Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    68—የእግዚአብሔር ህዝቦች መዳን

    እግዚአብሔር ህዝቦቹን ለማዳን የመረጠው ጊዜ አኩለ ሌሊት ነው፡፡ ኃጥአን በቅዱሳኑ ላይ እየተሳለቁባቸው እያለ ሳይታሰብ ጸሐይ ትፈነጥቅና በሙሉ ኃይሏ ታበራለች፡፡: ጨረቃም በነበረችበት ላይ መታየቷን ትቀጥላለች: ቅዱሳን ይህን የመዳናቸውን ምልክት በታላቅ ደስታ ሲመለከቱ ኃጥአን ግን ትዕይንቱን በመደነቅ ያዩ ነበር፡፡ ምልክቶችና :ስደናቂ ነገሮች በፍጥነት ተከታተሉ አሁን ሁለም ነገር ከተፈጥሮአዊ ሂደቱ ውጪ ያለ ይመስላል፡፡ ወንዞች መፍሰሳቸውን አቆሙ፡፡ በጽልመት የተሞሉ ከባባድ ደመናዎች መጥተው እርስ በርሳቸው ተጋ: በዚህን ወቅት በተረጋጋ ክብር ውስጥ መሆኑ በግልጽ የሚታይበት አንድ ብቻ ስፍራ የነበረ ሲሆን ይኸውም እንደ ብዙ ውሖች ይፈስ የነበረውና ሰማይንና ምድርን ያናውጥ የነበረው የእግዚአብሔር ድምጽ ነበር ታላቅ የመሬት መናወጥ ሆነ: መቃብሮች ተከፈቱና የሦስተኛውን መልአክ መልእክት በእምነት ተቀብለው ሰንበትን የጠበቁ፤ እግዚአብሔር ሐጉን ከጠበቁት ጋር የሚገባውን የሰላም ኪዳን ለመስማት ካንቀላፉበት የትቢያ መኝታ በመንቃት ከበሩ፡፡ EWAmh 211.2

    በነውጥ ውስጥ የነበረው ሰማይ አየተከፈተየሚዘጋ ይመስላል ተራሮች በነፋስ እንደተመታ ሸንበቆ በመወዛወዝ ዐለቶችን ይተፉ ነበር፡፡ ባህሩ እሳት ላይ እንደተጣደ ብረት ድስት በመንተክተክ ዐለቶችን አያፈናጠረ ወደ ደረቁ ምድር ይወረውር ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለህዝቡ የገባውን ዘላለማዊ ኪዳን በመጠበቅ የየሱስን መምጫ ቀንና ሰዓት ሲናገር ሳለ አንድ ዐረፍተነገር ከተናገረ በኋላ ቃላቶቹ ወደ ምድር አየተንከባለሉ እስኪወርዱ ባለው ጊዜ ውስጥ ጸጥታ ይሰፍን ነበር፡፡ ቅዱሳኑ ዐይኖቻቸውን ከፍ አድርገው በእስራኤል አምላክ ላይ በመትከል ከያህዌ አንደበት ይወጡ የነበሩት ቃላት እንደ ብርቱ የነጎድጓድ ድምጽ ወደ ምድር እየተንከባለሉ ሲወርዱ ያደምጡ ነበር ትዕይንቱ በታላቅ በክብር የተሞላ ነበር፡፡ በእያንዳንዱ ዐረፍተነገር መጨረሻ ላይ ቅዱሳኑ «ሐሌሉያ! ክብር ለእርሱ ይሁን!» እያሉ ይጮኻሉ፡፡ የፊታቸው ገጽታ ሙሴ ከሲና ተራራ ሲወርድ በታየበት ዓይነት የእግዚአብሔር ክብር አብርቶ ነበር:: በላያቸው ከሚስተዋለው ክብር የተነሳ ኃጥአን ሊመለከቷቸው አልተቻላቸውም ነበር፡፡ ሰንበትን ቅዱስ አድርገው በመጠበቅ ለእግዚአብሔር ክብር ሰጥተው የነበሩት ማብቂያ የሌለው በረከት በመቀበል፤ በአውሬውና በምስሉ ላይ ኃያል ድል የመቀዳጀታቸው ብርቱ ጩኸት ተሰማ:: EWAmh 211.3

    ከዚያም ምድሪቱ የምታርፍበት የኢዮቤሊዩ ዘመን ተጀመረ፡፡ በዚህን ወቅት በቅድስና የኖረው ባሪያ ታስሮበት የነበረውን ሰንሰለት በድል አድራጊነት ሲበጣጥስ፤ ክፉዎች የእግዚአብሔርን ድምጽ የማያውቁ እንደመሆናቸው አሳዳሪው ግራ ተጋብቶና የሚያደርገው ጠፍቶት ነበር EWAmh 212.1

    ወዲያውኑ ታላቅና ነጭ ደመና የታየ ሲሆን በላዩ ላይ የሰው ልጅ ተቀምጦበት ነበር፡፡ ደመናው ከሩቅ ብቅ ሲል አነስተኛ መስሎ ይታይ ነበር፡፡ መልአኩ ግን የሰው ልጅ ምልክት መሆኑን ተናገረ:፡፡ ደመናው ወደ ምድር እየቀረበ ሲመጣ በድል አድራጊነት እየገሰገሰ ያለውን አስገራሚው የየሱስ ክብር መመልከት ችለን ነበር: በአናቶቻቸው ላይ አብረቅራቂ ዘውዶችን የደፉ የክብር ተከታይ ቅዱሳን መላእት በጉዞው አጅበውት አድርገውለት ነበር፡፡ የትዕይንቱን በክብር መሞላት አንዳችም ቋንቋ ሊገልጸው አይችልም ነበር፡፡ ህያውና በንሱሣዊ ክብር የተሞላው ደመና አሁንም እየቀረበ ሲመጣ ተወዳጁን የየሱስ ማንነት በግልጽ መመልከት ችለን ነበር የሱስ በዚህን ወቅት በዐናቱ ላይ የእሾህ አክሊል ሳይሆን ነገር ግን የክብር ዘውድ ደፍቶ ነበር፡፡ በልብሱና በጭኑ ላይ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ» የሚል ስም ተጽፎአል፡፡ የፊቱ ገጽታ እንደ ቀትር ጸሐይ የሚያበራ፤ ዐይኖቹ ደግሞ እንደ እሣት ነበልባል ይመስሉ ነበር: እግሮቹ በእቶን እሳት የጋለ ብዙ ወራጅ ውሃ ድምፅ ነበር፡፡ ምድር በፊቱ ተንቀጠቀጠች፡፡ ሰማይ እንደ ጥቅል መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፤ ተራሮችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወገዱ፡፡ «ከዚህ በኋላ የምድር ነገሥታትና ገዢዎች፣ የጦር መኮንኖች፣ ሐብታሞች፣ ብርቱዎች፣ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራራዎች ዐለቶች ውስጥ ተሸሸጉ፤ ተራሮቹንና ዐለቶቹንም በላያችን ውደቁ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቁጣ ሰውሩን፤ ታላቁ የቁጣቸው ቀን መጥቶኣልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሏቸው፡፡ ከጥቂት ጊዜያቶች ቀደም ብሎ የእግዚአብሔርን ልጆች ከምድ ረ ገጽ ሊያጠፏቸው የነበሩ፤ አሁን ግን በእነዚህ ህዝቦች ላይ ላረፈው አምላካዊ ክብር ምስክሮች ሆነዋል በዚህ ሁሉ አስፈሪ ሁናቴ መሃል በደስታ የተሞሉት ቅዱሳን «እነሆ አምላካችን ይህ ነው፤ በእርሱ ታመንን እርሱም ዳነን›› ይላሉ፡፡ EWAmh 212.2

    በመቃብር ያንቀላፉትን ቅዱሳን የሚጣራ የእግዚአብሔር ልጅ ድምጽ ሲሰማ ምድር ትርዳለች:፡፡ ቅዱሳኑ በክብር የተሞላውን የማይሞት አካል ለብሰው «ድል በሞት ላይ! ሞት ሆይ ድል መንሳትህ የት አለ? ሞት ሆይ መንደፊያህስ የት አለ?” እያሉ በመጮኽ ለጥሪው ምላሽ ሰጡ፡፡ ከዚያም በህይወት ያሉትና ከመቃብር የተነሱት ቅዱሳን በህብረት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የድል ድምጽ አሰሙ እነዚያ የህመምና የሞት ተምሳሌት የነበ ረውን አካል ይዘው ወደ መቃብር የወረዱ ቅዱሳን አሁን ግን የማይሞተውን፣ ጤነኛና ብርቱ አካል ይዘው ተነሱ፡፡ በህይወት ያለት ቅዱሳን በዐይን ቅጽበት በመለወጥ ከመቃብር ከተነሱት ጋር ጌታን ለመቀበል በአየር ተነጠቁ፡፡: እንዴት ያለ በአምላካዊ ክብር የተሞላ ትዕይንት ነው! ሞት የለያያቸው ጓደኛሞች ከእንግዲህ ዳግመኛ ላይለያዩ ሆነው ተገናኙ:: የደመናው ሠረገላ በሁሉም አቅጣጫ ክንፎችከበታቹ ደግሞ ህያው ተሸከርካሪዎች ነበሩት ሠረገላው ወደ ላይ ሲወጣ ተሽከርካሪዎቹና ክንፎቹ «ቅዱስ» እያሉ ሲጮኹ፧ በደመናው ዙሪያ የነበሩትም መላእክት እንዲሁ «ቅዱስ® ቅዱስ፣ ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔርኃያል!” ይሉ ነበር በደመና ውስጥ የነበሩትም ቅዱሳን እንዲሁ «ሐሌሉያ ክብር ለእርሱ ይሁን” እያሉ እየጮኹ ሠረገላው ሽቅብ ወደ ቅድስት ከተማ የሚያደርገውን ጉዞ ቀጠለ፡፡ ወደ ከተማዋ ከመድረሱ አስቀድሞ ቅዱሳኑ ፍጹም የሆነ የአራት መአዘን ቅርጽ ሠሩ ይታይ ነበር ላሉት ሁሉ መታየት የሚችል ነበር የሱስን መሃላቸው አድርገው የሱስ ከሁሉም ከፍ ብሎና ልቆ የእርሱ ንጉሣዊ ቅርጽና ተወዳጅ ገጽታ በመአዘኑ ውስጥ ላሉት ሁሉ መታየት የሚቸል ነበር፡፡ ፡፡ EWAmh 213.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents