Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    2—የመጀመሪያው ራእዬ

    የዳግም ምጽአቱ ተከታይ ሕዝቦች ወደ ቅድስት ከተማ ስለሚያደርጉት ጉዞና የጌታቸውን መመለስ ለሠርጉ ለሚጠባበቁት ስለሚሰጣቸው ታላቅ ሽልማት---እግዚአብሔር በገለጠልኝ ነገር ዙሪያ አጠር ያለ ግንዛቤ ማስጨበጡ የእኔ ኃላፊነት ሊሆን ይችላል፡፡ የእግዚአብሔር ውድ ቅዱሳን በብዙ ፈተና ውስጥ ማለፍ ነበረባቸው፡፡ ሆኖም ለጊዜውም እንኳ በእኛ ላይ የደረሱብን ቀለል ያሉ ሥቃይና እንግልቶች ወደፊት እንድንገፋና ዘላለማዊ ክብሩን እንድናይ የሚበጁን ነበሩ፡፡ በዐይን የሚታየው ጊዜያዊና ኃላፊ እንደመሆኑ ትኩረታችን ወደ ማይታየውና ዘላለማዊ ወደሆነው ነበር፡፡ መላው የእስራኤል ጉባዔ ካሌብንና ኢያሱን በድንጋይ ሊወግሯቸው እንደ ነበር (. 14:10) እኔንም በብዙዎች ሊያስወግረኝ የሚችል መልካም ዘገባና ጥቂት የወይን ዘለላዎች ከሰማያዊው ከነዓን ይዤ ለመምጣት ሞክሬ ነበር፡፡ ምድሪቱ አምላካዊ በመሆንዋ ወደዚያ ተጉዘን በሚገባ ልንወርሳት እንደምንችል በጌታ ላላችሁ ወንድምና እህቶቼ ይፋ ላደርግ እወዳለሁ፡፡ EWAmh 8.1

    በቤተሰባዊው የጸሎት መስዊያ ስፍራ እየጸለይኩ ሳለ መንፈስ ቅዱስ ወ ረደብኝና ወደ ላይ ከፍ ከፍ እያልኩ ከጨለማው ዓለም እርቄ ተጓዝኩ፡፡ በዓለም ወዳሉት የዳግም ምጽአቱ ተጠባባቂ ሕዝቦች ለመመልከት ዘወር ብል ላገኛቸው አልቻልኩም ነበር፡ ሆኖም አንድ ድምè «ትንሽ ወደ ላይ ከፍ አድርገሽ ደግመሽ ተመልከቺ” አለኝ፡፡ እኔም ዐይኖቼን ከፍ አድርጌ ስመለከት ከምድር ሽቅብ ወደ ላይ የሚወጣ ቀጥ ያለ ጠባብ መንገድ ተመለከትኩ፡፡ አድቬንቲስቶች በዚህ ከጎዳናው መጨረሻ ላይ ወደምትገኘ ከተማ እየተጓዙ ነበር፡፡ ከእነርሱ ኋሳ በመንገዱ መጀመሪያ ላይ የበራላቸው ብሩህ ብርሃን የነበረ ሲሆን ይህንንም መልአኩ የእኩለ ሌሊቱ ጩኸት ነው ብሎ ነግሮኛል:፡ ይህ ብርሃን በመላው መንገዱ ላይ ፍንትው ብሎ ይበራ ስለነበር መደናቀፍ እንዳይገጥማቸው ለእግራቸው ብርሃን ሆኗቸው ነበር፡፡ ዐይኖቻቸውን ከፊት ለፊታቸው ሆኖ ወደ ከተማዋ በሚመራቸው የሱስ ላይ በሚያሳርፉ ጊዜ ደኅነት ይሰማቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ቀደም ብለው ወደ ከተማዋ እንደሚገቡ ጠብቀው የነበር አንዳንዶች ብዙም ሳይቆዩ ድካም እየተሰማቸው በመምጣት ከተማዋ እሩቅ ናት ማለት ጀመሩ፡፡ ከዚያም የሱስ ባለ ግርማውን ቀኝ እጁን ከፍ አድርጎ ሲያበረታታቸው ከእጁ ብርሃን በመውጣት በእነዚህ ሕዝቦች ላይ ተውለበለበ እነርሱም «ሐሌሉያ!» በማለት ጩኸታቸውን አሰሙ፡፡ ሌሎቹ ግን ከበስተኋላቸው ያለውን ብርሃን በጭፍን በመካድ እስከዚህ ድርስ የመራቸው እግዚአብሔር አለመሆኑን ተናገሩ፡፡ ከዚያም ከበስተኋላቸው የነበ ረው ብርሃን እግሮቻቸውን ፍጹም ለሆነው ጨለማ ትቶ ተሰወረ፡፡ አነርሱም በጨለማው እየተደነባበሩ ምልክቱንና የየሱስን ምስል በመሳት ከጎዳናው ውጪ ወዳለው ጽልመትና እርክስና ወደቁ፡፡ ወዲያውም የየሱስን ዳግም ምጽአት ቀንና ሰዓት የሰጠንን፤ እንደሚፈሱ ውሖች የሚወርደውን የአግዚአብሔር ድምፅ ሰማን፡፡ ኃጥአን የሰሙትን ነገር መብረቅና የመሬት መንቀጥቀጥ ነው ብለው ሲያስቡ ነገር ግን ቁጥራቸው 144 ሺህ የሆነው ሕያዎቹ ጻድቃን ድምፁን ያውቁት ነበር---አስተውለውትማል፡ እግዚአብሔር በተናገረ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን አፈሰሰብን፡፡ ሙሴ ከሲና ተራራ ሲወርድ እንደተስተዋለበት የእኛም ፊት ማብራት ጀመረ፡፡ በእግዚአብሔርም ክብር አንጸባረቀ:: EWAmh 8.2

    144 ሺህዎቹ በሙሉ ታትሞባቸውና ከእርሱ ጋር ፍጹም አንድነት ፈጥረው ነበር በግንባሮቻቸው ላይ እግዚአብሔር እንዲሁም አዲሲቱ የሩሳሌም የሚልና የየሱስን አዲስ ስም የያዘ ባለ ግርማ ኮከብ ተጽፎ ነበር፡፡ ኃጥአን በእኛ ደስተኛና ቅዱስ ስሜት በቁጣ በመገንፈል በጸንፈኝነት ወኅኒ ሊወ ረውሩን እጆቻቸውን ዘረጉ፡፡ እኛም በጌታ ስም እጆቻችንን ወደ እነርሱ ስንዘ ረጋ ርዳታቢስ ሆነው መሬቱ ላይ ይዘረሩ ነበር፡፡ አንዳችን የሌላውን እግር የምናጥበውንና በተቀደሰ አሳሳም ለወንድሞች ሰላምታ የምናቀርበውን እኛን እግዚአብሔር እንደወደደን የሰይጣን ማኅበር አውቆአል EWAmh 9.1

    ብዙም ሳይቆይ ዐይኖቻችን ወደ ምሥራቅ በማቅናት ትንሽና ጥቁር ደመና ብቅ ሲል ተመለከትን፡፡ ይህ የሰውን እጅ ግማሽ ያህል መጠን ያለው ደመና የሰው ልጅ መምጣት ምልክት መሆኑን ሁላችንም አውቀናል፡፡ ደመናው እየቀረበ ሲመጣ ሁላችንም ግርማ ባለው ጸጥታ ደመናውን አፍጥጠን ተመለከትነው፡፡ ትንሹ ደመና ግዙፍና ነጭ እስኪሆን ድረስ ክብሩ እየጨመረ ይሄድ ጀመር ከወደ ስሩ ላይ እንደሚንበለበል እሳት ሆኖ ሲታይ፧ ደመናው ላይ ቀስተደመና አርፎበት ነበር፡፡ አሥር ሺህ መላእክት ዙሪያውን ከበውት በእጅጉ ተወዳጅ መዝሙር ይዘምሩ የነበረ ሲሆን በላዩ ላይ ደግሞ የሰው ልጅ ተቀምጦአል፡፡ ነጭ የተጠቀለለ ጸጉሩ በትከሻዎቹ ላይ ዘንፈል ብሎአል፡፡ በዐናቱ ላይ ደግሞ ብዙ ዘውዶች ነበሩ እግሮቹ የሚንበለበል እሳት ይመስሉ ነበር፧ በቀኝ እጁ ስለታማ ማጭድ በግራ እጁ ደግሞ ብርማ ቀለም ያለው መለከት ይዞአል: ልጆቹን ከዳር እስከ ዳር የሚመለከቱት ዐይኖቹ የአሳት ነበልባል ይመስሉ የነበር፡፡ ከዚያም የሁሉም ፊት ብሩህ ገጽታ ይዞ በአንድ ሲሰበሰቡ በእግዚአብሔር ነቀፌታ የደረሰባቸው ግን ጥቀርሻ መስለው በአንድ ተከማቹ ከዚያም ሁላችንም «በፊቱ መቆም የሚችለው ማን ነው? የለበስኩት መጎናጸፊያ እንከን ዐልባ ነው?” በማለት ጩኸታችንን አሰማን፡፡ ወዲያውም መላእክት ዝማሬአቸውን በማቆም አስፈሪ ጸጥታ የነገሠበት ጊዜ ተስተዋለ፡፡ ነገር ግን የሱስ «ንጹህ እጆችና ልቦች ያሏቸው መቆም ይችላሉ---ጸጋዬ ይበቃችኋል» ብሎ ሲናገር ፊታችን አበራ ልባችንም በደስታ ተሞላ፡፡ ደመናው ከበፊቱ ይበልጥ ወደ ምድር እየተቃረበ በመጣበት በዚያን ወቅት መላእክት አቁመውት የነበረውን ዝማሪ ከበፊቱ ከፍ ባለ ድምፅ አንደገና ማሰማታቸውን ቀጠሉ፡፡ EWAmh 9.2

    የሱስ በሚንበለበል እሳት ተከብቦ ወደ ምድር እየወረደ ሳለ ያ የእርሱ ብርማ መለከት ድምፅ ተሰማ፡፡ በመቃብር አንቀላፍተው ወዳሉት ቅዱሳን መልከት አደረገና 0ይኖቹንና እጆቹን ወደ ሰማይ በማንሳት «በመቃብር ያንቀላፋችሁ ንቁ! ንቁ! ንቁ!” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡ ከዚያም ብርቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፡፡ መቃብሮች ተከፈቱ፣ ሞተው የነበሩም የማይሞተውን ለብሰው ተነሱ፡፡ 144 ሺህዎቹ በሞት የተለዩአቸውን ወዳጆቻ ቸውን ለይተው በማወቅ «ሐሌሉያ! ሲሉ ታላቅ ድምፅ አሰሙ፡፡ በዚያው ቅጽበት እኛ ሁላችን በመለወጥ ከእነርሱ ጋር በአንድ ላይ ጌታን በአየር ለመገናኘት ተነጠቀን:: EWAmh 10.1

    እኛ ሁላችን በአንድ ላይ በደመናው ውስጥ በመግባት ለሰባት ቀናት ወደ ብርጭቆው ባህር ወጣን:፡፡ ከዚያም የሱስ ዘውዶች ይዞ በመምጣት በቀኝ እጁ በአናቶቻችን ላይ ደፋልን፡፡ የወርቅ በገናዎችንና የድል አድራጊነት---የዘንባባ ዝንጣፊዎችን ሰጠን፡፡ በዚህ የብርጭቆ ባህር ላይ 144 ሺህዎቹ ፍጹም በሆነ አራት መአዘን ቅርጽ ቆመዋል፡፡ አንዳንዶቹ በጣም ደማቅ ዘውዶች የነበሯቸው ሲሆን የሌሎቹ ደግሞ ደብዘዝ ያሉ ነበሩ: አንዳንዶቹ ዘውዶች በከዋክብት ብዛት ክብደት የተሞሉ ሲሆን የሌሎቹ ከዋክብት ደግሞ ጥቂት ነበሩ፡፡ ሁሉም በነበሯቸው ከዋክብት ፍጹም አርካታ ተጎናጽፈው የነበ ረ ሲሆን፤ ከትከሻቸው እስከ እግሮቻቸው ድረስ ግርማ ያለውን መጎናጸፊያ ለብሰው ነበር፡፡ በብርጭቆው ባህር ላይ እየተራመድን ወደ ከተማዋ መግቢያ በራፍ ስናመራ መላእክት ከበውን ነበር የሱስ ኃያልና ባለግርማ ክንዱን አንስቶ ያንን የተንቆጠቆጠ በራፍ በመክፈት «ልብሶቻችሁን በደሜ በማጠባችሁና ለእውነትም በጽናት በመቆማችሁ---እነሆ ግቡ» አለን፡፡ እኛም ሁላችን ወደ ውስጥ በማለፍ ከተማዋ የመግባት ፍጹም ባለ መብት እንደነበረን ተሰማን፡፡ EWAmh 10.2

    በዚህ ስፍራ የህይወትን ዛፍና የእግዚአብሔርን ዙፋን ተመከትን፡፡ ከዙፋኑ ንጹህ የወንዝ ውሃ ይወጣ የነበረ ሲሆን በሁለቱም የወንዙ ዳርቻ ላይ የህይወት ዛፍ ነበር፡፡ በሁለቱም የወንዙ ዳርቻ የዛፍ ግንዶች የነበሩ ሲሆን እነዚህ ሁለቱም በውስጣቸው አሳልፈው የሚያሳዩ ንጹህ ወርቅ ነበሩ፡፡ በመጀመሪያ ላይ ሁለት ዛፎች ያየሁ መስሎኝ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደገና ደግሜ ስመለከት ከዐናታቸው አንድ ዛፍ ሆነው ተዋህደዋል፡፡ በዚህ መልኩ የህይወት ዛፍ በሁለቱም የወንዙ ማዶ ይገኝ ነበር፡፡ እኛ በነበርንበት ስፍራ ላይ የዛፉ ቅርንጫፎቸ ወደ ታች ተንዠርግገው የነበረ ሲሆን የዛፉ ፍሬ ግሩም፣ መልኩ ደግሞ የወርቅና ብር ቅልቅል ይመስል ነበር፡፡ EWAmh 11.1

    ሁላቸንም ወደ ዛፉ ግርጌ በማምራት የስፍራውን ግርማ ሞገስ ለመመልከት አረፍ አልን፡፡ የመንግሥትን ወንጌል ስብከው የነበሩትና እግዚአብሔር እነርሱን ለማዳን በመቃብር ያሳረፋቸው ወንድም ፊች እና ስቶክማን ወደ እኛ በመምጣት እነርሱ ባንቀላፉበት ወቅት ስላለፍንበት ሁኔታ ጠየቁን፡፡ የደረሰብንን ታላቅ መከራ ለማስታወስ ብንሞክርም ነገር ግን ያንን ተከትሎ ዙሪያችንን ከከበበን ዘላለማዊ ክብር ክብደት ጋር ሲነጻጸር ይህ ነው ብለን ለመናገር ከአንደበታችን ልናወጣው ባለመቻላችን «ሐሌሉያ ሰማይ ውድ አይደለም!» ብለን በመጮኽ ባለ ግርማ በገናዎቻችንን በመንካት የሰማያዊውን ዝማሬ ድምጽ አወጣን፡፡ EWAmh 11.2

    የሱስ ከበላያችን እንደሆነ ሁላችንም ከከተማዋ ቁልቁል ወደዚህች ምድር ወረድን፡፡ የሱስን መሸከም ያልቻለው ግዙፍና ኃያል ተራራ እርስ በርሱ ተለያየ፡፡ ከዚያም እጅግ የተንጣለለ ሜዳ ነበር፡፡ ቀና ብለን አሥራ ሁለት መሰ ረቶችና አሥራ ሁለት በሮች ያሏትን ታላቋን ከተማ ተመለከትን፡፡ ከተማዋ በአራቱ የተለያዩ አቅጣጫዎች ሦስት ሦስት በሮች የነበሯት ሲሆን በእያንዳንዱ በር ላይ አንድ መላእክ ነበር: በዚህን ጊዜ ድምጻችንን ከፍ ኣድርገን «ከተማዋ፣ ታላቋ ከተማ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደች» ብለን ጮኽን፡፡ ከተማዋ እኛ የነበርንበት ስፍራ ላይ ስትደርስ ጸናች፡፡ ከዚያም ከከተማዋ ውጪ የነበሩትን ባለ ግርማ ነገሮች መመልከት ጀመርን:: እያንዳንዳቸው አራት ምሰሶዎች ያሏቸው፣ ብርማ መልክ የሚስተዋልባቸውና እጅግ በከበሩ ሉሎች ያሸበረቁ ውብ ቤቶችን ተመለከትኩ፡፡ እነዚህ ቤቶች የቅዱሳን መኖሪያ የነበሩ ሲሆን እያንዳንዳቸው የወርቅ መደርደሪያዎች ነበሯቸው፡፡ አብዛኞቹ ቅዱሳን ወደየቤቶቻቸው በመግባት አብረቅራቂ ዘውዶቻቸውን ከአናቶቻቸው ላይ እያነሱ በመደርደሪያቸው ላይ በማስቀመጥ ለሥራ ወደ ውጪ ሲወጡ ተመለከትኩ፡፡ በእርግጥ እነርሱ በምድሪቱ ላይ የሚሠሩት ሥራ እኛ ከምንሠራው ጋር ፈጽሞ አንድ አይደለም: ግርማ የተሞላ ብርሃን በሁሉም ዐናቶች ላይ ያንጸርቅ የነበ ረ ሲሆን እነርሱም ያለማቋረጥ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀርቡ ነበር፡፡ EWAmh 11.3

    በሁሉም ዓይነት አበቦች የተሞላ ሌላ መስክ ተመለከትኩ፡፡ አበቦቹን ቀጠፍኳቸውና «ፈጽሞ አይጠወልጉም!» ብዬ ድምጼን ከፍ አድርጌ ጮኽኩ፡፡ በመቀጠል በረጃጅም ሣሮች የተሞላ መስክ አየሁ፡፡ ይህ ህያው አረንጓዴ ሆኖ የብርማና ወርቅማ ነጸብራቆች የሚስተዋሉበት ሣር ለንጉሡ የሱስ ክብር በኩራት ይዘናጠፍ ነበር ከዚያም በሁሉም ዓይነት የዱር አራዊቶች ወደተሞላው መስክ ገባንአንበሳ፣ የበግ ግልገል፣ ነብር እና ተኩላ ሁለም ፍጹም በሆነ ህብረት በአንድ ላይ ነበሩ፡፡ በመካከላቸው አለፍን እነርሱም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከተሉን፡፡ በመቀጠል ወደ ደን ውስጥ ገባን፡፡ ደኑ በምድር ላይ እንዳለው በጨለማ የተዋጠ ዓይነት ሳይሆን በብርሃን የተሞላና ግርማ ሞገስ የተላበስ ነበር የዛፎቹ ቅርንጫፎች ወዲያና ወዲህ ሲወዛወዙ ስንመለከት «አቤቱ በጫካው መሃል በደኅንነት እንኖራለን በደኑ ውስጥም ያለአንዳች ሥጋት እናንቀላፋለን›› በማለት ድምጾቻችንን ከፍ አድርገን ተናገርን፡፡ በዚህ መልኩ በደኑ ውስጥ አልፈን ወደ መንገዳችንየጽን ተራራ አመራን:፡፡ EWAmh 12.1

    በጉዞአችን እንደኛው የስፍራውን ባለ ግርማነት ከሚመለከቱ ቡድኖች ጋር ተገናኘን፡፡ እነዚህ ወገኖች የለበሱት ልብስ ዙሪያውን ቀይ ጥለት ነበ ረው፤ በአናቶቻቸው ላይ አንጸባራቂ ዘውዶች ደፍተዋል መጎናጸፊያቸውም እጅግ ነጭ ነበር፡፡ ሰላምታ እያቀረብንላቸው እነማን እንደሆኑ የሱስን ጠየቅኩት፡፡ የሱስም ለእርሱ የታረዱ ሰማዕታት መሆናቸውን ነገረኝ፡፡ ከእነርሱ ጋር ሊቆጠሩ የማይችሉ እጅግ ብዙ ታናናሾች ነበሩ፡፡ በልብሶቻቸውም ጫፍ ላይ እንዲሁ ቀያይ ጥለት ነበራቸው፡፡ የጽዮን ተራራ ከፊት ለፊታችን የነበረ ሲሆን በዚህ ተራራ ላይ በታላቅ ግርማ የተሞላ መቅደስ ይታያል፡፡ ከእርሱ ብዙም ሳይርቅ በላያቸው ጽጌረዳና ውብ የመስክ አበቦች የበቀሉባቸው ሌሎች ሰባት ተራሮች ነበሩ፡፡ ታናናሾች በእነዚህ ተራሮች ላይ እየወጡ ምርጫቸው ከሆነ ደግሞ አነስተኛ ክንፎቻቸውን እየተጠቀሙ በመብረር አናቶቻቸው ላይ በማረፍ እነዚያን ፈጽሞ የማይጠውልጉ አበቦች ሲቀጥፉ ተመለከትኩ፡፡ የቤተመቅደሱን ዙሪያ በመክበብ ለአካባቢው ሞገስ የሆኑ ሁሉም ዓይነት ዛፎች ነበሩ---ባሕር ዛፍ ፣ጥድ፣ ዘንባባ፣ ባርሰነት፣ ሮማን እንዲሁም የበለስ ዛፍ ተንዠርግገው ይታዩ ነበር፡፡ እኛም ወደ መቅደሱ ልንገባ ስንል የሱስ ተወዳጅ ድምጹን ከፍ አድርጎ «144 ሺህዎቹ ብቻ ወደዚህ ስፍራ ይገባሉ» በማለት ተናገረ---እኛም ሐሌሉያ ብለን ጮኽን፡፡ EWAmh 12.2

    መቅደሱ የቆመው ሙሉ ለሙሉ በውስጣቸው በሚያሳዩ በሰባት የወርቅ ምሰሶዎች ሲሆን፤ ግርማ ባላቸው ሉሎች ተንቆጥቁጦ ነበር: በዚያ የተመለከትኳቸውን አስደናቂ ነገሮች እዲህ ነው ብዬ ልገልጻቸው አልችልም: ምናልባትም በከነዓን ቋንቋ መናገር ብችል ኖሮ ጥቂትም ቢሆን ስለዚህ የተሻለ ዓለም ክብር በተናገርኩ ነበር፡፡ በዚያ ስፍራ የ144 ሺህዎቹ ስም በወርቅ ፊደል የተቀረጸበትን የድንጋይ ገበታ ተመለከትኩ፡፡ የቤተመቅደሱ ክብር ከተሰማን በኋላ የሱስ እዚያው ሲቀር እኛ ግን ወጥተን ወደ ከተማዋ ብንሄድም ነገር ግን ምንም ሳይቆይ ዳግመኛ ተወዳጅ ድምጹን ሰማን «ኑ--- ሕዝቦቼ እናንተፈቃዴን በመፈጸም ስለ እኔ ሥቃይ ተቀብላችሁ ታላቁን መከራ አልፋችሁ መጥታችኋል፡፡ እኔ እራሴ ታጥቄ አስተናግዳችኋለሁ» ብሎ ሲናገር «ሐሌሉያ! ክብር ለአንተ ይሁን!» በማለት ደምጻችንን ከፍ አድርገን በመጮኽ ወደ ከተማዋ ገባን፡፡ ከንጹህ ብር የተሠራ ገበታ ተዘርግቶ ነበር ገበታው ዐይኖቻችን ማየት ከሚችሉት በላይ ብዙ ኪሎ ሜትሮች ርዝማኔ ነበረው፡፡ በገበታው ላይ የህይወትን ዛፍ ፍሬ፣ መና፣ ለውዝ፣ በለስ፣ ሮማን፣ ወይን እንዲሁም ሌሎች ብዙ ፍራፍሬዎችን ተመልክቼ የነበረ ሲሆን፤ ከእነዚህ ፍራፍሬዎች ለመብላት የሱስ ይፈቅድልኝ ዘንድ ጠየቅኩት፡፡ እርሱም «አሁን አይደለም፡፡ የዚህን ምድር ፍራፍሬ የሚበሉ ሁሉ ዳግመኛ ወደ መሬት ተመልሰው አይሄዱም ነገር ግን ታማኝ ከሆንሽ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የህይወትን ፍሬ ትበያለሽ እንዲሁም የሚፈልቀውን ውሃ ትጠጫለሽ” ካለኝ በኋላ ዳግመኛ ወደ ምደር በመሄድ የገለጽኩልሽን መንገር ይኖርብሻል» በማለት አስታወቀኝ፡፡ ከዚያም መልአኩ ወደዚህ ጨለማ ምድር ይዞኝ መጣ፡፡ የምድር ሁኔታ አሰልቺና ህይወት ዐልባ እንደመሆኑ አንዳንዴ እዚህ ምንም ያህል ኣልቆይም ብዬ አስባለሁ:: ያን የተሻለውን ዓለም በመመልከቴ ምድራዊው ኑሮዬ በእጅጉ ብቸኝነት ይሰማኛል፡፡ ምናለ እንደ ርግብ ክንፍ በኖረኝና እዚያ በርሬ ባረፍኩ! EWAmh 13.1

    ራእዩን ተመለክቼ ካበቃሁ በኋላ ሁሉም ነገር የተለወጠ ሆኖ አገኘሁት--- በሁሉም ነገር ላይ ጽልመት ነግሦአል: አቤቱ ይህ ምድር ምንኛ ጨለማ ሆኖ ታየኝ! እራሴን በዚህ ምድር ላይ ባገኘሁት ጊዜ ክፉኛ አነባሁ የሰማያዊው ቤት ፍቆት ህመምም ተሰማኝ፡፡ ያንን የተሻለ ዓለም መመልከቴ ይህን ምድር አረከሰብኝ፡፡ ያየሁትን ራእይ ፖርትላንድ ለነበረው አነስተኛ መንጋችን ነገርኩ እነርሱም ይህ ከእግዚብሔር ለመሆኑ ሙሉ ለሙሉ አምነው ተቀበሉ፡፡ ዘላለማዊው ጽናት በእኛ ላይ ያረፈበት ያ ወቅት በእጅጉ ኃይለኛ ነበር፡፡ ይህ ከሆነ ከአንድ ሣምንት በኋላ ጌታ ላልፍበት ስለሚገባኝ መከራ የሳየኝን ሌላ ራእይ ሰጠኝ፡፡ እርሱ የገለጸልኝን ነገር ለሌሎች መንገር ነበረብኝ፡፡ ይህን በማድረጌ ደግሞ የሚደርስብኝን ከፍ ያለ ተቃውሞ፣ ሥቃይና ሃዘን መጋፈጥ የነበረብኝ ቢሆንም መልአኩ ግን «የእግዚአብሔር ጸጋ ይበቃሻል፤ እርሱ ደግፎ ይይዝሻል” አለኝ፡፡ EWAmh 13.2

    ይህን ራእይ ከተመለከትኩ በኋላ ውስጤ በእጅጉ ተሽበረ፡፡ የጤንነቴ ሁኔታ :ሽቆልቁሎ የነበረ ቢሆንም ዕድሜዬ ግን 17 ነበር፡፡ ብዙዎች እራሳቸውን ከፍ ከፍ በማድረጋቸው ውድቀት እንደረሰባቸው አውቅ ነበር፡፡ እንዲሁም ኣኔም በማንኛውም መልኩ የእነርሱን ፈለግ ብከተል እግዚአብሔር ሊተወኝ እንደሚችልና ያለ ጥርጥር እንደምጠፋ አውቅ ነበር፡፡ በጸሎት ወደ ጌታ በመቅረብ ይህን ሸክም በሌላ ላይ ያደርግ ዘንድ ለመንኩት፡፡ ሁኔታው እኔ መሸከም የማልችለው ዓይነት ነበር የሆነብኝ፡፡ ረዘም ላሉ ጊዜ ያት በጸሎት ተደፍቼ ብቆይም---የሚመጣልኝ ብርሃን ሁሉ «የገለጽኩልሽን ነገር ለሌሎች አሳውቂ» የሚል ነበር፡፡ EWAmh 14.1

    በቀጣይ በተመለከትኩት ራእይ እርሱ የገለጸልኝን መንገሬ የግድ ከሆነ ከውዳሴ ይጠብቀኝ ዘንድ ጌታን በጽናት ለመንኩት፡፡ ከዚያም ጸሎቴ መልስ ማግኘቱን በማሳየት በዚህ ውዳሴ ከንቱ አደጋ ላይ የምወድቅ ከሆነ እጁ በእኔ ላይ እንደሚሆንና ህመም እንደሚደርስብኝ ገለጸልኝ፡፡ ከዚያም መልአኩ «መልእክቱን በታማኝነት ካስተላለፍሽና እስከመጨረሻው በጽናት ከዘለቅሽ የህይወትን ዛፍ ፍሬ ትበያለሽ የህይወትንም ወንዝ ውሃ ትጠጫለሽ” አለኝ፡፡ EWAmh 14.2

    ብዙም ሳይቆይ ራእዮቹ በሰመመን ላይ የመውደቅ ውጤት እንደሆኑ ተደርጎ በመቅረቡ አብዛኛዎቹ አድቤንቲስቶች ይህንኑ ለማመንና ለማሰራጨት ዝግጁነታቸውን ገለጹ፡፡ አንድ ሰመመን ሰጪ ሃኪም የእኔ ራእዮች የሰመን ውጤት መሆናቸውን በመንገር ጉዳዩ ቀላል መሆኑንና እርሱ ራሱ እኔን በሰመመን ላይ በመጣል ራእይ ሊሰጠኝ እንደሚችል ነገረኝ ነገር ግን ሰመመን ከጥልቁ የሚመነጭ የዲያብሎስ መንገድ መሆኑንና የሰመንን መንገድ መቀጠል የሚመርጡ ወደዚያው አቀጣጫ እንደሚያመሩ ጌታ እራሱ በራእይ እንዳሳየኝ ነገርኩት፡፡ በመቀጠል እርሱ በሚለው ዓይነት ሰመመን ላይ ሊጥለኝ ይችል እንደሆነ ነጻነት ሰጠሁት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ከግማሽ ሰዓት በላይ ሙከራ ካደረገ በኋላ አቆመ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር በእምነት የእርሱን ተጽእኖ መቋቋም በመቻሌ በጥቂቱም እንኳ ቢሆን ሊያውከኘ አልቻለም ነበር፡፡EWAmh 14.3

    በጉባዔ መሃል ራእይ ብመለከት ብዙዎች የሆነ ሰው በሰመመን ውስጥ እንደከተተኝ አድርገው መናገር በቻሉ ነበር፡፡ በመሆኑም ከእግዚአብሔር በቀር የማንም ዐይኖችም ሆኑ ጆሮዎች ሊያዩኝ ወይም ሊሰሙኝ በማይችሉት በማይችሉት ደን ውስጥ ብቻዬን በመሄድ ለአርሱ እጸልይ ነበር፡፡ እርሱም አንዳንድ ጊዜ በዚያው እያለሁ ራእይ ይሰጠኝ ነበር በዚህም በእጅጉ በመደሰት ኣንዳችም ሥጋ ለባሽ---ሟች ተጽእኖውን ሊሳርፍብኝ በማይችልበት ሁናቴ ለብቻዬ ሳለሁ እግዚአብሔር የገለጠልኝን ነገር አነግራቸው ነበር ይህም ሆኖ ግን ራሴን በሰመመን ላይ የጣልኩ እንደሆነ ተደርጎ በአንድ ሰው ተነገረኝ፡፡ አምላካዊውን ተስፋ ለመለመንና የአርሱን ደኅንነት የግላቸው ለማድረግ ብቻቸውን በታማኝነት በእግዚኣብሔ ር ፊት የሚቀርቡ በሚያረክሰውና ነፍስን በሚኮንነው የሰመመን ተጽእኖ ስር እንደወደቁ ሆነው መከሰስ ይኖርባቸዋል? በማለት አሰብኩ፡፡ ለመሆኑ ቸር ከሆነው ሰማያዊ አባታችን «ድንጋይ” ወይም «ጊንጥ» ለመቀበል ዳቦ ስጠን ብለን ንጠይቀዋለን? ብዙዎች መንፈስ ቅዱስን አለማመናቸው ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሰዎች የተለማመዷቸው ሁሉ የሰመመን ውጤት ወይም የሰይጣን ማታለያ ነበሩ ማለት ነው---እነዚህ ነገሮች መንፈሴን በማቁሰላቸውና ነፍሴንም ስፋት ባለው ሥቃይ በመጫናቸው ተስፋ ወደ መቁረጡ ተቃረብኩ፡፡ EWAmh 14.4

    በዚህን ወቅት በሜይን አክራሪነት ተነስቶ ነበር፡፡ አንዳንዶች ሙሉ ለሙሉ ሥራቸውን በመተው የእነርሱን አመለካከት ጨምሮ ሌሎች ኃይማኖታዊ ግዴታዎች ናቸው ብለው ያመኑባቸውን ነጥቦች የማይጋሯቸውን በሙሉ ከቤተክርስቲያን አባልነት ሰርዘዋቸው ነበር እግዚአብሔር እነዚህን ስህተቶች በራእይ በመግለጽ እውነቱን እነግራቸው ዘንድ ወደእነዚሁ ልጆቹ ላከኝ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ መልእክቱን ሙሉ ለሙሉ በመቃወም ከዓለም ጋር ስምሙ ነሽ ብለው ሲከሱኝ በተቃራኒው ጥቂት አድቬንቲቶች ደግሞ በአክራሪነት ወንጅለውኝ ነበር: እኔ የተጣመመውን ለማረም በሠራሁ ነገር ግን በአንዳንዶች እንደ ሐሰተኛ፣ ክፉና የአክራሪዎች መሪ ሆኜ ተፈረጅኩ፡፡ የወንድሞችን መገፋፋትና ማነሳሳት ተከትሎ ጌታ ዳግም ይገለጽባቸዋል የተባሉ የተለያዩ ጊዚያት በተደጋጋሚ ተቆርጠው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን እነዚያ ሁሉ ጊዜያቶች እንደሚያልፉ ጌታ አሳይቶኝ ነበር፡፡ ከክርስቶስ ምጽአተ ስቀድሞ የመከራው ጊዜ የግድ መምጣት አለበት፡፡: ደግሞም ይህ እያንዳንዱ ተቆርጦ የነበረና ያለፈ ጊዜ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች እምነት ከማዳከም ውጪ የሚፈይደው አንዳችም ነገር አልነበረም፡፡ በዚህ የተነሳ በልቡ «ጌታዬ ይዘገያል” ካለው ክፉ አገልጋይ ጋር አንድ ናት ተብዬ ተከሰስኩ EWAmh 15.1

    አነዚህ ሁሉ ነገሮች በመንፈሴ ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠራቸውና ግራ መጋባት በማስከተላቸው አንዳንዴ የግል ተሞክሮዬን እስከመጠራጠር ወደ መፈተን ያደርሱኝ ነበር፡፡ የቤተሰብ ጸሎት በሚደረግበት በአንድ ማለዳ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል በላዬ ማረፍ ጀመረ ሆኖም ይህ የሰመመን ውጤት ነው የሚል አስተሳሰብ ወደ አእምሮዬ በመምጣቱ ተከላከልኩ: ከዚያም ወዲያውኑ እንደ ዲዳ በመሆን ለጥቂት ጊዜያት በዙሪያዬ የነበረውን ነገር በሙሉ ሳትኩ፡፡ በዚህን ወቅት የእግዚአብሔርን ኃይል በመጠራጠር የሠራሁትን ኃጢአት ተመለከትኩ፡፡ ያን ማድረጌን ተከትሎ---ደርቆ የነበረው ምላሴ ሃያ አራት ሰዓታት በማይሞሉ ቀጣይ ጊዜያት እየላላ የሚሄድ ዓነት ነበር በካርድ ላይ በወርቅ የተጻፉ ሃምሳ የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፎችና ጥቅሶች በፊቴ ቀርበው በራእይ ከተመለከትኩ በኋላ ነቃሁ: በዚህን ጊዜ በዲዳነቴ መናገር ያልቻልኩትንና ያየሁትን ነገር በጽሑፍ አሰፈርኩ፡፡ ምናለ እጅግ ትልቅ መጽሐፍ ቅዱስ በኖረኝ? ብዬ በመመኘት መጽሐፍ ቅዱስ ወስጄ እነዚያን በካርዱ ላይ የተመለከትኳቸን ጥቅሶች በሙሉ ገልጬ አወጣኋቸው:፡፡ ያን ቀን መናገር ሳልችል ዋልኩ፡፡ ነገር ግን በቀጣዩ ቀን ጠት ምላሴ ተፍታቶ ድምጼን ከፍ አድርጌ ለጌታ ምስጋና ማቅረብ በመቻ ሌ ነፍሴ በደስታ ተፍነከነከች : ከዚህ በኋላ ሌሎች ሊያስቡ እንደሚችሉት ለመጠራጠር ደፍሬም ሆነ የእግዚአብሔርን ኃይል ለአፍታ እንኳ ተከላክዬ አላወ ቅም:: EWAmh 15.2

    በ1846 ላይ በማሳቹሴትስ ፌይርሃቨን ሳለሁ እህቴ (ብዙውን ጊዜ አብራኝ የምትጓዝ) ኤ.፣ ወንድም ጂ. እና እኔ ራሴ በዌስትስ አይላንድ የሚገኙ ቤተሰቦችን ለመጎብኘት በጀልባ ላይ መቅዘፍ ጀመርን፡፡ ጉዞውን የጀመርነው አመሻሹ ላይ ነበር፡፡ በመሆኑም ጥቂት ርቀት ከተጓዝን በኋላ ሳይታሰብ ማዕበል ተነሳ:፡፡ ከፍተኛ የነጎድጓድ ድምፅና ብልጭታ እንዲሁም ዶፍ በላያችን ይወርድ ጀመር፡፡ በወቅቱ እግዚአብሔር ካልታደገን በቀር የመጥፋታችን ነገር በጉልህ የሚታይ ነበር፡፡ EWAmh 16.1

    ወዲያው በጀልባዋ ውስጥ ተንበርክኬ ጌታ ያድነን ዘንድ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ የነበርንበት ጀልባ አናት በማዕበሉ ተመትቶ በተወሰደበት--- በእንግልትና ከፍተኛ ማዕበል መሃል በራእይ ተነጥቄ ተወሰድኩ፡፡ ወቅቱ ሥራዬን ገና የጀመርኩበት አካባቢ እንደመሆኑ እኛ ከምንጠፋ ይልቅ በባሕሩ የነበረው እያንዳንዱ ጠብታ ውሃ ቢደርቅ እንደሚቀል ተመለከትኩ፡፡ ራእዩን ተመልክቼ ስነቃ ፍርሃቴ ሁሉ ብን ብሎ ጠፋ፣ መዝሙር ዘመርን እግዚኣብሔርንም አመሰገንን:፡፡ ያቺ ትንሽዋ ጀልባችንም በባህሩ ላይ የምትሰፍ ቤቴል ሆነችልን፡፡ የአድቬንቲስት ሔራልድ አዘጋጅ የእኔ ራእዮች «የሰመመን ሥራ ውጤት” ተብለው እንደሚታወቁ ተናገረ:: ነገር ግን በእንደዚያ ዓይነቱ ጊዜ መሃል የሰመመንን ሥራ ለመሥራት የሚያስችሉ ምን ዓይነት ዕድሎች ነበሩ? በማለት ጠየቅኩት ወንድም ጂ. ጀልባዋን ለመቆጣጠር ከሚችለው በላይ አድርጎአል፡፡ መልህቅ ለመጣል ሙከራ ቢያደርግም ነገር ግን መልህቁ ወርዶ መያዝ አልቻለም ነበር በመሆኑም ያቺ ትንሽዬ ጀልባችን በማዕበሉ እየዋለለች በንፋስ ትነዳ ጀመር፡፡ ጊዜው ጨለማ ስለነበር ከጀልባዋ አንደኛው ክፍል እስከሌላኛው ድረስ መመልከት አልቻልንም፡፡ ወዲያው ግን መልህቁ በመያዙ ወንድም ጂ. ለእርዳታ ተጣራ፡፡ በደሴቲቱ ላይ ሁለት ብቻ ቤቶች የነበሩ ሲሆን እኛ እየሄድንበት ወደ ነበረው ቤት ሳይሆን ነገር ግን ወደ ሌሳኛው መቃረባችንን አረጋግጠናል፡፡ አምላካዊው ጥበቃ ሆኖ ከባህሩ ላይ ያሰማነውን ጥሪ ካደመጠችው አንዲት ህጻን በቀር የዚህ ቤት ነዋሪ ቤተሰብ በሙሉ እንቅልፍ ላይ ነበሩ፡፡ አባቷ ለነበርንበት ችግር ፍቱን በመሆን በትንሽዬ ጀልባ ወደ እኛ በመምጣት ወደ ባህሩ ዳርቻ ወሰዱን፡፡ እኛም አብዛኛውን ያን ምሽት ለእግዚአብሔር ድንቅነትና መልካምነት--ምስጋናና ውዳሴ በማቅረብ አሳለፍን፡፡ EWAmh 16.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents