Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    62—ለጥቅም መስገብገብ

    ሰይጣን በተለይ የክርስቶስን ዳግም መገለጽ በሚጠባበቁና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በሚጠብቁ ላይ መላእክቱ የተለያዩ ወጥመዶችን ተጠቅመው እንዲያስቷቸው አዝዞ ነበር: ቤተክርስቲያኖች እያንቀላፉ መሆናቸውን ሰይጣን ለመላእክቱ ነግሯቸዋል፡፡ በመሆኑም ኃይሉን በመጨመርና የሐሰት አስደናቂ ነገሮችን በመዝራት በቁጥጥሩ ሥር ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ ሰይጣን እንዲህ ሲል ተናገረ ‹‹ነገር ግን ሰንበት ጠባቂዎችን እንጠላቸዋለን፡፡ እነርሱ ያለማቋረጥ ከእኛ በተቃራኒ እየሠሩና የሚጠላውን አምላካዊ ትእዛዝ እየጠበቁ ምርኮዎቻችንን እየወሰዱብን ነው፡፡ እንግዲህ ሂዱና የእርስትና የገንዘብ ባለቤት በማድረግ በእነዚህ ነገሮች እንዲሰክሩ አድርጓቸው፡፡ ለእነዚህ ነገሮች ልዩ ፍቅር እንዲኖራቸው ካደረጋችሁ በእጃችን ውስጥ ልናስገባቸው እንችላለን፡፡ እነርሱን ሊያስደስታቸው የሚችሉትን ነገሮች ምንነት እራሳቸው ሊናዘዙ ይችላሉ፡፡ እናንተብቻ ስለ የሱስ መንግሥት ወይም ስለ ምንጠላው የእውነት መስፋፋት በተቃራኒ---ስለ ገንዘብ እንዲያስቡ አድርጓቸው፡፡ ይህን ዓለም ይበልጥ ሊስብ በሚችል ብርሃን በፊታቸው ካቀረባችሁላቸው ሊወዱትና ጣኦት ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ሁላችንም በቁጥጥራችን ስር ልናውላቸው የምንችልባቸውን መንገዶች ሁሉ በአእምሮአችን ልናደርግ ይገባናል፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ወደ አገልግሎት የሚገቡባቸው መንገዶች በበዙ ቁጥር አብልጠው ምርኮዎቻችንን በመውሰድ በግዛታችን ላይ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡ በተለያዩ ስፍራዎች ጉባዔዎች ሲያደርጉ በዚያን ጊዜ አደጋ ላይ በመሆናችን እንቅስቃሴአቸውን በትጋት በመመልከት ከተቻለ ረብሻና ግርግር ልንፈጥር ይገባል፡፡ እነርሱን ኣጥብቀን ስለምንጠላ እርስ በርሳቸው እንዳይዋደዱ መተነኳኮስ፣ ተስፋ ማስቆረጥና አገልግሎታቸውን ተስፋ አስቆራጭ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ከገንዘብ ጋር የተጎዳኙ ነገሮችን በተቻለ መጠን በመቆጣጠር አገልግሎታቸው የገንዘብ እጥረት ያለውና አስጨናቂ ማድረግ ከቻልን ወኔአቸውንና በውስጣቸው ያለውን የጋለ ፍላጎት ማኮላሸት እንችላለን:: በያንዳንዱ ግዛ ቸው ላይ ውጊያ ማካሄድ፡፡ ለጥቅም እንዲስገበገቡና ለምድራዊው ሐብትና ንብረት ያላቸው ከፍተኛ አፍቅሮት ባህሪያቸውን የሚዘውር እንዲሆን ማድረግ፡፡ በእነዚህ ነገሮች አገዛዝ ስር እስከዋሉ ድረስ ደኅንነትና ጸጋ ከኋላ ይሸሸጋሉ፡፡ እንዲሁም ዙሪያቸውን ሊስባቸው በሚችል በእያንዳንዱ ነገር ካጨናነቅናቸው በእርግጠኝነት የእኛ ይሆናሉ፡፡ በተጨማሪ ያ የምንጠላው ተጽእኖአቸው ሌሎችን ወደ ሰማይ ለመምራት በሚያስችል መልኩ ሊለማመዱት አይችሉም፡፡ ነገር ግን ይህን ለማድረግ ሙ ከራ የሚያደርጉ ካሉ በውስጣቸው ቂመኛ ባህሪ ማስቀመጥ ተ ገቢ ነው፡፡ EWAmh 196.2

    ስይጣን ዕቅዱን በሚገባ እንዳወጣ ተመልክቻለሁ:፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ጉባዔዎችን ሲያካሂዱ ሰይጣንና መላእክቱ ሥራውን ለማሰናከል በዚያ ይገኛሉ፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ህዝቦች ጭንቅላት ውስጥ ያለማቋረጥ ማጉረምረም እየነዛ ይገኛል፡፡ ሰይጣን በወንድሞችና በእህቶች መሃል ክፉው ባህሪ እንዲጎለብት በማድረግ ያዋክባቸዋል:፡፡ ንፉግና ምቀኛ ለመሆን ምርጫቸው ከሆነ ሰይጣን ከጎናቸው በመቆም በተቻለው እየተቅበዘበዙበት ያለውን ኃጢአት ፍላጎት ያረካላቸዋል፡፡ አምላካዊው ጸጋና የእውነት ብርሃን የምቀኝነትና እራስ ወዳድ ስሜታቸውን ሊያቀልጠው ቢችልም ነገር ግን በዚህ ኃጢአት ላይ ሙሉ ለሙሉ ድል ካላገኙና ከአዳኙ ተጽእኖ ውጪ ከሆኑ ሰይጣን እያንዳንዱን በጸጋ የተሞላ መርኅ ስለሚያመነምነው እነዚህ ሰዎች ከእነርሱ አብልጦ እንደሚፈለግ አድርገው ያስባሉ፡፡ ይህን ተከትሎ ታካቾች በመሆን የሱስ ከሰይጣን ኃይልና ከተስፋቢስ ኃዘን ያድናቸው ዘንድ የከፈለውን ታላቅ መስዋዕት ይዘነጋሉ፡፡ EWAmh 197.1

    ማርያም እጅግ ውድ የሆነውን ሽቶ ሰብራ በየሱስ ላይ ባፈሰሰች ጊዜ ይሁዳን ተጸናውቶት የነበረው እራስ ወዳድ ባህሪ እንዲያጉረመርም አደ ረገው፡፡ ይሁዳ ድርጊቱን እንደ ታላቅ ብክነት በመቁጠር ሽቶው ተሽጦ ገንዘቡ ለድኾች ቢሰጥ የተሻለ እንደ ነበር ተናገረ፡፡ ለድኾች ግድ ያልነበረው ይሁዳ ይህን ለየሱስ የተደረገ በጎነት እንደ ብክነት ቆጠረው፡፡ ይሁዳ ጌታውን ለመሸጥ የተመናቸው ጥቂት ብሮች በቂ ሆኖ አገኛቸው፡፡ እንደ ይሁዳ ጌታቸውን ለመሸጥ የሚጠባበቁ አንዳንዶች እንዳሉ ተመልክቻለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች በሰይጣን ቁጥጥር ስር ቢሆኑም እነርሱ ግን ይህን አይገነዘቡም፡፡ እግዚአብሔር አነስተኛ መጠን ያለውን እንኳ ለጥቅም መስገብገብ ወይም እራስ ወዳድነት ይጸየፋል የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን የሚያውቀው ሰይጣን ሰዎች ይበልጥ ንፉግና ለጥቅም የሚስገበገቡ እንዲሆኑ ከመራቸው በኋላ በወጥመዱ ተሰናክለው ሲያገኛቸው ይከብርባቸዋል፡፡ የእነዚህ ሰዎች ዐይኖች ተከፍተው ቢሆን ኖሮ እርሱ ያባቀረበላቸውን ሃሳብ በመቀበላቸው በደረሰባቸው መሰናከል ሰይጣን ባለ ድል በመሆን ሲሳለቅባቸው ማየት በቻሉ ነበር:: EWAmh 198.1

    ሰይጣንና መላእክቱ ስግብግብና ለጥቅም ሟች የሆነትን ሁሉ በመየት ‹እሆ ወደ ሰማይ ለመሄድ በዝግጀት ላይ ያሉ የክርስቶስ ተከታዮች, በማለት በየሱስና በቅዱሳን መላእክት ፊት ወቀሳ ይሰነዝራሉ። ይጣን የእነዚህን ሰዎች ህይወት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በግልጽ ከተገጸው ጋር በማስተያየት እነዚህ ክርስቶስን የሚከተሉና ቃሉን የሚጠብቁ ናቸው! እነዚህ የክርስቶስ መስዋዕትነትና መPጀት ፍሬዎች ናቸው በማለት በሰማይ መላእክት ላይ ያፌዝባቸዋል: መላእክት ሁኔታውን በመጸየፍ ፊታቸውን ከትዕይንቱ ያዞራሉ። እግዚአብሔር በሕዝቡ በኩል የማያቋርጥ በነት እንዲኖር ይጠይቃል: የሱስ የገዛ ራሱን ህይወት ለከፈለላቸውና እርሱ የእኔ ባላቸው ሕዝቦቹ መሃል አነስተኛ የሚባለው እንኳ የእራስ ወዳድነት ባህሪ አግዚአብሔርን አብልጦ እንደሚያስከፋው ተመልክቻለሁ:: እያንዳንዱ በስስት የተሞላና ንፉግ ሰው ገውን ሳይጨርስ በመንገድ ሊቀር ይችላል ጌታውን አንደ ሸጠው ይሁዳ እነርሱም ለጥቂት ምድራዊ ጥቅም ሲሉ መልካም፣ ጻድቅና ለጋስ የሆኑትን ህሪዎች ይሽጧቸዋል: እንደነዚህ ዓይነቶቹ ከእግዚአብሔር ህዝቦች መሃል ተበጥረው ይወጣሉ፡፡ ሰማይን የሚሹ ሁሉ በላቸው ኃይል ሰማያዊውን መርኅዎች ሊያበረታቱ ይገባል ራስ ወዳድ በመሆን ፋንታ ነፍሶቻቸው በለጋስነት ሊዘረጉ ይገባል:: እያንዳንዱ ሰው በሚያገኘ ው አጋጣሚ ሁሉ ለሌሉች መልካም ማድረግን በማጎልበት ሰማያዊውን መርኀ የግል ሐብቱ ሊያደርግ ይገባል የሱስ ፍጹም ምሳሌ በመሆን ቀርቦልኝ ነበር የእርሱ ህይወት ከራስ ወዳድነት የነጻና የለጋስነት ተምሳሌት ነበር: EWAmh 198.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents