Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    58—ቤተ መቅደሱ

    የእግዚአብሔር ሐዝቦች ተስፋ ባደረጉት ጊዜ የሱስን ማየት ባለመቻ ላቸው የደረሰባቸውን ከፍ ያለ ኃዘን ተመልክቼ ነበር፡፡ እነዚህ ህዝቦች ትንቢታዊው ጊዜ ገና አለማለቁን የሚያሳይ መረጃ ማየት ባለመቻላቸው አዳኛቸው ያልመጣበትን ምክንያት ማወቅ አልቻሉም ነበር፡፡ መልአኩ እንዲህ አለ «የእግዚአብሔር ቃል ይወድቃል? እግዚአብሔር የገባውን ቃል መጠበቅ የሚሳነው አምላክ ነው? በፍጹም! እርሱ ቃል የገባውን ሁሉ ይፈጽማል፡፡ የሱስ የሰማያዊውን መቅደስ---የቅዱሱን በር ከዘጋ በኋላ መቅደሱን ለማንጻት የቅደስተቅዱሳኑን በር ከፍቶ ገባ:፡፡ በትዕግሥት የሚጠባበቁ ሁሉ ምስጢሩን ያስተውላሉ፡፡ በሰው በኩል ስህተት ቢገኝም ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አንዳችም እንከን አይኖረም፡፡ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይሆናል ባለው መሰረት እውን ሆነ፡፡ ሰዎች ግን ምድርን እንደ መቅደስ አድርገው በማመን በትንቢታዊ ጊዜያቶቹ መጨረሻ ላይ ትነጻለች ብለው ስህተት ሠሩ: እውን ሳይሆን የቀረው ሰብዓዊው እንጂ አምላካዊው ተስፋ አልነበረም:!» EWAmh 183.1

    መላእክት በኃዘን ውስጥ የነበሩትን ወገኖች አእምሮ የሱስ መቅደሱን ለማንጻትና ለእስራኤል ልዩ ስርየት ለማምጣት ወደ ገባበት ወደ ቅድስተቅዱሳኑ ይመሩ ዘንድ ላካቸው፡፡ የሱስ ባለበት ስፍራ ላይ የሚያገኙት ሁሉ ሊሠራ ያለውን ሥራ እንደሚያስተውሉ ለመላእክቱ ነግሮአቸው ነበር፡፡ የሱስ በቅድስተቅዱሳን ቆይታው ለየሩሳሌም ባሏ እንደሚሆን ተመልክቻ ለሁ: በቅድስተቅዱሳን የሚሠራው ሥራ ፍጻሜ ካገኘ በኋላ በንጉሣዊ ኃይሉ በምድር በመገለጥ በትዕግሥት ሲጠባበቁት የነበሩትን የከበሩ ልጆቹ ወደ እርሱ ይወስዳቸዋል፡፡ EWAmh 184.1

    ትንቢታዊ ጊዜያቶቹን ተከትሎ በ1844 ላይ በሰማይ ምን እንደተከሰተእንድመለከት ተደርጌ ነበር የሱስ በቅዱሱ ክፍል የነበረውን አገልግሎት ፈጽሞ የዚህን ክፍል በር እንደዘጋ የምጽአቱን መልእክት ሰምተው በተቃወሙት ላይ ታላቅ ጽልመት በማጥላቱ የሱስ ከእይታቸው ተሰወረ: በዚያን ጊዜ የሱስ የከበረውን ልብሰ ተክኅኖ ለብሶ ነበር፡፡ በዘርፋፋው መጎናጸፊያው ዙሪያ ደወልና የሮማን ፍሬ ነበር፡፡ የደረት መታጠቂያው ቁልቁል ከትከሻዎቹ ተንዠርጎ ወርዶ የነበረ ሲሆን፤ በሚንቀሳቀስ ጊዜ ይህ እንደ ዕንቁ የሚያብረቀርቅ መታጠቂያ በላዩ ላይ የተጻፈ ወይም የተቀረጸ የሚመስለውን ስም እያጎላ ያሳይ ነበር፡፡ በአናቱ ላይ ዘውድ የሚመስል ነገር ይታያል፡፡ የሱስ ሙሉውን ልብስ ተክህኖ ለብሶና በመላእክት ታጅቦ በእሳት ሰረገላ ወደ ሁለተኛው መጋረጃ አልፎ ገባ፡፡ EWAmh 184.2

    የሰማያዊውን መቅደስ ሁለቱን ክፍሎች እንደመለከት ተደርጌ ነበር፡፡ መጋረጃው ወይም በሩ ተከፍቶ ስለነበር እንድገባ ፈቃድ አገኘሁ:: በመጀመሪ ያው ክፍል መቅረዙን ከሰባት መብራቶች ጋር፣ የሕብስቱን ማስቀመጫ ጠረጴዛ፣ የዕጣን መሰዊያ እንዲሁም ጥና ተመለከትኩ፡፡ በዚህ ክፍል የነበሩት ቁሶች በሙሉ ከንጹህ ወርቅ የተሠሩ ያህል ወደ ስፍራው የገባውን ምስል ያንጸባርቃሉ፡፡ ሁለቱን ክፍሎች የለየው መጋረጃ ቀለምም ሆነ የተሠራበት ነገር የተለየና የሚያምር ዘርፍ ያለው ከመሆኑ በተጨማሪ በላዩ ላይ መላእክቱን የሚወክል ከወርቅ የተቀረጹ ምስሎች ነበሩበት፡፡ መጋረጃው ተገለጠና ወደ ሁለተኛው ክፍል ስመለከት ታቦቱን አየሁ:: ታቦቱ ከንጹህ ወርቅ የተሠራ ይመስል ነበር፡፡ በታቦቱ አናት ዙሪያ ዘውዶችን የሚወክል ውብ ሥራ ይስተዋል ነበር፡፡ በታቦቱ ላይ አሥሩን ትእዛዛት የያዙ ገበታዎች ነበሩ፡፡ EWAmh 184.3

    በሥርየት መክደኛው ዳርና ዳር ላይ ሁለት ተወዳጅ ኪሩቤል ሁለቱንም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት ተነካክተው በሥርየት መክደኛው ፊት ከቆመው የሱስ አናት ላይ ሆነው ይታያሉ፡፡ እርስ በርሳቸው ተይዩ በመሆን ፊታቸውን ቁልቁል ወደ ሥርየት መክደኛው ማድረጋቸው አምላካዊውን ሕግ በብርቱ ፍላጎት የሚመለከቱትን የመላእክት ሠራዊት ይወክላል፡፡ በኪሩቤል መካከል ከወርቅ የተሠራ ጥና የነበረ ሲሆን በእምነት የሚቀርበው የቅዱሳኑ ጸሎት ወደ የሱስ ሲመጣና እርሱ ደግሞ በአባቱ ፊት ይዞት ሲቀርብ በጣም የሚያምሩ ቀለማት ያሉት የሚመስል ግሩም መዓዛ ያለው ደመና ከዕጣኑ ላይ ይነሳ ነበር የሱስ ቆሞበት ከነበረው ከታቦቱ በፊት ከፍ ብሎ በሚገኘው ስፍራ ላይ ልመለከተው ያልተቻለኝ በከፍተኛ ክብር የተሞላ የእግዚአብሔር ዙፋን ያለበትን የሚመስል ብርሃን ነበር ሲወጣ ድንቅ የሆነ ክብር ከዙፋኑ ወደ የሱስ ይመጣ ነበር የመጣው ክብር ከእርሱ ላይ በመነሳት ጸሎታቸው እንደ መልካም የዕጣን መዓዛ ወደ መጣው ላይ ይፈስ ነበር በየሱስ ላይ የተትረፈረፈ ብርሃን በማ ረፍ የሥርየት መክደኛውን በመሸፈን እንደ ሰንሰለት የተያያዘ ክብር ቤተቅደሱን ሞላው፡፡ ይህን በእጅጉ ያንጸባርቅ የነበረ ብርሃን ትክ ብዬ መመልከት አልቻልኩም ነበር፡፡ እንዲህ ያለውን ክስተት ቋንቋ ሊገልጸው አይችልም:: ባየሁት ነገር በእጅጉ በመደነቅ ከዚያ ንጉሣዊና ባለ ግርማ ትዕይንት ላይ ዐይኖቼን አነሳሁ:EWAmh 184.4

    እንዲሁም ሁለት ክፍል የነበረውን ምድራዊ መቅደስ ተመልክቼ ነበር፡፡ ይህ ከሰማያዊው ጋር ተመሳሳይነት ያለው መቅደስ የሰማያዊው ምሳሌ መሆኑ ተነግሮኝ ነበር በምድራዊው መቅደስ የመጀመሪያው ክፍል የነበረው ቁሳቁስ ከሰማያዊው የመጀመሪያ ክፍል ጋር ተመሳሳይ ነበር መጋረጃው ተገልጦ በቅድስተቅዱሳኑ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ስመለከት እነርሱም እንዲሁ ከስማያዊው ጋር ተመሳሳይ ነበሩ፡፡ ቄሱ በሁለቱም ምድራዊ ክፍሎች አገልግሎት ይሰጥ ነበር፡፡ አገልጋዩ በመጀመሪያው ክፍል ላይ በየዕለቱ አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በላዩ ተላልፎ የነበረውን ኃጢአት ለማንጻት ወደ ቅድስተቅዱሳኑ ይገባ የነበረው በዓመት አንድ ጊዜ ነበር፡፡ የሱስ በሁለቱም ሰማያዊ መቅደስ ክፍሎች ያገለግል እንደነበር ተመልክቻ ለሁ፡፡ ቀሳውስቱ ለኃጢአት ሥርየት የሚውለውን የእንስሳ ደም ይዘው ወደ ምድራዊው መቅደስ ይገቡ ነበር፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ ወደ ሰማያዊው መቅደስ የገባው መስዋዕት የሆነውን የራሱን ደም ይዞ ነው፡፡ እነዚህ ምድራዊዎቹ ቀሳውስት ከአገልግሎት በሞት ስለሚለዩ አገልግሎታቸው እስከ መጨረሻው ቀጣይነት አልነበረውም፡፡ የየሱስ ካኅንነት ግን ዘላለማዊ ነው፡፡ የእስራኤል ልጆች በምድራዊው ቤተመቅደስ አገልግሎት ይቀርቡ በነበሩ መስዋዕቶችና ስጦታዎች አማካኝነት የሚመጣውን አዳኝ እንዲጠባበቁ ሆነው ነበር፡፡ ለአምላካዊው ጥበብ ምስጋና ይግባውና የሱስ በሰማያዊው መቅደስ እየሠራ ወጓለው ሥራ በመመልከት እናስተውለው ዘንድ እነሆ እያንዳንዱ ተግባር በዝርዝር ተሰጠን፡፡ EWAmh 185.1

    የሱስ በቀራኒዮ መስቀል ላይ በሞተጊዜ ተፈጸመ ብሎ ሲጮኽ የቤተመቅደሱ መጋረጃ ከላይ ወደ ታች ለሁለት ተቀደደ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የምድራዊው ቤተመቅደስ አገልግሎት ለዘላለም ማብቃቱን ለማሳየትና Áግዚአብሔር ከዚህ በኋላ ቀሳውስቱን በምድራዊው ቤተመቅደስ አገልግሎታቸው እንደማይገናኛቸው ለመግለጽ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት በራሱ በየሱስ አማካኝነት በሰማያዊው ቤተመቅደስ የሚቀርበው ደሙ ፈሰሰ፡፡ ቄሱ ምድራዊውን መቅደስ ለማንጻት በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተቅዱሳኑ እንደሚገባ ሁሉ የሱስም በዳን. ምዕ. 8 መሰረት በ2300 ቀናት መጨረሻ ላይ ቤተመቅደሱን በማንጻት በእርሱ አማላጅነት ተጠቃሚ ለሚሆኑት ሁሉ የመጨረሻውን ሥርየት ለማምጣት ወደ ሰማያዊው ቅድስተ ቅዱሳን ገባ፡፡EWAmh 186.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents