Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ገንዘብን በብልሃት መከፋፈል

  የቤተ ክርስቲያን አባሎች ቤተ ክርስቲያንን ለመደገፍ በፈቃደኝነት ገንዘብ ማዋጣት ይገባቸዋል፡፡ ገንዘብ አያያዝንና ለራሴ ብቻ አለማለትን መማር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከበጎ አድራጎት መንፈስ መራቅ የለባቸውም፡፡ የተሻለ አገር የምንፈልግ መናኞችና መጻተኞች ስለሆንን መሥዋዕት በማቅረብ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት አለብን፡፡ ነፍሳችን ለመመለስ የተሰጠን ጊዜያችን በማጠሩ ከዕለት ፍላጎታችን የተረፈውን በምሥጋና መልክ ለእግዚአብሔር እንመልስ፡፡GWAmh 303.4

  በቃልና በትምህርት የሚያምነኑ ሰዎች የሚያምነብትን በመስዋዕት መግለጥ ይኖርባቸዋል፡፡ የተለገሠውን ሥጦታ ተቀብለው ክተገቢ ቦታ ላይ እንዲያውሉት ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ኃላፊነታቸው ከባድ ነው፡፡ የአግዚአብሔርን ሥራ በሚገባ አጥንተው ገንዘቡን ከተፈላጊ ቦታ ላይ ማዋል አለባቸው፡፡ «መንግሥትህ ትምጣ፣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች አንዲሁም በምድር ትሁን» (ማቴ 6:10) የሚለውን የጌታ ጸሎት በመደገፍ መንግስቱን በምድር ላይ ለመቆርቆር የክርስቶስ ተባባሪዎች መሆን ተግባራቸው ነው፡፡GWAmh 304.1

  በዓለም ዙሪያ ያለው ሥራ ሁሉ መዘንጋት የለበትም፡፡ አዳዲስ የሥራ መስመሮችና ቦታዎች መከፈት አለባቸው፡፡ በአዲስ ቦታ ሥራ ለመቆርቆር ብዙ ድካምና ብዙ ገንዘብ ማስፈለጉን ወንድሞች ይወቁት፡፡ በውጭ አገር ለሚቋቋመው ሥራ የሚያጋጥመው ችግር ተገምቶ ፈዋደኛ ድጋፍ የሥራው መሪዎች የሆኑ ሰዎች በዓለም ዙሪያ ሊዳረስ ለሚገባው የአግዚአብሔር ዕውነት መጋቢዎች ናቸውና በልዩ ልዩ ይሰራ : የሚፈለገውን ነገር በጥልቅ ይመርምሩ፡፡ ተፈላጊውን ነገር ጠንቅቀው ላለማወቃቸው ምንም ዓይነት ምክንያት ቢያቀርቡ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በእያንዳንዱ የሥራ ዘርፍ ያለውን ጥቅምና ጉዳት ለይተው በማወቅ ራሳቸውን ሳይቀጥቡ ለጠቅላላው ሥራ ዕድገት መሥራት አለባቸው፡፡GWAmh 304.2

  የተገኘውን ገንዘብ በትክክል አከፋፍለው ከሥራው ላይ ለማዋል የሚፈልጉ መሪዎች በቅርብ በሩቅም ያለውን ችግር በትክክል ለማየት ይችሉ ዘንድ ዕውነተኛ ጥበብ ለመቀበል ወደ እግዚአብሔር ይቅረቡ፡፡ ልመናቸው በከንቱ አይቀርም፤ ሥራውን በልዩ ልዩ ቀበሌ ለማስፋፋት ከልብ ቢጠይቁ ከላይ ጥበብ ይላክላቸዋል፡፡GWAmh 304.3

  በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ለሚሠሩ ሠራተኞች «ለእኔ ብቻ» የማያሰኝ አኩልነት መደረግ አለበት፡፡ በአሥራትና በሥጦታ አማካይነት ከአባሎቹ የሚሰበሰበው ለሀገር ውስጥ ስራ ብቻ ሳይሆን ለውጭ አገርም መዋል እንዳለበት በበለጠ ማስተዋል አለብን፡፡ ከተቋቋሙ ብዙ ጊዜ በሆናቸው የሥራ ቦታዎች ያሉ ሰዎች ችግራቸውን ራሳቸው ለመወጣት በ.ሞክሩ አዲሶቹን ቦታዎች ለማራመድ ይቻላል። ቀደም ብለው በተቋቋሙት ድርጅቶች በዘንድ አንዳንድ ጊዜ ከጥቅም ላይ ጥቅም የመደረብ ፍላጎት ይታያል፡፡ እግዚአብሔር ግን እንዲህ አይሁን ይላል፡፡ በመዝገቡ ያለው ገንዘብ በዓለም ዙሪያ እንዲሠራበት ይፈልጋል፡፡GWAmh 304.4

  በጌታ የወይን ቦታ የሚገባውን ያህል ያልተሠራባቸው ቦታዎች ቀደም ብለው የተቋቋሙት ችግራቸውን አንዲያስተውሉላቸው ይፈልጋሉ፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድ በተስፋፋ ቦታ በመሥራት ላይ የሚገኙ ሰዎች አጃቸውን ለርዳት ለመዘርጋት ይነሳሱ፡፡ ሌላ መሥሪያ ቤቶች ሲጠፉ ሲያጣጥሩ ለራሳቸው ታላላቅ ነገሮችን ለመጨመር አይጓጉ፡፡ የሚሲዮናዊን የሥራ መስመሮች ተቸግረው ሳል ተጨማሪ ነገር የሚጠይቁ ቦታዎች ራሳቸውን በመውደድ ነው፡፡GWAmh 305.1

  እግዚአብሒር በአንዳንድ አገሮች የሚካሄደውን ሥራ በሌሎች አገሮች ከሚካሄደው አብልጦ ቢባርከው የመረዳዳትን መንፈስ ለማነሳሳት፣ በችግር ላይ ያሉትን ለማቋቋም ህብረት አንዲፈጠር፤ ሥራውንም በሚገባ ለማደራጀት ብሎ ነው፡፡ እግዚአብሔር በልዩ ልዩ ቦታ ባሉ ሰዎች መካከል ልዩነት አያደርግም፡፡ ሥራው አንድ የተሟላ ታላቅ ማህበር ነው፡፡ ዕውነቱ ለወገን፣ ለነገድ፣ ለቋንቋ፣ ለሕዝብም ሁሉ መዳረስ ስላለበት አዲስ ስፍራ ሲቋቋም መሰብሰቢያ ቤቶች መሥራትና ሌላም ዝግጅት መደረግ አለበት፡፡GWAmh 305.2

  በልዩ ልዩ የዓለም ማተሚያ ቤት ይቋቋም፡፡ በአዲስ ቦታ የተቋቋመው የእግዚአብሔር ሥራ ወደፊት አንዳይራመድ መለያየት እያደረጉ አንዳንድ ቦታዎችን ወድቀው አንዲቀሩ የሚያደርጉትን የአንዳንድ ሰዎችን ምሣሌነት መከተል ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማክበር ይገባል፡፡GWAmh 305.3

  የአንዳንድ ሰበካ ዓላማ ብዙ ገንዘብ ሰብስበው በግምጃ ቤታቸው ገንዘብ እንደተረፋቸው ማሳየት ነው፡፡ ግን እግዚአብሔር በዚህ አይከብርም፡፡ ተፈላጊ በሆነ ቦታ ለትጉ ሠራተኞች መደገፊያ ቢውል የበለጠ ሞያ ሠራ ማለት ነው፡፡ በገንዘብ አያያዛቸው መሪዎቻችን ገንዘብን በሚገባው ሥራ ላይ ባለማዋል ጉዳት እንዳያደርሱ ይጠንቀቁ፡፡ ትምህርት ቤቶችና የጤና ጣቢያዎች ለመሥራት እነዚህ መሥሪያ ቤቶች እግዚአብሔር የፈለገውን ያህል ሊስፋፋበት የሚችል በቂ ቦታ መገዛት አለበት፡፡ አትክልትና ፍራፍሬ የሚበቅልበት ቦታ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ለሥራው ተቃዋሚ የሆነ መሥሪያ ቤት አንዳያቋቁሙ- አካባቢውን ሠፋ አድርጎ መያዝ ተገቢ ነው፡፡GWAmh 305.4

  አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች በአንድ ቦታ ያለውን ሥራ አሳድገው ወደሌላ ቦታ ሲዛወሩ ውለታቸው ሳይታወቅ ለሥራቸው ማደፋፈሪያ ጥቅም ሳይቀበሉ ይቀራሉ፡፡ ይህ ነገር ተስፋ ያስቆርጣቸውና ለሥራውም እንቅፋት ይሆናል፡፡ በከተማ ውስጥ መሥራት ገንዘብና ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ የሚያፈገፍጉ ሰዎች ክርስቶስ ልጁን ያለማመንታት ለዓለም እንደሰጠ ያስታውሱ፡፡ ሰዎች ከልብ ቢነሳሱና በእግዚአብሔር ሙሱ ዕምነት ቢኖራቸው ናሮ ከተማዎቻችን መልዕክቱን ባገኙ : በሚሲዮን ሥራ የገንዘብ አያያዝ የእግዚአብሔር ሠራተኞች በጥበብና በትህትና መሥራት አለባቸው፡፡ ብዙ አየሞከሩ ጥቂት ብቻ የማያከናውኑ አሉ፡፡ ጥረታችን አተኩረን መመልከት አለብን፡፡ እያንዳንዱ የፈጸምነው ሥራ መታወቅ አለበት፡፡ ሰዎችን ለማቅረብ የተሻለውን ዘዴና መንገድ አስበን ልንደርስበት ይገባል፡፡ የሚሲዮን ሠራተኞቻችን የገንዘብ አያያዝ ማወቅ አለባቸው፡፡ ምንም ክፍተኛ ምንጭ ቢኖረን በዝባዦች መሪዎች ካሉ ምንጩ ሊደርቅ ይችላል፡፡ የሚያቁተው ማቋቻ አፍሳሽ ከሆነ ምንም ውኃ በዕቃው ውስጥ አይገኝም፡፡GWAmh 306.1

  ለአንድ ቦታ አስፈላጊ ወይም ከፍተኛ ጥረት እንዲደረግለት የመወሰኑ ጉዳይ በአንድ ሰው ትከሻ ላይ ብቻ መጣል የሰበትም፡፡ በአንድ የሥራ መስመር ብቻ ብዙ ወጭ አንዲደረግ የሚወስኑ ስዎች በሌላ በኩል የሚደረገውን የተሻለ ውጤት የሚያስገኙ ሥራዎችን መዝጋታቸው ነው፡፡GWAmh 306.2

  ወጣት ሠራተኞቻችን የበለጠ ሥራ ልምድ ካላቸው ሰዎች ጋር አየተመካከሩ ከሰዎች ጋር በዝግታና በማስተዋል መሥራትን ይማሩ፡፡ አንዳንዶቹ ራሳቸውን ከፍ አድርገው ይገምታሉ፡፡ በትህትና መንፈስ የሚመራ ሥራ የበለጠ ውጤት አለው። ወጣቶች ኃይልና ብርታታቸውን በሥራ ላይ ሰማዋል በሥራ መስመር መሰለፋቸው መልካም ነው: ግን ራሳቸው ብቻቸውን እንዲሠሩ በመፍቀድ የእግዚአብሔርን ሥራ ዕዳ ብቻ አንዲያደርጉት አይፈለግም፡፡ የራሳቸውን ወጭ ለመቋቋም ሁሉም በጥበብ መስተዳደር አለባቸው፡፡ ሥራው ራሱን የቻለ እንዲሆንና ሰዎቹም በራሳቸው አንዲተማመኑኑ ማስተማር ተገቢ ነው፡፡GWAmh 307.1

  ሥራውን በግል ጥረት የማካሄድ ስሜት ሳያድርባቸው ለመሰብሰቢያ አዳራሽ በርከት ያለ ገንዘብ መክፈል ወንጌላዊያን አይገባቸውም፡፡ ገንዘብን በማባከን የሚገኘው የሥራ ውጤት አጥጋቢ አይደለም፡፡ ሰዎች ለመስማት ቢፈልጉና ቤተ ክርስቲያኖቻቸውን ከፍተው ቢቀበሉ አንድ ወንጌላዊ ሄዶ ቢያስተምር መልካም ነው፤ ነገር ግን የተለየ ሥጦታ ወይም ችሎታ. አለኝ ብሎ ገንዘብ ቢያባክን ውጤቱ አያምርም፡፡GWAmh 307.2

  ወደ ውጭ ለሚሜሲዮናዊነት ሥራ ሰዎች ሲመረጡ የገንዝብ አያያዝ የሚያውቁ፤ ብዙ የቤተሰብ አባል የሴላቸው፤ የጊዜውን ማጠር ተገንዝበው ጠቅላላ ሀሳባቸውንና ጥረታቸውን ለተላኩበት ተግባር ብቻ የሚያውሉ መሆናቸው መረጋገጥ አለበት፡፡ ሚስቲቱ አንደሚገባት ለስራው ብትሰለፍ ከባሏ ጋር መልካም ሥራ ልታክናውን ትችላለች፡፡ ከልባቸው የተነሳሱ ሚሲዮናዊያን ያስፈልጉናል፡፡ ሌላውን ነገር ሁሉ ወደ ጎን ትተው የእግዚአብሔርን ስራ የሚያስቀድሙ መሆን አለባቸው፡፡ ዓይናቸውን በእግዚአብሔር ሥራ ላይ አሳርፈው በተጠሩበት ጊዜ ወደሚላኩበት ቦታ ለመሄድ የቁረጡ ዝግጁ ወታደሮች ይሁኑ። እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚወዱ፤ ሚስቶች ያሏቸው፤ በሥራውም ባሎቻቸውን የሚረዱ ታማኝ ባለቤቶች ያገቡ ሰዎች ለሥራው ይፈለጋሉ፡፡GWAmh 307.3

  ሠራተኛቻችን በእግዚአብሔር ቤት ብቻ ሳይሆን በራሳቸው ቤትም የገንዘብ አያያዝ ማወቅ አለባቸው፡፡ ቤተሰባቸውን በዝቅተኛ ወጭ ሊያስተዳድሩበት በሚችሉበት አካባቢ መኖር አለባቸው፡፡ ልመና መረዳጃ ለኛ ቤተ ክርስቲያን ሰራተኞች አይፈቀድም፣ ግን ባላቸው ገንዘብ መተዳደር የማይቸሉ ሰዎች ይህን ማድረግ ግድ ይሆንባቸዋል ወይም ሌላ ሥራ መያዝ ሊያስፈልጋቸው ነው፡፡ ራስን ከልክ በላይ የማስደሰት ልምድ ወይም የቤት አመቤቲቱ የቤተሰብ አስተዳደር አለማወቅ ለገንዘብ ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለቤት አያያዝ የሚበቃ ትምህርት ስለሌላት ወይም የርሷንና የልጆቿን ፍላጎት መቀነስ ተፈላጊ መስሎ ስላልታያት እናትዮዋ በደንብ የምትሠራ ይመስላት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ለሁለት ቤት የሚበቃ ገንዘብ አንድ ቤተሰብ ሊጨርስ ይችላል፡፡GWAmh 308.1

  ሁሉም ገንዘባቸውን ወይም ወጭና ገቢያቸውን መቆጣጠር መቻል ይገባቸዋል፡፡ አንዳንዶች ይህን ነገር ተፈላጊ አድርገው አለመገመታቸው ስህተት ነው፡፡ ብዙ ሠራተኞቻችን ሊማሩት የሚገባ ዋና ነገር ነው፡፡ ማንኛውም ወጭ በጥንቃቄ መጻፍ አለበት፡፡ በገንዘብ አያያዝ በኩል በሚታየው ጉድለት እግዚአብሔር አዝኗል፡፡ ትንሽ ተጨማሪ ጥንቃቄ ቢደረግ ኖሮ ስብሰባ ከማድረግና ከዚ ችግር በተዳነ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ግንኙነት ያለው ማንኛውም ነገር የሰው ችሎታ በፈቀደ መጠን ሊሆን ይገባዋል፡፡GWAmh 308.2

  የእግዚአብሔር ሠራተኞች ስለሆናችሁ እርስ በርሳችሁ መቀራረብ ይገባችኋል፡፡ መፈቃቀር፣ መከባበር፣ መተማመን የትም የት ቢሆን ሊታዩ ይገባል፡፡ የምታስተምሩትን በሥራ ላይ ማዋል አለባትች፡፡ አዲስ አማኞች እንደምሣሌ እድርገው እንደሚያዩአችሁ ልብ አድርጉ፡፡GWAmh 308.3

  አንዳንድ የምታገለግሏቸው ሰዎች የራሳቸው መንገድ ከሁሉ የተሻለ እየመሰላቸው ሥራው እነርሱ አንደወደዱት አንዲካሄድ ይመኛሉ፡፡ ነገር ግን ገርነት ካላትሁና በክርስቶስ ያደረ ልብ ቢያድርባችሁ፣ ብትፈቃቀሩና ብትከባበሩ ሥራውን አምላክ በወደደው መንገድ ልታከናውኑት ትችላላችሁ፡፡ ክርስቶስን አስክትመስሉ ነፍሳችሁን ለጌታ አስገዙ፡፡ እንዲህ ከሆነ የምታስተምራቸውን ወደ ዕውነት በበለጠ ልትስቧቸው ትችላላችሁ፡፡GWAmh 308.4

  የተደላደለ ፅቅድ ከሌለ በተለይ በውጭ አገር ያለው ሥራ ሊራመድ አይችልም፡፡ ከመሪዎች ጋር ተባብራችሁ ለመሥራት በምትሞክሩበት ጊዜ መፍትሄ የሚገኝላቸው የማይመስሉ አጋጣሚዎች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ያን ጊዜ በቦታው ያሉት ሰዎች ቀርበው መጋፈጥ አለባቸው፡፡ ቁርጠኛ ተግባር ወዲያው መደረግ የሚያስፈልጋቸው ጊዜ የማይሰጡ ነገሮች ይፈጸማሉ፡፡GWAmh 309.1

  በአዲስ ቦታ ሥራ ሲጀመር በትክክለኛ መንገድ መጀመሩ በጣም ጠቃሚ ነው : በጠባብ አስተሳሱበ ሥራውን እንዳይወሰን ሠራተኞቹ መጠንቀቅ አለባቸው፡፡ በገንዘብ በኩል ጥንቃቄ መደረግ ያለበት መስሎ ሲታይ ገንዝቡ ከትርፍ ይልቅ ጥፋትን እንዳያስከትል ያሰጋል፡፡ ሠራተኛቻችን ዋናው ዓላማቸው በተቻለ መጠን በጥቂት ገንዘብ ሥራው ለማካሄድ በሞከሩበት አንዳንድ ቦታ ላይ ካሁን በፊት ጉዳት አድርሰዋል፡፡ አያያዙ ተሻሽሎ ቢሆን ኖሮ ከዚያ የበለጠ በተደረገ ነበር፡፡ ከዚያም በላይ ከግምጃ ቤት ወጭ የሆነው የገንዘብ ልክ ዝቅተኛ በሆነ ነበር፡፡GWAmh 309.2

  በአዲስ ቦታዎች የሥራችን ዕድገት የማይፋጠነው የምናስተምረው የተለየ ዕውነት በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ስለማያገኝ ነው፡፡ የሰንበት አጠባበቅ ዕውነቱን ለሚቀበሱ ሁሉ ሸክም ይሆንባቸዋል፡፡ ብዙዎች ዕምነታችን መጽሐፍ ቅዱስን የተመረኮዘ መሆነን እያዩ መቀበሉ ይከብዳቸዋል፤ ምክንያቱም የተለዩ ሆነው ለመታየት ካለመፈለጋቸው በላይ ዕውነትን በመከተል ደጋፊ እንዲያጡ አይፈልጉም፡፡GWAmh 309.3

  እንዲህ ዓይነት ችግር ስላለ ዕውነቱን ለሕዝብ ለማቅረብ ዘዴና ብልሃት ያስፈልጋል፡፡ በአንዳንድ ቦታ በትንሽ የተጀመረው ሥራ ቀስ በቀስ ማደግ : ሠራተኞች ሁሉ ሊያደርጉ የሚችሉ ይህን ብቻ : ግን በሌላ በኩል መልካም ውጤት ሊያስገኝ የሚችል መልካም አጀማመር ለመቆርቆር በተቻለ ነበር፡፡ በእንግሊዝ አገር ያለው ሥራችንን ሲጀምሩ ወንድሞች በሌላ ዘዴ ባይጀምሩት ኖሮ ሥራው አሁን ካለው በበለጠ በሆነ ነበር፡፡ መልካም አዳራሾች በመከራየት፣ ድል አድራጊ መልዕክት የያዙ መሆናቸውን ለማስረዳት ሞክረው ቢሆን ናሮ ከፍተኛ ክንውንነት ባገኙ ነበር፡ እግዚአብሔር ሥራው አንዲጀመር የሚፈልግ ገና ካጀማመሩ ሰዎችን ሊስብ የሚችል ሆኖ ነው፡፡GWAmh 309.4

  የሜሲዮናዊነትን ሥራ ክቡርነት አንዳታዋርዱ ተጠንቀቁ፡፡ ከሥራችን ጋር ግንኙነት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ «ማነኝ? ምን ማድረግና ምን መሆን አለብኝ? ብለው ይጠይቁ፡፡ ራሳቸው የሌላቸውን ለሌሎች መስጠት እንደማይችሉ ሁሉም ይወቁ፡፡ እንዲ ከሆነ ባላቸው ነገር በቃኝ ይበሉ የተፈጥሮ ልምዳቸውን ለማሻሻል ይሞክራሉ፡፡ ጳውሎስ «ወደ ምልክቱ አፈጥናለሁ» ዘፊለ.. 3፡14) የተሟላ ጠባይ አንዲኖረን ከፈለግን የማያቋርጥ ጥረት ያስፈልገናል፡፡GWAmh 310.1

  ሥራውን በከፍተኛነት የሚመለከቱና ሲጀመር ጀምሮ ያለውን ዓላማ የሚገነዘቡ ሰዎች እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ በዓለማዊ ሥርዓት በመመራት ሥራው ካሰበው መንገድ እንዲወጣ አይፈልግም፡፡ ሥራው የባለቤቱን ባሕርይ ማሳየት አለበት፡፡GWAmh 310.2

  በአዲስ ቦታ ሥራ ስታቋቁሙ በማንኛውም መንገድ የገንዘብ አያያዛችሁን አሳምሩ፡፡ ምንም ሳትጥሉ ሁሉንም ስብሰቡ፡፡ የነፍሳት ማዳን ሥራ ክርስቶስ ባወጣጡ መስመር መመራት አለበት፡፡ እንዲህ ይላል፡፡ «እኔኑን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፡፡» ዘማቴ. 16፣24) ደቀመዛሙርቱ መሆን የምንችል ይህን ቃል ያክበርን እንደሆን ብቻ ነው፡፡ ወደ ዓለም መጨረሻ ስለተቃረብን ማንኛውንም የሥራ መስመር ራሳችን በመሰዋት በፍጥነት ማካሄድ አለብን፡፡GWAmh 310.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents