Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    19—የመሰብሰቢያው ጊዜ

    መስከረም 23 ቀን ጌታ ትሩፋን ህዝቡ እንዲያንሰራራ ለማድረግ እጁን ዳግመኛ ዘርግቶ እንደነበር አሳየኝ፡፡ በዚህ የመሰብሰቢያ ወቅት እንዲህ ዓይነቶቹ ጥረቶች በጥፍ መጨመራቸው የግድ ነው፡፡ እስራኤል በተበተነ ጊዜ የመመታትና የመበጣጠስ ዕድል ገጥሞተየነበረ ሲሆን ነገር ግን አሁን በመሰብሰቢያው ወቅት እግዚአብሔር ሕዝቡን ይፈውሳል አጽንቶም ያቆማል፡፡ በመበተን ወቅት እውነትን ለማሰራጨት ጥረቶች ቢደረጉም ነገር ግን አነስተኛ ውጤት ነበራቸው:: ያገኙት ክንውንም እንዲሁ በእጅጉ አነስተኛ ወይም ምንም የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በመሰብሰቢያው ወቅት አግዚአብሔር ሕዝቡን ሊሰበስብ እጁን ሲሰድ እውነትን ለማሰራጨት የሚደ ረጉ ጥረቶች የታለመላቸውን ውጤት ያገኛሉ፡፡ ሁሉም ህብረት ሊፈጥሩና ለሥራው የጋለ ቅንአት ሊኖራቸው ይገል፡፡ በመበቲን ወቅት የነበረውን ሁናቴ እንደ ምሳሌ በማንሳት በመሰብሰቢያውም ወቅት ተመሳሳይ ክስተት አንደሚኖር አድርጎ መጥቀስ የተሳሳተእንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ካለፈው የላቀ ነገር ካላደረገ በቀር እስራኤል ፈጽሞ አይሰበሰብም፡፡ የ1843ቱ አኻዛዊና ሥዕላዊ መግለጫዎችን እንዲሁም መረጃዎችን የያዘው ቻርት በጌታ እጅ ተመርቶ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ በመሆኑም መለወጥ የለበትም፡፡ በቻርቱ ላይ የነበሩ መረጃዎችና መግለጫ ዎች እርሱ በፈለጋቸው መንገድ የተቀመጡ ነበሩ፡፡ በአንዳንድ የተሳሳቱ መግለጫዎች ላይ እጁ በማረፉ ተሸሽገው ነበር በዚህም እጁ እስኪነሳ ድረስ ማንም ሊመለከታቸው ልቻለም: EWAmh 54.1

    መልእክቱ የሚናገረው በ1843 እንቅስቃሴ ወቅት ጥቅም ላይ ውሎ ስለነበረው ቻርት ነው ቻርቱ ትንቢታዊ ጊዜያቶችን በማስላቱ ረገድ ልዩ ማጣቀሻዎችን ያስቀመጠ ነበር በመቀጠል የቀረበው መልእክት አምላካዊው ጣልቃ ገብነት የተቸገረበት ስህተት ተፈጽሞ እንደነበር ይገልጻል: ሆኖም ይህ ሁናቴ ስህተቶቹን በማረም ቻርቱን በየጊዜው ከማሻሻል አላገደም::EWAmh 54.2

    ከዚያም «መስዋዕት» የሚለው ቃል ‹‹ዘወትሩ» (ዳን. 8:12) ከተሰኘው ጋር በቁርኝት የቀረበው በሰብዓዊው ጥበብ እንጂ የጥቅሱ ክፍል አለመሆኑን ተመለከትኩ፡፡ ጌታም የቃሉን ትክክለኛ ገጽታ የፍርዱ ሰዓት ጩኸት አካል ለሆኑት ሰጣቸው: ከ1844 ቀደም ብሎ አንድነት በተፈጠረ ጊዜ ሁሉም የውህደቱ አካል የሆኑት ከትክክለኛው የ«ዘወትሩ» ምልከታ አኳያ ነበር: ነገር ግን ከ1844 ጀምሮ በተከሰተው ውዥንብር ሌሎች አመለካከቶች መንጸባረቅ በመጀመራቸው በውጤቱ ጽልመትና መጋባት ተከሰተ፡፡ ጊዜ እስከ 1844 ድረስ መፈተኛ አልነበረም ወደፊትም ፈጽሞ አይሆንም፡፡ EWAmh 54.3

    የሦስተኛው መልአክ መልእክትወደፊት በመገስገስ ተበታትነው ለሚገ ኙት የጌታ ልጆች ሳይዘገይ በይፋ ሊነገር እንደሚገባ ጌታ አሳይቶኝ ነበር፡፡ አንዳንዶች የስብከት ክፍለ ጊዜን ተከትሎ ሐሰተኛ ደስታ ያገኙ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ ነገር ግን የሦስተኛው መልአክ መልእክት ከማንኛውም ጊዜ ይልቅ በእጅጉ ጠንካራ ነው፡፡ መልእክቱ በራሱ መሰረት ላይ መቆም እንደሚችልና ማጠናከሪያ ጊዜ እንደማያስፈልገው ተመልክቻለሁ: በመሆኑም የሦስተኛው መልአክ መልእክት ገናና በሆነ ኃይል ወደፊት ያመራል፧ ሥራውንም ይሠራል በመጨረሻም በጽድቅ ፍጻሜ ያገኛል፡፡ EWAmh 55.1

    ከዚያም ወደ ጥንቷ የሩሳሌም መሄድ የእነርሱ ተግባር መሆኑን በማመን ጌታ ከመምጣቱ አስቀድሞ በዚያ የሚሠሩት እንዳላቸው ወደ ሚያስቡና በታላቅ ስህተት ውስጥ ወደሚገኙ እንድመለከት ተደርጌ ነበር፡፡ እንዲህ ያለው አመለካከት በወቅቱ የጌታ ሥራ ከሆነው ከሦስተኛው መልአክ መልእክት የሰዎችን አእምሮና ፍላጎት ለማዛባት ታቅዶ የተዘጋጀ ነው፡፡ ወደ የሩሳሌም መሄድ እንዳለባቸው ገና የሚያስቡ አእምሮአቸው እዚያው ስለሚሆን እራሳቸውንም ሆነ ሌሎችን ከወቅታዊው እውነት በመግታት ያስቀራሉ፡፡ ስለ መጀመሪያው የክርስቶስ ምጽኣት በጣም ጥቂት አይሁዳውያንን እንኳ ማሳመን ከባድ እንደነበረ ሁሉ ዳግም ምጽአቱን እንዲቀበሉ ማሳመን ደግሞ ከዚህ በእጅጉ የገዘፈ ነው:: በመሆኑም እንዲህ ያለው ተልዕኮ አንዳችም ፋይዳ ያለው መልካም ክንውን እንደማያመጣ ተመልክቼአለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች በዙሪያቸው ያሉትን ነፍሳት በመርዳትና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንዲጠብቁ በመምራት ፋንታ እንዲጠፉ ይተዋቸዋል፡፡ ሰይጣን በዚህ ተግባሩ እነርሱንና በዙሪያቸው ያሉትን ነፍሳት በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳተተመልክቻለሁ:: በተጨማሪ አሮጌዋ የሩሳሌም ዳግመኛ ፈጽሞ እንደማትገነባ አይቻለሁ: ነገር ግን ሰይጣን የጌታ ልጆች መላውን ፍላጎታችውን በወቅታዊው የጌታ ሥራ ላይ እንዳያውሉና ለጌታ ቀን የሚያደርጉትን አስፈላጊ ዝግጅት ቸል እንዲሉ በማድረግ አሁን በመሰብሰቢያ ወቅት አእምሮአቸውን ወደነዚህ ነገሮች ለመምራት ባለው አቅም እየሠራ ነበር EWAmh 55.2

    የተወደዱ አንባቢ- ይህችን አነስተኛ መጽሐፍ የጻፍኩት ለወንድምና እህቶቼ የኃላፊነት ስሜት ተሰምቶኝ የነፍሳት ደም በእኔ ላይ እንዳይቀር ካለኝ ጽኑ ምኞት አኳያ ነው፡፡ ከራእዮቹ ጋር በተያያዘ በብዙዎች አእምሮ ውስጥ ስለሚኖረው አለማመን ግንዛቤ አለኝ፡፡ እንዲሁም ክርስቶስን እየፈለጉ እንደሆኑ የሚታዩና ያለነው «በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ ነው ብለው ሲያስተምሩ የሚደመጡን ሁሉ ሰይጣን ብለው ይጠሯቸዋል:: ከእንደነዚህ ዓይነቶቹ ብርቱ ተቃውሞዎችን እጠባበቃለሁ፡፡ ደግሞም ይህን አደርግ ዘንድ ጌታ እንደጠየቀኝ ባይሰማኝ ኖሮ ምናልባትም አቋሜን ይፋ ባላረኩ ነበር ነገር ግን ከሰው ይልቅ እግዚአብሔርን እፈራለሁ፡፡ EWAmh 55.3

    ጌታ ለሕዝቦቹ የማስተላልፈውን መልእክት መጀመሪያ ሲሰጠኝ በቀጥታ ያለውን ነገር መናገር ለእኔ አስቸጋሪ ነበር:: በመሆኑም ብዙውን ጊዜ መልእክቱን የምሰጠው አንዳዶችን እንዳላሳዝን በመፍራት በእጅጉ አለሳልሼና እነርሱንም በተቻለኝ አረጋግቼ ነበር:: ጌታ ለእነርሱ ያስተላለፈውን መልእክት መናገር ለእኔ ታላቅ ፈተና ነበር፡፡ እኔ በራእይ ወደ ክርስቶስ መገኘት እስከተወሰድኩበት ጊዜ ድረስ በዚህ ድርጊቴ ምን ያህል ታማኝ እንዳልነበርኩ አልተገነዘብኩም፣ በተደጋጋሚ ያደረኩትን የዚህን ነገር ኃጢአትነትና አደገኝነትም አልተመለከትኩም ነበር፡፡ የሱስ ኮስተር ብሎ ተመለከተኝና ፊቱን ከእኔ ዞረ: በወቅቱ ተሰምቶኝ የነበረውን ፍርሃትና ህመም ለመግለጽ አይቻልም፡፡ ከፊቱ ተደፍቼ ብወድቅም ነገር ግን አንዲት ቃል እንኳ ለመናገር አቅሙ አልነበረኝም:: ከዚያ አስፈሪ መኮሳተር ለመሸፈንና ለመደበቅ ምንኛ ናፈቅኩ! እነዚያ የጠፉት «ተራሮቹንና ዐለቶቹንም በላያችን ውደቁ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቁጣ ሰውሩን» በማለት ሲያለቅሱ የሚኖራቸውን ስሜት በመጠኑም ቢሆን ማስተዋል የቻልኩ ይመስለኛል፡፡ EWAmh 56.1

    ወዲያውኑ መልአኩ ከወደቅኩበት ካነሳኝ በኋላ ዓይኖቼ የተመለከቷቸው ነገሮች መገለጽ የማይቻሉ ዓይነት ነበሩ፡፡ ጸጉራቸው የተንጨባረረ፣ ልብሶቻቸው የተቦጫጨቁ፣ ተስፋ የቆረጡና በእጅጉ አስፈሪ ገጽታ ያላቸው ሰዎች ከፊቴ ቀረቡ፡፡ ወደ እኔ በመጠጋት ልብሶቻቸውን እያወለቁ በእኔ ልብስ ላይ ኣሹት፡፡ ወደ ልብሶቼ ዘወር ስል በደም ተበክለው ተመለከትኳቸው፡፡ ዳግመኛ እንደ ሞተሰው ሆኜ አስጎብኚዬ ከነበረው መልአክ እግሮች ስር ተዘረርኩ፡፡ አንድ እንኳ ምክንያት ማቅረብ አልቻልኩም ነበር ምላሴ አንዳች ነገር ለመተንፈስ እምቢ አለ፡፡ እኔም ከእንዲህ ያለው የተቀደሰ ስፍራ ለመራቅ ናፈቅኩ፡፡ ነገር ግን መልአኩ እንደገና በእሮቼ ካቆመኝ በኋላ እንዲህ አለኝ «ይህ የአሁኑን የአንቺን ሁናቴ የሚያሳይ ገጽታ ሳይሆን ነገር ግን ትዕይንቱ በፊትሽ እንዲያልፍ የሆነበት ምክንያት ለሌሎች እንድትነግሪ ጌታ የገለጸልሽን ነገር ከመናገር ችላ ካልሽ፧ ሁናቴሽ የግድ ወደዚያው የሚያመራ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ነገር ግን እስከ መጨረሻው ታማኝ ከሆንሽ የህይወትን ዛፍ ፍሬ ትበያለሽ ከህይወት ወንዝ ውሃም ትጠጫለሽ፡፡ ብዙ ሥቃይ ሊደርስብሽ ቢችልም ነገር ግን የጌታ ጸጋ ይበቃሻል፡፡ አስፈሪ ቁጣውን ሳይሆን ነገር ግን የእርሱን ይሁንታ አገኝ ዘንድ ጌታ እንዳደርግ ሊጠይቀኝ የሚችላቸውን ነገሮች ሁሉ ለማድረግ የፈቃደኝነት ስሜት ተሰማኝ:፡፡ EWAmh 56.2

    ከመንፈሳዊነት የተለየ አመለካት የሚጋራ አስተምህሮ አላት ተብዬ በተደጋጋሚ በሐሰት ተከስሻለሁ፡፡ የ Day-Star ህትመት ዋና አዘጋጅ ከንቱ ስሜት ውስጥ ከመግባቱ አስቀድሞ ስለ መንፈሳዊ አመለካከት አቋሞች በማስተማር ዙሪያ በእርሱና በሌሎች አማካኝነት በመንጋው ላይ ስለሚፈጠሩ አሳዛኝና ውድመት የሚያስከትሉ ውጤቶች ጌታ ራእይ ሰጠኝ፡፡ ተወዳጁን ሰብዓዊ የሱስ በተደጋጋሚ አይቼዋለሁ:፡፡ አባቱ ልክ እንደ እርሱ ዓይነት አካልና ተመሳሳይ ቅርጽ እንዳለው ጠይቄዋለሁ የሱስም «እኔ ከአባቴ ጋር አንድ አምሳል ነኝ በማለት ነግሮኛል፡፡ EWAmh 57.1

    የመንፈሳዊ አመለካከት አቋም መላውን ሰማያዊ ክብር ጠራርጎ በመውሰድ በብዙዎች አእምሮ የዳዊት ዙፋንና ተወዳጁ የየሱስ ስብእና በስፕሪቹዋሊዝም እሳት ውስጥ እንዲቃጠሉ መደረጋቸውን በተደጋጋሚ ተመልክቻለሁ፡፡ ተታልለው ወደዚህ ስህተት ውስጥ የገቡ አንዳንዶች ወደ እውነት ብርሃን እንዲወጡ ቢደረጉም ነገር ግን ከስፕሪቹዋሊዝም መታለል ሙሉ ለሙሉ ለመውጣተፈጽሞ የማይቻል ዓይነት መሆኑን ተመልክቻ ለሁ፡፡ እነርሱ ስህተታቸውን ተናዘው ለዘላለም ፊታቸውን ይመልሱ ዘንድ ጥንቃቄና ዘዴ የተሞላው ሥራ መሥራት ይጠይቃል፡፡ EWAmh 57.2

    ውድ ኣንባቢዬ- የእግዚአብሔርን ቃል የእምነትዎ መመሪያና ተግባር አድርገው ይጠቀሙት ዘንድ ልመክርዎ እወዳለሁ፡፡ እኛ የምንዳኘው በአምላካዊው ቃል ነው፡፡ እግዚአብሔር በመጨረሻዎቹ ቀናት” በቃሉ አማካኝነት ራእዮቹን ሊሰጠን ቃል ገብቶልናል፡፡ ይኸውም አዲስ ዓይነት የእምነት ሕግ ሳይሆን ነገር ግን ሕዝቡን ለማጽናናትና ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት የሳቱትን ለማረም ነው፡፡ ጴጥሮስ አይሁድ ወዳልሆኑ ሕዝቦች በመሄድ ይሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ተዋውሎ ነበር:: EWAmh 57.3

    ይህችን መጽሐፍ ለምታሰራጩ እንደ ማሳሰቢያ ልናገር የምወደው ነገር ቢኖር መልእክቱ የተዘጋጀው ከልብ ለሚወስዱት ብቻ እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ በሆነት ነገሮች ላይ ለሚሳለቁ አለመሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ EWAmh 57.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents