Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    22—ማሟያ

    ዝርዝር መግለጫ

    የተወደዳችሁ ክርስቲያን ወዳጆቼ፡፡ ይህ ያቀረብኩት አጠር ያለ የግል ተሞክሮና አመለካከት የያዘ መጽሐፍ በ1851 ዓ.ም. ላይ ታትሞአል፡፡ በዚህ አነስተኛ መጽሐፍ የቀረቡትን አንዳንድ ነጥቦች በመመልከት ተጨማሪ የቅርብ አመለካከቶቼን ማጋራት የእኔ ተግባር እንደመሆኑ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡፡ EWAmh 62.2

    1. «ሰንበት ቅዱስ መሆኑንና የዚህ ቀን ቅድስና እውነተኛይቱን የእግዚአብሔር እስራኤልና ኢአማንያኑን እንደ ግድግዳ በመክፈል የሚቀጥል መሆኑን ተመልቼአለሁ፡፡ በዚህም ሰንበት የእግዚአብሔርን ውድ ልጆች---የቅዱሳንን ልብ በአንድ ለማዋሃድ የሚቀርብ ታላቅ ጥያቄ ነው:፡፡ እግዚአብሔር ሰንበትን የማይመለከቱና የማይጠብቁ ልጆች እንደነበሩት ተመልክቼአለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች በሰንበት ላይ ያለውን ብርሃን አልተቃወሙም፡፡ እንዲሁም በመከራው ጊዜ መጀመሪያ ላይ ሰንበትን ይበልጥ በሙላት ለመስበክ ስንወጣና በይፋ ስንናገር በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተን ነበር፡፡” EWAmh 62.3

    ይህ አመለካከት የተሰነዘረው በ1847 ላይ በጣም አነስተኛ አድቬንቲስት ወንድሞች ሰንበትን ይጠብቁ በነበረበት ወቅት ሲሆን ሰንበትን መጠበቅ በእግዚአብሔር ሕዝቦችና አማኝ ባልሆኑት ሕዝቦች መሃል መለያ መስመር ለመሆን በቂ ነው የሚል አመለካከት ከእነርሱ መካከል በጥቂቶቹ ይሰነዘር ነበር፡፡ አሁን ያ አመለካከት ወደ ፍጻሜ እየመጣ መሆኑ መታየት ጀምሮአል፡፡ «የመከራው ወቅት መጀመሪያ” በሚል በዚህ ቦታ የተጠቀሰው ሃረግ መቅሰፍቶቹ መውረድ የሚጀምሩበትን ጊዜ ሳይሆን ነገር መውረድ ከመጀመራቸው አስቀድሞ ክርስቶስ በመቅደስ እያለ ስላለው አጭር ጊዜ ነው የሚናገረው፡፡ የደኅንነት ሥራ ወደ ፍጻሜ በሚመጣበት በዚያን ወቅት በምድር ላይ መከራ ይመጣል መንግሥታት ይቆጣሉ የሦስተኛው መልአክ ሥራ ግን አይስተጓጎልም፡፡ በዚያን ወቅት ‹‹የኋለኛው ዝናብ” ወይም ከጌታ ዘንድ የሚላከው መታደስ ለሦስተኛው መልአክ ጩኸት ኃይል በመስጠት ሰባቱ መቅሰፍቶች በሚወርዱበት ጊዜ ቅዱሳን ጸንተው እንዲቆሙ ያዘጋጃቸዋል፡፡ EWAmh 63.1

    2 . «የተከፈተውና የተዘጋው በር» በሚል የቀረበው መልእክት የተሰጠው በ1849 ዓ.ም. ላይ ነበር፡፡ ከሰማያዊው መቅደስ እና ከክርስቶስ አገልግሎት አኳያ የቀረበው የራእ. 3:7-8 አጠቃቀም ሙሉ ለሙሉ አዲስ ዓይነት ነው፡፡ በጥቅሱ የቀረበው ጽንሰ ሃሳብ ከዚህ ቀደም በማንም ሰው ተብራርቶ ሲቀርብ አልሰማሁም: የቤተመቅደሱ ጉዳይ በግልጽ እየተስተዋለ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የመልእክቱ አተገባበር ኃይልና ውበቱ ላይ መታየት ችሎአል፡፡ EWAmh 63.2

    3. «ትሩፋን ሕዝቦቹ ዳግም እንዲያንሰራሩ ለማድረግ ጌታ እጁን ለሁለተኛ ጊዜ ዘርግቶ ነበር” በሚል የተሰነዘረው አመለካከት በአንድ ወቅት ክርስቶስን ይሹ የነበሩ እነዚህ ሕዝቦች የነበራቸውን አንድነትና ጥንካሬ ብቻ የሚያሳይ ሲሆን፧ በእርግጥም ክርስቶስ ከዚህ መንጋ ጋር አንድ በመሆን ሕዝቡ ዳግመኛ እንዲያንሰራራ እያደረገ ነበር EWAmh 63.3

    4. የመናፍስት መገለጫዎች- «በኒውዮርክ እና በሌሎች ስፍራዎች የተስተዋለው ስውር የቤተክርስቲያንን ደጃፍ የማንኳኳት ደባ የመነጨው ከሰይጣን ኃይል መሆኑን ተመልክቻለሁ፡፡ በሌሎች ዘንድ ከፍ ያለ ተቀባይነትን ለማግኘት ያስችላቸው ዘንድ እነዚያን የተታለሉትን አሹሩሩ እያሉ በማባበልና የሚቻልም ከሆነ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች አእምሮ በመሳብ የመንፈስ ቅዱስን አስተምህሮና ኃይል እንዲጠራጠሩ የማድረጉ እንዲህ ያሉት ኃይማኖታዊውን ካባ በመደረብ የሚፈጸሙ ተግባራት ወደፊት ይበልጥ እየተለመዱ ይሄዳሉ፡፡» ይህ አመለካከት የተሰጠው ከአምስት ዓመት ቀደም ብሎ 1849 ዓ.ም. ላይ ነው፡፡ ይህ በሮችስተር ተወስኖ የነበረው የመናፍስት ግልጽ አሠራር «የሮችስተር ማንኳኳት” በመባል ይታወቃል፡፡ hዚያን ጊዜ አንስቶ የስህተት ትምህርት ማንም ከሚጠብቀው በላይ እየተሰራጨሄደ፡፡ EWAmh 64.1

    ቀደም ብሎ በመልእክቱ የቀረበውና ወርሃ ነሐሴ 1850 ዓ.ም. ላይ የተሰጠው «በምስጢር የመነጠቅ” አስተምህሮ በስፋት እየተሰራጨይገኛል፡፡ የሚከተለው የመልእክቱ አካል ነው «በስውር መነጠቅ ይበልጥ በስፋት እየተሰራጨእንደሚሄድና አስተምህሮው የተሳሳተ መሆኑን መናገር እንደ ስድብ የሚቆጠርበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን ተመልክቼ ነበር የሰይጣን ኃይል እየጨመረ በመሄድ አንዳንድ የልብ ተከታዮቹ ተአምራትን የማድረግ ኃይል እንደሚኖራቸውና በዚህም በሰዎች ፊት እሳት ከሰማይ እስከ ማውረድ እንደሚደርሱ ተመልክቻለሁ፡፡ እነዚህ ዘመናዊ አስማተኞች ስውር መነጠቅንና ሰመመናዊ አሠራርን በመተግበርና ተአምራቶቻቸውን ጌታ የሱስ ክርስቶስ ካደረጋቸው ጋር አዛምደው በማቅረብf ብዙዎች የእግዚአብሔር ልጅ በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ ያደርጋቸው የነበሩ ተአምራቶች በዚህ ተመሳሳይ ኃይል የታጀቡ እንደሆኑ ያምናሉ፡፡»EWAmh 64.2

    በስፋት እየተሰራጨና ተቀባይነት እያገኘ ያለው ከነቱ የሆነው የመነጠቅ አስተምህሮ የሚቻል ቢሆን የተመረጡትን እንኳ እንደሚያስት ተመልክቻ ለሁ፡፡: ሰይጣን አሁን በክርስቶስ አንቀላፍተው የሚገኙትን ዘመዶቻችንን ወይም ጓደኞቻችንን ገጽታና ቅርጽ ምንም ሳይቀየር እንዳለ ከፊታችን የማቅ ረብ ኃይል ይኖረዋል፡፡ እነዚህ ልክ በህይወት እንዳሉ አድርጎ የሚያመጣቸው ወዳጆቻችን የሚናገሯቸው ቃላትና የድምፃቸው ቃና ድሮ ከምናውቀው ጋር አንድ ዓይነትና ተመሳሳይ ይሆናል፡፡ ይህ ሁሉ ደባ ቅዱሳንን ለማሳትና አስመሳይ ወደ ሆነ የእምነት ወጥመድ ውስጥ ለመክተት ነው፡፡ EWAmh 64.3

    አምላካዊውን ቃል አጥብቀው መያዝ እንዳለባቸው የሚገደዱት ቅዱሳን ወቅታዊውን እውነት አንድ ባንድ ማስተዋል እንዳለባቸው ተመልክቻለሁ:: የዲያብሎስ መንፈስ የተወደዱ ጓደኞቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ሆኖ በመገለጥ ሰንበት መሻሩን ሊናገር ወይም ሌሎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተምህሮዎችን ሊያሰራጭ ስለሚችል ቅዱሳን የሙታንን ሁኔታ ማስተዋላቸው የግድ ይሆናል፡፡ የሚናገሩት ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ያለ ኃይላቸውን ተጠቅመው አስደሳችና አጽናኝ ቃላትን ያፈሳሉ ተአምራትንም ያደርጋሉ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሙታን ምንም እንደማያውቁ በማስተዋልና መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነት በመያዝ ያ የተገለጸው የዲያብሎስ መንፈስ መሆኑን በመገንዘብ መናፍስቱን ለመቋቋም ሊዘጋጁ ይገባል፡፡ ተስፋ ያደረግነውን ነገር ቅንና ትሁት በሆነ መልኩ ለመንገር ዝግጅት በማድረግ አእምሮአችን በወቅታዊው እውነት እንዲሞላ ከማድረግ ውጪ ዙሪያችን ባሉ ነገሮች እንዲወሰድ መፍቀድ የለብንም:፡፡ በዚህ የስህተት ትምህርትና ማስመሰል በበዛበት ዘመን ጸንተን መቆም እንችል ዘንድ ከሰማይ ጥበብ ልንጠይቅ ይገባል፡፡ EWAmh 65.1

    ተስፋ ያደረግንበትን ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጠቅሰን ማቅረብ ስለሚኖርብን የተስፋችንን መሰረት በሚገባ ልንመረምር ይገባል፡፡ ይህ ስህተት እየተሰራጨስለሚሄድ ፊት ለፊት እንጋፈጠዋለን፡፡ ታዲያ ከወዲሁ ዝግጅት ካለደረግን በቀር ወጥመድ ውስጥ ገብተን ድል ልንሆን እንችላለን፡፡ ነገር ግን ከፊታችን ላለው ውዝግብ ዝግጅት በማድረግ በእኛ በኩል ማድረግ የምንችለውን ካደረግን እግዚአብሔር በእርሱ በኩል ያለውን ይሠራል--- ኃያል የሆነው ክንዱም ይጠብቀናል፡፡ ታማኝ ለሆኑት ነፍሳት እፎይታ ይሆን ዘንድ እነዚህ ወገኖች በሰይጣን ሐሰትና አስደናቂ ተአምራቶች እንዳይታለሉና እንዳይወሰዱ ዙሪያቸውን የሚጠብቋቸውን መላእክት እግዚአብሔር በቅርቡ በክብር ይልካል፡፡ EWAmh 65.2

    ይህ የስህተት አስተምህሮ ምን ያህል በፍጥነት እየተሰራጨእንደነበር ተመልክቻለሁ: በመብረቅ ፍጥነት የሚከንፉ ባቡሮች በፊቴ ሆነው ተመልቻለሁ፡፡ ሁናቴውን በጥንቃቄ እመለከት ዘንድ መልአኩ በነገረኝ መሰረት ዓይኖቼን ተክዬ ስመለከት መላው ዓለም አብሮ ያለ እንጂ ማንም የቀረ ያለ አይመስልም ነበር: «ለመንደድ እንደ ተዘጋጀ እስር ናቸው” ሲል መልአኩ ነገረኝ፡፡ ከዚያም ሁሉም ተሳፋሪዎች የሚመለከቱትን የመንግሥት ባለሟልና የተከበረ ዓይነት የሚመስለውን የሚመራቸውን ሰው አሳየኝና «በብርሃን መልአክ አምሳያ ሆኖ የሚመራቸው እርሱ ሰይጣን ነው፡፡» አለኝ፡፡ በመቀጠል «እርሱ አምላካዊውን ቃል ወስዶ ግዞተኞቹ በማድረግ ሐሰትን እንዲያምኑ የሚያደርጉና የሚኮንኗቸው ጠንካራ ማታለያዎች ተሰጥቶአቸዋል:: ይህ በሁለተኛ ደረጃ የሥልጣን እርከን ላይ የሚገኝ ወኪል መሐንዲስ ሲሆን ሌሎች ወኪሎቹ ደግሞ እርሱ በፈለጋቸው ጊዜ ምላሽ የሚሰጡባቸውን የተለያዩ ኃላፊነት ስፍራዎችን ሸፍነው የሚሠሩ ይሠራሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ በሰዎች ላይ ዘላለማዊውን ጥፋት ለማምጣት በመብረቅ ፍጥነት ይጓዛሉ፡፡”EWAmh 65.3

    የቀረ አለወይ? ስል መልአኩን ጠየቅኩት፡፡ እርሱም ወደ አንድ አቅጣጫ አመላከተኝና አነስተኛ አባላት ያሉት ቡድን በጠባቡ መንገድ ሲጓዙ ተመለከትኩ፡፡ ሁሉም እውነትን መሰረተያደረገ ጠንካራ ትስስርና ህብረት ያላቸው ይመስላል፡፡ «ሦስተኛው መልአክ እነዚህን መንጋዎች ለሰማያዊው መከር እያተመ ነው» በማለት መልአኩ ነገረኝ፡፡ ይህ ትንሽ መንጋ በብዙ የከፉ ፈተናዎችና ውዝግቦች ውስጥ ያለፈ በሚመስል መልኩ የድካም ገጽታ ይስተዋልበታል፡፡ በትዕይንቱ ጸሐይ ከደመናው ጀርባ ብቅ ብላ በፊታቸው ላይ ማንጸባረቋ ድላቸው በቅርቡ መሆኑን በማብሰር የአሸናፊነት ገጽታ እንዲላበሱ አድርጎአቸዋል፡፡ EWAmh 66.1

    ዓለም የተሳሳተውን አስተምህሮ የሚለይበትን ልዩ ዕድል ጌታ በቃሉ አማካኝነት እንደሰጠ ተመልክቻለሁ፡፡: ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች ባይኖሩም እንኳ ይህ ብቻውን ለክርስቲያን በቂ መረጃ ነው፡፡ በመቃብር ያለው፣ ስሙ በአንድ ሺሁ ዓመት መጨረሻ ላይ የሚጠራውና ሁለተኛው ትንሳኤ ላይ የተዘጋጀለትን ሞትና ሥቃይ ለመቀበል የሚጠራው ቶማስ ፔይን አሁን በሰማይ ከፍ ከፍ እየተደረገ ሆኖ በሰይጣን እየቀረበ ይገኛል፡፡ ስይጣን ቶማስ ፔይንን በዚህ ምድር ላይ የሚችለውን ያህል የተጠቀመበት ሲሆን አሁን ደግሞ ይኸው ሰው በሰማይ በእጅጉ እየከበረ ሆኖ በመቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ ቶማስ ፔይን እዚህ ያስተምር እንደነበር በሰማይም እያስተማረ እንደሆነ አድርጎ ሰይጣን ከእነ ገጽታው ሊያቀርበው ይችላል፡፡ በህይወቱም ሆነ በሞቱ እርሱንና የተሳሳተአስተምህሮውን አስፈሪ አድርገው የሚመለከቱት እንደነበሩ ሁሉ ነገር ግን አሁን በእርሱ ለመማር እራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ እግዚአብሔርንና የእርሱን ሕግ የናቁ ክፉና አመጸኞች ናቸው፡፡EWAmh 66.2

    (ስለ ቶማስ ፔይን የተሰጡትን አስተያየቶች ለማስተዋል «የቶማስ ፔይን መንፈሳዊ ጉዞ» በሚል ርዕስ በ REV C.HAMMOND በታተመው መጽሐፍ ላይ ፔይን ሰባተኛ ተብሎ በተቀመጠው የመናፍስት ዓለም ደረጃ ላይ በመድረስ የከበረ መንፈስ ሆኖ ቀርቦአል: እንዲሁም በ «ኒውዮርክ የጥናትና የፍተሻ ተቋም” ዘገባ መሰረት ክርስቶስ ፔይንን ያናገረው መሆኑ የተጠቀስ ሲሆን ክርስቶስ ከፔይን በአንድ ደረጃ በመውረድ በመናፍስቱ ዓለም ስድስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አትቶአል:) EWAmh 66.3

    የውሸት ሁሉ አባት የሆነው እርሱ---መላእክቱን ተጠቅሞ ሐዋርያቱ እንደሚናገሩ በማስመሰል እነዚያን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተጻፉ መልእክቶች እርስ በርሳቸው እንደሚጋጩ አድርጎ በማቅረብ ዓለምን የማሳወርና የማታለል ሥራ ይሠራል፡፡ እነዚህ ሐሰተኛ መላእክት ሐዋርያት እራሳቸው ያስተማሯቸውን ትምህርቶች የተሳሳቱ ናቸው ብለው በይፋ እንዲናገሩ ያደርጓቸዋል፡፡ ሰይጣን የታመኑት ክርስቲያኖች በመጣሉና መላው ዓለም በእግዚአብሔር ቃል ላይ ጥርጣሬ እንዲኖረው በማድረጉ ደስ ይሰኛል:፡፡ ያ የተቀደስ መጽሐፍ የእርሱን አካሄድ በቀጥታ የሚያከሽፍና እቅዱን የሚያኮላሽ በመሆኑ የመልእክቱን መለኮታዊ ምንጭነት ወደ መጠራጠር ይመራቸዋል:፡፡ hዚያም ከሃዲው ቶማስ ፔይን በሞተጊዜ በመላእክት ታጅቦ ወደ ሰማይ እንደተወሰደና ቀድሞ በምድር ይጠላቸው ከነበሩ ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ዓለምን በማስተማሩ ሥራ እንደተጠመደ ይናገራል፡፡ EWAmh 67.1

    ሰይጣን እያንዳንዱ ወኪሉ የሚሠራውን ሥራ ሁሉም ተንኮለኛ፣ አጭበርባሪና አታላይ መሆናቸው ለአንዳንዶቹ የሐዋርያትን ገጸ ባህሪ ወስደው እንዲሠሩና እንደ እነርሱ እንዲናገሩ መመሪያ ሲሰጥ ሌሎቹ ደግሞ እግዚአብሔርን ተራግመው የሞቱ---አሁን ግን በእጅጉ ኃይማኖተኞች የሚመስሉ ከሃዲያንንና ርጉም ሰ ዎችን ገጸ ባህሪ እንዲወስዱ ያደርጋል፡፡ በጣም ቅዱሳን በሆኑ ሐዋርያትና በክፉው አረመኔ መሃል አንዳችም ልዩነት ባለመቀመጡ ሁለቱም የቀ ረቡት ተመሳሳይ ነገር እንደሚያስተምሩ ሆነው ነው፡፡ ሰይጣን ያለመው ብቻ ይሳካለት እንጂ ከሁለቱ የትኛውም እንደሚናገር አድርጎ ቢያቀርብ ለእርሱ ለውጥ የለውም፡፡ ፔይን በህይወት በነበረበት ጊዜ በሥራው እገዛ በማድረግ ሰይጣን ከእርሱ ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ነበረው፡፡ ተግባሩን በሚገባ የተወጣውና እርሱን በታማኝነት ያገለገለው ፔይን ይጠቀማቸው የነበሩትን ቃላትና የእጅ ጽሑፉን ማወቀ ለሰይጣን በእጅጉ ቀላል ነበር አብዛኛዎቹ የፔይን ጽሑፎች ሰይጣን በመላእክቱ አማካኝነት በቀጥታ እየነገረው የጻፋቸው እንደመሆናቸው በህይወቱ ታማኝ የሰይጣን አገልጋይ ከነበረው ከቶማስ ፔይን እንደ ወጡ አድርጎ ማስመሰል ለእርሱ ቀላል ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ሰይጣን ስኬት ያገኘበት ከፍ ያለው የሥራው ውጤት ነው፡፡ የእነዚህ ሉ በህይወት የሌሉ ሐዋርያት፣ ቅዱሳንና ክፉ ሰዎች አስመሳይ አስተምህሮዎች ቀጥተኛ ምንጭ ሰይጣን ነው፡፡ ይመድባል፡፡ ያስደስተዋል፡፡ EWAmh 67.2

    እግዚአብሔርን በእጅጉ ይጠላ የነበረና ሰይጣን አብልጦ ይወደው የነበ ረ ሰው አሁን ከቅዱሳን ሐዋርያትና መላእክት ጋር በክብር እንደሚገኝ ማውራቱ ብቻውን የሁሉንም አእምሮ ጋርዶ የያዘውን የሰይጣንን የሐሰት መጋረጃ በመግለጥ ጽልመት የወረሰውን የማታለያ ሥራን ለማጋለጥ በቂ ሊሆን ይገባል፡፡ በእግዚአብሔርም ሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ አመናችሁ ወይም አላመናችሁ ብቻ ደስ እንደምትሰኙ ሆናችሁ ኑሩ---ሰማይ ቤታችሁ ነው በማለት አዛኝ መስሎ ለዓለምና እምነት የለሽ ለሆነው ሕዝብ ይናገራል፡፡ ቶማስ ፔይን ያለው በሰማይ ከሆነና በዚያ እየከበረ ከሆነ ሁሉም ሰው በዚያ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ የስህተት ትምህርት ፈቃደኞች ከሆኑ ሁሉም በቀላሉ ሊያዩት የሚችሉት ነው፡፡ ሰይጣን ከውድቀቱ አንስቶ ሊያደርግ ሲሞክር የነበረውን ነገር እነሆ አሁን እንደነ ቶማስ ፔይን ባሉ ሰዎች ኣማካኝነት እያደረገው ይገኛል፡፡ እርሱ በኃይሉና በአስደናቂ የሐሰት ተአምራቶቹ አማካኝነት የክርስቲያንን ተስፋ መሰረት እየገረሰሰና ወደ ሰማይ በሚወስደው ጠባቡ መንገድ ላይ የምታበራውን ጸሐይ እያጨለመ ይገኛል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት የተጻፈ አምላካዊ ቃል ሳይሆን ነገር ግን ከታሪክ መጽሐፍነት የዘለለ አይደለም እያለ ዓለም እንዲያምነው እያደረገ በጎን በኩል ደግሞመንፈሳዊ መገለጥ! የቃሉን ቦታ እንዲወስድ እያደረገ ይገኛል፡፡ EWAmh 67.3

    መንፈሳዊ መገለጥ ሙሉ ለሙሉ የእርሱ ታማኝ መሣሪያና በቁጥጥሩ ስር የሚገኝ እንደመሆኑ ዓለምን በፈቀደው መንገድ ያሳምንበታል፡፡ እርሱና ተከታዮቹ የሚዳኙበትን ይህን መጽሐፍ ቀደም ብሎ እንደተደረገው እንዲቀመጥ በሚፈልግበት ጥላ ባጠላበት ስፍራ ላይ ያኖረዋል፡፡ ሰይጣን የዓለም አዳኝ የሆነውን አምላክ ከማንኛውም ተራ ሰው የበለጠ አድርጎ አያስቀምጠውም:፡፡ እነዚያ የየሱስን መቃብር ይጠብቁ የነበሩት ሮማውያን የኃይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎች የሐሰት ወሬ እንዲነዙ አፋቸውን እንደለጎሟቸው ሁሉ እነዚህም ምስኪንና የተታለሉ የማስመሰል መንፈሳዊ መገለጥ ተከታዮች የአዳኙን ውልደት፣ ሞትና ትንሳዔ ተአምራዊ አይደለም ሲሉ ይናገራሉ፡፡ የሱስ እንዳይታይ ከበስተኋቸው ከሸፈኑት በኋላ የዓለምን ትኩረት ወደራሳቸውና ወደሚሠሯቸው የሐሰት ተአምራቶችና አስደናቂ ነገሮች በመሳብ ከክርስቶስ ሥራዎች እጅግ ልቀው መሄዳቸውን በአደባባይ ይናገራሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ዓለም በወጥመዳቸው ውስጥ በመግባት ደኅንነትና እርጋታ የሞላው ስሜት ውስጥ እንደገባ አድርጎ የሚያስብ ሲሆን ይህ አስፈሪ ማታለያ የመጨረሻዎቹ ሰባት መቅሰፍቶች እስከሚወርዱ ድረስ ሊደ ረስበት አይችልም፡፡ መላው ዓለም በወጥመዱ ተይዞና ሰይጣን ያወጣው ዕ ቅድ በጥሩ ሁኔታ ሰምሮ ሲመለከት ይስቃል፡፡ EWAmh 68.1

    5. በመልእክቴ በግርማ የተሞላ የደመና ብርሃን አብን ስለ ሸፈነው መታየት አይችልም ነበር በማለት ጠቅሼ ነበር፡፡ እንዲሁም አብ ከዙፋኑ ላይ ሲነሳ አየሁት ብዬ ጽፌአለሁ፡፡ አብ በብርሃንና በክብር በመሸፈኑ የእርሱ አካል መታየት አይችልም ነበር፡፡ ደግሞም ይህ ብርሃንና ክብር ይወጣ የነበረው ከእርሱ አካል እንደነበር አውቅ ነበር፡፡ ይህ የብርሃን አካልና ክብር hዙፋኑ ላይ ሲነሳ ባየሁ ጊዜ አብ መነቃነቁን በማስተዋል---አብ ሲነሳ አየሁት ብዬ ጻፍኩ፡፡ የእርሱ ክብር ከዚያ ቀደም ፈጽሞ አይቼ የማላውቀው ዓይነት ነበር: ማንም እርሱን አይቶ በህይወት መኖር ባይችልም ነገር ግን እርሱን የሸፈነው ብርሃናማው አካልና ክብር መታየት የሚችል ነው፡፡ EWAmh 68.2

    እንዲሁም «ሰይጣን በእግዚአብሔር በዙፋን ላይ ተቀምጦ የእግዚአብሔርን ሥራ እየሠራ መስሎ ታየ» በሚል ጠቅሼ የነበ ረ ሲሆን ከዚሁ ገጽ ላይ ሌላ ዐረፍተነገር ማቅረብ እወዳለሁ፡፡ «አሁንም በዙፋኑ ፊት አጎንብሰው የነበሩትን ቡድኖች ለመመልከት ዘወር አልኩ” በዚህን ወቅት ይህ እየጸለየ የነበረ ቡድን በምድር ላይ ሙት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ለእኔ የተስተዋለኝ በዙፋኑ ፊት እንደተደፉ ሆኖ ነበር: እነዚህ ሰዎች በአዲሲቱ የሩሳሌም እንዳሉ አድርገው የማሰባቸው ነገር ፈጽሞ በአእምሮዬ አልነበረም ወይም ሰይጣን በአዲሲቱ የሩሳሌም ነው ብዬ ማመኔን ማንኛውም ሟች ያስባል ብዬ አልገምትም፡፡ ደግሞስ ዮሐንስ ታላቁን ቀይ ዘንዶ በሰማይ አልተመለከተምን? ተመልክቶአል «hዚህም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ እነሆ ሰባት ራሶችና አስር ቀንዶች የነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት አክሊል የደፋ ታላቅ ቀይ ዘንዶ ታየ» (ራእ. 12:3)፡፡ እዚህ ላይ አንዳንዶች በጽሑፌ ያቀረቡኳቸው ፍቺዎች ላይ ለመሳለቅ መልካም አጋጣሚ ሊሆንላቸው ይችላል፡፡ EWAmh 69.1

    በወርሃ ጥር 1850 ዓ.ም. ላይ የተሰጠው መልእክት በአብዛኛው ገጣሚነቱ ለዚያ ጊዜ ነው፡፡ የወቅታዊው እውነት ወዳጆች ከዚያን ጊዜ አንስቶ ባላቸው ነገር ሁሉ ለወቅታዊው እውነት ግስጋሴ የበኩላቸውን ለማድረግ የሚያስችሏቸውን ዕድሎች በአንክሮ ሲከታተሉ ኖረዋል፡፡ አንዳንዶች ገንዘቡን የሚቀበሏቸው ሰዎች ላይ ጉዳት ሊያደረስ በሚችል መልኩ በጣም በነጻነት እየመዘዙ ይሰጧቸው ነበር፡፡ ከእጥረት ይልቅ የጌታን ገንዘብ ግዴለሽና ልቅነት ከሚስተዋልበት አጠቃቀም ጋር ቁርኝት ያለውን አሠራር ለሁለት ዓመታት ያህል ተመልክቼ ነበር EWAmh 69.2

    በመቀጠል የቀረበው ሰኔ 2/1853 ዓ.ም. ላይ በጃክሰን ሚቺጋን የተሰጠ ሲሆን መልእክቱ በአብዛኛው የሚያወሳው በቦታው ስለነበሩ ወንድሞች ነው፡፡ «ንብረቶቻቸውን መስዋዕት አድርገው ማቅረብ የጀመሩ ወንድሞች ተጨባጩን ዓላማ ባላገናዘበ ልቅ በሆነ መንገድ ገንዘባቸውን አትረፍርፈው ይሰጡ ነበር መምህራን በቤተክርስቲያን የሚስተዋለውን ይህን ስህተት በማረምና መልካም ተጽእኖ በማሳረፍ ሊቆሙ እንደሚገባ ተመልክቻለሁ፡፡ አነስተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ወዲያውኑ ላስፈላጊው ተግባር ስለሚውል የሚያስከትለው አሉታዊ ውጤት አልነበረም: አንዳንዶች ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የገንዘብ ስጦታዎች ከተቀበሉ በኋላ ሌሎች በጣም በነጻነትና በግዴለሽነት እንዳያባክኑት ማድረግ የሚያስችል ተገቢ ምክርና ማስጠንቀቂያ መስጠት እየቻሉ ነገር ግን ያን ማድረግ ባለመቻላቸው መጥፎ ምሳሌ ሆነዋል፡፡ EWAmh 69.3

    «7ንዘብ የሚያስፈለገው አንገብጋቢ ጉዳይ ይኑር አይኑር ሳያጣሩና ገንዘቡ ለየትኛው ሥራ እንደሚያስፈልግ ሳይጠይቁ የሰጡ ስህተት ሠርተዋል፡፡ በዚህም ገንዘብ የመስጠት ዕድሉ የነበራቸው አስጨናቂ መደናገር ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ አንድ ወንድም እጁ ላይ በነበረው ከመጠን ያለፈ ዕድል አብልጦ ተጎድቶ ነበር፡፡ እርሱ የምጣኔ ሐብት ሳይንስ አላጠናም ኑሮውም ገንዘብ በማባከን ላይ የተመሰረተነበር፡፡ ለሚያደርጋቸው ጉዞዎችና ትርፍ ለሌለው ነገር እዚህም እዚያም ያወጣ ነበር፡፡ ይህን ዓይነቱን ከቁጥጥር ነጻ የሆነ የገንዘብ አጠቃቀም ተጽእኖ በጌታ ገንዘብ ላይ ማዋል በመጀመር ለራሱ በልቡም ሆነ ለሌሎች እንዲህ ይላል ጌታ ዳግም ከመምጣቱ አስቀድሞ ገንዘቡ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችሉባቸው ብዙ መንገዶች አሉ::’ አንዳንዶች በእንዲህ ያለው ብክነታቸው በእጅጉ ተጎድተውና የተሳሳተ አመለካከት ይዘው ወደ እውነት መጥተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች እየተጠቀሙበት የነበረው ገንዘብ የጌታ እንደነበር አላገናዘቡም፤ ምን ያህል የከበረ ዋጋ እንዳለውም አልተሰማቸውም፡፡ የሦስተኛውን መልአክ መልእክት ገና ተቀብለው እንዲህ ያለው ምሳሌ የተተወላቸው ምስኪን ነፍሳት እራስን ስለመካድና ለክርስቶስ ሥቃይ ስለመቀበል በእጅጉ ሊማሩት የሚገባ ነገር ይኖራቸዋል:: ለራሳቸው ምቾትና ድሎት መኖራቸውን አቁመው የነፍሳት ዋጋ ዘወትር በአምሮአቸው ሊመላለስ ይገባል፡፡ በላያቸው የኃዘን ስሜት የሚሰማቸው ጉዞውን ተደላድለውና ያለ ምንም ችግር ለማድረግ የሚያስችል ከፍ ያለ ዝግጅት አይኖራቸውም:: አንዳችም ዓይነት ጥሪ ያልተቀበሉ አንዳንዶች በመስኩ እንዲበረታቱ ሲሆኑ ነገር ግን በእነዚህ ነገሮች ተጽእኖ ስር የወደቁ ሌሎች፧ እራሳቸውን በመካድ የጌታን ገንዘብ ያለ ብክነት መያዝ እንዳለባቸው አልተሰማቸውም ነበር፡፡ EWAmh 70.1

    ሥራውን ደግፎ ለመያዝ በማስቻሉ ረገድ ንብረትን መስዋዕት አድርጎ በማቅረቡ ዙሪያ የተሰነዘረውን የአመለካከቴን ክፍል ቀንጭበው በመውሰድ በስህተት ጥቅም ላይ ማዋላቸውን መመልከቴ ለእኔ ቀላል ፈተና አልነበረም፡፡ ቀደም ብሎ በቀረበው መልእክት ላይ የሚከተለው ይነበባል «የእግዚአብሔር ሥራ ከእግዚአብሔር መልእክት በሌላቸው ሰዎች ሲጓተትና ክብር ሲነፈገው ተመለከትኩ፡፡ እንደነዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች ወደ ማይመለከቷቸው ስፍራዎች ጉዞ በማድረግ ላባከነት እያንዳንዱ ብር በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂነት ይኖርባቸዋል፡፡” በተጨማሪ በዚሁ አንቀጽ መጨረሻ ላይ ይህን እናነባለን «በእጆቻቸው አገልግሎት ለመስጠትና ሥራውን ደግፈው ለመያዝ ብርታት የነበራቸውም እንዲሁ---በገንዘባቸው ተጠያቂ እንደነበሩት እነደነዚያ-እነዚህም በብርታታቸው ተጠያቂነት እንደነበረባቸው ተመልክቼአለሁ፡፡» EWAmh 70.2

    እዚህ ላይ ለየት ያለ ትኩረት መስጠት እፈልጋለሁ፡፡ «በሉቃ. 12:33 የምናነባቸው ቃላት ጽንሰ ሃሳብ በግልጽ አልቀረበም፡፡» «የመሸጥ ዓላማ መሥራትና እራሳቸውን መርዳተለሚችሉት ለመመጽወት ሳይሆን ነገር ግን እውነትን ለማሰራጨት ነው፡፡ መሥራት እየቻሉ እጆቻቸውን አጣጥፈው የተቀመጡትን መደገፍ ኃጢአት ነው፡፡ አንዳንዶች በእያንዳንዱ ጉባዔ ለመካፈል የጋለ ስሜት ቢኖራቸውም ነገር ግን ይህን የሚያደርጉት ለእግዚአብሔር ክብር ለመስጠት ሳይሆን ‘ለዳቦና ዓሣ’ ሲሉ ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ‘መልካም የሆነውን ሁሉ’ በእጆቻቸው ቢሠሩና ለቤተሰባቸው የሚያስፈልገውን ቢያሟሉ እንዲሁም የከበረውን ወቅታዊ መልእክት የሚደግፉበት ጥቂት ነገር ቢኖራቸው በእጅጉ የተሻለ ይሆናል፡፡ አንዳንዶች ገንዘቡን በጣም ልቅ በሆነ አያያዝ ለማባከን ወንድሞች ንብረቶቻቸውን በተቻ ኮለ መንፈስ እንዲሸጡ መገፋፋታቸውና ተጽእኖ ማሳደራቸው የሰይጣን ዕ ቅድ ነበር፡፡ በእንዲህ መልኩ ንብረቶቻቸው ኃላፊነት በጎደለውና በተቻኮለ አካሄድ የጠፈባቸው ነፍሳት ሊጎዱና ሊጠፉ ይችላሉ፡፡ አሁን እውነት ይበልጥ በስፋት እየተሰራጨሲሄድ የሥራ ማስኬጃ እጥረት ሊከሰት ይችላል፡፡ EWAmh 71.1

    የመንፈሳዊ በራሪ ጽሑፎችን ህትመት በገንዘባቸው ለመደገፍ የሚያስችል ብቻ ንብረት ወዳላቸው የሚመለከቱ የብዙዎችን ስህተት ጌታ አሳይቶኛል፡፡ ሁሉም የየራሳቸውን ድርሻ ሊያበረክቱ ይገባል፡፡ በእጆቻቸው አገልግሎት ለመስጠት ብርታት ያላቸውና ሥራውን ለመደገፍ የሚያስችል ገቢ ያላቸው በገንዘባቸው ከሚያገለግሉ ጋር እኩል ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ወቅታዊውን እውነት አምኖ መቀበሉን ይፋ ያደረገ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ በሥራው የየራሱን ድርሻ ለማበርከት የጋለ ፍላጎት ሊኖረው ይገባል፡፡ EWAmh 71.2

    ሐምሌ 1853 ዓ.ም. ላይ የእግዚአብሔር የሆነና የእርሱን ይሁንታ ያገኘ የህትመት ሥራ ወቅቱን ሳይጠብቅ አልፎ አልፎ መውጣቱ አግባብ አለመሆኑን ተመልክቼ ነበር፡፡ እኛ በምንኖርበት ዘመን ሳምንታዊ የህትመት ሥራ ድጋፍ ይጠይቃል፡፡ hዚህ ቀደም ብለው በነበሩት ጊዜያት ሪቪዩ ኤንድ ሔ ራልድ ይታተም የነበረው መደበኛ ወቅቱን ባልጠበቀ መልኩ ሲሆን አሁን ግን በየአሥራ አምስት ቀኑ መደበኛ ዕትም ሆኖ መውጣት ጀምሯል፡፡ እንዲሁም በዚህ ዘመን እየጨመረ ያለውን ስህተት ማሳያ የሚሆኑ የሌሎች በዛ ያሉ ተጨማሪ በራሪ ጽሑፎች ህትመት አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ሥራው በገንዘብ ምክንያት ተጓቷል፡፡ እውነት ወደፊት መሄድ እንዳለበትና በጣም ልንፈራ እንደማይገባን ተመልክቻለሁ:: የተናቀ ነገር ግን ለበራሪ ጽሑፎቹ ዋጋ የሚሰጥ አንድ ሰው በመልእክቶቹ ተጠቃሚ መሆን ይችላል፡፡ ሰይጣን የሚገለጽባቸው መንገዶች እየጨመሩ በመሆናቸው የመጨረሻው ቀን ምልክቶች ግልጽ ሆነው መቅረብ እንዳለባቸው ተመልክቻለሁ፡፡ የሰይጣንና ወኪሎቹ ህትመቶች እየጨመሩና ኃይላቸው እየጎለበተየሚገኝ በመሆኑ እውነትን ለሌሎች ለማቅረብ የምናደርገውን እንቅስቃሴ በፍጥነት ልናከናውን ይገባል፡፡ EWAmh 72.1

    አሁን አንድ ጊዜ ታትሞ የሚወጣው እውነት-እውነት በመሆኑ እስከ መጨረሻዎቹ ቀናት ጸንቶ ይኖራል፡፡ ጽሑፉ የተላበሰውን ንጽሕና እንዲያንጸባርቅ መፍቀድ እንጂ ስለ ራሱ ለማሳመን አያሌ ቃላት ሊደረደሩ አይገባም፡፡ እውነት ከሐሰት ጋር ሳይቀላቀል ሲቀር ቀጥተኛና ግልጽ ሆኖ እራሱን ለመከላከል በድፍረት ይቆማል፡፡ እውነት ተጣሞ ሲቀርብ ያን የተጠማዘዘ ማንነቱን ለመግለጽ አያሌ ቃላት ይሻል፡፡ ሰዎች በአንዳንድ ስፍራ ዎች የተቀበሏቸው ብርሃናት በሙሉ ምንጫቸው በራሪ ጽሑፎች መሆናቸውን ተመልክቻለሁ፡፡ እነዚህ ነፍሳት በዚህ መንገድ እውነትን ከተቀበሉ በኋላ የተቀበሏቸውን እውነቶች ለሌሎች ያጋራሉ፡፡ ዛሬ ብዙ አማኞች ያሉባቸው አካባቢዎች የእነዚህ ድምፅ ዐልባ መልእክቶች ውጤት ናቸው፡፡ የእነርሱ ብቸኛ ሰባኪ ጽሑፍ ነበር፡፡ የእውነት መስረት ወደፊት የሚያደርገው ግስጋሴ ሊገታ አይገባም፡፡ EWAmh 72.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents