Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    49—የአመጽ ምስጢር

    የሰዎችን አእምሮ ከየሱስ ላይ አንስቶ በሰዎች ላይ በማሳረፍ የግል ተጠያቂነትን ማጥፋት ሁልጊዜም ቢሆን የዕይጣን ዕቅድ ነው:: ሰይጣን የእግዚአብሔርን ልጅ ለመፈተን ባደረገው እቅድ ባይሳካለትም ነገር ግን በኃጢአት የወደቀው ሰብዓዊ ፍጡር ላይ የተሻለ ስኬት አግኝቶአል: ክርስትና ከሐሰት አስተምህሮ ጋር ተቀላቀለ፡፡ የጳጳሳዊው ሥርዓት መሪ ዎችና ቀሳውስት የከበረውን ስፍራ ለመያዝ በማሰብ ሕዝቡ ለኃጢአቱ ይቅርታ እንዲያገኝ ወደ ክርስቶስ መመልከቱን ትቶ እነርሱን እንዲያይ አስተማሩት፡፡ EWAmh 152.2

    ህዝቡ ሙሉ ለሙሉ ተታለለ፡፡ ጳጳሳትና ቀሳውስት የክርስቶስ ወኪሎች ናቸው ተብለው ተማሩ፡፡ ነገር ግን እነርሱ የሰይጣን ወኪሎች ስለነበሩ ለኃይማኖት መሪዎቹ የሰገዱ ሁሉ ያመልኩት የነበረው ሰይጣንን ነበር ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስ በእጁ እንዲኖረው ቢጠይቅም ነገር ግን ይህን ቢፈቅዱ ሕዝቡ በሚያገኘው ሰማያዊ ብርሃን የመሪዎቹን ኃጢአት ስለሚያጋልጥ ይህ ዓይነቱ ጥያቄ እንደ አደገኛ ተቆጠረ፡፡ ሕዝቡ ከእነዚህ አታላዮች አንደበት የሚወጣውን እያንዳንዱን ቃል እንደ እግዚአብሔር ቃል አድርጎ እንዲቀበል ተማረ እግዚአብሔር ብቻ ሊይዘው የሚገባውን ሰብዓዊውን አእምሮ ተቆጣጠሩ፡፡ ማንም በራሱ መንገድ እግዚአብሔርን ለማምለ ቢሞክር ሰይጣንና አይሁድ በየሱስ ላይ የተለማመዱት ጥላቻ በእነርሱ ላይ ገቢራዊ ይሆናል፡፡ በዚህ ሳያበቃ ደም የጠማቸው መመሪዎች ሰለባ hመሆን ማምለጫ መንገድም አልነበራቸውም፡፡ EWAmh 152.3

    ሰይጣን በተለይ ሽንፈት የደረሰበትን ጊዜ እንድመለከት ተደርጌ ነበር አያሌ ክርስቲያኖች እምነታቸውን በንጽህና በመጠበቃቸው ብቻ በአስፈሪ ሁኔታ ተጨፍጭፈው ተገደሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ተጠላ:፡፡ አምላካዊውን ቃል ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ጥረት ተደረገ፡፡ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንዳያነቡ ተከለከሉ፡፡ ሲያነቡ ቢገኙ ሥቃይ ይደረስባቸዋል ወይም ሞት ይፈረድባቸዋል እንዲሁም እጃቸው ላይ የሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች በሙሉ ይቃጠላሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለቃሉ የተለየ ጥንቃቄ ያደርግ በማድረግ መጽሐፍ ቅዱስን ከመጥፋት ታድጎት እንደ ነበር ተመለከትኩ፡፡ ምንም እንኳ በተለያዩ ዘመናት የነበሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ብዛት በእጅጉ አናሳ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በመጨረሻዎቹ ጊዜያት ላይ እያንዳንዱ ቤተሰብ ሊኖረው የሚችለውን ያህል ቅጂ በዝቶ ነበር፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች በጣም አነስተኛ በነበሩባቸው ዘመናት ቃሉ በስደት የነበሩትን የሚያጽናና የከበረ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡: በዚያን ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ ይነበብ የነበ ረው በድብቅ ነበር፡፡ በመሆኑም ይህን አምላካዊ ቃል የማንበብ የከበረ ዕድል የነበራቸው ሁሉ ከእግዚአብሔር ከልጁ ከየሱስ እንዲሁም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቃለ መጠይቅ እንዳደረጉ ይሰማቸው ነበር ሆኖም ይህ የተባረከ ዕድል የብዙዎችን ህይወት ዋጋ ጠይቋል፡፡ ምክንያቱም ማንኛውም ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነብ ቢገኝ አንገቱን ለሚቀላ ይሰጣል፣ ይሰቀላለ ወይም በጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ በረሃብ ተሰቃይቶ እንዲሞት ይደረጋል፡፡ EWAmh 153.1

    ሰይጣን የደኀንነትን እቅድ ይዞ ማስቀረት አልተለውም፡፡ የሱስ ተሰቀለ ነገር ግን ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ፡፡ የየሱስን ስቅላትና ትንሳኤ ሰይጣን ለራሱ ጥቅም እንደሚያውለው ለመላእክቱ ነግሯቸው ነበር፡፡ አይሁዳውያኑ ያቀርቧቸው የነበሩ መስዋዕቶችና ይፈጽሟቸው የነበሩ ሥርዓቶች ክርስቶስ በሞተ ጊዜ ማብቃታቸውን በየሱስ እናምናለን የሚሉ እንዲያምኑ ፈቃደኛ ነበር፡፡ ምክንያቱም እነዚህን ሰዎች በመጠኑ መገፋት ከቻለ አሥርቱ ትእዛዛትም እንዲሁ ከክርስቶስ ጋር ተቸንክረዋል ብሎ ለማሳመን ይረዳዋል፡፡: EWAmh 153.2

    በዙዎች በእንዲህ ዓይነቱ የሰይጣን ምክር ለመሸነፍ ዝግጁ እንደነበሩ ተመልክ መላው ሰማይ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ሕግ ረገጥ ሲመለከት ቅዱስ በሆነ ቁጣ ተሞላ፡፡ ከእግዚአብሔር ሕግ ተፈጥሮ ጋር የሚተዋወቁት የሱስና መላው የሰማይ ሰራዊት እርሱ እንደማይለውጠው ወይም እንደማይሽው ያውቁ ነበር ሰው ከወደቀ በኋላ የነበረው ተስፋ አስቆራጭ ሁናቴ በሰማይ ጥልቅ ኃዘን በማስከተሉ የሱስ የእግዚአብሔርን ሕግ ለተ ላለፉ ለመሞት እራሱን ሰጠ፡፡ ነገር ግን ሕጉ መሰረዝ የሚችል ቢሆን ኖሮ ሰው ያለ ክርስቶስ ሞት መዳን በቻለ ነበር:: በመሆኑም የእርሱ ሞት የአባቱ ሐግ እንዲጠፋ አላደረገም ይልቁንም ከፍ ከፍ በማድረግና በማክበር ሁሉም ለቅዱሱ ሕግ እንዲታዘዙ መንስዔ ሆነ፡፡ EWAmh 153.3

    ቤተክርስቲያን ንጹህና ታማኝ እንደሆነች ብትቀር ኖሮ ሰይጣን እነርሱን ማሳትም ሆነ የእግዚብሔርን ሕግ እንዲረግጡ ማድረግ ባልቻለ ነበር፡፡ ሰይጣን በዚህ ድፍረት የተሞላ ዕቅዱ ጥቃቱን በቀጥታ የሚሰነዝረው በሰማይና በምድር ባለው የእግዚአብሔር መንግሥት መስረት ላይ ነው፡፡ ዐመጻው ከሰማይ እንዲባረር አድርጎታል፡፡ ሰይጣን ከአመጸ በኋላ እራሱን ለማዳን ሲል እግዚአብሔር ሕጉን እንዲለውጥ ቢመኝም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕግ እንደማይቀየር በመላው የሰማይ ሰራዊት ፊት ተነግሮት ነበር፡፡ ሰይጣን ሰዎች ይህን አምላካዊ ሕግ እንዲጥሱ ቢያደርግ ሕጉን የሚተላለፉ ሁሉ መሞት እንዳባቸውና ያሰበውን እንደሚያሳካ ያውቃል፡፡ EWAmh 154.1

    ሰይጣን አሁንም ርቆ ለመጓዝ ወሰነ፡፡ አንዳንዶች ለእግዚአብሔር ሕግ ቀናተኞች በመሆናቸው በዚህ ወጥመድ ውስጥ መውደቅ እንደማይችሉ በማውሳት፤ አስርቱ ትእዛዛት ግልጽ ሆነው የተቀመጡና ዛሬም ብዙዎች ስለሚያምኑባቸው ከመካከላቸው አንደኛው ላይ ብቻ ጥቃት መሰንዘር እንዳለባቸው ሰይጣን ለመላእክቱ ነገራቸው፡፡ ከዚያም ከትእዛዛቱ ሁሉ የእውነተኛውን አምላክ ገጽታ የያዘውን፣ እርሱ የሰማይና ምድር ፈጣሪ መሆኑን በብቸኝነት የሚናገውን አራተኛውን ትእዛዝ ለመለወጥ ሙከራ እንዲያደርጉ መራቸው፡፡ ሰይጣን በክብር የተሞላውን የየሱስ ትንሳኤ በፊታቸው በማቅረብ እርሱ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ከሙታን በመነሳቱ የሰንበትን ቀን ከሰባተኛው ቀን ወደ ሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እንደለወጠው ነገራቸው፡፡ EWAmh 154.2

    ሰይጣን በዚህ አሠራር የየሱስን ትንሳኤ የገዛ ዓላማውን ከግብ ለማድ ረስ ተጠቀመበት ይህ እርሱና መላእክቱ የነደፉት ስህተት---የክርስቶስ ወዳጆች ነን የሚሉትን ሁሉ መዳፋቸው ውስጥ ለማስገባት በሚያስችላቸው መልኩ በመዘጋጀቱ ፈነጠዙ፡፡ አንዱ በኃይማኖት ላይ እንደተሰነዘረ ጥቃት የሚቆጥረውን ሌላው ግን ይቀበለዋል፡፡ በመሆኑም የተለያዩ ስህተቶች በብዙ ዎች ዘንድ ተቀባይነት ሲያገኙ፧ ለእውነት መርኅ በመገዛት ጸንተው ለመቆም የመረጡም ነበሩ፡፡ ግልጽ ሆኖ በቃሉ ላይ የሰፈረው አምላካዊ ፈቃድ የእግዚአብሔር ትእዛዛት እንደሆኑ ተደርገው በቀረቡ ስህተቶች እንዲሁም በባህልና ወጎች ተሽፈኑ፡፡ ምንም እንኳ ይህ በሰማይ ላይ የተሰነዘ ረ ድፍረት እስከ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቢቀጥልም ነገር ግን በእነዚህ የስህተትና የማታለል ጊዜያቶች ሁሉ እግዚአብሔር ሕዝቡን ያለ ምስክር አልተወም፡፡ በቤተክርቲያን ላይ ጽልመትና ስደት ቢደርስም ነገር ግን ሁል ጊዜም የእግዚአብሔር ትእዛዛት ሙሉ ለሙሉ የሚጠብቁ እውነተኞችና ታማኞች አሉ:: EWAmh 154.3

    የመላእክት ሰራዊት በክብር ንጉሥ ላይ የደረሰውን ሥቃይና ሞት ሲመለከቱ ተደንቀው እንደነበር ተመልክቻለሁ: ደግሞም ይህ ስማይን በደስታና በፍቅር የሞላ የህይወትና የክብር ጌታ የሞትን ሰንሰለት በመበጣጠስ ከታሰረበት ቤቱ ተራምዶ በመውጣት በድል አድራጊነት ስለሚገዛ መላእክቱ እምብዛም አለመገረማቸውን ተመልክቼ ነበር፡፡ በመሆኑም ከእነዚህ ሁለት ክስተቶች ውስጥ በየጊዜው በመታሰቢያነት ሊኖር የሚገባው ጊዜ ቢኖር ስቅለቱ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሥቅለቱም ሆነ ትንሳኤው የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲለውጡ ወይም እንዲሽሩ ተደርገው አለመነደፋቸውን ተመልክቻለሁ፡፡ እንደውም እነዚህ ሁለቱም ለሐጉ አለመለወጥ ብርቱ ማረጋገጫ ይሰጣሉ፡፡EWAmh 155.1

    እነዚህ ሁለቱም አስፈላጊ ክስተቶች የየራሳቸው መታሰቢያ አላቸው፡፡ በጌታ እራት ሥነ ሥርዓት ላይ ተካፋይ በመሆን ሕብስትና የወይን ጭማቂ በመውሰድ ሞቱን እስከ ጌታ ዳግም ምጽአት ድረስ እናሳያለን:: ሥነ ሥርዓቱ እርሱ የተቀበለው ሥቃይና ሞት ዘወትር ትኩስ ሆኖ ወደ አእምሮአችን እንዲመጣ ያስችላል፡፡ ከእርሱ ጋር በውሃ ውስጥ በመቀበር አዲስ ህይወት ለመኖር እንደ እርሱ ትንሳኤ መነሳታችን---ለክርስቶስ ትንሳኤ በመታሰቢያነት ይውላል EWAmh 155.2

    የእግዚአብሔር ሕግ በአዲሲቱ ምድርም እንዲሁ ሰዘላለም ጸንቶ እንደሚኖር ተመልክቼ ተመልክቻለሁ፡፡ የምድር መሰረት በተጣለበት የፍጥ ረት ወቅት የእግዚአብሔር ልጆች የፈጣሪን ሥራ በአድናቆት ተመለከቱ፤ መላው የሰማይ ሰራዊትም በደሰታ ጮኹ፡፡ የሰንበት መሰረት የተጣለው በዚያን ጊዜ ነበር፡፡ የፍጥረት ሥራ በሰድስተኛው ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ እግዚአብሔር ከሠራው ሥራ ሁሉ በሰባተኛው ቀን አረፈ፡፡ እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ ካከናወነው የመፍጠር ሥራው ሁሉ ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነው፡፡ ስንበት የተቋቋመው ሰው ከመውደቁ አስቀድሞ በኤደን ገነት በመሆኑ አዳምና ሔዋን እንዲሁም መላው የሰማይ ሠራዊት በዚህ ዕለት ያርፉ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን በማረፍ ይህን ዕለት ባረከው፤ ቀደሰውም የተዋጁተቅዱሳንና መላው የመላእክት ሰራዊት ለታላቁ ፈጣሪ ክብር በመስጠት ለዘላለም ይጠብቁታል እንጂ ሰንበት እንደማይወገድ ተመልክቻለሁ፡፡ EWAmh 155.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents