስቶስ መከራ አንቀበልም በመከራው ወቅት አንከብርም፡፡ EWAmh 82.2

    እግዚአብሔርን በመርኅ ደረጃ በማገልገሉ ረገድ በክርስቲያኖች ዘንድ ታላቅ የብርታትና ጥንካሬ እጦት ይስተዋላል፡፡ ለእግዚአብሔር ክብር ልንሰጥ ይገባል ንጂ እራሳችንን ለማስደሰትና ለማርካት መመኘት የለብንም:: በድርጊታችንም ሆነ በንግግራችን ዐይኖቻችን ከክብሩ ላይ ሊነጠሉ አይገባም:: ልቦቻችን በአስፈላጊ ቃላት እንዲማረኩ የምንፈቅድ ከሆነ በቀላሉ በፈተና አንወድቅም፡፡ ከአንደበታችን የሚወጡት ቃላትም ጥቂትና የተመረጡ ይሆናሉ፡፡ «ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን»፣ «ሰዎች ስለተናገሩት ከንቱ ቃል ሁሉ በፍርድ ቀን ይጠየቁበታል»፣ «እግዚአብሔር ያየኛል» EWAmh 83.1

    እኛ ምስኪን ኃጢአተኞች በከበረው በየሱስ ደም ይቅርታ እናገኝና ለእግዚአብሔር እንዋጅ ዘንድ እራሳችንን የመቆጣጠር ስሜትና ለእኛ ሲል የተሰቃየውን ሥቃይ ለመቀበል የሚያስችል ጥልቅ ምኞት ሳይኖረን እነዚህን ስለ የሱስ ሥቃይ የሚያወሱ አስፈላጊ ቃላት ልናስብም ሆነ ወደ አእምሮአችን ልናመጣቸው አንችልም:፡፡ በነዚህ ነገሮች የምንኖር ከሆነ የተወደደው አኔነት ከእነ ክብሩ ትሁት በመሆን፤ ስፍራው ከሌሎች የሚሰነዘሩ ትችቶችን መቋቋም በሚችልና በቁጣ በማይገነፍል ውስብስብ ባልሆነ የህጻናት ማንነት ይተካል፡፡ ይህ ሲሆን እኔነትን ያማከለ መንፈስ ነፍስን ሊገዛ አይመጣም፡፡ EWAmh 83.2

    እውነተኛው የክርስቲያኖች ደስታና ምቾት እውን የሚሆነውና ሊሆንም የሚገባው በሰማይ ነው፡፡ ወደፊት የሚመጣውን ዓለም ኃይል ቀምሰው በሰማያዊ ደስታ ሐሴት ያደረጉና ያን የሚናፍቁ በምድራዊው ነገር እርካታ ሊያገኙ አይችሉም፡፡ እነዚህ ሰዎች በትርፍ ጊዜያቸው የሚሠሯቸው ብዙ ነገሮች ይኖራቸዋል፡፡ ነፍሶቻቸው እግዚአብሔርን ይናፍቃሉ፡፡ መዝገብ ባለበት ልብም በዚያው ስለሚሆን ከሚወዱትና ከሚያመልኩት እግዚአብሔር ጋር ጣፋጭ የአንድነት ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡ ለእነርሱ ደስታ የሚሰጣቸው ሰማያዊ መዝገባቸው ያለበት---ዘላለማዊ ቤታቸው የሆነችውን አዲስ የተፈጠ ረችውን ምድርና ቅድስቲቷን ከተማ ማሰላስል ነው፡፡ እነርሱ በዚህ ከፍ ባሉ ንጹህና ቅዱስ በሆኑ ነገሮች ውስጥ ሲኖሩ ሰማይ ቅርባቸው፣ የመንፈስ ቅዱስም ኃይል የሚሰማቸው ይሆናሉ፡፡ በዚህም ምቾታቸውና ዋንኛ ደስታቸው በዚህ በዓለም ሳይሆን ነገር ግን ጣፋጭ በሆነው ሰማያዊ መኖሪያቸው ይሆናል፡፡ ወደ አግዚአብሔርና ሰማያዊው ነገር የሚስባቸው ኃይል ከፍተኛ ስለሚሆን የነፍሳቸውን ደኀንነት አስተማማኝ ከማድረግና ለእግዚአብሔር ተገቢውን ክብር ከመስጠት ውጪ ኣእምሮhቸውን ወደሌላ የሚስብ ነገር አይኖርም፡፡ EWAmh 83.3

    እኛን በትክክለኛው ጎዳና ጠብቆ በመምራቱ ረገድ ምን ያህል ታላቅ ነገር እንደተደረገልን ሳስብ ሳለ እንዴት ያለ አስደናቂ ፍቅር ነው--- እግዚአብሔር ልጅ ለእኛ ለኃጢአተኞች ምንኛ ታላቅ ነገር አደረገልን! በማለት እጮኻለሁ፡፡ ለእኛ ደኅንነት መደረግ ያለበት ማንኛውም አስፈላጊ ነገር ተደርጎልን ሳለ ነገር ግን እኛ ግዴለሽና የማናስተውል ልንሆን ይገባል? መላው ሰማይ በእኛ ላይ ብርቱ ፍላጎት ያለው እንደመሆኑ ካንቀላፋንበት ህያው ሆነን በመንቃት ክብር ልንሰጠው ከፍ ከፍ ልናደርገውና ይህን ታላቅ አምላክ ልናመልከው ይገባል፡፡ እኛን በሙሉ ፍቅሩ ለወደደንና ርኅራኄውን ላሳየን አምላክ ልባችን በፍቅርና በምስጋና ሊፈስ ይገባል፡፡ እርሱን በህይወታችን በማክበር እኛ የተወለድነው ከላይ መሆኑን ንጹህና ቅዱስ በሆነ አነጋገ ማሳየት ይኖርብናል፡፡ እኛ ወደ ተሻለው አገር የምናመራ በጉዞ ላይ ያለን እንግዶችና መጻተኞች እንጂ ይህ ምድር መኖሪያችን አይደለም፡፡ EWAmh 84.1

    ብዙዎች የክርስቶስን ስም ይዘናል የሚሉና በቅርቡ እውን የሚሆነውን ዳግም ምጽአቱን የሚጠባበቁ ለክርስቶስ መሠቃየት ማለት ምን እንደሆነ አያውቁም:፡፡ በልዩ ልዩ መንገዶች እንደሚታየው ልቦቻቸው በአምላካዊው ጸጋ አልተሸነፉም---እኔነት ህያው ሆኖ ከመስተዋል ውጪ hልሞተም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እነዚህ ሰዎች ስለ ፈተና ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ነገር ግን ለፈተናዎቻቸው ቀዳሚው መንስዔ ያልተሸነፈው ልብ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ትሁት የክርስቶስ ተከታይና እውነተኛ ክርስቲያን ማለት ምን እንደሆነ መገንዘብ ቢችሉ ኖሮ በትክክል ከልባቸው መሥራት ይጀምሩ ነበር፡፡ በቅድሚያ እኔነት እንዲሞት ያደርጉና በጸሎት በመትጋት እያንዳንዱን የልብ ፍትወት በጥንቃቄ ይመረምራሉ፡፡ ወንድም ሆይ በራስ መተማመንህንና መመካትህን ትተህ ተሁት የሆነውን ምሳሌ ተከተል፡፡ የሱስ ምሳሌህ መሆኑን ሁል ጊዜም በማሰብ ዱካውን ተከተል፡፡ ሐፍረትና ውርደትን በመቀበል መስቀሉን በደስታ ወደ ተሸከመውና በአስቸጋሪ ሁናቴ ውስጥ ወዳለፈው የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ ወደሆነው ወደ የሱስ ተመልከት: በኃጢአተኞች የደረሰበትን ተቃርኖ በማለፍ ይህ ትሁት ጠቦት ለበደላችን ሲል---ጉዳት ደረሰበት፣ ችግርን ቀመሰ፣ ቆሰለ፣ ታረደ፡፡ EWAmh 84.2

    የክብሩ ተካፈዮች ሆነን የድል አክሊል በመቀበል---በክብር የተሞላ፣ ህያውና ዘሳለማዊ ህይወት ይኖረን ዘንድ በዚህ ምድር እለት እለት እራሳችንን በመስቀል በደስታ የክርስቶስ ሥቃይ ተካፋዮች እንሁን፡፡ EWAmh 84.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents