Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    43—የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት

    ደቀ መዛሙርቱ የተሰቀለውንና ከሙታን የተነሳውን አዳኝ በታላቅ ኃይል ሰበኩ፡፡ ተአምራትና ድንቃድንቅ ነገሮችን በየሱስ ስም ያደርጉ ነበር፡፡ በሽተኛ ተፈውሶአል እንዲሁም ከመወዱ አንስቶ ሽባ የነበረ ሰው ወደ ፍጹም አቋም በመመለስ በብዙ ሕዝብ ፊት እየተራመደና እየዘለለ እግዚአብሔርን በማመስገን ከጴጥሮስና ዮሐንስ ጋር ወደ ቤተመቅደሱ አደባባይ ገብቶአል፡፡ ወሬው በመሰራጨቱ ሕዝቡ ደቀ መዛሙርቱን ማጨናነቀ ጀመረ:: ብዙ ዎችም በተመለከቱት ፈውስ አብልጠው ተደነቁ፡፡: EWAmh 135.2

    የሱስ በሞተጊዜ ከዚህ በኋላ የነበረው መደመም ረግቦ ሕዝቡ ዳግመኛ ወደ ሰብዓዊው ልማድና ወግ ፊቱን ከመመለስ ውጪ በደቀ መዛሙርቱ መካከል ተአምራት ይኖራል ብለው ቀሳውስቱ አላሰቡም ነበር፡፡ ነገር ግን በደቀ መዛሙርቱ መካከል ተአምራት በመደረጉ ሕዝቡ በአግራሞት ተሞላ፡፡ ቀሳውስቱ---የሱስ ተሰቅሎአል---ታዲያ እነዚህ ተከታዮቹ ይህን ኃይል ከወዴት አገኙት? በማለት ይደነቁ ጀመር የሱስ አብሮአቸው በነበረ ጊዜ የሚያደርጓቸው ተአምራቶች ምንጭ ከእርሱ የሚቀበሉት ኃይል እንደሆነ ያስቡ ነበር፡፡ ነገር ግን እርሱ በሞተጊዜ ከዚህ በኋላ ተአምራቶቹ ይቆማሉ ብለው ነበር የጠበቁት ይህን ግራ መጋባታቸውን ያስተዋለው ጴጥሮስ እንዲህ አላቸው «የእስራኤል ሕዝብ ሆይ በዚህ ለምን ትደነቃላችሁ? ደግሞም በእኛ ኃይል ወይም በእኛ ጽድቅ ይህ ሰው ድኖ እንዲመላለስ እንዳደረግነው በመቁጠር ለምን ወደ እኛ አተከ ራችሁ ትመለከታላችሁ? የአባቶቻችን አምላክ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ብላቴናውን የሱስን ከአበረው፧ እናንተግን እንዲሞት አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፧ ጲላጦስ ሊፈታው ቢፈልግም እናንተበእርሱ ፊት ከዳችሁ፤ ቅዱሱንና ጻድቁን ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ፤ የሕይወት መገኛ የሆነውን ገደላችሁት፧ እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሳው፤ እኛም ለዚህ ምስክሮች ነን፡፡ ይህ የምታዩትና የምታውቁት ሰው የበረታው በየሱስ በማመን ነው፤ ሁላችሁም እንደምታዩት ፍጹም ፈውስ እንዲያኝ ያደረገው የየሱስ ስምና በእርሱ አማካይነት የሚገኘው እምነት ነው፡፡» EWAmh 135.3

    የቀሳወስት ለቆችና ሽማግሌዎች እነዚህን ቃላት መቋቋም ባለመቻ ላቸው ጴጥሮስና ዮሐንስ በእነርሱ ትእዛዝ ተይዘው እስር ቤት ተhተቱ፡፡ ነገር ግን በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ ከደቀ መዛሙርቱ በሰሙት አንድ ብቻ መልእክት ተለውጠው፤ በክርስቶስ ትንሳኤና እርገት አምነው ነበር:፡፡ ሁናቴው ቀሳውስቱንና ሽማግሌዎችን አወካቸው፡፡ የሕዝቡ አስተሳሰብ ወደ እነርሱ እንዲዞር በመሻት እነዚህ የኃይማኖት መሪዎች የሱስን ቢገድሉትም ነገር ግን ጉዳዩ ከቀድሞው ይልቅ የከፋ ሆኖአል፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ ለመግደላቸው አሁን በግልጽ በደ መዛሙርቱ እየተከሰሱ ባሉበት በዚህ ሁናቴ እነዚህ ነገሮች እስከየት እንደሚሄዱም ሆነ በሕዝቡ ፊት እንዴት እንደሚታዩ መገመት አልቻሉም:፡፡ ምንም እንኳ ጴጥሮስንና ዮሐንስን እንዲታሰሩ በማድረጋቸው ቢደሰቱም ነገር ግን ሕዝቡን በመፍራታቸው ሊገድሏቸው አልደፈሩም ነበር፡፡ EWAmh 136.1

    በቀጣዩ ቀን ሐዋርያቱ በሸንጎው ፊት እንዲቀርቡ ተደረገ፡፡ የየሱስን ደም በመሻት አብልጠው የጮኹ በስፍራው ነበሩ፡፡ ጴጥሮስ ከክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሃል አንዱ ነህ ተብሎ ክስ ሲቀርብበት እየማለና እየተገዘተጌታውን ሲክድ የሰሙ እርሱን ለማዋከብ ተስፋ አደርገዋል፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስ ተቀይሮ ስለነበር የቀድሞውን ጥድፊያና ፍራቻ የተሞላውን እንከን በማስወገድ ለጌታው ነፍጎት የነበረውን ክብር የሚመልስበትን ዕድል እንዳገኘ ተመለከተ፡፡ በመሆኑም ጴጥሮስ ቅድስና በተሞላው ድፍረትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ያለ ፍርሃት እንዲህ ሲል በይፋ ነገራቸው «እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔር ግን ከሙታን ባስነሳው በናዝሬቱ በየሱስ ክርስቶስ ስም መዳኑንና ፊታችሁ መቆሙን እናንተም ሆናችሁ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይህን ይወቅ፡፡ እርሱም እናንተግንበኞች የናቃችሁት የማእዘን ራስ የሆነው ድንጋይ ነው፡፡ ደኅንነት በሌላ በማንም አይገኝም፧ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተስጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና፡፡»EWAmh 136.2

    ሰዎቹም ጴጥሮስና ዮሐንስ እንዲህ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ በመደነቅ ከየሱስ ጋር እንደነበሩ ተገነዘቡ፡፡ ምክንያቱም በእነርሱ ላይ የታየው ማንነት ልክ የሱስ በጠላቶቹ ፊት ያሳይ የነበረው ዓይነት ጻድቅና ፍርሃት የሌለው ባህሪ ነበር፡፡ ጴጥሮስ የሰ ስን በካደው ጊዜ በገጽታው ላይ ያሳየው ርኅራኄና ኃዘኔታ ገስጾት ነበር አሁን ደግሞ ለጌታው በድፍረት እውቅና የስጠው ጴጥሮስ ድጋፍና በረከት እንዲቸረው ሆነ፡፡ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ መሞላቱ ከየሱስ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘቱ ምልክት፡፡ EWAmh 137.1

    ቀሳውስቱ በደቀ መዙሙርቱ ላይ ያላቸው ጥላቻ ይታይባቸው ዘንድ ድፍረት አልነበራቸውም:: በመሆኑም ከሸንጎው እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ በአንድነት ተሰብስበው በመምከር እንግዲህ እነዚህን ሰዎች እንዴት እናድርጋቸው? በየሩሳሌም የሚኖር ሁሉ በእነርሱ እጅ የተደረገውን ድንቅ ታምር አውቆአል፧ ስለዚህ ይህን ማስተባበል አንችልም” ተባባሉ፡፡ ይህ ድንቅ ሥራ በሕዝቡ ዘንድ እንዳይሰራጭ ፈርተው ነበር፡፡ ወሬው ሙሉ ለሙሉ ከታወቀ ቀሳውስቱ ያላቸውን ኃይል እንደሚያጡ ተሰምቶአቸዋል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ በሕዝቡ ዘንድ እንደ የሱስ ገዳይ ሊታዩ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ለማድረግ የደፈሩት ሐዋርያቱን አስፈራርተው ከዚህ በኋላ በየሱስ ስም እንዳይናገሩ ትእዛዝ መስጠት ነው ነገር ግን ጴጥሮስ የዩአቸውንና የሰሟቸውን ነገሮች በድፍረት እንደሚናገሩ በይፋ አስታወቃቸው:: EWAmh 137.2

    ደቀ መዛሙርቱ በሥቃይና በህመም የነበሩትን በየሱስ ኃይል መፈወሳቸውን ቀጠሉ፡፡ በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕዝቦች በተስቀለው፣ ከሞት በተነሳውና ወደ ሰማይ ባረገው አዳኝ ሰንደቅ ዓላማ ስር ይሰለፉ ነበር፡፡ ቀሳውስትና ሽማግሌዎች እንዲሁም ከእነርሱ ጋር ልዩ ቁርኝት የነበራቸው ፍርሃት ገብቶአቸውና ታውከው ነበር እነዚህ ሰዎች በሕዝቡ ዘንድ የሚስተዋለውን መደነቅ ለማርገብ በማሰብ ሐዋርያቱን ዳግመኛ እስር ቤት ጨመሯቸው፡፡ በድርጊቱ ሰይጣንና መላእክቱ ኩራት ተሰማቸው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን የእግዚአብሔር መላእክት የወህኒ ቤቱን በራፍ በመክፈት ከቀሳውስት አለቆችና ሽማግሌዎች ትእዛዝ በቶቃራኒ «ሂዱ በቤተመቅደሱም አደባባይ ቁሙ የዚህንም ህይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ ንገሩ” አሏቸው:: EWAmh 137.3

    ጉባዔው ከተሰበሰበ በኋላ ሐዋርያትን ከእስር ቤት እንዲያመጡ ሰዎችን ላኩ:: ነገር ግን ኃላፊዎቹ የእስር ቤቶቹን በራፍ ቁልፎች ሲከፍቱ አላገኟቸውም ነበር: ከዚያም ወደ ቀሳውስቱና ሽማግሌዎቹ በመመለስ «እስር ቤቱ በሚገባ ተቆልፎ፤ ጠባቂዎቹም በበሩ ላይ ቆመው አገኘን፤ ከፍተን ስንገባ ግን በውስጡ ማንም አልነበረም» አሏቸው፡፡ ከዚያ አንድ ሰው መጥቶ «እነሆ እስር ቤት ያስገባችኋቸው ሰዎች በቤተመቅደሱ አደባባይ ቆመው ሕዝቡን እያስተማሩ ናቸው አላቸው: የጥበቃ ሹሙም ከወታደሮቹ ጋር ሄዶ ይዞ አመጣቸው ያመጧቸው ግን ሕዝቡ በድንጋይ እንዳይወግሯቸው ስለፈሩ በኃይል ሳያስገድዱ ነበር፡፡ ሐዋርያትንም አምጥተው በሸንጎው ፊት አቆሟቸው ሊቀ ካኅናቱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው በዚህ ስም እንዳታስተምሩ በጥብቅ አስጠንቅቀናችሁነበር፧እናንተግን የሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ ደግሞም እኛን ለዚህ ሰው ደም ተጠያቂዎች ልታደርጉን ቆርጣችሁ ተነሳችሁ!» EWAmh 137.4

    እነዚህ የአይሁድ መሪዎች ለእግዚአብሔር ከነበራቸው ፍቅር ይልቅ የሰዎችን ምስጋናና ውዳሴ የሚወዱ ግብዞች ነበሩ: ልባቸው በእጅጉ ከመደንደኑ የተነሳ በሐዋርያቱ ይደረጉ የነበሩ ብርቱ ተአምራቶች እነርሱን ከማስቆጣት ውጪ ሌላ ፋይዳ ኣልነበራቸውም: ደቀ መዛሙርቱ ስለ የሱስ ስቅለት፣ ተንሳኤና እርገት ከሰበኩ ገዳዩ መሆናቸውን በመመስከር የጸጸት ስሜት እንደሚያመጣባቸው ያውቁት ነበር፡፡ በመሆኑም ደሙ በአኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” በማለት በፍጹም ጥላቻ ከመናገር ወጪ የየሱስን ደም ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም:፡፡ EWAmh 138.1

    ሐዋርያቱ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ሊታዘዙ እንደሚገባ በድፍረት ነገሯቸው «ከሰው ይልቅ ለግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል! እናንተበእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁት የሱስን የአባቶቻችን አምላክ ከሙታን አስነሳው፤ እርሱም ለእስራኤል ንስሐንና የኃጢአትን ሥርየት ይሰጥ ዘንድ እግዚአብሔር የሁሉ አዳኝና እራስ አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው፡፡ እኛም ለእነዚህ ነገሮች ምስክር ነን ደግሞም እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ምስክር ነው፡፡» ገዳዮቹ በእነዚህ ከፍርሃት ነጻ በሆኑ ቃላት በቀጣ በመንደዳቸው ሐዋርያትቱን በመግደል ዳግመኛ እጆቻቸውን በደም ሊነክሩ ወሰኑ፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተላከ አንድ መልአክ የገማልያልን ልብ በመንካት ለቀሳውስቱና ለገዢዎቹ ምክር እንዲለግስ አደረገ «እነዚህን ሰዎች ተዉአቸው፤ አትንኳቸው ሐሳባቸው ወይም አድራጎታቸው ከሰው ከሆነ ይጠፋልና ከእግዚአብሔር ከሆነ ግን ልትገቷቸው አትችሉም እንዲያውም ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ትገኙ ይሆናል» አላቸው፡፡ ቀሳው ስቱና ሽማግሌዎች ሐዋርያትን እንዲያስገድሉ ለማድረግ የክፉ መእክት በስፍራው ይሰፉ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ከራሳቸው ከአይሁድ መሪዎች አንዱን በማስነሳት ለአገልዮቹ የቆመ ድምጽ እንዲሰማ አደረገ: ሐዋርያቱ የሚሠሩት ሥራ ገና ባለማብቃቱ ለየሱስ ስም፣ ላዩአቸውና ለሰሟቸው ነገሮች ምስክር በመሆን በነገሥታት ፊት መቆም ነበረባቸው:: ሐዋርያፋን አስጠርተው ካስገረፏቸው በኋላ ዳግኛ በየሱስ ስም እንዳይናገሩ አዘው ለቀቋቸው «ሐዋርያትም ስለ ስሙ ውርደትን ለመቀበል በመብቃታቸው ደስ እያላቸው በቤተመቅደስም ሆነ በየቤቱ የሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ከማስተማርና ከመስበክ ወደ ኋላ አላሉም ነበር፡፡” በዚህም የእግዚአብሔር ቃል ያድግና ይስፋፋ ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ባዩአቸውና በሰሟቸው ነገሮች ምስክር በመሆን በየሱስ ስም ታላላቅ ተአምራቶችን ያደርጉ ነበር፡፡ EWAmh 138.2

    በእያንዳንዱ ትውልድ ለሚገኙ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደ መልህቅ የሚያገለግሉ ቅዱስ እውነቶችን በተለየ ጥንቃቄ እንዲጠብቁ ከእግዚአብሔር የተላኩ መላእክትን ተመልክቼ ነበር፡፡ ለጌታችን ስቅለት፣ ትንሳኤና እርገት ምስክር በሆኑት በሐዋርያቱ ላይ መንፈስ ቅዱስ በተለይ አርፎ ነበር የክርስቶስ ስቅለት፣ ትንሳኤና እርገት በተለይ ለእስራኤላውያኑ ተስፋና አስፈላጊ እውነቶች ነበሩ፡፡ ሁሉም ትኩረታቸውንና ብቸኛ ተስፋቸውን በዓለም አዳኝ ላይ በማድረግ እርሱ ህይወቱን መስዋዕት አድርጎ በከፈተው መንገድ ላይ እየተጓዙና የእግዚአብሔርን ሕግ እየጠበቁ እንዲኖሩ ተጠርተዋል፡፡ የሱስ በአይሁድ የተጠላበትንና የተገደለበትን ተመሳሳይ ሥራ ለሚሠሩት ደቀ መዛሙርት ኃይል በመስጠቱ የእርሱን ጥበብና መልካምነት ተመልክቻለሁ፡፡ እነርሱ በስሙ በሰይጣን ሥራ ላይ ኃይል ነበራቸው፡፡ በየሱስ ሞትና ትንሳኤ ወቅት በአናቱ ዙሪያ ክብ ብርሃንና ክብር ተመልክቼ ነበር---የዓለም አዳኝ እንደነበር የሚያመላክት ቅዱስና ሕያው እውነት::EWAmh 139.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents