Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    27—በቂ ተሞክሮ ለሌላቸው

    አንዳንድ የተመለከትኳቸው ሰዎች እውነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ወይም የሚያስከትለውን ውጤት ባለመገዘብ ለአፍታ የሚሰማቸውን ግፊት ወይም እጅግ ደስ የተሰኙበትን ስሜት ተከትለው በመንጎድ ቤተክርስቲያናዊውን ሥነ ሥርዓት በግዴለሽነት ያያሉ፡፡ በእንደነዚህ ዓይነቶቹ አስተሳሰብ መሰረት ኃይማኖት በዋነኝነት የያዘው ጩኸት ነው፡፡ የሦስተኛ ውን መልአክ መልእክት እውነት ገና የተቀበሉ አንዳንዶች በእውነት ላይ ለዓመታት የተመሰረቱትን፣ መከራ የተቀበሉትንና የሚቀድሰው የመልእክቱ ኃይል የተሰማቸውን ለመገሰጽና ለማስተማር ዝግጁ ናቸው፡፡ በጠላት ተወጥረው ያሉ የሚቀድሰው የእውነት ተጽእኖ ሲሰማቸው ይህ እውነት እንዴት እንዳገኛቸው የሚገነዘቡበትን ስሜት ያገኛሉ «ጎስቋላ፣ ምስኪን፣ ደኻ፣ ዕውርና የተራቆተ»፡፡ እውነትን በፍቅር ተቀበለውት እነርሱን ማጠብና ማጥራት ሲጀምር ይህን ታላቅ ነገር በእነርሱ ውስጥ እውን እንዲሆን ያደ ረገው· ሰው ሐብታም እንደሆነና በንብረት እንደበለጸገ አይሰማውም--- የሚፈልገውም ነገር የለም፡፡ EWAmh 88.2

    ተቀዳሚዎቹን የእውነት መርኅዎች ገና ሳይማሩ እውነትን እናምናለን፡፡ ሙሉ ለሙሉ እናውቀዋለን የሚሉ፧ የመምህራኑን ስፍራ ለመውሰድ በመንቀሳቀስ በአስቸጋሪ ወቅት ለዓመታት በእውነት ላይ ጸንተው የቆሙትን የሚገስጹ---በእውነት ላይ አንዳችም ማስተዋል እንደሌላቸውና የእውነትን ውጤት አለመገንዘባቸውን በግልጽ ያሳያሉ፡፡ በመጠኑም ቢሆን የሚቀድሰውን ኃይል አውቀውት ቢሆን ኖሮ ሰላማዊውን የጽድቅ ፍሬ በማፍራት ጣፋጭ በሆነው ብርቱ ተጽእኖው ስር በትህትና በቀረቡ ነበር፡፡ ለእግዚአብሔር ክብር ፍሬ በማፍራት እውነት ለእነርሱ ያደረገላቸውን ነገር ያስተውሉ ነበር እንዲሁም ከራሳቸው አስበልጠው ለሌሎች ዋጋ ይሰጡ ነበር፡፡: EWAmh 88.3

    ትሩፋኑ በምድር ላይ ስለሚመጣው ነገር እንዳልተዘጋጁ ተመልክቼ ነበር:፡፡ የመጨረሻው መልእክት እንዳለን የሚያምኑ ብዙዎች አለማስተዋልና ስንፍና ተጸናውቶአቸው ይታያል፡፡ አብሮኝ ያለው ድምጽ እንዲህ ሲል ጮኸ «ተዘጋጁ! ተዘጋጁ! ተዘጋጁ! የጌታ ቁጣ ይመጣል፡፡ ከምህረት ጋር ያልተቀላቀለው ቁጣው ሊፈስ ነው እናንተም አልተዘጋጃችሁም:: ልብሳችሁን ሳይሆን ልባችሁን ቅደዱ። ለትሩፋኑ ታላቅ ሥራ ሊሠራ ይገባል፡፡ ብዙዎች በአነስተኛ ፈተናዎች እየኖሩ ነው፡፡ ሌጌዮን የክፉ መላእክት በዙሪያችሁ ሆነው በላያችሁ አስፈሪውን ጽልመት በመጣል በወጥመዳቸው ሊከቷችሁ እየሞከሩ ነው፡፡ በእነዚህ በመጨረሻ ጊዜያቶች አእምሮአችሁ---ለዝግጅት መሠራት ካለባቸው ሥራዎችና ከሁሉም አስፈላጊ እውነቶች በፍጥነት እንዲያፈነግጥ በመፍቀድ በእጅጉ አነስተኛ ፈተናዎችን ብቻ ለመፈተን ፈቀዳችሁ” ጉዳዩ በሚመለከታቸው መሃል የነበረው ንግግር ለሠዓታት ዘግይቶ ነበር፧ በዚህም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ጊዜ መባከን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ለጸጋው የማይሸነፍ ልብ ያላቸውን እነዚህን ሁለት ቡድኖች ያደምጡ ዘንድ ታግተው ነበር ኩራትና እራሰ ወዳድነት መወገድ ቢችሉ ኖሮ አስቸጋሪ የሚባሉትን ሁናቴዎች ለማስወገድ አምስት ደቂቃ በቂ በሆነ ነበር፡፡ የእራስን ትክክለኛነት ለማሳየት በባከኑት ሰዓታት እግዚአብሔር አዝኖአል መሳእክትም ተከፍተው ነበር፡፡ እግዚአብሔር ጎንበስ ብሎ የሚቀርቡትን ረጃጅም ምክንያቶች አይሰማም፡፡ ደግሞም አገልጋዮቹ የሳቱት እየተከተሉ ያለውን ጎዳና ከማሳየትና ነፍሳትን ከእሳት ከማውጣት ይልቅ እንዲህ እያደረጉ የከበሩትን ጊዜያቶች በከንቱ ያባክኑ ዘንድ ፍላጎቱ አለመሆኑን ተመልክቻለሁ:: EWAmh 89.1

    የእግዚአብሔር ሕዝቦች በድግምት ተተብትበው በሚፈነጥዙት ግዛት ላይ እንደነበሩ ተመልክቻለሁ፡፡ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ የጊዜውን ማጠርና ነፍሳት ያላቸውን ዋጋ ጭራሹኑ ከአእምሮአቸው አውጥተውታል የአለባበስና የገጽታ ኩራትና መታበይ በሰንበት ጠባቂዎች መሃል አሸምቆ እየገባ ነበር፡፡ መልአኩ እንዲህ አለኝ «ሰንበት ጠባቂዎች እኔነትን፣ ትዕ ቢትንና መመጻደቅን ሊገድሉ ይገባል”EWAmh 89.2

    የሚያድነው እውነት በጨለማ ላሉት እውነትን ስተራቡ ሊሰጥ የግድ ነው፡፡ ብዙዎች እግዚአብሔር ትሑታን ያደርጋቸው ዘንድ እንደጸለዩ ተመልክቻለሁ: ነገር ግን እግዚአብሔር ጸሎታቸውን መመለስ ቢኖርበት ኖሮ በጽድቅ ላይ አስከፊ ሁናቴ በተከሰተነበር ፡፡ እነዚህ ሰዎች እራሳቸውን ትሑታን ማድረግ የእነርሱ ተግባር ነበር፡፡ እራስን ከፍ ከፍ ማድረግ በመካከላቸው ቢከሰት በእርግጥም በበታተናቸው ነበር ይህን ችግር ማሽነፍ ባይችሉ ውድቀታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ አንድ ሰው እራሱን ከፍ ከፍ በማድረግ መታበይ ሲጀምርና በራሱ ኃይል አንድ ነገር ማድረግ እንደሚችል ሲያስብ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእርሱ እየራቀ ይሄዳል፡፡ እርሱም ውድቀት እስኪደርስበት ድረስ በራሱ ብርታትና ጥንካሬ መጓዙን ይቀጥላል፡፡ አንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ ትክክል ቢሆን የእግዚአብሔርን ክንድ ማነቃነቅ እንደሚችል---ነገር ግን ትክክል ያልሆኑ ብዙዎች በአንድ ላይ ቢሆኑም እጅግ ደካሞችና አንዳችም ውጤት ማምጣት የማይችሉ መሆናቸውን ተመልክቻ ለሁ፡፡ EWAmh 89.3

    ብዙዎች ያልተሸነፈና ትህትና የጎደለው ልብ ያላቸው አብልጠው የሚያስቡት ስለ ኃጢአተኞች ነፍስ ሳይሆን ነገር ግን ኢምንት ስለሆነው ስለራሳቸው ብሶትና ፈተና ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ክብር ቢመለከቱ ኖሮ በዙሪያቸው እየጠፉ ያሉት ነፍሳት ሁኔታ በተሰማቸው፣ እራሳቸው የሚገኙበትን አደገኛ ሁኔታ በማስተዋል ባለ ኃይላቸው እርሱን አጥብቀው በያዙ፣ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት በተለማመዱ-እንዲሁም! ጣፋጩ የምህረት ድምጽ እየከሰመ ከመሄዱ አስቀድሞ የአገልጋዮችን እጆች በመያዝ በድፍረትና በፍቅር እውነትን በተናገሩ ነበር፡፡ መልአኩ እንዲህ አለኝ «በስሙ ማመናቸውን የሚናገሩ ገና አልተዘጋጁም፡፡” ሰባቱ መቅሰፍቶች መከላከያ በሌላቸው ኃጥአን ላይ ሊወርዱ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ እንዲሁም በመንገዳቸው ላይ የቆሙ--ኃጢአተኞች የሚሰነዝሯቸውን መራራ ወቀሳዎች በመስማት ልባቸው ይቀልጥ ነበር፡፡ EWAmh 90.1

    መልአኩ እንዲህ አለኝ «እስከ ዛሬ አነስተኛ ፈተናዎችን ብቻ ስትጋፈጡ እንደመኖራቸሁ በውጤቱ ኃጢአተኞች ሊጠፉ የግድ ነው» በምናደርጋቸው ስብሰባዎች እግዚአብሔር ለእኛ ለመሥራት ፈቃደኝ ነው:፡፡ ነገር ግን ሰይጣን «ሥራውን አስተጓጉላለሁ» ሲል ወኪሎቹ «አሜን» ይላሉ፡፡ በእውነት ላይ ጸንተው የቆሙ ታማኞች ሰይጣን ከፊታቸው አግዝፎ ለማስቀመጥ የሚሞክራቸውን አነስተኛ ፈተናዎችና አስቸጋሪ ሁናቴዎች ይቋቋማሉ፡፡ ጌዜ ፈጽሞ ሊታወስ ከሚችለው በላይ ባክኖአል፡፡ የእውነት ጠላቶች ድክመቶቻችንን ተመልክተዋል፧ እግዚአብሔር በእጅጉ አዝኖአል፧ ክርስቶስም ቆስሏል፡፡ የሰይጣን ተጨባጭ ዓላማ የታለመለትን ግብ መትቶአል፧ እቅዶቹ ተሳክተዋል፤ ድልም ተቀዳጅቶአል፡፡ EWAmh 90.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents