Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    67—የመከራው ዘመን

    ቅዱሳኑ በቡድን ሆነው ከተሞችንና መንደሮችን በመልቀቅ ሰው ወደ ማይኖርበት ስፍራ መኖር እንደ ጀመሩ ተመልክቼ ነበር፡፡ ኃጥአን በረሃብና ጥማተሲያልቁ ለእነዚህ ወገኖች ግን መላአክት ያሟሉላቸው በመቀጠል የምድር መሪዎች በአንድነት ሲመክሩ የተመለከትኩ ሰይጣንና መላእክቱ በእነርሱ ዙሪያ በሥራ ተጠምደው ነበር እንግዳውን እምነታቸውን ካልተዉ፣ በሰንበት ማረፋቸውን አቁመው በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን አምልኮ ካላደረጉ ህዝቡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እነርሱን ለመግደል ነጻ መሆኑን የሚገልጹ ቅጂዎች በምድሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ተበተኑ ነገር ግን በዚህ የመከራ ሰዓት ቅዱሳኑ የማምለጫ መንገድ ይዘጋጅላቸው ዘንድ ተረጋግተውበአምላካዊው ተስፋ ላይ ታምነውና እርሰን ተደግፈው ነበር፡፡ በአንዳንድ ስፍራዎች ቅዱሳኑ እንዲገደሉ የሚደነግገ ሕግ ከመውጣቱ አስቀድሞ ኃጥአን ሊገድሏቸው ቢቻኮሉም ነገር ግን መላእክት በሰው ተመስለው ተዋግተውላቸዋል፡፡ ሰይጣን የልዑሉን ቅዱሳን በማጥፋት ውጤታማ ለመሆን ቢመኝም ነገር ግን መላእክት እንዲጠብቋቸው የሱስ አዝዞላቸው ነበር፡፡ በአረማውያን ዙሪያ እየኖሩ አምላካዊውን ሕግ ከጠበቁት ጋር በሚገባው ኪዳን እግዚአብሔር የሚከብር ሲሆን፤ እርሱን ረዘም ላሉ ጊዜያቶች ሲጠባበቁ የኖሩ ታማኞች ሞትን ሳያዩ በመለወጣቸው ደግሞ የሱስ ይከብራል፡፡ EWAmh 209.1

    ከዚህ በኋላ ቅዱሳኑ ታላቅ የአእምሮ ሥቃይ ሲደርስባቸው ተመለከትኩ፡፡ እነዚህ ወገኖች በምድር ክፉ ነዋሪዎች የተከበቡ ይመስሉ የነበረ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ሰዉ በእነርሱ ላይ ጸንፈኛ አመለካከት ነበረው፡፡ ከቅዱሳኑ አንዳንዶቹ በክፉዎቹ እጅ እንዲጠፉ እግዚአብሔር እንደፈቀደ አድርገው በማሰብ መፍራት ጀምረው ነበር፡፡ ሆኖም ዐይኖቻቸው ቢከፈቱ ኖሮ በእግዚአብሔር መላእክት መከበባቸውን መመልከት በቻሉ ነበር፡፡ በመቀጠል የክፉው መላእክት ሰራዊት ኃጥአን ቅዱሳኑን እንዲገድሏቸው መገፋፋት ጀመሩ፡፡ ነገር ግን ኃጥአን ወደ እግዚአብሔር ህዝቦች መድረስ ከመቻላቸው አስቀድሞ የኃያላኖቹን ቅዱሳን መላእክት አጥር ማለፍ ነበረባቸው፡፡ ይህ ደግሞ የማይታሰብ ነው: የግዚአብሔር መላእክትኃጥአንን ከብበው ሲገፋፉአቸው የነበሩትን ክፉ መላእክትን በመጣል ኃጥአን እንዲበታተኑ ያደርጉ ነበር EWAmh 209.2

    ወቅቱ ለቅዱሳኑ አስፈሪና ከባድ ህመም የታከለበት ነበር በመሆኑም እነዚህ ህዝቦች እግዚአብሔር ያድናቸው ዘንድ ቀንና ሌሊት በዕንባ ይታጠቡ ነበር የነበሩበት ሁናቴ ከውጭ ሲታይ ከኃጥአኑ በትር ሊያመልጡ የሚችሉበት አንዳችም ቀዳዳ ያለ አይመስልም፡፡: በወቅቱ ኃጥን ድል የቀናቸው በመምሰል ለምንድን ነው አምላካችሁ ከጃችን ያላዳናችሁ? ለምን ወደ ሰማይ ሄዳችሁ እራሳችሁን አታድኑም? እያሉ ቢያንባርቁባቸውም ቅዱሳኑ ግን ለሚናገሩት አንዳችም ትኩረት ባለመስጠት እንደ ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር ይታገሉ ነበር፡፡ መላ ክት እነዚህን ወገኖች ለማዳን ቢናፍቁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ህዝቦች ጽዋውን መጠጣትና ጥምቀቱን መጠመቃቸው የግድ በመሆኑ ጥቂት መጠበቅ ነበረባቸው ስሙ በኃጥአን የተነቀፈ ታግሶ መቆየት የማይሆንለት አምላክ ገናናነቱን የሚያሳይበትና ቅዱሳኑን የሚታደግበት ጊዜ ተቃርቦ ነበር፡፡ አርሱ ስማቸው በመጽሐፉ ላይ ተጽፎ በትዕግሥት በመጠባበቅ የቆዩትን እያንዳንዳቸውን ለስሙ ክብር ሲል ያድናል፡፡ EWAmh 210.1

    ወደ ጥንታዊው የኖህ ዘመን እንድመለከት ተደርጌ ነበር፡፡ ዝናቡ ሲወርድና ምድር በጎርፍ ስትጥለቀለቅ ኖህና ቤተሰቡ መርhቧ ውሰጥ ገብተው---በሩ በእግዚአብሔር ተቆልፎ ነበር፡፡ ኖህ ለዚያ የጥንት ዓለም ህዝብ በእምነት ላይ ተመርኩዞ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም እነርሱ ግን ያሾፉና ይሳለቁበት ነበር፡፡ ነገር ግን ዝናብ ሲዘንብና ሰዎች መስጠም ሲጀምሩ በውሃው ላይ መንሳፈፍ በመጀመር ታማኙን ኖህና ቤተሰቡን እያዳነ ወዳለው መርከብ ተመለከቱ፡፡ በተመሳሳይ ከሚመጣው አምላካዊ ቁጣ በእምነት ዓለምን ሲያስጠነቅቁ የነበሩ የእግዚአብሔር ህዝቦች እንደሚድኑ ተመልክቻ ለሁ: ለአውሬው ሳይሰግዱ ወይም ምልክቱን ሳይቀበሉ በመቆማቸው እንደሚለወጡ የሚጠባበቁትን ቅዱሳን ኃጥአን ያጠፏቸው ዘንድ እግዚአብሔር አይታገስም፡፡ ኃጥአን ቅዱሳኑን እንዲገድሉ ጸንተው ቢፈቀድላቸው ኖሮ በእግዚአብሔር ላይ መራር ጥላቻ ያላቸው ሰይጣንና መላክቱ አብልጠው በከበሩ ነበር ነገር ግን በቅዱሳኑ ወደ ሰማይ የመሄድ እውነታ ላይ ሲሳለቁ የነበሩ ሁሉ እግዚአብሔር ለህዝቡ ለሚያደርገው ጥንቃቄ ምስክር በመሆን በአስደናቂ ግርማ የተሞላውን ደኅንነታቸውን ያያሉ፡፡ EWAmh 210.2

    ኃጥአን ከተሞችንና መንደሮችን እየለቀቁ የሚሄዱትን ቅዱሳን ለመግደል በመመኘት ይከታተሏቸዋል፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔርን ህዝቦች ለመግደል የታሰበበት ሠይፍ ተሰብሮና አንደ ገለባ ተልፈስፍሶ ይወድቃል፡፡ የአግዚአብሔር መላእክት ለቅዱሳኑ ጋሻ ይሆኗቸዋል አምላካቸው ይታደጋቸው ዘንድ ቀንና ሌሊት የሚያሰሙትም ለቅሶ በጌታ ፊት ይደርሳል፡፡: EWAmh 211.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents