Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    37—የየሱስ መልክ መቀየር

    የሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ አንድ ከፍ ያለ ተራራ ይዞአቸው በመውጣት የእርሱን ክብር እንዲመለከቱና ስለ መለኮታዊው ባህሪ የሚመሰክ ረውን ድምጽ ከሰማይ እንዲሰሙ መደረጋቸው እምነታቸውን በእጅጉ አጠንክሮታል፡፡ የሱስ በሚሰቀል ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ላይ በሚደርስባቸው መራራ ኃዘንና ተስፋ መቁረጥ ወቅት በእርሱ ላይ የነበራቸው መተማመን ሙሉ ሙሉ ከውስጣቸው ተሟጦ እንዳይጠፋ ለማድረግና የሱስ ቃል የተገባው መሲህ ለመሆኑ ጠንካራ ማረጋገጫ ለመስጠት ሲል እግዚአብሔር ይህን ለማድረግ መረጠ፡፡ የየሱስ መልክ በተለወጠበት ወቅት እርሱ ስለሚቀበለው ሥቃይና ሞት ያዋዩት ዘንድ እግዚአብሔር ሙሴንና ኤልያስን ላካቸው፡፡ መላእክት የሱስን ያናግሩት ዘንድ በመላክ ፋንታ እግዚአብሔር እነዚህን በምድር ላይ ፈተናን የተለማመዱ ሰዎችን ወደ እርሱ ለመላክ መ ረጠ፡፡ EWAmh 111.1

    ኤልያስ እርምጃውን ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎ ነበር፡፡ ጌታ በእርሱ አማካኝነት የእስራኤልን ኃጢአት ወቅሶ ስለነበር የእርሱ ሥራ አድካሚና ፈታኛ ነበር፡፡ ንም እንኳ ኤልያስ ህይወቱን ለማትረፍ ከቦታ ወደ ቦታ እንዲንከራተት አስገዳጅ ሁናቴዎች ቢገጥሙትም ነገር ግን እርሱ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር፡፡ የገዛ ራሱ ሕዝብ ሊያጠፋው እንደ ዱር አውሬ እያደነው ሲያድነው እግዚአብሔር ግን ቀየረው፡፡ መላእክት በክብር ተሸክመው በድል ኣድራጊነት ሰማይ ይዘውት ገቡ:፡፡ EWAmh 111.2

    ሙሴ ከእርሱ በፊት ከኖሩት ሁሉ ታላቅ ሰው ነበር፡፡ እርሱ ልክ እንደ ጓደኛው ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት መነጋገር የቻለና በእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ክብር የተቸረው ሰው ነበር፡፡ ሙሴ አብን የከበበውን ታላቅ ብርሃንና አስደናቂ ክብር እንዲመለከት ተፈቅዶለት ነበር፡፡ ጌታ በሙሴ አማካኝነት የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ባርነት ነጻ አውጥቶአል፡፡ ሙሴ በሕዝቡና በእግዚአብሔር ቁጣ መሃል በተደጋጋሚ አማላጅ ሆኖ መቆም የቻ ለ ሰው ነበር፡፡ በእስራኤላውያኑ አለማመን መንስዔ የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ በነደደ ጊዜ ሙሴ ለእነርሱ የነበረው ፍቅር ተፈትኖአል፡፡ እግዚኣብሔር እስራኤላውያኑን አጥፍቶ እርሱን የታላቅ ሕዝብ መሪ እንደሚያደረገው ሃሳብ አቅርቦለት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሙሴ በትህትና በእነርሱ ቦታ ሆኖ በመለመን ለእስራኤላውያኑ ያለውን ፍቅር አሳይቶ ነበር፡፡ እርሱ በከፍተኛ ሃዘን በመሆን እግዚአብሔር ከቁጣው እንዲመለስና እስራኤልን ይቅር እንዲል ያለበለዚያ ግን ስሙን ከህ3ወት መጽሐፍ እንዲደመስስ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ EWAmh 111.3

    እስራኤላውያኑ በምድረበዳ ውሃ ማግኘት ባልቻሉ ጊዜ እኛንና ልጆቻችንን በውሃ ጥም ልትገድለን ለምን ከግብጽ ምድር አወጣኸን በማለት በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ አንጎራጎሩ:፡፡ እግዚአብሔርም ማጉረም ረማቸውን ሰምቶ ሙሴ ዐለቱን እንዲናገረውና ውሃው ፈልቆ እንዲጠጡ አስታወቀው:፡፡ ነገር ግን ሙሴ ዐለቱን በመናገር ፋንታ በቁጣ በመምታት ክብሩን ለራሱ ወሰደ፡፡ የእስራኤል ልጆች የማያቋርጥ አመጻና ማንጎራጎር ሙሴን በእጅጉ የሐዘን ሰው አድርጎት ነበር፡፡ በመሆኑም እግዚአብሔር ምን ያህል እንደተሸከማቸውና የነርሱ ማጉረምረም በእርሱ ላይ ሳይሆን ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ መሆኑን ሙሴ ለጥቂት ጊዜያት ዘንግቶ ነበር ሙሴ ስለራሱ ብቻ በማሰቡ የከፋ ስህተት ላይ እንዲወደደቅ አድርጎታል፡፡ ሙሴ ለእስራኤላውያኑ ላሳየው ጥልቅ ፍቅር ያገኘው ምስጋና እዚህ ግባ የማይሉት ነበር፡፡ EWAmh 112.1

    እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን ፍቅርና ጥንቃቄ በመገንዘብ እርሱን ማገልገልና ማክበር ይማሩ ዘንድ ሕዝቡን በተደጋጋሚ ወደ ቀጥተኛ ስፍራ ዎች በመምራት የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች በእርሱ ኃይል እንዲሟላላቸው ማድረግ አምላካዊው እቅድ ነበር፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ እግዚአብሔርን ያመልክና ከፍ ከፍ ያደርግ ዘንድ ሙሴ በፊታቸው እርሱን ከማክበርና ስሙን ከማወደስ ተሰናክሎ ነበር፡፡ በዚህ ድርጊቱ ጌታ በእርሱ ላይ እንዲያዝን ሆነ፡፡ EWAmh 112.2

    ሙሴ ሁለቱን የድንጋይ ገበታዎች ይዞ hተራራው ላይ ሲወርድ እስራኤ ላውያኑ የወርቅ ጥጃ ሠርተው ሲያመልኩ ተመለከተ:: ከዚያም በዚህ ድርጊታቸው በእጅጉ በመበሳጨት የድንጋይ ገበታዎቹን ወርውሮ ሰባበራቸው፡፡ ሙሴ ይህን በማድረጉ ኃጢአት እንዳልሠራ ተመልክቻለሁ:፡፡ እርሱ ይህን ያደረገው ለእግዚአብሔር በመቆርቆርና ለክብሩ በመቅናት ነበር፡፡ ነገር ግን ተፈጥሮhዊውን የልቡን ስሜት ማስገዛቱን አስመልክቶ ለእግዚአብሔር ይገባ የነበረውን ክብር ለራሱ በመውሰዱ ኃጢአት ሠራ: በዚህ ኃጢአቱ የተሳ ሙሴ ከንአን ይገባ ዘንድ እግዚአብሔር መፍቀድ አልቻ ለም:: EWAmh 112.3

    ሰይጣን ሙሴን በመላእክቱ ፊት የሚከስበትን መንገድ ይፈልግ ነበር፡፡ ሙሴ እግዚአብሔርን የሚያሳዝንበትን መንገድ በመፈለግ ባገኘው ክንውን ከፍ ከፍ ብሎ የነበረው ሰይጣን፤ ኣዳኙ ሰብዓዊውን ፍጡር ለመዋጀት ወደዚህ ምድር በሚመጣ ጊዜ ሊያሸንፈው እንደሚችል ለመላእክቱ ነግሮአቸው ነበር፡፡ ሙሴ በዚህ መተላለፉ በሰይጣን ኃይል---በሞት ግዛት ስር ዋለ፡፡ እርሱ እንከን ሳይገኝበት እንደ ቀድሞው በጽናት ቢቀጥል ኖሮ ጌታ ወደ ተስፋው ምድር እንዲገባ በመፍቀድ ሞትን ሳያይ ተቀይሮ ሰማይ እንዲገባ ባረገው ነበር EWAmh 112.4

    ሙሴ በሞት ውስጥ አልፎአል፡፡ ሆኖም የሙሴ አካል ከመበስበሱ አስቀድሞ ሚካኤል ወርዶ ህይወት ሰጠው፡፡ ሰይጣን የሙሴ አካል ይገባኛል በሚል ይዞ ሊያስቀረው ቢሞክርም ነገር ግን ሚካኤል ለሙሴ ትንሳኤ በመስጠት ወደ ሰማይ ይዞት ሄዶአል፡፡ ሰይጣን ግዳዬ ነው ይገባኛል የሚለውን የሙሴን አካል እግዚአብሔር በመውሰዱ ጻድቅ አይደለም በማለት ክፉኛ በማማረር አወገዘው፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋይ የወደቀው በእርሱ ፈተና ሆኖ ሳለ ክርስቶስ ግን በትህትና አባቱን ጠቅሶ «ጌታ ይገስጽህ” አለው አንጂ ይህን ጠላቱን አልገሰጸውም ነበር: EWAmh 113.1

    የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል እስኪመጣ ድረስ ሞትን ሳይቀምሱ ከእርሱ ጋር የሚቆሙ አንዳንዶች እንደሚኖሩ የሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ነግሮአቸው ነበር፡፡ የሱስ በተለወጠ ጊዜ ይህ ተስፋ ሰምሮ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት የየሱስ ገጽታ በመቀየር እንደ ጸሐይ አንጸባረቀ፡፡ የእርሱ ቅሬታዎች ነጭና አንጸባራቂ ነበሩ፡፡ ሙሴ በየሱስ ዳግም ምጽአት ወቅት ከሙታን የሚነሱትን በመወከል በዚያ ቦታ ተገኝቶ ነበር፡፡ አንዲሁም ሞተን ሳያይ ተለውጦ ሰማይ የተወሰደው ኤልያስ በየሱስ ዳግም ምጽአት ወቅት ሞትን ሳይቀምሱ የማይሞቱ ሆነው በመቀየር ወደ ሰማይ የሚሄዱትን ይወክል ነበር ደቀ መዛሙርቱ አስደናቂውንና በክብር የተሞላውን የየሱስ ግርማ በአድናቆትና በፍርሃት እየተመለከቱ ሳለ ብሩህ ደመና ሸፈናቸውና በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” የተሰኘው የእግዚአብሔር ድምጽ ተሰማ፡፡ EWAmh 113.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents