Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    13—” በምስጢር መነጠቅ »

    በወርሃ ነሐሴ 24/ 1850 ዓ.ም. በምስጢር መነጠቅ በሰይጣን ኃይል እንደሚደረግ ተመልክቼ ነበር: አንዳንዶቹ በቀጥታ ከእርሱ የተወሰዱ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በወኪሎቹ ቢተገበሩም ነገር ግን የሁሉም ምንጩ እርሱ ነው፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሰምሮ የሚታየው ይኸው የራሱ ሥራ በቤተክርስቲያንም ሆነ በዓለም ያሉ ብዙዎች ይህ ክስተት የእግዚአብሔር ኃይል ውጤት ነው ብለው በማሰብና ወደፊት ይዘውት በመገስገስ በታላቅ ጨለማ ውስጥ ተከርችመው ነበር መልአኩ እንዲህ አለ «ሕዝበ አምላኩን መፈለግ አይገባውምን? ህያዋን ወደ ሙታን ይሄዳሉን?» በህይወት ያሉ ዕውቀት ለማግኘት ወደ ሙታን ሊሄዱ ይገባል? ሙታን አንዳችም አያውቁም፡፡ በሕያው አምላክ ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ? እነርሱ አንዳችም ከማያውቁት ከሙታን ጋር ለመነጋገር ከሕያው አምላክ ተለይተዋል፡፡ (ኢሳ. 8፡፡19-20)፡፡ EWAmh 41.1

    በስውር መነጠቅ ይበልጥ በስፋት የተሰራጨእንደሚሄድና አስተምህሮው የተሳሳተመሆኑን መናገር እንደ ስድብ የሚቆጠርበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን ተመልክቼ ነበር፡፡ የሰይጣን ኃይል እየጨመረ በመሄድ አንዳንድ የልብ ተከታዮቹ ተአምራትን የማድረግ ኃይል እንደሚኖራቸውና በዚህም በሰዎች ፊት እሳት ከሰማይ እስከ ማውረድ እንደሚደርሱ ተመልቻለሁ፡፡ እነዚህ ዘመናዊ አስማተኞች ስውር መነጠቅንና ሰመመናዊ አሠራርን በመተግበርና ተአምራቶቻቸውን ጌታ የሱስ ክርስቶስ ካደረጋቸው ጋር አዛምደው በማቅረብ ብዙዎች የእግዚአብሔር ልጅ በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ ያደርጋቸው የነበሩ ተአምራቶች በዚህ ተመሳሳይ ኃይል የታጀቡ እንደሆኑ ያምናሉ፡፡ EWAmh 41.2

    (ይህ ራእይ በተሰጠ ጊዜ ስፕሪቹዋሊዝም ገና ማቆጥቆጥ እየጀመረና አነስተኛ ተከታዮችን በማፍራት ላይ ነበር ሆኖም ከዚያን ጊዜ አንስቶ በመላው ዓለም በመሰራጨት ተከታዮቻቸው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሆነዋል ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ስፕሪችዋሊስቶች መጽሐፍ ቅዱስን ክደዋል በክርስትናም ላይ ዘብተዋል:: ግለሰቦች በተለያዩ ጊዜያት ይህን ሁኔታ ቢተቹና ቢቃወሙም ነገር ግን ጥራቸው አነስተኛ በመሆኑ ትኩረት የሰጣቸው አልነበረም:: አሁን ስፕሪችዋሊስቶች ቀድሞ ይከተሉት የነበረውን ዘዴ በመቀየር ብዙዎች እራሳቸውን «ክርስቲያን ስፕሪችዋሊስት» በማለት እየጠሩ ይገኛሉ: እራስን በዚህ ስያሜ መጥራት እውነተኛ የተሰኘውን አስተሳሰብ የሚያጠናክር የክርስትናው እምነት ፓስተሮች መስተዋላቸውን ልብ ይሏል: እኛ ዛሬ በዚህ ዘመን ላይ ሆነን ይህ በ1850 ዓ.ም. ላይ የተሰጠ ትንቢት ሙሉ ለሙሉ ፍጻሜ የሚያገኝበት ጎዳና ወለል ብሎ እየተመለከተን እንገኛለን፡፡:)EWAmh 41.3

    የክርስትና እምነት ተከታየች ናቸው አይሆንም:: ዛሬ አያሌ ዝነኛ ለስፕሪችዋሊዝም ድጋፋቸውን ሲሰጡ ወደ ኋለኛው ሙሴ ወደ ነበረበት ዘመን እንድመለከት ተደርጌ እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት በፈርዖን ፊት ያደረጋቸውን ምልክቶችና አስደናቂ ነገሮች ያየሁ ሲሆን ከእነዚህ አስደናቂ ነገሮች ወስጥ አብዛኞቹ በግብፅ አስማተኞች ተመሳስለው ተደርገው ነበር በተመሳሳይ በመጨረሻ ላይ ቅዱሳኑ ከመዳናቸው አስቀድሞ እግዚአብሔር ለሐዝቡ በኃይል ይሠራል፡፡ እንዲሁም እነዚህ ዘመናዊ አስማተኞች የእግዚአብሔርን ሥራ አስመሰለው ይሠሩ ዘንድ የፈቀድላቸዋል EWAmh 42.1

    ያ ጊዜ በቅርብ የሚመጣ በመሆኑ ጠንካራውን የያህዌ ክንድ አጥብቀን መያዝ ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሁሉ በዲያብሎስ የሚደረጉ ታላላቅ ምልክቶችና አስደናቂ ተአምራቶች ዓላማ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ለማሳትና ለማሸነፍ ነው:: አእምሮዎቻችን በእግዚአብሔር ላይ ጸንተው ሊቆሙ ይገባል፡፡ ኃጥአን የሚፈሩት ነገር እኛን ሊያስበረግግ ወይም እነርሱን የሚያስደምም እኛን ሊያስደንቅ አይገባም፡፡: ይልቁንም ለእውነት ደፋርና ጀግና ሆነን ልንቆም ይገባል፡፡ ዐይኖቻችን ተከፍተው ቢሆን ኖሮ እኛን ለመ ረበሽና ለማጥፋት አዳዲስ መንገዶችን የሚፈለስፉትን የክፉውን መላእክት መመልከት በቻልን ነበር: ደግሞም ከእነርሱ ኃይል የሚጠብቁንን የእግዚአብሔርን መላእክት እንመለከታለን--የእግዚአብሔር ዐይኖች ምን ጊዜ ም ለእስራኤል በጎ ይሆን ዘንድ በሕዝቡ ላይ ናቸውና፡፡ ይህ ሕዝብ መተማመኑን በዚህ አምላክ ላይ እስካደረገ ድረስ እርሱ ሕዝቡን ይጠብቃል-ያድንማል! ጠላት እንደ ጎርፍ ሲመጣ የጌታ መንፈስ ከለላ ይሆናቸዋል፡፡ EWAmh 42.2

    መልአኩ «የቆማችሁት በግዞት ምድር ላይ መሆኑን አስታውሱ” እንዲህ በማለት ተናገረ:: ሁላችን በንቃት በመጠበቅ ሙሉ የጦር ዕቃ ትጥቅ ለብሰንና የእምነት ጋሻ አንስተን ጸንተን ስንቆም ያን ጊዜ ከኃጥአን የሚወ ረወሩ ፍላጻዎች ሊጎዱን አይችሉም:: EWAmh 42.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents