Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ቀደምት ጽሑፎች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    63—ነውጥ

    በጽኑ እምነትና ህመም ባለው ለቅሶ እግዚአብሔርን የሚማጸኑትን ተመልክቼ ነበር፡፡ የገረጣው የፊታቸው ገጽታና የሚስተዋልባቸው ጥልቅ ጭንቀት በውስጣቸው ያለውን ትግል ይገልጽ ነበር፡፡ ጽናትና ቅንነት መገለጫቸው ሆኖ ይታይ ከነበረው ከእነዚህ ወገኖች ግንባር ላይ ትላልቅ የላብ ጠብታዎች ይወርዱ ነበር ከጊዜ ወደ ጊዜ ፊታቸው በአምላካዊው ይሁንታ እያበራ በመምጣት ጽኑና ቅን ገጽታ በላያቸው ያርፍ ነበር፡፡ EWAmh 199.1

    ክፉ መላእክት ዐይኖቻቸውን ዙሪያቸውን ወደ ከበበው ጨለማ በመሳብ በእግዚአብሔር ላይ እንዳይታመኑና በእርሱ ላይ እንዲያጉረመርሙ በማድ ረግ የሱስን ከዕይታቸው ለማጥፋት ዙሪያቸውን አጨናንቀዋቸው ነበር የእነዚህ ሕዝቦች ብቸኛው የደኅንነታቸው ማስተማመኛ ዐይኖቻቸውን ሽቅብ ማንሳት ነበር፡፡ የእግዚኣብሔር መላእክት ለሕዝቦቹ ተመድበው ስለነበር መርዛማው የክፉው መላእክት አየር በእነዚህ በጭንቀት ውስጥ ባሉ ወገኖች ላይ ሲነፍስ ሰማያዊው መላእክት ያለማቋረጥ በክንፎቻቸው ዙሪያቸውን እየሰፈፉ ድቅድቁን ጨለማ ይበትኑ ነበር፡፡ EWAmh 199.2

    በጸሎት ላይ የነበሩት ጩኸታቸውን በጽናት ማሰማት እንደቀጠሉ በጊዜ ውስጥ ከየሱስ የተላከ የብርሃን ጨረር ልባቸውን ሊያበረታና ገጽታቸውን ሊያበራ ወደ እነርሱ መጣ፡፡ አንዳንዶች በዚህ ህመም ባለው ጽኑ ተማጽኖ ውስጥ ተሳታፊ ባለመሆን ምላሽ ቢስና ግዴለሽነት ይስተዋልባቸው እንደ ነበር ተመልክቻሁ፡፡ እነዚህ ስዎች ዙሪያቸውን የከበባቸውን ጽልመት እየተቋቋሙ ስላልነበር በድቅድቅ ደመና ተሸፈኑ፡፡ የአግዚአብሔር መላእክትም እነርሱን ትተው በጸሎት ጸንተው የቆሙትን ለመደገፍ አመሩ፡፡ መላእክቱ ባለ ኃይላቸው የክፉውን መላእክት ለመቋቋም ትግል ውስጥ በመሆን በትጋት እግዚአብሔርን ሲጣሩ የነበሩትን ሰመርዳት ሲገሰግሱ አየሁ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር መላእክት እራሳቸውን ለመርዳት አንዳችም ጥረት ያላደ ረጉትን ስለተዉአቸው ከዕይታዬ ተሰወሩ፡፡ EWAmh 199.3

    ያየሁትን ነውጥ ትርጓሜ ብጠይቅ ነውጡ የማያወላዳ አቋም ባላቸው በላውዶቅያ እውነተኛ ምስክሮች ስብስብ አማካኝነት ገቢራዊ እንደሚሆን ተመለከትኩ፡፡ ነውጡ እውነትን በሚቀበለው ልብ ላይ አዎንታዊ ተጽእኖውን በማሳረፍ የማያወላውለውን የእውነት መርኀ ወደ ማስተጋባት ይመራዋል፡፡ ነገር ግን አንዳንዶች ይህን ቀጥተኛ ምስክርነት አንግበው ወደፊት በመጓዝ ፋንታ ተጻራሪ በመሆናቸው በእግዚአብሔር ህዝቦች መሃል ነውጥ እንዲከሰት መንስዔ ይሆናል፡፡ የእውነተኞቹ ምስክሮች ምስክርነት በከፊል ብቻ እንደማይፈለግ ተመልክቼ ነበር፡፡ የቤተክርስቲያን መዳረሻ ያረፈበት ጽኑው ምስክርነት ሙሉ ለሙሉ ቸል ባይባልም ነገር ግን ቀላል ዋጋ ተሰጥቶት ነበር: ምስክርነቱን በእውነት የሚቀበሉ ሁሉ ስለሚታዘዙትና ስለሚነጹበት በጥልቅ ንስሐ እንዲሠራ ሊደ ረግ ይገባል፡፡ EWAmh 199.4

    መልአኩ «መዝግበሽ ያዢ!” አለኝ፡፡ ሁሉንም ዓይነት የሙዚቃ መሣሪያ ዎችን ያካተተየሚመስል ግሩም ጣዕመ ዜማ ያለውን ድምጽ አደመጥኩ፡፡ ድምጹ ከዚህ ቀደም የሰማኋቸውን ሁሉ በሚልቅ መልኩ በምህረትና በርኅራኄ የተሞላ እንዲሁም ቅዱሱ ደስታ እንዲጨምር የሚያደርግ ስለ ነበር በመላው እኔነቴ ውስጥ ታላቅ ደስታ ፈጠረብኝ፡፡ መልአኩ «ተመልከች!” አለኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ትኩረቴ በእጅጉ ሲርዱ ወዳየኋቸው ስብስቦች ዞረ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከዚህ ቀደም በታላቅ ህማም ሲያነቡና ሲጸልዩ እንድመለከታቸው ተደርጌ ነበር፡፡ በእነርሱ ዙሪያ የነበሩት ጠባቂ መላእክት በእጥፍ እንዲጨምሩ በመደረጋቸው ከአናታቸው አንስቶ እስከ እግሮቻቸው ድረስ የጦር ትጥቅ ነበራቸው፡፡ አረማመዳቸው ወታደራዊ ሥርዓትን የተከተለ ነበር፡፡ ገጽታቸውም ያለፉበትን አስቸጋሪ ትግልና በህመም የተሞላ ውዝግብ ይገልጽ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ማንነታቸው የቀድሞውን ውስጣዊ አስቸጋሪ ሁናቴ ቢመሰክርም አሁን ግን ባለ ድል፣ በቅዱስ ደስታ የተሞሉና በሰማያዊው ብርሃንና ክብር የሚያንጸባርቁ ሆነዋል፡፡ EWAmh 200.1

    የቡድኑ አኻዝ እያሽቆለቆለ መሄድ ጀመረ: አንዳንዶች ተበጥረው በመውጣታቸው በጉዞው ላይ ቀሩ፡፡ ሳይታክቱ ተማጽኖአቸውን በማቅረብ በህማም ውስጥ አልፈው ድል በማስመዝገብ የደኅንነት ባለቤት ከሆኑት ጋር ያልተቀላቀሉት ግዴለሽና ምላሸቢሶች የዚህ ባለቤት መሆን ባለመቻላቸው ወደ ኋላ ቀርተው በጨለማ ውስጥ ተተዉ፡፡ የእነርሱ ቦታ እውነትን አጥብቀው በመያዝ ወደ ደረጃ በመጡት ተሸፈነ፡፡ ክፉ መላእክት አሁንም ዙሪያቸውን ቢተራመሱም ነገር ግን በእነርሱ ላይ ኃይል አልነበራቸውም፡፡ EWAmh 200.2

    የጦር ትጥቅ ለብሰው እውነትን በታላቅ ኃይል የሚናገሩትን ሰማሁ፡፡ የእነዚህ ሰዎች መልእክት ውጤት ስለነበረው ሚስቶች በባሎቻቸው ልጆች ደግሞ በወላጆቻቸው ተገፋፍተውና ተበረታተው ነበር: እውነትን እንዳይሰሙ ክልከላ ደርሶባቸው የነበሩ አሁን ግን በተለየ ጉጉት አጥብቀው ይዘዋል:: ዘመዶቻቸው ላይ ፍራቻ የነበራቸው አሁን በላያቸው እውነት በመንሡ ፍራቻቸው ሁሉ ተወግዶአል፡፡ እነዚህ ህዝቦች እውነትን ሲራቡና ሲጠሙ ነበር። እውነት ደግሞ ከህይወት ይልቅ ውድና የከበረ ነው ይህ ታላቅ ለውጥ እውን እንዲሆን መንስዔው ምን እንደሆነ ጠይቄ ነበር መልአኩም ይህ ከታ ፊት የሚወጣው የማያረርስ የሦስተኛው መልአክ ታላቅ ጩኸት—የኋለኛው ዝናብ ነው በማለት መለሰልኝ:: EWAmh 200.3

    በእነዚህ በተመረጡ ወገኖች ዘንድ ታላቅ ኃይል ነበር መልአኩ ‹‹ተመልከች አለኝ ትኩረቴ ወደ ኃጥአን ወይም አማኞች ወዳልነበሩት ዞረ: ሁሉም በእንቅስቃሴ ላይ ያሉ ይመስሉ ነበር: በእግአብሔር ሕዝቦች ዘንድ የነበረው የጋለ ፍላጎትና ኃይል እነዚህ ሰዎች እንዲነሳሱና ቁጣ እንዲርባቸው አድርጎ ነበር በየአቀጣጫው ግራ መጋባትና ውዥንብር ይስተዋል ነበር᎓ የእግዚአብሔር ብርሃንና ኃይል በነበራቸው ላይ እርጃዎች ተወስደው እንደነበር ተመልክቻለሁ: ምንም እንኳ ዙሪያቸውን ጽልመት ቢከባቸውም እነርሱ ግን በእርሱ ታምውና ጸንተው በመቆማቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ነበራቸው: በመጀመሪያ ግራ የተጋቡ መስለው አይቻቸው ነበር። በመቀጠል በጽናት ወደ እግዚአብሔር ሲያለቅሱ ሰማኋቸው ‹‹አቤቱ ፈቃድህ ይፈጸም! ለስምህ ክብር ማምጣት የሚችል እስከሆነ ድረስ ለህዝህ ማምለጫ መንድ አዘጋጅ! ዙሪያችንን ከከበቡን አረማውያን አድነን፡፡ እነርሱ ሊገድሉን ወስነዋል አቤቱ የአንተክንድ ግን ደኅንነት ሊያመጣልን ይችላል እነዚህ ቃቶች ከተናገሯቸው ውስጥ የማስታውሳቸው ናቸው: ሁሉም የማይገቡ መሆናቸው በጥልቅ ቢሰማቸውም ነገ ግን እራሳቸውን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ አሳልፈው መስጠታቸው በግልጽ ይስተዋል ነበር ልክ እንደ ያዕቆብ እያንዳንዱ ሰው ደኅንነት ለማግኘት ተማጽኖውን ያቀር0ና ይታገል ነበር EWAmh 201.1

    እነዚህ ህዝቦች ጽኑውን ጩኸታቸውን ማሰማት ከጀመሩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መላእክት ወደ እነርሱ ሄደው ሊታደጓቸው ቢወዱም ነገር ግን አንድ ረጅም ቁመና ያለው አዛዥ መልአክ ይህን እንዲያደርጉ አልፈቀደላቸውም ነበር ‹የእግዚአብሔር ፈቃድ ገና አልተፈጸመም: ጽዋውን መጠጣት አለባቸው:: በጥምቀቱ ሊጠመቁ ይገባል፡፡» EWAmh 201.2

    ወዲያው ሰማይና ምድርን ያናወጠውን የእግዚአብሔር ድምጽ ሰማሁ በየአቅጣጫው የነ ህንጻዎች ተንቀጠቀጡ በዚህን ወቅት ከፍ ያለና በጥራት የማደሙጥ የድል አድራጊነት ጩኸት ሰማሁ ከጥቂት ጊዜያት ቀደም ብሉ በሥቃይና ግዞት ውስጥ የነበሩትን ወገኖች ተመለከትኩ፡፡ ¡ስራታቸ ሞላ ብርሃን በላያቸው አንጸባርቆ ነበር ምንኛ ውብ ሆነው የጭንቀትና የድካም ምልክት ከላያቸው ጤናማነትና ውበት ይታይ ነበር፡፡ ተፈትተውና በግርማ የተይታዩ ነበር! እያንዳንዱ ላይ ተገፍፎ በመሄዱ በእያንዳንዱ ገጸታ ላይ EWAmh 201.3

    ደኅንነት ባገኙት በቅዱሳኑ ላይ ያንጸባረቀን ብርሃን በዙሪያዎቻቸው የነበሩ ጠላቶቻቸው መቋቋም ስላቃታቸው እንደ ሞቱ ሰዎች ሆነው ተረሩ የሱስ በደመና እስኪገለጥ ድረስ ይህ ብርሃንና ክብር አብሯቸው የነበረ ሲሆን ከያም እነዚህ ህዝቦች በቅጽበተዐይን ከክበር ወደ ክብር እየተለወጡ ሄዱ: መቃብሮች ተከፍተው ቅዱሳን የማይሞ ውን ለብሰው በመነሳት «ድል በሞትና በመቃብር ላይ» እያሉ ጮኹ። በእያንዳንዱ ህያው አንደበት ላይ በክብር የተሞ ሙዚቃዊ ጩኸት እየተሰማ በህይወት ካሉት ቅዱሳን ጋር በመሆን ጌታቸውን በአየር ለመቀብል ተነጠቁ:: EWAmh 201.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents