Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለሕይወት አንጀራ መራብ፡፡

    አንዲት መንፈሳዊት ሴት አንድ ጊዜ እንዲህ አለች፡፡ «የወንጌልን መልዕክት ዱሮ ስንሰማ አንደነበረጡ በሰማን ኖር! ወንጌላዊው መልካም ሰው ነው:: ግን የሰዎቹን መንፈሣዊ ፍላጐት አያስቀጥልም፡፡ የቀራንዮን መስቀል በአበባ ይከልለውና ነውርና ሐፍረቱን ይጋርደዋል፡፡ ነፍሴን የሕይወት እንጀራ እራባት፡፡ ቀለል ባለ አነጋገር በግልጽ ጥቅስ የሕይወት አንጀራ ቢቆረስልን እኔና አንደእኔ ያሉት እንዴት በተደሰትን፡፡GWAmh 20.1

    ማስተማር ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን የሚያገለግሉ የሃይማኖት ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ከእግዜአብሔር ጋር የሚራመዱ፤ከሰማይ ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የሚናገሩት ንግግር ለሰዎች ልብ የሚሰማ ዕውነተኛ ሰዎች ያስፈልጋል፡፡GWAmh 20.2

    ዕውቀታቸውን ለማሳየት የሚጥሩ ሰዎች ሳይሆን የእግዚአብሔርን መልዕክት በቀጥታ የሚያስተላልፉ ሰዎች ያስፈልጋል፡፡ አንድ የወንጌላዊ አንድ መልካም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በኋላ ‹ያስተማርኸውን በዕውነት ታምንበታለህ?» የሚል ጥያቄ ተሰነዘረበት፡፡ እርሱም «አንዴታ! » ሲል መለሰ:: ታዲያ ያልኸው ሁሉ ዕውነት ነው?” ሲል ጠያቂው በድጋሚ ጠየቀ፡፡ «ታዲያ ዕውነት ከሆነ ምን ማድረግ ይሻለናል” ሲል ጠያቂው ጠየቀ፡፡ ወንጌላዊውን የመጨረሻው ጥያቄ አሳሰበው፡፡ መልስ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር : ለሶስት ሳምንታት በፀሎት ተጠምዶ ሰነበተ፡፡ በመጨረሻ ሰውየው /ወንጌላዊው/ያስተማረው ትምሀርት በአዳማጮቹ ላይ ምንም ስሜት አንዳላሳደረ ተሰማው: የሥራውን ከባድነት ተገንዝቦ ከእግዚአብሔር ዕርዳታ በጠየቀ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ መነቃቃት ተፈጠረ፡፡GWAmh 20.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents