Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ዕውነተኛ ትምህርት

    «አከአይወተ የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሥበት ጊዜ ይመጣልና ነገር ግን ጆሮአቸውን የሚያሳክክ ስለሆነ እንደገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ ዕውነትንም ከመስማት ጆሮአቸውን ይመልሳሉ፡፡ ወደተረትም ፈተቅ : አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፣ መክራን ተቀበል፣ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ አገልግሎትህንም ፈጽም፡፡” (2ኛ. ጢሞ. 4፡3-5)GWAmh 202.3

    «ዕውነተኛ ትምህርት” ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ነው:: እርሱም ሃይማኖትንና ዕውነተኛነትን ያጐለምሣል፡፡ ዕውነተኛ ትምህርት ለተቀባዩም ለአቀባዩም ይበጃል፡፡ ማንም የሚሠራው ሥራ ዕውነተኛ ነት ወይም ሀሰተኛነት የራሱን ኃላፊነት ይጠይቃል፡፡ ጳውሉስ አንደገና እንዲህ ሲል ይጽፋል፡፡GWAmh 202.4

    «ቃሱ የታመነ ነው እንዲህ የሚለው፡፡ ከእርሱ ጋር ብንሞት ከእርሱ ጋር ደግሞ አንኖራለን፡፡ ብንጸና ከእርሱ ጋር እንነግሣለን፡፡ ብንክደው እርሱ ደግሞ ይክደናል፣ ባናምነው የታመነ ሆኖ ይኖራል፡፡ ራሱን ሊክድ አይችልምፍ፡፡GWAmh 202.5

    ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሱ በእግዚአብሔር ፊት ምክራቸው፡፡ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውፍ› (2ኛ ጢሞ. 2፡11-14)GWAmh 202.6

    በጳውሎስ ዘመን የነበሩ ሰዎች ዕውነቱን እየሰሙ ያልሆነ ጥያቂ በመሰንዘር የመምህሩን ሀሳብ ከጠቃሚ ትምህርት ያስወግዱታል፡፡ ያልረባ ጭቅጭቅና ጥል ማብረድ የወን?ላዊን ክቡር ጊዜ ያባክን ነበር፡፡ ጳውሎስ የጠላትን ዘዴ ስለሚያውቀው ከመታለል አዲድኑ ይመክራል፡፡ የወንጌላዊው ዋና ዓላማ የነዓና፡ሳች መመለስ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ለጭቅጭቅና ለንትርክ ቦታ መስጠት የለበትም፡፡GWAmh 202.7

    ቅዱስ ጳውሎስ «እውነትን በቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ስታቀርብ ትጋ፡፡ ነገር ግን ሰዓለም ከሚመች ከከንቱ መለዓለፍ ራቅ፣ ኃጢዓተኝነታቸውን ከፊቱ ይልቅ ይጨምራሉና::› 2ኛ ጢሞ. 2:15- 16) ሲል ጽፈል፡፡GWAmh 203.1

    ዛሬም የክርስቶስ አገልጋዮች ይኸው አደጋ ተደቅኖባቸዋል፡፡ ዕውነት በሰዎች ልብ ውስጥ አንዳይዘራ ሰይጣን የሰዎችን አስተሳሰብ ወዳልሆነ መንገድ ይጠመዝዘዋል፡፡ ወንጌላዊያንና ሕዝቡ ዕውነትን ተጠማጥመው በእርሷ ካልተቀደሱ አእምሮአቸው በአጉል ጥያቄና ክርክር ይይዛል፡፡ ብዙ የሚፈጥሩ ነገሮች ይገኙና ሁከትና ንትርክ ይበዛል፡፡GWAmh 203.2

    ችሎታ ያላቸው ሰዎች ፅድሜ ልካቸውን መጽሐፍ ቅዱስን በጸሎት ተጠምደው ቢመረምሩተም ገና ያልተብራራ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል : አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በወዲያኛው ዓለም ክርስቶስ አስቲያብራራላቸው ድረስ በፍጹም የማይስተዋሉ ናቸጡ::: የማይመረመሩ ምሥጢራት፣ የማይስተዋሉ ዐረፍተ-ነገሮች አሉ፡፡ ሰይጣን በእነዚህ ጥቅሶች አሳብቦ ጭቅጭቅ ስለሚያስነሳ አለመነጋገሩ መልካም ነው:::GWAmh 203.3

    ዕውነተኛ መንፈሣዊ ሠራተኛ ጊዜውን በጥቃቅን ነገሮች ከማጥፋት ይልቅ ለዓለም ሊታወጅ የሚገባውን ታላቅ ዕውነት ጠንቅቆ ይመረምራል፡፡ ሕዝቡን ወደ መዳን ታሪክ፤ ወደ እግዚአብሔር ትእዛዝና ወደ ክርስቶስ ዳግም ምፃዛት ያመላክታቸዋል፡፡ በእነዚህ አርአስቶች በቂ የአእምሮ ምግብ መኖሩ አይጠረጠርም፡፡GWAmh 203.4

    ባለፈው ጊዜ ሰዎች የማያስፈልጉ ትምህርቶችን አውስተዉልኝ አንዳንዶቹ አማኞች ሲጸልዩ ዓይኖቻቸውን መግለጥ አለባቸው አሉኝ፡፡ ያለፉት የብሉይ ኪዳን ካህናት ወደ ቤተመቅደስ ሲገቡ ጫማቸጡን አውልቀው እጆቻቸውን ታጥበጦ ነበርና ዛሬም አማኞች ወደቤተ-ጸሎት ሲገቡ ጫማቸውን ማውሰቅ አለባቸው ያሉም ነበሩ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ፅኛውን ትፅዛዝ በማውሳት ተባዮች አንኳን መገደል የለባቸውም አለሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የሚድኑት አይሸብቱም ብለው በማይረባው ነገር ለመከራክር ይፈል? ነበር፡፡GWAmh 203.5

    እንደነዚህ ያሉ የማይረባ ትምህርቶችን የሚያቀርቡ ሰዎች ወንጌልን በሚገባ ያላጠኑ መሆናቸው ተነግርኛል፡፡ በእንዲህ ያሉ ጥቃቅን ነገሮች ጠላት ዕውነትን ያደናቅፋል፡፡GWAmh 204.1

    በወንጌላዊነት ተሰልፈው በጥቃቅን ነገሮች ጊሼኬሼያቸውን የሚያሳልፉ ስዎች በስንፍና ታስረው እንደተቀመጡ አንጂ አንደሠሩ አይቁጠሩት፡፡ እንደነዚህ ያሉን ነገሮች በማውጣት በማጡረድ ወንጌላዋያን ጊዜአቸውን አያጥፉ፡፡ ምን አንደሚያስተምሩ የተደናገራቸውና አርእስቱ የጠፋባቸው ታላቁ ሙምህር ያስተማረውን በማጥናት ክከእርሱ ይማሩ፡፡ የሱስ ተፈላጊነት አንዳላቸው የቀጠራቸው ትምህርቶችን ዛሪ እኛ ልናስተምራቸው ይገባናል፡፡ ዘለዓለማዊ በሆኑት አርዕስተ-ነገሮች ክርስቲያናት እንዲኖሩ አናደፋፍራቸው፡፡GWAmh 204.2

    አንድ ጊዜ አንድ ወንድማችን ዓለም ጠፍጣፋ ነች የሚል ክርክር ይዞ ወደ እኔ በመጣ ጊዜ «እንግዲህ ሂዚድና ዓለምን ሁሉ አስተምሩ እነሆ እኔ ከአላንት ጋር ነኝ እስከ ፍጻሜ ከመን” የሚለውን መምሪያ እንድነግረው ታከዝሁ፡፡ (ማቴዎስ 28፡19፣20ዐ)፡፡GWAmh 204.3

    ለእንዲህ ያሉ ክርክሮች አግዚቢአብሔር «ያ ሰእናንተ ምን ያደርግላኙ3ቷል? ተክተሉኝ፣ ትዕዛዝና መመሪያ ሰጥቻችኃለሁ፡፡ በሚጠቀቅማትሁ ነገር ተመራመሩ፡፡ ለሥራችሁ ዕርዳታ በማይሰጡ ነገሮች ጊዜ አታባክኑ” : በክዲስቱ ምድር ምን ይገኝ ይሆን አያሱ ወንጌላዊያን በክርክር መድክም የለባቸውም፡፡ እግዚአብሔር ያልገለጠልንን ነገር በግምት አየቀመሩ መከራከር የማይፈለግ አጉል ድካም ነው፡፡ በሚመጣው የሚበጀንን መምሪያ ሁሉ ገልጦልን ሳል ከዚያ አልፈን በሀሳብ ባሕር መዋኘት ሰጥሞ ለመዋቀረት : የሚመጣውን ሕይወት ባሁኑ ኑሮ ልንገምተው አንችልም፡፡GWAmh 204.4

    ለወንጌላዊያን ወንድሞቼ ቃሱን አስተምሩ. አሳሰሁ፡፡ ማንንም የማይጠቅሙትን አንደ ገለባ፤ አእንጨትና ድርቆሽ የሚቆጠሩትን የራሳችሁን አስተያየቶች ለመሠረት አተጠቀሙሙባቸው፡፡ ተፈላጊነት ያላቸው ነገሮች ተገልጠውልናል፤ ለመማርና ለመመራመር የሚበጅ እነርሱ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ያልነገርንን ልንመራመር አንችልም፡፡GWAmh 204.5

    ያልተረጋገጥንበት ጥያቄ ሲያጋጥመን «መጽሐፍ ምን ይላል?» ብለን አንጠይቅ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚያ ጥያቄ ምንም ካላለ አንተወው፡፡ አዲስ ነገር የሚፈልጉ ከአዲስ መወለድ የሚገኘውን የሕይወት መታደስ ይሹ:: ሕይወታቸውን ዕውነትን በመታዘዝ በዕውነት ያንጹ፡፡ ክርስቶስ የሰጠውን ዋና ትምህርት ይታዘከኩ፡፡ በፍርድ ቀን የሚጠየቀጡ ጥያቄ «ትዕዛዛቴን አክብረዋል ወይ?” ነው፡፡GWAmh 205.1

    ያልሆነ ጥያቄና በማይረባ ነገር መክራከር በእግዚአብሔር አቅድ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ዕውነትን የሚያስተምሩ ሰዎች የሚያስተምራቸውን ወደ አሜካላ ሜዳ ከተው በገባችሁበት ው የማይሉ ጽኑ ሰዎች መሆን አለባቸው፡፡GWAmh 205.2

    ክርስቶስ ኃጢዓትን ለመሻር መሠዋቱ፣ ሴሉች ዕውነቶች ሁሉ የሚያብራሩት ታላቁ ዕውነት ነው:: ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ዮሐንስ ያለው ትምህርት በሙሉ ይስተዋል ዘንድ ከቀራንዮ መስቀል ጋር መዛመድ አለበት፡ በፊታችሁ የሚቀርብሳችሁ ታላቅ የመዳን ሐውልትና የምህረት አርማ የተሰቀሰውን ክርስቶስ ነወ: ወንጌላዊያን ሲያስተምሩበት የሚገባ አቢይ አርዕስት ይህ ነው፡፡GWAmh 205.3

    በአሁነ ዘመን የሚፈለጉ የሕዝቡን ፍላጐት አስተውለው እንደ አስፈላጊነቱ የሚሠሩ ሰዎች ናቸው:: ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ በጥንቃቂ ያስተምራል፤ ይገስጻል፤ ያስጠነቅቃል፣ ያደፋፍራልም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አባሪነት እያንዳንዱን ሰው ፍጹም አድርገ ለማቅረብ ይጥራል፡፡ እንዲህ ያሰ ሰው በክርስቶስ ምሣሌነት የሚራመድ ታላቅ አገልጋይ ተብሎ ይቅጠራል፡፡GWAmh 205.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents