Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    59—የሦስተኛው መልአክ መልእክት

    የሱስ በቅዱሱ ክፍል ይሰጥ የነበረው አገልግሎት ፍጻሜ አግኝቶ ወደ ቅድስተቅዱሳኑ ክፍል በማለፍ የእግዚአብሔርን ሕግ ከያዘው ታቦት ፊት በመቆም ለዓለም ሦስተኛውን መልእክት የያዘ ሌላ ኃያል መልአክ ላከ:: መልእክቱ በእጁ የተሰጠው መልአክ በታላቅ ኃይልና ክብር ወደ ምድር በመውረድ ከዚህ ቀደም ለሰው ልጅ ያልተሰጠውን አስፈሪ ማስጠንቀቂያ አወጀ:: መልእክቱ የእግዚአብሔር ልጆች ከፊታቸው ላለው የፈተናና የሥቃይ ጊዜ እራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማሳየት ታቅዶ የተሰጠ ነበር፡፡ መልአኩ እንዲህ አለኝ «ከአውሬውና ከአውሬው ምስል ጋር ውጊያ ይገጥማሉ፡፡ የእነርሱ ብቸኛ የዘላለማዊ ህይወት ተስፋ በጽናት መቆም ብቻ ነው፡፡ ምንም እንኳ ህይወታቸው አደጋ ላይ ቢሆንም እውነትን አጥብቀው መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡” ሦስተኛው መልአክ «የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና ለየሱስም ታማኝ ሆነው በትዕግሥት የሚጸኑ ቅዱሳን የሚታወቁት በዚህ ነው» በማለት መልእክቱን ደመደመ መልአኩ እነዚህን ቃላት ደግሞ በሚናገር ጊዜ ወደ ሰማያዊው መቅደስ ያመላክት ነበር፡፡ ይህን መልእክት የተቀበሉ ሰዎች አእምሮ ገና በምህረት ውስጥ ላሉትና አምላካዊውን ሕግ ባለማወቅ ለጣሱት የመጨረሻውን የማማለድ ሥራ ለመሥራት በቅድስተቅዱሳኑ ክፍል በታቦቱ ፊት ወደ ቆመው የሱስ የሦስተኛው መስከ -ስእከት አነጣጠረ ይህ ሥርየት እውን የሆነው በመቃብር አንቀላፍተው ለሚገኙት ጻድቃንም ሆነ በህይወት ላሉት ነው፡፡ ሥርየቱ በክርስቶስ አምነው በእግዚአብሔር ትእዛዛት ላይ ብርሃን ባለመቀበላቸው ባለማወቅ የተላለፉትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ EWAmh 186.2

    የሱስ የቅድስተቅዱሳኑን በር ከከፈተበኋላ የሰንበት ትእዛዝ በመታየቱ እስራኤላውያኑ ጥንት የእግዚአብሔርን ሕጎች በመጠበቁ ዘሪያ እንደተፈተኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ሕዝቦችም ተፈተኑ፡፡ ሦስተኛው መልአክ የሰማያዊውን የቅድስተቅዱሳን ክፍል ጎዳና በኃዘን ውስጥ ለነበሩት ወገኖች ሲያመላክታቸው አይቻለሁ፡፡ እነዚህ ህዝቦች በእምነት ወደ ቅድስተቅዱሳኑ ክፍል ሲገቡ የሱስን ማግኘት በመቻላቸው ዳግም በተስፋና በደስታ ታደሱ፡፡ ከየሱስ ዳግም ምጽአት እወጃ እስከ 1844 ማለፍ ድረስ የነበራቸውን ተሞክሮና ያለፉበትን ጎዳና ወደ ኋላ ዞር ብለው ሲቃኙ ተመለከትኩ፡፡ ቀደም ብሎ አዝነውበት የነበረው ነገር አሁን ተብራርቶ ስለቀረበላቸው እንደገና በደስታና በእርግጠኝነት ታደሱ፡፡ ሦስተኛው መልአክባለፈው ጊዜ ላይ፣ በአሁኑና በወደፊቱ ላይ በማብራቱ በእርግጥም እግዚአብሔር በምስጢራዊው ጣልቃ ገብነት እንደመራቸው አወቁ፡፡ EWAmh 187.1

    ትሩፋኑ የሱስን ተከትለው ወደ ቅድስተቅዱሳኑ በመግባት ታቦቱንና የሥርየት መክደኛውን በመመልከት በእነዚህ ነገሮች ክብር ተሞልተው እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ ከዚያም የሱስ የታቦቱን ሽፋን ሲያነሳው አስርቱ ትእዛዛት በላያቸው የተጻፈባቸው የድንጋይ ጽላቶች ታዩ፡፡ ህያው የነበሩትን ትእዛዛት ከመጀመሪያ አንስተው እየተመለከቱ አራተኛው ላይ ሲደርሱ ከሌ ሎቹ ዘጠኝ ይልቅ በዚህኛው ትእዛዝ ላይ ብርሃን አንጸባርቆበትና ዙሪያው በክብር ተሞልቶ አዩ፡፡ እነዚህ ህዝቦች ስለ ሰንበት ማብቃት ወይም ወደ ሳምንቱ መጀመሪያ ቀን መቀየር የሚያሳይ አንዳችም ነገር አልተመለከቱም ነበር፡፡ ትእዛዛቱ እግዚአብሔር በተራራው ላይ በከባድ ደመና፣ ነጎድጓድና መብረቅ ታጅቦ በድምጽ የተናገራቸውና በድንጋይ ገበታ ላይ በገዛ ጣቱ የጻፋቸው ናቸው «የሰንበትን ቀን ቅዱስ አድርገህ አክብር፡፡ ስድስት ቀን ትሠራለህ ሥራህን ሁሉ አከናውን፡፡ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው»፡፡ ትሩፋኑ ለአስርቱ ትእዛዛት የተስጠውን አጽንኦተሲመለከቱ በእጅጉ በመደነቅ ትእዛዛቱ ከያህዌ አጠገብ በመሆን በአምላካዊው ቅድስና አንጸባርቀውና ተጠብቀው ተመለከቱ፡፡ ትሩፋኑ በያህዌ ተቀድሶ በተሰጠው ቀን ምትክ በአረማውያንና በጳጳሳት የተሰጣቸውን ቀን በመጠበቅ አራተኛውን ትእዛዝ ሽረው እንደነበር በማስተዋላቸው እራሳቸውን ትሁት አድርገው በእግዚአብሔር ፊት በማቅረብ ላለፈው መተላለፋቸው አለቀሱ፡፡EWAmh 187.2

    የሱስ ንስሐና ጸሎታቸውን ተቀብሎ ወደ አባቱ ሲያቀርብ በጥናው ላይ ያለው ዕጣን ሲስ ተመለከትኩ፡፡ ጭሱ ወደ ላይ ሲወጣ ብሩህ ብርሃን በየሱስና በሥርየት መክደኛው ላይ አረፈ፡፡ እነዚያ በጽናት ሲጸልዩ የነበሩና የእግዚአብሔርን ሕግ ተላላፊ መሆናቸውን በማስተዋላቸው የተረበሹ አሁን ብሩካን በሆን የፊታቸው ገጽታ በተስፋና በደስታ ተሞላ፡፡ እነዚህ ህዝቦች በሦስተኛው መልአክ ሥራ ተሳታፊ በመሆን ብርቱውን ማስጠንቀቂያ ለማወጅ ድምጾቻቸውን ከፍ አደረጉ:: ምንም እንኳ በመጀመሪያ ላይ መልእክቱን የተቀበሉት ጥቂት ቢሆኑም ነገር ግን ታማኝ የሆኑት መልእክቱን ለማወጅ በሙሉ ኃይላቸው መንቀሳቀሳቸውን ገፉበት፡፡ hዚያም የሦስተኛውን መልአክ መልእክት የተቀሉ ብዙዎች በመጀመሪያ ማስጠንቀቂያውን ከሰጡት ጋር ድምጾቻቸውን ከፍ አድርገው በመቀላቀል የእርሱን የተቀደሰ የዕረፍት ቀን በመጠበቅ ክብር ሰጥተው ሲቀላቀሏቸው ተመለከትኩ፡፡ EWAmh 187.3

    የሦስተኛውን መልአክ መልእክት የተቀበሉ ብዙዎች የበፊቶቹ ሁለት መልእክቶች ተሞክሮ አልነበራቸውም፡፡ ሰይጣን ይህን በማስተዋሉ በክፋት የተሞሉት ዐይኖቹ እነርሱን ለመጣል ይከታተሏቸው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሦስተኛው መልአክም ሆነ እነዚያ ባለፉት መልእክቶች ተሞክሮ የነበሯቸው ወደ ሰማያዊው ቅድስተቅዱሳን የሚወስደውን ጎዳና ያመላክቷ ቸው ነበር፡፡ ብዙዎች በመልአኩ መልእክቶች ውስጥ ይስተዋል የነበረውን ፍጹም የእውነት ሰንሰለት በመመልከትና በቀረበው ቅደም ተከተል ደስ በመሰኘት የሱስን በእምነት ወደ ሰማያዊው ቅድስተቅዱሳን ተከተሉት፡፡ እነዚህ መልእክቶች ለእግዚአብሔር ህዝቦች እንደ መልህቅ የሚያገለግሉ ሆነው ቀርበውልኝ ነበር መልእክቶቹን የሚያስተውሉና የሚቀበሏቸው ሁሉ በሰይጣን ማታለያዎች ተጠርገው ከመወሰድ ይድናሉ፡፡ EWAmh 188.1

    ከታላቁ የ1844 መከፋት በኋላ ሰይጣንና መላእክቱ የዚህ መንጋ እምነት እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ መሰናክሎችን በመደርደር ተጠምደው ነበር፡፡ ሰይጣን በመልእክቱ ተሞክሮ የነበሯቸውንና እራሳቸውን የማዋረድ ማንነት ይስተዋልባቸው የነበሩ ሰዎችን አእምሮ ያውክ ነበር፡፡ ለመጀመሪያውና ለሁለተኛው መልእክትእውን መሆን አንዳንዶች የወደፊቱን ሲያመላክቱ ሌ ሎች ደግሞ የኋለኛውን በማሳየት በወቅቱ ፍጻሜ እንዳገኙ ይናገሩ ነበር፡፡ አንዳንዶች ከመንጋው መንፈሳዊ አቋም በተለየ የግላቸውን ለመገንባት የሚያስችላቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናት ያደርጉ ነበር፡፡ ከመልህቁ እየላሉ የነበሩትን በተለያዩ ኃይማኖታዊ ነፋሶች በመጠራረግ አደጋ ሊያመጣባቸው እንደሚችል ያውቅ የነበረው ሰይጣን በእነዚህ ተግባራት ስኬት አግኝቶ ነበር: አሁን በመጀመሪያውና በሁለተኛው መልእክቶች ሲመሩ የነበሩ ብዙች መልእክቶቹን በመካዳቸው በመንጋው ውስጥ መከፋፈልና ግራ መጋባት ተከሰተ:: በመቀጠል ትኩረ ወደ ዊልያም ሚለር እንዲሆን ተደረገ:፡፡ ግራ የተጋባና የተደናገረ የሚመስለው ይህ ሰው በጭንቀትና በብዙ ችግር ለህዝቡ ለጸሎት ተደፋ፡፡ በ1844 ላይ ፍቅርና ኅብረት የነበረው ቡድን አሁን ግን ፍቅሩ እየከሰመና አንዱ ሌላውን እየተቃወመ ወደ ቀዝቃዛ የማፈግፈግ ሁናቴ ውስጥ መስመጥ ጀምረዋል፡፡ ሚለር ይህን ሲመለከት ያደረበት ከፍተኛ ኃዘን ብርታቱን ተሻምቶት ነበር፡፡ በመሪነት ኃላፊነት ላይ የነበሩ ወደ ሚለር በመመልከት የሦስተኛውን መልአክ መልእክትና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንዳይቀበል ፍርሃት እንዳደረባቸው ተመለከትኩ፡፡ ሚለር በሰማያዊው ብርሃን ላይ ሲደገፍ አእምሮ ከዚህ እውነት ለማራቅ በማሴር እቅዶችን ያውጠነጥኑ ነበር፡፡ እርሱን በጽልመት ውስጥ በመተው ተጽእኖውን እውነትን በተቃወሙት ላይ ለማስቀረት ሰብዓዊ ተጽእኖ ቢደ ረግም ነገር ግን ዊልያም ሚለር ከሰማይ ይመጣ ከነበረው ብርሃን በተጻራሪ ባለው ኃይል ላይ ድምጹን በብርታት ከፍ አድርጎ አሰማ፡፡ በሚለር ላይ የደ ረሰውን መከፋት በብቃት በመግለጽ ባለፈው ተሞክሮ ላይ በክብር የተሞላ ብርሃን የሚፈነጥቅለትን፣ የደከመውን ኃይሉን የሚያበረታለትን፣ ተስፋውን የሚያበራለትንና እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ እንዲያደርግ ሊመራው ይችል የነበረውን መልእክት ሳይቀበል ቀረ፡፡ ይህ ሰው በመለኮታዊው ምትክ ሰብዓዊው ጥበብ ላይ በመደገፍ ለጌታው መርኅ በመቆም ጠንክሮ በመሥራቱ ረገድ ቢሰናከልም ለሆነው ሁሉ እርሱ ወደ እውነት እንዳይመጣ አጥብቀው የገቱትን ያህል ተጠያቂ አልነበረም በመሆኑም እነዚህ ሰዎች ኃላፊት ስላለባቸው ኃጢአቱ በእነርሱ ላይ ይሆናል፡፡ EWAmh 188.2

    ዊልያም ሚለር የሦስተኛውን መልአክ ብርሃን ቢመለከት ኖሮ ለእርሱ ጨለማና ምስጢራዊ የነበሩ አያሌ ነጥቦች በተብራሩለት ነበር፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ጥልቅ ፍቅርና ፍላጎት ካሳዩት ወንድሞቹ መለየት እንደማይችል ኣሰበ:: ልቡ ወደ እውነት ያዘነብልና ወደነዚህ ወንድሞቹ ሲመለከት ከእነርሱ ተቃውሞ ይገጥመዋል፡፡ ከጎኑ በመቆም የሱስ ዳግም ይመጣል እያሉ ሲያውጁ ከነበሩት ከእነዚህ ወንድሞች መገንጠል ይሆንለታል? እነዚህ ሰዎች ወደ ጥፋት መንገድ እንደማይወስዱት እምነት ነበረው፡፡ EWAmh 189.1

    ሚለር በሰይጣን የሞት ግዛት ስር እንዲወድቅ እግዚአብሔር በመፍቀዱ ያለማቋረጥ ከእውነት ይገቱት ከነበሩት ነጥሎ በመቃብር አኖረው፡፡ ሙሴ ወደ ተስፋው ምድር ለመግባት በተቃረበ ጊዜ ስህተት ሠርቶ እንደ ነበር ሁሉ ዊልያም ሚለርም ወደ ሰማያዊው ከነዓን ለመግባት ጥቂት ሲቀረው ስህተት መፈጸሙን ተመልክቼ ነበር፡፡ ሚለርን ወደዚህ ጎዳና የመሩት ሌሎች እንደመሆናቸው ኃፊነቱን መሸከም ይኖርባቸዋል በዳ7ም ምጽአት መለከት ሲነፋ የሚነቃውን የዚህን የእግዚአብሔር አገልጋይ የከበረ ትቢያ መላእክት ተመልክተዋል፨EWAmh 189.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents