Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ጳውሎስ፣ የአህዛብ ሐዋርያ

  በታማኝነትና በማያቋርጥ “የጳውሎስ ከማንኛውም ወንጌላዊ በላይ ሆኖ ይገኛል፡፡ የሕይዎት ታሪኩና ስለሥራው ቅዱስነት ያለው አስተሳሰብ ዛሬ በሥራው ላይ ለተሰለፉ ሰዎች ማነቃቂያ ነው::GWAmh 35.2

  ጳውሎስ ሳይመለስ በፊት የክርስቶስን ተከታዮች በጥብቅ ያሳድድ ነበር፡፡ ግን በደማስቆ በር ላይ ድምጽ ሰማ ብርሃን አንጸባረቀበት፣ ያ ከተሰቀለው ጌታ የሰማው ድምጽ ሕይወቱን በሙሉ ቀየረው፡፡ ክዚያ በኋላ ያሳድደው የነበረውን ጌታውን በፍጹም ልቡ ወደደው:: ‹ከበለዓለም ዘመን ጀምሮ የተሰወረውን” የመግለጽ ኃይል ተሰጠው፡፡ «ይህ በአህዛብ፤ በነገሥታትም በአሥራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ሰእኔ የተመረጠ ዕቃ ነው» አለ እግዚአብሔር፡፡GWAmh 35.3

  በረዥሙ የአገልግሉት ሥራው ጳውሎስ የጌታውን ታማኝነት አሳጓደለም፡፡ «ወንድሞቼ ሆይ እኔ ገና አንዳልያዝሁት እቆጥራለሁ፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፡፡ በኋላየ ያለውን አየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፡፡ በክርስቶስ የሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ አንዳገኝ ምልክትን አፈጥናለሁ::» ጳውሎስ ልዩ ልዩ ሙያ ነበረው፡፡ ከከተማ ወደ ከተማ፣ ከአገር ወደ አገር በመዘዋወር ወንጌል እያስተማረ፤ ነፍሳትን እየመለሰ አቢያተ-ክርስቲያናትን ይቆረቁር: ላቋቋማቸው አቢያተ-ክርስቲያናት ይጠበብና ይጨነቅ በየጊዜው ለትምህርት የሚጠቅሙ ደብዳቤዎች ይጽፍላቸው በዚህ ላይ የዕለት ጉርሱን ለማግኘት መሥራት ነበረበት፡፡ ቢሆንም ፈጽሞ ወደ ከፍተኛው መጠራት የመገሥገሥ ዓላማውን አልሳተም፡፡ ጳውሎስ ሰማያዊ ስሜት ነበረው ፤ ተከታዮች ሁሉ ከክርስቶስ ጋር ትብብር አንዳለው ተሰምቶቸዋል፡፡ ሮሜ 1፲6:25፤ የሐዋርያት ሥራ 9፡፡15፤ ፊሊጺሲዮስ 3:13:14:GWAmh 35.4

  የራሱ አራአያነት ያለው ኑሮው ለወንጌል ሥራው መቃናት ምክኒያት ሆነው፡፡ የዕውነት ኃይል እስከዚህ ድረስ ነው፡፡ በክርስትና ዓለም ውስጥ ምሣሌነት ካለው ቅዱስ ሕይወት የበለጠ ሰሰዎች ትምህርት የሚሰጥ የለም፡፡ ክርክርና ጭቅጭቅ ጥልን ሊያስከትል : ግን የዕውነተኛGWAmh 36.1

  የሐዋርያው ጳውሎስ ልብ ሊጠፉ ባዘነበሉ ኃጢዓተኞች ፍቅር ተጠመደና በፍጹም ኃይሉ ከጥፋት ሊያወጣቸው ይታገል ነበር:: አንደአርሱ ያለ ራሱን የካደ ትጉ ወንጌላዊ የለም፡፡ የተቀበለውን በረከት ሌሎችን በመባረክ ተጠቀመብት፡፡ በችግር ያሉትን ከመርዳት ስለመድኅን ከመመስክር ተቆጥቦ አያውቅም፡: አማዳጭ ባገኘ ቁጥር ሰዎችን ከስህተት መንገድ መልሶ በጽድቅ መንገድ ማራመድ ይሞክር ነበር፡፡ ጳውሉስ የክርስቶስ አገልጋይነቱን አልዘነጋም፡፡ በቸልተኛነቱ ነፍሳት ቢጠፉ በኋላፊነተ መጠየቁንም አልሳተውም፡፡ «ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹህ አንደሆንሁ በዚሀት ቀን አመሰክርላችሁአለሁ ይላል፡፡ «ስለእናንተ እንደተሰጠኝ አንደ እግዚአብሔር መጋቢነት የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽሜ አንዳስተምር እኔ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ሆንሁ፡፡ ይህም ቃል ከበለዓለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ የዘለዓለም ምሥጢር ነው፡፡ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጦአል፡፡ ለእነርሱም የእግዚአብሔር በአህዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለጠግነት ምን አንደሆነ ሊያስታውቅ: ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው፡፡ እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሰጽን በጥበብ ሁለ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው:: ለዚህም ነገር ደግሞ አየተጋደልሁ እደክማለሁ::» የሐዋሪያት ሥራ 20፡26፤ ቆላሳይስ 1:25-29::GWAmh 36.2

  ይህ አነጋገር የእግዚአብሔር ሠራተኛ ሊደርስበት የሚችለውን ደረጃ ያመለክታል፡፡ ግን ራሱን ለክርስቶስ ያላስገዛ ሰው ከዚህ ደረጃ ሊደርስ አይችልም፡፡ ከክርስቶስ ዘንድ ያለው ኃይል የለውም፡፡ ከክርስቶስ ጋር ራሱን ያስተሣሠረ ሰው ከዚህ ኃይል ተቀብሎ ሰዎቸን ዕውነተኛውን የሕይወት ትርጉም ያስተምራቸዋል፡፡ የጳውሎስ አጻጻፍ «አገልግሎታችን እንዳይነቀፍ: በአንዳች ነገር ከቶ ማሰናኪያ አንሰጥም” ይላል፡፡ ለቲቶስም እንዲህ ሲል «ጎበዞችም ደግሞ ራሳቸውን አእንዲያስገዙ ምክራቸው የሚቃወም ሰው ስለእኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ አንዲያፍር በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግና ምሣሌ የሚሆን ራስህን ! በትምህርትም ደኀንነትን፣ጭምነትነትን፣ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ፡፡”GWAmh 36.3

  ስለራሱ ሥራ ለቆሮንቶስ አማኞች በጻፈው መልዕክቱ እንዲህ ይላል፡፡ «ነገር ግን በሁሉ አንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፡፡ በብዙ መጽናት፣ በመከራ፤ በችግር፣ በጭንቀት፣ በመከራ፤ በወህኒ፣ በሁከት፣ በድካም፣ በመጦም፣ በንጽህና፣ በዕውቀት፣ በትዕግሥት፣ በቸርነት፤ በመንፈስ ቅዱስ፤ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፣ በዕውነት ቃል፤ በእግዚአብሔር ኃይል፣ ለቀኝና ለግራ በሚሆን ለጽድቅ የጦር ዕቃ፣ በክብርና በውርደት፣ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን አናማጥናለን፡ አሳቾች ስንባል ዕውነተኞች ነን፣ ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን:: የምንሞት ሰንመስል አነሆ ሕያዋን ነን: የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፣ ሐዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፡፡ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለጠጐች አናደርጋለን፡፡ አንዳች የሌለን ስንሆን ሙሉ ነው፡፡» 2ኛ ቆሮ 6:3፤ቲቶ 2፡6-8፤ 2ኛ ቆሮ 6:4-10::GWAmh 37.1

  ጳውሎስ የኃላፊነት ስሜት ስላለው የምህረትና የቅንነት ምንጭ ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር ጥብቅ ግንኙነት ነበረው፡፡ ለክንውንነቱ ማስተማመኛ አድርጐ የክርስቶስን መስቀል ተጠቀመው፡፡የመድኃኒታችን ፍቅር ራሱን ለማሸነፍና ክፉን ለመቋቋም የጦር መሣሪያው ክርስቶስን ለማገልገል የጠላቶቹን ተቃውሞና የክፉዎችን እንቅፋት ሁሉ ጥሶ ወደፊት ገሠገሠ፡፡GWAmh 37.2

  ዛሬም ቤተክርስቲያን የምትፈልግ፣ አንደ ጳውሎስ ራሳቸውን ከጥቅም ላይ ለማዋል በመንፈስ የሠለጠኑ፤ በእግዚአብሔር ሥራ ሕይወታቸው የተመራ፤በበጐ ፈቃድና በንቃት የተነሱ ሰዎችን ነው፡፡ የተቀደሱ ራሳቸውን ለመሠዋዕትነት አሳልፈው የሰጡ ሰዎች ያስፈልጋሉ: በልባቸው ክርስቶስ «የክብር ተስፋ” የሰፈነባቸው ጀግኖች፣ በመንፈስ ቅዱስ እሳት አፋቸውን የፈቱና «የማያስተምሩ» ሰዎች ይፈለጋሉ፡፡ እንደእነዚህ ያሉ ሰዎች በመታጣታቸው የእግዚአብሔር ሥራ ይጐሳቆላል፡፡ ሐሰት ሰምተን ግብረገብ አንደመርዝ ይበክላል፡፡ ታማኞቹ ተራቸውን አድርሰው ሲያልፉ በአግራቸው የሚተካ ማን ይሆን?GWAmh 37.3

  ወጣቶቻችን ይህን ቅዱስ ሥራ ለማካሄድ የአባቶቻቸውን ጋሻ ያነሱ ይሆን? ታማኞች በመሞታቸው የተገኘውን ክፍት የሥራ ቦታ ለመሙላት ፈቃደኛ ናቸው? ወጣቶች ራሳቸውን መውደድ ትተው የሐዋርያትን ተማጽኖ ይቀበሉት ይሆን?GWAmh 37.4

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents