Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    66—የሦስተኛው መልአክ መልእክት መዘጋት

    የሦስተኛው መልአክ መልእክት ወደ ተዘጋበት የመጨረሻ ጊዜ እንድመለከት ተደርጌ ነበር: የእግዚአብሔር ኃይል በህዝቦቹ ላይ አርፎ ስለ ነበር ሥራቸውን አገባድደውና ከፊታቸው ላለው የፈተና ሰዓት ተዘጋጅተው ነበር፡፡ እነዚህ ህዝቦች ከጌታ ፊት የሚወርደውን የሚያረሰርስ የኋለኛ ዝናብ ተቀብለዋል---ሕያው የሆነው ምስክርነታቸውም ታድሶአል፡፡ የመ ረሻውና ታላቁ ማስጠንቀቂያ በየስፍራው በማስተጋባቱ መልእክቱን የማይቀበሉ የምድር ነዋሪዎችን በመበጥበጥ በቁጣ እንዲገነፍሉ አድርጎኣል፡፡ EWAmh 206.2

    መላእክት በፍጥነት ወደ ሰማይ ሲወጡና ሲወርዱ ተመለከትኩ፡፡ አነስተኛ የቀለም ማስቀመጫ በጎኑ የያዘ አንድ መልአክ ከምድር ወደ የሱስ ተመልሶ በመምጣት ቅዱሳን ተቆጥረውና ታትመው ማብቃቱንና ሥራው ፍጻሜ ማግኘቱን ሪፖርት አደረገ፡፡ ከዚያም አስርቱን ትእዛዛት ከያዘው ከታቦቱ ፊት ያገለግል የነበረው የሱስ ጥናውን ወደታች ሲወ ረውር ተመለከትኩ፡፡ የሱስ እጆቹን ወደ ላይ ብድግ ካደረ7 በኋላ ድምጹን ከፍ አድርጎ «ተፈጸመ” በማለት ጮኸ የሱስ «ዐመጸኛው በአመጹ ይቀጥል፤ ርኩሱም ይርከስ፤ ጻድቁም ይጽደቅ፤ ቅዱሱም ይቀደስ» የተሰኘ ውን ጸኑ ቃል ሲያስተጋባ መላው የመላእክት ሰራ ዊት በአናቶቻቸው ላይ የደፉትን ዘውድ አያወለቁ አስቀመጡ፡፡ EWAmh 206.3

    እያንዳንዱ ጉዳይ በህይወት ወይም በሞት ተወስኖ አብቅቶአል የሱስ በቤተመቅደስ እያገለገለ በነበረበት ወቅት በመጀመሪያ በመቃብር ላሉ ጻድቃን በመቀጠል ደግሞ በህይወት ላሉት ጻድቃን ፍርድ እየተሰጠ ነበር፡፡ ክርስቶስ ለህዝቡ ሥርየት በማምጣትና ኃጢአታቸውን በመሰረዝ መንግሥቱን ተቀብሏል፡፡ የመንግሥቱ ወራሾች ተዘጋጅተዋል የበጉ ሠርግ ፍጻሜ አግኝቶአል፡፡ ከሰማይ በታች ያሉ መንግሥታት ልዕልና፣ ሥልጣንና ታላቅነት ለየሱስና ለደኅንነት ወራሾች ተሰጡ፡፡ የሱስ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ሆኖ ሊነግሥ ነበር EWAmh 207.1

    የሱስ ከቅድስተቅዱሳኑ ሲወጣ በመጎናጸፊያው ግርጌ ላይ የሚያንቃጭሉትን የደወል ድምጾች ሰማሁ:፡፡ ከዚያም ይህን ስፍራ ለቅቆ ሲወጣ በጽልመት የተዋጠ ደመና የምድርን ነዋሪዎች ሸፈነ፡፡ በዚህን ወቅት በበደለኛውና በሰብዓዊው ፍጡር ኃጢአት ቅር በተሰኘው እግዚአብሔር መሃል የሚያማልድ አልነበረም የሱስ በእግዚአብሔርና በበደለኛው ሰው መሃል ቆሞ በነበረበት ወቅት በህዝቡ መሃል እራስን የመግዛት ሁናቴ ነበር: ነገር ግን እርሱ ከህዝቡና ከአብ መሃል ሲወጣ ይህ አራስን የመግዛት ክህሎት በመወሰዱ ሰይጣን በጨረሻ ንስሐ ባልገቡት ላይ ሉ ለሙሉ ሥልጣን ኖረው:: የሱስ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ በነበረበት ወቅት መቅሰፍቶቹ መውረድ አይችሉም ነበር፡፡ ነገር ግን በዚያ የነበረው ሥራው ፍጻሜ ካገኘና የማማለድ ሥራው ከተደመደመ በኋላ የእግዚብሔርን ቁጣ ከመውረድ የሚያግደው አንዳችም መንስኤ አልነበረም በመሆኑም በደኅንነት ነበር፡፡ የሱስ ላይ የተሳለቁ መከላከያ ዐልባ ኃጢአተኛችን አናት በቁጣ የነደለ ወረደ፡፡ የየሱስ የማማለድ ሥራ በተዘጋበት በዚያ -ስፈሪ ወቅት ቅዱሳን ያለ አንዳች አማላጅ በቅዱሱ እግዚአብሔር ዐይኖች ጥበቃ ብቻ ይመላለሱ እያንዳንዱ ጉዳይ ተወስኖና---እያንዳንዱ ዕንቁ ተቆጥሮ አብቅቶ ነበር ከታቀደው አጠር ላሉ ጊዜያት በሰማያዊው መቅደስ የውጪያው ክፍል በመዘግየት እርሱ በቅድስተቅዱሳኑ ውስጥ እያለ በኑዛዜ የቀረቡት ኃጢአቶች በሙሉ የተነሳሒዎቹን ቅጣት መቀበል በሚገባውና የኃጢአት ጠንሳሽ በሆነው ሰይጣን ላይ ተላከኩ፡፡ EWAmh 207.2

    ከዚያም የሱስ ልብሰ ተክኅኖውን በማውለቅ ንጉሣዊ መጎናጸፊያውን ለብሶ አየሁት በአናቱ ላይ አንዱ በሌላው ላይ የተደራረበ አያሌ ዘውዶች ነበሩ:: የሱስ በመላእክት ሰራዊት ተከብቦ ሰማይን ለቅቆ ወጣ፡፡ በዚህን ወቅት መቅሰፍቶቹ በምድር ነዋሪዎች ላይ ይወርዱ ነበር አንዳንዶች እግዚአብሔርን ሲያወግዙና ሲራገሙ ሌሎች ግን ፈጥነው ወደ እግዚአብሔር ህዝቦች በመሄድ ከአምላካዊው ፍርድ እንዴት ማምለጥ እንዳለባቸው ይነግሯቸው ዘንድ ልመናቸውን ያቀርቡ ነበር ሆኖም ቅዱሳኑ አንዳችም ሊያደርጉላቸው የሚችሉት ነገር አልነበረም፡፡ ለኃጢአተኞች የመጨረሻው ዕንባ ፍስሶአል፣ የመጨረሻው በህመም የተሞላ ጸሎት ተጸልዮአል፣ የመጨረሻው ሽክም ተራግፎአል እንዲሁም የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአል፡፡ ከዚህ በኋላ ለእነርሱ ጥሪ የሚያቀርብ በምህረት የተሞላ ድምጽ የለም ቅዱሳንና መላው ሰማይ ለእነርሱ ደኅንነት ከፍተኛ ፍላጎት በነበራቸው ወቅት እነርሱ ግን ለራሳቸው ደንታ አልነበራቸውም፡፡ ህይወትና ሞት በፊታቸው ቀርቦ ነበር ብዙዎች ህይወትን ቢመኙም ነገር ግን ለማግኘት አንዳችም ጥረት አላደረጉም: ህይወትን ባለመምረጣቸው አሁን ለበደለኛው ሥርየት የሚሆን ደም፣ ልመናውን የሚያቀርብላቸው ርኅሩኅ አዳኝም ሆነ «ኃጢአተኛውን ለጥቂት ጊዜ ታደጉ” ብሎ የሚጮኽ ድምጽ የለም፡፡ መላው ሰማይ «ተፈጸመ! አበቃ!» የተሰኘውን ከየሱስ አንደበት የወጣ ድምጽ ሲሰማ ከእርሱ ጋር ህብረት ፈጠረ የደኅንነት ዕቅድ ፍጻሜ ቢያገኝም ሊቀበሉት ፈቃደኞች የሆኑት ግን ጥቂቶች ነበሩ፡፡ የምህረት ድምጽ እየተመናመነ ሲሄድ ኃጥአን በፍርሃትና ሽብር ተሞሉ፡፡ ግልጽ በሆነ ቋንቋ «በጣም ዘገያችሁ! በጣም ዘገያችሁ! የሚል ድምጽ ሰሙ: EWAmh 208.1

    ለእግዚአብሔር ቃል ዋጋ ሳይሰጡ የቀሩት አሁን አምላካዊውን ቃል በመሻት ከባሕር ጫፍ እስከ ባሕር ጫፍ ከሰሜን እስከ ምስራቅ ይቅበዘበዙ ነበር፡፡ መልአኩ እንዲህ ሲል ተናገረ «የእግዚአብሔርን ቃል አያገኙም፡፡ በምድሪቱ ላይ ረሃብ ይሆናል፡፡ ይህ ረሃበ የምግብ ወይም የውሃ እጦት ሳይሆን ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ረሃብ ነው፡፡ በየቀኑ ህይወታቸው ደኅንነትን በመቃወም ከሰማያዊው ሐብት ይልቅ ለምድራዊው ንብረትና ፈንጠዝያ ከፍ ያለ ዋጋ ሰጥተዋል፡፡ የሱስን በመቃወም ቅዱሳኑን አዋርደዋል፡፡ ዐመጸኛው በዐመጹ ለዘላለም መቀጠል አለበት፡፡» EWAmh 208.2

    አያሌ ኃጥአን ሥቃይ እያስከተለባቸው ባለው መቅሰፍት በእጅጉ ተበሳጭተው ነበር እየወረደ ያለው መቅሰፍት አስፈሪ ህመም ፈጥሮባቸው ነበር፡፡ ወላጆች አምርረው ልጆቻቸውን ለችግሩ መንስዔ ሲያደርጉ ልጆች ደግሞ ወላጆቻቸውን ወንድም እህቱን፣ እህት ወንድሟን ይወነጅሉ ነበር፡፡ «hዚህ አስፈሪ ሰዓት ሊያድነኝ ይችል የነበረውን እውነት እንዳልቀበል ምክንያቱ አንተነህ (አንቺ ነሽ!” የሚሉ ኸቶች ከየአቅጣጫው ይሰሙ ነበር ህዝቡ ፊቱን በአገልጋዮቹ ላይ በማዞር በመራራ ጥላቻ «ለሚመጣው ነገር አላስጠነቀቃችሁንም፡፡ ዓለም ወደ ተሻለ ሁናቴ እንደሚለወጥ በመለፈፍ ሰላም፣ ሰላም እያላችሁ ከመጮኽ ውጪ ስለዚህ ሰዓት አልነገራችሁንም፡፡ ስለዚህ ወቅት ማስጠንቀቂያ ሲሰጡን የነበሩትን—ውድቀት ሊያመጠ ብን የሚችሉ አክራሪዎችና ክፉዎች በማለት ኮነናኋቸው፡፡» አገልጋዮች ከእግዚአብሔር ቁጣ እንደማያመልጡ ተመልክቻ ለሁ፡፡ በእነርሱ ላይ የሚደርሰው ሥቃይ ሲመሯቸው ከነበሩት ህዝቦች አሥር ጥፍ የበሪታ ነበር፡፡EWAmh 208.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents