Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    47—ጳውሎስ የሩሳሌምን መጎብኘቱ

    ጳውሎስ ከተለወጠ በኋላ የሩሳሌምን በመጎብኘት በዚያ የሱስን ሰበከ አስደናቂ ጸጋውንም በመመስከር የእርሱ ተአምራዊ በሆነ መንገድ ጌታን መቀበል ቀሳውስቱንና ገዢዎችን ምን ያህል እንዳበሳጨና ሊገድሉት እንደፈለጉ ተናገረ፡፡ ጳውሎስ እየጸለየ ሳለ የሱስ በራእይ ተገልጦ «አሁኑኑ ፈጥነህ ከየሩሳሌም ውጣ ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉምና” አለው፡፡ ጳውሎስ ሲመልስ «ጌታ ሆይ በአንተየሚያምኑትን ሰዎች ለማሰርና ለመደብደብ በየምኩራቡ እዞር እንደነበር እነዚህ ሰዎች ያውቃሉ፤ ደግሞም የአንተን ሰማእት እስጢፋኖስን ደም በሚያፈሱበት ጊዜ በድርጊታቸው ተስማምቼ በቦታው ቆሜ የገዳዮቹን ልብስ እጠብቅ ነበር፡፡” ጳውሎስ በእርሱ ላይ የታየው ይህ ጌታን የመቀበል ታላቅ ለውጥ እውን መሆን የቻለው በእግዚአብሔር ኃይል ብቻ ስለሆነ የየሩሳሌም ሐዝብ ይህን ሊቃወም አይችልም ብሎ አስቦ ነበር፡፡ ሆኖም ከጌታ የተሰጠው ምላሽ ከበፊቱ ይልቅ ቁርጥ ያለ ነበር «ሂድ፤ በሩቅ ወዳሉት አሕዛብ እልክሃለሁና»፡፡ EWAmh 146.1

    ጳውሎስ የሩሳሌም ባልነበረባቸው ጊዜያቶች ው ስጥ ስለ ተሞክሮውና ስለ ብርቱ ምስክርነቱ አያሌ ደብዳቤዎችን ለተለያዩ ቦታዎች ጽፎአል፡፡ ሆኖም አንዳንዶች የእነዚህን ደብዳቤዎች ተጽእኖ ለማጥፋት ሙከራ አድርገው ነበር፡፡ ሰዎቹ ደብዳቤዎቹ ክብደት ያላቸውና ብርቱ መሆናቸውን ለመቀበል ቢገደዱም ነገር ግን እርሱ በአካላዊ አቀራረቡ ደካማና ንግግሩም የሚናቅ እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ EWAmh 146.2

    ነገር ግን ተጨባጩ እውነታ ጳውሎስ ከፍ ያለ ዕውቀት ባለቤት ከመሆኑ ባሻገር የነበረው ጥበብና ባህ አድማጮቹን የሚስደምም ነበር የተማሩ ሰዎች በጳውሎስ ዕውቀት በመርካታቸው ብዙዎቹ በየሱስ አምነዋል፡፡ ጳውሎስ በነገሥታት ፊትና በታላላቅ ጉባዔዎች ላይ ሲቆም በአንደበተርቱዕነቱ ብዙዎችን ሲያስደምም ቀሳውስቱንና ሽማግሌዎችን ግን ያበሳጭ ነበር ጳውሎስ ጠለቅ ባለ የማሰብ ኃይልና ከፍ ባለ አስተምህሮ ሕዝቡን ይዞ በመጓዝ ጥልቅና የከበረውን የእግዚአብሔር ጸጋ በአስደናቂው የክርስቶስ ፍቅር ያቀርብላቸው ነበር፡፡ ሐዋርያው ቀላልና ውስብስብነት የሌለውን አቀራ ረብ ተከትሎ ዝቅ ወዳለው የሕብረተስብ ክፍል ማስተዋል በመውረድ ብርቱ ተሞክሮውን ያካፍል ነበር፡፡ ጳውሎስ በዚህ ዘዴው ሰዎች የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን ኃይለኛ ቅንአት እንዲያድርባቸው አድርጎአል EWAmh 146.3

    ጌታ አሁንም ለጳውሎስ በመገለጥ እስከ የሩሳሌም በመሄድ በዚያ ለስሙ አስራትና ሥቃይ እንደሚቀበል ገለጸለት፡፡ ምንም እንኳ እርሱ ረዘም ላሉ ጊዜያት እስረኛ የነበረ ቢሆንም ጌታ ግን በፊቱ የተለየ አገልግሎት ዘረጋ፡፡ የእርሱ እሥራቶች የክርስቶትን ማንነት ዕውቀት የሚያሰራጩና ክብርን ለእግዚአብሔር የሚሰጡ ነበሩ፡፡ ጳውሎሰ ከከተማ ወደ ከተማ እየተላከና በዚያ እየተዘዋወረ ስለ የሱስ ይደርስበት የነበረው ፈተና፣ ይሰጥ የነበረው ምስክርነት እንዲሁም የመለወጡን አስደናቂ መልእክት በነገሥታትና ገዢ ዎች ፊት ቆመሞ ሲናገር አፋቸውን ያስይዛቸው ነበር፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ በጌታ አምነዋል በስሙም ሐሴት አድርገዋል፡፡ ጳውሎስ ባደረገው የባሕር ላይ ጉዞ የእግዚአብሔር ልዩ ዓላማ ክንውን ማግኘቱን ተመልክቻ ለሁ፡፡ የመርከቡ ሠራተኞች በጳውሎስ አማካኝነት ለእግዚአብሔር ኃይል ምስክር መሆናቸው፣ ኢአማንያኑም እንዲሁ የየሱስን ስም መስማታቸውና ብዙዎች በእርሱ ትምህርትና ባደረጋቸው ተአምራቶች መለወጣቸው አበይት ስኬት ነበር፡፡ ጳውሎስ ጥልቅ በሆነ የማሰብ ኃይል የሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆኑ በልዩ ቅንአትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከራሱ ተሞክሮ ጋር በማያያዝ ባቀረበው መልእክት ነገሥታትና ገዢዎች ተደምመዋል፡፡ በጳውሎስ ንግግር በእጅጉ በመገረም «ክርስቲያን ልታደርገኝ ትንሽ ቀረህ” ያሉም ነበሩ፡፡ ሰዎች እውነትን እንደሰሙና ልባቸው ለስላሳ በሆነበት ሰዓት ዕድሉን በማዘግየት ወደ ውሳኔ ሳይመጡ ሲቀሩ ሰይጣን አጋጣሚውን ተጠቅሞ ልባቸው ያደነድናል፡፡ በዚህም እስከ መጨረሻው ጠፍተው ይቀራሉ፡፡ EWAmh 147.1

    ሰይጣን በመጀመሪያ የአይሁድን ዐይኖች ያሳውር ነበር በመቀጠል የሱስን እንደ አዳኛቸው እንዳይቀበሉ ልባቸውን ይደፍንና ወደ ቅናት መንገድ ይመራቸዋል: ከዚህ በኋላ በኃያል ሥራዎቹ ላይ በመመቅኘት ህይወቱን ለመቅጠፍ እንዲመኙ ያደርጋቸው እንደ ነበር ተመልክቻለሁ:: ሰይጣን ከየሱስ ተከታዮች በአንደኛው ውስጥ በመግባት እንዲክደውና ይህን የህይወት ጌታ ይሰቅሉት ዘንድ በእጃቸው አልፎ እንዲሰጣቸው መራው፡፡ EWAmh 147.2

    የሱስ ከመቃብር ከተነሳ በኋላ አይሁድ የእርሱን ትንሳኤ ለመደበቅ ሲሉ የሮማውን ወታደር በገንዘብ ገዝተው ሐሰት እንዲነዛ በማድረግ በኃጢአት ላይ ኃጢአት ጨመሩ፡፡ ሆኖም በየሱስ ትንሳኤ ወቅት ከመቃብር የተነሱ አያሌ ሰዎች ምስክርነት የእርሱን ትንሳኤ እርግጠኝነት በእጥፍ አባዙት፡፡ የሱስ ከትንሳኤው በኋላ ለደቀ መዛሙርቱና ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ሰዎች በአንድ ጊዜ የታየ ሲሆን እነዚህ ሁሉ ደግሞ የየሱስን ትንሳኤ ለሌሎች አብስረዋል፡፡ EWAmh 148.1

    ሰይጣን አይሁድ የእግዚአብሔርን ልጅ ላለመቀበል እንዲወስኑና እጃቸውን በደሙ እንዲነክሩ በማድረግ በእግዚአብሔር ላይ እንዲያምጹ አነሳስቶአቸው ነበር የሱስ የእግዚብሔር ልጅና የዓለም አዳኝ ለመሆኑ የትኛውም ዓይነት ብርቱ መረጃ ቢቀርብላቸውም እነርሱ ግን ገደሉት፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ሌላ የሚቀበሉት ተጨማሪ መረጃ አይኖርም:: ሰይጣን ከወደቀ በኋላ እንዳደረገው እነርሱም ብቸኛ ተስፋና መጽናኛቸው የሆነውን የእግዚአብሔርን ልጅ ለማሸነፍ እየሞከሩ ነበር: በዚህ መልኩ የክርስቶስን ደቀ መዛሙርት በማሳደድና በመግደል የአመጻ ተግባራቸውን ገፉበት፡፡ የሰቀሉትን የየሱስን ስም የመስማትን ያህል ለጆሮአቸው የሚሰቀጥጣቸው አንዳችም ነገር ባለመኖሩ ስለ እርሱ የሚቀርብ ምንም ዓይነት መረጃ ላለመስማት ቁርጥ ሃሳብ አድርገው ነበር፡፡ የሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆኑ በእስጢፋኖስ በኩል ድንቅ መረጃ ቢቀርብላቸውም ነገር ግን ምናልባትም ልባቸውን ሊነካው ስለሚችል ላለመስማት ጆሮዎቻቸውን ደፈኑ፡፡ ሰይጣን የየሱስን ገዳዮች በእቅፉ ውስጥ አጥብቆ ይዟቸው ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ለእርሱ ክፉ ሥራ ተባባሪ ለመሆን ፈቃዳቸውን በማሳየት ሰይጣን በእነርሱ አማካኝነት የክርስቶስ አማኞች ላይ ችግር የመፍጠርና እነርሱን የማመስ ሥራ ይሠራ ነበር፡፡ ሰይጣን አይሁድን ተጠቅሞ አሕዛብ በየሱስና በተከታዮቹ ላይ እንዲነሳሱ ኣድርጎአል:: ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ ያዩትንና የሰሙትን በመመስከር በመጨረሻም በታማኝነት ምስክርነታቸውን በደማቸው እንዲያትሙበሥራቸው የሚያበረታቷቸውን መላእክት እግዚአብሔር ላከላቸው፡፡ EWAmh 148.2

    አይሁዳውያኑ በወጥመዱ ወስጥ በመውደቃቸው ሰይጣን ተደስቶ ነበር አይሁድ ከየሱስ ሞት በኋላ ያንኑ የቀድሞውን ከንቱ መስዋዕትና ሥርዓት መፈጸሙን ገፍተውበት ነበር ነገር ግን የሱስ በመስቀል ላይ «ተፈጸመ” ብሎ በጮኸ ጊዜ የቤተመቅደሱ መጋረጃ ከላይ ወደታች ለሁለት መቀደዱ እግዚአብሔር ከዚህ በኋላ ሰዎችን የሚገናኘው በቤተመቅደስ በካኅኑ አማካኝነት በሚቀርበው መስዋዕት አለመሆኑን፤ በተጨማሪም በአይሁድና ጳውሱስ የሩሳሴምን መጎብኘቱ አይሁድ ባልኑ ዝርያዎች መሃል የነበረው ግድግ መፍረሱን ለማሳየት ነበር፡፡ የሱስ እራሱን መስዋዕት አድርጎ ያቀረበው ለሁለቱም ዝርያዎች በመሆኑ! ለመዳን ብቸኛ መስዋዕት ሆኖ የቀረበውን ይህን የዓለም አዳኝ ሁለቱም ማመናቸው የግድ ይሆናል፡፡ EWAmh 148.3

    የሱስ በተሰቀለ ጊዜ ወታደሩ ጎኑን በጦር ሲወጋው ሁለት የተለያዩ ነገሮች ከአካሉ ወጥተው ነበር---ውሃ እና ደም:: ደሙ በእርሱ ስም የሚያምኑትን ኃጢአት የሚያጥብ ሲሆን ውሃው ደግሞ ለአማኙ ህይወት የሚሰጠውን ከየሱስ የሚገኘውን ህያው ውሃ የሚወክል ነበር፨EWAmh 149.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents