Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    56—የዳግም ምጽአቱ ተከታዮች እንቅስቃሴ ማብራሪያ

    በአንድ ዓይነት አመራር ስር የነበሩ የሚመስሉ ብዛት ያላቸውን ስብስቦች ተመልክቼ ነበር፡፡ አብዛኞቹ እነዚህ ሐዝቦች በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ይገኙ ነበር 0ይኖቻቸውን ወደ ምድር በማቀርቀራቸው በእነርሱና በየሱስ መሃል ግንኙነት ያለ አይመስልም ነገር ግን በእነዚህ የተለያዩ ስብስቦች መሃል በገጽታቸው ላይ ብርሃን የሚስተዋልባቸውና ዐይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ያነሱ ወገኖች ተበትነው ይገኙ ነበር፡፡ ከየሱስ የተላከ እንደ ጸሐይ ጮራ ያለ ብርሃን በላያቸው አርፎ ነበር ጉዳዩን በጥንቃቄ እመለከት ዘንድ መልአኩ አዘዘኝ፡፡ መልአኩ ለእነዚያ በላያቸው የብርሃን ጮራ ይስተዋልባቸው ለነበሩት የተለየ ጥንቃቄ ሲያደርግ፣ በጽልመት ውስጥ የነበሩት ግን በክፉ መላእክት ተከብበው እንደነበር ተመለከትኩ፡፡ «እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርም ስጡት፧ ምክንያቱም የፍርዱ ሰዓት ደርሶአል” እያለ መልአኩ ሲጮህ ሰማሁ EWAmh 175.1

    በዚህን ጊዜ ይህን መልእክት በተቀበሉት ላይ በክብር የተሞላ ብርሃን አረፈ:: በጨለማ ውስጥ ይገኙ የነበሩ አንዳንዶች ብርሃኑን በመቀበል ደስ ቢሰኙም፤ ሌሎች ግን መልእክቱ እነርሱን ለመበታተን እንደመጣ አድርገው በማሰብ ሰማያዊውን ብርሃን ላለመቀበል ልቦቻቸውን አደነደኑ፡፡ በመሆኑም ብርሃኑ አልፎአቸው በመሄዱ በጨለማ ውስጥ ተተው፡፡ ከየሱስ ብርሃን ተቀብለው የነበሩ በላያቸው ያንጸባርቅ በነበረ እየጨመረ በሚሄድ ብርሃን አብልጠው ደስ በመሰኘት የከበረ ዋጋ ሰጥተውት ነበር ዐይኖቻቸው በማያባራ ፍላጎት በየሱስ ላይ ተተክለው፤ ፊቶቻቸው ደግሞ በቅዱሱ የደስታ ጮራ ፈክተው ነበር፡፡ ከእነዚህ ወገኖች ይወጣ የነበረው ድምጽ እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርም ስጡት ምክንያቱም የፍርዱ ሰዓት ደርሶአል” ከሚለው ከመልአኩ ጩኸት ጋር ሕብር ፈጥሮ ይደመጥ ነበር፡፡ መልእክቱን ከፍ ባለ ድምጽ በሚያስተላልፉበት ወቅት በጨለማ ውስጥ የነበሩት ከፊትና ከኋላ ሆነው ያጨናንቋቸው እንደ ነበር ተመልክቻለሁ ቅዱስ ለሆነው ብርሃን ተገቢውን ዋጋ የሰጡ ብዙዎች ጠፍንጎአቸው የነበረውን አመራር በጣጥሰው ከመካከላቸው ተለይተው ወጡ፡፡ በዚህ ወቀት በእነርሱ ክብር ያገኙ በሌሎች ቡድኖች የነበሩ ሰዎች ስርገው ገቡ፡፡ ከአንዳንዶቹ አንደበት አስደሳች ቃላት ሲደመጥ በሌሎች ላይ ቁጣ አዘል ገጽታ ይስተዋል ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች «እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፣ በብርሃን ውስጥ እንመላለሳለን፣ እውነትን ይዘናል» በማለት ያለማቋረጥ ሲናገሩ ይደመጡ ነበር፡፡ የእነዚህን ሕዝቦች ማንነት ብጠይቅ---አገልጋዮች መሆናቸውን ብርሃኑን ተቃወመው የነበሩትን እንደሚመሩና ሌሎችም ይቀበሉ ዘንድ ፈቃደኞች አለመሆናቸው ተነገረኝ:፡፡ EWAmh 175.2

    ለተሰጠው ብርሃን ከፍ ያለ ዋጋ በመስጠት የሱስ ዳግም ተገልጦ ወደ ራሱ ይወስዳቸው ዘንድ በጽኑ ምኞት ይጠባበቁ የነበሩትን ተመለከትኩ፡፡ ሆኖም ወዲያውኑ ደመና በላያቸው አልፎ በመሄዱ ፊታቸው በኃዘን ተሞላ፡፡ የዚህን ደመና ምንነት ብጠይቅ የኃናቸው መንስዔ መሆኑን እንድመለከት ተደረግኩ:፡፡ አዳኛቸው ይመጣል ብለው የተጠባበቁት ጊዜ አለፈ፡፡ የሱስም ሳይገለጽ ቀረ፡፡ የጌታን ምጽአት ሲጠባበቁ በነበሩት ላይ ኃዘንና መከፋት ሲደርስ አገልጋዮችና ቀደም ብዬ ተመልክቻቸው የነበሩ መልእክቱን በመቃወም ሲመሩ የነበሩ እንዲሁም ብርሃኑን የተቃወሙ ከፍ ያለ ድል በመቀዳጀት በደስታ ተሞሉ፡፡ ሰይጣንና መላእክቱም ከበሩ፡፡ EWAmh 176.1

    ከዚያም ሌላው መልአክ «ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች» እያለ ሲጮኽ ሰማሁ፡፡ የጌታን መገለጽ በጽኑ ይጠባበቁ በነበሩ ተክዘው በሚገኙ ወገኖች ላይ ብርሃን ፈንጥቆና ዐይኖቻቸውም ዳግመኛ በየሱስ ላይ ተተክለው ነበር፡፡ ብዛት ያላቸው መላእክት «ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” በማለት ከጮኸው መልአክ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ እርሱን በመቀላቀል «ሙሽራው እየመጣ ነው፤ ወጥታችሁ ተቀበሉት!» ብለው ሲጮኹ ተመለከትኩ፡፡ ሙዚቃዊ ቃና የነበረው የመላእክቱ ድምጽ በሁሎም ስፍራ የሚደርስ ይመስል ነበር፡፡ ለበራላቸው ብርሃን ዋጋ ሰጥተው በነበሩት ዙሪያ እየጨመረ የሚሄድ ብሩህና በክብር የተሞላ ብርሃን አንጸባረቀ፡፡ የእነዚህ ሰዎች ፊት በአስገራሚ ክብር በማንጸባረቅ «ሙሽራው እየመጣ ነው፤ ወጥታችሁ ተቀበሉት!» እያሉ መላእክቱን ተቀላቀሏቸው:: ኸት ለተለያዩ ቡድኖች በሚያሰራጩበት ወቅት ብርሃነን የተቃወሙ ገፏቸው፤ በተበሳጨአኳኋንም ኣሾፉባቸው፡፡ ሰይጣንና መላእክቱ ሰማያዊውን ብርሃን እንዲቃወሙ በመምራት በላያቸው ጽልመት ለመጣል ቢመኙም፧ የእግዚአብሔር መላእክት ግን እነዚህን ስደት የገጠማቸውን ወገኖች በክንፎቻቸው ሸፈኗቸው፡፡ EWAmh 176.2

    ከዚያም «ከመካከላቸው ውጡ፧ ንጹህ ያልሆነውንም አትንኩ» የሚል ድምጽ ተገፍተው ለነበሩትና ለተፌዘባቸው ሲመጣ ሰማሁ፡፡ ከፍተኛ ቁጥር የነበራቸው ሰዎች ይህን ድምጽ በመታዘዝ ዙሪያቸውን ተብትቧቸው የነበ ረውን ገመድ በጣጥሰው በጨለማ ውስጥ የነበሩትን እየተዉ ቀደም ብለው ነጻነታቸውን ከተቀዳጁት ጋር በመቀላቀል ድምጾቻቸውን ከእነርሱ ጋር በአንድ አዋሃዱ: እስከዚህ ወቅት ድረስ በጨለማ ውስጥ ከነበሩት ቡድኖች ጋር የቀሩ የጥቂቶችን ጽኑ እና በህማም ውስጥ ያለ የጸሎት ድምጽ ሰማሁ፡፡ ምንም እንኳ አገልጋዮችና መሪዎች በእነዚህ ቡድኖች ዙሪያ በመመላለስ እነርሱን የጠፈነጉበትን ገመድ ቢያጠብቁም ጽኑውን ጸሎታቸውን ግን ሰምቼ ነበር በመቀጠል ነጻና በእግዚአብሔር ደስ እየተሰኙ የነበሩትን ቡድች ይቀላቀሉ ዘንድ ለእርዳታ እጆቻቸውን ከፍ አድርገው ይጸልዩ የነበሩትን ተመለከትኩ፡፡ በጽናት ወደ ሰማይ በመመልከት ለጸለዩት ጸሎት የመጣላቸው ምላሽ «ከመካከላቸው ውጡ፤ ተለዩ” የሚል ነበር፡፡ ግለሰቦች ነጻነታቸውን ለመቀዳጀት ሲታገሉና በመጨረሻም ዙሪያቸውን የተበተባቸውን ገመድ ሲበጣጥሱ ተመልክቼ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች እነርሱን ለመጠፍነግ ይደረግ የነበረውን ጥረት በመቋቋም «እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው» «እውነት አለን” ለሚለው በተደጋጋሚ አባባል ትኩረት ለመስጠት እምቢተኞች ሆኑ EWAmh 177.1

    ግለሰቦች ያለማቋረጥ በጨለማ የነበሩትን ቡድኖች እየተዉ በመውጣት ከምድር ከፍ እያሉ ያድጉ የነበሩትን ነጻ ሰበካዎች መቀላቀል ያዙ፡፡ አምላካዊው ክብር ሽቅብ ይመለከቱ በነበሩት በእነዚህ ሕዝቦች ላይ በማረፉ በደስታ ለክብሩ ጮኹ:፡፡ እጅግ ተቀራርበው ሕብረት በመፍጠራቸው በሰማያዊው ብርሃን የተሸፈኑ መስለው ታዩ፡፡: በዚህ መንጋ ብርሃን ተጽእኖ ስር የወደቁ ነገር ግን መንጋውን ያልተቀላቀሉ አንዳንዶች ነበሩ ለብርሃኑ ተገቢውን ዋጋ ስጥተው የነበሩ ሁሉ በማያባራ ፍላጎት ሽቅብ ሲመለከቱ የሱስም ጣፋጭ በሆነ የይሁንታ 0ይን ይመለከታቸው ነበር፡፡ መገለጹን በመናፈቅ የሱስ እንደሚመጣ ተስፋ በማድረጋቸው ዐይኖቻቸውን ለአፍታም እንኳ ከሰማይ ነቅለው ወደ ምድር አልተመለከቱም፡፡ ነገር ግን በእነዚህ ተጠባባቂዎች ላይ ዳግመኛ ደመና ባንዣበበ ጊዜ ዝለው የነበሩ ዐይኖቻቸው ቁልቁል ወደ ምድር ሲመለከቱ አየሁ: ይህ ለውጥ እንዲሆን መንስዔው ምን እንደሆነ ብጠይቅ መልአኩ እንዲህ አለኝ «የሱስ ወደ ምድር ገና የማይመጣ በመሆኑ እነዚህ ሕዝቦች እርሱን በመጠባበቅ በድጋሚ መፋት ደርሶባቸዋል: ስለ እርሱ ታላላቅ ፈተናዎችን ማለፋቸው የግድ ነው:: ከሰዎቹ የተቀበሏቸውን ስህተቶች እንዲሁም ወግና ልማዶች በመተው ፊታቸውን ሙሉ ለሙሉ ወደ እግዚአብሔርና ወደ ቃሉ ሊያዞሩ ይገባል፡፡ ተፈትነው መንጻታቸው የግድ ይሆናል፡፡ መራራውን ፈተና የሚያልፉ ዘላለማዊውን ድል ይቀዳጃሉ፡፡” EWAmh 177.2

    የሱስ ምጽአቱን በደስታ ይጠባበቁ የነበሩ ሰዎች ተስፋ እንዳደረጉት ምድርን በእሳት በማንጻት መቅደሱን ለማጥራት አልመጣም ነበር፡፡ እነዚህ ሕዝቦች ትንቢታዊውን ጊዜ በማስላቱ ረገድ ትክክል እንደነበሩ ተመልክቻ ለሁ፡፡ ትንቢታዊው ጊዜ 1844 ላይ ሲዘጋ በመጨረሻው ዘመን የሱስ ቤተመቅደሱን ለማንጻት ወደ ቅድስተቅዱሳኑ ውስጥ ገባ፡፡ የእነርሱ ስህተት የቤተመቅደሱን ምንነት አለመረዳታቸውና የሚነጻበትን ተፈጥሮአዊ መንገድ አለማወቃቸው ነበር ወደነዚህ የሚጠባበቁና የተከፉ ወገኖች ዳግመኛ ስመለከት በኃዘን ውስጥ እንደነበሩ አስተዋልኩ፡፡ ትንቢታዊውን ስሌ ት ተከትለው በመጓዝ የእምነታቸውን ተጨባጭ ማስረጃዎች በጥንቃቀ ቢፈትሹም አንዳችም ስህተት ማግኘት አልቻሉም ነበር፡፡ በስሌቱ መሰረት ትንቢቱ ፍጻሜ ቢያገኝም አዳኛቸው ግን የታለ? እርሱ የነበረበትን ስፍራ ስተው ነበር፡፡EWAmh 178.1

    «ጌታዬን ደቀ መዛሙርቱ ወደ የሱስ መቃብር መጥተው አካሉን ባጡ ረሰባቸውን ኃዘን እንድመለከት ተደርጌ ነበር፡፡ ማርያም ወስደውታል የት እንዳኖሩትም አላውቅም” በማለት ተናገረች፡፡ መላእክት የጌታን ትንሳኤ በመናገር ቀድሞአቸው ወደ ገሊላ እንደሚሄድ በስፍራው ለነበሩት ደቀ መዛሙርት አሳውቀዋቸው ነበር፡፡ EWAmh 178.2

    በተመሳሳይ የሱስ ምጽአቱን በመጠባበቅ አዝነው የነበሩትን ወገኖች በጥልቅ ርኅራኄ በመመልከት ይከተሉት ዘንድ የሚገኝበትን ስፍራ እንዲያመላክቷቸው መላእክቱን እንደላከ አይቻለሁ፡፡ ይህ ምድር መቅደስ አለመሆኑን፧ ነገር ግን እርሱ ለሕዝቡ ሥርየት ለማምጣትና ከአባቱ መንግሥቱን ለመቀበል ወደ ሰማያዊው ቅድስተቅዱሳን ከገባ በኋላ ለዘላለም ከእርሱ ጋር ይኖሩ ዘንድ ሊወስዳቸው ዳግም እንደሚገለጽ አሳያቸው፡፡ በመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ላይ የተስተዋለው ኃዘን በ1844 የጌታቸውን ዳግም መገለጽ በተጠባበቁት የደረሰውን በሚገባ ይገልጻል፡፡ EWAmh 178.3

    ክርስቶስ በድል አድራጊነት የሩሳሌም ወደ ገባበት ጊዜ በራእይ ተወስጄ ነበር፡፡ በወቅቱ በደስታ ተውጠው የነበሩት ደቀ መዛሙርት ክርስቶስ መንግሥቱን በጊዜያዊነት ወስዶ ይነግሣል በሚል እምነት ንጉሣቸውን ከፍ ባለ ተስፋ ተከተሉት፡፡ ከፊትና ከኋላ አጅቦት ይሄድ የነበረው ሕዘብ በጋለ ስሜት ውብ የሆኑትን የዘንባባ ዝንጣፊዎች እየቆረጡ፣ ልብሶቻቸውን እያወለቁና በመንገድ ላይ እያነጠፉ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ይኹ ነበር በሕዝቡ ዘንድ የተስተዋለው ከፍተኛ ደስታ ፈሪሳውያኑን ስለረበሻቸው የሱስ ይገስጻቸው ዘንድ ቢመኙም እርሱ ግን «እነርሱዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሎ በማለት መለሰላቸው፡፡ በዘካ. 9:9 ላይ የተሰጠው ትንቢት ፍጻሜ ሊያገኝ ይገባ የነበረ ቢሆንም ደቀ መዛሙርቱ ግን በመራራ ኃዘን ወስጥ ወድቀው ነበር ከዚህ በኋላ በነበሩት ጥቂት ቀናት ውስጥ የሱስን ወደ ቀራኒዮ በመከተል በጨካኙ መስቀል ላይ ሲደማና ሥቃይ ሲቀበል እንዲመለከቱት ሆኑ፡፡ ነገር ግን ከሞት ተነስቶ አዝነው ለነበሩት ደቀ መዛሙርት ከታያቸው በኋላ ተስፋቸው ለመለመ፡፡ ዳግመኛም አገኙት፡፡ EWAmh 178.4

    ጌታ በ1844 ዳግም ይገለጻል ብለው በማመን ሲጠባበቁ የነበሩ አማኞች ኃዘን ከመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ጋር እኩል እንዳልነበር ተመልክቻለሁ፡፡ የመጀመሪያውና የሁለተኛው መልአክ መልእክት ትንቢቶች ፍጻሜ አግኝተዋል፡፡ መልእክቶቹ በትክክለኛው ጊዜ እንዲሰጡ በማድረግ እግዚአብሔር በእነዚህ ሕዝቦቹ በኩል ክንውን እንዲያገኝ ያቀደውን ሥራ ወደ ፍጻሜ አምጥቶአል፡፡ EWAmh 179.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents