Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    39—የክርስቶስ ፈተና

    መሳእክት አንጸባራቂ አክሊሎቻቸውን በአዘኔታ ከአናቶቻቸው ላይ አንስተው ሰማይን ለቅቀው ሄዱ፡፡ አዛዣቸው ሥቃይ እየደረሰበትና የእሾህ አክሊል ጉንጉን ሊደፋ መሆኑን እየተመለከቱ እነርሱ አክሊሎቻቸውን ሊደፉ አልቻሉም፡፡ ሰይጣንና መላእክቱ ፍርድ በሚሰጥበት ሸንጎ ሰብዓዊውን ስሜትና አዘኔታ በማጥፋት ሥራ ላይ ተጠምደው ነበር፡፡ የእነርሱን ተጽእኖ ተከትሎ አየሩ ይከብድ ነበር ንጽህናም አልነበረም፡፡ የካኅናት አለቆችና ሽማግሌዎች በተጽእኖአቸው ሥር በመሆን ሰብዓዊው ተፈጥሮ ሊቋቋመው አዳጋች በሆነ አኳኋን የሱስን ለመስደብና ለመጉዳት ተነሳስተው ነበር፡፡ እንዲህ በእርሱ ላይ መዘበታቸውና የጭካኔ ተግባር ማሳየታቸው የእግዚአብሔር ልጅ አንዳች አጸፋዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ ወይም መለኮታዊ ኃይሉን ተጠቅሞ እራሱን ከዚያ መሃል አውጥቶ የደኅንነት እቅድ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ለማድረ7 በሰይጣን የታቀደና ተስፋ የተደረገ ዘዴ ነበር፡፡ EWAmh 117.1

    በጌታው ላይ ክህደት ከደረሰ በኋላ ጴጥሮስ ተከተለው፡፡ ጴጥሮስ በየሱስ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ነገር በጭንቀት ይከታተል ነበር፡፡ ሆኖም ከየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነህ ተብሎ በተከሰሰ ጊዜ ለደኅንነቱ ፍርሃት ስለተሰማው ይህን ሰው አላውቀውም ሲል በይፋ ተናገረ:፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ከአንደበቶቻቸው ሊወጡ ስለሚገቡ ንጽህና የተሞላቸው ቃላት ያውቁ የነበ ረ ቢሆንም ጴጥሮስ ግን ከክርስቶስ ደቀ ዛሙርት አንዱ እንዳልሆነ ከሳሾቹን ለማሳመን በመሞከር ይህንኑ ደጋግሞ እየማለና እየተገዘተለሦስተኛ ጊዜ ተናገረ፡፡ ከጴጥሮስ በተወሰነ ርቀት ላይ የነበረው የሱስ ዘወር አለና በኃዘኔታ አስተያየት ተመለከተው፡፡ በዚህን ጊዜ ደቀ መዝሙሩ በጌታ ራት ወቅት የሱስ የተናገራቸውን ቃላትና እርሱ ከልብ በመነጨስሜት የተናገረውን አስታወሰ «ሌሎች በሙሉ በአንተምክንያት ቢሰናከሉ እንኳ እኔ በፍጹም አልሰናከልም!»፡፡ አሁን ጴጥሮስ ጌታውን ከድቶአል-ያውም እየማለና እየተገዘተ፡፡ ነገር ግን የሱስን ሲመለከት ያየው ገጽታ ልቡ እንዲቀልጥ በማድረግ አዳነው ወዲያውም አምርሮ በማልቀስ ለሠራው ታላቅ ኃጢአት ንስሐ ገባ፡፡ ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ የተለወጠ ሰው በመሆን ወንድሞቹን ለማጠንከር የተዘጋጀ ሆነ፡፡ EWAmh 117.2

    ሕዝቡ በከፍተኛ ጩኸትና ሁካታ የየሱስን ደም በመሻት፤ በጭካኔ እየተራገሙ ቀይ አሮጌ ንጉሣዊ መጎናጸፊያ አጠለቁለት እንዲሁም በተቀደሰው አናቱ ላይ የእሾህ አክሊል ደፉበት፡፡ የሸምበቆ በትር በእጁ በማስያዝ በፊቱ ተንበርክከው «የአይሁድ ንጉሥ ሆይ ሰላም ለአንተይሁን!» በማለት አሾፉበት---ተፉበትም፡፡ የሸምበቆ በትሩን ከእጁ ወስደው የእሾህ አክሊሉ ወደ አናቱ ውስጥ እንዲሰነቀር እራሱ ላይ ደግመው ደጋግመው መቱት፡፡ ደሙ በፊቱና በጺህሙ ቁልቁል ይወርድ ነበር፡፡ EWAmh 117.3

    መላእክት እንዲህ ያለውን ዘግናኛ ትዕይነት ለመቋቋም ተቸግረው ነበር፡፡ ምንም እንኳ እነርሱ ሊያድነት ተመኝተው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ይህ ለሰው ልጅ መከፈል ያለበት የኃጢአት ዋጋ መሆኑን በማውሳት ሞት ከእንግዲው ወዲህ በሰው ላይ ሥልጣን እንደማይኖረው የየቡድኑ ተጠሪ መላእክት በመንገር ከለከሏቸው፡፡ የሱስ የደረሰበትን ውርደት መላእክት ይመለከቱ እንደነበር አውቆአል: ደካማ የተባለው ቅዱስ መላእክ ያንን የሕዝብ ፌዝና ጩኸት ቀጥ በማድረግ የሱስን ማዳን ይችል ነበር፡፡ ይህ ይሆን ዘንድ የአባቱ ፈቃድ ቢሆን ኖሮ መላእክት ወዲያውኑ ይታደጉት እንደነበር የሱስ ያውቃል፡፡ ነገር ግን የደኅንነት ዕቅድ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ በአመጸኛ ሰዎች ሥቃይ ይቀበል ዘንድ በእነርሱ እጅ ተላልፎ መሰጠት ነበ ረበት፡፡ EWAmh 118.1

    ሕዝቡ በየሱስ ላይ የከፋ ጉዳት ሲያደርስበት ሳለ እርሱ ግን በትህትና ቆሞ ነበር፡፡ ያ ከጸሐይ ይልቅ በሚያንጸባርቀው፣ ለእግዚአብሔር ከተማ ብርሃን የሚሰጠውንና አንድ ቀን አመጸኞች ሸሽጉን በሚሉት ፊቱ ላይ ይተፉበት ነበር፡፡ ክርስቶስ በክፉ አድራጊዎቹ ላይ የቁጣ ፊት አላሳያቸውም፡፡ እነርሱ ግን ዓይኑን ሸፍነው «እስቲ ትንቢት ተናገር የመታህ ማን ነው? እያሉ ይጠይቁት ነበር፡፡ መላእክቱ አሁንም ሊያድኑት ቢመኙም ነገር ግን አዛዦቻቸው አልፈቀዱላቸውም ነበር EWAmh 118.2

    ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶቹ የሱስ ወደነበረበት ስፍራ ዘልቀው በመግባት ይደርስበት የነበረውን አስከፊ ሁናቴ ለመታዘብ ብርታት አግኝተው ነበር እነዚህ ደቀ መዛሙረት የሱስ መለኮታዊ ኃይሉን ተጠቅሞ እራሱን ከጠላቶቹ እጅ በማዳን ለፈጸሙ በት የጭካኔ ተግባር አጸፋውን በመመለስ ይቀጣቸዋል ብለው ጠብቀው ነበር፡፡ ትዕይንቱ በቀጠለ ቁጥር የእነርሱም ተስፋ አንዴ ሲጨምር ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲቀንስ ቆየ፡፡ አንዳንዴ ጥርጣሬ ይገባቸውና ተታልለው እንደሆነ በማሰብ ፍርሃት ይርዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን የየሱስ መልክ በተቀየረበት ተራራ የሰሙት ድምጽና የተመለከቱት ክብር በእርግጥም እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆኑ እምነታቸውን አጠነከረው፡፡ እነዚያን የታዘቡአቸውን ትዕይንቶች አስታወሱ፡፡ የሱስ በሽተኞችን በመፈወስ ተአምራት አድርጎአል፣ የዓይነ ሥውሩን ዓይን አብርቶአል፣ መስማት የተሳነውን ፈውሶአል፣ አጋንንትን ገስጾአል፣ ከሰዎች ውስጥ አውጥቶአል የሞተውን አስነስቶአል እንዲሁም ነፋስም ሆነ ባሕሩ ታዝዘውታል፡፡ በመሆኑም የሱስ ይሞታል ብለው ሊያምኑ አይችሉም፡፡ ይልቁንም የሱስ የእግዚአብሔርን ቤት የግንግድ ቤት ያደረጉትን ገዢና ሻጮች ከቤተመቅደስ በኃይል ሲያስወጣቸው ሕዝቡ የታጠቁ ወታደሮች የመጡበትን ያህል ፈርጥጦ ሲወጣ ከተስተዋለው ትዕይነት በተመሳሳይ አሁንም በዚያ ትእዛዝ ሰጪ ድምጹ እነዚህን ደም የተጠሙ ሕዝቦች በታኖ በኃይል ይነሳል ብለው ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ የሱስ በዚህ መልኩ በሚያሳየው ኃይል እርሱ የእስራኤል ንጉሥ እንደነበር ያሳምናቸዋል የሚል እምነት ነበራቸው፡፡ EWAmh 118.3

    ይሁዳ የፈጸመውን የክህደት ተግባር ተከትሎ በመራራ ጸጸትና ሐፍ ረት ተሞላ፡፡ በአዳኙ ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተጊዜ ተሸነፈ፡፡ እርሱ የሱስን ይወደው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ለገንዘብ የነበረው ፍቅር ከየሱስ የላቀ ነበር፡፡ የሱስ ሲመራው ለነበረ ሐዝብ የአመጻ ተግባር እራሱን ኣሳልፎ ይሰጣል ብሎ አላሰበም ይልቁንም ተአምራት በማድረግ እራሱን ከእጃቸው ያድናል ብሎ ተጠባብቆ ነበር ነገር ግን ፍርድ በሚሰጥበት ሸንጎ ውስጥ የነበረውን ደም የጠማውንና በቁጣ የጋለ ሕዝብ ስሜት ሲመለከት የሠራው ስህተት ጥልቅ ጸጸት ፈጠረበት፡፡ ብዙዎች የሱስን በኃይል ሲከሱት ሳለ ይሁዳ ከሕዝቡ መሃል በመውጣት ንጹሁ በሆነው ደም ላይ ክህደት በመፈጸም ኃጢአት መሥራቱን ተናዘዘ፡፡ ቀሳውስት ከፍለውት የነበረውን ገንዘብ በመመለስ የሱስ ሙሉ ለሙሉ ንጹህ መሆኑን ከተናገረ በኋላ እንዲለቁት ለመናቸው:: EWAmh 119.1

    በቀሳውስቱ ዘንድ የተስተዋለው ግራ የመጋባትና የብስጭት ስሜት ለጥቂት ጊዜ ጸጥ እንዲሉ አደረጋቸው፡፡: ከየሱስ ተከታዮች መሃል ለአንዱ በመክፈል ክህደት ፈጽሞ በእጃቸው እንዲሰጣቸው ማድረጋቸውን ሕዝቡ እንዲያውቅ አልፈለጉም ነበር የሱስን እንደ ሌባ በድብቅ አድነው መያዛቸውን መደበቅ ፈልገዋል፡፡ ነገር ግን የይሁዳ ኑዛዜ አንዲሁም ፊቱ ላይ ይነበብ የነበረው የጭንቀትና የጸጸተኝነት ስሜት---ቀሳውስቱ የሱስ እንዲያዝ ያደረጉበት መንስዔ ጥላቻ መሆኑን በማሳየት በሕዝቡ ፊት እንዲጋለጡ አደ ረጋቸው፡፡ ይሁዳ ድምጹን ከፍ አድርጎ የየሱስን ንጽህና ሲናገር ታዲያ እኛ ምናገባን፤ የራስህ ጉዳይ ነው!” አሉት እነርሱ የሱስን አንዴ እጃቸው ውስጥ በማስገባታቸው ምን ሊያደርጉት እደሚገባ አንዴ ቆርጠዋል፡፡ በከባድ ሃዘንና ሥቃይ የተሸነፈው ይሁዳ ብሩን እግራቸው ስር ወርውሮ በብዙ ሃዘንና ፍርሃት ሄዶ እራሱን ሰቀለ፡፡ EWAmh 119.2

    የሱስ ይቀርቡለት ለነበሩ ብዛት ያላቸው ጥያቄዎች መልስ አለመስጠቱ አያሌ ደጋፊዎቹንም ሆነ በስፍራው የነበሩትን አስደንቆ ነበር፡፡ የዚያ ሁሉ በገጽታው ላይ አንዳችም ?ኩርፊያ ወይም የመሸበር ይልቁንም ከፍ ከፍ ብሎና ተረጋግቶ ይታይ ነበር ይህ ሁኔታው ተመልካቾቹን እንዲደነቁ አድርጓቸዋል: ተመልካቾች---ፍጹም የሆነ ቁመናውንና ክብር የሰፈነበትን ሁኔታውን በፍርድ ሽንጎ ከተቀመጡት ከሳሾቹ ሁናቴ ጋር በማስተያየት ከማናቸውም ገዢዎች ይልቅ እርሱ ይበልጥ ንጉሣዊ ገጽታ እንደሚታይበት አንዱ ለሌላው ይነግረው ነበር፡፡ የሱስ አንዳችም የወንጀለኝነት ምልክት አይታይበትም ነበር፡፡ ዓይኖቹ ለስላሳ፣ ግልጽና ፍርሃት የማይታይባቸውግንባሩ ደግሞ ሰፊና ወጣ ያለ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ገጽታ ርኅራኄ በተሞላውና ጻድቅ በሆነ መርኅ ተቀምሮ ይስተዋል ነበር፡፡ በእርሱ ዘንድ ይታይ የነበረው ከሰው የማይመሳሰል ትፅ ግሥትና ቻይነት ብዙዎች በፍርሃት እንዲርዱ አድርጓል፡፡ ሌላው ቀርቶ ሔ ሮድስና ጲላጦስ እንኳ በእርሱ ጻድቅነትና አምላካዊ ገጽታ በእጅጉ ተረብሸው ነበር፡፡EWAmh 119.3

    ሕዝብ አሠጻና ፌዝ ስሜት አልፈጠረም ጲላጦስ ገና ከመጀመሪያው የሱስ ተራ ሰው አለመሆኑን ተረድቶአል፡፡ እርሱ እጅግ ግሩም ባህሪ እንዳለውና በተከሰሰበት ነገር ሙሉ ለሙሉ ንጹህ መሆኑን አምኖ ነበር የሮማው ገዥ ልብ በየሱስ መነካቱን መላእክት በአንክሮ ይመለከቱ ነበር፡፡ በመሆኑም ጲላጦስ ክርስቶስን ጥፋተኛ በድርጎ እንዲሰቀል ከሚሰጠው አስፈሪ የፍርድ ውሳኔ ለመታደግ አንድ መልአክ ወደ ጲላጦስ ሚስት ተላከ፡፡ መልአኩ ባሏ በንጹሁ የእግዚአብሔር ልጅ ላይ ሊፈርድ እየተዘጋጀ መሆኑን ለጲላጦስ ሚስት በህልሟ ነገራት፡፡ እርሷም በእርሱ ምክንያት በህልሟ ብዙ ስትሰቃይ ማደሯን በመጥቀስ በዚህ ንጹህ ሰው ላይ አንዳችም ነገር እንዳያደርግ በመንገር መልእክትኛ ላከችበት: መልእከተኛው በፍጥነት በሕዝቡ መሃል አልፎ ወደ ጲላጦስ በማምራት ደብዳቤውን በእጁ ሰጠው:፡፡ ጲላጦስ መልእክቱን እንዳነበበ ተንቀጠቀጠ ፊቱም በአንዴ ገረጣ:: ወዲያውም የሱስ እንዲሞት ውሳኔ መስጠት እንደሌ ለበት አመነ፡፡ አይሁዳውያኑ የየሱስን ደም የሚፈልጉ ከሆነ ሊፈታው ከመሞከር ውጪ አንዳችም ተጽእኖ ማድረግ እንደሌለበት ተሰማው፡፡ EWAmh 120.1

    ጲላጦስ በየሱስ ችሎትና ኩነ ዙሪያ እራሱን ከኃላፊነት ነጻ ለማድ ረግ ተስፋ አድርጎ ነበር፡፡ በመሆኑም የሔሮድስን በየሩሳሌም መኖር ሲሰማ ታላቅ እፎይታ ተሰምቶት የሱስን ከሳሾቹ ጋር በፍጥነት ወደ እርሱ ላከው፡፡ ይህ ገዢ ልቡ በኃጢአት የደነደነ ነበር፡፡ ሔሮድስ መጥምቁ ዮሐንስን መግደሉ እራሱን ከጥፋተኝነት ነጻ ማድረግ የማይችልበትን ጠባሳ በህሊናው ላይ ጥሉ አልፎ ነበር፡፡ ሔሮድስ ስለ የሱስና ስላደረጋቸው ተአምራት ሲሰማ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነስቶ ነው ብሎ በማመን በፍርሃት ተንቀጠቀጠ፡፡ ነገር ግን የሱስ በጲላጦስ እጅ ተላልፎ ሲሰጥ ድርጊቱ የእርሱን ኃይል፣ ሥልጣንና ፍርድ በማን እንደተደረገ አስቦ ነበር፡፡ ሁናቴው ዚህ ቀደም ቁርሾ የነበራቸውን መሪዎች ወዳጅ አደረጋቸው፡፡ በመሆኑም የሱስ አንዳንድ አስደናቂ ተአምራትን ለራሱ ሲያደርግለት ለማየት በመፈለግ እርሱን በማየቱ ደስ ተሰኝቶ ነበር፡፡: ነገር ግን የየሱስ ሥራዎች የዋሉት ለግል ዝናውና ጥቅሙ አልነበረም፡፡ ተአምራዊው መለኮታዊ ኃይሉ ጥቅም ላይ የዋለው ለግሉ ሳይሆን ነገር ግን ለሌሎች ደኅንነት ነበር፡፡EWAmh 120.2

    በሔሮድስ ቀርበውለት ከነበሩት ብዛት ያላቸው ጥያቄዎች ውስጥ የሱስ አንዱንም አልመለሰም ወይም በጥላቻ ይከሱት የነበሩ ጠላቶቹን መልሶ አልጠየቀም የሱስ በሔሮድስ ሥልጣን ላይ አንዳችም ፍርሃት ባለማሳየቱ በእጅጉ በመበሳጨት ከወታደሮቹ ጋር በመሆን የእግዚአብሔርን ልጅ ናቀው፣ አፌዙበት:: ሔሮድስ ሐፍረት በጎደለው መልኩ የሱስን ቢያመናጭቀውም ነገር ግን በእርሱ ላይ በተመለከተው ጻድቅና አምላካዊ አምሳያ ተደንቆአል፡፡ በዚህ የተነሳ በየሱስ ላይ ፍርድ ለመስጠት ፈራ: ከዚያም መልሶ ወደ ጲላጦስ ላከው፡፡ EWAmh 121.1

    ሰይጣንና መላእክቱ ጲላጦስን በመፈተን ወደገዛ ውድቀቱ እንዲያመራ ለመገፋፋት ያደርጉ በነበረው ሙከራ እርሱ በየሱስ ላይ ባይፈርድ ሌሎች ሊፈርዱበት እንደሚችሉ አስታውቀውት ነበር፡፡ ሕዝቡ የየሱስን ደም የተጠማ እንደመሆኑ እንዲስቀል ባይሰጣቸው የነበረውን ዓለማዊ ሥልጣን፣ ክብርና ዝና በማጣት የየሱስ ተከታይ ተብሎ ውግዘት ይደርስበታል፡፡ ሆኖም ጲላጦስ ኃይልና ሥልጣኑን እንዳያጣ በመፍራት የሱስ ይሞት ዘንድ ፈቃዱን ሰጣቸው፡፡ ምንም እንኳ ጲላጦስ የየሱስን ደም በከሳሾቹ ላይ ቢያ ረግና ሕዝቡ በአንድ ድምጽ «ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን!» ማለታቸውን ቢቀበልም ነገር ግን ከየሱስ ደም ንጹህ አልነበረም እርሱ ለገዛ ራስ ወዳድ ፍላጎቱና ከዚህ ምድር ታላላቅ ሰዎች ክብርና መወደድ በመሻቱ ንጹሁ ሰው ይሞት ዘንድ አሳልፎ ሰጠው፡፡ ጲላጦስ በውስጡ የነበረውን መነካት ተከትሎ ቢሆን ኖሮ በሱስ ላይ ምንም ነገር ባላደረገ ነበር EWAmh 121.2

    የሱስ ችሎት ቡቀረበበት ወቅት የነበረው ገጽታውና ከአንደበቱ የወጡት ቃላት በስፍራው ተገኝተው በነበሩ በብዙዎች አእምሮ ላይ ጥልቅ ተጽእኖ አሳድሮ ነበር፡፡ የዚህ ተጽእኖው ውጤት ከትንሳኤው በኋላ መታየት በመቻሉ በየሱስ ችሎት ላይ ከነበሩት መሃል አብዛኞቹ ኋላ ላይ ወደ ቤተክርስቲያን ተጨምረዋል: EWAmh 121.3

    ሰይጣን አይሁዳውያኑን በየሱስ ላይ በማነሳሳትሁሉንም ዓይነት የጭካኔ ተግባር እንዲፈጽሙበት ቢያደርግም ነገር ግን የሱስ አንዳችም ማንራጎር ባለማሰማቱ ኃይለኛ ንዴት ይዞት ነበር ምንም እንኳ የሱስ ሰብዓዊውን ተፈጥሮ ቢወስድም ነገር ግን በአምላካዊ አምሳል መጠጊያ ተደግፎ ነበር: በመሆኑም ከአባቱ ፈቃድ በጥቂቱ እንኳ ፈቅ አላለም:: EWAmh 121.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents